Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

አሜሪካ ሰዎች በማይኖሩበት የፔንግዊኖች ደሴት ላይ ታሪፍ የጣለችው ለምን ይሆን?

$
0
0

በቅርቡ በመላው የዓለም ሀገራት ላይ ታሪፍ የጣሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አንድ አስደናቂ ውሳኔ አሳልፈዋል።

አሜሪካ ታሪፍ ከጣለችባቸው ሥፍራዎች መካከል ኸርድ ኤንድ ማክዶናልድ ደሴቶች ይገኙበታል።

እኒህ ደሴቶች ሰዎች አይኖሩባቸውም። ፔንግዊን እና ሲል የተባሉ የባሕር እንስሳት መገኛ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ሚኒስቴር ደሴቶቹ ላይ ታሪፍ የተጣለበትን ምክንያት አብራርቷል።

ኸርድ ኤንድ ማክዶናልድ ደሴቶች ላይ ታሪፍ የተጣለው ሀገራት በደሴቶቹ በኩል ዕቃ የጫነ መርከብ ይዘው እንዳያልፉ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ሀዋርድ ላትኒክ ተናግረዋል።

ደሴቶቹ ከአውስትራሊያ 4 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛሉ። የአውስትራሊያ ባለሥልጣናት ደሴቶቹ ላይ ታሪፍ በመጣሉ መገረማቸውን አልደበቁም።

የአውስትራሊያ ንግድ ሚኒስትር ዶን ፋሬል “መቼም ይህ ውሳኔ በስኅተት የተላለፈ ነው” ሲሉ ኤቢሲ ኒውስ ለተሰኘው ጣቢያ ተናግረዋል። አክለው “የችኮላ ሥራ” መሆኑን ያሳያል ብለዋል።በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ የአውስትራሊያ አካል የሆኑት ሰው አልባ ደሴቶች ላይ እንዴት ታሪፍ ሊጣል ቻለ ሲል ጠይቋል።

“አንዳንድ ሥፍራዎችን ዝርዝር ውስጥ ካላካተትን አሜሪካ ላይ የበላይነት መቀዳጀት የሚፈልጉ ሀገራት በዚያ በኩል ሊያልፉ ይችላሉ” ሲሉ ላትኒክ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ፕሬዝደንቱን ይህን ያውቃሉ። ይህ ጉዳይ ያሳስባቸዋል። ዓላማቸው ይህን ማስተካከል ነው።”

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በበርካታ የዓለም ሀገራት ላይ ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ ባለፈው አርብ የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ 2020 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ5 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል።

ሀገራት በመርከብ አማካይነት የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን ከአንድ ወደብ ወደ ሌላኛው የሚያደርጉት ጉዞ ትራንስሺፕመንት ይባላል።

ፒው ቻሪቴብል የተባለው የሕዝብ ፖሊሲ ተቋም “አንዳንድ የጥፋት ኃይሎች ይህን ሥርዓት ሊበዘብዙት ይችላሉ” ይላል።

መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት እንደሚለው በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጡ ቱና እና ሌሎች ዓሳዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ይተላለፋሉ።

ከኸርድ ኤንድ ማክዶናልድ ደሴቶች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ምን ያክል ምርት እንደሚጓጓዝ የሚታወቅ ነገር የለም።

የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከደሴቶቹ ወደ አሜሪካ የተጋዘው ምርት መጠን አነስተኛ የሚባል ነው።

በ2022 አሜሪካ 1.4 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ዋጋ ያለው ሰው አልባ “ማሽን እና የኤሌክትሪክ ዕቃ” ከደሴቶቹ አስጭናለች።

በትራምፕ የታሪፍ መዝገብ ላይ ከተካተቱ ሥፍራዎች መካከል ብሪቲሽን ኢንዲያን የውቅያኖስ ግዛት ይገኝበታል። ይህ ሥፍራ በወታደሮች የተያዘ ሲሆን ለመጎበኝት ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>