
አለም አቀፍ የሆቴል ኩባንያ የሆነው ሂልተን ‘ደብል ትሪ ባይ ሂልተን አዳማ’ እና ‘ደብል ትሪ ባይ ሂልተን ድሬዳዋ’ የተሰኙ ሁለት ግዙፍ ሆቴሎችን ለመክፈት ከብራይተን ሆቴሎች እና ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር ስምምነት መፈረሙን አስታወቀ።
ስምምነቱ በሁለቱ ከተሞች ውስጥ የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ ብራንድ ሆቴሎች እንዲከፈቱ ያስችላል የተባለ ሲሆን ይህም ሂልተን በሚቀጥሉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ስምንት ሆቴሎችን ለመክፈት በማቀድ በኢትዮጵያ መዳረሻውን ለማስፋት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል ተብሏል። የብራይተን ሆቴሎች እና ቢዝነስ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ መስራች የሆኑት ያደታ ጁኔይዲ በክሪ በበኩላቸው “አዲስ ዓለም አቀፍ ብራንድ ወደ አዳማ እና ድሬዳዋ ከተሞች ለማምጣት ከሂልተን ጋር በመስራታችን ደስተኞች ነን” ብለዋል።