Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

አሜሪካ የታይዋንን ነፃ ሀገርነት በተመለከተ ያሳየችው የአቋም ለውጥ ቻይናን አስቆጣ

$
0
0

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዋሺንግተን የታይዋንን ነፃነት አትደግፍም የሚለውን አንቀፅ ከድረ-ገፅ ማንሳቷ ቻይናን አስቆጥቷል። ቻይና የአሜሪካ አቋም “መገንጠል ለሚሹ እና ስለታይዋን ነፃነት ለሚያቀነቅኑ የተሳሳተ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ብላለች። ዋሺንግተን “ግድፈቷን እንድታርም” ቤይጂንግ ጠይቃለች። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለታይዋን-አሜሪካ ግንኙነት በሚያትተው አንቀፁ ከዚህ ቀደም “የታይዋንን ነፃነት አንደግፍም” የሚል መስመር ነበረው። ነገር ግን ይህ አንቀፅ ባለፈው ሳምንት የተወገደ ሲሆን፣ ይህ የሆነው “በተለመደ” የሲስተም መሻሻል ምክንያት ነው ተብሏል። የአሜሪካ ቃል አቀባይ ሀገራቸው “አንድ ቻይና” የተሰኘውን ፖሊሲ መከተል እንደምትቀጥል መናገራቸው የተዘገበ ሲሆን፣ አሜሪካ ከታይዋን ሳይሆን ከቻይና ጋር ነው ይፋዊ ግንኙነት ያላት ብለዋል። ቻይና ራስ ገዟን ታይዋን ለጊዜው እንደተገነጠለች፤ ነገር ግን ወደፊት ወደ ግዛቷ እንደምትመልሳት የምታምን ሲሆን፣ ይህን ለማሳካት የኃይል አማራጭ ከመጠቀም ወደኋላ እንደማትል ጠቁማለች።በርካታ የታይዋን ዜጎች ራሳቸውን እንደ ነፃ ሀገር ዜጋ ነው የሚቆጥሩት። ቢሆንም አብዛኞቹ አሁን ያለው ሁኔታ ማለትም ታይዋን ራሷን የቻለች ሀገር ሳትሆን፤ ከቻይናም ሳትቀላቀል ብትቆይ ይመርጣሉ። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባለፈው ሐሙስ አንቀፁን ከማንሳቱም ባለፈ ዩናይት ስቴትስ ታይዋን “እንደአስፈላጊነቱ” የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባል እንድትሆን ድጋፍ ትሰጣለች ይላል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አስተያየታቸውን የሰጡት በታይዋን የአሜሪካ ኢንስቲትዩት የተሰኘው እንደ አሜሪካ ኤምባሲ ሆኖ የሚያገለግለው ተቋም ቃል አቀባይ “ጉዳዩ አሜሪካ ከታይዋን ጋር ስላላት ኦፊሴላዊ ያልሆነ ግንኙነት ለሕዝቡ መረጃ ለመስጠት የተደረገ ነው” ብለዋል። የታይዋን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊን ቺያ-ሉንግ ዩናይትድ ስቴትስን አመስግነው “ለታይዋን የሚገባ የቃላት አጠቃቀም ነው” ብለዋል።ዘውትር ሰኞ መግለጫ የሚሰጡት የቤይጂንግ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካን አቋም በፅኑ አውግዞ ውሳኔው አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ያሳየችው አቋም “ከባድ ጥሰት ነው” ብሏል። “ውሳኔው መገንጠል ለሚሹ እና ስለታይዋን ነፃነት ለሚያቀነቅኑ የተሳሳተ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው። አልፎም አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠር ታይዋንን እንደ መሣሪያ የምትጠቀምበት ትክክለኛ ያልሆነ ፖሊሲ ማሳያ ነው” ሲሉ የቻይናው ቃል አቀባይ ጉዎ ጂያኩን ተናግረዋል።”ዩናይትድ ስቴትስ ግድፈቷን በፍጥነት እንድታርም እና ወደ አንድ ቻይና ፖሊሲ እንድትመለስ እንጠይቃለን” ብለዋል።

ዜና ምንጭ BBC News https://www.bbc.com/amharic/articles/cvg8gv37ezwo


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>