Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት አብሯቸው የሚሠራ ባልደረባቸውን በማገት ከባንክ ገንዘብና ክላሸንኮቭ መሣሪያ ይዘው የተሰወሩ 2 ተከሳሾችን በእስራት ማስቀጣቱን የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

$
0
0

ተከሳሾቹ ወንጀሉን የፈፀሙት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ከሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ደሞ ደዲ ቅርንጫፍ ከሌሊቱ 7፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ ነው።

ፍቅሩ እንግዳ እና ናቶሊ ደሴ የተባሉ ተከሳሾች በመመሳጠርና አስቀድመው በመዘጋጀት የማታ ጥበቃ ባልደረባቸው የሆነን ሠራተኛ እጅና እግሩን በማሰር ከተንቀሰቀስክ እንገልሀለን በማለት ታጥቀው ባንኩን ሲጠብቁበት የነበረን ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከ15 ጥይት ጋር እንዲሁም የባንኩን ካዝና በፌሮ ብረት በመስበር ከ230ሺ ብር በላይ ይዘው የተሰወሩ መሆኑን የምርመራ መዝገባቸው ያስረዳል፤ ፖሊስም አቤቱታው ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ባደረገው ብርቱ ክትትል ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቦሌ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

በተከሳሾቹ ላይ የምርመራ ሒደቱን ያጠናቀቀው ፖሊስ ጉዳያቸውን ለዐቃቤ ህግ ያስተላለፈ ሲሆን የተከሳሾችን ጉዳይ ከግራና ቀኝ ሲያይ የቆየው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸውና የስራ ባልደረባቸው ላይ በፈፀሙት የውንብድና ወንጀል ሌሎች ወንጀል ፈፀሚዎችን ያስጠነቅቃል ግለሰቦቹንም ያስተምራል በማለት ጥር 02 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት እንደ ወንጀሉ ተሳትፏቸው መጠን በፍቅሩ እንግዳ ላይ 7 ዓመት ከ 5 ወር እንዲሁም ናቶሊ ደሴ የ7 ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።

የጥበቃ ሥራ ከፍተኛ አደራና እምነት የሚጣልበት ሙያ በመሆኑ ተቋማት ሰራተኞችን ሲቀጥሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ያሳሰበው ፖሊስ የተቋም ኃላፊዎች ዕለታዊ የሆነ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>