Clik here to view.

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛውን የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ከቀበሌዎች ከተወጣጡ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።በውይይቱም የኦሮሞ ብ/ዞን ብ/ፓርቲ አደረጃጀት ሃላፊ ወ/ሮ ሀዋ አደም፤የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰይድ ሙሃመድ፤የኦ/ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ አህመድ እብራሂም፤የጨፋ ሮቢት ከ/አስተዳደር ብ/ፓ/ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ አብዱ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፤የሃይማኖት አባቶች፤የአገርሽማግሌዎች፤ወጣቶች ናሴቶች፤ ከቀበሌዎች የመጡ አባላት ተገኝተዋል።በውይይቱ ላይ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰይድ ሙሃመድ እንዳሉት እንደ ከተማ አስተዳደራችን ብሎም እንደ አገራችን በ2ኛ ዙር ብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ የተላለፉትን ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን በጋራ ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።የኦሮሞ ብ/ዞን ብ/ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ሀዋ አደም እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ በአስተሳሰብ፤በተግባርና በሰው ሃይል እንደ አፍሪካ ግዙፍ ፓርቲ ነው።በ2ኛ ዙር ጉባኤም የወሰነውን ውሳኔና ያስቀመጠውንም አቅጣጫ ከላይ እስከታች በጋራ ተባብርን ሁሉም ሃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ ዙር ጉባኤ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ አቶ ሷሊህ ሙሄ የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ብ/ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።በመጨረሻም በሰነዱ ላይ ከተሳታፊው ለተነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ይገኛል።