Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

በታላቁ ሶሀባ ሰልማን አልፋሪሲይ የተሰየመው መስጂድ ተጠናቆ ለማሕበረሰቡ ተላለፈ።

$
0
0

በሐጂ አሕመድሺር ኢብራሂምና በወንድማቸው መሐመድሰዓዲ ኢብራሂም የተገነባው መስጂድ ለዘንድሮው የረመዳን ኢባዳ ኢንዲደርስ በማሰብ ከተጀመረ በስድስት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ሌት ከቀን በተደረገ በርብርብ ተሠርቶ መጠናቀቁን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።ሰልማን አልፋሪሲይ (አላህ መልካም ስራቸውን ሁሉ ይውደድላቸውና) ኢስላምን በሁሉም መልኩ የረዱ፣ የኢስላም ምልክት ናቸው። ለዲን ሲሉ የተንከራተቱ አብሪ ኮከብ ናቸው።ዛሬ በስማቸው የተሰየመው ሰልማን አልፋሪሲይ መስጂድ ባማረ መልኩ ተገንቦቱ ለማሕበረሰቡ ተላልፏል።በመስጂዱ ውስጥ ሃያ ኡስታዞች ከሰባት መቶ በላይ ተማሪዎችን ይዘው ያስተምሩ የነበረበት ሁኔታ መስጂዱን በሰፊው ለመስራት እንዳነሳሳቸው መስጂዱን የገነቡት ሐጂ አሕመድ በሺር ተናግረዋል።የፌደራልና የክልል መጅሊሶች አመራሮች በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከመስጂዱ ጅማሮ እስከ መጠናቀቅ ድረስ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላት ምስጋና ቀርቦላቸዋል።በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ ዛሬ ደስታው እጥፍ ድርብ የሆነበት ቦታ ላይ ተገኝተናል ሲሉ መልዕክታቸውን ጀምረዋል።”በምድር ላይ የአላህን ቤት(መስጂድ) የሠራ፤ አላህ በጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል” የሚለውን የነብዩን (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሀዲስ ያስታወሱት ክቡር ዶክተር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ መስጂዱን ገንብተው ለሙስሊሙ ማሕበረሰብ ያስረከቡትን ሐጂ አሕመድ በሺርን አመስግነዋል።የአካባቢው ነዋሪዎችም የተረከባችሁትን መስጂድ ለዓላማው እንዲውል ማድረግ አለባችሁ ያሉ ሲሆን አንድነታችሁን ጠብቃችሁ መስጂዱን በኢባዳ ማሳመር ይጠበቅባችኋል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች በመስጂድ ጥበት ምክንያት ሲቸገሩ ነበር፤ አሁን ምስጋና ለአላህ ይሁንና በሐጂ አሕመድ በሺር አማካኝነት ችግሩ ተፈቷል በማለት መልዕክታቸውን የጀመሩት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ጋሊ ሙክታር ናቸው። ።ፕሬዝደንቱ ሼህ ጋሊ ሙክታር የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ በኢትዮጵያውያን እየተቀየረ ነው፤የኦሮሚያ መጅሊስም ለዚህ ዓይነት ስራዎች ዕውቅና ይሰጣል፣ ያበረታታል፣ ያመሰግናል በማለት ገልፀዋል።በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መስጂዶቻችን በውጭ ሀገራት ደጋፊዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፤ ይህ በመሆኑም ሀገራችን ውስጥ ያሉትን መልካም ሰዎች እንዳንመለከት አድርጎናል ሲሉ አስታውሰዋል።ይሁንና ይህንን መስጂድ የመሰለ በርካታ መስጂድና መድረሳ የሰሩ አህለል ኸይሮች ስንመለከት ዓይናችን ከውጪ ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል፤ ሼህ አሕመድ በሺርም ለዚህ ምሳሌ ናቸው ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።መስጂድ ለሙስሊም ሁሉ ነገሩ ነው ያሉት ፕሬዝደንቱ ክቡር ዶክተር ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ታላላቅ የኢስላም መሪዎች የፈለቁት ከመስጂድ ነው፤ መስጂድ ለሙስሊሞች ሁለንተናዊ ማዕከል ነው በማለት ይህንን ተቋም ለሚገነቡ አህለል ኸይሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።መስጂድ ሰሪዎች ከአላህ ዘንድ የሚገኘውን ታላቅ ምንዳ ተረድተው ነው መስጂድ የሚሠሩ ያሉት ፕሬዝደንቱ፤ ባለሀብቶች እነዚህን መልካም ሰዎች ተመልክተው አርአያነታቸውን መከተል አለባቸው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ለመስጂዱ ግንባታና መጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ ተባባሪዎች ምስጋናና የዕውቅና ሽልማት ተበርክቷል። ከመስጂዱ ጋር በተካተተው መድረሳ በልዩ ልዩ የቂርአት ደረጃ ላይ የሚገኙ ከአንድ ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚማሩ ተገልጿል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>