Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞቹን ውዝፍ ዕዳ ሊያስከፍላቸው መሆኑን አስታወቀ

$
0
0

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከደንበኞች ለወራት ሳያስከፍል የቆየውን ውዝፍ ዕዳ ከሚቀጥለው ክፍያቸው ላይ ተቀናሽ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 መሠረት ደንበኞች ከመስከረም ጀምሮ ውዝፍ የታክሱ ዕዳ እንዳለባቸው፣ የአገልግሎቱ ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ታዬ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በቅድመ ክፍያ (ካርድ የሚሞሉ) ደንበኞቹን በአዋጅ ቁጥር 1341/2016 መሠረት ከመስከረም ጀምሮ መከፈል የነበረበት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተቀናሽ ሳይደረግ መቆየቱን አቶ መላኩ ገልጸው፣ በአንዴ ለመክፈል እንዳይቸገሩ በማለት አጠቃላይ ወጪውን አገልግሎቱ ለገቢዎች መክፈሉን አስረድተዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ደንበኞች በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ቅሬታቸውን መግለጻቸውን የተናገሩት ሥራ አስፈጻሚው፣ ይህ የሆነው የቅድመ ክፍያ (ካርድ የሚሞሉ) ደንበኞች ሲስተም ሲስተካከል በመቆየቱ ያለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ኃይል ሲያገኙ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ደንበኞች ከሰሞኑ የከፈሉት ለሁለት ወራት መክፈል የነበረባቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሆነ፣ ከመስከረም እስከ ኅዳር ያልከፈሉት ውዝፍ ዕዳ እንዳለባቸውና በቀጣይ ከሚከፍሉት ገንዘብ (ከሚሞሉት) ላይ ተቀናሽ ይደረግባቸዋል ብለዋል፡፡

ከደንበኞች የተሰበሰበው ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደ ማንኛውም ሰብሳቢ ተቋም በየወሩ ለገቢዎች ገቢ እንደሚደረግ አቶ መላኩ አስረድተዋል፡፡

የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ከመስከረም ጀምሮ 15 በመቶ ቫት ባለመክፈላቸው፣ ክፍያው እንዳይበዛባቸው የሁለት ወራት ብቻ ተቀናሽ ነው የተደረገው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ይህ ማለት የመስከረም፣ የጥቅምትና የኅዳር ወራት ተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይጨመርበት ክፍያ የፈጸሙ በመሆናቸው፣ ወደፊት ከሚሞሉት ኃይል ላይ ተቀናሽ ይደረጋል ብለዋል፡፡

አዋጁ ሲወጣ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዳይጎዱ በማሰብ፣ በወር ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በታች የሚጠቀሙ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መደረጋቸውን አስታውሰው፣ ከዚህ በላይ የሚጠቀሙ ደንበኞች ግን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍሉ አዋጁ እንደሚያስገድድና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ደግሞ ከደንበኞች መሰብሰብ ግዴታ እንደተጣለበት ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ጉዳይ የድኅረ ክፍያ (ቆጣሪ ተነቦ የሚከፍሉ) ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሒሳባቸው ላይ ተጨምሮ እየከፈሉ እንደሆነ፣ የቅድመ ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይከፍሉ እንዲጠቀሙ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

የአገልግሎቱ ሲስተም ከተስተካከለ በኋላ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚዎች ባለፈው ወርና የሚጠቀሙትን 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከሚገዙት ኃይል በመቀናነሱ ምክንያት ክፍያው ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የቴሌቪዥን ክፍያን በተመለከተ በመመርያ ቁጥር 1021 እና በአዋጅ ቁጥር 1278/2015 መሠረት ከ50 ኪሎ ዋት ሰዓት በታች ገጠር ውስጥ የሚገኙ ኃይል በብዛት የማይጠቀሙ፣ አንዳንድ ደግሞ ቴሌቪዥን የሌላቸው ናቸው ተብለው ስለሚታሰቡ አይከፍሉም ብለዋል፡፡

ነገር ግን ከ50 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የሚጠቀሙ በየወሩ አሥር ብር ተሰብስቦ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደሚከፍሉ አስረድተዋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>