Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

አሜሪካ በሱዳኑ ጦር መሪ አል ቡርሃን ላይ ከሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጋር በተያያዘ ማዕቀብ ጣለች

$
0
0
የአሜሪካ መንግሥት በሱዳን ጦር መሪ እና የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተደርገው በሚቆጠሩት ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ መጣሉን የግምጃ ቤት ሚኒስቴር አስታወቀ። ለ21 ወራት በዘለቀው ደም አፋሳሹ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች አንዱ የሆነው ጦሩ መሪ ናቸው ጄነራል አል ቡርሃን። ጦርነቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለማችን እጅግ የከፋ መፈናቀል ብሎ በጠራው ቀውስ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሲፈናቀሉ አገሪቱ በከፋ ረሃብ ላይ ትገኛለች። ጄነራል አል ቡርሃን "ሱዳንን አለመረጋጋት ውስጥ በመክተት እና የዲሞክራሲ ሽግግርን ቀልብሰዋል" ስትል አሜሪካ በሰጠችው አጭር መግለጫ ከሳለች። የአሜሪካ ማዕቀብ የተሰማው በቅርቡ በዋድ ማዳኒ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ ተከትሎ ቢሆንም መግለጫው ይህንን ግድያ አልጠቀሰም። ባለፈው ሳምንት ከጦሩ ጋር እየተፋለመ ያለው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ ወይም ሄምቲ በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። አሜሪካ የደጋሎ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሱዳን ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ሲል ከሷል። ሐሙስ ዕለት በቡርሃን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አስመልክቶ ይፋ በተደረገበት ወቅት እርሳቸው የሚያዙት ጦር "ትምህርት ቤቶችን፣ ገበያዎች እና ሆስፒታሎችን" ኢላማ አድርጓል እንዲሁም "በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያን ፈጽሟል" ተብሏል። የአሜሪካ መንግሥት በሱዳን ጦር መሪ እና የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ተደርገው በሚቆጠሩት ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ መጣሉን የግምጃ ቤት ሚኒስቴር አስታወቀ። ለ21 ወራት በዘለቀው ደም አፋሳሹ የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች አንዱ የሆነው ጦሩ መሪ ናቸው ጄነራል አል ቡርሃን። ጦርነቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለማችን እጅግ የከፋ መፈናቀል ብሎ በጠራው ቀውስ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሲፈናቀሉ አገሪቱ በከፋ ረሃብ ላይ ትገኛለች። ጄነራል አል ቡርሃን "ሱዳንን አለመረጋጋት ውስጥ በመክተት እና የዲሞክራሲ ሽግግርን ቀልብሰዋል" ስትል አሜሪካ በሰጠችው አጭር መግለጫ ከሳለች። የአሜሪካ ማዕቀብ የተሰማው በቅርቡ በዋድ ማዳኒ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ ተከትሎ ቢሆንም መግለጫው ይህንን ግድያ አልጠቀሰም። ባለፈው ሳምንት ከጦሩ ጋር እየተፋለመ ያለው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ ወይም ሄምቲ በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።አሜሪካ የደጋሎ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሱዳን ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ሲል ከሷል።ሐሙስ ዕለት በቡርሃን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አስመልክቶ ይፋ በተደረገበት ወቅት እርሳቸው የሚያዙት ጦር "ትምህርት ቤቶችን፣ ገበያዎች እና ሆስፒታሎችን" ኢላማ አድርጓል እንዲሁም "በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያን ፈጽሟል" ተብሏል።

Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>