Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

በነዳጅ ማደያዎች የቴሌብር ወኪሎች እንዲነሱ ትዕዛዝ ተላለፈ

$
0
0

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ሲሠሩ የነበሩ የቴሌብርም ሆነ የማደያ ወኪሎች እንዲነሱ ሲል የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ለሁሉም የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች፣ ለኢትዮ ቴሌኮምና ለኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር በላከው ደብዳቤ አስታወቀ፡፡ ባለሥልጣኑ መንግሥት የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ ወይም በካሽ የነበረውን ለማስቀረት ከመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ወደ ዲጂታል ግብይት ዘዴ የቀየረ መሆኑን ገልጾ፣ በዚሁ መሠረት ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ሲስተሙን እስኪለምድ ድረስና የግብይት ሥራውን ለማቀላጠፍ ሲባል የቴሌብር ወኪሎች በማደያዎች እንዲመደቡ መደረጋቸውን አስታውሷል፡፡ ማኅበረሰቡ ስለሲስተሙ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ ያገኘ ስለሆነ ባለሥልጣኑ ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. በደብደቤ ቁጥር 2.1/132/2016 በሁሉም ነዳጅ ማደያዎች የሚገኙ የቴሌ ተወካዮችም ሆነ ነዳጅ ማደያው በራሱ ያስቀመጣቸው የቴሌብር ወኪልነት እንዲቆም ያሳወቀ ቢሆንም፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልቆመ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል፡፡ ስለዚህም ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ላይ ምንም ዓይነት የቴሌ ብር ወኪል ሆነ የማደያ ወኪል እንዳይኖር ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ ብሏል፡፡ ባለሥልጣኑ በሚያደርጋቸው የክትትል ሥራዎች ሆነ በሌሎች ጥቆማዎች በነዳጅ ማደያዎች ላይ የቴሌብር ወይም የማደያ ወኪል ቢገኝ፣ አስፈላጊውን ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ ሪፖርተር የተመለከተው የባለሥልጣኑ ደብዳቤ ያመለክታል፡፡ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ ተፈርሞ ለሁሉም የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች፣ ለኢትዮ ቴሌኮምና ለኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር የወጣው ደብዳቤ፣ ተጠቃሚዎች በቀጥታ በግላቸው የቴሌብር አካውንት የነዳጅ ክፍያቸውን መፈጸም እንዳለባቸውና ይህም በአግባቡ የነዳጅ የግዥ ቁጥጥርን ከፍ እንዲል ከማስቻሉም በላይ፣ በተገቢው መንገድ አጠቃላይ የግብይትና የሥርጭት ሒደቱን ጤናማ እንደሚያደርገው ያስረዳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ብልጫ ያለውን ድርሻ ኢትዮ ቴሌኮም የወሰደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግን የዲጂታል የነዳጅ ገበያ ድርሻው ብልጫ እንዲይዝ ለማድረግ በየማደያው ባለሙያዎችን በመመደብ ጭምር እየሠራ በመሆኑ፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ያለውን ገበያ በአብዛኛው መያዙም ይነገራል፡፡  በአገር ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከሚጠይቁ ገቢ ምርቶች መካከል ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ አገሪቱ ከምታገኘው አነስተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በነዳጅ ግዥ ወጪ ይደረጋል፡፡ አሁን ደግሞ ከዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የሚጠይቀው የውጭ ምንዛሪ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር ይታመናል፡፡ ከየትኞቹም የገቢ ንግድ ምርቶች በአስፈላጊነቱ ቀዳሚ የሆነው ነዳጅ በውድ ዋጋ እንደ መሸመቱ፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ለማለት እንደማይቻል የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡

ዜና ምንጭ ሪፓርተር https://www.ethiopianreporter.com/137390/


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>