Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከ480 በላይ ሠራተኞች አላግባብ ከሥራችን ተባረርን አሉ

$
0
0
  • ‹‹ከዚህ በኋላ ለልመና መውጣት እንጂ ወዴት እንሄዳለን?››

ከሕግ አግባብ ውጭ ተሰናበትን ያሉ ሠራተኞች

  • የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መልስ ከመስጠት ተቆጥቧል

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከ480 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች፣ ከአግባብ ውጭ ከሥራቸው መሰናበታቸውን ተናገሩ፡፡ ድርጅቱ ግን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ሠራተኞቹ ከድርጅቱ በተጻፈ የስንብት ደብዳቤ ከነገ ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ መሰናበታቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የድርጅቱ ሠራተኞች እንደገለጹት፣ በኃላፊነት ደረጃ ለ25 ዓመታት በድርጅቱ እንደሠሩ ተናግረው፣ ‹‹ሪፎርም ለመሥራት›› በሚል እንዳሰናበቷቸው ተናግረዋል፡፡‹‹ለጊዜው ምክንያቱ ያልገባን ድንገተኛ ዱብዳ ነው የሆነብን›› ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ምንም ዓይነት ጥፋት እንደሌለባቸው ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ የሠራተኛ ቅነሳ ብሎ እኛን ካሰናበተ በኋላ፣ የኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል፤›› ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ድንጋጌ መሠረት፣ አንድ ሠራተኛ ውል ተዋውሎ ከተቀጠረ በኋላ፣ ያለ ምንም ጥፋት ማሰናበት እንደማይቻል መደንገጉን ተናግረው፣ በዚህም መሠረት ወደ ሕግ ለመሄድ እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡‹‹በእኛ ላይ የተደረገው ነገር በማንም ላይ ተደርጎ አያውቅም›› ያሉት ተበዳዮቹ፣ በሠራንበትና ባገለገልንበት አገር፣ ውለታው ይህ ከሆነ በጣም ያሳዝናል ሲሉ›› በድርጊቱ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ከዚህ በኋላ ስላለው ሕይወታቸው ሲናገሩ፣ ‹‹ልመና መውጣት ነው እንጂ ሌላ ምን ይሠራል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡አንዲት ከሥራ ተቀናሽ ሠራተኛ በድርጅቱ ለ17 ዓመታት በፅዳት ሠራተኝነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ተናግረው፣ ‹‹መሥፈርት አላሟላችሁም›› በሚል መቀነሳቸውን ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳን እስከ 12ኛ ክፍልን እንዳጠናቀቁ ማስረጃ ቢኖራቸውም፣ ‹‹ለፅዳት ሠራተኝነት አይመጥንም›› በሚል መቀነሳቸውን ተናግረው፣ ድርጅቱ በምትካቸው ሌሎች ሠራተኞችን መቅጠሩን ተናግረዋል፡፡‹‹ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ በድንገት ነው የተሰናበትነው›› ያሉት ቅሬታ አቅራቢዋ፣ ‹‹በአራት ቀን ውስጥ እጃችሁ ላይ ያለውን ንብረት አስረክባችሁ ውጡ›› የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ድርጅቱ ‹‹ጉዳዩ የሥራ ስንብትን ይመለከታል›› በሚል ያወጣውን ማስታወቂያ ሪፖርተር እንደተመለከተው፣ ‹‹ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮከድርጅቱ ጋር ያለዎት ውል የተቋረጠ መሆኑን አውቀው፣ በእጅዎ የሚገኙትን ንብረቶች በማስረከብና ሌሎች በሕግ የሚጠበቅብዎትን ግዴታ በመወጣት፣ እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አጠናቀው እንዲጨርሱ›› ሲል ያሳሰበ ሲሆን፣ ‹‹በተሰጠው ጊዜ የሚጠበቅብዎትን አጠናቀው ባለመጨረስዎ ለሚመጣ የዘገየ ክፍያም ሆነ ሌሎች ግዴታዎች፣ ድርጅቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን›› በሚል በደብዳቤው ላይ አስቀምጧል፡፡ድርጅቱ በዚሁ ደብዳቤ ሠራተኞችን ለምን እንደቀነሰ ሲገልጽ ‹‹ድርጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤታማነቱ በመቀነሱ፣ የአሠራር ዘዴዎችን በመለወጥ ትርፋማነትን ለማሳደግ ያስችለው ዘንድ፣ የመዋቅር ጥናት በማድረግ ውጤታማ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመመደብ ባስቀመጠው መሥፈርት፣ እርስዎ መመዘኛውን የማያሟሉ በመሆኑ በሕግ የተቀመጠው መብትና ጥቅምዎ ተጠብቆ፣ ከሥራ የተሰናበቱ መሆኑን እናሳውቃለን፤›› በሚል በደብዳቤው ገልጿል፡፡ምንም አንኳን ድርጅቱ የሠራተኞቹን መብትና ጥቅም ጠብቆ እንደሚያሰናብት በደብዳቤው ቢገለጽም ‹‹ከስንብት ደብዳቤ ውጭ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያም ሆነ ሌላ የሰጣቸው ነገር እንደሌለ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>