Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ስጋት አለኝ(አንድነት)

$
0
0

ከኖርዌይ የሚመለሱትን ኢትዮጵያውያንን  አስመልክቶ አንድነት ፓርቲ በቅርበት ይከታተል እንደነበር የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ተመስገን ገለፁ…

በተለይ አቶ ተመስገን የኖርዌይ መንግሥት  ኢትዮጵያውያንን ስደተኞች ያለ ፍላጐታቸው ወደ  ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉ ከሰለጠነ መንግሥት
የማይጠበቅ፤ኢትዮጵያና ኖርዌይ የፈረሟቸው  የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚጥስ በመሆኑ ፓርቲው እንደሚቃወመው ገለፀውልናል፡፡ ለዚህም
እንደ ምክንያትነት ያነሱት ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ  ከተደረጉት ውስጥ የፖለቲከኛ ስደተኞች እንዳሉበት  እየታወቀ ወደ ሚቃወሙት መንግሥት መመለስ ለአደጋ
አጋልጦ መስጠት እንደሆነና ለዚህም ምንም ዋስትና  ስለሌለ ስጋት እንዳደረባቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም  በመቃወም አዲስ አበባ ላለው ኖርዌይ ኤምባሲ
አምባሳደር በአካል በመሄድና በማነጋገር፣ለኖርዌይ  ጠቅላይ ሚኒስትር፣እና አፈ-ጉባዔ እንዲሁም ለተለያዩ  ዓለም አቀፍ ተቋማት ደብዳቤ መላካቸውንና ፓርቲው
የሚመለሱት ኢትዮጵያውያን ደህንነት ዋስትና  እንደሚያሳስበው መግለፁን አስታውሰዋል፡፡



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles