በዳዲሞስ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማ በየሣምንቱ እየታተመ ለንባብ የሚቀርበው የ“ሎሚ” መጽሄት ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ሠናይ አባተ ተከሰሰ፡፡ ጋዜጠኛ ሠናይ ሕዳር 17 ቀን 2006 ዓ.ም በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቀርቦ ቃሉን እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ በዋስ ተለቋል…
የሎሚ መጽሄት አዘጋጅ የተከሰሰው በትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ሲሆን፣ የክሱ መነሻም በመጽሄቱ ቁጥር 54 ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም “ጓንታናሞ በትግራይ” በሚል ርዕስ አቶ አሰገደ ገ/ሥላሴ በተባሉ ግለሰብ በተጻፈ ጽሁፍ እንደሆነ ገልጿል፡፡ አቶ አሰገደ በዚህ በጽሁፍ ላይአህፈሮም አስገደና የማነ አስገደ በተባሉ ልጆቻቸው በእስር ቤት ስለሚደርስባቸው በደሎችና ስለ እስር ቤቱ ስላለው ዝርዝር ጉዳዮች አካተው በመጻፋቸው መሆኑን ተናግሯል፡፡ አዘጋጁም በጽሁፉ ዙሪያ በመርማሪዎች ምርመራ ከተደረገበትና ቃሉን ሠጥቶ ከጨረሰ በኋላ ለሕትመት ከበቃውና ከተከሰሰበት ጽሁፍ ውስጥ የመርማሪው አለቃ የተወሰነ ዐረፍተ ነገር በማውጣት እንደገና እንዲፃፍና እንድፈርም አድርገውኛል ሲል ተናግሯል፡፡
Related articles
- አቶ ሽመልስ ከማል ‹‹ የሳውዲ መንግስት ሉአላዊ መብት አለው›› (dawitfw.wordpress.com)
