Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Watch»ኢትዮጵያዉያን ትክክለኛ ባልሆነ መጠለያ እና በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን ገለፀ ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ፤ «Human Rights

$
0
0

የሳዉዲ አረብያ መንግስት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ህገ-ወጥ እስካሁን 110 ሺ የዉጭ ሀገር ዜጎችን ከሀገር ማባረሩን ገለፀ። የሳዉዲ መንግስት በህገ-ወጥ ያለመኖርያ ፈቃድ የሚኖሩትን ለማባረር ከወሰነበት ከጥቅምት 25 ጀምሮ እስካሁን 110,243 የዉጭ ሀገር ነዋሪዎችን ማስወጣቱን ገልጾአል…

saudi-3-300x225

ባለፈዉ ወር መንግስት ህገ ወጥ ለሚላቸው ለውጭ ዜጎች መኖርያ ፈቃዳቸዉን እንዲያስተካክሉ አልያም ሀገር ለቀዉ እንዲወጡ የሰጠው የ7 ወር የምህረት ቀነ ገደብ ካበቃ በኃላ፤ የፀጥታ ኃይላት የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸዉን የዉጭ ሀገር ዜጎች በየቤቱ ማደን መጀመራቸዉ ይታወቃል። የሳዉዲ መንግስት በሀገሪቱ ይኖሩ የነበሩትን የዉጭ ሀገር ዜጎች የሚያስወጣዉ ለዜጎቹ የስራ ዕድል ለመስጠት መሆኑን ነዉ የገለጠዉ። የዓለም የገንዘብ ድርጅት ባወጣዉ ዘገባ መሠረት በሳውዲ አረቢያ ሥራ አጥነት 12 በመቶ ደርሷል። እንደ ጎ 2010 ዓ,ም የተደረገዉ ጥናት እንደሚያሳየዉ በሳዉዲ አረብያ ከሚገኘዉ 29 ሚሊዮን ነዋሪ 9 ሚሊዮኑ የውጭ ዜጋ ነዉ። የሀገሪቱ የባህልና የመረጃ ሚኒስትር አብዱል አዚዝ ሃዋጃ፤ ለጀርመኑ የዜና አገልግሎት dpa እንደገለፁት፤ ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች፤ ከፍተኛ ወቀሳና ነቀፊታ እየደረሰብን ቢሆንም፤ ሀገሪቱ ዉስጥ ህገ-ወጥ ያልናቸዉን ዜጎች ማደናችንን እንቀጥላለን ብለዋል። ሳዉዲ አረብያ በጀመረችዉ በዚህ ዘመቻ በተለይ ኢትዮጵያዉያን፤ ላይ ችግሩ ማየሉን እና ፤ እስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ፤ ትክክለኛ ባልሆነ መጠለያ እና በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ፤ «Human Rights Watch» አስታዉቋል።



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>