Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

ሰበር ዜና – ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ”ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች” አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ

$
0
0

ሰበር ዜና

ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ”ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች” አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ
”አህራም ኦን ላይን” የተሰኘው የግብፅ ድህረ ገፅ ጋዜጣ በዛሬው ግንቦት 28፣2005 ዓም ባወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ብዙ ያልተሳካ  ሙከራ ማድረጓን መግለፃቸውን እና  አሁን ”በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ማድረግ እና ሴራ ማድረግ” የሚሉ አስተያየቶች ጊዜ ያለፈባቸው የከሸፉ ሃሳቦች  ”old failed concept.” እና የቀን ሕልም ”day dreaming.” ከመሆን ያልዘለለ መሆኑን አክለው መናገራቸውን ዘግ ቧል።
የጋዜጣውን አጭር ዜና ከእዚህ በታች በጉዳያችን ጡመራ ላይ ያንብቡ።

A spokesman for Ethiopia’s prime minister is downplaying suggestions by Egyptian politicians that Egypt should sabotage Ethiopia’s new Nile River dam.

Political leaders in Egypt on Monday proposed carrying out hostile acts against Ethiopia. Egypt, which is dependent on the Nile, fears a diminished flow.
Getachew Reda, a spokesman for Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, said late Tuesday that Egyptian leaders in the past have unsuccessfully tried to destabilize Ethiopia. He called the suggestions of attack or sabotage an “old failed concept.” He also labeled it “day dreaming.”
Ethiopia last week ago began diverting the flow of the Nile toward its $4.2 billion hydroelectric plant that has been dubbed the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The project, currently about 20 percent complete, has raised concerns in Nile-dependent Egypt.


አዜብ መስፍን የሙስና ንግስት ጉድ ፈላባት ዘንድሮ

$
0
0

Sarah Brown with the First Lady of Ethiopia

By Ashenafi Abrha
ግፊቱ ጨምሯል!!አዜብ መስፍን የሙስና ንግስት ጉድ ፈላባት ዘንድሮ
እነመላኩ ፋንታን ተከትሎ በአዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል::
የሙስና ኮሚሽን በአቶ ገብረዋህድ ቤት ባደረገው ፍተሻ እንዲሁም ከኣሁን ቀደም በመርማሪ ደህንነቶች ክትትል በተደረገ የስልክ ጠለፋ የቀድሞ ሟች ጠ/ሚ ባለቤት እና በአለም ትልቁ የሙስና አባት ኤፈርት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገብረዋህድ ባለቤት እና እህት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ስራ ይሰሩ እንደነበር እና… ከታሰሩት ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች ጋር የንግድ አጋርነት እንዳላት አረጋግጧል::ይህንን የሚጠቁሙ ሰነዶች እና ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች ምርመራው ወደ አዜብ መስፍን አምርቶ ለጥያቄ እንደምትፈለግ ፍንጭ እየሰጠ ነው ሲሉ የሙስና ኮሚጽሽን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
ለሙስና ኮሚሽን ከደረሱት አቤቱታዎች ከፊሎቹ :-ኤፈርትን ተገን በማድረግ የተለያዩ እቃዎችን ካለቀረጥ እያስገባች ነው:: ኤፈርት ለመንግስት መክፈል የሚገባውን ህጋዊ የግብርም ሆነ ሌላ ክፍያዎች እንዳይፈጸም አድርጋለች:: ዩዲ ኒሳን ዲዝል ገልባጭ መኪኖችን ካለቀረጥ ነጻ በማስገባት በአቶ ከተማ ከበደ/ኬኬ/ ስም ሸጣለች:: ከዚህ ቀደም እያሱ በርሄ ጋር በኋላም ከኮሎኔል ሃይማኖት ጋር የተከለከሩ የቴለኮሚኒኬሽን ኬብሎችን እና ቴክኖሎጊካል የመገናኛ መሳሪያዎችን ካለቀረጥ በማስገባት ሰርታለች::በነጻ ትሬዲንግ በኩል የተለያዩ ዘመናዊ መኪኖችን ካለቀረጥ እያስገባች በአቶ ነጋ ገ/ዝጌር ስም ትሸጣለች::በሰበታ አለምገና አከባቢ የአበባ ሰፊ እርሻዎች አላት :: በህገወጥ የዶላር እና የኢሮ ዝውውር ውስጥ መሪ ተሳታፊ ናት:: ባንክ ኦፍ ማሌዥያ እና የሲንጋፖር ባልሃብቶችን እንዲሁን ቻይናውያንን በህገወጥ አለማቀፍ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪ አድርጋ እየሰራች ነው::በተለያዩ አረብ አገራት እና በሃገር ውስጥ ባስቀመጠቻቸው ደላሎች ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በሱዳን እና በየመን አድርጋ ወደ አረብ አገራት ትሸጣለች::በተለያዩ የቤተሰብዋ አባላት ስም ባወጣችው የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃዶች ጨረታዎችን በጉልበት ከመቀማት እየሰራሽ ሲሆን ሌሎች ባለሃብቶችን በስማቸው በመጠቀም የተለያየ ቢዝነሶችን እያካሄደች ነው የሚሉ አቤቱታዎች እና ጥቆማዎች ለሙስና ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ደርሷል::
ይህንን ተከትሎ ጠንካራዎቹ የወያኔ አባላት በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ግፊት እያደረጉ ሲሆን ወይዘሮዋ በአሁን ሰአት ራሳቸውን በተለያየ ምክንያት ገኖ ለማውጣት ላይ ታች እያሉ መሆኑን ታውቋል::

የአዲስ አበባ ተማሪዎች በፌዴራል እየተደበደቡ ነው!

$
0
0

EMF: ዛሬ ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱበት የመጨረሻ ቀን ነው። በዚህ የመጨረሻ ቀናቸው ተማሪዎች ስለፈተናው ማውራት፣ በቡድን በቡድን እየሆኑ መሄድ የተለመደ መሆኑ ይታወቃል… ሆኖም ካለፈው የግንቦት 25 ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኋላ ገዢው ፓርቲ ውስጥ ውስጡን በንዴት ሲጦፍ ከርሞ አሁን እነዚህን ተማሪዎች፤ “ለምን በቡድን በቡድን ሆናቹህ ትሄዳላቹህ?” በማለት፤ ፌዴራል ፖሊሶች በአሰቃቂ ሁኔታ በማባረር እየደበደቧቸው መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

                 
ከፈተና በኋላ ተማሪዎች ላይ የማሳደድ ድብደባ በፌዴራል ፖሊስ ደርሶባቸዋል።
ይህ በተለይ እየሆነ ያለው ከስድስት ኪሎ ንስካየ ህዙናን ተማሪዎች ጀምሮ የየካቲት 12 ተማሪዎችም እየተደበደቡ ናቸው። ጥቂት ተማሪዎችም በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል። ከላይ እንደገለጽነው፤ በፌዴራል ፖሊስ በኩል የበቀል እርምጃ እየተወሰደ ያለ ይመስላል። ተጨማሪ ዘገባዎች ካሉ በዚህ ጉዳይ እንመለስበታለን።

ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ተከሰሱ

$
0
0

Likun_astatke_jpg

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ በከፍተኛ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ወህኒ ወረዱ። ሊቀትጉሃን አስታጥቄ በተመሰረተባቸው ክስ ጠበቆቻቸው ዋስትና ቢጠይቁባቸውም ፍርድ ቤቱ ግን ዋስትና ለመፍቀድ ወይም ላለመፍቀድ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ቢባልም ዘ-ሐበሻ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልደረሳትም..

በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎት የማታለል ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ሊቀ ትጉሃን አብረዋቸው ሁለት የማህበሩ አመራሮችም ክስ እንደተመሰረተባቸው መንግስታዊ ሚድያዎችም ጭምር ዘግበዋል። ለዘ-ሐበሻ እንደደረሱት መረጃዎች ከሆነ ሊቀትጉሃን በተለያዩ ክሶች የተከሰሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል በ1998 ዓ ም ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ለአቅመ ደካማ ጀግኖች አርበኞች የተሰጠውን 25 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለግል ጥቅማቸውና ለወዳጆቻቸው አከፋፍለዋል የሚለው በዋነኝነት ተጠቅሷል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አንድነት ማህበር ሊቀመንበርና አጋሮቻቸው የማህበሩን ሃብትና ንብረት ያለአግባብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉትና እየመዘበሩት እንደሚገኙ፣ አንዳንድ የማህበሩ አባላት እንደገለጹለት ጠቅሶ አውስትራሊያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ቅዱስ ሃብት በላቸው ከወራት በፊት ዘገቦ እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛው ባጠናቀረው ዜና መሰረት የማህበሩ ሊቀመንበር የሆኑት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ቁጥሩ ቀላል የማይባል ጥሬ ገንዘብና ንብረት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል። ከዚህም መካከል በዓመት 800 ሺህ ብር ከሚከራየው ህንፃ 240 ሺህ ብር፣ እንዲሁም ካሳንቺስ አካባቢ የሚገኘው የማህበሩ ንብረት ከሆነው ቡና ቤት ኪራይ የሚገኘው 150 ሺህ ብር የት እንደሚገባ ተለይቶ እንደማይታወቅ የማሕበሩን ም/ፕሬዚዳንት ጨምሮ ሌሎች የማህበሩ አባላት ማስታወቃቸውን፤ ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ መስተዳድር ለአቅመ ደካማ የማህበሩ አባላት እንዲከፋፈል የሰጠው 15 የቀበሌና 30 የኮንዶምኒየም ቤቶች ውስጥም የማህበሩ ፕሬዚዳንትና ጥቂት አመራሮች የግል ቤት እያላቸው ለራሳቸው ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ፤ የተቀረውንም ቢሆን አብዛኛውን ለቤተሰቦቻቸውና እነርሱ ለሚቀርቧቸው ጥቂት አባላት ማከፋፈላቸው ታውቋል ሲል ጋዜጠኛ ቅዱስሃብት በላቸው ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ማህበር ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ በዱር በገደሉ ተማርተው የፋሺሽት ኢጣሊያን ጦር ድል አድርገው ከአገር ባባረሩ አርበኞች የተቋቋመ ማህበር ነው።

http://www.zehabesha.com


ወያኔ የፈጠረዉ የፍርሀት ድባብ ሲሰበር . . .

$
0
0

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰዉ በደልና መከራ ወለደን ብለዉ ለትግል ጫካ የገቡት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ ከተደላደሉ በኋላ በህዝብ መብትና ነጻነት፤ በአገር አንድነትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ጥቆሞች ላይ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችልና ከእነሱ በፊት ከነበሩት መንግስታት ጋር ሲተያይ እጅግ በጣም የከፋ በደል ፈጽመዋል እየፈጸሙም ይገኛሉ… ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ የኢትዮጵያን መንበረ ስልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በፊት ዕቅድ አዉጥተዉና ተዘጋጅተዉ የመጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፤ በሐይማኖትና በክልል በመከፋፈል በጠመንጃ ኃይል የያዙት ስልጣን በግዜና በህገመንግስት ያልተገደበ መሆኑን ለማረጋገጥና የእኛ ነዉ ለሚሉት የህብረሰተብ ክፍልና ለሚተባበሯቸዉ ሆዳሞች ተቆጥሮ የማያልቅ ሀብት ማጋበስ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር ነዉ። የወያኔ መሪዎች ይህንን አገራዊ በደል ያለምንም ተቃዉሞ መፈጸም እንዲችሉ ከአገሩ ይልቅ የተወለደበትን ክልል ብቻ፤ ከብሔራዊ አንድነቱና አጋራዊ ጥቅሙ ይልቅ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚመለከትና የእነሱን ኃይለኝነትና የተለየ ጀግንነት እየሰበከ የሚኖር በፍርሀት የተሸበበ ፈሪ ትዉልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
የወያኔ ክፋት፤ ዘረኝነትና “ልማት” በሚል ሽፋን የተደበቀ አገር የማፍረስ ሴራ ከወዲሁ የገባቸዉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ከ1997ቱ ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ የወያኔን ገመና ለማጋለጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ፤ ለነጻነቱና ለእኩልነቱ እንዲታገል ለማድረግ እንደሻማ እየቀለጡ ብርሀን ሆነዉ አልፈዋል።

ይህ የዕልፍ አዕላፋት የትግል መስዋእትነትና ምሳሌነት ፍሬ እያፈራ መጥቶ በላፈዉ እሁድ ግንቦት 25 ቀን የተካሄደዉንና ወያኔ ከሃያ አመታት በላይ ሲቋጥር የከረመዉን የፍርሀት መቀነት የበጠሰ እጅግ በጣም የሚያበረታታ ትዕይንተ ህዝብ እንዲደረግ አስተዋጽኦ እድርጓል፡፡ ይህ ባለፈዉ እሁድ የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተባብሩት፤ አቅጣጫ የሚያሳዩትና ጉያዉ ዉስጥ ገብተዉ እያበረታቱ የሚመሩት መሪዎችን ካገኘ እንኳን ምንም አይነት ህዝባዊ መሠረት የሌለዉን ወያኔን የመሰለ ፀረ ህዝብ ሃይል ቀርቶ ለማንም የማይበገር ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ሰልፍ ነዉ።

በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራዉና የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ይሁንታ ያገኘዉ የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ያስረናል ወይም ይገድለናል እየተባለ አላግባብ እየተፈራ በቀጠሮ ሲተላለፍ የቆየዉን ህዝባዊ ትግል ከፍርሀትና እንደ ገመድ ከረዘመ ቀጠሮ ዉስጥ በጣጥሶ ያወጣና የህዝብን የትግል መንፈስ ያነቃቃ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር በሰልፉ ላይ የታየዉ የህዝብ ስሜትና ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፉት መልዕክቶች በግልጽ ይናገራሉ። ባለፈዉ እሁድ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየዉ ህዝብዊ መነሳሳት ሊበረታታ የሚገባዉና እንዲሁም በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵየዉያን የመብትና የነጻነት ትግላቸዉ አካል አድርገዉ ሊቀላቀሉት፤ ሊረዱት፤ሊተባሩትና ህዝባዊ ትግሉ የሚጠይቁዉን አመራር ሊሰጡት የሚገባ እጅግ በጣም አበራታች ጅምር ነዉ። ለትግልና ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጣዉ መሪ ነዉ እያልን አግባብ የሌለዉ ጩከት ከመጮህ ይልቅ አገራችንን የምንወድ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ መሪዎችን በትግል ሂደት ዉስጥ የምንፈጥረዉ እኛዉ እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ይህንን የሚያበረታታ ተስፋ የሰጠንን ሰላማዊ ሰልፍ የምናጠናክርበትንና ተከታታይነት ኖሮት ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትትበትን መንገድ ልንቀይስ ይገባል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቢሆን ለመብቱ፤ለነጻነቱና ለአንድነቱ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ በግልጽ አሳይቷል። አሁን የሚቀረዉ ህዝባዊ ትግሉን የመምራት ታሪካዊ ሀላፊነት የወደቀበት የህብረተሰብ ክፍል ጨርቄን ማቄን ማለቱን ትቶ ወቅቱ የሚፈልገዉን የትግል አመራር መስጠት ብቻ ነዉ።
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አንዴ የታጠቀዉን ጠመንጃ በመጠቀም ሌላ ግዜ ደግሞ ፓርላማዉንና የህግ ተቋሞችን ተጠቅሞ ተቃዋሚ ኃይሎችን የሚያጠፋ ህግ በማዉጣት የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የነጻነት ፍላጎት ለማፈን ብዙ ጥሯል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ እራሱን “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” ትዉልድ ብሎ በመጥራት ህዘብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ እንዲኖር ለማድረግ ብዙ ታግሏል። ቆራጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ስድቡን፤ ንቀቱን፤ እስራቱን፤ግድያዉንና ስደቱን እንዳመጣጡ መክቶ በፍርሀት ዉስጥ የማይኖር ህዝብ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ ለወዳጁም ለጠላቱም በግልጽ አሳይቷል። ይህ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓም አዲስ አበባ ዉስጥ የታየዉ የትግል መነሳሳት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማቀፍ ወያኔና በጠመንጃ ኃይል የመሰረተዉ ዘረኛ ስርአቱ እስከተወገዱና ኢትዮጵያ ፍትህ፤ ነጻነትን ዲሞክራሲ የነገሱባት ምድር እስክትሆን ድረስ መቀጠል ይኖርበታል፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ሰዉ ቆሞ መታገል ይኖርበታል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

“ይህ መንግሥት አይመጥነንም”

$
0
0

ሰሞኑን ኢትዮጵያ የዓለም መገናኛ አጀንዳ ሆናለች። ለዘመናት እጇን ኢትዮጵያ ላይ ተክላ የኖረችው ግብጽ የምትዝተው ዛቻና፣ በቅርቡ ተቋቁሞ ታላቅ ታሪክ በማስመዝገቡ የተረጋገጠለት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ አጀንዳዎቹ ናቸው…

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ    የ“ምርቃና” መግለጫ ለኢህአዴግ ድንጋጤ

shemelis2-

በወጣት አመራሮች የተገነባውና በርካታ ሴት አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በዋናነት የተገኘው ድል የፍርሃት ደመና መገፈፉ ነው። አቶ መለስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ በ1997 ዓ.ም ዜጎች አልመው በሚተኩሱ የአጋዚና ታማኝ የህወሃት አባሎች ደረትና አናታቸው እየተወጋ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ የማይታሰብ ሆኖ ላላፉት ስምንት ዓመታት ቆይቶ ነበር።

ከዳር እስከዳር ድምጽ አልባ ሆኖ የተሸነፈው ኢህአዴግ በጠመንጃ ፣ በወቅቱ የነበሩት የቅንጅት አመራሮች ታሪካዊና ሊረሳ የማይችል ስህተት ተዳምረው የህዝቡን ቅስም የሰበረው የ1997 ዓ ም ምርጫ ጣጣውና ቆፈኑ እንዲሁ በቀላሉ የሚለቅ እንዳልሆነ በወቅቱ አስተያየት ተሰጥቶ ነበር።

“ሁለት አስርት ዓመታት ወደኋላ ተመልሰናል” ተብሎ የተዘጋውን በር የበረገደው ሰማያዊ ፓርቲ ከህዝብ ባገኘው ድጋፍ አዲስ አበባን የተቃውሞ ጎርፍ አጎረፈባት። ሰላማዊ ሰልፉ ሰላማዊና የተሳካ እንደነበር ኢህአዴግ ራሱ ተናገረ። ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ የሶስት ወር ጊዜ ከሰጠ በኋላ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

አዲስ አበባ አንድ ለአምስት፣ የጎንዮሽ፣ የሽቅብ፣ የህቡዕ፣ የገሃድ፣ የዘር፤ የታማኞች፣ የበጣም ታማኞች፣ የልማት፣ የአነስተኛ ስራ ፈጠራ፣ የጾታ፣ የዘር፣ የእድሜ፣ የተፈጥሮ ሁኔታ፣ የጥቅም ወዘተ የፈጠረው አደረጃጀት አፈር ድሜ መብላቱ ያስጨነቀው ኢህአዴግ ሰልፉ ተበትኖ ሲያበቃ ላንቃውን አላቀቀ።

እንደ ገበጣ ጠጠር በፈለገበት ጉድጓድ የሚወረውራቸውን ቅምጥ አሽከሮች ለመግለጫ አሰማራ። ለስምንት ዓመታት ታፍኖ የኖረ ህዝብ መቦረቁ አስደነገጠውና ከፊልም ክምችት ህግ መዝዞ ለመክሰስ ያመች ዘንድ ህጸጽ እንዲነቀስ አዘዘ። አቶ ሽመልስ ከፈረሹበት ፍራሽ ተነስተው በምርቃና የአፋቸውን ለሃጭ እንኳን በወጉ መቆጣጠር እያቃታቸው በሉ የተባሉትን ተፉ። አቶ ሬድዋንም ሰው በሌለበት የ2002 ምርጫ በስድብ አቶ መለስን በማስደሰታቸው ባገኙት ሃላፊነት ለጌቶቻቸው ምላስ ሆነው ህዝብ አወገዙ። እሳቸውም ተፉ።

አይ ጋዜጠኛነት – “አትነሳም ወይ”   

አንድ ህዝብ ለተቃውሞ ሲወጣ ሊያወግዝ፣ ሊዘልፍ፣ የፈለገውን ጉዳይ በማንሳት ሊራገም፣ ለተነሳበት ጉዳይ “ተነሱ” ብሎ በፍርሃትና ሚና ባለመለየት የተቀመጡትን ለመቀስቀስ፣ ለማበረታታት ነው። ከድሮ ጀምሮ አገርና ህዝብ እንዲተባበሩ ሲፈለግ፣ መሪዎች ሲገዝቱ በሠንደቅዓላማና የሁሉም ማተብ የሆነችውን አገር ስም በመጥራት ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን በጨነቀው ጊዜ ባወገዘውና በሚጠላው ሠንደቅ ሲነግድበት ታይቷል። አቶ መለስ “ጨርቅ” ብለው ባዋረዱት “ባንዲራ” እንዲገነዙ የፈቀደ ፓርቲም ነው። ታዲያ ከጥንት ጀምሮ ሰንደቅ ዓላማውን “ማተቤ” እያለ የሚጠራ ህዝብ የሰንደቁን flagስም እየጠራ “አትነሳም ወይ” በማለት ማዜሙ እንዴት ይበዛበታል? ደግሞስ ኢህአዴግና በዙሪያው የሰበሰባቸው አሽከር ባለስልጣኖቹ ስለ ሰንደቅ ክብር የመቆርቆር ሞራሉስ አላቸው?

ኢህአዴግን “ውሸትህ ሰለቸን” እያሉ ሲረግሙት ከነበሩት በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች መካከል “ለምን አዲሱን ሰንደቅ ዓላማ ያዝክ” በሚል የሚጨቃጨቁ አስር የማይሞሉ ሰዎች በካሜራ አድኖ ሰልፉን “ህገ ወጥ” ለማስመሰል የዳዳው ጋዜጠኛ ሙያውንም ሆነ ራሱን ስለማርከሱ ጉልህ ማሳያ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው።

ስለ ሰንደቅዓላማ ይነሳ ከተባለ ዜናው “በሰልፉ ላይ ባንዲራ ለምን አልወጣም? ሰንደቀዓላማውን የነፍሱ ያህል የሚያመልክ ህዝብ እንዴት አስቻለው? ሰንደቅዓላማ የተሸሸገበትስ ምክንያት ምንድን ነው?” የሚለውና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ነበሩ።

በባድመ ጦርነት ወቅት በዳግም ጥሪ አገሩን ሊታደግ የመከላከያ ሰራዊትን የተቀላቀለው /የደርግ ሠራዊት ሲባል የነበረውን/ ወገን ኩርፊያ ለማስታገስ “የቀድሞውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ” በባላደራነት በመስጠት ኢህአዴግ የሰውን ልጅ ለማይጠቅም ጦርነት መማገዱን ለሚያወቁ ዜጎች ኢህአዴግ ስለ ሰንደቅ የመቆርቆር መብት እንደሌለው ይረዳሉ። እንዲህ ያለው “ድርጅታዊ ክህደትና ዓላማ ያለው አታላይነት” ዝም ተብሎ አስር ሰዎች ተሟገቱ ብሎ የክስ ማመቻቺያ ሪፖርት ማዘጋጀት ጋዜጠኛ አያስብልም። ሰዎቹ እነማን ናቸው? አንድ ባንዲራ ብቻ እንዴት ሊታይ ቻለ? ማን አመጣው? እንዴት መጣ? ብዙ መጠየቅ የሚቻልበት ጉዳይ ሆኖ ሳለ መታለፉ አስገራሚ ይሆናል። ለነገሩ ሰልፉን አስመልክቶ አቋም ይዞ የጻፈ የአገር ውስጥ ሚዲያም አላጋጠመኝም። ለለቅሶ ግጥምና ሙሾ የደረደሩ ጋዜጠኞች ለህዝባዊ ተቃውሞ የሰጡት ሽፋን ደረጃው ዝቅ ቢልም ከመወረፍ አያድናቸውም።

አትነሳም ወይ በሚል መፈክር ማውረድና የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ መጠየቅ ህግን መተላለፍና የፍርድ ሂደት ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሆነ የሚዘግብ ዘጋቢ የሙያው ባለቤቶች ነን ለሚሉ ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ነው። አቶ መለስ እንደ ቴአትር ቤት ድራማ ይጫወቱበት በነበረው ፓርላማ ፊት፣ በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍ ዝግጅት፣ በፖለቲካ እስረኞችና ተከሳሾች ላይ አስቀድመው ውሳኔ ሲሰጡና ብይን ያሰሙ በነበረበት አገር “እስረኞች ይፈቱ” ብሎ መጠየቅ ወንጀል ሆኖ “ህግ ተጥሷል” ሲያስብል መስማት ሞቶ መበስበስ ሲታሰብ የሚዘገንነውን ያህል ይቀፋል። ለዚያውም በአቶ ሽመልስ ከማል አንደበት ሲነገር።

“የስካር መግለጫ”

የአቶ በረከት ተላላኪ የሚባሉትና ለታይታ የሚኒስትር ታፔላ የተለጠፈባቸው አቶ ሽመልስ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ ከንግራቸው በላይ መነጋገሪያ የሆነው በወቅቱ የነበሩበት የሙቀት ስሜት ነበር። አፋቸው ዳርና ዳር አረፋ ይደፍቃቸው ነበር። ሲያመነዥጉ የዋሉትን የጫት መጠንና አይነት መዘርዘር ቢከብድም ከፍራሽ ላይ ተጠርተው የችኮላ መግለጫ እንደሰጡ መደረጉን መሸሸግ አይቻልም። እዚህ ላይ “ምን አገባህ?” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል። ምን አልባትም የግል ጉዳይ እንደሆነ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። እኔ እስከማወቀው ግን ሰክሮ የተከበረ ህዝብ ፊት መቅረብ፣ መናገር እስኪያቅት ድረስ አይን እያጉረጠረጡ ለህዝብ ማውራት አግባብ አይደለም። አንድ ኪሎ ጫት ከ100 ብር በላይ በሚሸጥበት ሁኔታ ቀን በቀን ጫት ማመንዠክ ከመንግሥት ሠራተኛ (ባለሥልጣንም ጭምር) ወርሃዊ ደመወዝ ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ ለስርቆትና ሙስና ስለሚዳርግ የሚወገዝ ነው።

shemelisአንድ ክስተት ትዝ አለኝ፡፡ የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቦሪስ ዪልሲን በአልኮሆል አፍቃሪነታቸው ብዙ የተባለባቸው ነበሩ፡፡ እርሳቸው ከሥልጣን ለቅቀው በስፖርተኛነታቸው የሚታወቁትና በጁዶ የጥቁር ቀበቶ ተሸላሚው ቭላዲሚር ፑቲን ሥልጣን ከያዙ ጥቂት ዓመታት በኋላ ግመገማዊ ጥናት ተደረገ፡፡ በውጤቱም በዘመነ ዪልሲን እጅግ አሻቅቦ የነበረው የሰካራም ቁጥር ፑቲን ሥልጣን ከያዙ በኋላ መቀነሱ ይፋ ሆነ፡፡ ኢትዮጵያስ ድሮና ዘንድሮ…?

ወደጉዳዬ ስመለስ እንግዲህ እኚህ ሰው (ሽመልስ) ናቸው “ህገወጥ” በማለት የህዝብን ቁጣ የፈረጁት። የሚላላኩለት ኢህአዴግ ህግ አክባሪ ሆነና ይህ የታፈነ ህዝብ ህገ ወጥ ተብሎ ተፈረጀ። ኢህአዴግና ፍርድ ቤት የተለያዩ አካላት ተደርገው ታዩና “የፍርድ ሂደት ላይ ጫና ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ፣ ቀናውን የፍርድ ሂደት ለመበረዝ …” የተቃጣ ሰልፍ ሆኖ ቀረበ። ዳሩ ኢህአዴግ የሚሰበስባቸውን ሰዎች ለሚያውቁ፣ አቶ ሽመልስን በቅርብ ለሚያውቃቸው ጉዳዩ አይገርምም። ስርዓቱ የቆመው እንዲህ ባሉ ሰዎች መሆኑ ግን ያሳዝናል። አሁን ከሶስት ወር በኋላ በሚካሄደው ሰልፍ “የባለሥልጣኖች የጫትና የሺሻ ኮታ ይፋ እንዲሆን እንጠይቃለን” የሚል ጥያቄ ቢቀርብ ማን ቀርቦ “ሰልፉ ህግ መንግስቱን የሚጻረር፣ ጸረ ሰላም ሰልፍ ነው” ይል ይሆን?

“ይህ መንግስት አይመጥነንም”

ለዚህ ጽሁፍ መነሻዬ ይህ ሃሳብ ነው። መንግስት ህዝብን ካልመጠነ ችግር ነው። የደህንነትና ፖሊስ ሃይል ህዝብን ከሚሰልል ይልቅ ከህዝብ ጋር ሆኖ አገርን በጋራ ሊጠብቅ እንደሚገባ የሚጠይቁ አገር ወዳዶች “የሚመጥናቸው መንግስት” አለማግኘታቸው አሳሳቢ ነው። 22 ዓመት ሙሉ ጥላቻ ቢሰበክም እርስ በርሱ ሳይጫረስ እዚህ ደረጃ መድረሱ የሚያናድዳቸው የኢህአዴግ አውራ መሪዎች “ዛሬም ድረስ አልረኩም” የሚሉ ሰልፉ ላይ ነበሩ። እነዚህ ሰዎች ሲሉ የነበሩት ጉዳይ ከመድረክ ተነሳ። “ይህ መንግስት አይመጥነንም” ሲባል ተጮኸ። ድጋፍ ተሰጠ። በማይመጥናቸው አገዛዝ መተዳደር የማይፈልጉ የፍርሃት ቀንበራቸውን ሰበሩself። ሰማያዊ ፓርቲ ይህን ገድል በልጅነቱ ሰራ።

ሰማያዊ ፓርቲ ሰዎች በሚጥናቸው ፓርቲ መተዳደር እስኪችሉ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ ተናገረ። አሁንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አስተጋቡ “አዎ” አሉ። ይህ እውነት ነው። የማይመጥን አገዛዝ የሚወከለው አገዛዙ በሚሰበስባቸው ተላላኪዎቹ ነው። በማይመጥነው አገዛዝ መመራት ያንገሸገሸው ህዝብ ተቃውሞውን ገልጾ ሲገባ “ህገ ወጥ ነህ” የሚሉት አስቀድሞ በካርዱ፣ ከስምንት ዓመት በኋላ በድምጹ፣ በየጊዜው በተለያየ መልኩ የሚያወግዛቸው “ገለባ” ባለጊዜዎች ነው። አስቀድሞ አትመጥኑንም የተባሉ፣ ቢናገሩ ማን ያደምጣል? የተሻሉ የሚባሉ ባለስልጣናት ቢኖሩም ዝምታን እስከመረጡ ድረስ ለህዝብ የሚሰጡት ዋጋ የለምና አብረው ከመደመር አይድኑም።

“አለ ገና” – ተባለ!

ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው ሰማያዊ ፓርቲ እንዳስታወቀው ላቀረባቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች መልስ ካልተሰጠው ከሶስት ወር በኋላ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ሌሎች ፓርቲዎችም የሰማያዊ ፓርቲን ፈለግ ተከትለው በየክልሉና በሚታወቁ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት ዝግጅት ላይ እንደሆኑ አስታውቀዋል። በኦሮሚያ የኦህዴድ መፋዘዝን ተከትሎ የከረረ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። እንደ ጠላት እየታየ የሚፈናቀለው የአማራ ክልል ተቃውሞ ማካሄድ ከጀመረ ከወረዳ ወረዳ የሚዘል እንደሚሆን ይታሰባል። በደቡብ ሲዳማ የተቃውሞ ሰልፍ ከጀመረ ከርሟል። በቅርቡ በተካሄደው የማሟያ ምርጫ ወቅት አምጾ ነበር። አሁንም በቋፍ ላይ ነው።

የተቀመጠበት መቀመጫ እንደ ምጣድ የጋለበት ኢህአዴግ አስቀድሞ ወደ ማስፈራራት የሮጠው አቶ መለስ  “በ97 የተፈጸመው ዓይነት ጥፋት ሁለተኛ አይታሰብም” በማለት የተናገሩትና ያስተላለፉት ትዕዛዝ “ኦርኔል” ስለታወሰው ነው “አለ ገና” መባሉ እንቅልፍ ስለነሳው ነው። ተቃውሞው ወደ ክልሎች ይዛወራል መባሉ ቅዠት ውስጥ ስለከተተው ነው። ሁሉም ወደ ፊት የሚታዩ ቢሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ መፈቀዱ የሚመሰገን ነው። ተሰለፉ፣ ተቃወሙ ብሎ ፈቅዶ ለምን ጎነተላችሁኝ ብሎ ለክስና ለእስር መሯሯጥ ደግሞ ግለቱን የሚጨምር በመሆኑ ቢቀር የሚል የሚለውን ምክር እንደዜጋ ለመሰንዘር እወዳለሁ። ከሰሜን አፍሪካ ወደተነሳው የውሃ ፖለቲካ አውድማ ተምዘግዝገን ገብተናልና ቢያንስ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ወደሚያስችለን መንገድ ብናመራ ይበጃል። የአሁኑ ሰልፍና ተቃውሞ ጅምር ነው። ኢህአዴግ ከሰማ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። ብሔራዊ መግባባት በመፍጠር አንድ የውስጥ ጉዳያችንን እንዝጋ:: ህዝብ ወሳኝ አካል እንዲሆን የፈሰሰውን ደም እናስብ። በፍርሃቻና በስካር መግለጫ በማስፈራራት ህብረት መፍጠር አይቻልምና። (የጎልጉል ሪፖርተር ካለበት የዘገበው)


የግብጽ አምባሳደር በአስቸኳይ የመንግስታቸውን አቋም ጠይቀው እንዲያስረዱ መጠየቁን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንደምታራምድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ…

ኢትዮጵያ ከጎረቤት እና ከሌሎችም አገሮች ጋር በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ በጽናት ስታራምድ መቆየቷ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ዓባይ ግድብ ዙሪያ በግብጽ ዘንድ ሰፍኖ የቆየውን ጥርጣሬ ለማስወገድ ግድቡ ግብጽንም ሆነ ማንኛውንም የታችኛውን ተፋሰስ አገር እንዳይጎዳ የሚያረጋግጥ የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኢትዮጵያ እና አለም አቀፍ ባለሙያዎች የሚገኙበት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋምና ሪፖርት እንዲያቀርብ ሃሳብ አቅርባ ስራው ሲሰራ የሚኒስቴሩ መግለጫ አስታውሷል፡፡

የአጣሪ ቡድኑ ስራውን ሰርቶ ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ የሚፈጥረው ችግር እንደሌለ ባረጋገጠበት ማግስት አንዳንድ የግብጽ ባለስልጣናትና የፖለቲካ ድርጅቶች ተቀባይነት የሌለውና በሁለቱ አገሮች መካከል ተጀምሮ የነበረውን መልካም ግንኙነት የሚያሻክር ፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ማድረጋቸው የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስትንም ኣሳዝኗል ብሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናት የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩ ወደተባባሰ ሁኔታ እንዳይገባ በትእግስት ለማለፍ ቢሞክርም ይህ ገንቢ ያልሆነ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አሁንም ቀጥሏል ያለው መግለጫው በመሆኑም በትላንትናው ግንቦት 27 / 2005 ዓ.ም የግብጽ አምባሳደር ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠርተው ስለዚህ ሁኔታ በአስቸኳይ የመንግስታቸውን አቋም ጠይቀው እንዲሰጡ ተነግሯቸው ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አገራችን አሁንም ዋነኛ ትኩረቷ ድህነትን ማሸነፍ እና ለዚሁ አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ከሩቅና ቅርብ አገሮች የወዳጅነት ግንኙነት መፍጠር በመሆኑ ከግብጽ ጋር የተጀመረውን የትብብር ግንኙነት በዚሁ መርህ መሰረት አጠናክራ መቀጠል ትሻለች፡፡

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ ለአገራችን እድገት መፋጠን ከሚያደርገው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ግብጽንም ጨምሮ ለሌሎች ጎረቤት አገሮች ያለውን ጠቀሜታ አሁንም በድጋሚ ማስታወስ ትፈልጋለች ማለቱን ኢሬቴድ ዘግቧል፡


በአባይ ጉዳይ ሱዳን ከግብፅ የተለየ አቋም አሳየች

$
0
0

ሱዳን ከግብፅ የተለየ አቋም መያዟን የሱዳኑ ማስታወቂያ ሚኒስትር እና የመንግስት ቃል አቀባይ አህመድ ቢላል ኦስማን ለቴሌቭዥን ቃለመጠይቅ የሰጡትን ቃል ”የሱዳን ትሪቡን” ጋዜጣ ለህትመት አብቅቶታል።
ይህ ጉዳይ ውሎ አድሮ ሱዳን የአባይ ተፋሰስ ሃገራት በ2010 ዓም እ.አ.አቆጣጠር ለፈረሙት ለ”ኢንተቤንውል” እንድትገዛ ያደርጋት ይሆናል…..
ጋዜጣው በዘገባው የሱዳኑ ማስታወቂያ ሚኒስትር እና የመንግስት ቃል አቀባይ አህመድ ብላል ኦስማን ” የእኛ(ሱዳኖች)እይታ ግብፅን ላያስደስት እና ቅር ሊያሰኝ ይችላል።ነገር ግን ሱዳን ከኢትዮጵያ ግድብ ተጠቃሚ ትሆናለች……ሱዳን ለግብፅ ጥቅም አትገዛም” ማለታቸውን ጠቅሷል።

A rare disagreement has occurred between Sudan and Egypt over the possible impact of an Ethiopia dam on the downstream Nile basin countries.

The controversial Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) could see the course of the Blue Nile tampered with and Egypt has warned it would spare no effort to guarantee its share of the water.

But Sudan is warning of a possible water war between the Nile Basin countries because of Egypt’s ‘provocative’ stance.

Sudanese government spokesman Ahmed Bilal has asked Egypt to stop what he called provocations after an Egyptian opposition leader described Khartoum’s stand on in the issue as disgusting.

An Egyptian opposition leader, Mr Ayman Nour, publicly described the Sudanese stand on the Nile as disgusting.

Meanwhile, the US has asked the three countries to resolve the problem amicably through dialogue.

Mr Bilal demanded, at a press conference in Khartoum on Wednesday, that Cairo works with Sudan to safeguard Egypt’s interests instead of resorting to provocations.

He added that Sudan would get many benefits from the dam, including better supply of electricity and year-long regulation of the Blue Nile’s flow.

Egypt has warned that all options were open to protect its share of the Nile waters.

“We cannot let even one drop of Nile water be affected,” President Mohammed Morsy said during talks with political and religious leaders broadcast live on state television on Tuesday.

President Morsy also wrote on his official Twitter account: “It is necessary that we take steps to ensure Egyptian water security.”

“The current situation necessitates unity among our ranks to prevent any threat against Egypt,” added President Morsy.

The border

Egyptian Cabinet also met and issued a statement saying it opposed all projects that could affect the flow of the Nile.

Egypt said it had planned “several scenarios” depending on the outcome of an assessment to be conducted by the three governments.

In Khartoum, the Foreign ministry said Sudan would not be affected by the project, stressing in a statement that there were agreements and consultations between Sudan, Egypt and Ethiopia.

“Sudan respects the agreements to cooperate with those two countries (Egypt and Ethiopia) in matters that concern sharing the waters of the Nile and sharing mutual revenues,” the ministry said.

Egypt believes its “historic rights” to the Nile are guaranteed by two treaties of 1929 and 1959, which give it 87 per cent of the Nile’s flow as well as veto power over upstream projects.

But a new deal signed in 2010 by upstream Nile Basin countries, including Ethiopia, allows them to work on river projects without Cairo’s prior agreement.

The agreement signed in Uganda has endorsed new water sharing between the Nile basin’s 11 countries.

Ethiopia has begun diverting the Blue Nile 500 metres from its natural course to construct a $4.2 billion (3.2 billion euro) the GERD hydroelectric project.

The first phase is expected to be complete in three years, with a capacity of 700 megawatts.

Once complete, the dam will have a capacity of 6,000 megawatts.

The project, in Ethiopia’s northwestern Benishangul-Gumuz region near the border with Sudan, was launched in April 2011 by Prime Minister Meles Zenawi.

The Blue Nile joins the White Nile in Khartoum to form the mighty Nile River, which flows through Sudan and Egypt before emptying into the Mediterranean.

source:africareview.com



ኦባንግ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ ለማሰር መጣድፍ እንደማያዋጣ አስጠነቀቁ

$
0
0

obang-metho1-620x310ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውንና በሰላም የተጠናቀቀውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ላኩ…. በደብዳቤው ላይ ኢህአዴግ ሰልፈኞቹንም ሆነ የፓርቲውን አመራሮች ለማሠር የሚያደርገውን ሃሳብ ከመፈጸም እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡

አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ላይ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በቅድሚያ ግን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ሠልፉን በመፍቀዳቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ ከቀድሞው መሪ መለስ እንደሚለዩና ምናልባትም ህዝብን ለማዳመጥ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቋሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ መለስ በእንደዚህ ዓይነቱ ሠልፈኞች ላይ የህወሓት አልሞ ተኳሾች ተኩስ በመክፈት እንዲገደሉ ማድረገቸውና የፓርቲ አመራሮችን ማሳሰራቸውን እንደ ማስረጃ ጠቅሰዋል፡፡

የሕዝብ ጥያቄ በአግባቡ ምላሽ እስካላገኘ ድረስ እንዲህ ዓይነቱ የታቃውሞ ሠልፍ እየቀጠለ እንደሚሄድ የተናገሩት ኦባንግ የሕዝብን ጥያቄ ማዳመጥና ተገቢውን ምላሽ አማራጭ መፍትሔ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ ሌላ በአንዳንድ የኢህአዴግ አመራሮች ሠልፉ የጥቂቶች እንደሆነ ለማስመሰል የተወሰደው አካሄድ ፈጽሞ እንደማይሠራ ጠቁመዋል፡፡ በሠልፉ ላይ የታዩት ኢትዮጵያውያን ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ እንደሆኑና እነዚህም ክርስቲያን፣ ሙስሊም፣ የማያምኑ፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ሥራ የሌላቸው፣ አካለ ስንኩላን፣ የኢህአዴግ አባላት፣ ተማሪዎች፣ ወዘተ መሆናቸውን በማስረጃ አስረድተዋል፡፡

ይህንን ዓይነት ሕዝባዊ ትዕይንት ላዘጋጁት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ሰልፉን በሰላም ጀምሮ በሰላም በመጨረስ ጨዋነቱን ላሳየው ኅብረተሰብ በድርጅታቸውና በራሳቸው ስም ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ያቀረቡት አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዲህ ዓይነቱ ሠልፍ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎችና ከተሞች ቢካሄድ ኖሮ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛና ውጤቱም ከዚህ የማይለይ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በቅርቡም ይህንን ለማየት የሚቻል መሆኑን የጠቆመው ደብዳቤያቸው አቶ ኃይለማርያም እንደመሪ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉና በሕዝብና በመንግሥት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በምን ዓይነት ድልድይ እንደሚያገናኙት ጥያቄ በማቅረብ ይህንን የመወጣት ከፍተኛ ኃላፊነት እንደተደቀነባቸው ተናግረዋል፡፡

ትዕይንተሕዝቡን የጥቂቶች በተለይም የሙስሊሞች መጠቀሚያ እንደሆነ ለመናገር የሞከሩትን የኢህአዴግ አመራሮች ሊሄዱ ያሰቡት አካሄድ የተሳሳተ መሆኑን የጠቀሱት ኦባንግ በተለይ ሕዝቡን በሃይማኖት በመከፋፈል ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ለማግለል የተወሰደው አካሄድ የሚወገዝ መሆኑን በደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር መሬትን ብቻ ሳይሆን በደምም አገራችንን እንደሚጋራ ያስረዱት የአኢጋን ዳይሬክተር ከዚህ ውጪ ግን ሙስሊሙን በማግለል በአሸባሪነት ላይ ጦርነት እያደረጉ ለማስመሰል በኢህአዴግ በኩል የተደረገው ሙከራ የምዕራባውያንን ልብ እንደማያማልል ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ባለፈው አንድ ዓመት ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሰላም ያደረገው የተቃውሞ ሠልፍ በራሱ ማስረጃ እንደሚሆን ጠቅሰዋል፡፡

ሠልፉ ከተጠናቀቀና መንግሥት ራሱ በሰላም መጠናቀቁን ካመነ በኋላ በሌላ ሁኔታ ሠልፈኞችንም ሆነ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ለማሰር የማስፈራሪያና የዛቻ ንግግር ከኢህአዴግ አመራሮች መሠጠቱ ፈጽሞ አግባብነት የሌለው መሆን የተናገሩት አቶ ኦባንግ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም የሚከተለውን ብለዋል፡፡ “የእርስዎ አስተዳደር እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ የሚወስድ ከሆነ የበለጠ የህዝብን ቁጣ የሚያነሣሣ መሆኑን ላስጠነቅቅዎ እወዳለሁ” ካሉ በኋላ ይልቁንም እስካሁን የታሠሩት እንዲፈቱ፤ አፋኝ ሕጎች እንዲሠረዙ ግልጽና ፈጣን እርምጃ ባስቸኳይ እንዲወስዱ አማራጭ የሌለው ቁርጥ መፍትሔ አቅርበዋል፡፡

በአቶ መለስ ትዕዛዝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከተገደሉና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከታሠሩና ከታፈኑ በኋላ ኢህአዴግ ሁሉም ሰላም ነው በሚልበት ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ ሰልፍ ሕዝብን በማሰርና በመግደል የሕዝብን ድምጽ ማፈን በጭራሽ እንደማይቻል ያረጋገጠ መሆኑን የጠቆሙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ሰማያዊ ፓርቲና ሕዝቡ የሚጠይቀውን በመመለስ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ የማሸጋገር ከፍተኛ ሃላፊነት እንደወደቀባቸውና ይህንንም ሕዝብ እየጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡት፤ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ጸሐፊ ዶናልድ ያማሞቶ፤ ለአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ፤ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ከፍተኛ አባል ሴናተር ቦብ ኮርከር፤ በሕግ መወሰኛ ም/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሴናተር ክሪስቶፈር ኩን፤ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ክሪስቶፈር ስሚዝ፤ ለእንግሊዝ ውዕ ጉዳይ ሚ/ር፤ በአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም ለቢቢሲ፣ ጋርዲያን፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ወዘተ የዜና አውታሮች በግልባጭ የተላከው የደብዳቤው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ነው፡፡

SMNE Calls on Prime Minister Hailemariam Desalegn

To Lead Ethiopia towards Change by Answering the Demands of the People

June 3, 2013

His Excellency Hailemariam Desalegn,

Prime Minister of the Federal Republic of Ethiopia

Office of the Prime Minister

P.O. BOX – 1031

Addis Ababa, Ethiopia

Dear Prime Minister Hailemariam,

On behalf of the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE), I, as the SMNE’s executive director, am writing to you regarding the peaceful rally that took place in Addis Ababa yesterday, June 2, 2013. We highly commend you and the TPLF/EPRDF for allowing the rally to proceed without interference. Even though freedom of assembly is allowed under the Ethiopian Constitution; since 2005, Ethiopians have been denied this right. For the first time in eight years, after some negotiation with the Semayawi (Blue) party’s leadership to change the date, the TPLF/EPRDF government agreed to provide the permit that allowed the Ethiopian people the right to express their beliefs without arrests, brutality or death.

In response to this opportunity, an astounding number of Ethiopians came out—estimated at hundred of thousands—all to show their support for change. No one expected such a response, even the leaders of the rally; but it serves as an important revelation to all of us as to the deep thirst for freedom, justice, peace and opportunity that is within the hearts and minds of Ethiopians. That same thirst has united Ethiopians of different ethnicities, religions, genders, regions, socio-economic levels and political alliances in their call for change.

First of all we truly commend you, Mr. Prime Minister for allowing this rally to go forward. It shows a different kind of leadership—even though it is under the same TPLF/EPRDF government—because it takes strength, principle and wisdom to hear the discontent of the people. You may also better understand the risks of ignoring the very real rumblings of the people on the ground, which will not go away until they are genuinely addressed. It is even more important in this changing world where support from the people makes a difference in a government’s ability to function and be secure.

Like your predecessor, Meles, you could have ordered TPLF/EPRDF security forces to gun down our young people, arrest the leaders of the protest or to detain large numbers of demonstrators; however, you did not. We believe you, and other members of the TPLF/EPRDF, only allowed this rally to proceed because you may be more ready to listen to the people than ever before.

This should not only be applauded by us, but should also be recognized by others such as national and international human rights groups, civic organizations, donor countries, religious leaders and defenders of the law and freedom who have been wanting good governance, democracy and respect for human rights to come to Ethiopia.

Secondly, the rally itself was historic in nature by being very peaceful and we want to give credit to the police and security forces for not interfering in the peaceful demonstration. Though they were present, they treated people with respect. No one was arrested or detained and no one was harmed, harassed or threatened to our knowledge. This is exemplary.

Thirdly, we give enormous credit to the hundreds of thousands of Ethiopians who came out from their homes to show their support for change. Regardless of what political viewpoint one might hold, we should all be proud of how well they presented themselves and in doing so, represented all Ethiopians as they shouted during the rally the following: “We cannot be divided by our ethnicity! We cannot be divided by our religion.”

7The rally was carried out with great discipline, respect, civility and basic good manners towards others. There was no bloodshed or destruction. From start to finish it was peaceful. It makes Ethiopians a shining example to the world and is evidence once again that we are not people of violence, but people who seek a better future for the country we all share and love. Congratulations to the people!

Fourthly, we believe the Semayawi (Blue) party leadership, who called for this rally, should be commended for their extraordinary leadership in organizing and carrying out a peaceful protest where the diverse people of Ethiopia could demand the God-given rights of all Ethiopians.

First of all, their name, Semayawi, which means “blue”, denotes the calm and peace one sees on the colour of the clear sky and gentle flowing of the deep sea waters. The name reflects the nature of the movement as one that seeks to move an inclusive Ethiopia forward, but not by turbulence or violence but peacefully and with determination and persistence. Their expectations of participation were for several thousand participants. They were obviously greatly surprised with the huge numbers of people who came out.

Another excellent outcome was the diverse makeup of those participating in the rally. It demonstrated how dissatisfaction with the status quo was not merely a position held by a few but that it was widespread at the grassroots level. The people who came were not only from the Blue party, but were from different political parties, ethnicities, religions and regions.

Those rallying certainly included opposition members, but we believe it also could have included some who were pro-TPLF/EPRDF who saw the need for reforms. Among the participants were Muslims, Christians, non-believers, women, men, young, old, public servants, unemployed, students, teachers, business owners, religious leaders, the healthy, the disabled and in general, people from all walks of life.

This rally was only held in the capital city, but if Ethiopians had been given the opportunity to rally throughout our beautiful country, the number would have been in the millions. This shows that the people of Ethiopia want change. What they are demanding are four actions, which should not be difficult for the government to move forward on remedying. These include: 1) the release of all prisoners of conscience, such as politicians and journalists, 2) for measures to be taken to stop the forced eviction of Ethiopians from their homes and land, 3) to stop government interference in religious affairs, such as with Muslims and Ethiopian Orthodox, and 4) for the TPLF/EPRDF government to take action against injustice, the high cost of living and corruption. The good thing is that the protestors are asking for these peacefully.

Mr. Prime Minister,

You and the TPLF/EPRDF should understand that this is an important opportunity to act for the good of Ethiopia that should not slip from your hands. It is not in the interest of anyone, including the TPLF/EPRDF, to doggedly cling to the status quo. No longer can anyone pretend that the government is a government of the people. Instead, as the people now demand change, it clearly shows that the TPLF/EPRDF is not with the people and does not represent their interests even though the TPLF/EPRDF speaks of doing exactly that.

Governments, like Egypt, Libya and Tunisia, found themselves in similar trouble when they did not answer to the inspiration of the people. We all know what happened to them when they ignored the people and we should learn from their history. Now the response to the Ethiopian people’s demands are in your hands. There is no turning back from this reality; ignoring it will only create a worse crisis. Instead, we should all look at it as a God-given opportunity to create a better Ethiopia, a New Ethiopia, for all of us. As the African proverb says, “If you want to go faster, go alone; but if you want to go further, go together.” This offer is here before you today but it may not be there indefinitely. What can you do as the leader of Ethiopia to help build the bridge to a new Ethiopia for all our people? 5

Mr. Prime Minister,

We urge you to meet these demands; however, we are deeply disturbed by the statements coming from the following EPRDF officials: Ato Shimelis Kemal, the State Minister of Government Communication Affairs, Ato Redwan Hussien, the Head of the Secretarial Council of the EPRDF and Ato Bereket Simon, the Ethiopian Minister of Communication. Their statements all fail to acknowledge the great divide between those clinging to the “one group rules all” system of domination of the past and the majority wanting an inclusive Ethiopia for all of us as our future.

Furthermore, it shows a continuation of the TPLF/EPRDF efforts to try to divide Ethiopians, often by ethnicity but this time along religious lines between Muslims and Christians. It will no longer work. The Ethiopian Muslims are our precious brothers and sisters. They are our people. We do not only share land; we share blood.

The statements from Shimelis Kemal and Redwan Hussien both attempt to label some of us as terrorists, without cause, in order to prolong EPRDF hegemony. This is not only wrong, it is in error and very dangerous. They hope to label the Muslims in order to isolate them from the mainstream of Ethiopians and in order to gain support from the west in the War on Terror.  Western donors should be made aware of this unfair scapegoating.

The truth is that Ethiopian Muslims have been peacefully demanding their religious rights for over a year, as they gathered on the grounds of their own religious compound. Now TPLF/EPRDF officials are slandering them as they accuse them of being terrorists. What have they done? Nothing! In the last year, they have never vandalized anything, let alone ever harmed another human being. Yet, their leaders have been arrested and their mosque disrespected.

Their peaceful actions give evidence that they are different from what the government has portrayed them to be. They have consistently chosen a non-violent path to demand freedom from EPRDF government interference in the practice of their religion—a right guaranteed under the Ethiopian Constitution—and should not be accused of something they are not.

When they came out with the Blue party for this demonstration, they did not come out only as Muslims but they came out as human beings, asking for the same freedom, justice and peace that everyone else is demanding. There is no need to single them out from others like they were outsiders. If you saw the demonstration or viewed the pictures, you would see our beautiful people of differing backgrounds and beliefs, including Muslims, intermingled with each other in peaceful protest. There should be no boundary placed between them and others. They are us!

Mr. Prime Minister,

Let me be very clear, the SMNE is not for one group of people, but for all Ethiopians, including the TPLF/EPRDF and those who have different viewpoints, strategies or goals than we do. Will you and the government you represent do the same? There should be no “us” and “them” if we Ethiopians are to have a healthy, peaceful, prosperous society for ourselves and our descendants.

No government holds onto power forever and because of that we believe the TPLF/EPRDF only stands to gain from helping to build a society where the wellbeing and security of all people will be held in high regard—putting humanity before ethnicity. When such principles are embedded into the fabric of society we will all better flourish for no one is free until all are free. When one Ethiopian is harmed or hurt, we all are. When the pain is inflicted on one, it is inflicted on all of us.  What the people are demanding is not as a separate voice but as one people—no matter what religion, what ethnicity or from what region they come from, for we will stand together.

Some are fearful that your administration will quietly arrest, harass or intimidate leaders of the Semayawi (Blue) Party or other leaders and activists. I must warn you, Mr. Prime Minister and your government that such actions would only incite the people, especially following this government-permitted peaceful protest. What Ethiopia needs is not more arrests but for all our people to be released. We all know that the law has been repeatedly subverted for political purposes and that some of our best heroes and heroines our locked up. We call on you to release them so they might be part of building a better society. Repeal this anti-terrorism law that has been used to silence truth and the Charities and Societies Proclamation that has been used to suppress civil society. Now is the time for Ethiopians to be more united rather than divided if we are to build a shared future of hope rather than of doom.

If change does not follow these demands, the government should know that there is a limit on how much repression that people will endure. As the people of Ethiopia unite together, the likelihood of more pressure for change will only increase. There are simply not enough prisons to hold all the Ethiopians who demand change. Arresting the leaders will not make the people’s struggle die for the desire for change is here. Those who commit unjust acts against the people will ultimately be held accountable. In 2005, the government tried to stop the push for change, but here we are in 2013 and the people are still demanding it. Neither have the people forgotten those who committed the crimes of 2005. They are holding on to the belief that justice will eventually be done.

God created human beings to seek freedom. Where human beings are oppressed, there will be a struggle for liberation. Ethiopians, like others, will surely pursue freedom, especially as they embrace the shared struggle with other Ethiopians. If you, Mr. Prime Minister, as a different kind of leader than your predecessor, can lead the current government of Ethiopia to embrace a different vision from the status quo, you could be instrumental in ushering in an Ethiopia that would be a “win-win” for everybody. If not, the resistance to authoritarian rule will predictably arise and eventually, the people will bring change, but such change must be based on the right foundation so it does not simply replace one flawed system for another of the same ilk.

Mr. Prime Minister,

This is an opportunity for all of us. In light of this, we ask you, to demonstrate your leadership, even though most people believe that the TPLF leadership is using you to advance their own interests, limiting you from acting as you otherwise might do. If this is the case, this is where you should stand up for your principles and do whatever is morally right; even if you are isolated for it or must resign in protest over their wrongful control.

You will find that not only will Ethiopians stand with you, but even the people of moral fiber beyond the borders of Ethiopia will stand with you for doing the right thing. For the well being of our country, our descendants and our shared future, it is critical to give up something to get something better for all of us.

This is especially important at this critical time when external forces are talking about bombing the Grand Renaissance Dam.  According to The Associated Press articles news, entitled: “Egyptian politicians suggest attacking Ethiopia over Nile dam” published today June 03 2013. Please click at the following link to read the news reporthttp://www.thestar.com/news/world/2013/06/03/egyptian_politicians_suggest_attacking_ethiopia_over_nile_dam.html.

The AP reported that: “Politicians meeting with Egypt’s president on Monday proposed hostile acts against Ethiopia, including backing rebels and carrying out sabotage, to stop it from building a massive dam on the Nile River upstream” If this kind of thing happened, which we hope it will not, Ethiopia will be vulnerable. This is even more the case when the TPLF/ERPDF government fails to have the support of the people. If it happened, the powerful players of the world may side with others, not with Ethiopia. 

Mr. Prime Minister,

Please take time to reflect on the gravity of the times. The decision you make at this hour is not about only saving your power or the TPLF/ERPDF government but about saving our country and the future of our people and children.

May God give you and others within the government the wisdom and insight to realize what is at risk and then the strength and courage to act accordingly. As for the SMNE, we will always work with those who are genuinely seeking a more unified, free and just Ethiopia. We will stand with the people of Ethiopia, as they demand change. If you or others in the TPLF/ERPDF are part of bringing that change, we will also stand by you.

As we look at our ancient land, we are reminded that the blood that flows through our veins and nourishes our bodies also connects us to each other as one people through our ancestors, even those beyond our regions and borders. We must care about each other if we are to thrive for no one is free until all are free.

With faith in God, He is able to multiply our efforts and our resources to build our nation to be more righteous, just and livable. No blessings should be kept to oneself or one’s own ethnic group, but also should be used to bless all Ethiopians and others, including our neighbors in the world, just like the mighty Nile River that originates with us but nourishes millions of lives with its flow.

We are urgently awaiting your response.

Your brother Ethiopian,

Obang Metho,

Executive Director of the SMNE

910- 17th St. NW, Suite 419.

Washington, DC 20006 USA

Email:Obang@solidaritymovement.org.


ኢራን የኢትዮጵያ ግድብ ግብጽን ይጎዳታል ስትል አሳወቀች

$
0
0

የኅዳሴ ግድብ ንድፍ

ኢራን ዛሬ በነጋታው በለቀቀችው የኢራን መንግስት የዜና አውታር በሆነው press TV ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግብጽን የሚጎዳ ነው ብላለች…

ዜናውን ስታሰራጭ የትንተና ባለሞያው ተናገሩ ብላ ነው የዘገበችው። ሆኖም ይህ ዘገባ የግብጽ ሱዳን እና የኢትዮጵያ ሁለት ሁለት እና ዓለም ዓቀፍ አራት ባለሞያዎች የተሳተፉበት አጥኚ ቡድን ግድቡ ጉዳት እንደሌለው እና ጥቅሙ አመዛኝ መሆኑን በይፋ ለሶስቱም ሃገራት መንግስታት መግለጫ ልከው አቋማቸውን ማሳወቃቸው እየታወቀ እና ግድቡን በተመለከተ ግብጽን ጨምሮ ወካይ የላኩ ሃገራት የተማመኑባቸውን ባለሞያዎች በማጣጣል ተንታኝ ብላ ያለችውን ግለሰብ የግል ቁንጽል አስተሳሰብ አሰራጭታለች።

የዘገባው አቅራቢ መረጃ ላይ ተንተርሶ መናገር ሲገባው ለግብጽ የሚሞግት ዘመን ያለፈበት እና ያረጀ አስተሳሰቦችን ሲለፍፍ ተደምጧል።

ኢራን በኒውክሌር ግንባታ ፍላጎቷ ዓለም ዓቀፍ ተቃውሞ የገጠማት ሃገር እንደመሆኗ ከማንም በላይ ባለድርሻ አካላት ላልወደዱት ነገር የአንድን ሃገር ፍላጎት ሊጫኑት እንደሚችሉ ከማንም በላይ ተገነዘባለች። ሆኖም ይህን እያስተዋለች ይህንን ዘገባ በብሄራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ማሰራጨቷ የሚያስገምታት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዝንባት ምክንያት የሆነ ነው።

ኢትዮጵያ ግድቡን ለመስራት የተነሳሳችው ለልማታዊ ተግባር የኤልክትሪክ ሃይል ለማመንጨት እንደሆነ እና ለትብብር በሯ ክፍት እንደሆነ ከመጀመሪያው ማሳወቋ፡ ይህን ተከትሎ የተቋቋመ የሶስትዮሽ የባለሞ ያዎች ቡድን ባደረገው ጥናት ግድቡ ዓለም ዓቀፍ ስታንዳርዶች እንደሚያሟላ እና ጥቅም እንጂ ጉዳት እንደሌለው እያሳወቀ ያንን ችላ በማለት ባለሞያ የተባሉት እኚህ ግለሰብ ”ግብጽ የራሷን ፍላጎጎት የማስጠበቅ መብት አላት። ሌሎች ሰዎችም የራሳቸውን ፍላጎቶች የመጠቀም መብት ሊኖራቸው ይችላል። ሆኖም ግድቡ ግብጽን መጉዳት የለበትም። አለዚያ ሁሉም አማራጭ ክፍት ነው” ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የተጠየቁ የኢራን እና ፐርዥያ ጥናት ባለሞያ ይሄ የኢራን ህዝብ የሚደግፈው ከሆነ እጅግ አሳፋሪ ነው። ሆኖም ኢራናውያን በእንዲህ ዓይነት የከሰረ ንግድ አይሳተፉም ብሏል። ይህ የፖለቲከኞች ስካር ከመባል የማያልፍ ለግብጽም ምንም የማይፈይድላት ራስን ማስገመት ልንለው የምንችለው ተግባር ነው ሲሉ ባለሞያው አክለዋል።

ባለሞያው ኢራን ይህን ዜና ልታሰራጭ የሚኖራት ብቸኛ ምክንያት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ካላት ወዳጅነት እና ኢራን በኒውክሌር ግንባታዋ ምክንያት ከአሜሪካ ጋር ጸበኛ በመሆኗ ነው። ይህን ጸብ ተከትሎ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ማዕቀብ የጣለባት ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ምንም ነዳጅ ከኢራን መግዛት አቋርጧል።

ስለዚህ የተቀጥያ ትንኮሳ መሆኑ ነው ያሉት እኚሁ ባለሞያ ናቸው


Article 1

$
0
0

ዓባይና የመለስ ዜናዊ (ወያኔ) ታላቁ ሴራበከፋለ  ሰሞኑን የአለምንና የኢትጵያውያንን ሀሳብና አስተየት ለመለዎጥ ወይም ለማሳሳት ወያኔ በወኪሎቹ አማካይነት የተለመደዉን ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ከርሞአል… ዓባይ እንደሚጠቅመን ሆኖ ቢገደብልን እጂግ ደስ ይለን ነበር። የወያኔ ትግሬዎች ሰለአባይ ከባለቤቱ ከኢትጵይያ ህዝብ በላይ የሚያቀነቅኑበት የሚጮሁበትና ሚያስመስሉበት ምክንያቱ ሌላ ነው። እነሱ ሃገር ወዳድ ሌሎች ኢትዮጵዉያን ሀገራቸዉ ብታድግና ብትጠቀም የሚጠሉ ሆነው አይደለም።

የኢትዮጵያም ህዝብ ይህንን በደንብ ያዉቀዋል። ከእባብ እንቁላል እርግብ ኣልጠብቅም ብሎአቸዋ። ታዲያ ይኸ ሁሉ የአዞ እንባ ማፍሰስና የኢትዮጵያን ሀዝብ ጩኸት ለመቀማት የመሞከር ሚስጥሩ ምንድነው??? ወያኔ ኢትዮጵያን ለመጉዳትና ለረጂም ጊዜ እችግር ዉስጥ ለማስገባት ካስጠናቸዉ ትልልቅ ጉዳዮች (ፕሮጀችቶች) ኣንደኛዉና ዋናው የአባይ ግድብ ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚከተሉትን ነጥቦች ተመልከቱ:

ሀ) ግድቡ የሚሰራው በጥንቃቄ የመሀል ሀግሩን ህዝብ በተለይም አማራዉንና ኦሮሞዉን እንዳይጠቅም በጣም እርቆ በጠረፍ ላይ ነዉ። ይህም በተለይ አማራዉና ሌሎች በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦች በምንም አይነት ለእርሻ (ለመስኖ) ለመጠጥ ለኢንዱስትሪና ለኤሌክትሪክ ኣገልግሎት እንዳይጠቀሙ ታስቦ የተሰራ ነው።

ለ) ሁለተኛዉ የተንኮል አካል ይኽ ጥቅም የማይሰጥ ነገር ግን ሆን ተብሎ በኣካባቢዉ ግጭት እንዲነሳና በዚያ ጥቅም በሌለዉ ግድብ ክዚህ በፊት በሺራሮና በባድመ ላይ እንደተደረገዉ ሁሉ የኢትዮጵያዉያንን ደም በማፍሰስና እነሱ እየዘረፉ ለመኖር የዘረጉት ወጥመድ ነው። ግድቡ ከፍ ብሎ ከተሰራ ወደ ሌሎች ኣካባቢዎች ወደ ምስራቅና ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተዘርግቶ ሌሎች የሀገሪቱ ኣካሎች ይጠቀሙ ነበር ። ነገር ግን ያ ባለመፈለጉ የግድቡ ስራ ኤሌክትሪክ ለሱዳንና ለግብጽ ማመንጨትና መሽጥ ብቻ ሲሆን የተመረጠዉም ቦታ እድንበር ኣካባቢ ነው:: ይህም በመሆኑ ድንገት ግጭት ቢከሰት እድንበር ላይ በመሆኑ በግብጽም ሆነ በሱዳን በቀላሉ የሚመታና የሚመክን ነዉ። ልክ ወደ ትግሬ የባቡር ሃዲዱ ሲዘረጋ አማራዉንና ኦሮሞዉን አግልሎ ወይም ሳይነካ ከአዋሽ ተነስቶ ዳር ዳሩን እየዞረ በአፋር በረሀ እንደ ደጋን ጎብጦ ከተጉአዘ በሁዋላ ወደ ቀኝ በመታጠፍ የትግሬ ከተሞችን አዳርሶ እንደቆመው የባቡር መንገድ አይነት መሆኑ ነው።

ሐ) ሶስተኛዉ ትልቁ የሴራው አካል በአባይ ግድብ ስም እጂግ ግዙፍ የሆነ የኢትዮጵያ ሀዝብ ገንዘብ በህጋዊ መልክ መዝርፍና ማደህየት ነው። በዚህ ግዙፍ የዝርፊያ ስልት በኑሮ ውድነት ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች አርሶ ኣደሮች ነጋዴዎችና ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ካፋቸዉ እየተነጠቁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማይጠቅምና በራሳቸዉ ላይ ችግር ለሚፈጥር ሰራ እየተበዘበዙ (እየገበሩ) ነው። በሌላ በኩል በጣም የሚያሳዝነዉ ወያኔዎች የዘርፉትና በግልጽ አለም ካወቀዉ ገንዘብ ዉስጥ 3 .00 ቢሊዮን በመለስ ሰም የተቀመጠ ሲሆን 11.70 ቢሊዮኑ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ የሽሸ ነው። ይህ ማለት ወያኔወች የዘርፉት ገንዘብ ብዛት አራት የአባይ ግድቦችን ሊያሰራ የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ በመድማት ላይ መሆኑዋን የዉጭ ሚዲያዎ በግልጽ ጽፈዋል።

መ) ሌላዉ ኣስገራሚ ሚስጥር አልጃዚራ ላይ ከግብጽ ከኢትዮጵያና ከእንግሊዝ አገር ተጋብዘው በተደርገው ዉይይት ላይ ግብጻዊቱዋ እዲህ ብላለች ” ግድቡ ሀገራዊ (ናሽናል) ሳይሆን ክፍለ አሁጉራዊ (ሪጂናል) መሆኑን ሙዋቹ መለስ ዜናዊ ተስማምቶበታል”…. በማለት የዎያኔዉ መሪ ክህደት መፈጸሙን አጋልጣለች (ይህንን ታሪካዊቪዲዮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማየት ኣለበት)። ይህም ማለት የግደቡ ባለቤቶች ሱዳን ግብጽና ሌሎች በአካባቢዉ የሚገኙ ሀገሮች ጭምር ናቸዉ ማለት ነው::

ከዚህም አልፎ ተርፎ ዜጎች መሰዋእትን ከፍለዉ ባቆዩዋት ሀገር ዉስጥ መብታቸዉን በመጠየቃቸዉ ብቻ በጸራራ ጸሃይና በድብቅ ሲገደሉ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ወገኖቻችንን ከሚኖሩበርት ቦታ በግፍ እያፈናቀሉ የነጻነት ታጋዮችን እያሳደዱ እየደበደቡ እያሰሩና እያሰቃዩ ለህዝቡ ጠላት ከመግዛት በስተቀር ለእድገት ለማይጠቅም ግድብና በአባይ ስም ለኢትዮጵያ አሳቢ መስሎ ለመታየት እየሞከሩ ነው። ፕሮጀክቱ ሲነደፍ በጥላቻና ግዙፍ ገንዘብ ለመዝረፊያ በመሆኑ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዉያንንና በአባይ ተፋሰስ አካባቢ ኑዋሪ የሆነውን ሰፊ ሕዝብ አላማከሩም። ህዝቡም ሃሳቡን ተጠይቆ አልተሳተፈበትም።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወያኔ ለአንተ በታሪክ ዉሰጥ ጥሩ አስቦም ሆነ ሰርቶ ስለማያዉቅ በምትወደዉ ወንዝሕ በአባይ ሽፋን የተጋረጠብህን ተንኮል በጣጥሰህ ወያኔን በማስወገድ በሚጠቅምህ መልኩ አባይንና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችህን ወደፊት ለመገንባት ስለምትችል አሁን ወያኔ በሚነዛው የዉሸትና ፕሮፓጋንዳ እንዳትረታ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ


Somalis march in Cape Town against South Africa attacks

$
0
0

BBC News

Members of the Somali community in South Africa have marched to parliament in Cape Town to protest against recent attacks on foreigners…

Three Somalis have been killed this month and the Somali government has requested the South African authorities to do more to protect their nationals.

The protest march

About 200 people took part in the protest, holding a banner reading: “Everyone is a foreigner somewhere.”

Correspondents say xenophobic attacks have increased recently.

Some of the protesters accused the authorities of not doing enough to prevent attack on foreigners, especially Somalis, or prosecute those responsible.

Two Somali brothers were allegedly hacked to death with an axe in the northern Limpopo province on Thursday night.

Last week, Abdi Nasr Mahmoud was stoned to death in Port Elizabeth.

Mohamed Aden Osman told the BBC that criminals saw Somalis as “soft targets”.

According to the Centre for Human Rights at the University of Pretoria, South Africans are becoming “increasingly desensitised” to attacks on foreigners, The Sowetan newspaper reports.

The BBC’s Mohammed Allie in Cape Town says the violence is linked to the massive unemployment among young South Africans.

In the past two decades, many thousands of Somalis have fled conflict at home and moved to South Africa, where many have opened small shops and kiosks in townships.


መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ሊጠራ ነው

$
0
0

መንግስት ለውይይት ካልተዘጋጀ 33ቱ ፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅደዋል ዋና ኦዲተርና የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰሞኑን ለፓርላማ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በነገው ዕለት በመድረክ፣ በመኢአድ፣…. በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮዎች የፓርቲዎቹ አመራሮች ውይይት እንደሚያደርጉና መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠራ ተገለፀ፡፡ የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የፓርቲዎቹ አመራሮች በነገው ውይይት የሚደርሱበትን የጋራ መግባባት በመያዝ፣ መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራትና በአዲስ አበባ ከተማ በመዘዋወር የመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ ሙስና የስርአቱ መገለጫ በሆነበት፣ የህዝብ ሃብት እየባከነና የዲሞክራሲ መብቶች እየተጣሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ መንግስት እምቢተኝነቱን ትቶ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እንዲያደርግ ጥሪ እንደሚተላለፍለት ገልፀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚቀርብለትን የውይይት ሃሳብ ተቀብሎ ወደ ውይይት ካልመጣ፣ 33ቱ ፖርቲዎች ሰላማዊ ትግሉን ተጠቅመው አገራዊ ንቅናቄ በማድረግ፣ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውንም አስረድተዋል፡፡


አቶ ማርክነህ የቀበሩት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተያዘ

$
0
0

Ethiopian Currency (Birr)

የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ህግምክትል ዳይሬክተር የነበሩትአቶ ማርክነህ አለማዮሁ አሸሽተውት የነበረው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ መያዙን የምርምራ ቡድኑ አስታወቀ

የምርመራ ቡድኑ እንዳስታወቀው አቶ ማርክነህ አለማሁበወንድማቸው አማካይነት ለመሰወር አቅደው የቀበሩት አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሺህ ብር የተገኘው ግንቦት 30/2005 በወላይታ ሶዶ ዙርያ ወረዳ ወራንዛላሸ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።

አቶ ማርክነህ አለማየሁ በባለስልጣኑ በሃላፊነት ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ባለመክሰስና መክፈል የሚገባቸውን የመንግስት ገቢ እንዳያስገቡ በመመሳጠር የሰበሰቡትን ገንዘብሊያሸሹ ቢሞክሩም በህብረተሰቡ ጥቆማ ከተቀበረበት ተቆፍሮ መገኘቱን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

የወንጀል ሃብትን የሚያሸሽ ወይም የሚተባበር በህግ ተጠያቂ እንሚያደርግ የምርመራ ቡድኑ አሳስባል።

ህብረተሰቡ ላደረገው ጥቆማ ያመሰገነው የምርመራ ቡድኑ ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረ አቅርባል።


Oromo Students in Germany Take to the Streets to Protest Human Rights Violations in Oromia

$
0
0

Statement of peaceful demonstration of Union of Oromo Students in Germany We, members of the Union of Oromo Students in Germany (UOSG),,,, protest against human rights violations of the criminal Ethiopian regime known as the Tigray People’s Liberation Front or Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (TPLF/EPRDF). For example, the Oromia Support Group in United Kingdom, a non-political organization founded to raise awareness of human rights violations in Ethiopia, has reported four-thousand two-hundred seventy-nine (4,279) extra-judicial killings and 987 disappearances of civilians in Ethiopia from 1994–2010.

Video: Bilisummaa.info

Gadaa.com

The TPLF/EPRDF regime’s anti-peace characteristics are demonstrated by multidimensional human rights violations: eviction of peasants from ancestral land without compensation, large-scale displacement of rural communities through initiation and aggravation of local conflicts, killing freedom of expressions, illegal interference in religious affairs, increasing refugees, environmental degradation, perpetrating & aggravating conflicts in the Horn of Africa, maintaining border conflicts, negative impacts of border war with Eritrea, war crime in Somalia, and etc.

We believe it is necessary to refrain from sponsoring anti-peace and authoritarian policies of the TPLF/EPRDF regime in order to realize sustainable peace and stability particularly in Ethiopia and generally in the Horn of African region. Principle of peace & security for all humanity is the universal value that it should also be applicable for the human beings in Ethiopia and the Horn of Africa.

Therefore, we appeal respectfully to families of international communities in general and the Federal Democratic government of Germany in particular to stop indirect or direct involvements in activities suppressing the struggle of the Oromo people in particular and the oppressed peoples of the Horn of African region.

We would like to remind you that objectives of the struggle of the Oromo people are to overcome century-old injustice, to live in freedom, to build peace, to practice democracy, and to achieve stability.

Justice and Peace Shall Prevail!

Members of Union of Oromo Students in Germany Aschaffenburg and Würzburg Branch

4th of June 2013, Würzburg, Germany



“ከወያነ ያነሰ የአገር ፍቅር ያለን አይመስለኝም” – ዶ/ር መረራ ጉዲና

$
0
0
  • “የጦርነት መንገድ ለኢትዮጵያም ለግብፅም አይጠቅምም” – አቶ ሙሼ ሰሙ “ከገዢው ፓርቲ ያነሰ የአገር ፍቅር ያለን አይመስለኝም” – ዶ/ር መረራ ጉዲና …..ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ መቀየሯንና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግብጽና በሱዳን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተጽእኖ እንዲያጠና የተቋቋመው የኤክስፐርቶች ቡድን ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ፤ የግብጽ ተቃዋሚዎች የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማስተጓጐል ያቀረቡትን ሃሳብ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ተቃወሙት፡፡ የግብፁ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ከአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ከተቃዋሚዎችና ከሃይማኖት ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፤ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጅና፣ የአገሪቱን ተቃዋሚዎች በመደገፍ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንድታስተጓጉል ማስገደድ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተቃዋሚዎች የግብፅን ዛቻ አጣጣሉት

  • በስብሰባው ላይ የተንፀባረቀውን ሃሳብ በተመለከተ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ “በርግጥም ግብፃውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቀዳዳ አይጠቀሙም ብሎ መከራከር ያስቸግራል፡፡ የአገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ለውጭ ሃይል መጠቀሚያ ለመሆን ይዘጋጃሉ የሚል ግምት የለኝም” ብለዋል፡፡ “በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ቢያንስ ቢያንስ ከኢህአዴግ ያነሰ የአገር ስሜት አላቸው ብዬ አልገምትም” ያሉት ዶ/ር መረራ “ይሄም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ፈርጀ ብዙ ችግሮች ካልተፈቱ የውጭ ሃይሎች ባገኙት ክፍተት ተቅመው የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር አይሞክሩም ማለት አይቻልም” ብለዋል፡፡ “ከሰባት ዓመት በፊት በፓርላማ የሶማሌን ጉዳይ በሚመለከት ስንወያይ ዳር ድንበራችንን አገራችን ውስጥ ሆነን መከላከል ይሻላል፣ የሰው አገር መግባት አስቸጋሪ ነው፣ እና አሜሪካ እንኳን ያን ያህል ሃብትና ቴክኖሎጂ ይዘው በድል መውጣት አልቻሉም” ብለን ለቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሃሳብ አቅርበን ነበር፡፡ እሳቸው ግን “በእኔ ይሁንባችሁ ጥቂት ሳምንት ብቻ ነው በዚያ የምንቆየው” ሲሉን ነበር፡፡

ኢትዮጵያ አሁንም እዚያው ነች፤ ያ ቀዳዳ አለ፤ የኦጋዴን፣ የኤርትራ፣ የሱዳን ቀዳዳዎች አሉ፡፡ የውጪ ሃይሎች እነዚህን ክፍተቶች ለመጠቀም አይሞከሩም ማለት አይቻልም፡፡ የአባይ ወንዝን በሚመለከት ከገዥው ፓርቲ ያነሰ የአገር ፍቅር አለን የሚል ግምት የለኝም ብለዋል ዶ/ር መረራ፡፡ አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፤ “የግብፅ መንግስት በአገር ውስጥ ያሉና በሰላማዊ ትግል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን የፈለጋቸው፣ የራሱን አጀንዳ ለመሸጥ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የመልካም አስተዳደር የፍትህ እጦት አሳስቦት አይደለም፣ የአባይ ግድብ እንዳይገደብ ተቃዋሚዎችን መሳሪያ አደርጋለሁ ብሎ መነሳቱ አግባብ አይመስለኝም፣ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም አጀንዳ ስላልሆነ ትርጉም የለውም” ብለዋል፡፡

“መሐመድ ሙርሲ፤ የኢትዮጵያ መንግስትንና ህዝቡን አከብራለሁ የሚል አስተያየት ሲሰጡ በቅርብ ሰዎቻቸው ተሰምተዋል፡፡ በደጋፊዎቻቸውም ይሁን በህዝቡ ወይም በማንም ተባባሪ ሃይል ቢታገዝም፣ የጦርነት መንገዱ ብዙ ርቀት አያስኬድም፡፡ የጋራ ጥቅማችንን ለማስከበር በሩ ክፍት እስከ ሆነ ድረስ ተቀራርቦ መነጋገር እንጂ፣ በጦርነት መልኩ ማሰብ ዘመኑ የሚፈቅደው አይደለም፡፡ በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዲያደርጉ በስምምነት ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ያወጡትን ዝርዝር ሰነድ መመልከትና በምስራቅ አፍሪካ አገሮች የሚገኙ ህዝቦችን መጥቀም የሚችልበትን አቅጣጫ መከተል ነው የሚበጀው፡፡ የጦርነት መንገድ ለኢትዮጵያም ለግብፅም አይጠቅምም” ብለዋል፡፡

Source:www.addisadmassnews.com


ሰበር ዜና ትናንት ሌሊት በሞጆ ከተማ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ሹፌሩን ጨምሮ 16 ሰዎች ሞቱ

$
0
0
ትናንት ሌሊት በሞጆ ከተማ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ሹፌሩን ጨምሮ 16 ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን ሌሎች አምስት ተካፋዬችም ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል..
አደጋው የደረሰው ኮድ 3 አዲስ አበባ የሰሌዳ ቁጥሩ 27 8 55 የሆነው የሚኒባስ ተሽከርካሪ ከተፈቀደው የጭነት ልክ በላይ ዘጠኝ ትርፍ ሰዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት ሲጓዝ በሞጆ ከተማ በብልሽት ከቆመ ማርቼዲስ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በአደጋው የሞቱት 16 ሰዎች አስከሬን በአዳማ ሆስፒታል ለጊዜው የገባ መሆኑንን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ለ 15 ቀናት ያክል በቆየው እና ትላንት በተጠናቀቀው በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ ሲካሄድ በነበረው በኢትዬጲያ እየተጠናከረ የመጣውን የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ በሃይል ለመስቆም በሚቻልበት መንገድ ላይ የሚመክር ስብሰባ ተካፍለው ከነበሩት አቃቤ ህጎች እና ዳኞች መካከል 15ቱ ሞጆ ከተማ ላይ በገጠማቸው የመኪና አደጋ ሂወታቸው ማለፉን እየተነገረ ነው፡፡

ዶ/ር መራራ ጉዲና “ለእኛ እንቢ የተባለው ሰልፍ እንዴት ለእነርሱ ለሰማያዊዎቹ ተፈቀደ?”

$
0
0

የሰማያዊው ፓርቲ ሰልፍ ሰሞኑን አነጋጋሪ ሆኖዋል፤ ገናም አነጋጋሪነቱም ይቀጥላል። መድረክን በተለይም ደግሞ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መራራ ጉዲና የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ የምጽፈውን ነገር አሰበኩኝ እና ብዕሬ ልተፋብኝ የምትችውን የቃላት ውርጅብኝ በመፍራት ላልፋቸው ወደድኩኝ…. ቢያንስ እነዚህ ሰዎች ስለእኔ እና ስለራሳቸው ሲሉ ደክመዋል እና እግዚአብሔር ድካማችሁን ይቁጠርላችሁ፣ በቁማችሁ ኢትዮጵያ ነጻ ወጥታ ለማየት ያድላችሁ በማለት ለመመረቅ እወዳለሁኝ።

ደግሞ በተለያዮ ጊዜአት የሚያነሱዋቸውን አተያየት በተመለከተ ሰምቶ እንዳልሰማ ቅር ተሰኝቶ ቅር እንዳልተሰኘ በመሆን ዝም ብሎ ማለፉንም አልወደድኩትምና የማደርገውን አሰብኩኝ ለጥቂት ጊዜም….ምን ላድርግ ይሆን? በማለት እያሰብኩ…እያወረድኩኝ… እያጠነጠንኩኝ ሳለ በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁኝ ዶ/ር መራራ ጉዲና ስለ ግል ሕይወታቸው ፣ ስለ ቤተሰባቸው እና ስለ አጠቃላይ ስለ መላው እምነታቸው ከተወሰንን የዮኒቨርስቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን አዘውትረው መኪናቸውን ከሚያቆሙበት ስፍራ ሄደን የተለያዮ ጥያቄዎችን ጠይቀናቸው…. ዶ/ር መራራ ግልጽ እና ተግባቢ ሰውን አቅራቢ የሆኑ ሰው ናቸው እናም በወቅቱ ለጥያቄዎቻችን ሁሉ ያገኘነውን ምላሽ አልረሳውም….. አንዳንዱ ምላሻቸው በተለይ ቤተሰብን፣ ትዳር እና ልጆችን በተመለከተ የዶ/ር መራራ መስዋዕትነት ትልቅ መሆኑን አስገንዝቦኝ ነበረና ነው። ምንም እንኳን አሁን ሰማያዊዎቹን በተመለከተ የሰጣችሁት አተያየት ባልስማማም እናንትን ከልቤ ማክበሬን በመግለጽ ወደ ፍሬ ነገሬ ወይ ወደ ፍሬ ከርስኪዮ ልግባ ( በቅንፍ ለእኔ ፍሬ ነገር የሆነው ለሌላው ፍሬ ከርስኪ ቢሆንስ ብዮ ነው)።

ሰላማዊ ሰልፍን አስመልክቶ መራራ ቆይ ለእኛ እንቢ የተባለው ሰልፍ እንዴት ለእነርሱ ለሰማያዊዎቹ መሆኑ ነው ተፈቀደ? ብለዋል እናም ጣቶቻቸውን ወደ ወያኔም ወደ ሰማያዊዎቹም ቀስረዋል…..በአገራችን የልማድ አባባል አመልካች ጣትን ወደ ሌላው ሲቀስሩ የተቀሩት ጣቶች የሚያመላክቱት ወደ ራስ ነውና ሰልፉ የተከለከለበትን ምክንያት በተመለከተ ራስንስ መፈተሽ መልካም አይለምን? እናም ወዳጆቼ ነገሩ ያለው ሰልፉን ከሚፈቅደው ወይንም ስለ ሰልፉ ከሚጠየቀው ከወያኔ ብቻ ባይሆንስ? ነገሩ ያለው ከጠያቂውስ ቢሆን? ለምሳሌ ወያኔ ፈቃድ አልሰጥም ሲል ይሕውላችሁ ይህ ጨቋኝ መንግስት ፈቃድ አልሰጥም አለኝ አይገርማችሁም? በማለት ከፍተኛ ጩኸት በመፍጠር ሃላፊነትን ከራስ ላይ እያወረዱስ ቢሆን? እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት እነይልቃል ሰልፉ የተፈቀደላቸው በግድ ነው፤ እንዴት? ሰማያዊዎቹ የሰልፍ ለፍቃድ ለማግኘት የሚያስፈልገው ማሳወቅ ብቻ ነው ….. ሕጉ የሚለው አሳውቁ እንጂ እስኪፈቀድላችሁ ዝም ብላችሁ ጠብቁ አይልም በማለት ለማሳውቅ ሄዱ….። እናስ? ለማሳወቅ ሲሄዱ ብልጡ ወያኔ ስለ ሰልፉ አላውቅም ለማለት ደብዳቤውን አልቀበልም ማለት.. ይህችን “ አኳኩሉ” ጨዋታ ድሮ እናቃታለን አሉላቹሃ እነ ይልቃል። ስለሆነም ምስክሮችን በማደራጀት ስብሰባ አስተባባሪው የመንግስት ክፍል በመሄድ እና በተገኘው የመገናኛ ብዙሃን ሁላ ነገሩን ለፈፉታ….እና ወያኔ እንዴት አልሰማሁም ይበል? በቃ ወያኔ ጨዋታው እንደተነቃበት ሲያውቅ ከተደበቀበት ብቅ ብሎ ……ማንም “ የአኳኩሉው” ጨዋታ ነጋ ሳይለው ነጋ አለላችሁ እና እፍርቱን ቀጠለ…የሚሰማው ሲያጣ በቃ ቀኑ ይቀየር አለ፤ ቦታውም ተቀየረ … የኮባው አደባባይም ከ250 ሺህ ሰዎች በሚልቁ ሰልፈኞች ደመቀ። ይህ ቁጥር ቀላል መስሎዋችሁ ከሆነ ተሳስታችሃል የድፍን የሓዋሳን ህዝብ እጥፍ ማለት ነው። ( እዚህ ጋር ለሰልፉ አስተናባሪዎች ዘፈን ልጋብዛቸው….አንበሳው አገሳን ልጋብዝ ወይንስ የቴዴን ታሪክ ተሰራን!!!.)…..( ሌላ ቅንፍ ከርዕስ ውጪ የራስ ትዝታ ይህችን የኮባ አደባባይ የተዋወቅሃት በልጅነቴ ከኳስ ሜዳ አካባቢ ለአስረኛው አብዮት ክብረ ባህል መጥቼ ነበር፤ ካልተሳሳትኩኝ በ1977 ዓ.ም ነበር… ሰማያዊዎቹ ከስንት ዓመታት በሃላ እዚሁ ኩባ አደባባይ ይዘውኝ ተሰየሙ….አምላክ ይባርካቸው!!!!)

አሁን መድረክን ….ከክብር እና ከታላቅ አክብሮት ጋር የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ…. የሰላማዊ ሰልፍን የሚያክል አስደንጋጭ ጥያቄ ወያኔን ስትጠይቁ የወያኔን ባህሪይ እና የሰላማዊ ሰልፉን ሕግ ሳታውቁት ነውን? ብዮ ልጠይቅ አሰብኩኝ እና ይህንን ጥያቄ በመጠየቅ መምህሮቼ እና አባቶቼ የሆናችሁትን እንደመሳደብ ሆኖ ስለተሰማኝ ጥያቄይቱን ተውኳት…. ምን ላድርግ የዕድሜያችሁን ሩብ እና እኩሌታውን ያህል ወያኔን ለመሞገት ያባከናችሁትን ጊዜ እንደ ቀልድ እና ቀለል ነገር ልቆጥረው አልወደድኩም እና ነው። ወደ ጥያቄ ልግባ …ከዚህ በፊት የብርቱኳን ሚደቅሳን እስር በተመለከተ ሰላማዊ ሰልፍ ስታቀነባብሩ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ መገኘት ያለበት የሰው ብዛት 200 ሰው ብቻ ነው ሲላችሁ እሺ ብላችሁ መስማማታችሁ በራሱ ሳስበው ዲሞክራቶች ስለመሆናችሁ ተጠራጠርኳችሁ…ቆይ ብርቱኳን ትፈታ የሚለውን ጥያቄ በመደገፍ የኢትዮጵያን 80 እና 90 ሚሊየኑን ሕዝብ ትታችሁ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ለዚያውም የቀበሌ 12 እና የኢየሱስ ሰፈር ልጆች ቢወጡ እንኳን ቁጥራቸው ከ20000 በላይ ቢሆን እንጂ ከዚያ አያንስም ….እና ብርቱኳን የፈፀመች ወንጀል የለም ወንጀል ተፈፀመባት እንጂ ብለው የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ከእናንተ ጋር ሰልፎን ለመቀላቀል ቢወጡ አይ እኛ የተፈቀደልን ለ200 ሰዎች ብቻ ነው ብላችሁ ልትከለክሉ ነበርን? ወያኔ የሰልፉን ተሰላፊ ቁጥር የመተመን መብትክ አይደለም፣ ይህ ዲሞክራቲክ አካሄድ አይደለም ልትሉት ሲገባ አሜን ብላችሁ መስማማታችሁ እና ሰልፉን ማካሄዳችሁ ምን አልባት ከእነይልቃል ይልቅ እናንተ ለወያኔ ያደረ እና የተንበረከከ ስለመሆናችሁ አያሳይም ትላላችሁ? ነገሩ፣. ነገሩን ለማስረዳት ልትምሉ ልትገዘቱ ትወዱ ይሆናል፤ እውነቱ ግን ተግባራችሁ ራሱ በራሱ ቆሞ ስለእናንተ እውነቱን ይነግረናል፣ አሁን እነርሱ እነይልቃል የወያኔን ብልጣ ብልጥነት እምቢ በማለታቸው ….እምቢተኝነታቸው ይኸው አደመቃቸው… ነገ ዘብጥያም ሊያወርዳቸው እንዲችል እነይልቃል ይረዱታል…. ለዛም የጨከኑ ይመስላል።

ወዳጆቼ፦ ተንብርካኪ ማንነት ይዞ ፖለቲካ ውስጥ ራስን መዶል ተገቢ አይደለም እንደ ጥፋት የምቆጥረው በዚህ ማንነት ፖለቲካ ውስጥ መነከሩ ላይ ነው፣ ትውልዱን ተንበርካኪ እንዲሆን እና በትውልዱ ላይ ፍርሃት እንዲነግስ ቀን እና ማታ በማወቅም ባለማውቅ ከመስራት መጠንቀቅ ያሻናል።

ስለ መድረክ ባላባቶች እንዴ….ታሪክን ወደሃሊት እንምዘዘዋ……ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ አሁን ይኸው በሰማያዊዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ግለት እስቲ ወደ 1997ዓ.ም እንጓዝ…. የ1997 ዓ.ምቱን ምርጫ ግለት ከፍ እንዲል እና እንዲሟሟቅ ያደረገው ማን ነው? ቅንጅት ወይንስ ህብረት/መድረክ? እንደሚታወቀው አብዛኛዎቹ ከዚህ በፊት ምርጫ ተሳትፈዋል። ምንም ግለት አልነበረም፤ ምናልባት በ1997 ምርጫ ልዮ ክስተት የባለ “ ቪ”ው ምልክት ቅንጅት መከሰት ነው። አሁን የህብረትን ምልክት አስታውስ ብትሉኝ ትዝም አይለኝም…..የ1997 ምርጫ ማዕበል እንዲቀጣጠል ያደረገው ነገሩን የተቀሰቀሰው በቅንጅቱ ነው። ይህንን እኔ ብቻ ሳልሆን ታሪክም ይናገረዋል፣ ህብረቱ እኔም አለሁበት ቢል የአይጢቲን ታሪክ ማስታወሱ በቂ ይመስለኛል። አንዲት አይጥ ከዝሆኑ ጀርባ ላይ ቂብ ብላ አብራ በድልድይ ላይ ስትሻገር … ድልድዮ ሲያረገርግ …አይጢቱ ወደ ዝሆኑ ዘንበል በማለት ድልድዮን አነቃነቅነው ያለቺው አይነት ካልሆነ በስተቀር …. ድልድዮ ያረገረገው በቅንጅት እና በሕዝቡ ነበር። ከቅንጅት ደግሞ የልደቱ/ክደቱ ኢ.ዴ.ፓ እና የሃይሉ ሻውል መ.ኢ.አ.ድ ከዚህ በፊት የነበሩትን ምርጫዎች የተሳተፉ ብዙም ለውጥ ያላመጡ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲዎች ናቸው…በ.ቅንጅት ውስጥ የቅንጅቱ እምብርት የነበሩት የብርሃኑ ነጋ ቀስተዳማዎች እና የዓለማየሁ ረዳ ኢ.ድ.ሊዎች ነበሩ።

ከሁሉም በላይ በወቅቱ ለነበረው እንቅስቃሴ እምብርት የነበረው ብርሃኑ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ ብርሃኑ የመደራደር እና የማግባባት ልማዱን ከዘሩ በደም የቀዳው ይመስል ወያኔን እያቄለ እና እያረጋጋ የሚዲያውን በር ውልል ብሎ እንዲከፈት ያሰደረገ ተቃዋሚዎች ያላቸውን ድርጅታዊ አሰላለፍ፣ ፕሮግራም ለመላው ህዝብ እንዲያስተዋውቁ ዕድል እንዲፈጠር ያደረገ ጀግናም ነው፤ በዚያን ወቅት ህብረቶች እኛ ስንት ዓመት ስንደክም ነገሩ ሳይከፈት እንዴት አሁን ይህ ሁሉ በር ይከፈታል በማለት ብርሃኑ ነጋን ከወያኔ ጋር አብሮ ያበረ የተባበረ ሰይጣን አድርገው ሲያወሩ፣ የወያኔ ጆሮ ጠቢ ነውም ሲሉን ነበር፤ እውነቱ ግን እንዲህ አልነበረም፤ ብርሃኑ ነጋ ከእነበረከት ስምኦን ጋር እንደሚተዋወቅ ራሱ በግልጽ አብሮም ጫካ በመውረድ ሲታገልም እንደነበር በመገናኛ ብዙሃን በሚደረጉ ክርክሮች ላይ አስታውቆ ነበር፤ ብርሃኑ ነጋ የሚደበቅበት ምክንያት ስላልነበረው ሁሉንም በግልጽ ያወራም ነበር። ለእውነት ትንሽ ጊዜ ብቻ ከሰጠናት እና ካስተዋልን እውነት ፍንትው ብላ ትወጣለች… እናማ እውነቱ ፍንትው ሲል 200 ሰዎች ሞተው ወደ ፓርላማ አንገባም ብለው ለመረጣቸውን ሕዝብ እነብርሃኑ ነጋ እና እነ ሃይሉ ሻውል ክብር ሲሰጡ…. የ200 ሰዎች ንጹሃንን ሞት ከቁብ ሳይቆጥሩ በደማቸው ላይ ተረማምደው ፓርላማ ተንደርድረው የገቡት እነ ህብረት እና ከቅንጅት ደግሞ እነ ልደቱ/ክደቱ ናቸው….እዚህ ጋር ፍሬን መያዝ ያስፈልጋል። ጥያቄ፦ ያኔ ለወያኔ ያደረው ማን ነው? ለወያኔ የተንበረከከውስ ማን ነው? እነርሱ ያለምንም ሕፍረት ወደ ፓርላማ ተንደርድረው ሲገቡ እነ ብርሃኑ ነጋ ግን ወደ እስር ቤት ተግዘዋል ፤ በወቅቱ የልደቱ/ክህደቱ ሸርታታነት ስለበረታ ህብረቶችን እናንተም ሸርታታ ናችሁ ያላቸው የለም…. በልደቱ/ክህደቱ እኩይ ተግባር የህብረቶች ሸርታታነት ተሸፈነ እንጂ ህብረቶች ከድሮውም ጀምሮ ሸርታታ መሆናችሁን አሳምረን እናውቃለን.. አቋም የሚባል እንዳልፈጠረባችሁ አስተውለናቸዋል።

ሕብረቶች በእነብርሃኑ ላይ ብዙ ዘመቱ…..የተሳካላቸውም መሰለ…..ቀስተዳመናን ይዞ የተከሰተው ብርሃኑ ከእስር ቤት የነጻነት ጎሕ ሲቀድ የተሰኘውን መጽሐፍ አስነበበን…… ይህ ሰው የቅንጅቱ እምብርት መሆኑን በድጋሜ በደንብ አስመሰከረ፤ አብዛኛዎቹ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስረው ጠዋት እና ማታ ካርታ እና ዳማ ሲጫወቱ (እውነታቸውን ነው ቃሊቲን እስር ቤት ካርታ ከመጫወት ሌላ አማራጭ ላይኖር ይችላል) አጅሬው ግን ተደብቆ ይጽፍ ነበር። ስሙ ብርሃኑ የመጽሓፉም ስም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቱ ስም ከብርሃን ጋር የተያያዘ ነበር ቀስተዳመና፣.የነጻነት ጎህ ሲቀድ ይለናል። ሰውየው ግጥጥሞሹ ድንገተኛ አጋጣሚ ነው ወይንስ ነገሩ እንዲገጥም ታስቦበት ነው? በሉልኝ። (እዚህ ጋር ለብርሃኑ ነጋ ከፍ ያለ ምስጋናዮን ላቀርብ እወዳለሁኝ…….ደግሞ ይህቺን ውዳሴ አንብባችሁ ግንቦት ሰባት ብላችሁ ክሰሱኝ አሉዋችሁ፤ ስለ ክስ ሳነሳ…እነ ብርሃኑ ስንት እና ስንተ ክስ ሲመሰረትባቸው እነ በየነ ጴጥሮስ ከዶ/ር እና ከረዳት ፕሮፌሰርነት ወደ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሸጋግረዋል አይደል? እንግዲህ አስቀድሜ ተናግሪአለሁ የሰማያዊው ሰልፍ ብቀል አናቴ ላይ ወጥቶዋልም ብያለሁ። አንዱ ሲሾም አንዱ ዘብጥያ ሲወርድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተመልክተናል፤ .ዘብጥያ የወረደውን የወያኔ አድር ባይ ሰላይም ነው ሲሉት ሹመት እና ሽልማት ከወያኔ የተለገሳቸው ደግሞ ታጋይ እና ጀግና ተደርጎም ሲቀቡት አይተናል.. በዚሁ አገር በእኛው ምድር፤ ወዳጆቼ የዚህ ነገር ሒሳብ ድምር ፣ ብዜት፣ ምኑም አልገባኝም።

ግን ግን……መድረኮች ለምንድን ነው ዝም ማለት ያቃታችሁ? እናንተ መስራት ያልቻላችሁትን እኮ ልጆቻችሁ መስራት መቻል አለባቸው ይህንን በራሱ እኮ ትልቅ ድል ነው። በተለይ እናንተ ሳትሞቱ በቁም እያላችሁ መፍጠር ያቃታችሁን ጉዳይ አዲሱ ትውልድ ፈጥሮት ሕዝቡም በመሃል አደባባይ ነጻነት…ነጻነት እያለ ሲጮህ ለተመለከተ እና የዕድሜውን ሩብ ለትግል እና ለነጻነት የሰዋ ሰው ሊደሰት እና ሊቦርቅ ሲገባው የሰጣችሁት አተያየት ስሰማ መገረምን ሞልቶኛል…..ምናለ ቢያንስ ዝም ብትሉ ….መጽሐፉ በምሳሌ 17፡28 ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቆጠራል ይለናል እና ዝም ብትሉ ኖሮ ጠቢባን መስላችሁ በተቆጠረችሁ…. እዚህ ጋር መስፍን ወልደማሪያምን ለማክበር ዕድል ስጡኝ….ትውልዱን ለመቀስቀስ ለመደገፍ የማይቦዝን ትልቅ ጋሼ…..ትልቅ አባት ነው…. አቦ ዕድሜክን እንደማቱሳላ ያርዝምልክ ከማለት ውጪ ምን ልለው እችላለሁኝ። ስለ አገሪቷ የተመኘከውን እና በልብህ የፀለይከውን በሕይወት ሳለህ ለማየት ያብቃክ… ምኞትህ መክሸፍ አይግጠመው። ከእኛም ስትለይ የጀግንነትህን ክብር ምድሪቷ አትንፈግህ…ለዚህ እኛንም አንተንም አምላክ ይርዳን አንተ ጠቢብ እና አስተዋይ ሰው ነህና። እንደመስፍን ያሉ አርቆ አስተዋይ በተፈጠሩበት አገር መድረኮችን በተለይ ደግሞ አንጋፋዎቹ የተመለከተ እንዲሁም የምትሰጡት አተያየት ያደመጠ ነገሩ ያረጀ ያፈጀ የማይረባ ከንቱ ይሆንበታል …. መድረኮች ከቻላችሁ በማስተዋል ተረጋጉ፣ መረጋጋት ካልቻላችሁ ደግሞ ዝም በሉ። ዝም አንልም ካላችሁ ግን ያው ይህ ድንጋይ ነገር ነው ብለን ወደመረገጥ መወርወራችን አይቀሬ ነው።

ወደ ሰማያዊዎቹ እና ወደ ሰልፉ ስመለስ በሰማያዊ ፓርቲ ስር የተሰባሰቡት ልጆች አንድም የወያኔን መሰሪ ባህሪይ በቅጡ የተረዱ ይመስለኛል፤ ይህንን ለማለት ካነሳሳኝ ምክንያቶቼ መካከል የሰላማዊ ሰልፉዋ ቀን አንዷ ናት። ለሰላማዊ ሰልፉ የመረጡዋት ጊዜ በራሱዋ ቅድስት ቀን ነበረች፣ ለአፍሪካዊያን በተለይም ለኢትዮጵያ የተቀደሰች ቀን፤ ይህችን ቀን ቀድመው ቅድስነቱዋን ስለተረዱ ሰማያዊዎቹ ቀኒቷ ላይ ቅዱስ እና ሰላማዊ አሳብ ይዘው ከተፍ አሉ። እነ አባቶቼ መራራ እና በየነ ግን ስንት እና ስንት ቅድስት ቀናት በአይናቸው ስር ሲያሳልፉ ሳይጠቀሙባቸው ከርመው፣ ስንቱን የአፍሪካ ስብሰባ ሲያልፍ ችላ ብለው ተመልክተው፣ ዛሬ እንዴት ለእኛ ተከልክሎ ለእነርሱ ይፈቀዳል? በማለት ጠየቁ
እንደ እኔ እምነት ይህ ጥያቄ ተገቢ ጥያቄ ነው። እንዴት እነዚያ ተከለከሉ? እንዴት እነዚህ ተፈቀደላቸው? የተከለከሉት ሰዎች በፖለቲካው የከረሙ ፖለቲካም የሚያስተምሩ ሁሉ ናቸው፤ የተፈቀደላቸው ደግሞ ወደ ፖለቲካ ከገቡ ጥቂት በጣት ለዚያውም በአንድ ጣት ብቻ የሚቆጠር ዕድሜ ያላቸው እምቦቅላ ነገሮች ናቸው። የመድረክ ጥያቄ ተገቢነቱን በተመለከተ እኔ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ እስማማለሁ፤ የፖለቲካ ሰዎች የትላንቱን ድካም እና ብርታት አመዛዝነው ለተተኪው ትውልድ ጥንካሬአቸውን በማስተላለፍ በወቅቱ የሚገኘውን ዕድል ለመጠቀምም ሆነ ከፊታቸው የተደቀነውን ጋሬጣ ለመቀነስም ይረዳል የሚል እምነት አለኝ እና ነው። ነገር ግን መድረኮች ይህንን ጥያቄ ያነሱት ሌላውን ጥፋተኛ ለማድረግ እንጂ ለድካማቸው ለመማር አይደለም…. መድረኮች በተለይም ባለአባቶቹ እኛ ዳንኪራ ያልረገጥንበት መድረክ የተቀደሰ አይደለም የሚሉ ባተሌዎች ናቸው።ይህንን ባህሪያቸውን በ1997 ምርጫ ወቅት በቅንጅቱ ላይ በከፈቱት ክፉ ወሬም ታዝቤአቸው ነበር፤ አሁንም ይኸው ደግሜ በሰማያዊዎቹ ታዘብኩዋቸው።

ምንም እንኳን ለምን ለእኛ ሳይፈቀድ ለእነርሱ ተፈቀደ የምትለውን የመድረኮችን ጥያቄ ብወዳትም ድምዳሜውን ግን ከቶውኑ ልስማማበት አልችልም። ድምዳሜያቸው ፖለቲካ እና ፖለቲከኛም አይሸትም….ወያኔ ጠቅላዮ ከሞቱ በሃላ አናት የሌለው አውሬ ሆኖ ሳለ የሕዝብን ሙቀት ለመጨመርም ሆን ብሎ ሰልፍ የሚፈቅድበት ምክንያት ወይንም ከአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ሰልፉን የሚያያይዝ ሞኝ ስብስብ እንደሆነ እኔ አላውቅም…ወያኔ መሰሪ እንደመሆኑ መጠን ፈሪም ነው በተለይ የሕዝብ ድምፅ እና ተቃውሞ ይፈራል፡፡ ይህ አይነቱን ድንጉጥ ማንነት ያላቸውን ግለሰቦች ያሰባሰበ የወያኔ ቡድን ሕዝብ እንዲቃወመው በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ባለበት ወቅት ፈልጎ ነው የሚል መላ ምት ሊዋጥልኝ አይችልም። ነገር ግን ወያኔ በታሪኩ እንዲህ ያለውን የእሳት ጨዋታ የሚጫወትበት ተነሳሽነትም ፣ ሞራልም፣ ዝግጅትም የሌለው የመንደር ዋልጌ እና ዱርዮ ሰዎች የተሰበሰቡበት ስብስብ ከመሆኑም ከላይ ድንገት ድንገት ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲገኝመው ምን አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚነሳ ይታወቃል። ይህንን ለመገንዘብ ሚያዚያ 10 ቀን 1992፣ የ1997 ምርጫን፣ በ1986 የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲውን የተማሪዎች ተቃውሞ ማስታወሱ ብቻ ይበቃል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማዕበል በውስጡዋ ተሸክማ የምትጓዝ አገር ሆናለች፤ ለምሳሌ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጠንካራ ደረጃ በደረሰበት በዚህ ጊዜ፣ የማህበረሰቡ ኑሮ የሚያማርር በሆነበት በአሁኑ ወቅት፣ የተማረ ሰው ዝቅ ብሎ ድንጋይ በሚፈልጥበት ሁኔታ፣ የሰው መብት፣ አፈናው፣ ስደቱ፣ እንግልቱ፣ በዘር ሐረግ ምክንያት መፈናቀሉ፣ በታሪካችን በከፍተኛ የውርደት ልክ ላይ በደረስንበት ዘመን ላይ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፉን ለመፍቀድ አስቦ ነው ብሎ የሚያስብ መላምት በራሱ ስንኩል ትምስለኛለች፣ ከስንኩልነቷም ይልቅ ወያኔን ሁሉ በሁሉ የሆነ ገዢ ነው ብሎ የሚያምንን የፖለቲከኛ ማንንትም ታሳያለች።

የመድረክ ታላላቅ አዛውንቶች ለሰማያዊዎቹ ክብረ ከመስጠት ይልቅ ይህች አሳብ የወያኔ ናት በማለት ላለፉት 20 ዓመታት የነበራቸውን የትግል መስመር በግልጽ ለእኛም ያመላከተች ነች። እኔ እንደገባኝ ከሆነ እነርሱ በነበራቸው ሃያ ዓመታት እና ከዚያም በላይ ባፈጀው የትግል እንቅስቃሴ የሚሰሩትን ሁሉ የሰሩት ከወያኔ አንጻር ብቻ እንጂ እነርሱ ከቆሙለት የትግል መስመር እና ዓላማ አንጻር አለመሆኑን ያስገነዝበናል። የሰማያዊዎቹን ሰላማዊ ሰልፍ ለመረዳት አምልኮተ-ወያኔን እና ፍርሃትን ከልብ መሻር ያሻል። ይህ ሰልፍ የወያኔ አሳብ ናት ካሉ…ቀድሞውኑ ብርሃኑን ነጋን በእንዲህ ከጠረጠሩ እኛስ እነርሱን የማንጠረጥርበት ምክንያት ካለ ይህንን ጽሑፊን የሚያነብ ሰው ይንገረኝ። ይህንን እና ያንን ያደረገው ወያኔ ነው እያሉ ሲያወሩ ስመለከት እንደውም እኔ ከይቅርታ ጋር እነርሱን ጠረጠርኳው፣ ተመኮሮአቸውን እያወሩንስ ቢሆን? አልኩኛ፤ ደግሞስ የገብርኤል መገበሪያን የበላ ምን ያደረርገዋል እንዲሉስ ቢሆን?። ስለ ጥርጣሬዮ እዚህ ጋር ፍሬን ልያዝ.. ስለመድረክን መኳንንቶች ልጻፍ።

እኔ እንደታዘብኳቸው የመድረኮች መኳንንቶች ለሚያደርጉት የትግል እንቅስቃሴ ሁላ የወያኔን ይውንታ የሚጠባበቁ፣ ወያኔ የከፈተውን የፖለቲካ አውድ ብቻ ለመከተል ከራሳቸው ጋር ተማምለው የቆረጡ ሰዎች የተሰባሰቡበት ስብስብ ይመስለኛል። ወያኔ የከፈተላቸውን ቦይ ብቻ ተከትለው የሚፈሱ፣ የሰላማዊውን የትግል መስመር እምነት የሚያራምዱ ስብስቦች ናቸው። ሰማያዊውም ፓርቲ ሰላማዊ ትግልን የሚያቀነቅን ፓርቲ ነው። ልዮነታቸው የሚጀምረው መድረኮች መርሃ ግብር የሌላቸው ታጋዮች ሲመስሉ ሰማያዊዎቹ ግን እንቅስቀሴአቸውን በመርሃ ግብር ሸንሽነው እና ቀምረው የሚንቀሳቀሱ …መርሃ ግብራቸውን ለመፈፀመም ምቹ ነገሮችን እና አስገዳጅ ሁኔታዎችን የሚጠቀሙ የወያኔን መሰሪነት የተረዱ ይመስላሉ። በእርግጥ መድረኮችም ይህንኑ የወያኔ ባህሪይ የተረዱ ስለመሆናቸው በየመግለጫቸው ይሰማል፣ ልዮነቱ መድረክ ወያኔን ሁልጊዜ የሚያሸንፍ ጉልበተኛ በማደረግ ትግላቸውን ሲጀምሩ ሰማያዊዎቹ ግን ወያኔን ለማሸነፍ የወያኔን ደካማ ማንነት በመረዳት የጀመሩም ይመስላል። ሌላው እና ትልቁ ልዮነት መድረኮች ሕዝብ ተኮር ያልሆነ እና ሕዝብን ያላሳተፈ የባላባት መደቦች ሲሆኑ ሰማያዊዎቹ ግን ገና ከመነሻቸው ሕዝብ ተኮር አደረጃጀትን የተከተሉ፣ የሕዝብ ተሳትፎ ሃያልነት የተረዱ… ለዚህም አደረጃጀት የራሳቸውን አሰላለፍ ምቹ ያደረጉ ናቸው…መድረኮች ኑ እና አባል ሁኑን በማለት ጥሪ ሲያቀርቡ ሰማያዊዎቹ ግን ወደ ሕዝቡ በመውረድ እና በመስረጽ የሕዝቡን የልብ ትርታ በመረዳት የሚንቀሳቀሱ ናቸው።

ጽሑፌንም ሳጠቃልል…..ሰማያዊዎቹን በማወደስ ብቻ አልጠቀለልውም፤ ወያኔ የሚቃወመውን ሁሉ ወደ እስር ቤት ማጋዝ ልማዱ ነው። ስለዚህ ለወያኔ ምሱን እንስጠው ወያኔን መቃወም የሚፈልግ ሁላ ለመታሰርም ዝግጁ ይሁን። ዛሬ እነይልቃልን ድንገት ከየቤታቸው ለቅሞ ቢያስራቸው…. ነገ ብዙ ይልቃሎች…. ብዙ አቡበከሮች…… ብዙ እስክንድሮች …አንደ አሸን እና እንደ እንጉዳይ ወደ ትግሉ መድረክ ብቅ ልንል ይገባል።. ምናልባት ወደ እንደዚህ አለው ትግል ለመግባት ፍርሃታችን ይዞን ይሆናል….ላለመታሰር ብለንም ፈርተን ይሆናል….. አልገባን ይሆን ይሆናል ወይንም እውነታውን እየካድን ሊሆን ይችል ይሆናል እንጂ አሁንም የወያኔ እስረኞች ነን። ምናልባት ከእነ አቡበክር እና ከእነ እስክንድር ከእነ ርዕዮት ዓለሙ የሚለየን እኛ መዝገብ የማያውቀን እስረኞች እና ቤታችን የምናድር ግዞተኛ መሆናችን ብቻ ነው። እኛ ሁላችን ከፍርሃት በታች ተዘግተን ፣ ለፍርሃት ባሮች ሆንን ድፍን 21 ዓመታት አናታችን ላይ ዳንኪራቸውን እረገጡብን፣ በብዙ አዋረዱን ላላፉት 21 ዓመታት የፍርሃት ፣ የወያኔ የማስፈራሪያ ሰለባዎች ሆንን። አሁን ግን ሁላችን ከተሸሸግንበት ፣ የሞት ሽታ ከሸተተን መንደር ወጥተናል እና ወያኔ…በተራው ሊፈራ እና ሊደነግጥ ጀምሮዋል።

ወዳጆቼ በአዲስ አበባ ላይ የምንኖር ብቻ ቁጥራችን ከ2 ሚሊዮን በላይ የምንዘል በወጣት የዕድሜ ክልል የምንገኘ ሁሉ መዝገብ የሚያውቀው እስረኛ ለመሆን ብንፈቅድ እንኳን ወያኔ እኛን ሁላችንን ለማሰር አቅም አይኖረውም። በ1997 ዓ.ም በነበረው ታላቅ ትግል እንኳን ማሰር የቻሉት 50 ሺህ ሰው እንኳን አይሞላም፤ በፍርሃት በየቤታችን ተቀፍድደን ከምንታሰር በዘመናችን ትውልድ የሚዘከረው ታላቁ የኢትዮጵያዊያንን ትግል እንቀላቀል። ይህ ታላቅ ዘመቻ በእርግጥ ታላቁን የኢትዮጵያን ሕዳሴ ለመጀመር ፈር ቀዳጅ ይሆናል። አሁን ከፍርሃታችን ወጥተን ትልቅን እርምጃ ተራምደናል፤ ከዚህ በሃላ ተልሰን ወደፍርሃት ቀንበር መግባት አይገባንም። ወያኔ ምንም ሊያደርገን አይችልም፤ ምናልባት ሊያደርጉን ከቻሉ የሚችሉት እኛን ማሰር ብቻ ነው፤ ይህ ደግሞ በራሱ ትልቅ ድል ነው። 2 ሚሊዮን መዝገብ የነካውን እስረኛ መመገብ፣ ማስተዳደር፣ መጠበቅ በራሱ ወያኔን ያናጋዋል፣ ያፈርሰዋል። ስለዚህ ሰልፍ መውጣጣችንም ሆነ መታሰራችን ወያኔን ከተቀመጠበት የስልጣን ኮርቻ ሊያወርደው የሚችል ትልቅ ውሳኔ ነውና ወደፊት እንበል ይለይለት።

ድል ለመላው ሕዝብ


Anti-Government Protests in Ethiopia Supported by Egypt

$
0
0
Thousands of Ethiopian opposition activists demonstrate in Addis Ababa on June 2. The protests were the largest in the country since post-election violence in 2005, in which 200 people were killed and hundreds more arrested.
(STRINGER/AFP/Getty Images)
As the Arab Spring revealed, Mohamed Morsi and the Muslim Brotherhood are masters at co-opting democratic
revolutions for Islamist causes. Will Ethiopia be the next nation to fall to this strategy?
  Thousands of Ethiopian opposition activists demonstrate in Addis Ababa on June 2. The protests were the largest in the country since post-election violence in 2005, in which 200 people were killed and hundreds more arrested.(STRINGER/AFP/Getty Images)

A startling new revelation has emerged about the recent anti-government protest in Ethiopia. In light of increasing tensions between Egypt and Ethiopia over Nile River rights, the Muslim Brotherhood government in Egypt has decided to cooperate with the Muslim Brotherhood government in Sudan to support Ethiopian radical Islamist leaders sitting in exile in Khartoum. These Egyptian-supported, Islamist leaders were largely responsible for prompting the 10,000-strong, anti-government demonstrations that took place in Addis Ababa during the first days of June.

This anti-government demonstration may have been officially organized by the secular Semayawi (Blue) Party and it may have attracted the support of many Christian youth, but the majority of the 10,000 demonstrators were Muslims calling for increased religious freedom and the release of political prisoners.

As the Egyptian “Arab Spring” revealed, Mohamed Morsi and the Muslim Brotherhood are masters at co-opting democratic revolutions for Islamist causes. According to analyst George Copley of the International Strategic Studies Association, the Egyptian military knows that Egypt is not in a position—even allied with neighboring Sudan—to take direct military action against Ethiopia at this time. For this reason, the Morsi government has initiated a return to covert war against Ethiopia via Islamist proxies.

Not coincidentally, a senior Egyptian ministry of defense delegation arrived in Somalia on June 4 to officially begin discussions on how Egypt can best help rebuild and train the Somali Armed Forces, with the intent to support a Somali move to assume control of the Republic of Somaliland to the country’s north. By ensuring that the Republic of Somaliland remains under the control of southern Somalia, Egypt also ensures that landlocked Ethiopia remains cut off from the economic opportunities presented by a Red Sea coastline.

Egypt is advancing on several fronts to control the Nile by isolating Ethiopia: through Somalia; through Sudan; through Eritrea; and through sponsorship of Ethiopian Islamist and other opposition movements (e.g. the Oromo Liberation Front).

As editor in chief Gerald Flurry said in a Key of David program last September, based on Daniel 11:42-43, Egypt is prophesied to help swing both Libya and Ethiopia into the Iranian-led, radical Islamic camp. Once these national reorientations are complete, Iran will then have the power to close down seaborne trade through the Red Sea and kick off a process that will lead to the last world war.

While other scriptures, such as Psalm 68, foretell of a soon-coming time of peace and prosperity for Ethiopia (and the rest of the planet), the sad truth is that humanity is going to have to go through a time of intense suffering before it is willing to accept God’s rule on Earth. Be sure to read Libya and Ethiopia in Prophecy to see for yourself exactly how events will unfold in north Africa, and how they will ultimately lead to the establishment of peace throughout the world! ▪


‹መድረክ›|ያለፈው ሰልፍ ድራማ ሊሆን ይችላል – እኛም አቅደናል

$
0
0

 

Beyene Petros

 

ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፉ “የኢህአዴግ ድራማ” ሊሆን ይችላል አሉ  ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ፣ ከ97 ምርጫ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መሆኑን የሚናገሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ላለፉት ስምንት ዓመታት እንኳን ሰልፍ ስብሰባም ማካሄድ እንዳልቻሉ በመግለጽ….፤ የእሁዱም ሰልፍ “የኢህአዴግ ድራማ ሊሆን ይችላል” በማለት እንደሚጠራጠሩ ገለፁ ፡፡ የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፣ ህገመንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚፈፀሙ ሰላማዊ ሰልፎች እንደማይከለከሉና ድሮም የነበረ አሰራር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የመድረክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፤ እስከአሁን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ይቅርና አዳራሽ ለመከራየት እንኳን ሆቴሎች የመስተዳድሩን ፈቃድ አምጡ እያሉ ሲያስቸግሯቸው እንደነበር ገልፀው፤ የሰሞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍም ምናልባትም ከአፍሪካ ህብረት ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ያደረገው ጨዋታ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

“ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እኛም ዕቅድ ይዘን እየተነጋገርን ነው” የሚሉት ፕ/ር በየነ፤ ኢቴቪ ሰልፉን መዘገቡን ብቻ በማየት መሻሻሉን ለማወቅ እንደማይቻል ገልፀዋል፡፡ “ኢቴቪም ቢሆን ድራማውን እየሰራ ይሆናል” በማለት ዘገባውን የሰራው አንዳንድ የሚያስወነጅሉ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ነው ብለዋል፡፡ “አላማቸውና መሻሻላቸው የሚታወቀው ወደፊት መቀጠሉ ሲታይ ነው” ብለዋል – ፕሮፌሰሩ፡፡ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው፤ ሰላማዊ ሰልፉ መካሄዱ ችግሮችን ካልፈታ ልክ በአረብ አገራት ላይ እንደታየው አይነት ችግሮች ሊከሰት እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ “የህዝብ ችግር እስካልተፈታ ድረስ ህዝብ አንድ ቀን በቃኝ ሊል ይችላል – መብቱ ካልተከበረለትና የሚበላው ካጣ ችሎ የሚቀመጥበት መንገድ የለም፡፡ ይሄ ህዝብ መብቱ እንዲከበርለት፣ ነፃነት እንዲያገኝ፣ በልቶ እንዲያድር ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ ይህንን ችግር መፍታት ካልቻለ፣ ህዝቡ አሁንም “መሪውን ይበላል” የሚባለውን ሊተገብር ይችላል፡፡” የሚሉት ዶ/ር መራራ፤ እኛን አዳራሽ እየከለከሉ ለሌላው ሰላማዊ ሰልፍ የሚፈቅዱት የህዝብ ሙቀት ለመፍጠር በማሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

 

“ምናልባትም የኢህአዴግ አዲስ አሰራር ከሆነ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ በነካ እጁ ለመድረክና ለሌሎች ፓርቲዎችም እንዲፈቅድ ጥያቄያችን ነው” ብለዋል፡፡ አቶ ሬድዋን በበኩላቸው፤ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ተከለከልን ማለታቸውን አይቀበሉትም፡፡ “በራሳቸው ምክንያት ሳይካሄዱ የቀሩ ካልሆኑ በስተቀር፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በፊትም ነበር፤ አሁንም ተካሂዷል፡፡ ሃሳብን በነፃነት በአደባባይ ወጥቶ የመግለጽ መብት አዲስ አሠራር ነው ብለን አናስብም” ብለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዳራሽ ተከለከልን፣ ሰልፍ አልተፈቀደልንም የሚል ቅሬታ ያነሳሉ የሚሉት አቶ ሬድዋን፤ የአዳራሽ ጉዳይ የባለ አዳራሾች እንጂ የመንግስት አለመሆኑን ጠቅሰው፣ “መንግስት አዳራሽ አያከራይም፡፡ ለዚህኛው ፓርቲ አከራይ፣ ለዚህኛው አታከራይ የሚል ነገርም የለም” ይላሉ፡፡

 

በአደባባይ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን በተመለከተም፤ “ነፃና ክፍት በሆነ ሰዓትና ቦታ፣ ህጉን ጠብቀውና ፎርማሊቲውን አሟልተው እስካካሄዱ ድረስ የሚከለከሉበት ሁኔታ የለም፡፡ ከዚህ በኋላም አይኖርም” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በአዘጋገብ ላይ ያሳየውን ለውጥ በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ሬድዋን፤ “ከዚህ በፊትም የማውቀው ኢቴቪ፤ ሁሉንም ወገን ለማናገር ጥረት ሲያደርግ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሲያጋጥም የነበረው ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ኢቴቪ እንዳይመጣና እንዳይዘግብብን፣ ከዘገበም ሙሉውን እንዳይቀርጽብን የሚል አቋም እንደነበራቸው ነው፡፡ ተቋሙ የሚሰጣቸውን እድል ያለመጠቀም፣ አትግቡብን የሚል የራሳቸው የሆነ ችግር እንዳለባቸው ነው የማውቀው፡፡ የሆኖ ሆኖ ፕሮግራሙን የሚያየው ተመልካች የራሱን ፍርድ መስጠት ይችላል” በማለትም መልሰዋል፡፡

 

“መድረክ” ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ሊጠራ ነው

 

ዋና ኦዲተርና የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሰሞኑን ለፓርላማ ያቀረቡትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በነገው ዕለት በመድረክ፣ በመኢአድ፣ በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮዎች የፓርቲዎቹ አመራሮች ውይይት እንደሚያደርጉና መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠራ ተገለፀ፡፡

 

የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የፓርቲዎቹ አመራሮች በነገው ውይይት የሚደርሱበትን የጋራ መግባባት በመያዝ፣ መድረክ ለሰኔ 17 ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራትና በአዲስ አበባ ከተማ በመዘዋወር የመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ ሙስና የስርአቱ መገለጫ በሆነበት፣ የህዝብ ሃብት እየባከነና የዲሞክራሲ መብቶች እየተጣሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ መንግስት እምቢተኝነቱን ትቶ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እንዲያደርግ ጥሪ እንደሚተላለፍለት ገልፀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ የሚቀርብለትን የውይይት ሃሳብ ተቀብሎ ወደ ውይይት ካልመጣ፣ 33ቱ ፖርቲዎች ሰላማዊ ትግሉን ተጠቅመው አገራዊ ንቅናቄ በማድረግ፣ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውንም አስረድተዋል፡፡


Viewing all 931 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>