Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 940 articles
Browse latest View live

ሁለት የአረና ለትግራይ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ከፓርቲው ለቀቁ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ  ለረዥም ጊዜ መድረክ ወደ ውህደት እንዲመጣ ሲለፉና ሲታገሉ የነበሩት ሁለት ለአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉአላዊነት ሥራ አስፈጻሚ አባላት ከፓርቲው ራሳቸውን ማግለላቸውን ለድርጅቱ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ አስታወቁ…. አስራት አብርሃም የተባሉ የዓረና የስራ አስፈፃሚ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ እንዲሁም፤ ጉዕሽ ገብረፃዲቅ የዓረና የስራ አስፈፃሚ አባልና የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት እነዚህ ሁለት የድርጅቱ አመራር አባላት ከድርጅቱ ለመልቀቅ ለምን እንደወሰኑ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ላይ “እኛ ፓርቲውን ለመመስረት ከታሰበበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች እስካሁን እየሰራን መቆየታችን የሚታወቅ ነው።

asreat-abrham

አቶ ግዑሽና አቶ አስራት

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመድረክ ውስጥ እየተከሰተ ባለው ፖለቲካዊ ድባብና በሌሎች ከዚህ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው ሁኔታውን ገምግሞ፣ “መድረክ ከዚህ በኋላ ወደ ምንፈልገው ግብ ያደርሰናል ወይስ አያደርሰንም? በእኛ በእኩል መድረክ ወደ እሚፈለገው ግብ እንዲደርስ ምን ዓይነት እስትራቴጂና የትግል ስልት እንከተል?” የሚሉ ጉዳዮች በጥልቀት ለማየትና የእስትራቴጂ ማስተካኪያ ለማድረግ ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑን በመገንዘብ፤ ከዚህም በተጨማሪ በዓረና ውስጥ እየተስተዋሉ ባሉት እንግዳ ሁኔታዎች ምክንያት ፓርቲው እንዲከፋፈልና እንዲዳከም የሚያደርጉ መሆናቸውን በመገንዘብ፤ ይህን ሁኔታ ለማረም ደግሞ በሌሎች የስራ አስፈፃሚ አባላት ዘንድ ዳተኝነት መኖሩ ግልፅ እየሆነ በመምጣቱ፤ የዚህ አካል ላለመሆንና ፓርቲውን ደግሞ የበለጠ እንዳይከፋፈል በማሰብ፣ ይህ ደብዳቤ ከተፃፈበት ዕለት ጀምሮ ፓርቲውን ለመልቀቅ የወሰንን መሆናችንን በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን።” ብለዋል።
“ለዓረና/መድረክ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ ስላሳለፍነው ጥሩ የአብሮነት ጊዜ ማመስገን እንፈልጋለን። ብዙ የትግል ልምድ ካለው አመራር ጋር አብሮ መስራት በራሱ እንደ አንድ ትልቅ እድል ነው ምናየው። ለዓላማ የመኖር ፅናት፣ ትዕግስትና ፖለቲካዊ ተሞክሮ አግኝተንበታል። ከዚህ በተጨማሪም ስለአገራችን ፖለቲካ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለመረዳት እድል ፈጥሮልናል። በእዚያ ባሳለፍነው አስቸጋሪ የፖለቲካ ጉዞ ውስጥ ስብዕናህን የሚፈታተኑ፣ ትግል የምታደርግበትን ምክንያት እስኪጠፋህ ድረስ የሚያደርሱና ፀጉር የሚያቆሙ ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የነበሩበት ቢሆንም፤ የዚያው ያህል ደግሞ ብዙ የተማርንበት፣ አቅምና ክህሎት ያገኘንበት፣ ከአገር ውስጥም ከውጭም ብዙ ለአገርና ለወገን ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎች ለመተዋወቅ ዕድል የፈጠረልን በመሆኑ ሁላችሁም እናመሰግናለን።” ያሉት አቶ አስራት አብርሃም እና ጉ ዕሽ ገብረጻዲቅ “ከሁሉም በላይ ደግሞ ዓረና የፖለቲካ ጥርሳችን የነቀልንበት፣ ስለሀገር፣ ስለሰው ልጅ፣ ስለስልጣን ምንነት፣ ስለሁሉም ነገር በጥልቀት እንድናውቅ ዕድል የሰጠን ፓርቲ በመሆኑ በህይወታችን ሁሉ ስናስታውሰው የሚኖር ነው። ባለፉት ስድስት ዓመታት የተማርነው ነገር ብዙ ነው፤ አገራችን የብዙ ችግሮች ባለቤት መሆኗም ተገንዝበናል። ይህ ሁሉ ችግር ለማቃለልም አሁንም ቢሆን እልህ አስጨራሽ ትግል ማድረግ ግድ የሚል መሆኑን እንረዳለን፤ ከዚሁ ትግል ደግሞ እኛ ወደኋላ እንል ዘንድ ስብዕናችንና ተፈጥሯዊ ባህርያችን የሚፈቅድልን አይደለም።” ብለዋል።
“ዛሬ ከፓርቲው በዚህ ሁኔታ ብንለይም ፓርቲው እስከ አሁን ይዞት የመጣውን ለመርህ የመገዛት፣ በጋራ አመራር የማመንና ተግባብቶ የመስራት ባህሉ መቀጠልና መጠናከር አለበት እንላለን። ውስንነት ቢኖረውም ውስጣዊ ልዩነቶችን አቻችሎ የሚጓዝበት፣ ችግሮች ሲከሰቱ ደግሞ በሰከነ ሁኔታ የሚፈታበት መንገድ ለሌሎችም ትምህርት ሊሆን የሚችል ነው። ይህ ልምድም መጠበቅ አለበት። በአንፃሩ ደግሞ ጎጂ የሆኑ ዝንባሌዎች ማለትም ወግ አጥባቂነትን፣ ቡድናዊነትን፣ ግላዊ ጥቅመኝነትንና ስልጣን ወዳድነትን ሥር እንዳይሰዱ ነቅቶ መጠበቅና መታገል የሚገባ ነገር ነው።” ሲሉ በደብዳቤያቸው ላይ ያተቱት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚዎች “በተለይ ደግሞ መድረክ አሁን ካለበት የተሻለ አደረጃጀትና አሰራር እንዲኖረው፣ በአባል ፓርቲዎች መሀከል ያሉትን ጥቃቅን ልዩነቶች በማቀራረብና በማመቻመች የተሻለ መተማመንና አብሮ መስራት የሚቻልበት ብሎም ወደ ውህደት የሚመጣበትን መንገድ እንዲፈጠር ጠንክሮ መስራቱ ለሁሉም የሚበጅ ነው የሚሆነው። ዓረና በዚህም በእኩል ከሸምጋይነት ሚናው ወጥቶ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ የሚጠበቅበት ነው። ጠብ እና አለመተማመን በመርህ፣ ብሎም ተቀራርቦ በመስራት ይፈታሉ እንጂ የመርህ ችግር በሽምግልና የሚፈታ አይደለም።” ሲሉ አስረድተዋል።
“መድረክ የአመራር ዳይናሚዝም ለመፍጠር የሚያስችል አሰራር መከተል፣ ብቃት ያላቸው አዳዲስ አመራሮች ማብቃና ወደፊት ማምጣት ይጠበቅበታል። ነባርና ልምድ ያለው አመራር መኖር ለአንድ ፓርቲ እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም የተለየ እንቅስቃሴ ማድረግ ግድ ለሚለው የሀገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚመጥን ፖለቲካዊ አመራር መስጠት ባልተቻለበት ሰዓት ግን “የማርያም መንገድ አለኝ” ለሚል አዲስ አመራር ዕድል መስጠት ተገቢ ይሆናል። ደግሞም አመራርነት በብቃትና በአባላቱ ዘንድ በሚኖረው ቅቡልነት ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል እንላለን።” በሚል የተነተኑት እነዚህ ሁለት አመራር አባላት “ውድ የዓረና/መድረክ አባላትና ደጋፊዎች፣ እኛ ዜጋ በዜግነቱ የሚከበርባት፣ ፍትሃዊትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እስክትፈጠር ድረስ ፖለቲካዊ ትግሉን የምናቆም አይደለንም። ከዚህ በኋላም ቢሆን በሀሳብና በተግባር በአጠቃላዩ የሀገራችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ መኖራችን የሚቀጥል ነው የሚሆነው። እኛ የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ተስማምቶና ተግባብቶ ለመኖር ያለውን መልካም ፍላጎት ከማንፀባረቅና ከማሳየት ውጪ ሌላ ዓላማ የለንም። ከአሁን በኋላም ቢሆን ይህን ጉዳይ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ከመግለፅና ከማሳየት ወደኋላ የምንል አይደለንም። ከሁሉም በላይ ደግሞ በአገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ፣ ፖለቲካዊ እኩልነትና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነቱ፣ መብቱና ክብሩ እኩል ተጠብቆለት፣ በአገሪቱ ውስጥ እንደ ዜጋ በሙሉ ነፃነት የመንቀሳቀስ እና ሰርቶ የመኖር መብቱ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር በምንችለው አቅም ሁሉ ከመታገል ወደኋላ አንልም።” ሲሉ የወደፊቱን የትግል አቅጣጫቸውን አስምረውበታል።
“በአንድ መንገድ ይሁን በሌላ፣ ለሁላችንም የምትስማማ፣ የተሻለች አገር ለመፍጠር መታገላችን እስከቀጠልን ድረስ ተለያየን አንልም። የእኛ እና የሌሎች በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደረጉ ትግሎች ተደማምሮ ነው ውጤት ሊመጣ የሚችለው።” የሚሉት አቶ አስራት እና አቶ ጉዕሽ “እንግዲህ በዚሁ ስንሰናበት ሀዘናችን በጣም ጥልቅ ነው። ስትለያይ ሀዘን መኖሩ፣ ቅር ማለቱ ያለና የማይቀር ነገር ቢሆንም ሀዘናችን እጅግ በጣም ጥልቅ እንዲሆን የሚያደርገው በዚህ ሁኔታ መለያየታችን ነው። ብፆት ሰላም ኹኑ! ድል ለዴሞክራሲያውያን ታጋዮች! ድል አዲሱ ኢትዮጵያዊ ትውልድ!” በማለት ለድርጅታቸው የጻፉትን ግልጽ ደብዳቤ ቋጭተዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ አቶ አስራት አብርሃም እና ጉዕሽ ገብረፃዲቅ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ይቀላቀላሉ ተብሎ በሰፊው እየተወራ ነው።



ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

$
0
0

969694_588045714550673_1440883208_n

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ የግብፅ አንዳንድ ባለስልጣናት ፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የተለያዩ ማህበራት ሀላፊዎች ሲያካሂዱ የከረሙትን አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ በተመከለተ ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል ….

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያላትን ገንቢ አቋም ገልፃ ነገር ግን በግብፅ በኩል የአገሪቱን አቋም በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደርን ከአንዴም ሁለት ጊዜ ጠርታ መጠየቋንና ለግብፅ መንግስት ጥያቄ ማቅረቧን ያስታውሳል ።

ኢትዮጵያ ከምንም በላይ ለትብብር ፣ ለወዳጅነትና ለጋራ ጥቅም ያላትንም ፅኑ እምነት በወቅቱ ግልፅ አድርጋለች ያለው መግለጫው ፥ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ብሄራዊ የናይል ጉባኤ በተሰኘው ስብሰባ ላይ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሚኒስትሮችና ሌሎችም በተገኙበት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ አፍራሽ መልዕክቶች ሲተላለፉ መቆየታቸውን አንስቷል ።

የህዳሴ ግድብ በግብፅ ላይ አደጋ በመደቀኑ በኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ መንገዶች ተፅእኖ የማሳረፍና የግድቡን ግንባታ እንድታቆም የማድረግ እንቅስቃሴ ስለ ማድረግ የሚገልፁ ፣ በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ፍላጎትና አድራጎት ውጪ እንዲሁም የህዳሴ ግድቡን እንዲያጠና ግብፅ ጭምር ያለችበት የዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት ጭምር የሚያጣጥሉ ፀብ ጫሪ አስተያየቶች በመድረኩ ሲስተናገዱ መስተዋላቸውን ነው መግለጫው የጠቆመው ።

በዚህ ረገድ በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው ገልጿል ።

በህዳሴው ግድብ ሽፋን የውስጥ ችግርን ለማቃለል የሚደረገው ጥረት የግብፅን ዘላቂ ጥቅም አይጠብቅምም ብሏል ።

ጦርነትና ሌሎች አፍራሽ ስልቶችን ስለመጠቀም የሚቀርቡት ሀሳቦች ያረጁና ያፈጁ ፣ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከሙ ፣ ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች እንደሆኑና ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለሰኮንድም እንደማታቆም አረጋግጧል ።

የግብፅ ወገንም ከዚህ አፍራሽ ድርጊት ተቆጥቦ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠናከር የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል ።

በዚህ አጋጣሚ የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር የህዳሴ ግድቡን ግንባታ ጠቀሜታ አስመልክተው ያሰሙት ሀሳብ ገንቢ በመሆኑ አመስግኗል ፤ ሌሎች ከዚህ የሚቀስሙት ትምህርት እንዳለም አስታውቋል ።

በሌላ በኩል ይህ ግድብ ግብፅን ጭምር የሚጠቅም መሆኑን በማሳሰብ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር በወዳጅነትና በትብብር ለመስራት ፅኑ ፍላጎት እንዳላት ገልጿል ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)


መንግሥት ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

$
0
0

የግብፅ ፖለቲከኞች ከአፍራሽ ድርጊታቸው ይቆጠቡ ብሏል

872ede1c1b32b96ba8500685aaa6a3f8_Lየግብፅ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ባለፈው ሰኞ በተካሄደው ብሔራዊ የናይል ኮንፈረንስ ላይ ታላቁን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ በተንፀባረቀው አፍራሽ መልዕክት የተበሳጨው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ሕዝቡ ለአገሩ ዘብ እንዲቆም” ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡ የግብፅ ፖለቲከኞችም ከአፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

የግብፅ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትሮችና የፀጥታ ባለሥልጣናት በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ፣ “የህዳሴ ግድቡ በግብፅ ላይ አደጋ በመደቀኑ በኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ መንገዶች ተፅዕኖ በመፍጠር የግድቡን ሥራ ለማስቆም እንቅስቃሴ እናደርጋለን፤” በማለታቸው የኢትዮጵያ መንግሥት “አፍራሽ ድርጊት” በማለት አጣጥሎታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነበር የመንግሥትን አቋም ግልጽ ያደረጉት፡፡ “በህዳሴው ግድብ ሽፋን የውስጥ ችግርን ለማቃለል የሚደረገው ጥረት የግብፅን ዘላቂ ጥቅም አያስጠብቅም፤” ያሉት አምባሳደር ዲና፣ “ጦርነቶችና ሌሎች አፍራሽ ድርጊቶች ያረጁና ያፈጁ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከማቸው ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች ናቸው፤” በማለት የግብፅ ባለሥልጣናትን ድርጊት አጣጥለውታል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለአንዲት ሰከንድም ቢሆን እንደማታቆም አረጋግጠዋል፡፡ “የግብፅ ወገኖችም ከዚህ አፍራሽ ድርጊት እንዲቆጠቡ፤” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት የግብፅ መንግሥት እየያዘው ባለው መንገድ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠራ ነው ወይ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ መንግሥት አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸው፣ እንደነሱ በስሜት የመልስ መልስ መስጠቱ ግን አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም ብለዋል፡፡

እንደ እሳቸው አባባል፣ የግብፅ ተቃዋሚዎችና ባለሥልጣናት ያንፀባረቁት ሐሳብ የመንግሥት አቋም ስለመሆኑ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የግብፅ አምባሳደር ማብራርያ እንዲሰጡ የጠየቀ መሆኑን፣ ጉዳዩን አጀንዳ ለማድረግ እየተሯሯጡ ያሉት ጥቂት ፖለቲከኞች መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የውኃ ኤክስፐርቶች ቡድን የግድቡ ሪፖርት ይፋ ከተደረገ በኋላ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ግንዛቤ እንዲያገኙ መደረጉን፣ እስካሁን የዓረብ አገሮች አምባሳደሮች ቡድንና የቡድን ስምንት የበለፀጉ አገሮች በጉዳዩ ላይ ማብራርያ እንዲያገኙ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

የዓባይ ግድብን ግንባታ ለማካሄድ የተደረገው የወንዙን የፍሰት አቅጣጫ የመለወጥ ሥራ ምንም አዲስ ነገር እንደሌለውና የግንባታው አንድ አካል መሆኑን የተናገሩት አምባሳደር ዲና፣ የግብፅ ባለሥልጣናት የወቅቱ ድርጊት ግን የግብፅ ሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስ እንደሆነ አስምረውበታል፡፡

ያም ሆኖ ግን፣ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአገሩ ዘብ መቆም አለበት” ያሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ሰዎች ይህንን ግንዛቤ በመፍጠር ሚናቸውን እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትን ዝግጅት አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ አስፈላጊ የሚባሉት የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ካይሮ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሠልፍ እንቅስቃሴ ስለመደረጉ በተመለከተው “ከ30 እና 40 የሚያንሱ ናቸው፡፡ እንዲያውም የፀጥታ ኃይሎች ቁጥር ይበዛል፤” ሲሉ የሕዝቡ ጉዳይ አይደለም በማለት አጣጥለውታል፡፡ በሰሞኑ ጉዳይ ከግብፅ ጋር ትብብር ለማድረግ ያልፈለገችውን የሱዳን አቋምን ያደነቁት አምባሳደር ዲና፣ ግብፆችም ከእነሱ መማር አለባቸው ብለዋል፡፡


አልጃዚራ ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች ሲል ዘግቧል! ማናቸውንም እርምጃ ለመውሰድ በሩ ክፍት ነው .ግብጽ

$
0
0

አልጃዚራ ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች ሲል ዘግቧል። አቶ ባድር የፖለቲካ ቁማር እንደሆነ የገለጹትን ይህን የሞሃመድ ሞርሲን ንግግር አልጃዚራ ሁኔታው የተባባሰ የማስመሰል ጥረት ማድረጉ ይህ የዜና አውታር ገለልተኛ መሆኑን አጠያያቂ ያደርገዋል ሲሉ የገለጹት ቀድሚ ጋዜጠኛ የነበሩ አስተያየት ሰጪ ናቸው….

ይህን ያሉትም ሚዲያው በማጋነን ለአንድ አካል ያደላ ዜና ጽፏል በሚል ነው። በተለይም ”ሁሉም አማራጭ ክፍት ነው” ያሉት የሞርሲ ንግግር ኢትዮጵያ ለልማት ብቻ እንጂ ግብጽን ለመጉዳት አለመፈለጓ እየታወቀ በመሆኑ ይህንን ክግብጽ የናይል ጥገኝነት እና የጥፋት ፍራቻ ጋር ማያያዝ እንዲሁም የኢትዮጵያን አመለካከት ወደ ጎን መተው ፍትሃዊነት የለውም ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

በሁለቱ አገሮች መካከል መተነኳኮሱ እየባሰ የመጣው ዘንድሮ ግንቦት 20 ቀን የተከበረውን የገዥውን ፓርቲ በኣል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ፦” የአባይ ወንዝን የተፋሰስ አቅጣጫ አስቀየስኩ” ብላ ማወጇን ተከትሎ ነው።
ይህን ተከትሎ በተለይ የግብጽ መንግስት -ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ እስከ ወታደራዊ ጥቃት ድረስ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የመከሩበት ስብሰባ በይፋ ታየ፤
ይሁንና የግብጽ መንግስት-ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ስለታሰበው እርምጃ ሲመክሩበት የነበረው ስብሰባ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት መተላለፉ፤ግብጽ -ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መፈለጓን የሚያሳይ ተራ ጨዋታ ነው በሚል ብዙዎች ትኩረት ሳይሰጡት ቆይተዋል
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት የግብጹ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ፦ኢትዮጵያ በምትሠራው ግድብ ሳቢያ ወደ ግብጽ ከሚፈሰው የ አባይ ወንዝ የጠብታ ያህል ከቀነሰ አገራቸው ግብጽ ማናቸውንም እርምጃዎች ኢትዮጵያ ላይ ለመውሰድ ዝግጁነቱ እንዳላት አስታውቀዋል።
ከ ኢትዮጵያ ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ፤ ግድቡን ለማስቆም የሚያደርጉት ጥረት ካልተሳካ ግን ሁሉንም አማራጭ እርምጃዎች ለመውሰድ እንደሚገደዱ ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት።
ኢትዮጵያ – አቅጣጫውን የቀየረው የወንዙ ፍሰት ሀይል ካመነጨ በሁዋላ ተመልሶ በመደበኛው መስመር እንደሚፈስ እና በግብጽም ሆነ በሱዳን ላይ የሚፈጥረው ነገር እንደማይኖር ደጋግማ ብታሳውቅም፤ፕሬዚዳንት ሙርሲ ፈጽሞ የግብጽ የውሀ ደህንነት ሊነካ አይገባም! በማለት የ ኢትዮጵያን ምላሽ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።
“የ አገሪቱ ፕሬዚዳንት እንደመሆኔ መጠን ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰዱ በሩ ክፍት መሆኑን አሳውቃለሁ” ነው ያሉት -ፕሬዚዳንት ሙርሲ።
በማያያዝም፦”ግብጽ የዓባይ ስጦታ ከሆነች፤ዓባይ የግብጽ ስጦታ ነው”ብለዋል-በስሜት ውስጥ ሆነው በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር።
እንደ አንድ ታላቅ ህዝብ የግብፃውያን ህይወትና ኑሮ ከ ዓባይ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሙርሲ፤ ፍሰቱ በ አንዲት ጠብታ ከቀነሰ ያለን ቀሪ አማራጭ ደማችን ነው”ብለዋል።
የግብጽን ተደጋጋሚ ዛቻ ተከትሎ የ ትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፦<<ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም>>ብሏል።

ኢትዮጵያ ከምንም በላይ ለትብብር ፣ ለወዳጅነትና ለጋራ ጥቅም ያላትንም ፅኑ እምነት በወቅቱ ግልፅ አድርጋለች ያለው የሚኒስቴሩ መግለጫ ፥ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ብሄራዊ የናይል ጉባኤ በተሰኘው ስብሰባ ላይ የግብጽ ፕሬዚዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሚኒስትሮችና ሌሎችም በተገኙበት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ አፍራሽ መልዕክቶች ተላልፈዋል ብላል ።
በዚህ ረገድ በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል ።
ጦርነትና ሌሎች አፍራሽ ስልቶችን ስለመጠቀም የሚቀርቡት ሀሳቦች ያረጁና ያፈጁ ፣ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከሙ ፣ እና ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች እንደሆኑ የገለጸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለሰኮንድም አታቆምም ብላል።
ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተሉ ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ሁለቱ መንግስታት የቃላት ጦርነት ውስጥ የገቡት በውስጣዊ አስተዳደራቸው የተፈጠረባቸውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመጠምዘዝ እንደሆነ በስፋት አስተያየት ሢሰጡ ይደመጣሉ።


ነፃነት አምባገነንና ጨቋኝ መሪዎች

$
0
0

ሰዎችን እንደፈለጉ በመግዛት የነሱ አገልጋይ ለማድረግ በመጀመሪያ ሰዎች በራሳቸው ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያጡ በማድረግ፡ስሜታቸውን በመጉዳት፡መንፈሳቸውን በመግደል ይጀምራሉ፡፡ስሜታቸውን እና መንፈሳቸውን ከተቆጣጠሩ አካልን መግዛት እጅግ ቀላል ነውና…፡አካል የሚሰራው ሰሜት ሲኖር፡መንፈስ ሲጠነክር ነው፡፡ስሜቱና መንፈሱ የሞተ የሌሎች ባሪያ ነው፡፡ባሪያ ደግሞ በአሳዳሪዎቹ አንደ ዕቃ ነው የሚቆጠረው፡፡

እቃን ማሰተዳደር ደግሞ እጅገ ቀላል ነው፡፡አህጉራችን አፍሪካም የዚህ የሰነ-ልቦና ጦርነት ምርኮኛ ካደረጓት በኃላ ነበር እንደ አንባሻ ቆራርጠው ተፈጥሯዊ ሀብቷን የመዘበሩት፡ ህዝቦቿን በባሪያ ንግድ እንደ ሸቀጥ የተቸበቸቡት፡፡ህዝቦች ለራሳቸው ዋጋ መስጠት ሲያቆሙ፡አልችልም በሚል ወረርሽኝ ሲመቱ፡ተፈጥሯዊው ክብራቸውን አጥተው አንገት ሲደፋ ባሪያ ከመሆን ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡ለዛም ነው አምባገነኖች ፡ ውስጣቸው በክብር የተሞላ፡መንፈሳቸው ጠንካራ ፡”ለምን ?” “አይሆንም?”የሚል ጥያቄ የሚያነሱ፡ ለራሳቸው ክብር የሰጡ ግለሰቦች ሁሌም የለውጥ ሀይል እንደሆኑ በመገንዘብ፡እነዚህ ሰዎች እሰካሉ ያሰብነው አይሳካም በሚል መራራውን የጭካኔ በትራቸውን በማሳረፍ፡አካለቸውን በማንገላታት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንዲኖሩ ለማሰገደድ የሚጥሩት፡፡
ከአህጉራችን አፍሪካ በግፍ በባርነት ወደ አሜሪካ
የወሰዷቸውን ሰዎች ፈተና ይፈትኗቸው ነበር፡፡ፈተናው ከባሪያዎቹ ውስጥ ማነው ለራሱ ክብርና ዋጋ የሚሰጥ ? ማን ነው “ለምን ? አይሆንም ?” የሚለውን ለመለየት ነበር የሚሰጠው፡፡እናም “ለምን ? አይሆንም ?” ያለ፡ለራሱ ክብርና ዋጋ በመስጠት እኔ ባሪያ አይደለሁም ሲል የሞገተ ኤዲ የሚባል ገራፊ ጋር ይወስዱትና አስቃቂ ግርፊያ ይፈፀምበት ነበር፡፡ ታዲያ ይህንን ፈተና ተፈትኖ እምቢተኛ ነው ተብሎ የታመነበት ፍሬድሪክ ዳግላስ የተባለ “ባሪያ” ወደ ኤዲ ወስደውት ለሰድስት ወር ቀን በቀን እንዲገረፍ አደረጉ፡፡ፍሬድሪክ ግን ውሰጡ ጠንካራ፡ለራሱ ክብርና ትልቅ ግምት የሚሰጥ በመሆኑ ግራፋቱ መንፈሱን ሊገድለው፡ክብሩን ሊገፈው አልቻለም፡፡እንደውም አንድ ቀን የማይደረገውን አደረገ፡፡ ኤዲ ሊገርፈው ሲገባ ተነሰቶ ተናነቀው፡ታገለው፡በመጨረሻም ክፉኛ ጉዳት አደረሰበት፡፡በወቅቱ ባሪያ አሳደሪውን ለመጉዳት ካሰበ ቅጣቱ ስቅላት ነው ፡፡ግና ፍሪድሪክ “በክብር መኖር ካልቻልክ በክብር የምትሞትበት ጊዜ ደርሷል “ የሚለውን መርህ በሚገባ ስለተረዳ የሚደርስበት ጉዳት አላሳሰበውም፡፡አሳዳሪዎቹ በካቴና ጠፍረውት እየጎተቱ ሲወስዱት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ ዛሬ ክብሬንና ነጻነቴን አግኝቻለሁ፡፡ይህንን ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም እራሴ
አሳልፌ ካልሰጠሁ በስተቀር፡፡ዛሬ የክብርንና የነፃነት ፅዋ ተጎንጭቻለሁ፡እንዴት ይጣፍጣል መስላችሁ”አለ፡፡ ዛሬም ይኸው ሙስሊሞች ነፃነታቸውንና ክብራቸው አጥተው “ባሪያ “ሁነው አንዲያድሩ ጦርነቱ ታውጃል፡፡የሀገሬም አምባገነኖች ይህን አዋጅ ሰምተው በዜጎቻቸው ላይ ጦርነቱን ከፍተዋል፡፡”ለምን ?እንዴት ? አይሆንም ?”የሚሉትን ለራሳቸው ክብር የሰጡትን በየእስር ቤቱ አጉረው መንፈሳቸውን ሊገድሉ ክብራቸውን ሊገፋ፡አንገታቸው ሊያሰደፋ ከዛም ብዙሀኑን “ባሪያ” አድርገው ሊገዙ ከንቱ ልፋት እየለፉነው፡፡ውድ ኮሚቴዎቻችን በመንፈሳዊ ጥንካሬ የተሞሉ፡ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ለራሳቸው ቦታና ክብር የሰጡ በመሆናቸው፡እነሱ ላይ በመጀመሪያ ፕሮፓጋንዳ፡ከዛም ዘለፋና ማሰፈራሪያ፡ይህ አልሳካ ሲላቸውም ለእስር ዳርገው፡ እጅግ አሰቃቂ ድብደባና ስቃይ፡የክብር ማዋረድና ዘለፋ አሳረፉባቸው፡፡በኮሚቴዎቻችንም ሳያበቃ ስለ ነፃነታቸን እና ስብዐዊ ክብራችን እንሟገታለን ያሉት ላይ ይህን በትራቸው አሳርፈዋል፡፡አልተሳካላቸውም እንጂ ፡፡አዎ እነዚህ ጀግኖች መንፈሳዊውን ትግል በድል ተወጥተውታል፡፡ ታስረው ነፃ ናቸው፡፡ አሁንም ይህ ዘመቻ አላቆመም በየጁመዐው ስለ ነፃነታቸው የሚጮሁት ላይ በትሩ አያረፈ ነው፡፡ፕሮፓጋንዳው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ይቀጥላልም፡፡በዚህ ትግል አሸናፊ ለመሆን ለራሳችን የምሰጠውን ግምት ና ክብር ማሳደግ ተገቢ ነው፡፡ አካላችንን እንጂ መንፈሳችን ሊጎዱት አይችልም፡፡ ክብራችንና ነፃነታችን ያለው በእጃችን ነው፡፡ነፃ ነን ብለን ካሰብን ምንም “ባሪያ” አያደርገንም፡፡ግና “ለምን ? አንዴት ? አይሆንም ? ”ማለት ስናቆም ፡ዱላውና እስራቱ በዛብኝ አሁንስ “አልችልም በቃኝ “ሰንል ያኔ “ባሪያ” አንሆናል፡፡ያኔ መንፈሳችንን ያሸንፉታል፡ስሜታችን ይገዙታል ክብራችንን ይቆጣጠሩታል፡፡ከዛ በኃላ አካላችን
ነፃ ቢሆንም እኛ ግን ————–


ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ ይበቃታል

$
0
0

በፋኑኤል ክንፉ የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የሕዳሴውን ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ…፣ አንድ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ኤክስፐርት የግብፅ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ በቂ ነው ሲሉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።

ኤክስፐርቱ እንደገለፁት “ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግንባታ ግድብ በጦር መሣሪያ ለመምታት ካስቀመጠቻቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን በመጠቆም ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመታ ለኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በአፀፋው የአስዋን ግድብን እንዲመታ ሕጋዊ ፍቃድ መስጠቷን ልታውቅ ይገባል” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “ግብፅ በወታደራዊ እቅዷ ከገፋችበት በኢትዮጵያ በኩል አማራጭ መንገዶችን መመልከት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻ አድርገህ ላቲቲውዱን በ14.3000 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን በ36.6167 ዲግሪ ብትወስደው እንዲሁም አስዋን የሚገኝበት ላቲቲውድ 23.9706 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 32.8779 ዲግሪን አቀናጅተህ ብታሰላው በአየር ላይ ያለው ርቀት ከ1100 እስከ 1500 ኪሎ ሜትር የአየር ርቀት ነው ያለው። በዚህ ውጤት መነሻ የኢትዮጵያ መንግስት ከ1500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ የስከድ ሚሳኤሎችን መታጠቅ ብቻ በግብፅ አሰዋን ግድብ ላይ ተመጣጣኝ ሃይል ሊፈጥር ይችላል።”  ብለዋል።
ወታደራዊ የአየር ርቀቱን ለመለካት የተሄደበትን አሰራር ቢያብራሩት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “ይህ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። http://www.movable-type.co.uk/scripts/latlong-gridref.html በሚለው ድረ ገጽ ዲግሪውን በመጠቀም ማስላት ይቻላል። ቁም ነገሩ ግን ወታደራዊ አማራጭ ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ አያደርግም። ብቸኛው አማራጭ በዲፕሎማሲ ደረጃ ለመፍታት መሞከር ነው” ሲሉ ኤክስፐርቱ አሳስበዋል።

በአሁን ሰዓት በዓለማችን ላይ ከ1ሺ 500 ኪሎ ሜትር እስከ 15ሺ ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል የታጠቁ ሀገሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲአረቢያ እና አሜሪካ ይገኙበታል።


“ለሐገሬ ምን ሠራሁ እንጂ ሐገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል፡፡”

$
0
0
By Umer Faruq (Ethio Al-Habeshi) ቅድመ ማሳሰቢያ፡ ይህንን ፅሁፍ እስከመጨረሻው ሳያነቡ እባክዎን አስተያየት ለመስጠት አይቸኩሉ፡፡ ትናንት በገባሁት ቃል መሠረት ፅሁፌን እነሆ ብያለሁ፤ መልካም ንባብ፡-
ይላል ዕውቁ የነፃነት ታጋይ እና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብረሃም ሊንከን…. ይህን አባባል በጥልቅ የተረዱት አሜሪካውያን እንደተባለው ለሐገራቸው መስራትን አስቀደሙ፡፡ ሐገራቸውም እንደ ሐገር ጥቁር ነጭ እያለች የበደል ፅዋ ታፈራርቅባቸው የነበረውን ጎጂ ብሒሏን እርግፍ አድርጋ በመተው ልጆቿን አንዱን ካንዱ ሳትለይ አቀፈች፡፡ ጥቁር የበታች ነው፤ ይህ ጥቁሮች የማይማሩበት ት/ቤት ነው፤ እና የመሳሰሉ በርካታ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ ትተገብራቸው የነበሩትን እኩይ ተግባራት፡ ተይ አይበጅሽም ሲሏት ከመሪር ትግል በኋላም ቢሆን ለዕድገቷ በማሠብ እንደ “አንዳንዶቹ” ተሳስተሻል አትበሉኝ ብላ እልህ ውስጥ ሳትገባ ስህተቷን አረመች፡፡ ሐገር እና ህዝብ ተጋግዘውም ከነበሩበት የበታችነት አዘቅት ውስጥ ወጥተው በነፃነት እና ኃያልነት ማማ ላይ ሲፈናጠጡ “ያልነቃው” የዓለም ክፍል እርስ በርሱ እየተናከሰ አጀባቸው፡፡ እንደ አትሌት ኃይሌ በዓይናቸው በብረቱ እየተመለከቱ አሜሪካ በጣጥሳቸው ወደፊት ገሠገሠች፡፡ ይህ ነው የህዝብ ሉአላዊነት ውጤት፡፡ አንባገነንነትን የፊጥኝ ያሉቱ እነ ሶቪየት ህብረት፡ የተመኩበት ኃይል ከመፈረካከስ አላዳናቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የኛው ሶሻሊስት አንባገነን መንግስቱ ኃ/ማሪያም ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ጦር ቢያዘጋጅም ህዝብ እንጂ መሳሪያ ለጭንቅ ቀን አይሆንምና እያጨበጨበ ቀኑን ሲቆጥርለት የነበረው የገዛ ህዝቡ ምንነታቸውን ከማያውቃቸው ሽርጥ ለባሽ ጎፈሬ ታጋዩች ጋር ሆኖ ገረሠሠው፡፡ መንግስቱ ኃ/ማሪያም ላይ በዋነኛነት የህዝቡን ጥርስ ያስነከሰበት ምግባሩ ልማት ማጓደሉ ነበርን? ትምህርትን አለማስፋፋቱና መሐይምነትን አለማጥፋቱ ነበርን? በፍፁም!

ደርግን የተኩት ባለተራዎች በልማት ብቻ የህዝብ ልብ እንደሚገኝ በማሠብ ሌላ ነገር አትጠይቁን አሉ፡፡ ግንብ እና አስፋልት ላይ እኮ የሚንፈላሠሠው ስጋዬ ነው፡፡ ስጋዬ ውስጥ ደግሞ በነፃነት መኖርን ከምንም በላይ የሚሻ ህሊናና ሠብአዊ ማንነት አለኝ፡፡ የስጋዬ ደስታም ሆነ ሐዘን የሚገለፀው በዚያ መታፈንን በማይሻው ሠብአዊ ማንነቴ ውስጥ ነው፡፡ እንደውሻ አንገቴን አስረው መሮጥ ሲያምረኝ እያጠበቁ የምሮጠው እነርሱ ሲፈቅዱ እንጂ እኔ ሲያሻኝ እንዳልሆነ እያሳዩኝ በሚያምር አስፋልት ላይ ቢነዱኝ እና ጣፋጭ አጥንት ቢያስግጡኝ አንጀቴ ውስጥ ጠብ ሊል ይችላልን? ስለ ሠብዓዊ መብቴ መከበር ስጠይቅ “ግንብ እና አስፋልት ሠርተንልሃል” ብለው መመለሳቸው በራሱ ለኔ “ግንብ ውስጥ ከኖርክ ምን አነሰህ?” አይነት የንቀት ንቀት ነው፡፡ መናገር የፈለግኩትን ተናግሬ፤ ስጠይቅ ተሠምቼ፤ ስመርጥ ድምፄ ተከብሮ ቆሎ ቆርጥሜ፡ የሳር ቤት ውስጥ ያለፍርሃት እና ያለሠቀቀን መኖር ካሁን አሁን መጥተው በተቃዋሚነቴ / በሙስሊምነቴ አሠሩኝ፤ ገደሉኝ፤ ልጄን፡ ወንድሜን፡ እህቴን አልያም አባቴን ያለማንም ሃይ ባይ ጎትተው ወሠዱብኝ እያልኩ እየተሳቀቅኩ ቪላ ቤት ውስጥ ከመኖር (ያውም እድሉ ካለኝ) ሺህ ጊዜ ይበልጥብኛል፡፡ ኢህአዴግ ከደርግ እና ዓለም ካወቀቻቸው በርካታ አንባገነን መንግስታት ፍፃሜ ትምህርት ሊቀስም በፍፁም አልቻለም፡፡ ርዕሴን አልዘነጋሁም፤ በጥሞና ይከተሉኝ፡፡

በ “ዘመቻ ህዳሴ ግድብ” የመሳተፍ እና ያለመሳተፍ ጉዳይ የሐገር ጉዳይ ብቻ ነውን?

መግቢያዬ ላይ በጠቀስኩት ታሪካዊ ጥቅስ፡ አብረሃም ሊንከን “ሀገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል” ሲል አንተ ያቅምህን ለሐገርህ ስትታገል የልብህን ለማድረስ ሃገርህ እጇ ቢያጥር አትውቀሳት ለማለት እንጂ አንተ ደፋ ቀና ስትልላት “የአይንህ ቀለም አላማረኝም” ብላ ብታስርህ እና ብትገርፍህ አሜን ብለህ ተቀጥቀጥ ለማለት እንዳልሆነ የሚያግባባን ይመስለኛል፤ እርሱም በጥቁርነቱ ሲጨቆን ያንን አላደረገምና፡፡ በዚህ አግባብ በአሁኑ ሠዓት እኔ ለሐገሬ የማበረክተውን እና ሐገሬ ለሠራሁት ሥራ ተገቢውን ክፍያ ያልከፈለችኝ “እጅ አጥሯት” ነው ብዬ በአብረሃም ሊንከንኛ ባቀነቅንም፡ መብቴን ባልኩ የተቀጠቀጥኩበት እና የገርባ እና የአሳሳ ወንድም እህቶቼ እንደሌላው ኢትዩጲያዊ ወገናቸው የተገደሉበት ማናለብኝነት እና ትምክህት ለአብረሃም ሊንከን ቢደርስ ቢያንስ ለዛሬዋ ሐገሬ (መንግስቴ) ባለዕዳ እንደማያደርገኝ አምናለሁ፡፡ ወዴት እያመራሁ እንደሆነ የተገነዘባችሁ ይመስለኛል፡፡ ኦዎን! በአሁኑ ሠዓት ሐገሬ ኢትዩጲያ “ህዳሴዋን” እንዳታበስር ጠላት ተሠድሮባታል፡፡ ክፉውን ያርቀውና አካባቢው ጦርነት ጦርነት መሽተት ጀምሯል፡፡ በሀገሬ ጥቅም የመጣ ማንኛውም (ማንኛውም ይሰመርበት) ጠላት ያው ጠላት ነው፡፡

በዚህ አቋማችን ባንለያይም ይህን ጠላት ለመፋለም የኢህአዴጓ ሐገሬ “በክፉ ቀኔ” ሳትደርስልኝ በክፉ ቀኗ ብትጠራኝ የሚኖረኝ ምላሽ ምክኒያቴን ላላገናዘበ ማንኛውም አንባቢ ላይዋጥለት ይችላል፡፡ በርግጥም ሐገሬ እንደስከዛሬው በኢህአዴግ እየተመራች ከየትኛውም ጠላት ጋር ለፍልሚያ ብትጠራኝ አልሰማትም፡፡ ይህን የምለው ፖለቲካን ከሐገር መለየት ተስኖኝ አልያም ሐገሬን ኢትዩጲያን ከማንም ያነሠ አፍቅሬ እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም ጥሎብኝ ከልጅነቴ ጀምሮ የሐገሬ ነገር አይሆንልኝም፡፡ በኢትዩ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ዕድሜዬ ለአቅመ ጦርነት ባይደርስም ከተዋጉት ባልተናነሰ ትንፋሼ ቁርጥ እስኪል ሁለመናዬ አይንና ጆሮ ሆኖ የሐገሬን ድል በጉጉት የተጠባበቀው ማንነቴ አሁንም አለ፡፡ ኢትዩጲያዬ ላይ እንኳን ሠይፍ የመዘዘባትን ቀርቶ በሠላማዊው የእግር ኳስ ሜዳ የተገዳደራትን እንኳን በዙሪያዬ ኳሱን ከሚከታተለው ህዝብ በተለየ ብርድ እንደመታው ጥርሴ እየተንገጫገጨ ከውስጥ በሚንተገተግ የሐገር ፍቅር ስሜት ድሏን በጭንቀት እጠባበቅ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ከሐገሬ ውጪ እንደሌላው ለ አርሴና ማንቼ የማውሰው አይንም የኳስ ፍቅርም አልነበረኝም፡፡ ይህ የሐገር ፍቅር ከደም የተቀላቀለ የማንነት መገለጫ እንጂ ሲፈልጉ የሚገዙት ሲፈልጉ የሚሸጡት ሸቀጥ አይደለም፡፡ ዛሬም ወደፊትም ይኖራል፡፡ እንዲህ የሆንኩላት ሐገሬ ግን ሳትፈልግ መሪዋን በጨበጡ ሽፍቶች አገለለችኝ፡፡ እንኳን በአደባባይ፡ ሻሂ ቤት ቁጭ ብዬ ለምተነፍሳት ቃል ሁለት ጊዜ እንዳስብ አስገድዳ ያለጥፋቴ ስትፈልግ የምትገርፈኝ ስትፈልግ የምትዘርፈኝ ባሪያዋ አደረገችኝ፡፡ መብት የሚባል ነገር በፍፁም እንዳልጠይቅ ፤ አንገቴን ደፍቼ እንድገዛ ፈረደችብኝ፡፡ መንግስቴ የገዛ የሐይማኖት መሪዬን እራሴው ልምረጥ የሚለውን ሊያሳስር እና ሊያስገድል ቀርቶ ሊያስገለምጥ የማይገባውን ህገመንግስታዊ እና ሠብዓዊ መብቴ የሆነውን ጥያቄዬን ሳይቀበል ዛሬ አንተን ሲቀጠቅጡ የነበሩትን “ቀይ ለባሽ” ውሾቼን ሊመታብኝ የመጣ አካል አለና፡ ና ተከላከልልኝ ቢሎ ባንቺ ስም ቢጠራኝ እና ባልሠማው ሐገሬም አትታዘቢኝም፡፡

ሐገሬ የዘንድሮ በደልሽ መች ተቆጥሮ ያልቅና? ሌላው ቀርቶ ከምንም ነገር ጋር ሊገናኝ የማይችል፡ አውሮፓንና አሜሪካን ሳይቀር ያጥለቀለቀውን ወለድ አልባ ባንክ መስርቼ ዕምነቴም ይርጋልኝ፤ ሃገሬም ትልማልኝ ብል ያለ አንዲት የይስሙላ እንኳን ምላሽ በደፈናው “አይሆንም” ተባልኩኝ፡፡ ለምን አላልኩም፡፡ ምክኒያቱም የማለት መብት የለኝም፡፡ የሐገሬ ፌዴራሎች እና ወታደሮች በየመንገዱ ሳያቸው እኔን ሊጠብቁ ሳይሆን እኔን ሊጠባበቁና ሊያስፈራሩ እንደቆሙ ስለማውቅ ቢያንስ እንደ ወገን ይቆጥራቸው የነበረው ማንነቴ አሁን የለም፡፡ እኚያ ወታደሮችሽ ትላንት አባት፡ ወንድም፡ እህቶቼን ያለ አንዳች ጥፋት እስኪበቃቸው ቀጥቅጠዋል፤ አሁንም ከመቀጥቀጥ አልቦዘኑም፡፡ እኚያ እንደ አይኔ ብሌን የምሳሳላቸውን፡ ከሞቀ ቤታቸው ጎትቼ መርጬሃለውና መልዕክቴን ለመንግስት አድርስ ብዬ በሚሊዩን የሚቆጠር ህጋዊ ፊርማ አስጨብጬ የላኳቸውን ኮሚቴዎቼን አይሁድ እንኳን የማያደርገውን ግፍ ወታደሮችሽ ፈፀሙባቸው፡፡ በተሠባበረ ብርጭቆ ላይ እግራቸው እየደማ ነዷቸው፡፡ አልኮል ባደነዘዘው ርካሽ አንደበታቸው በዕምነታቸው ተሳለቁባቸው፡፡ የዘር ፍሬያቸው ላይ ሳይቀር ከባድ ዕቃ አንጠልጥለው አስለቀሷቸው፡፡ አንድ፡ ሁለት ብዬ መቁጠር የምችላቸው እህቶቼን፡ ሃፍረተ ገላቸውን ቀርቶ ሁለመናቸውን ከየትኛውም ወንድ ከልለው ተከብረው በኖሩበት ምድር ወንድም አባቶቻቸዉን ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ ብለው አስረው እየተፈራረቁ ደፈሯቸው፤ ተንከራተው ያፈሩትን ወርቅና ገንዘብም አይናቸው እያየ ዘረፏቸው፡፡ ይህ የተፈፀመው ጫካሽ ውስጥ እንዳይመስልሽ ሃገሬ፤ አልሙልኝ በምትዪን በመዲናሽ አዲስ አበባ አገር እያወቀ ነው፡፡ ቀና ብዬ ለማየት እንኳን የምሳቀቅላቸውን ኡለሞችና መምህሮቼን በየተገኙበት አዋረዷቸው፡፡ አስረው ገረፏቸው፤ ያለአንዳች ማስረጃና ክስ ወዳሻቸው እስር ቤት አጋዟቸው፡፡ ታዲያ ለየትኛው ኑሮዬ መሻሻል ብዬ ስለ አባይ ላስብ? በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይብስ ብለው እኚህ ውሾችሽ መስጊዶችን ቀረጥ እንዳልከፈለ የንግድ ሱቅ “ታሽጓል” ብለው ፅፈው ከርችመው እፀልያለሁ ብሎ የመጣን አማኝ ይናከሱ ጀምረዋል፡፡ ኸረ ስንቱን በደልና ግፍ ዘርዝሬ እችለዋለሁ?!

ታዲያ ከነዚህ በላይ በዚች ምድር ላይ ጠላት ባይኖረኝ ይገርማልን? ከነዚህ አውሬዎች ጎን ተሠልፌ እና በነርሱ እየታዘዝኩ በስመ “የሐገር ጉዳይ” እራሴን ለመሰዋት ባልስማማ ትታዘቢኝ ይሆን? ይህን ሁሉ ችዬ ከሐገር አይበልጥም ብዬ ለውጊያ ብሰናዳስ ዛሬ በስም ጭምር እየጠቀስኩ እነ እገሌ እና እገሊት ለፓርቲህ ታማኝ ቢሆኑም ለኔና ለሐገሬ ግን ታማኝ አይደሉምና ለፍርድ ይቅረቡልኝ፤ የዳኞቹ አለቃ እራሱ ዳኝነት አስፈልጎታል፤ ስል ሌላው ቀርቶ እንደዜጋ ክስ የመመስረት መብት እንኳን መነፈጌ መች ተዘነጋ? እርሜን አደባባይ ወጥቼ ተው ስማኝ ብዬ ብለምነው መንግስትሽ መልስ ለመስጠት እንኳን እጅግ ንቆኝ “በሲጋራ አፉ” ያላገጠብኝ ሳይረሳ ነገ ከተሠዋሁለት ግድብ ቤሳቤስቲን አይደርስህም ብሎ በለመደው ሠፊ እጁ እየዘገነ “ምን ታፈጣለህ?” ቢለኝ የማን ያለህ ልል ነው? አሁን ኢኮኖሚያችን ስላደገ ደሞዝ ይጨመርልኝ፤ ታክስ ይቀነስልኝ ወዘተርፈ ጥያቄ ባነሳ እንደዛሬው አሸባሪ ብሎ ቃሊቲ እና ማዕከላዊ እንደማይልከኝ በዚህ አጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ ሆኖ እንኳን መች ፍንጭ ሠጠኝ? ታዲያ የትኛውን ጥያቄ ሠሚ መንግስት አምኜ ልዋደቅልሽ? እመኚኝ ሐገሬ ይህ ባንዳነት አይደለም፡፡ ላንቺው ወግኜ የኔንም ያንቺንም ትልቅ ጠላት መወገድ ከትንሹ ጠላት ቅድሚያ ለመስጠት ስል የወሰንኩት ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ ዘመቻ ብሳተፍ የማቆየው ግድብሽን ብቻ ሳይሆን ልጆችሽን ደም እያስለቀሰ ያለውን ሠይጣንሽንም ጭምር ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንቺንም ቢሆን ይጎዳሻል እንጂ አይጠቅምሽም፡፡

ሙስሊምነት እና የህዳሴው ግድብ/ ግብፅ

ይህን ንዑስ ርዕስ መጨመር ያስፈለገኝ ከላይ የገለፅኩት አቋሜ በአንዳንድ ትንሽ ነገር ሲጠብቁ በነበሩ ወገኖች በሙስሊምነቴ የያዝኩት አቋም እንዳይመስላቸው በመስጋት ነው፡፡ ኃይማኖት ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለምን እንደሚነሳ አይገባኝም፡፡ ኢትዩጲያዊያን ሙስሊሞች እኮ የሐገሪቱ ግማሽ ነን፡፡ ይህች ሃገር ከኛ በላይ የማንም አይደለችም፡፡ የሙስሊሞችን ብሔራዊ ስሜት ጥያቄ ውስጥ መክተት በራሱ እንደ ቀደምት አፄዎች የሙስሊሞችን ኢትዮጲያዊነት ከመጠራጠር ይመነጫል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጲያ ጋር የተፋጠጠችው ግብፅም እኮ የሙስሊም ብቻ ሳትሆን የክርስቲያንም (ለዚያውም ከአብዛኛው ክርስቲያን ዓለም በተለየ እንደ ሐገራችን ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስ አማኞች የበዙባት) ሐገር ናት፡፡ ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጋርም ልዩ ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ሐገር ናት፡፡ ግብፆችስ ይህን ስለተረዱ አይደል በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጲያ ላይ ጫና ለማሳደር ከኢስላም ሊቃውንት በፊት የግብፅ ኮፕቲክ ቤ/ክ ጳጳሳትን እንደዋነኛ ተደራዳሪ ያዘጋጁት? ታዲያ ሙስሊሙን ለይቶ ከግብፅ ጋር የሚያስተሳስር ምን ልዩ ነገር ይመጣል ተብሎ ተጠረጠረ? ነገሩ የሐይማኖት ቢሆንማ ሱዳን ከግብፅ ኢትዮጲያን ትመርጥ ነበርን? ስለዚህ ጉዳዬ ከኢትዮጲያዊነቴ አልያም ከዕምነቴ ጋር ሳይሆን ከጭቁን ማንነቴ ጋር ብቻ የተሳሰረ መሆኑን እና ዕምነት ከምጥልበት መንግስት ጋር ብሠለፍ በሐገሬ የመጣን ማንንም እንደማልምር ይመዝገብልኝ፡፡

ማጠቃለያ

አይበለውና የተፈራው ጦርነት በግብፅ እና በኢህአዴግ ጦር መሐል ቢቀሰቀስ የትኛውም ወገን ቢያሸንፍ ድምፁ የታፈነው ጭቁኑ ህዝብ አትራፊ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግ አሸንፎ ግድቡ ቢያልቅ እና ዛሬ ላይ ሆነን “ፍትህ አዛብተውብናል፤ ዘርፈውናልና ለፍርድ ይቅረቡ” ስንል (መምህሩ እያለ ደቀመዝሙሩን በማሰር) ካላገጡብን ለማዳ ሌቦች ተርፎ ለሐገሪቱ ጠብ የሚል ሽርፍራፊ ከተገኘ ያው መስዋዕትነት ባይገባውም ጥቅም ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ቁሳዊ ጥቅም ነው፡፡ ግብፅ አሸንፋ ግድቡንም ወያኔንም ጠራርጋ “ማንኛውንም” ሌላ መሪ ብናገኝ በእርግጠኝነት በደርግ እና በኢህአዴግም ጭምር እንደታየው መጪው መንግስት ስራውን የሚጀምረው ያለፈውን መንግስት እና ህዝቡን ያጋጩ ነጥቦችን ለይቶ በማከም ነው፡፡ የህዝቡን ልብ የሰበሩ እና ከኢህአዴግ ጋር በዋነኛነት ያቃቃሩትን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማክበር፤ እንዲሁም በአቋማቸው ብቻ አሸባሪ የተባሉ የህሊና እስረኞችን በመፍታት፤ አለም አቀፍ ውግዘት ያስከተሉትን አፋኝ ህጎች በማስተካከል እና በተለይ የፈለግነውን ዕምነት የመከተል መብት እንደተቀረው ዓለም በማክበር ነው፡፡ በዚህም ከካድሬዎቹ ተርፎ ግድቡ ሊያስገኝልን የሚችል የነበረን ምናባዊ “ዕድገት” እና “የተሻለ ኑሮ” ብናጣም የሚገኘው ህሊናዊ እረፍት እና የመንፈስ መረጋጋት በቁስ የማይመነዘር ነው፡፡ ይህ አባባሌ በኢትዩጲያዊ የአርበኝነት ስሜትም ሆነ በ“ሐገር እና ፖለቲካ ይለያያሉ” ድፍን ያለ አስተሳሰብ ያስከፋችሁ ወገኖቼን ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ የኔ የግሌ አቋም ነው፡፡ ከተጋረጡብኝ ሁለት ግዙፍ ጠላቶች (ግብፅና ወያኔ) ቀድሞ እንቅልፍ የነሳኝ ወያኔ ቢወገድ በዘረዘርኳቸው በርካታ በደሎች ምክኒያት እመርጣለሁ፡፡ ከዚያም ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ማንነቴን ካከበረልኝ እና ስልጣኑን ከፈቀድኩለት መጪ መንግስት ጋር በመሆን በንፁህ ህሊና ወገቤን አስሬ ሐገሬን አለማለሁ፡፡ ነፃነት ከልማት ይቀድማልና!!! አበቃሁ፡፡

ድምፃችን ሳይሠማ “ዘመቻ ህዳሴ ግድብ”?</p>
<p>By Umer Faruq (Ethio Al-Habeshi)</p>
<p>ቅድመ ማሳሰቢያ፡ ይህንን ፅሁፍ እስከመጨረሻው ሳያነቡ እባክዎን አስተያየት ለመስጠት አይቸኩሉ፡፡ ትናንት በገባሁት ቃል መሠረት ፅሁፌን እነሆ ብያለሁ፤ መልካም ንባብ፡- </p>
<p>“ለሐገሬ ምን ሠራሁ እንጂ ሐገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል፡፡” ይላል ዕውቁ የነፃነት ታጋይ እና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብረሃም ሊንከን፡፡ ይህን አባባል በጥልቅ የተረዱት አሜሪካውያን እንደተባለው ለሐገራቸው መስራትን አስቀደሙ፡፡ ሐገራቸውም እንደ ሐገር ጥቁር ነጭ እያለች የበደል ፅዋ ታፈራርቅባቸው የነበረውን ጎጂ ብሒሏን እርግፍ አድርጋ በመተው ልጆቿን አንዱን ካንዱ ሳትለይ አቀፈች፡፡ ጥቁር የበታች ነው፤ ይህ ጥቁሮች የማይማሩበት ት/ቤት ነው፤ እና የመሳሰሉ በርካታ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ ትተገብራቸው የነበሩትን እኩይ ተግባራት፡ ተይ አይበጅሽም ሲሏት ከመሪር ትግል በኋላም ቢሆን ለዕድገቷ በማሠብ እንደ “አንዳንዶቹ” ተሳስተሻል አትበሉኝ ብላ እልህ ውስጥ ሳትገባ ስህተቷን አረመች፡፡ ሐገር እና ህዝብ ተጋግዘውም ከነበሩበት የበታችነት አዘቅት ውስጥ ወጥተው በነፃነት እና ኃያልነት ማማ ላይ ሲፈናጠጡ “ያልነቃው” የዓለም ክፍል እርስ በርሱ እየተናከሰ አጀባቸው፡፡ እንደ አትሌት ኃይሌ በዓይናቸው በብረቱ እየተመለከቱ አሜሪካ በጣጥሳቸው ወደፊት ገሠገሠች፡፡ ይህ ነው የህዝብ ሉአላዊነት ውጤት፡፡ አንባገነንነትን የፊጥኝ ያሉቱ እነ ሶቪየት ህብረት፡ የተመኩበት ኃይል ከመፈረካከስ አላዳናቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የኛው ሶሻሊስት አንባገነን መንግስቱ ኃ/ማሪያም ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ጦር ቢያዘጋጅም ህዝብ እንጂ መሳሪያ ለጭንቅ ቀን አይሆንምና እያጨበጨበ ቀኑን ሲቆጥርለት የነበረው የገዛ ህዝቡ ምንነታቸውን ከማያውቃቸው ሽርጥ ለባሽ ጎፈሬ ታጋዩች ጋር ሆኖ ገረሠሠው፡፡ መንግስቱ ኃ/ማሪያም ላይ በዋነኛነት የህዝቡን ጥርስ ያስነከሰበት ምግባሩ ልማት ማጓደሉ ነበርን? ትምህርትን አለማስፋፋቱና መሐይምነትን አለማጥፋቱ ነበርን? በፍፁም! </p>
<p>ደርግን የተኩት ባለተራዎች በልማት ብቻ የህዝብ ልብ እንደሚገኝ በማሠብ ሌላ ነገር አትጠይቁን አሉ፡፡ ግንብ እና አስፋልት ላይ እኮ የሚንፈላሠሠው ስጋዬ ነው፡፡ ስጋዬ ውስጥ ደግሞ በነፃነት መኖርን ከምንም በላይ የሚሻ ህሊናና ሠብአዊ ማንነት አለኝ፡፡ የስጋዬ ደስታም ሆነ ሐዘን የሚገለፀው በዚያ መታፈንን በማይሻው ሠብአዊ ማንነቴ ውስጥ ነው፡፡ እንደውሻ አንገቴን አስረው መሮጥ ሲያምረኝ እያጠበቁ የምሮጠው እነርሱ ሲፈቅዱ እንጂ እኔ ሲያሻኝ እንዳልሆነ እያሳዩኝ በሚያምር አስፋልት ላይ ቢነዱኝ እና ጣፋጭ አጥንት ቢያስግጡኝ አንጀቴ ውስጥ ጠብ ሊል ይችላልን? ስለ ሠብዓዊ መብቴ መከበር ስጠይቅ “ግንብ እና አስፋልት ሠርተንልሃል” ብለው መመለሳቸው በራሱ ለኔ “ግንብ ውስጥ ከኖርክ ምን አነሰህ?” አይነት የንቀት ንቀት ነው፡፡ መናገር የፈለግኩትን ተናግሬ፤ ስጠይቅ ተሠምቼ፤ ስመርጥ ድምፄ ተከብሮ ቆሎ ቆርጥሜ፡ የሳር ቤት ውስጥ ያለፍርሃት እና ያለሠቀቀን መኖር ካሁን አሁን መጥተው በተቃዋሚነቴ / በሙስሊምነቴ አሠሩኝ፤ ገደሉኝ፤ ልጄን፡ ወንድሜን፡ እህቴን አልያም አባቴን ያለማንም ሃይ ባይ ጎትተው ወሠዱብኝ እያልኩ እየተሳቀቅኩ ቪላ ቤት ውስጥ ከመኖር (ያውም እድሉ ካለኝ) ሺህ ጊዜ ይበልጥብኛል፡፡ ኢህአዴግ ከደርግ እና ዓለም ካወቀቻቸው በርካታ አንባገነን መንግስታት ፍፃሜ ትምህርት ሊቀስም በፍፁም አልቻለም፡፡ ርዕሴን አልዘነጋሁም፤ በጥሞና ይከተሉኝ፡፡</p>
<p>በ “ዘመቻ ህዳሴ ግድብ” የመሳተፍ እና ያለመሳተፍ ጉዳይ የሐገር ጉዳይ ብቻ ነውን?</p>
<p>መግቢያዬ ላይ በጠቀስኩት ታሪካዊ ጥቅስ፡ አብረሃም ሊንከን “ሀገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል” ሲል አንተ ያቅምህን ለሐገርህ ስትታገል የልብህን ለማድረስ ሃገርህ እጇ ቢያጥር አትውቀሳት ለማለት እንጂ አንተ ደፋ ቀና ስትልላት “የአይንህ ቀለም አላማረኝም” ብላ ብታስርህ እና ብትገርፍህ አሜን ብለህ ተቀጥቀጥ ለማለት እንዳልሆነ የሚያግባባን ይመስለኛል፤ እርሱም በጥቁርነቱ ሲጨቆን ያንን አላደረገምና፡፡ በዚህ አግባብ በአሁኑ ሠዓት እኔ ለሐገሬ የማበረክተውን እና ሐገሬ ለሠራሁት ሥራ ተገቢውን ክፍያ ያልከፈለችኝ “እጅ አጥሯት” ነው ብዬ በአብረሃም ሊንከንኛ ባቀነቅንም፡ መብቴን ባልኩ የተቀጠቀጥኩበት እና የገርባ እና የአሳሳ ወንድም እህቶቼ እንደሌላው ኢትዩጲያዊ ወገናቸው የተገደሉበት ማናለብኝነት እና ትምክህት ለአብረሃም ሊንከን ቢደርስ ቢያንስ ለዛሬዋ ሐገሬ (መንግስቴ) ባለዕዳ እንደማያደርገኝ አምናለሁ፡፡  ወዴት እያመራሁ እንደሆነ የተገነዘባችሁ ይመስለኛል፡፡ ኦዎን! በአሁኑ ሠዓት ሐገሬ ኢትዩጲያ “ህዳሴዋን” እንዳታበስር ጠላት ተሠድሮባታል፡፡ ክፉውን ያርቀውና አካባቢው ጦርነት ጦርነት መሽተት ጀምሯል፡፡ በሀገሬ ጥቅም የመጣ ማንኛውም (ማንኛውም ይሰመርበት) ጠላት ያው ጠላት ነው፡፡ </p>
<p>በዚህ አቋማችን ባንለያይም ይህን ጠላት ለመፋለም የኢህአዴጓ ሐገሬ “በክፉ ቀኔ” ሳትደርስልኝ በክፉ ቀኗ ብትጠራኝ የሚኖረኝ ምላሽ ምክኒያቴን ላላገናዘበ ማንኛውም አንባቢ ላይዋጥለት ይችላል፡፡ በርግጥም ሐገሬ እንደስከዛሬው በኢህአዴግ እየተመራች ከየትኛውም ጠላት ጋር ለፍልሚያ ብትጠራኝ አልሰማትም፡፡ ይህን የምለው ፖለቲካን ከሐገር መለየት ተስኖኝ አልያም ሐገሬን ኢትዩጲያን ከማንም ያነሠ አፍቅሬ እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም ጥሎብኝ ከልጅነቴ ጀምሮ የሐገሬ ነገር አይሆንልኝም፡፡ በኢትዩ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ዕድሜዬ ለአቅመ ጦርነት ባይደርስም ከተዋጉት ባልተናነሰ ትንፋሼ ቁርጥ እስኪል ሁለመናዬ አይንና ጆሮ ሆኖ የሐገሬን ድል በጉጉት የተጠባበቀው ማንነቴ አሁንም አለ፡፡ ኢትዩጲያዬ ላይ እንኳን ሠይፍ የመዘዘባትን ቀርቶ በሠላማዊው የእግር ኳስ ሜዳ የተገዳደራትን እንኳን በዙሪያዬ ኳሱን ከሚከታተለው ህዝብ በተለየ ብርድ እንደመታው ጥርሴ እየተንገጫገጨ ከውስጥ በሚንተገተግ የሐገር ፍቅር ስሜት ድሏን በጭንቀት እጠባበቅ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ከሐገሬ ውጪ እንደሌላው ለ አርሴና ማንቼ የማውሰው አይንም የኳስ ፍቅርም አልነበረኝም፡፡ ይህ የሐገር ፍቅር ከደም የተቀላቀለ የማንነት መገለጫ እንጂ ሲፈልጉ የሚገዙት ሲፈልጉ የሚሸጡት ሸቀጥ አይደለም፡፡ ዛሬም ወደፊትም ይኖራል፡፡ እንዲህ የሆንኩላት ሐገሬ ግን ሳትፈልግ መሪዋን በጨበጡ ሽፍቶች አገለለችኝ፡፡ እንኳን በአደባባይ፡ ሻሂ ቤት ቁጭ ብዬ ለምተነፍሳት ቃል ሁለት ጊዜ እንዳስብ አስገድዳ ያለጥፋቴ ስትፈልግ የምትገርፈኝ ስትፈልግ የምትዘርፈኝ ባሪያዋ አደረገችኝ፡፡ መብት የሚባል ነገር በፍፁም እንዳልጠይቅ ፤ አንገቴን ደፍቼ እንድገዛ ፈረደችብኝ፡፡ መንግስቴ የገዛ የሐይማኖት መሪዬን እራሴው ልምረጥ የሚለውን ሊያሳስር እና ሊያስገድል ቀርቶ ሊያስገለምጥ የማይገባውን ህገመንግስታዊ እና ሠብዓዊ መብቴ የሆነውን ጥያቄዬን ሳይቀበል ዛሬ አንተን ሲቀጠቅጡ የነበሩትን “ቀይ ለባሽ” ውሾቼን ሊመታብኝ የመጣ አካል አለና፡ ና ተከላከልልኝ ቢሎ ባንቺ ስም ቢጠራኝ  እና ባልሠማው ሐገሬም አትታዘቢኝም፡፡</p>
<p>ሐገሬ የዘንድሮ በደልሽ መች ተቆጥሮ ያልቅና? ሌላው ቀርቶ ከምንም ነገር ጋር ሊገናኝ የማይችል፡ አውሮፓንና አሜሪካን ሳይቀር ያጥለቀለቀውን ወለድ አልባ ባንክ መስርቼ ዕምነቴም ይርጋልኝ፤ ሃገሬም ትልማልኝ ብል ያለ አንዲት የይስሙላ እንኳን ምላሽ በደፈናው “አይሆንም” ተባልኩኝ፡፡ ለምን አላልኩም፡፡ ምክኒያቱም የማለት መብት የለኝም፡፡ የሐገሬ ፌዴራሎች እና ወታደሮች በየመንገዱ ሳያቸው እኔን ሊጠብቁ ሳይሆን እኔን ሊጠባበቁና ሊያስፈራሩ እንደቆሙ ስለማውቅ ቢያንስ እንደ ወገን ይቆጥራቸው የነበረው ማንነቴ አሁን የለም፡፡ እኚያ ወታደሮችሽ ትላንት አባት፡ ወንድም፡ እህቶቼን ያለ አንዳች ጥፋት እስኪበቃቸው ቀጥቅጠዋል፤ አሁንም ከመቀጥቀጥ አልቦዘኑም፡፡ እኚያ እንደ አይኔ ብሌን የምሳሳላቸውን፡ ከሞቀ ቤታቸው ጎትቼ መርጬሃለውና መልዕክቴን ለመንግስት አድርስ ብዬ በሚሊዩን የሚቆጠር ህጋዊ ፊርማ አስጨብጬ የላኳቸውን ኮሚቴዎቼን አይሁድ እንኳን የማያደርገውን ግፍ ወታደሮችሽ ፈፀሙባቸው፡፡ በተሠባበረ ብርጭቆ ላይ እግራቸው እየደማ ነዷቸው፡፡ አልኮል ባደነዘዘው ርካሽ አንደበታቸው በዕምነታቸው ተሳለቁባቸው፡፡ የዘር ፍሬያቸው ላይ ሳይቀር ከባድ ዕቃ አንጠልጥለው አስለቀሷቸው፡፡ አንድ፡ ሁለት ብዬ መቁጠር የምችላቸው እህቶቼን፡ ሃፍረተ ገላቸውን ቀርቶ ሁለመናቸውን ከየትኛውም ወንድ ከልለው ተከብረው በኖሩበት ምድር ወንድም አባቶቻቸዉን ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ ብለው አስረው እየተፈራረቁ ደፈሯቸው፤ ተንከራተው ያፈሩትን ወርቅና ገንዘብም አይናቸው እያየ ዘረፏቸው፡፡ ይህ የተፈፀመው ጫካሽ ውስጥ እንዳይመስልሽ ሃገሬ፤ አልሙልኝ በምትዪን በመዲናሽ አዲስ አበባ አገር እያወቀ ነው፡፡ ቀና ብዬ ለማየት እንኳን የምሳቀቅላቸውን ኡለሞችና መምህሮቼን በየተገኙበት አዋረዷቸው፡፡ አስረው ገረፏቸው፤ ያለአንዳች ማስረጃና ክስ ወዳሻቸው እስር ቤት አጋዟቸው፡፡ ታዲያ ለየትኛው ኑሮዬ መሻሻል ብዬ ስለ አባይ ላስብ? በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይብስ ብለው እኚህ ውሾችሽ መስጊዶችን ቀረጥ እንዳልከፈለ የንግድ ሱቅ “ታሽጓል” ብለው ፅፈው ከርችመው እፀልያለሁ ብሎ የመጣን አማኝ ይናከሱ ጀምረዋል፡፡ ኸረ ስንቱን በደልና ግፍ ዘርዝሬ እችለዋለሁ?! </p>
<p>ታዲያ ከነዚህ በላይ በዚች ምድር ላይ ጠላት ባይኖረኝ ይገርማልን? ከነዚህ አውሬዎች ጎን ተሠልፌ እና በነርሱ እየታዘዝኩ በስመ “የሐገር ጉዳይ” እራሴን ለመሰዋት ባልስማማ ትታዘቢኝ ይሆን? ይህን ሁሉ ችዬ ከሐገር አይበልጥም ብዬ ለውጊያ ብሰናዳስ ዛሬ በስም ጭምር እየጠቀስኩ እነ እገሌ እና እገሊት ለፓርቲህ ታማኝ ቢሆኑም ለኔና ለሐገሬ ግን ታማኝ አይደሉምና ለፍርድ ይቅረቡልኝ፤ የዳኞቹ አለቃ እራሱ ዳኝነት አስፈልጎታል፤ ስል ሌላው ቀርቶ እንደዜጋ ክስ የመመስረት መብት እንኳን መነፈጌ መች ተዘነጋ? እርሜን አደባባይ ወጥቼ ተው ስማኝ ብዬ ብለምነው መንግስትሽ መልስ ለመስጠት እንኳን እጅግ ንቆኝ “በሲጋራ አፉ” ያላገጠብኝ ሳይረሳ ነገ ከተሠዋሁለት ግድብ ቤሳቤስቲን አይደርስህም ብሎ በለመደው ሠፊ እጁ እየዘገነ “ምን ታፈጣለህ?” ቢለኝ የማን ያለህ ልል ነው? አሁን ኢኮኖሚያችን ስላደገ ደሞዝ ይጨመርልኝ፤ ታክስ ይቀነስልኝ ወዘተርፈ ጥያቄ ባነሳ እንደዛሬው አሸባሪ ብሎ ቃሊቲ እና ማዕከላዊ እንደማይልከኝ በዚህ አጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ ሆኖ እንኳን መች ፍንጭ ሠጠኝ? ታዲያ የትኛውን ጥያቄ ሠሚ መንግስት አምኜ ልዋደቅልሽ? እመኚኝ ሐገሬ ይህ ባንዳነት አይደለም፡፡ ላንቺው ወግኜ የኔንም ያንቺንም ትልቅ ጠላት መወገድ ከትንሹ ጠላት ቅድሚያ ለመስጠት ስል የወሰንኩት ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ ዘመቻ ብሳተፍ የማቆየው ግድብሽን ብቻ ሳይሆን ልጆችሽን ደም እያስለቀሰ ያለውን ሠይጣንሽንም ጭምር ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንቺንም ቢሆን ይጎዳሻል እንጂ አይጠቅምሽም፡፡</p>
<p>ሙስሊምነት እና የህዳሴው ግድብ/ ግብፅ</p>
<p>ይህን ንዑስ ርዕስ መጨመር ያስፈለገኝ ከላይ የገለፅኩት አቋሜ በአንዳንድ ትንሽ ነገር ሲጠብቁ በነበሩ ወገኖች በሙስሊምነቴ የያዝኩት አቋም እንዳይመስላቸው በመስጋት ነው፡፡ ኃይማኖት ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለምን እንደሚነሳ አይገባኝም፡፡ ኢትዩጲያዊያን ሙስሊሞች እኮ የሐገሪቱ ግማሽ ነን፡፡ ይህች ሃገር ከኛ በላይ የማንም አይደለችም፡፡ የሙስሊሞችን ብሔራዊ ስሜት ጥያቄ ውስጥ መክተት በራሱ እንደ ቀደምት አፄዎች የሙስሊሞችን ኢትዮጲያዊነት ከመጠራጠር ይመነጫል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጲያ ጋር የተፋጠጠችው ግብፅም እኮ የሙስሊም ብቻ ሳትሆን የክርስቲያንም (ለዚያውም ከአብዛኛው ክርስቲያን ዓለም በተለየ እንደ ሐገራችን ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስ አማኞች የበዙባት) ሐገር ናት፡፡ ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጋርም ልዩ ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ሐገር ናት፡፡ ግብፆችስ ይህን ስለተረዱ አይደል በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጲያ ላይ ጫና ለማሳደር ከኢስላም ሊቃውንት በፊት የግብፅ ኮፕቲክ ቤ/ክ ጳጳሳትን እንደዋነኛ ተደራዳሪ ያዘጋጁት? ታዲያ ሙስሊሙን ለይቶ ከግብፅ ጋር የሚያስተሳስር ምን ልዩ ነገር ይመጣል ተብሎ ተጠረጠረ? ነገሩ የሐይማኖት ቢሆንማ ሱዳን ከግብፅ ኢትዮጲያን ትመርጥ ነበርን? ስለዚህ ጉዳዬ ከኢትዮጲያዊነቴ አልያም ከዕምነቴ ጋር ሳይሆን ከጭቁን ማንነቴ ጋር ብቻ የተሳሰረ መሆኑን እና ዕምነት ከምጥልበት መንግስት ጋር ብሠለፍ በሐገሬ የመጣን ማንንም እንደማልምር ይመዝገብልኝ፡፡</p>
<p>ማጠቃለያ</p>
<p>አይበለውና የተፈራው ጦርነት በግብፅ እና በኢህአዴግ ጦር መሐል ቢቀሰቀስ የትኛውም ወገን ቢያሸንፍ ድምፁ የታፈነው ጭቁኑ ህዝብ አትራፊ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግ አሸንፎ ግድቡ ቢያልቅ እና ዛሬ ላይ ሆነን “ፍትህ አዛብተውብናል፤ ዘርፈውናልና ለፍርድ ይቅረቡ” ስንል (መምህሩ እያለ ደቀመዝሙሩን በማሰር) ካላገጡብን ለማዳ ሌቦች ተርፎ ለሐገሪቱ ጠብ የሚል ሽርፍራፊ ከተገኘ ያው መስዋዕትነት ባይገባውም ጥቅም ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ቁሳዊ ጥቅም ነው፡፡ ግብፅ አሸንፋ ግድቡንም ወያኔንም ጠራርጋ “ማንኛውንም” ሌላ መሪ ብናገኝ በእርግጠኝነት በደርግ እና በኢህአዴግም ጭምር እንደታየው መጪው መንግስት ስራውን የሚጀምረው ያለፈውን መንግስት እና ህዝቡን ያጋጩ ነጥቦችን ለይቶ በማከም ነው፡፡ የህዝቡን ልብ የሰበሩ እና ከኢህአዴግ ጋር በዋነኛነት ያቃቃሩትን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማክበር፤ እንዲሁም በአቋማቸው ብቻ አሸባሪ የተባሉ የህሊና እስረኞችን በመፍታት፤ አለም አቀፍ ውግዘት ያስከተሉትን አፋኝ ህጎች በማስተካከል እና በተለይ የፈለግነውን ዕምነት የመከተል መብት እንደተቀረው ዓለም በማክበር ነው፡፡ በዚህም ከካድሬዎቹ ተርፎ ግድቡ ሊያስገኝልን የሚችል የነበረን ምናባዊ “ዕድገት” እና “የተሻለ ኑሮ” ብናጣም የሚገኘው ህሊናዊ እረፍት እና የመንፈስ መረጋጋት በቁስ የማይመነዘር ነው፡፡ ይህ አባባሌ በኢትዩጲያዊ የአርበኝነት ስሜትም ሆነ በ“ሐገር እና ፖለቲካ ይለያያሉ” ድፍን ያለ አስተሳሰብ ያስከፋችሁ ወገኖቼን ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ የኔ የግሌ አቋም ነው፡፡ ከተጋረጡብኝ ሁለት ግዙፍ ጠላቶች (ግብፅና ወያኔ) ቀድሞ እንቅልፍ የነሳኝ ወያኔ ቢወገድ በዘረዘርኳቸው በርካታ በደሎች ምክኒያት እመርጣለሁ፡፡ ከዚያም ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ማንነቴን ካከበረልኝ እና ስልጣኑን ከፈቀድኩለት መጪ መንግስት ጋር በመሆን በንፁህ ህሊና ወገቤን አስሬ ሐገሬን አለማለሁ፡፡ ነፃነት ከልማት ይቀድማልና!!! አበቃሁ፡፡” src=”<a href=https://fbcdn-sphotos-h-a.akamaihd.net/hphotos-ak-frc1/s403x403/1003985_444670825632115_2110037783_n.jpg&#8221; width=”533″ height=”280″ />

ኢሕአፓ በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች በህቡዕ ወረቀት በተንኩ አለ

$
0
0

በስውር የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)አባላት በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች ረቡዕ ሌሊት ሰኔ 5/2005 ዓ.ም. /June 12, 2013/  ተነሥ  በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ቀስቃሽ ፅሑፎችን የበተኑ ሲሆን በዋናነት …..በቦሌ፣በካዛንቺስ፣በአራት ኪሎ፣በሽሮ ሜዳ፣በቄራ፣በፈረንሳይ ለጋሲዪን፣በሜክሲኮ፣በፒያሳ፣በመገናኛ፣በኮልፌ፣በመርካቶ፣በጎፋ እና በመሳሰሉት ዋና ዋና የከተማዋ ክፍል በሚገኙ የማስታወቂ ቦርዶች ላይ ተለጥፈው የታዩ ሲሆን በተለይ ሐሙስ ሰኔ 6/2005 ዓ.ም. በርካታ ነዋሪዎች ጽሑፉን ማንበብ ችለዋል።ይሁን እንጂ ይህ ዜና የደረሳቸው የገዢው ፓርቲ አመራሮች ወዲያው የፌደራል ፖሊሶችን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትን በማሰማራት በዋና ዋና ቦታዎች ላይ የሚገኙትን ያነሱ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢ ግን ጽሑፎቹ እስከ ቀትር ሳይነሱ በበርካታ ሰዎች መነበብ ችለዋል።

 

eprp1

 

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በ5ለ1 አደረጃጀት ጠርንፎ እንደያዘ የሚነገርለት ኢህአዴግ ይህ አይነቱ ድንገተኛ ክስተት ዛሬም ድረስ ከህዝብ ጋር ሆድ እና ጀርባ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ትዝብታቸውን የገለፁ ሲሆን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ የወጣቶች ሊግ አመራሮች አስቸኳይ ስብሰባ ሐሙስ ዕለት እንደተቀመጡ ከስፍራው መረዳት ተችሏል።

eprp2

ተነሥ  በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የዚህ ጽሑፍ ይዘት የሚከተለው ነው፦ “እጅግ የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት፤ይልቁንም ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራን የፈነጠቅህ ፋና ወጊ የነፃነት አርበኛ መሆንህ የአደባባይ ምስጢር ነው።ይሁን እንጂ የዚህ ሁሉ ጥንካሬህ መሠረት የሆነው አንድነትህ በጎጠኛው የወያኔ ቡድን የዘውጌ አስተዳደር ተሸርሽሮ ዛሬ በሀገርህ ተንቀሳቅሰህ የመስራት መብትህ ተገድቦ፣ከችሎታህና ከግለሰባዊ ክህሎትህ ይልቅ በዘር ማንነትህ እየተመዘንክ የኢኮኖሚ መገለል እየደረሰብህ ህይወት ብርቱ ሠልፍ ሆናብህ ሀገርህን ጥለህ እንድትሰደድ በተሰላ ስሌት በመኖርና ባለመኖር ቅርቃር ውስጥ እንድትባዝን ተደርገህ፣ሰብዓዊና ዴሞክራሲዊ መብትህ ተገፎ የመናገርና ሃሳብህን በነፃነት የማራመድ መብትህን ከመነጠቅህ ባሻገር በአጠቃላይ ህልውናህ በወያኔ የግፍ መዳፍ ውስጥ ወድቋል።ስለሆነም እንደመዥገር በላይህ ላይ ተጣብቆ በደምህ የሰባውን ይህን ዘረኛ ቡድን ከጫንቃህ ላይ አራግፈህ በፍትህ አደባባይ የምታቆምበት ጊዜው አሁን ነው።ሀገርህንና ራስህን ለማዳን ተነሥ!!!”



የግብጽ መከላኪያ ሚንስተር በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ግዜው ገና ነው አሉ

$
0
0

Egyptian armed forces spokesperson Ahmed Mohamed Ali said Thursday that it is too early to talk about military action against Ethiopia over the Grand Renaissance Dam dispute.

 

Egypt has other political, economic and social means with which to tackle the matter, Ali stated, adding “military action is usually a last resort.”

The statement comes after President Mohamed Morsy warned Monday that Egypt does not want war with Ethiopia but will keep “all options open,” piling pressure on an ongoing dispute over the giant dam Addis Ababa is building across the River Nile.

In a televised speech to cheering Islamist supporters, Morsy voiced his understanding for the development needs of poorer nations upstream in the Nile basin, but still deployed emotive language to claim Egyptians would not tolerate any reduction in water supplies.

“Egypt’s water security cannot be violated in any way,” Morsy said. “As head of state, I confirm to you that all options are open.”

“We are not calling for war, but we will never permit our water security…to be threatened,” the president added.

Drawing on an old Egyptian song about the Nile, he said: “If it diminishes by one drop then our blood is the alternative.”

Source/www. egyptindependent.com


ፍርድ ቤት የባንክ ሂሳባቸውን ያገደባቸው የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ

$
0
0

ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቁጥር የኮ/መ/ቁ 134048 ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 429 የመንግሥት ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በመንግሥትና በግል ባንኮች ያላቸው ገንዘብ የታገደባቸው መሆኑን ፣ የአንዳንዶች ደግሞ የድርጅታቸው የባንክ ሂሳብና መኪኖቻቸው እንዲታገድባቸው ትእዛዝ አስተላልፎአል…

ይፋ የሆነው ዝርዝር እንደሚያሳየው ከሙስና ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሰዎች ቤተሰቦች እና ዘመዶች የባንክ ሂሳብ ቁጥር እንዲታገድ ተደርጓል። ከባለሀብቱ አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ቤተሰቦች መካከል የኤፍሬም ነጋ  የገ/እግዚአብሄር፣  ሄኖክ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ፣ ይትባረክ ነጋ ገ/እግዚአባሄር ፣ሠላም ነጋ ገ/እግዚአብሔር እንዲሁም የራሄል ነጋ ገ/እግዚአብሄር የባንክ ሂሳብ ደብተር እንዲታገድ ሲደረግ ከአቃቢ ህጉ አቶ ማርክነህ አለማየሁ ቤተሰቦች መካከል ደግሞ የ ዮናታን ማርክነህ አለማየሁ፣ ኤልሻዳይ ማርክነህ አለማየሁ ፣ ባልጊቴ አለማየሁ ወዳቦ ፣ ባፋነ አለማየሁ ወዳቦ ፣ አየለ አለማየሁ ወዳቦ ፣ ብርሃኑ ዓለማየሁ ወዳቦ ፣ አበራ አለማየሁ ወዳቦ እና ትግስት ዓለማየሁ ወዳቦ ይገኙበታል።

ከታዋቂ ሰዎች መካከል የአቶ ስየ አብረሀ ወንድሞች የሆኑት የ ህሉፍ አብርሃ ሐጎስ ፣ አስመለሻ አብርሃ ሐጎስ፣ ስዬ አብርሃ ሐጎስ፣ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ ፣ ወ/ስላልሴ አብርሃ ሐጎስ ፣ እንዲሁም ትምኒት አብርሃ ሐጎስ የባንክ ሂሳቦች እንዲታገዱ ተደርጎአል።

የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸውን ሰዎች ሙስ ስም ዝርዝር

  1. አባቡ አለሙ ገብሩ
  2. ምስጋናው ይስሃቅ እጅባ
  3. በረከት ይስሃቅ እጅባ
  4. ታደሉ አለምነው ተፈራ
  5. ፀጋነሽ አለምነው ተፈራ
  6. አባተ ጋሻው ቦጋለ
  7. ጌጤ ጋሻው ቦጋለ
  8. ዘርፌ ጋሻው ቦጋለ
  9. ፀሐይ ጋሻው ቦጋለ
  10. ትዕግስት ጋሻው ቦጋለ
  11. አስፋው ጋሻው ቦጋለ
  12. መብራት አበበ አብርሃ
  13. ቤቴልሄም አማኑኤል ሰይፈ
  14. እቁባይ ተከለ አርአያ
  15. ብሌን አማኑኤል ሰይፈ
  16. ሊዲያ አማኑኤል ሰይፈ
  17. እየሩሳሌም ስማቸው ከበደ
  18. መቅደላዊ ስማቸው ከበደ
  19. ኤልሻዳይ ስማቸው ከበደ
  20. ኢቫና ስማቸው ከበደ
  21. አያልነሽ ይመር ጌታሁን
  22. ሠለሞን ከበደ ካሳ
  23. ምንትዋብ ከበደ ካሳ
  24. ዳንኤል ደባሽ ሀገሩ
  25.  ናኑ ደባሽ ሀገሩ
  26. ሰላማዊት ደባሽ ሀገሩ
  27. ሣራ ደባሽ ሀገሩ
  28. ኤፍሬም ነጋ ገ/እግዚአብሄር
  29. ሄኖክ ነጋ ገ/እግዚአብሔር
  30. ይትባረክ ነጋ ገ/እግዚአባሄር
  31. ሠላም ነጋ ገ/እግዚአብሔር
  32. ራሄል ነጋ ገ/እግዚአብሄር
  33. ዮርዳኖስ ደሣለኝ ገ/እግዚአብሄር
  34. ቅድስት ድጉማ ዋቅጅራ
  35. አናኒያ ብርሃኔ እጅጉ
  36. ተዋበች ወርቁ ወልፃዲቅ
  37. ብሩክ ከበደ ታደሰ
  38. ፍቅረማርያም ከበደ ታደሰ
  39. ክብነሽ ከበደ ታደሰ
  40. ዳኝነት ከበደ ታደሰ
  41. ትዕግስት ከበደ ታደሰ
  42. ሙሉነህ ከበደ ታደሰ
  43. ትዕዛዙ ከበደ ታደሰ
  44. ቴዎድሮስ ማዕረግ አዱኛ
  45. አይንአዲስ በረከት ኃ/ጊዮርጊስ
  46. ወይንሸት ወርቁ አንጋሶ
  47. መብራቱ እጅጉ አበራ
  48. የማነ ብርሃን እጅጉ አበራ
  49. መሀሪ እጅጉ አበራ
  50. ዮሐንስ እጅጉ አበራ
  51. ለምለም እጅጉ አበራ
  52. ሠናይት እጅጉ አበራ
  53. ካሰች አምደመስቀል መገርሳ
  54. ዮናታ ማርክነህ አለማየሁ
  55. ኤልሻዳይ ማርክነህ አለማየሁ
  56. ባልጊቴ አለማየሁ ወዳቦ
  57. ባፋነ አለማየሁ ወዳቦ
  58. አየለ አለማየሁ ወዳቦ
  59. ብርሃኑ ዓለማየሁ ወዳቦ
  60. አበራ አለማየሁ ወዳቦ
  61. እጀትግስት ዓለማየሁ ወዳቦ
  62. ሚካኤል አምደመስቀል መገርሳ
  63. ዳኛቸው አምደመስቀል መገርሳ
  64. ተረፈ አምደመስቀል መገርሳ
  65.  ተክሉ አምደመስቀል መገርሳ
  66. ደርባቸው አምደመስቀል መገርሳ
  67. መቅደስ አምደመስቀል መገርሳ
  68. ትዝታ አምደመስቀል መገርሳ
  69. ሙሉጸጋ አምደመስቀል መገርሳ
  70. ውቢት ኃይለገብርኤል አስፋው
  71. ያዕቆብ ደጉ ሆቢቾ
  72. ዮናታል ደጉ ሆቢቾ
  73. ዳግማዊ ደጉ ሆቢቾ
  74. ኡፋይሴ ሆቢቾ አልቤ
  75.  ዲቃም ቤቢሶ አልቤ
  76. ካሳሁን ኃይለገብርኤል አስፋው
  77. አምሃ ኃይለገብርኤል አስፋው
  78. ዝናሽ ኃይለገብርኤል አስፋው
  79. ምሳዬ ኃይለገብርኤል አስፋው
  80. አበባ ኃይለገብርኤል አስፋው
  81. ፍሬህይወት ጌታቸው ሀብቴ
  82. ጌታቸው ምስጋና ተፈሪ
  83. ዮሴፍ ጌታቸው ምስጋና
  84. ዮናታን ጌታቸው ምስጋና
  85. ጌታቸው ሀብቴ ተክለሃይማኖት
  86. አብረኸት ገብረመድህን ጣሰው
  87. አበባው ጌታቸው ሀብቴ
  88. ገስጥ ጌታቸው ሀብቴ
  89. ደሳለኝ ጌታቸው ሀብቴ
  90. ቤተልሄም ጌታቸው ሃብቴ
  91. ዜና ጌታቸው ሀብቴ
  92. ሳህሌ ገላው ፈንቴ
  93.  ላይኩን ውብየ ተሰማ
  94. አበባው ላይኩን ውብየ
  95. በትረወርቅ ላይኩን ውብየ
  96. ዳዊት ላይኩን ውብየ
  97. አብርሃም ለይኩን ውብየ
  98. ህሉፍ አብርሃ ሐጎስ
  99. አስመለሻ አብርሃ ሐጎስ
  100. ስዬ አብርሃ ሐጎስ
  101. አሰፋ አብርሃ ሐጎስ
  102. ወ/ስላልሴ አብርሃ ሐጎስ
  103. ትምኒት አብርሃ ሐጎስ
  104. ፀሐይነሽ ገ/ሚካኤል ገብሩ
  105. ንግስቲ ሳመሶነ ብሩ
  106. እጅግጋየሁ ሳምሶን ብሩ
  107. ኢትዮጵያ ሳምሶን ብሩ
  108. ያለም መብራት ሳምሶን ብሩ
  109. ቢተወደድ ሳምሶን ብሩ
  110. ሚዛን ሳምሶን ብሩ
  111. በእግዚአብሔር አለበል ኃይሉ
  112. ኤልሳ ታደለ ኃይሉ
  113. ናአምን በእግዚአብሔር አለበል
  114. ቅዱስ በእግዚአብሄር አለበል
  115. በረኽት በእግዚአብሄር አለበል
  116. አለበል ኃይሉ አዱኛ
  117. እቴነሽ ብሩክ ደስታ
  118. ዘላለም አለበል ኃይሉ
  119. ነፃነት አለበል ኃይሉ
  120. የሰውዘር አለበል ኃይሉ
  121. በሁሉም አለበል ኃይሉ
  122. ሰላም አለበል ኃይሉ
  123. ዮናስ ታደለ ኃይሉ
  124. ሚካኤል ታዳለ ኃይሉ
  125. ዮሴፍ አዳዩ ገብሩ
  126. ሃና በርሄ ሀጎስ
  127. ግሎሪ ዮሴፍ አዳዩ
  128. ሊዮ ዮሴፍ አዳዩ
  129. አዳዩ ገብሩ ዲኒ
  130. አብርሃ አዳዩ ገብሩ
  131. ራህዋ አዳዩ ገብሩ
  132. ብርክቲ አዳዩ ገብሩ
  133. ኢንዲሪያስ አዳዩ ገብሩ
  134. ፋና አዳዩ ገብሩ
  135. ታበቱ አዳዩ ገብሩ
  136. ስላስ አውዓለ ሐጎስ
  137. ኃ/ስላሰ በርሄ ሀጎስ
  138. ተስፋይ በርሄ ሀጎስ
  139. ብሩር በርሄ ሀጎስ
  140. ዘቢብ በርሄ ሀጎስ
  141. ጌታነህ ግደይ ንርኤ
  142. ኤደን ብርሃነ ገ/ህይወት
  143. አበባ ግደይ ንርኤ
  144. ዙፋን ግደይ ንርኤ
  145. ደስታ ግደይ ንርኤ
  146. ዮሐንስ ግደይ ንርኤ
  147. መንግስቱ ግደይ ንርኤ
  148. ሀብቶም ግደይ ንርኤ
  149. ቢኒያም ብርሃነ ገ/ህይወት
  150. ኤልሻዳይ ብርሃነ ገ/ሕይወት
  151. ብርክታዊት ብርሃን ገ/ህይወት
  152. ገ/መድህን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
  153. ገ/ህይወት ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
  154. ኪዳን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
  155. ሱራፌል ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
  156. ብርያ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
  157. እግዜሄሩ ወ/ጊዮርጌስ ወ/ሚካኤል
  158. ግደይ ተስፋ ገ/ስላሴ
  159. ስላስ ተስፋይ ገ/ስላሴ
  160. ለተመስቀል ተስፋይ ገ/ስላሴ
  161. ማህተመሥላሴ ጥሩነህ በርታ
  162. ማሞ በርታ ባቦ
  163. ታደሰ በርታ ባቦ
  164. ዳዊት በርታ ባቦ
  165. ብሩክ በርታ ባቦ
  166. አበበች በርታ ባቦ
  167. አመለወርቅ በርታ ባቦ
  168. እመቤት በርታ ባቦ
  169. ፍቅርተ በርታ ባቦ
  170. ይልማ ፈንታ ቻይ
  171. አንጋች ፈንታ ቻይ
  172. ሸዋዬ ፈንታ ቻይ
  173. ፈጠነ ታገለ አወቀ
  174. ቻለ ታገለ አወቀ
  175. እማዋ ታገለ አወቀ
  176. አልጋነሽ ታጋለ አወቀ
  177. እመቤት ታጋለ አወቀ
  178. ዳዊት አሰፋ ዘውዱ
  179. ትዕግስት አሰፋ ዘውዱ
  180. ጥሩወርቅ አሰፋ ዘውዱ
  181. ተወዳጅ አሰፋ ዘውዱ
  182. መልካም አሰፋ ዘውዱ
  183. ማህሌት አሰፋ ዘውዱ
  184. ዝናሽ ብርሃኑ በሻህ
  185. ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
  186. ፍሬህይወት ብርሃኑ በሻህ
  187. አብዮት ብርሃኑ በሻህ
  188. ግልነሽ ብርሃኑ በሻህ
  189. ሰለሞን ብርሃኑ በሻህ
  190. አዲስ ብርሃኑ በሻህ
  191. ካህሳይ ጉላል አለመ
  192. ዘውዲቱ ለምለም ገ/ማርያም
  193. ብስራት ገ/መድህን ተስፋይ
  194. ግርማይ ብስራት ገ/መድህን
  195. ዮሀንስ ብስራት ገ/መድህን
  196. አበባ ብስራት ገ/መድህን
  197. ለተመስቀል ብስራት ገ/መድህን
  198. ሚዛን ብስራት ገ/መድህን
  199. አክበረት ብስራት ገ/መድህን
  200. ገ/መድህን ሀጎስ ንጉሴ
  201. ጌቱ ገ/መድህን ሀጎስ
  202. ሳራ ገ/መድህን ሃጎስ
  203. ፍፁም ገ/መድህን አብርሃ
  204. ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
  205. አለም ስንሻው አማረ
  206. ሐጎስ ፍፁም ገ/መድህን
  207. ኃይሌ ፍፁም ገ/መድህን
  208. ኤርሚያስ ፍፁም ገ/መድህን
  209. ደሊና ፍፁም ገ/መድህን
  210. ገነት ገ/መድህን ሀጎስ
  211. ኮነ ምህረቱ እሸቱ
  212. መንበረ ታምራት በየነ
  213. ፍስሐ ኮነ ምህረቱ
  214. ፍረህይወት ኮነ ምህረቱ
  215. መስከረም ኮነ ምህረቱ
  216. ቅድስት ኮነ ምህረቱ
  217. ዘይሰድ ኢሳ አወል
  218. ተስፋዬ ወልዱ ፍስሃ
  219. ሰብለወንጌል ዘውዴ ዋለ
  220. ዳንኤል ዘውዴ ዋለ
  221. ሙሉቀን ዘውዴ ዋለ
  222. ብርሃኑ ዘውዴ ዋለ
  223. ጌትነት ዘውዴ ዋለ
  224. ታምራት ዘውዴ ዋለ
  225. አምባው ሰገድ አብርሃ
  226. ብርነሽ ሐጎስ ካህሳይ
  227. ህሊና አምባው ሰገድ
  228. ብሩክ አምባው ሰገድ
  229. ሜሮን ገ/ስላሴ ገብሩ
  230. ሳባ ኪሮስ ወ/ገብርኤል
  231. አፀደ ገ/ስላሴ ገብሩ
  232. አብርሃ ገ/ስላሴ ገብሩ
  233. ያሬድ ሰገድ አብርሃ
  234. ክብሮም ሰገድ አብርሃ
  235. ፀዳለ ሰገድ አብርሃ
  236. ፅጌ ሰገድ አብርሃ
  237. ፀሐይነሽ ሰገድ አብርሃ
  238. ተክለአብ ዘርአብሩክ ዘማርያም
  239. ፅጌረዳ ደርበው አዳነ
  240. ዘርአብሩክ ዘማርያም ረዳ
  241. ሂሩት ፀጋዬ ገ/መድህን
  242. አቤል ተክለአብ ዘርአብሩክ
  243. ምህረትአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
  244. ሠላማዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
  245. ፀጋዘአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
  246. ሣምራዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
  247. ዳንኤል ደርበው አዳነ
  248. ሠላዊት ደርበው አዳነ
  249. ሄሳን ደርበው አዳነ
  250. ኤደን ደርበው አዳነ
  251. ጌታሁን ቱጂ ደበላ
  252. ምኞት ብርሃኑ አበራ
  253. ሮዳስ ጌታሁን ቱጂ
  254. አዴራት ጌታሁን ቱጂ
  255. ሲሳይ ቱጂ ደበላ
  256. እመቤት ቱጂ ደበላ
  257. ጋሻው ብርሃኑ አበራ
  258. አዲሱ ብርሃኑ አበራ
  259. ሠላም ብርሃኑ አበራ
  260. ክብረወሰን ብርሃኑ አበራ
  261. ዘለቀ ልየው ካሳ
  262. ግንቻየው አድሮ ኃይሉ
  263. ዮሐንስ ዘለቀ ልየው
  264. ሊዲያ ዘለቀ ልየው
  265. ጥሩአለም አድሮ ኃይሉ
  266. ዮሴፍ አድሮ ኃይሉ
  267. ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
  268. ተናኜ እሸቴ አዳፍሬ
  269. ሠላማዊት ያዴሳ ሚዴቅሳ
  270. ገመቺሳ ያዴሳ ሚዴቅሳ
  271. ብልሴ ያዴሳ ሚዴቅሳ
  272. መኮንን ሚዴቅሳ ዲባባ
  273. በጂጌ ሜዴቅሳ ዲባባ
  274. ሽታዬ ሚዲቅሳ ዲባባ
  275. ፅጌ ሚዴቅሳ ዲባባ
  276. ልኪቱ ሞሲሳ ቦኮ
  277. ከበደ ደጀኔ ገለታ
  278. ፍስሐ ደጀኔ ገለታ
  279. የሻነው ደጀኔ ገለታ
  280. ዘላለም ደጀኔ  ገለታ
  281. ትዕግስት ደጀኔ ገለታ
  282. መታሰቢያ ደጀኔ ገለታ
  283. ሠናይት ደጀኔ ገለታ
  284. መላኩ ግርማ ገብሬ
  285. እህተ ቱኒ ኦርጋጋ
  286. ብርሃኑ ግርማ ገብሬ
  287. ጌትነት ግርማ ገብሬ
  288. አብርሃም ግርማ ገብሬ
  289. ዳዊት መኮንን ተመስገን
  290. እሴታ ባረጋ ሽራጋ
  291. አሚን ዳዊት መኮንን
  292. ዘሪሁን ዳዊት መኮንን
  293. ዜና መኮንን ተመስገን
  294. ማርታ መኮንን ተመስገን
  295. መኮንን ተመስገን የሽታ
  296. ፍሬሕይወት ማሞ አና
  297. መቅደስ ባረጋ ሽራጋ
  298. ብርሃኑ ባረጋ ሽረጋ
  299. ቅጣው ባረጋ ሽራጋ
  300. ባረጋ ሽራጋ ሽራጋ
  301. አስፋው ስዩም ታፈረ
  302. ማርታ የማነህ ተስፈሚካኤል
  303. መስፍን ስዩም ታፈረ
  304. መንገሻ ስዩም ታፈረ
  305. አንባቸው ስዩም ታፈረ
  306. ሂሩት ስዩም ታፈረ
  307. ሠላማዊት ግርማ ፈለቀ
  308. በፀሎት አበበልኝ ተስፋዬ
  309. ኪሮስ ገ/መድህን ገ/ተክለ
  310. ትዕግስት ተስፋዬ ፊታሞ
  311. ሊዲያ ተስፋዬ ፊታሞ
  312. ሐዲያወርቅ ተስፋዬ ፊታሞ
  313. ታሪኩ አበበ ፊታሞ
  314. ፍስሃ አበበ ፊታሞ
  315. ማርክስ አበበ ፊታሞ
  316. ምንአለ አበበ ፊታሞ
  317. ዘይነባ እሸቱ ኃይሌ
  318. ኑርሃን ጌታቸው አሰፋ
  319. ሐይመን ጌታቸው አሰፋ
  320. ሰሚሩ ጌታቸው አሰፋ
  321. ኢምራን ጌታቸው አሰፋ
  322. የንጉስነሽ አሰፋ ሀምዛ
  323. መንገሻ አሰፋ ሃምዛ
  324. መሰለ አሰፋ ሃምዛ
  325. ልዑልሰገድ አሰፋ ሀምዛ
  326. መሐመድ አሰፋ ሀምዛ
  327. ናስር እሸቱ ሃይሌ
  328. ዛህር እሸቱ ሃይሌ
  329. መሐመድ እሸቱ ሀይሌ
  330. ራቢያ እሸቱ ሃይሌ
  331. ምፅላል ሃይሉ አለማየሁ
  332. ጌጤ ማቲዮስ ገ/ኪዳን
  333. ትዕግስት በላቸው በየነ
  334. ሱራፌል በላቸው በየነ
  335. ሰላማዊት በላቸው በየነ
  336. አበባየሁ ዘበነ ተኮላ
  337. ማሚቱ በየነ ገ/ዮሐንስ
  338. አዳነ ተሰማ በረሳ
  339. ታሪኩ ተሰማ በረሳ
  340. ሲሳይ ተሰማ በረሳ
  341. ተፈሪ ተሰማ በረሳ
  342. ዜና ተሰማ በረሳ
  343. ሙሉጌታ ተሰማ በረሳ
  344. እመቤት ተሰማ በረሳ
  345. ጠጅነሽ ጎሳዬ በረሳ
  346. አንለይ አሳምነው ተሰማ
  347. ራሄል ገበደ ኃ/ማርያም
  348. ናርዶስ አንለይ አሳምነው
  349. ፍፁም አሳምነው ተሰማ
  350. ማናዬ አሳምነው ተሰማ
  351. ይርጋለም አሳምነው ተሰማ
  352. ፍፁም ከበደ ኃ/ማርያም
  353. በኃይሉ ከበደ ኃ/ማርያም
  354. ሱራፌል ከበደ ኃ/ማርያም
  355. ቢኒያም ከበደ ኃ/ማርያም
  356. መስፍን ከበደ ኃ/ማርያም
  357. እመቤት ከበደ ኃ/ማርያም
  358. መሰረት መንግስቱ በየነ
  359. ሠላማዊት ማሩ ፍቅሩ
  360. ፍቅርተ ማሩ ፍቅሩ
  361. ስንታየሁ ወይም አሰለፈች ማሩ ወርዶፋ
  362. በቀለች ማሩ ወርዶፋ
  363. ጥሩወርቅ መንግስቴ በየነ
  364. ገ/መድህን ገ/የሱስ ስብሃት
  365. ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የሱስ
  366. ንብረት ገ/መድህን ገ/የሱስ
  367. ማሞ ኪሮስ በዛብህ
  368. ራሄል አስረስ መኮንን
  369. አዶኒያስ ማሞ ኪሮስ
  370. ብሩክ ማሞ ኪሮስ
  371. ዳግም ማሞ ኪሮስ
  372. ኢዮስያስ ማሞ ኪሮስ
  373. ናሆም ማሞ ኪሮስ
  374. ደሳዊ ማሞ ኪሮስ
  375. ኪሮስ ገ/ህይወት በርሄ
  376. አለም ኪሮስ በዛብህ
  377. ፅጌ ኪሮስ በዛብህ
  378. ፋና ኪሮስ በዛብህ
  379. አፀደ ኪሮስ በዛብህ
  380. አብይ አስረስ መኮንን
  381. ቤተልሄም አስረስ መኮንን
  382. ሂሩት አስረስ መኮንን
  383. ፀደይ አስረስ መኮንን
  384. ሸዋዬ መስፍን አበራ
  385. ኤልዳና ስንሻው አለምነህ
  386. አርሴማ ስንሻው አለምነህ
  387. ምስጋና ይሳቅ ገድባ
  388. በረከት ይሳቅ ገድባ
  389. የመከረ መኮንን ተሰማ
  390. ማራማዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
  391. መቅደላዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
  392. ቤተል ዳዊት ኢትዮጵያ
  393. ወለላ ተስፋዬ ብሩ
  394. ተፈሪ ኢትዮጵያ መኮንን
  395. ፍሪው ኢትዮጵያ መኮንን
  396. ግሩም ኢትዮጵያ መኮንን
  397. ትዕግስት ኢትዮጵያ መኮንን
  398. ውቢቱ ኢትዮጵያ መኮንን
  399. ለምለም ኢትዮጵያ መኮንን
  400. ፀሐይነሽ መንግስቱ አዳል
  401. መቅደስ መኮንን ተሰማ
  402. እሸቱ ግረፍ አስታክል
  403. ብስኩት ደመቀ ታከለ
  404. ማየት እሸቱ ግረፍ
  405. ቤተል እሸቱ ግረፍ
  406. ኢዮስያስ እሸቱ ግረፍ
  407. ታደሰ ደመቀ ታከለ
  408. በኃይሉ ደመቀ ታከለ
  409. ብርሃኑ ደመቀ ታከለ
  410. ልፍነሽ ገለታ ዳዲ
  411. እቴነሽ ግረፍ አስታክል
  412. በላይነሽ ግረፍ አስታክል
  413. ዘውዱ ግደይ ካህሲ
  414. በረከት ተመስገን ስዩም
  415. ሚሚ ተመስገን ስዩም
  416. ካህሳይ ጉልላት አለመ
  417. ሰመረ ግደይ ካህሲ
  418. ኢሊኑ ግደይ ካህሲ
  419. ምህረት ገ/መድህን ገ/የስ
  420. ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የስ
  421. ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ
  422. ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማ
  423. ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል
  424. አዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ
  425. ምፍአም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  426. ነፃ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  427. ዎው ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  428. ኤምዲ ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  429. ዲ ኤች ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Museveni Warns Egypt As Nile War Looms

$
0
0

President Yoweri Museveni has sternly warned the Egyptian “government and other groups” against making “chauvinist and irrational statements” in the wake of Ethiopia’s decision to construct a multi-billion dollar electricity dam, Chimp Corps report ….

Museveni writes a condolence message at the funeral ceremony of departed Ethiopia President Meles Zenawi. Museveni maintains close ties with Ethiopia (INTERNET PHOTO)Museveni writes a condolence message at the funeral ceremony of departed Ethiopia President Meles Zenawi. Museveni maintains close ties with Ethiopia (INTERNET PHOTO)

“I have seen in the print media statements coming out of Egypt regarding the commendable work of the Government of Ethiopia of building dams for electricity in that country,” said Museveni.

 

“This is what the whole of Africa needs to do.  That is one reason the economy of Ethiopia has been growing in double digits.  It is, therefore, advisable that the new Government of Egypt and some chauvinistic groups inside Egypt should not repeat the mistakes of the past Egyptian Governments,” he added.

 

Museveni said Africa will not allow Egypt to continue hurting Black Africans, warning “Egypt should not repeat mistakes of past leaders.”

 

The President was speaking shortly after the reading of the 2013/14 national budget at Kampala Serena Hotel on Thursday evening.

 

Analysts say Museveni’s statement blew the cover off the simmering tensions between Uganda and Ethiopia on one hand and Egypt on the other.

 

The Grand Ethiopian Renaissance Dam, formerly known as the Millennium Dam and sometimes referred to as Hidase Dam, is an under-construction gravity dam on the Blue Nile River in Ethiopia.

 

It is in the Benishangul-Gumuz Region of Ethiopia, about 40 km (25 mi) east of the border with Sudan. At 6,000 MW and 63 billion cubic meters, the dam will be the largest hydroelectric power plant in Africa when completed, as well as the 13th or 14th largest in the world sharing the spot with Krasnoyarskaya.

 

The potential impacts of the dam have been the source of regional controversy. The Government of Egypt, a country which relies heavily on the waters of the Nile, protests the dam and its political leaders have discussed methods to sabotage it, including arming Ethiopian rebels.

 

“I confirm that all options are open to deal with this subject,” Egypt President Mohammed Morsi told hundreds of his supporters late on Monday.

 

“If a single drop of the Nile is lost, our blood will be the alternative. We are not warmongers, but we will never allow anyone to threaten our security.”

 

On June 3, while discussing the International Panel of Experts report with President Mohammad Morsi, Egyptian political leaders suggested methods to destroy the dam, including support for anti-government rebels.

 

The discussion was televised live without those present at meeting aware.

 

Ethiopia requested that the Egyptian Ambassador to explain the meeting.

 

Morsi’s top aide apologized for the “unintended embarrassment” and his cabinet released a statement promoting “good neighborliness, mutual respect and the pursuit of joint interests without either party harming the other.”

 

An aide to the Ethiopian Prime Minister stated that Egypt is “…entitled to day dreaming” and cited Egypt’s past of trying to destabilize Ethiopia.

 

Morsi reportedly believes that is better to engage Ethiopia rather than attempt to force them.

 

However, on 10 June 2013, Morsi said that “all options are open” because “Egypt’s water security cannot be violated at all,” clarifying that he was “not calling for war,” but that he would not allow Egypt’s water supply to be endangered

 

Egypt and Sudan fear a temporary reduction of water availability due to the filling of the dam and a permanent reduction because of evaporation from the reservoir.

 

The reservoir volume is about equivalent to the annual flow of the Nile at the Sudanese-Egyptian border (65.5 billion cubic meter). This loss to downstream countries would most likely be spread over several years.

 

The dam will retain silt. It will thus increase the useful lifetime of dams in Sudan – such as the Roseires Dam, the Sennar Dam and the Merowe Dam – and of the Aswan High Dam in Egypt. The beneficial and harmful effects of flood control would affect the Sudanese portion of the Blue Nile, just as it would affect the Ethiopian part of the Blue Nile valley downstream of the dam.

 

Museveni speaks out

 

Museveni said leaders of Egypt should not be victims of the “misguided policies of past leaders.”

 

He further stressed that threat of the Nile is not the construction of dams but the “lack of electricity and underdevelopment in the tropics.”

 

“The biggest threat to the Nile is continued under-development in the tropics i.e. lack of electricity and lack of industrialization.  On account of these two, peasants cut the bio-mass for fuel (firewood – enku) and invade the forests to expand primitive agriculture.  Here in Uganda, the peasants destroy 40 billion cubic metres of wood per annum for firewood.  They also invade the wetlands (ebisaalu, ebitoogo, entobazi, ebifuunjo, ebisharara) to grow rice,” he noted.

 

“This interferes with the transpiration that is crucial for rain formation.  Our experts have told me that 40 percent of our rain comes from local moisture – meaning from our lakes and wetlands,” said Museveni, adding, “That is why, for instance, West Nile and West Acholi have got more rain than Karamoja being on the same latitude notwithstanding.  It is, apparently, on account of the huge wetlands in South Sudan, the forest in Congo and the wetlands in Uganda.”

 

Ironically, said Museveni, the Egyptians wanted to drain the wetlands in South Sudan through the Jonglei canal.

 

“It was one of the causes for the people of South Sudan to wage war against Khartoum, which was collaborating with the Egyptian Government’s misguided and dangerous policies of that time,” he added.

 

Therefore, said Museveni, the threat to the Nile is lack of electricity in the tropics and lack of industrialization thereof.

 

“Electrification so that people stop using wood fuel and industrialization so that people shift from agriculture to industry and services is the correct way.”

 

Museveni also pointed to unknown diplomatic efforts aimed at persuading Egypt not to pursue the path of war.

 

“I have given these views to the past Egyptian Governments and to the present one.  Therefore, it is advisable that those chauvinistic statements coming out of Egypt are restrained and through the Nile Valley Organization rational (not emotional and informed statements) discussions take place.”

 

“No African wants to hurt Egypt; however, Egypt cannot continue to hurt black Africa and the countries of the tropics of Africa,” he concluded his speech.

 

Ethiopia boasts one of the most advanced and deadliest armies on the continent.

 

The battle-hardened army derives its unwavering determination to protect its strategic interests right from the late 1980s when it resisted the wave of colonialism that swept Africa.

 

Responding to Morsi’s threats recently, Ethiopia’s premier, Hailemariam Desalegn, the construction of the Grand Renaissance Dam would was “unstoppable.”

 

“All options include a war. I don’t think they will take that option unless they go mad,” warned Hailemariam, adding, “I urge them to abandon such an unhelpful approach and return to dialogue and discussion.”

 

Observers say Morsi is fanning anti-Ethiopia sentiments to divert attention from the resistance facing his unpopular domestic policies.

 

On Thursday evening, news came in that the Ethiopian Parliament had voted unanimously to repeal 1929 Nile water treaty that had granted Egypt the lion’s share of the Nile waters.

 

East Africa had criticized the treaty as a colonial relic considering that Egypt is guaranteed access to 55.5bn cubic metres of water, out of a total of 84bn cubic metres.

 

NILE WAR

 

Interestingly, a Nile treaty signed by the upper riparian states in 2010, the Cooperative Framework Agreement, has not been signed by either Egypt or Sudan, as they claim it violates the 1959 treaty which gives Sudan and Egypt exclusive rights to the Nile’s waters.

 

The Nile Basin Initiative provides a framework for dialogue among all Nile riparian countries.

 

Egypt, Ethiopia and Sudan established an International Panel of Experts to review and assess the study reports of the dam. The panel consists of 10 members; 6 from the three countries and 4 international in the fields of water resources and hydrologic modelling, dam engineering, socioeconomic, and environmental.

 

The panel held its fourth meeting in Addis Ababa in November 2012. It reviewed documents about the environmental impact of the dam and visited the dam site.

 

The panel submitted its preliminary report to the respective governments at the end of May 2013. Although the full report has not been made public, and will not be until it is reviewed by the governments, Egypt and Ethiopia both released details.

 

The Ethiopian government stated that, according to the report, the dam meets international standards and will be beneficial to Egypt, Sudan and Ethiopia. According to Egyptian government, the report found that the dimensions and size of the dam should be changed.

 

 

At 4,132 miles from its source in Lake Victoria, the Nile is the world’s longest river with its main two tributaries – the White Nile and Blue Nile, flowing from Ethiopia before joining at Sudan’s Capital, Khartoum


በወገኖቻችን ስደት ላይ ስለሚሰማው የሰሞኑ ፌዝና ቧልት ጥቂት ስለማለት

$
0
0

ዶ/ር ዘላለም ተክሉበሰሞኑ ከዓባይ ተፋሰስ ፖለቲካ ቀጥሎ ታላቁ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ  ከሃገራችን በመቶ ሺዎች ተሰደው ስለሚወጡ ወገኖቻችን መሆኑ ይገነዘቧል….. ከ”መለስ ራዕይ” አስፈጻሚው “ጠ/ ሚንስትር” በተዋረድ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንደ ገደል ማሚቶ  በሚስተጋባው ዘገባ፣ ወገኖቻችን ከአረብ ሃገራት እስከ ደቡብ አፍሪካ፣አውሮጳና አሜሪካ ድረስ ህጋዊና ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ተሰደው የሚኮበልሉት “ባደገችው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያሉትን የስራና የንግድ ዕድሎች አሟጠው ሳይገነዘቡና ሳይሞክሩ” እንደሆነ እየተነገረ መሆኑ ሁላችንን እያስስገረመን እያስደመመን ይገኛል::

መቼስ እደዚህ ዓይነት ሽምጥጥ ያለ ሽወዳ ለህወሐት መንግስት አዲስ አይደለም:: የዚህን የተቀናጀ ፕሮፖጋንዳ ስመለከትና ሳነብ በ 2011 መጨረሻና 2012 መጀመሪያ አካባቢ በዚሁ ጉዳይ ያደረኩት አነስተኛ የዳሰሳ ጥናት ትዝ አለኝ:: በዚህ ጥናት ላይ ያገኘሁት መረጃ አሁን እየተለፈፈ ካለው አሰልቺ ድራማ ጋር አልጣጣም ስላለኝ ለናንተ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ::

ጥናቱ የተካሄደው ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከጥቅምት እስከ ታህሳስ 2011 ቀጥታ በተሰበሰበ መረጃ (Primary data) ነበር:: የናሙና መረጃው ከአዲስ አበባ ብቻ የተሰባሰበበት ምክንያት ሁሉንም የአገሪቱ ክልሎች የሚወክሉ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ሀብታምና ደሃዎች፣ ነጋዴውዎችና የመንግስት ሰራተኞች፣ ሥራአጥና ጎዳና ተዳዳዎች ሁሉ የሚኖሩበት ከተማ በመሆኑ ነው::  ከዚህ በተጨማሪም መረጃውን ለማሰብሰብ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ተቋማት ከሌሎቹ አካባቢዎች በተሻለ መልኩ መገኘት በመቻሉ ነው:: መረጃውም የተሰበሰበው ለ 200 ግለሰቦች የስልክ ቃለመጠይቅ ግብዣ ተደርጎላቸው ፍቃደኛነታቸውን ከገለጹ 151 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከተገኘ ምላሽ ነበር:: የናሙና መረጃው የተሰበሰበው Stratified Random Sampling በሚባል የስታቲስቲክስ ዘዴ ነበር:: በዚሁ ዘዴ ምላሻቸውን ከሰጡት ሰዎች ውስጥ በጾታ 64 በመቶውቹ ወንዶችና 36 በመቶዎቹ ደግሞ ሴቶች ነበሩ:: በዕድሜ አንጻር 41 በመቶዎቹ ከ 21-45 ዓመት፣ 35 በመቶዎቹ ከ 46-60 ዓመት፣ እንዲሁም 23 በመቶ የሚሆኑት ከ21 ዓመት በታችና ከ60 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸው ነበሩ:: በትምህርት ደረጃም ሲደለደል ከናሙናው ውስጥ 49 በመቶዎቹ የ12ኛ ክፍልን ያላጠናቀቁ፣ 29 በመቶዎቹ የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ፣ 19 በመቶዎቹ ሰርተፊኬት/ ዲፕሎማ ያገኙ፣ 3 በመቶዎቹ በጀመሪያ ዲግሪና 1 በመቶዎቹ በከፍተኛ ዲግሪ የተመረቁ ነዋሪዎች ነበሩ::

ይህ ጥናት ያተኮረው አጠቃላይ የሃገሪቱን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ዕድገትና ድህነት ቅነሳ ሁኔታን ለመዳሰስ ነበር::  ስደትን ብቻ በተመለከተ በተናጠል ለጥናቱ ተካፋዮች የቀረቡላቸው ጥያቄዎች ( 1) እድሉን ብታገኝ/ኚ ከሃገርህ/ሽ ተሰደህ/ሽ መውጣት ትፈልጋለህ/ሽ አትፈልግም/ጊም? (2) ለመሰደድ የምትፈልገው/ጊው በምን ምክንያት ነው? የሚሉ ነበሩ:: ለእነዚህን ሁለት ጥያቄዎች የተሰጠው ምላሽ ሲተነተን የተገኘው ውጤት በጣም አስደንጋጭ ሆኖ ነበር ያገኘሁት:: የተሰበሰበው መረጃ ተተንትኖ ከዚህ በታች በቀረበው ቻርት መሰረት ሦስት አራተኛው ወገኖቻችን  (3/4ኛው) አገራቸውን ጥለው ለመሰደድ ምንም እንደማያመነቱ ያመለከቱ ሲሆን የመሰደዳቸው ዋነኛው ምክንያትም 66 በመቶ በኢኮኖሚ ችግር እንዲሁም 14 በመቶ ደግሞ በሀገራቸው ያለው ዕድልና ተስፋ መሟጠጥ እንደሆነ ታውቋል:: ተምሮ ወይም ጥሪት አካብቶ ለመመለስ የሚመኘውም  ከአምስቱ ዜጋ አንዱ ብቻ እንደሆነም ታውቋል::

Ethiopian immigrants flow

ትንሽም ቢሆን ካገኘነው ሳይንሳዊ መረጃ እንደተረዳሁት ህዝባችን የሚሰደደው “ስላደገችው ኢትዮጵያ” ግንዛቤ በማጣቱ ሆኖ አላገኘሁትም::   ኢኮኖሚው በእርግጥ ቢያድግ ኖሮ አብዛኛው ህዝብ በሀገር ውስጥ ሰርቶ የማግኘት፣የመሻሻልና በደስታ የመኖር ዕድልና ተስፋው ባደገ ነበር:: በእርግጥ ህዝቡ በሃገሩ ቢተማመን ኖሮማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በህገ ወጥ መንገድ ወደ የመን፣ ሊቢያ፣  ሊባኖስ፣ ሳውዲ አረቢያና ሌሎች አረብ ሃገራት ተሰደደው በየእስር ቤቶችና በየበረሃው ባልተንገላቱ፣ ባልተደበደቡና ባለተደፈሩ፣የፈላ ውኃ በአናታቸው ባልተደፋ፣ በእምነታቸው ሰበብ እስር ቤት ባለተወረወሩ ነበር:: የተወራለት የኑሮ መሻሻልና ሰርቶ የማደግ ተስፋ እውነት በሃገሪቱ ቢኖርማ ኖሮ እህታችን ዓለም ደቻሳ ወደ ሃገሯ አልመለስም እያለች አስፋልት ዳር እንደ እንስሳ ስትጎተት የዓለም ህዝብ በቪዲዮ ባላያትና በመጨረሻም ህይወቷን ማጣቷ ባልተሰማ ነበር::  ተስፋውና ዕድገቱ እንደተፎከረበት ቢሆንማ ከኖርዌይ በግዳጅ ወደሃገራቸው ሊባረሩ የተዘጋጁ ብዙ ወገኖቻችን ላለመመለስ ባለመኑና ባልተማጸኑ ነበር::

ለኔ ከህዝባችን ውስጥ ሦስት አራተኛው “በሃገሩ ያለውን አበረታች ዕድል ባለማወቅ ነው የሚሰደደው” የሚለው መከራከሪያ ፌዝና ቡዋልት እንጂ ውሃ የሚቋጥር እውነታ ሆኖ አላገኘሁትም::

እናንተስ?


8ኛውን አመት የሰኔ 1997 ሰማዕታት የምናስታውሰው የተሰውለትን ክቡር አላማ ለማሳካት ዝግጁነታችንን እየገለጽን ነው

$
0
0

የምርጫ 1997 ውጤት በወያኔ/ኢህአደግ መሰረቁን ተከትሎ ተቃውሞአቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡት ዜጎቻችን ላይ በመለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው አጋአዚ ጦር ፋሽስታዊ እርምጃ መውሰድ የጀመረበት ሰኔ 1 1997 8ኛ አመቱን ባለፈው ቅዳሜ አገባዷል…..
በግፍ የተጨፈጨፉትን የሰኔ 97 ሰማዕታቶቻችንን ባሰብን ቁጥር ሁሌም በአይነ ህሊናችን የሚመላለሰው፣ አገርን ከወራሪ ጠላት ለመከላከል በሚያስችል ወታደራዊ አቅምና ዝግጅት እስከ አፍንጫው ድረስ ታጥቆ የነበረውና; በመላው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተርመሰመሰ በወገኖቻችን ላይ ያን ሁሉ የተኩስ ናዳ ሲያዘንብ የሰነበተው የአጋአዚ ጦርና በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የቴሌቪዥን መስኮቶች የተመለከትናቸው በደም የተጨመላለቁ አካላት ምስል ፤ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ከተስተጋባው የሟቾች ቤተሰቦች የድረሱልን ለቅሶና ዋይታ ጋር ተደበላልቆ ነው። “መሪያችሁን ወጥታችሁ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ምረጡ” ብሎ የፈቀደ ሃይል ሲሸነፍ: ታንክና መተረየስ የታጠቁ አልሞ ተኳሾችን ያዘምትብናል ብሎ ያሰበ አልነበረምና ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነበት አገር ባለቤት ለመሆን ተስፋ ሰንገው ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት ከቤታቸው የወጡ ዳግም ላይመለሱ እስከወዲያኛው ተለዩን።          ፋሽስት ጣሊያን አገራችንን በቅኝ ግዛትነት የራሷ ለማድረግ በነበራት ህልም ለነፃነቱ ቀናዕ የሆነውን ህዝባችንን በፍርሃት ለማሽመድመድ የሩዶልፍ ግራዚያኒ ጦር የካቲት 12 ቀን 1928 በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፈጸመው የጭካኔ እርምጃ ፈጽሞ ባልተናነሰ አረመኔያዊነት ሰኔ 1 ቀን 1997 ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ያ አሰቃቂ ጭፍጨፋ፡ ታዳጊዎችን ከአዋቂ ፤ አዛውንትን ከጎልማሳ፤ አካለ ስንኩላንን ከጤነኛ ፤ ሴቶችን ከወንዶች መለየት ሳያስፈልግ አደባባይ የወጣውን ሁሉ “ የትግሬ ጠላትና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ናቸውና በሉዋቸው” የሚል ትዕዛዝ ባስተላለፉ የዘር ጥላቻ ሂሊናቸውን ባናወዛቸው ጥቂት “ከትግራይ ህዝብ አብራክ የተገኘን እንቁዎች ነን” በሚሉ ዘረኞች የተቀነባበረ እንደሆነ ታወቃአል።
መለስ ዜናዊ ፤ በረከት ስሞን ፤ ሳሞራ ይኑስና ታደሰ ወረደ ከነዚህ ቀንደኛ ዘረኞች ዋንኞቹ እንደሆኑ ሲታወቅ “የተጭበረበረው የምርጫ ድምጻችን ይመለስልን!! ፤ እንዲመሩን የመረጥናቸው ሰዎች ያስተዳድሩን !!” በማለት ጥያቄ ያነሳውን ህዝብ ለመቅጣት ሲባል የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በሙሉ በአንድ ዕዝ ሰንሰለት ሥር ገብቶ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመለስ ዜናዊ እንዲሆን ምርጫው በተካሄደበት የግንቦት 7/ 1997 ምሽት መመሪያና አዋጅ በሬዲዮና በቴሌቭዥን በራሱ በመለስ ዜናዊ ካስነገሩ ቦኋላ: እስከዛሬ ወደ አፎቱ ያለተመለሰ የጥቃት ሳንጃቸውን በህዝባችን ላይ መዘዋል።
ዘረኝነት ምን ያህል ጭካኔ ሊያመነጭ እንደሚችል ትምህረት ሰጥቶ ባለፈው የሰኔ 97 ጭፍጨፋ ሰለባ ከሆኑት መቶዎች ውስጥ፡ መርካቶ አካባቢ ይጫወትበት የነበረውን የጨርቅ ኳስ አንስቶ ለመሸሽ ጎንበስ ባለበት ተደፍቶ የቀረው የ10 አመቱ ታዳጊ ህጻን እንዲሪስ፤ ደብተሩን ተሸክሞ ከትምህረት ቤት ሲመለስ ፍልውሃ አካባቢ የተገደለው የ14 አመቱ ነብዩ አለማየሁ፤ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፊት ለፊት ግንባሯን በጥይት ተመታ የተገደለቺው የ18 አመቷ ወጣት ሽብሬ ደሳለኝ፤ ባሌን አትውሰዱብኝ በማለታቸው ደረታቸውን በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የ8 ልጆች እናት ወ/ሮ እቴነሽና ቀድሞ በተተኮሰ ጥይት የወደቀውን ወንድሙን አብረሃም ይልማን አስከሬን ቀና ለማድረግ ሲሞክር ጀርባውን በጥይት ተበሳስቶ የተገደለው የፈቃዱ ይልማ ወላጅ ቤተሰቦች በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያሰሙት የድረሱልን እሮሮና ለቅሶ ዛሬም ድረስ ሂሊናችን ውስጥ እያንቃጨለ እረፍት ይነሳናል። በተለይም ደግሞ ድንገተኛ ሞት ከረጂሙ የጥፋት አላማው ከቀጨው መለስ ዜናዊ በስተቀር የዚህ ሰቆቃ ፈጻሚዎች ዛሬም ድረስ በሰሩት ወንጀል ፍትህ ፊት ሳይቀርቡና ተገቢውን ቅጣታቸውን ሳያገኙ መቅረታቸው ያንገበግበናል፤ ይቆጨናል፤ እስከመጨረሻው የድል ቀን ድረስ ፀንተን እንድንታገላቸው ሞራላችንንና ወኔያችንን በየደቂቃው ይሰቀሰቃል።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በምርጫ 97 የተነጠቅነውን የህዝብ ድል ለማስመለስና ወያኔ በአገዛዝ ዘመኑ በህዝባችን ላይ ለፈጸመው ሰቆቃና አገራችን ላይ ለፈጸማቸው ወንጀሎች ህግ ፊት ቀርቦ ተጠያቂ እንዲሆን ለማድረግ ተግቶ እየታገለና እያታገለ ያለው ለነጻነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን መሰዋዕት የከፈሉ ወገኖቻችን አደራና የህዝባችን የነጻነት ጥማት ከሁሉም በላይ ስለሚያሳስበው እንደሆነ ደጋግሞ ገልጾአል።
ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ የአገራችንን ሉአላዊነት ለማፍረስና የህዝባችንን አንድነት ለመናድ የሚያደርገውን እኩይነት ተቃውሞ ሲታገሉ የታሰሩ፤ የተደበደቡ፤ የተገደሉና ለአካለ ጎዶሎነት የተዳረጉት ዜጎቻችን መስዋዕትነት መና ሆኖ እንዳይቀር እንዲሁም ከሰኔ 1997 እስከ ህዳር 1998 በአጋአዚ ጦር የተጨፈጨፉ የዲሞክራሲ ለውጥ አርበኞች አጥንትና ደም እንዳይፋረደን እያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ትግሉን ከዳር ለማድረስ እየተካሄደ ያለውን የነፃነት ትግል ለማገዝ ዛሬውኑ እንዲቀላቀለን ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪዉን ለያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ያቀርባል። አውራው እንደሞተበት ንብ እየተበታተነ ያለው የወያኔ ኢህአደግ አባላትና ደጋፊዎችም በጭፍጨፋ ወንጀል ተሳታፊ እስካልነበሩ ድረስ የሚመጣው ለውጥ ለነርሱም የተስፋና የነፃነት ዋስትና የሚሰጥ በመሆኑ ምንም ሳያቅማሙ የትግሉን ጎራ ዛሬውኑ እንዲቀላቀሉ ወገናዊ ጥሪውን ያስተላለፋል።
ወያኔ ላለፉት 22 አመታት በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ማስቆም የሚቻለው ወያኔን በማስወገድ ብቻ እንደሆነ አቋም የያዘው የግንቦት 7 ንቅናቄ አመራርና መላው አባላቱ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልጹት በታላቅ ብሄራዊ ስሜትና ኩራት ነው። ለሰኔ 97 ሰማዕታትና ለቤተሰቦቻቸው ከዚህ የበለጠ ቃልኪዳን የለምና። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!


በደቡብ ጎንደር ዞን መምህራን በደህንነት ሀይሎች ታፍነው ተወሰዱ

$
0
0
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደብረ ታቦር ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ መምህራን ትናንት ማታ እና ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሐይሎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል…
gondar_6

 

መምህር ታደሰ መንግስቴና መምህር ፈቃዱ ጌትነት የሚባሉ በ ፈቀደ እግዚ ኮሌጅ ውስጥ አስተማሪዎች ሲሆኑ መምህር አሸናፊ አለሙ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው።
አብይ ሃይሌ እና ማስረሻ የተባሉ ወጣቶችም እንዲሁ ታፍነው ተወስደዋል።
ታፍነው ከተወሰዱት መካከል የሁለቱ የቅርብ ጓደኛ የሆነ ወጣት እንደገለጸው ቤተሰቦቻቸው የአካባቢውን ፖሊሶች ሲጠይቁ ” የት እንደተወሰዱ አናውቅም” የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

“ፓርላማው ጥርስ አውጥቷል?”

$
0
0

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፓርላማ ውስጥ የመነቃቃት ስሜት መፈጠሩን የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች፤ የምክር ቤቱ አባላት በተለየ ሁኔታ መንቀሳቀስ እንደ ጀመሩ ይገልፃሉ፡፡ በፊት አንድ የሚኒስቴር መ/ቤት ያቀረበውን ሪፖርት አዳምጠው “የሚበረታታ ነው….”፣ “መልካም ጅምር ነው” የመሳሰሉ አስተያየቶች ሰጥተው ይሸኙ ነበር ይላሉ – ታዛቢዎች፡፡ አሁን ግን በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመስርተው መሞገት፣ የሰላ ሂስ መሰንዘርና ድክመቶችን መንቀስ ጀምረዋል፡፡

girma

 

“ፓርላማው ጥርስ እያወጣ ነው” ይላሉ፡፡ በዚህ የሚስማሙም የማይስማሙም የም/ቤት አባላት አሉ፡፡

“ፓርላማው ድሮም አሁንም ጥርስ የለውም” – አቶ ግርማ ሠይፉ -

በፓርላማ የመድረክ ተወካይ “ፓርላማው በቅርቡ ጥርስ ማውጣት ጀምሯል በሚለው አልስማማም” -ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ – “የፓርላማውን እንቅስቃሴ የማወዳድረው ከልጅ እንዳልካቸው ዘመን ጋር ነው” – ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋ – በአ.አ.ዩ የፍልስፍና መምህር “የፓርላማ አባላት አሁን እየሠሩ ያሉት ቀደም ሲል የሚሰሩትን ነው” – አቶ ታደሠ መሠሉ – የፓርላማ አባል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመድረክ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሠይፉ፤ ፓርላማው ጥርስ አውጥቷል በሚባለው ነገር እንደማይስማሙ ይናገራሉ፡፡

“ባይሆን ነቃ ነቃ ብሏል” ቢባል ይሻላል የሚሉት አቶ ግርማ፤ ፓርላማው ድሮም አሁንም ጥርስ እንደሌለውና ለማብቀልም ብዙ እንደሚቀረው ገልፀዋል፡፡ የፓርላማው መነቃቃት ከቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ህልፈት ጋር የተያያዙ ሊሆን እንደሚችል የገለፁት አቶ ግርማ፤ በፊት ጠ/ሚኒስትሩ ሁሉ ነገር ስለነበሩ የፓርላማው ሚና አነስተኛ ነበር ይላሉ፡፡ “አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃ/ማሪያም ደሣለኝ ግን አውቀውም ይሁን ሳይውቁ ፓርላማውን በእጅ አዙር የመቆጣጠር አዝማሚያ የላቸውም” የሚሉት አቶ ግርማ፤ የምክር ቤት አባላትም ይህን ዕድል በመጠቀም የሚፈልጓቸውን አካላት ለመቆጣጠር እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን የፖሊሲ ለውጥ ባይኖርም ሹፌሩ ሲለወጥ በተወሠነ መልኩ ለውጥ እንደሚመጣ ጠቅሠው፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ የፓርላማውን መነቃቃት እንዲፈጠር ያምናሉ፡፡

ፓርላማው ጥርስ አወጣ የሚባለው መቼ ነው በሚል ተጠይቀው ሲመልሱም፤ “ጥርስ ማውጣት ማለት በስራ አፈፃፀሞች፣ የሚታዩ ጥፋቶችን ሞግቶ አስተማማኝ ድምፅ በመስጠት ሚኒስትሮችን ማስቀየር ሲችል ነው” ብለዋል አቶ ግርማ፡፡ ፓርላማው ይሄ ስልጣን ቢኖረውም ለበርካታ ጊዜያት እንዳልተጠቀመበት በመግለጽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠንከር ያሉ ውይይቶችን ማድረግ እንደጀመረ ተናግረዋል፡፡ “ሁሉም ሚኒስትሮች ሲመጡ ከፓርላማ ተወካዮች የሚቀርቡት ጥያቄዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከሩ መጥተዋል” ያሉት አቶ ግርማ፤ ቀደም ሲል “አበረታች ነው”፣ “ገንቢ ነው” በማለት የሚታወቁ የፓርላማ ተወካዮች፤ “ልክ አይደላችሁም”፣ “በደንብ አልሰራችሁም” ማለት መጀመራቸው ትልቅ ለውጥ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ ሆኖም “ጥርስ አውጥቷል” እስከሚለው አያደርስም ብለዋል፡፡ አቶ ግርማ አንድ ስጋት አላቸው፡፡ “የፓርላማ አባላቱ ዘንድ መነቃቃቱ የተፈጠረው ከጠ/ሚኒስትር ለውጥ ጋር ተያይዞ ነው የሚል አዝማሚያ ከታየባቸው ጠርናፊዎች ወደ ቀድሞ ዝምታቸው ሊመልሷቸው ይችላሉ” ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋ በበኩላቸው፤ “የአሁኑን የፓርላማ እንቅስቃሴ የማወዳድረው ከልጅ እንዳልካቸው ዘመን ጋር ነው” ይላሉ፡፡ “ከተሞክሮዎች እንደሚታወቀው አንድ ጠንካራ ሠው ከቦታው በሚነሳ ጊዜ የፖለቲካ ክፍተት ይፈጠራል” ያሉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ በዚህ ጊዜ የተለያዩ አካላት እንደሚበረቱ ገልፀው፤ የሀገራችን ፓርላማም እዛ ሠዓትና ወቅት ላይ እንዳለና ይህ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ እንደመጣ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ የፓርላማ እንቅስቃሴው ቀጣይነት ቢኖረው ጠቀሜታው የጐላ እንደሆነ የገለፁት ምሁሩ፤ “የእኔ ስጋት የተወሠነ ቡድን ወይም ሀይል ጫና አሣድሮ ይሄ ጭላንጭል እንዳይጠፋ ነው” ብለዋል፡፡ “የፓርላማው ስራ ሁለት ነው፤ አንዱ ህግ ማውጣት ሲሆን ሌላው የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን እየተከታተሉ የስራ አፈፃፀማቸውን መገምገም ነው” የሚሉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ አሁን እየታየ ያለው የፓርላማ አባላት እንቅስቃሴና ጠንካራ ሙግቶች በጣም አስገራሚ በመሆኑ ጅምሩን ልናበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡

“እኔ በሁኔታው በጣም እየተረገምኩ ነው፤ ይህን ሁሉ ጉልበት ከየት አመጡት? እስከዛሬ የት አስቀምጠውት ነበር?” ሲሉ የጠየቁት ምሁሩ፤ ይህንን ጠንካራ እንቅስቅሴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጋር የሚያያይዙት “አቶ መለስ አትናገሩ ብለዋቸዋል” ለማለት ሳይሆን ብዙ የሚያውቅ ሠው ባለበት ቦታ የሌሎች አንገት መድፋት በፖለቲካ ውስጥ የሚከሠትና የተለመደ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ “የፓርላማ አባላት ሁሉንም ነገር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያውቃሉ” ብለው ሥለሚያምኑ ለመናገር ድፍረት ያንሳቸው እንደነበር እገምታለሁ” ሲሉም አስረድተዋል፡፡ በተለይ አሁን ከፍተኛ ሙግትና ትችት እያነሱና በድፍረት እየታገሉ ላሉት ሴት የፓርላማ ተወካዮች ትልቅ አክብሮት እንዳላቸው የገለፁት ዶ/ሩ፤ በተለይም “ይህን ጉዳይ ሌላ ስም አጥቼለት ነው፤ ግን ሌብነት ነው” ሲሉ በሙስና በተጠረጠሩ ሙሠኞች ላይ ትችት ለሠነዘሩት ሴት የፓርላማ ተወካይ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡ ስለፓርላማው እንቅስቃሴ ከወዲሁ ድምዳሜ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡ የፓርላማውን እንቅስቃሴና ቀጣይነት ወደፊት የምናየው ይሆናል በማለት፡፡

የኢህአዴግን ፖሊሲ እደገፋለሁ የሚሉት በፓርላማ የግል ተመራጭ የሆኑት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፤ የፓርላማውን እንቅስቃሴ በተመለከተ የተለየ አስተያየት አላቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፓርላማው ጥርስ ማውጣት ጀምሯል በሚለው ጉዳይ አልስማማም ባይ ናቸው። ፓርላማው በፊትም መስራት ያለበትን ሥራ እየሰራ መሆኑንና አዲስ የተፈጠረ ነገር እንደሌለም ይናገራሉ። “እኔ ገና በግሌ ተወዳድሬ ፓርላማ ስገባ. አብዛኛው ወንበር የኢህአዴግ በመሆኑ ስጋት ገብቶኝ ነበር” ያሉት ዶ/ር አሸብር፤ የመጀመሪያው ስጋታቸው በአንድ ፓርቲ አብላጫ መቀመጫ የተያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሙግቶችና የሀሳብ መንሸራሸሮች አይኖሩም የሚል እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ ሌላው ስጋታቸው ደግሞ በግላቸው ተወዳድረው እንደመግባታቸው በፓርላማው ብቸኛና ባይተዋር እሆናለሁ የሚል እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ “ወደ ፓርላማ ስገባ የጠበቅሁትና ከገባሁ በኋላ ያገኘሁት ሁኔታ ግን በጣም ይለያያል” ያሉት ዶ/ር አሸብር፤ ፓርላማው ሥራ ከጀመረ በኋላ አዋጆች ከመፅደቃቸው በፊት ብዙ ክርክሮች ይደረጉ እንደነበር ተናግረዋል። በብዙዎቹ ሪፖርቶች ላይም ከፍተኛ ክርክሮች፤ ውይይቶችና አስተያየቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን በመግለጽ፤ ሰሞኑን የተለየ እንቅስቃሴ እንዳለ አድርጐ መናገሩ ትክክል አይደለም ብለዋል፡፡

በፓርላማው ወደ 16 ያህል ቋሚ ኮሚቴዎች እንዳሉ የጠቆሙት ዶክተሩ፤ እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ በተመደበባቸው መስሪያ ቤቶች ቁጥጥር፣ ግምገማና የመስክ ጉብኝት ሳይቀር በማድረግ ሃላፊቱን ሲወጣ መቆየቱንና አሁንም እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል። “በመሆኑም ፓርላማው በሙሉ ቁመናው እየሰራ ነው” ባይ ናቸው፡፡ሰዎች ጉዳዩን እንደ አዲስ የቆጠሩት ለምን እንደሆነ ሲያስረዱም፤ በፓርላማውና በሚዲያው በኩል ያለው ክፍተት እየጠበበ በመምጣቱና ሚዲያዎች የፓርላማውን እንቅስቃሴ በትክክል እየዘገቡ በመሆናቸው ነው ያሉት የፓርላማ ተወካዩ፤ ከበፊትም ጀምሮ እያንዳንዱ መስሪያ ቤት ወደ ፓርላማ ሲመጣ ተጨብጭቦለት ሳይሆን የሚሄደው በደንብ ተጠይቆ፤ ተገምግሞና ተፈትሾ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፓርላማ አባላት የመገዳደር አቅማቸው የጠነከረው የስራ ልምድ እየጨመረ ሲሄድ ከሚዳብር እውቀት እንጂ ምንም አዲስ ነገር አልተፈጠረም” ያሉት ዶ/ር አሸብር፤ “እኔ እንደሚገባኝ በፊት ፓርላማውና ሚዲያው የተገናኙ አልነበሩም፤ አሁን ሚዲያው የፓርላማውን ሙግትና ፍጭት አጉልቶታል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አለመኖር የተነሳ የፓርላማ ተወካዮች ከፍርሀት ተላቀው መናገር ጀምረዋል በሚለው ጉዳይ ፈፅሞ እንደማይስማሙ የገለፁት ዶ/ሩ፤ “እውነት ለመናገር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ፤ ሠዎች ሲናገሩ ሲከራከሩና ሀሣባቸውን ሲገልፁ የሚወዱ እንጂ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ አልነበሩም” ብለዋል፡፡ ምናልባት እንዲህ አይነት ፍርሀት የሚፈጠረው ከአቅምና ከእውቀት ችግር ይሆናል፤ በእውቀቱና በአቅሙ ሙሉ የሆነ ሠው ፍርሃት አያድርበትም ሲሉ አብራርተዋል። “እሳቸው እያሉ እንዴት እናገራለሁ -በጭንቅላትም፣ በልምድም በትምህርትም ይበልጡኛል ብሎ ቅድሚያ ተሸንፎ የገባ አባል ካለ፤ እሱን አላውቅም፤ ነገር ግን በሀሣብና በእውቀት ሙሉ ሆኖ ለቀረበና ለሚገዳደራቸው ሠው ተደስተው ተገቢውን ምላሽ ይሠጣሉ” ብለዋል ዶ/ር አሸብር፡፡ ፓርላማው በአሁኑ ሠዓት አገርን ማዕከል ያደረገ፣ የህዝብን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ክርክር እንጂ የተቃዋሚና የደጋፊ ፓርቲ የሚል አጀንዳ እንደሌለው የገለፁት ዶ/ሩ፤ አላማው ይህቺን አገርና ህዝቧን ከፍ ወዳለ ደረጃ ማድረስ በመሆኑ ድሮ ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው፤ አሁን ጥርስ እያወጣ ነው የሚለውን ትተን፣ በአገሪቱ እና በህዝቧ ጥቅም ላይ ፓርላማው አትኩሮ መስራቱን እንዲቀጥል ትኩረት ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በፓርላማ የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ታደሠ መሠሉም፤ ከዶ/ር አሸብር ሃሳብ ጋር ይስማማሉ፡፡

አሁን በፓርላማው እየተሰራ ያለው ድሮም የነበረ እንጂ አዲስ ነገር የለም ይላሉ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች አስፈፃሚ አካላትን የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመደገፍ ሀላፊነት ተሰጥቶታል ያሉት አቶ ታደሰ፤ እየሰራ ያለውም ይሄንኑ ነው ብለዋል፡፡ ምክር ቤቱ የጐደሉ የስራ አስፈፃሚ በጀቶችንና በአግባቡ ያልተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ መሞገቱ ከዚህ ቀደምም የሚያደርገው እንጂ አዲስ አይደለም ሲሉም አክለዋል፡፡ የፓርላማ አባላት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሚፈሩ አይናገሩም ነበር፤ አሁን በድፍረት መናገር ጀመሩ በሚባለው ጉዳይ ፈጽሞ እንደማይስማሙ የገለፁት አቶ ታደሠ፤ “ለሰው የተለየ ነገር የመሠለው ይህቺን አገር ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ሲታትሩ ያለፉትን የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር ራዕይ ለማሳካት የፓርላማው አባላት በእልህና በቁጭት መነሳሳታችን ነው” በማለት ብለዋል፡፡ ም/ቤቱ፤ ስራ አስፈፃሚውን ብቻ ሳይሆን የአስፈፃሚውን መሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጭምር ጠርቶ የማነጋገር ስልጣን አለው ያሉት የፓርላማ አባሉ፤ ጠ/ሚኒስትሩ ምክር ቤቱ እየጠራቸው ሪፖርትም ማብራሪያም ይሠጡ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ አቶ ታደሰ እንደሚሉት፤ የም/ቤት አባላቱ በየጊዜው በሚያገኙት ሥልጠና ልምዳቸውን እያካበቱ መምጣታቸው፣ ከባለራዕዩ መሪ ሞት ጋር ተዳምሮ በእልህና በወኔ እንዲንቀሳቀሱ አድርጓቸዋል፡፡ ይሄ ማለት ግን ድሮ አይንቀሣቀሱም፤ አይሠሩም ማለት እንዳልሆነ በመጥቀስ የፓርላማው እንቅስቃሴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም ብለዋል፡፡



Over 400 names of traders, officials, whose accounts were frozen, made public

$
0
0

ESAT News June 14, 2013

The Ethiopian Federal High Court on a letter written on May 21, 2013, number 134048, has ordered that the bank accounts, monies and cars of 429 government officials, businesspeople  and their family members be frozen and impounded…

The 429 people include suspects of corruption who are currently imprisoned and their family members. One of the frozen accounts is of investor Nega Gebregziabher and his families, Ephrem Nega Gebregziabher, Henok Nega Gebregziabher, Yetbarek Nega Gebregziabher, Selam Nega Gebregziabher, and Rahel Nega Gebregziabher. The bank accounts of Markneh Alemayehu, Chief Prosecutor of the Ethiopian Revenue and Customs Authority (ERCA), and his family members such as Yonatan Markneh Alemayehu, Elshadaye Markneh Alemayehu, Balgeti Alemayehu Wedano, Bafne Alemayehu Wedabo, Ayele Alemayehu Wedabo, Berhanu Alemayehu Wedabo, Abera Alemayehu Wedabo and Tigrest Alemayehu Wedabo, have also been frozen.

Similarly, the bank account of Siye Abraha, the incumbent’s former military chief and now an opposition, and the accounts of his brothers and sisters; Heluf Abraha Hagos, Asmelash Abraha Hagos, Asefa Abraha Hagos, Woldeselasie Abraha Hagos and Temnit Abraha Hagos, have all been frozen.

 

The list of the names of the 429 people, whose accounts have been frozen, can be viewed here http://goo.gl/ObypL


አንድነት ፓርቲ ለመድረክ ምላሽ ሰጠ፤ የተደበቀውን አፍረጠረጠው

$
0
0

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ በመሠረቱ ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) መድረክ እንዲመሠረትና አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ለመድረክ መፈጠርና መጎልበት በአደረገው ጉልህ ተሳትፎ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት መሆኑን መድረክም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው….

የግምገማው ግኝቶች በየትኛውም ገጽና ቦታ የመድረክ ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብና የስምምነት ሰነድ በመድረክ አባል ድርጅቶች በጋራና በሙሉ ስምምነት መጽደቃቸውን አላስተባበለም፡፡ አልካደምም፡፡ በተጨማሪም መድረክ እንደ አንድ የፖለቲካ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ ህሊና ውስጥ ከፍተኛ ተስፋን የፈጠረ ብቻ ሳይሆን አዲስ የጉዞና የአሠራር አቅጣጫን የቀየሰ መሆኑን ጭምር አንድነት ያውቀዋል፡፡ ያምንበታልም፡፡

መድረክ ከመቀናጀት ወደ ግንባር የተሸጋገረበት ሂደትም ብዙ ችግሮችና ድክመቶች ቢኖሩትም በአባል ድርጅቶች ሙሉ ስምምነትና ፍቃደኘነት መሆኑን አንድነት አምኖ የሚቀበለው እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም የመድረክ ድክመቶች፣ ስህተቶችና ችግሮች በሙሉ አንድነት ፓርቲም አብሮ የሚጋራውና የሚጠየቅበት ነው፡፡ የግምገማው ዓላማ ችግሮችንና ድክመቶችን ወደ ሌሎች የመግፋት (blame-shifting) አባዜ አለመሆኑን አበክረንና አጠንክረን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡

በአባል ድርጅቶች መካከል ስምምነት ያልተደረሱባቸው የፕሮግራምም ሆነ የህገ-ደንብ ጉዳዩችም በቀጣይ ውይይቶች ለማቀራረብ እንደሚሞከርና ይህ ካልተሳካም መድረክ የመንግሥት ሥልጣን ሲይዝ በሕዝብ ውሳኔ መፍትሔ እንዲያገኙ እንደሚደረግም ሙሉ ስምምነት ያገኘ ጉዳይ መሆኑ እውነት ነው፡፡

የመድረክ መግለጫ፣ ችግርች የሚጀምረው በመጀመሪያ ያልተካሄዱ ጉዳዩችን እንደተካሄዱ አርጎ ከማቅረቡ ላይ ነው፡፡ ሁለተኛውና መሠረታዊው ችግር ደግሞ ድርጅቶች በአንድ ወቅትና ሁኔታ ተስማምምተውና ወደው የተቀበሉት ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግምገማ ማካሄድ የለባቸውም የሚለው ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአንድ ወቅትና ሁኔታ የተወሰኑ ሰነዶችን ፓርቲዎች በስምምነት ስለተቀበሉት ብቻ ሰነዶችን ትክክል ያደርጋቸዋል የሚለው ግንዛቤ ነው፡፡ ባጠቃላይ ሕይወትና በውስጡ ያሉ ክስተቶች በሙሉ የማያቋርጥ የለውጥ ሂደትና እንቅስቃሴ አካል ናቸው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ሥነ አመክኖ (Logic) ሰነዶች ከወቅት፣ ከጊዜና ከሁኔታዎች አኳያ (አንፃር) ይፈተሻሉ፣ ይገመገማሉ ይሻሻላሉ፣ ይለወጣሉም፡፡

በመግቢያው ላይ እንደተቀመጠው የግምገማው ዓላማ የመድረክ ድክመቶች የሚስተካከሉበትና ጥንካሬዎቹ የሚጎለብቱበት ሁኔታ እንዲፈጠርና ብሎም ትግሉ የሚፈልገውን ሁለንተናዊ አቅም ለመፍጠር እንዲቻል ነው፡፡ በዚህ ረገድ የአንድነት ፓርቲ ምን ዓይነት ሚና መጫወት ይገባዋል የሚለውን ጭምር ለመፈተሽ ነው፡፡ በግምገማው ሂደትም የታዩት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ) ለአለፉት በርካታ ዓመታት በተቃዋሚ ጎራ አብሮ ላለመስራት ፈታኝ ሆኖ የቆየውን የኢትዮጵያ ብሔርተኘነትና ብሔር ላይ በተመሰረቱ ፓርቲዎች መካከል የነበረውን ክፍተት በተወሰነ መልኩ ማጥበቡ በአዎንታነት የሚታይ ቢሆንም፤ መድረክ ከተመሠረተ አራት ዓመት ቢያልፈውም በፕሮግራም ልዩነቶች ላይ አንድም ቀን ውይይት አለማካሄዱና ደንበቦችንም ቢሆን አብረን የቆየንባቸውን ጊዜያት ያገናዘበና ትግሉ የሚጠይቀው ደረጃ የሚመጥን ለውጥ አለማድረጉን ነው፡፡ ይህም አንዱ ዋና ምክንያት በመሆኑ መድረክ ከተመሠረተ ጀምሮ ፓርቲዎቹ የመድረክ አባል ለመሆን ያለመቻላቸው ነው፡፡

ለ) የመድረክን ሕገ-ደንብ በኢ-ዴሞክራሲያዊነት ለማስቀመጥ አስገዳጅ የሆነው አንዱ ምክንያት ፓርቲዎች የመተማመንና የአብሮ የመስራትን መንፈስ መፍጠራቸውና ከ4 ዓመት በኋላም በሙሉ ድምጽ ስምምነት ማለፍ ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸው ጭምር ነው፡፡ የቪቶ ሥልጣን የተሰጠውም የፓርቲዎችን ፍላጎትና ስጋቶች ለማስተናገድ ነው የሚለውም በግምገማው ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው፡፡ ትልቅ ቦታም ሊሰጠው ይገባ የነበረው ለሕዝብና ለአገር ፍላጎትና ስጋቶች ስለ ነበር ነው፡፡

ሐ) በግንባሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እያንዳንዱ የመድረክ አባል ፓርቲዎችና አመራሮች በአባል ድርጅቶች ላይ አፍራሽ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው የሚል ሆኖ ሳለ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በአንድነት ፓርቲና በአመራሮቹ ላይ የተሰነዘሩ አፍራሽና ጎጂ አስተያየቶችን በግልጽ በማስቀመጥ ፓርቲዎችና አመራሮች ወደ ትክክለኛው አቅጣጫና መስመር ይመለሱ ዘንድ አባሎችና ሕዝቡም የራሱን ገንቢ አስተዋጽአ እንዲያደርግ ነው፡፡ ከሁሉም በጣም ቅር የሚያሰኘው የመድረክ መግለጫ አፍራሽ አስተያየቶችን ሃሳብን በነፃነት ከመግለጽ መብት ጋር ማያያዙ ነው፡፡ በምን መመዘኛ ነው፡-

‹‹አንድነት ዶ/ር ነጋሶን ሊቀመንበር አድርጎ ቢመርጥም የአማራ ፓርቲ ወይም የአዲስ አበባ ልሂቃን ፓርቲ መሆኑን መካድ አያስፈልግም››
‹‹የአንድነት አዝማሚያ በደቡቦች፣ በአረና እንዲሁም በኦሮሞ ላይ የበላይነትን ለማሳየት ነው››
‹‹ አንድነቶች ፌዴራሊዝምን አይወዱም ፌዴራሊዝሙን የሚጠሉት አማራሮች ናቸው››
‹‹ ከዶ/ር ነጋሶ ውጭ መሪዎቹ አማሮች ናቸው፡፡ ይህን የምለው ስለማውቀው ነው››
‹‹ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ሲዳማ ወለጋ ወ.ዘ.ተ ሄዶ ድምጽ ማግኘት አይችልም››
‹‹ ኦሮሞ አማራ ክልል ሄዶ ምረጡኝ ቢል ድምጽ አያገኝም፡፡ ኦሮሞ ከሆነ
ለምን ኦሮሞ ፓርቲ አይገባም አማራው ኦሮሞ አገር ሄዶ አይመረጥም››

ይህን የተናገሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩልም ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በተደጋጋሚ፡-

1. የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን መመረጥ የሚያውቀው ኢህአዴግ ነው፡፡ የእሳቸው መመረጥ የኢህአዴግ አሻጥር ነው፡፡

2. ስንትና ስንት የዴሞክራሲ አርበኞች ባሉበትና ደጋግመው በምርጫ ያሸነፉ ሰዎች እያሉ አንድ ተወዳዳሪ ብቻ አሸንፋል መባሉ አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ህብረት ፓርቲ በአቀረበው የክስ ማመልከቻ፡-

አንድነቶች ‹‹በአቋራጭ ሥልጣን የሚልፈጉ የነፍጠኛ አቋም ያላቸው ናቸው›› እነዚህ አነጋገሮች አፍራሽና አጥፊ ፕሮፓጋንዳ አካል ናቸው፡፡ ከላይ በአንድነት ፓርቲ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑቱ ‹‹ጠባብ ብሔርተኝነት›› ባህሪያት የማያመላክቱ ከሆነ ምንን ነው የሚያመላክቱት? ሌሎችንም ምሳሌዎችንና ድርጊቶችንም መጨመር ይቻል ነበር፡፡ ሁኔታው በአጭሩ ለመተው ሲባል እንጂ፡፡
መ) ግምገማው የአንድነትን ብሔራዊ ምክር ቤትን፣ የሥራ አስፈፃሚውንና በመድረክ የአንድነት ተወካዮች ሚና በትኩረት የተመለከተውና የሰሉ ሂሶችን እንደየ ተጠያቂነታቸው ደረጃ የአሳረፈባቸው እንጂ እንዲያው ችግሮችን ወደ መድረክና አባል ፓርቲዎች የወረወረ አይደለም ወደ ውጭ እንዳየ ሁሉ ወደ ውሰጥም አይቷል፡፡

ሠ) በመጨረሻም ግምገማው የመፍትሔ አሳቦችን በአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ በመከፋፈል ጠቃሚ አስተያየቶችን ሰጥቷል፡፡ በተለይም ተቀዋሚ ፓርቲዎች አሁን የሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ምህዳር እጅግ ፈታኝ የሆነበት ወቅት በመሆኑ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በአገራችን ጠንካራ መሠረት እንዲይዝ የተቃዋሚ ኃይሎች የመጠላለፍ፣ የመጠፋፋት ፖለቲካ የትም እንደማያደርስ በመገንዘብ በመተጋገዝ በአብሮ መስራት መንፈስ አብሮ መቆም እንዳለባቸው ነው፡፡ የሚያሳየው ከአብሮ መሥራት ውጭ በአገራችን ውስጥ ለውጥ ሊመጣበት የሚችልበት እድል ዝግ እንደሆነ ነው ያመላከተው፣ ያሳየው፡፡ ማንኛውም ፓርቲ የቱንም ያህል ትልቅነኝ ቢልም፣ ትልቅ ቢሆንም ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበትን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ብቻውን ሊወጣው እንደማይችል ነው የታመነበት፡፡

እውነታውና የግምገማው ዓላማና ግኝቶች ይህ ሆኖ ባለበት ሁኔታ አንድነትን በመድረክ አፍራሽነት ለመፈረጅ መሞከር ‹‹ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ›› ያስመስለዋል፡፡ ይልቁንም አንድነት ለግምገማውም ሆነ በተግባር ያረጋገጠው ለመድረክ ጥንካሬ ብርታትና ወደ ፊት መራመድ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ አሁንም በትጋት እንደሚሰራ በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡ ግምገማዎችን ማካሄድና ውስጣዊ ድክመቶች አንጥሮ በማውጣት ከዚያም ትምህርት አግኝቶና እርምት አድርጎ መራመድ ‹‹ኢህአዴግን ነው የሚጠቅመው፤ ሕዝብን ያሳዝናል›› በሚል መርህ በሽፍንፍን መጓዝ ከአገኘነው ተሞክሮ አፃር ሲታይ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

በመጨረሻም ለመድረክ የምናሳስበው ቁም ነገር የተፈፀሙን የአካሄድ ስህተት ምክንያት በማድረግ የግምገማውን ይዘት አልቀበልም ማለቱ ማንንም እንደማይጠቅም በድጋሚ ተመልክቶ በይዘቱ ላይ ውይይት እንዲከፈት እንዲያደርግ በአጽኖት እንጠይቃለን፡፡ ይህ እስከሆነ ድረስ የአብሮ መስራቱና መተባበሩ ተግባር አሁንም ይቀጥላል፡፡

ሰኔ 5 ቀን 2ዐዐ5 ዓም

አዲስ አበባ


አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

$
0
0

“አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?”  በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው….

የሁለት አገር ነዋሪዎች

 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት ናቸው” በሚል ወደ ውጪ በጉቦ የላካቸው ሰዎች ጉዳይም ከሳቸው ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ።  ከጨው ንግድ፣ ከካሜራ ፊልም ብቸኛ አስመጪነት ሌላ በአሁኑ ወቅት ሂልተን ጀርባ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ቪክ ሬስቶራንት ጎን ግዙፍ ህንጻ ያስገነቡት አቶ ነጋ ቃሊቲ ባላቸው የነዳጅ ማደያ የከፈቱት ብቸኛ የክብደት መለኪያ/የከባድ የጭነት መኪኖች የክብደት መለኪያ “የገንዘብ ማምረቻ ማሽን” አግባብነት የሌለው ቢዝነስ እንደሆነ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ የግል የንግድ ተቋማቸው ነው። ቀደም ሲል ከኤርትራዊያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ነጋ ሃብታቸው በድንገት የተመነጠቀው ከ1991 ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ እንደሆነ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ከኢህአዴግ የቀድሞው የኦዲት ኮሚሽን ጸሐፊ ከነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃና ከቴክኒክ ክፍል ሃለፊው መቶ አለቃ ዱቤ ጁሎ ጋር በጋራ ይሰሩ እንደነበር ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ማስረጃ እንደደረሰው የገለጸ የጎልጉል ምንጮች፣ የፌዴሬሽኑ የውጪ ምንዛሬ ሂሳብና በአትሌቶች ስም ወደ ውጪ የተላኩ በርካታ ወጣቶች ጉዳይ እንደሚመመረመር ጠቁመዋል። ኮሚሽኑ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖረውም ማህበራትንና የርዳታ ድርጅቶችን መመርመር የሚያስችል ህጋዊ ውክልና ስለሌለው ሙስና አለባቸው በሚባሉት ማህበራትና ርዳታ ተቋማት ላይ ምርመራ ለማድረግ አዲስ ህግ ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። የኢህአዴግ የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድ ካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን አስፍሯል። በቤተሰብ ተዘረፈ የተባለው ሃብት በስም ዝርዝር ባለቤቶቹም ይፋ ሆነዋል።

በሙስና ቤተሰብ ስም የተከማቸ ሃብት ንብረቶች ታገዱ

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ተፈፀመ በተባለው የሙስና ወንጀል በ544 ተጠርጣሪዎች ድርጅቶችና በቤተሰቦቻቸው ስም በመንግስትና በግል ባንኮች የተቀመጡ ጥሬ ገንዘብ ፣ አክሲዮኖች እንዲሁም የከበሩ ማእድናት ታገዱ።

በሌላ በኩል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች እስካሁን 92 ተሽከርካሪዎች እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በአቶ ገብረዋህድ ባለቤት ኮረኔል ሃይማኖት ተስፋይ ስም የተመዘገቡ ሲሆኑ ፥ 54 የሚሆኑት ደግሞ በአቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ስም የተያዙ ናቸው።

ከተሽከርካሪዎች አራቱ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የአዳማ ቅርንጫፍ ስራ አሰኪያጅ በነበሩት አቶ አሞኘ ታገለ ስም የተመዘገቡ ሲሆን ፥ ከውጭ የሚመጡ ባለሃብቶች ወደ ሃገር ቤት እቃዎቻቸውን ሳያስፈትሹ እንዲያስገቡ በማድረግ በእነርሱና በጉሙሩክ የስራ ሃላፊዎች መካከል ጉቦ በማቀባበል መንግስትን ጎድቶ ራሳቸውን ጠቅመዋል በሚል በተጠረጠሩት በአቶ ዳዊት መኮንን ስም  እንዲሁ አራት ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።

ሌሎች ሰባት ተሽከርካሪዎች በአልቲሜት ፕላን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲመዘገቡ ፥ ስድስት የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች ደግሞ በኢትባ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተመዝግበው ይገኛሉ።

የፌደራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በተጠቀሱ ግለሰቦች ፣ ድርጅቶች እና ሌሎች አካላት እግድ የተጣለባቸው ተሽከርካሪዎች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ እና ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ አስደርጓል።

የእነ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እና ሌሎች መዝገቦችን ሳያካትት በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ በተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች ፥ ተፈጸመ በተባለው የሙስና ወንጀል  ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ከተገኙ ሰነዶች ብቻ መንግስት ከ 230 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰበት ነው የሚለው የኮሚሽኑ መረጃ የሚያመለክተው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)

በፌስቡክ “የኮንዶሚኒየም ዕድለኞች ስም ዝርዝር ይፋ ወጣ” እየተባለ የተዘበተባቸው የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ሙስ ስም ዝርዝር

አባቡ አለሙ ገብሩ
ምስጋናው ይስሃቅ እጅባ
በረከት ይስሃቅ እጅባ
ታደሉ አለምነው ተፈራ
ፀጋነሽ አለምነው ተፈራ
አባተ ጋሻው ቦጋለ
ጌጤ ጋሻው ቦጋለ
ዘርፌ ጋሻው ቦጋለ
ፀሐይ ጋሻው ቦጋለ
ትዕግስት ጋሻው ቦጋለ
አስፋው ጋሻው ቦጋለ
መብራት አበበ አብርሃ
ቤቴልሄም አማኑኤል ሰይፈ
እቁባይ ተከለ አርአያ
ብሌን አማኑኤል ሰይፈ
ሊዲያ አማኑኤል ሰይፈ
እየሩሳሌም ስማቸው ከበደ
መቅደላዊ ስማቸው ከበደ
ኤልሻዳይ ስማቸው ከበደ
ኢቫና ስማቸው ከበደ
አያልነሽ ይመር ጌታሁን
ሠለሞን ከበደ ካሳ
ምንትዋብ ከበደ ካሳ
ዳንኤል ደባሽ ሀገሩ
ናኑ ደባሽ ሀገሩ
ሰላማዊት ደባሽ ሀገሩ
ሣራ ደባሽ ሀገሩ
ኤፍሬም ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ሄኖክ ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ይትባረክ ነጋ ገ/እግዚአባሄር
ሠላም ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ራሄል ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ዮርዳኖስ ደሣለኝ ገ/እግዚአብሄር
ቅድስት ድጉማ ዋቅጅራ
አናኒያ ብርሃኔ እጅጉ
ተዋበች ወርቁ ወልፃዲቅ
ብሩክ ከበደ ታደሰ
ፍቅረማርያም ከበደ ታደሰ
ክብነሽ ከበደ ታደሰ
ዳኝነት ከበደ ታደሰ
ትዕግስት ከበደ ታደሰ
ሙሉነህ ከበደ ታደሰ
ትዕዛዙ ከበደ ታደሰ
ቴዎድሮስ ማዕረግ አዱኛ
አይንአዲስ በረከት ኃ/ጊዮርጊስ
ወይንሸት ወርቁ አንጋሶ
መብራቱ እጅጉ አበራ
የማነ ብርሃን እጅጉ አበራ
መሀሪ እጅጉ አበራ
ዮሐንስ እጅጉ አበራ
ለምለም እጅጉ አበራ
ሠናይት እጅጉ አበራ
ካሰች አምደመስቀል መገርሳ
ዮናታ ማርክነህ አለማየሁ
ኤልሻዳይ ማርክነህ አለማየሁ
ባልጊቴ አለማየሁ ወዳቦ
ባፋነ አለማየሁ ወዳቦ
አየለ አለማየሁ ወዳቦ
ብርሃኑ ዓለማየሁ ወዳቦ
አበራ አለማየሁ ወዳቦ
እጀትግስት ዓለማየሁ ወዳቦ
ሚካኤል አምደመስቀል መገርሳ
ዳኛቸው አምደመስቀል መገርሳ
ተረፈ አምደመስቀል መገርሳ
ተክሉ አምደመስቀል መገርሳ
ደርባቸው አምደመስቀል መገርሳ
መቅደስ አምደመስቀል መገርሳ
ትዝታ አምደመስቀል መገርሳ
ሙሉጸጋ አምደመስቀል መገርሳ
ውቢት ኃይለገብርኤል አስፋው
ያዕቆብ ደጉ ሆቢቾ
ዮናታል ደጉ ሆቢቾ
ዳግማዊ ደጉ ሆቢቾ
ኡፋይሴ ሆቢቾ አልቤ
ዲቃም ቤቢሶ አልቤ
ካሳሁን ኃይለገብርኤል አስፋው
አምሃ ኃይለገብርኤል አስፋው
ዝናሽ ኃይለገብርኤል አስፋው
ምሳዬ ኃይለገብርኤል አስፋው
አበባ ኃይለገብርኤል አስፋው
ፍሬህይወት ጌታቸው ሀብቴ
ጌታቸው ምስጋና ተፈሪ
ዮሴፍ ጌታቸው ምስጋና
ዮናታን ጌታቸው ምስጋና
ጌታቸው ሀብቴ ተክለሃይማኖት
አብረኸት ገብረመድህን ጣሰው
አበባው ጌታቸው ሀብቴ
ገስጥ ጌታቸው ሀብቴ
ደሳለኝ ጌታቸው ሀብቴ
ቤተልሄም ጌታቸው ሃብቴ
ዜና ጌታቸው ሀብቴ
ሳህሌ ገላው ፈንቴ
ላይኩን ውብየ ተሰማ
አበባው ላይኩን ውብየ
በትረወርቅ ላይኩን ውብየ
ዳዊት ላይኩን ውብየ
አብርሃም ለይኩን ውብየ
ህሉፍ አብርሃ ሐጎስ
አስመለሻ አብርሃ ሐጎስ
ስዬ አብርሃ ሐጎስ
አሰፋ አብርሃ ሐጎስ
ወ/ስላልሴ አብርሃ ሐጎስ
ትምኒት አብርሃ ሐጎስ
ፀሐይነሽ ገ/ሚካኤል ገብሩ
ንግስቲ ሳመሶነ ብሩ
እጅግጋየሁ ሳምሶን ብሩ
ኢትዮጵያ ሳምሶን ብሩ
ያለም መብራት ሳምሶን ብሩ
ቢተወደድ ሳምሶን ብሩ
ሚዛን ሳምሶን ብሩ
በእግዚአብሔር አለበል ኃይሉ
ኤልሳ ታደለ ኃይሉ
ናአምን በእግዚአብሔር አለበል
ቅዱስ በእግዚአብሄር አለበል
በረኽት በእግዚአብሄር አለበል
አለበል ኃይሉ አዱኛ
እቴነሽ ብሩክ ደስታ
ዘላለም አለበል ኃይሉ
ነፃነት አለበል ኃይሉ
የሰውዘር አለበል ኃይሉ
በሁሉም አለበል ኃይሉ
ሰላም አለበል ኃይሉ
ዮናስ ታደለ ኃይሉ
ሚካኤል ታዳለ ኃይሉ
ዮሴፍ አዳዩ ገብሩ
ሃና በርሄ ሀጎስ
ግሎሪ ዮሴፍ አዳዩ
ሊዮ ዮሴፍ አዳዩ
አዳዩ ገብሩ ዲኒ
አብርሃ አዳዩ ገብሩ
ራህዋ አዳዩ ገብሩ
ብርክቲ አዳዩ ገብሩ
ኢንዲሪያስ አዳዩ ገብሩ
ፋና አዳዩ ገብሩ
ታበቱ አዳዩ ገብሩ
ስላስ አውዓለ ሐጎስ
ኃ/ስላሰ በርሄ ሀጎስ
ተስፋይ በርሄ ሀጎስ
ብሩር በርሄ ሀጎስ
ዘቢብ በርሄ ሀጎስ
ጌታነህ ግደይ ንርኤ
ኤደን ብርሃነ ገ/ህይወት
አበባ ግደይ ንርኤ
ዙፋን ግደይ ንርኤ
ደስታ ግደይ ንርኤ
ዮሐንስ ግደይ ንርኤ
መንግስቱ ግደይ ንርኤ
ሀብቶም ግደይ ንርኤ
ቢኒያም ብርሃነ ገ/ህይወት
ኤልሻዳይ ብርሃነ ገ/ሕይወት
ብርክታዊት ብርሃን ገ/ህይወት
ገ/መድህን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ገ/ህይወት ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ኪዳን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሱራፌል ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ብርያ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
እግዜሄሩ ወ/ጊዮርጌስ ወ/ሚካኤል
ግደይ ተስፋ ገ/ስላሴ
ስላስ ተስፋይ ገ/ስላሴ
ለተመስቀል ተስፋይ ገ/ስላሴ
ማህተመሥላሴ ጥሩነህ በርታ
ማሞ በርታ ባቦ
ታደሰ በርታ ባቦ
ዳዊት በርታ ባቦ
ብሩክ በርታ ባቦ
አበበች በርታ ባቦ
አመለወርቅ በርታ ባቦ
እመቤት በርታ ባቦ
ፍቅርተ በርታ ባቦ
ይልማ ፈንታ ቻይ
አንጋች ፈንታ ቻይ
ሸዋዬ ፈንታ ቻይ
ፈጠነ ታገለ አወቀ
ቻለ ታገለ አወቀ
እማዋ ታገለ አወቀ
አልጋነሽ ታጋለ አወቀ
እመቤት ታጋለ አወቀ
ዳዊት አሰፋ ዘውዱ
ትዕግስት አሰፋ ዘውዱ
ጥሩወርቅ አሰፋ ዘውዱ
ተወዳጅ አሰፋ ዘውዱ
መልካም አሰፋ ዘውዱ
ማህሌት አሰፋ ዘውዱ
ዝናሽ ብርሃኑ በሻህ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
ፍሬህይወት ብርሃኑ በሻህ
አብዮት ብርሃኑ በሻህ
ግልነሽ ብርሃኑ በሻህ
ሰለሞን ብርሃኑ በሻህ
አዲስ ብርሃኑ በሻህ
ካህሳይ ጉላል አለመ
ዘውዲቱ ለምለም ገ/ማርያም
ብስራት ገ/መድህን ተስፋይ
ግርማይ ብስራት ገ/መድህን
ዮሀንስ ብስራት ገ/መድህን
አበባ ብስራት ገ/መድህን
ለተመስቀል ብስራት ገ/መድህን
ሚዛን ብስራት ገ/መድህን
አክበረት ብስራት ገ/መድህን
ገ/መድህን ሀጎስ ንጉሴ
ጌቱ ገ/መድህን ሀጎስ
ሳራ ገ/መድህን ሃጎስ
ፍፁም ገ/መድህን አብርሃ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
አለም ስንሻው አማረ
ሐጎስ ፍፁም ገ/መድህን
ኃይሌ ፍፁም ገ/መድህን
ኤርሚያስ ፍፁም ገ/መድህን
ደሊና ፍፁም ገ/መድህን
ገነት ገ/መድህን ሀጎስ
ኮነ ምህረቱ እሸቱ
መንበረ ታምራት በየነ
ፍስሐ ኮነ ምህረቱ
ፍረህይወት ኮነ ምህረቱ
መስከረም ኮነ ምህረቱ
ቅድስት ኮነ ምህረቱ
ዘይሰድ ኢሳ አወል
ተስፋዬ ወልዱ ፍስሃ
ሰብለወንጌል ዘውዴ ዋለ
ዳንኤል ዘውዴ ዋለ
ሙሉቀን ዘውዴ ዋለ
ብርሃኑ ዘውዴ ዋለ
ጌትነት ዘውዴ ዋለ
ታምራት ዘውዴ ዋለ
አምባው ሰገድ አብርሃ
ብርነሽ ሐጎስ ካህሳይ
ህሊና አምባው ሰገድ
ብሩክ አምባው ሰገድ
ሜሮን ገ/ስላሴ ገብሩ
ሳባ ኪሮስ ወ/ገብርኤል
አፀደ ገ/ስላሴ ገብሩ
አብርሃ ገ/ስላሴ ገብሩ
ያሬድ ሰገድ አብርሃ
ክብሮም ሰገድ አብርሃ
ፀዳለ ሰገድ አብርሃ
ፅጌ ሰገድ አብርሃ
ፀሐይነሽ ሰገድ አብርሃ
ተክለአብ ዘርአብሩክ ዘማርያም
ፅጌረዳ ደርበው አዳነ
ዘርአብሩክ ዘማርያም ረዳ
ሂሩት ፀጋዬ ገ/መድህን
አቤል ተክለአብ ዘርአብሩክ
ምህረትአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሠላማዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ፀጋዘአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሣምራዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ዳንኤል ደርበው አዳነ
ሠላዊት ደርበው አዳነ
ሄሳን ደርበው አዳነ
ኤደን ደርበው አዳነ
ጌታሁን ቱጂ ደበላ
ምኞት ብርሃኑ አበራ
ሮዳስ ጌታሁን ቱጂ
አዴራት ጌታሁን ቱጂ
ሲሳይ ቱጂ ደበላ
እመቤት ቱጂ ደበላ
ጋሻው ብርሃኑ አበራ
አዲሱ ብርሃኑ አበራ
ሠላም ብርሃኑ አበራ
ክብረወሰን ብርሃኑ አበራ
ዘለቀ ልየው ካሳ
ግንቻየው አድሮ ኃይሉ
ዮሐንስ ዘለቀ ልየው
ሊዲያ ዘለቀ ልየው
ጥሩአለም አድሮ ኃይሉ
ዮሴፍ አድሮ ኃይሉ
ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ተናኜ እሸቴ አዳፍሬ
ሠላማዊት ያዴሳ ሚዴቅሳ
ገመቺሳ ያዴሳ ሚዴቅሳ
ብልሴ ያዴሳ ሚዴቅሳ
መኮንን ሚዴቅሳ ዲባባ
በጂጌ ሜዴቅሳ ዲባባ
ሽታዬ ሚዲቅሳ ዲባባ
ፅጌ ሚዴቅሳ ዲባባ
ልኪቱ ሞሲሳ ቦኮ
ከበደ ደጀኔ ገለታ
ፍስሐ ደጀኔ ገለታ
የሻነው ደጀኔ ገለታ
ዘላለም ደጀኔ ገለታ
ትዕግስት ደጀኔ ገለታ
መታሰቢያ ደጀኔ ገለታ
ሠናይት ደጀኔ ገለታ
መላኩ ግርማ ገብሬ
እህተ ቱኒ ኦርጋጋ
ብርሃኑ ግርማ ገብሬ
ጌትነት ግርማ ገብሬ
አብርሃም ግርማ ገብሬ
ዳዊት መኮንን ተመስገን
እሴታ ባረጋ ሽራጋ
አሚን ዳዊት መኮንን
ዘሪሁን ዳዊት መኮንን
ዜና መኮንን ተመስገን
ማርታ መኮንን ተመስገን
መኮንን ተመስገን የሽታ
ፍሬሕይወት ማሞ አና
መቅደስ ባረጋ ሽራጋ
ብርሃኑ ባረጋ ሽረጋ
ቅጣው ባረጋ ሽራጋ
ባረጋ ሽራጋ ሽራጋ
አስፋው ስዩም ታፈረ
ማርታ የማነህ ተስፈሚካኤል
መስፍን ስዩም ታፈረ
መንገሻ ስዩም ታፈረ
አንባቸው ስዩም ታፈረ
ሂሩት ስዩም ታፈረ
ሠላማዊት ግርማ ፈለቀ
በፀሎት አበበልኝ ተስፋዬ
ኪሮስ ገ/መድህን ገ/ተክለ
ትዕግስት ተስፋዬ ፊታሞ
ሊዲያ ተስፋዬ ፊታሞ
ሐዲያወርቅ ተስፋዬ ፊታሞ
ታሪኩ አበበ ፊታሞ
ፍስሃ አበበ ፊታሞ
ማርክስ አበበ ፊታሞ
ምንአለ አበበ ፊታሞ
ዘይነባ እሸቱ ኃይሌ
ኑርሃን ጌታቸው አሰፋ
ሐይመን ጌታቸው አሰፋ
ሰሚሩ ጌታቸው አሰፋ
ኢምራን ጌታቸው አሰፋ
የንጉስነሽ አሰፋ ሀምዛ
መንገሻ አሰፋ ሃምዛ
መሰለ አሰፋ ሃምዛ
ልዑልሰገድ አሰፋ ሀምዛ
መሐመድ አሰፋ ሀምዛ
ናስር እሸቱ ሃይሌ
ዛህር እሸቱ ሃይሌ
መሐመድ እሸቱ ሀይሌ
ራቢያ እሸቱ ሃይሌ
ምፅላል ሃይሉ አለማየሁ
ጌጤ ማቲዮስ ገ/ኪዳን
ትዕግስት በላቸው በየነ
ሱራፌል በላቸው በየነ
ሰላማዊት በላቸው በየነ
አበባየሁ ዘበነ ተኮላ
ማሚቱ በየነ ገ/ዮሐንስ
አዳነ ተሰማ በረሳ
ታሪኩ ተሰማ በረሳ
ሲሳይ ተሰማ በረሳ
ተፈሪ ተሰማ በረሳ
ዜና ተሰማ በረሳ
ሙሉጌታ ተሰማ በረሳ
እመቤት ተሰማ በረሳ
ጠጅነሽ ጎሳዬ በረሳ
አንለይ አሳምነው ተሰማ
ራሄል ገበደ ኃ/ማርያም
ናርዶስ አንለይ አሳምነው
ፍፁም አሳምነው ተሰማ
ማናዬ አሳምነው ተሰማ
ይርጋለም አሳምነው ተሰማ
ፍፁም ከበደ ኃ/ማርያም
በኃይሉ ከበደ ኃ/ማርያም
ሱራፌል ከበደ ኃ/ማርያም
ቢኒያም ከበደ ኃ/ማርያም
መስፍን ከበደ ኃ/ማርያም
እመቤት ከበደ ኃ/ማርያም
መሰረት መንግስቱ በየነ
ሠላማዊት ማሩ ፍቅሩ
ፍቅርተ ማሩ ፍቅሩ
ስንታየሁ ወይም አሰለፈች ማሩ ወርዶፋ
በቀለች ማሩ ወርዶፋ
ጥሩወርቅ መንግስቴ በየነ
ገ/መድህን ገ/የሱስ ስብሃት
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የሱስ
ንብረት ገ/መድህን ገ/የሱስ
ማሞ ኪሮስ በዛብህ
ራሄል አስረስ መኮንን
አዶኒያስ ማሞ ኪሮስ
ብሩክ ማሞ ኪሮስ
ዳግም ማሞ ኪሮስ
ኢዮስያስ ማሞ ኪሮስ
ናሆም ማሞ ኪሮስ
ደሳዊ ማሞ ኪሮስ
ኪሮስ ገ/ህይወት በርሄ
አለም ኪሮስ በዛብህ
ፅጌ ኪሮስ በዛብህ
ፋና ኪሮስ በዛብህ
አፀደ ኪሮስ በዛብህ
አብይ አስረስ መኮንን
ቤተልሄም አስረስ መኮንን
ሂሩት አስረስ መኮንን
ፀደይ አስረስ መኮንን
ሸዋዬ መስፍን አበራ
ኤልዳና ስንሻው አለምነህ
አርሴማ ስንሻው አለምነህ
ምስጋና ይሳቅ ገድባ
በረከት ይሳቅ ገድባ
የመከረ መኮንን ተሰማ
ማራማዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
መቅደላዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
ቤተል ዳዊት ኢትዮጵያ
ወለላ ተስፋዬ ብሩ
ተፈሪ ኢትዮጵያ መኮንን
ፍሪው ኢትዮጵያ መኮንን
ግሩም ኢትዮጵያ መኮንን
ትዕግስት ኢትዮጵያ መኮንን
ውቢቱ ኢትዮጵያ መኮንን
ለምለም ኢትዮጵያ መኮንን
ፀሐይነሽ መንግስቱ አዳል
መቅደስ መኮንን ተሰማ
እሸቱ ግረፍ አስታክል
ብስኩት ደመቀ ታከለ
ማየት እሸቱ ግረፍ
ቤተል እሸቱ ግረፍ
ኢዮስያስ እሸቱ ግረፍ
ታደሰ ደመቀ ታከለ
በኃይሉ ደመቀ ታከለ
ብርሃኑ ደመቀ ታከለ
ልፍነሽ ገለታ ዳዲ
እቴነሽ ግረፍ አስታክል
በላይነሽ ግረፍ አስታክል
ዘውዱ ግደይ ካህሲ
በረከት ተመስገን ስዩም
ሚሚ ተመስገን ስዩም
ካህሳይ ጉልላት አለመ
ሰመረ ግደይ ካህሲ
ኢሊኑ ግደይ ካህሲ
ምህረት ገ/መድህን ገ/የስ
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የስ
ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ
ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማ
ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል
አዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ
ምፍአም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ነፃ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዎው ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኤምዲ ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዲ ኤች ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የስም ዝርዝሩን የወሰድነው ከኢሳት ነው።

goolgul


“እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ፤ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ”ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ

$
0
0

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. June 14, 2013)፦ ላለፉት አስራ ስምንት ወራት በእስር ላይ ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በዚህ ሣምንት መፈቀዱን ለመረዳት ችለናል… ዛሬ ጠዋት ቃሊቲ ሄደው ከጠየቁት ውስጥ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ አንዷ ስትሆን፤ አላግባብ ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ላሰሙና ለሚያሰሙ ሁሉ በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው ብሏታል።

ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ለሚያሰሙ ምስጋና አቅርቧል “ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ!” እስክንድር ነጋ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ Jornalist Eskinder Nega

 

ካላግባብ፣ ከሕግና ከሰብዓዊ መብት ውጭ ጋዜጠኛ እስክንድር ከልጁና ከባለቤቱ በስተቀር ማንም ወዳጅ ዘመድ እንዳይጠይቀው መደረጉ በገዥው ፓርቲ የፖለቲካ አመራሮች ግለሰባዊ ትዕዛዝ እንደነበር ብዙዎች ሲተቹት እንደነበር ይታወቃል። ከዚህም ሌላ የምዕራባውያን ሀገሮች ባለሥልጣናትና መንግሥታት ካላግባብ እንደ እስክንድር በእስር ላይ ያሉት ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ እየጎተጎቱ ይገኛሉ።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር በነበረው ቆይታ እንዲህ ሲል ምስጋና አቅርቧል፤ “የታሠርኩት ከሕግ ውጭ መኾኑን ተረድታችሁ በሁሉም መንገድ እንድፈታ ለወተወታችሁ፣ ላሳሰባችሁ፣ አሁንም እየወተወታችኹ ላላችኹና ባላችኹበት ላሰባችኹኝ ኹሉ ዲሞክራሲ በአገራችን ሰፍኖ ከእስር ወጥቼ በአካል ምስጋናዬን እስካቀርብላችሁ ድረስ ባላችሁበት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ!”።
ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዛሬ በፌስ ቡክ ገጿ ላይ “እስክንድር ነጋን አገኘሁት!” በሚል ርዕስ ባስነበበችው ማስታወሻዋ ላይ ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር በነበራት ቆይታ፣ ስለጋዜጠኛው ያላትን አመለካከት እንዲሁም ስለሁኔታው አስመልክታ እንዲህ ስትል አስነብባለች፦
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ከገባ ከዐሥራ ስምንት ወራት በላይ አስቆጥሯል። ለዚህን ያህል ጊዜም ከባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ናፍቆት በስተቀር አንድም ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው አልተፈቀደለትም ወይም በወዳጅ ዘመዶቹ የመጠየቅ መብቱ ተነፍጎ ነበር። ከቀናት በፊት ግን ይህ መብቱ ተከብሮለት ሰዎች ገብተው እንዲጠይቁት መፈቀዱን ሰማኹና ዛሬ ጠዋት እስክንድርን ለማየት ወደ ቃሊቲ አመራሁ። እስክንድርንም አገኘኹት ብዙም ተጨዋወትን። እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ።
ከእርሱ ይልቅ እርሱን ያሳሰበው በውጭ ያሉት ወዳጆቹ ጤንነት እስኪመስለኝ ድረስ በጋራ የምናውቃቸውን ሰዎች እና ጓደኞቻችንን ስም እያነሳ ጠየቀኝ። በቻልኩት መጠን ሰላምታ እንዳቀርብለትም አሳሰበኝ። በመጨረሻም እንዲህ አለኝ፤ “የታሠርኩት ከሕግ ውጭ መኾኑን ተረድታችሁ በሁሉም መንገድ እንድፈታ ለወተወታችሁ፣ ላሳሰባችሁ፣ አሁንም እየወተወታችኹ ላላችኹና ባላችኹበት ላሰባችኹኝ ኹሉ ዲሞክራሲ በአገራችን ሰፍኖ ከእስር ወጥቼ በአካል ምስጋናዬን እስካቀርብላችሁ ድረስ ባላችሁበት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ!” መልዕክቱን በፌስቡክ ገጼ ላይ እንደማሰፍርለት ቃል ገብቼለት ተሰናብቼው ወጣሁ። በገባሁት ቃል መሠረትም ምስጋናውን አድርሻለኹ።
እስክንድር ነጋ የሞያ አጋሬ ብቻ አይደለም፤ በቀናነታቸው እና በአስተዋይነታቸው የመጀመሪያውን የወዳጅነት ቦታ ከምሰጣቸው ጓደኞቼ ውስጥ የምመድበው ሰው ነው። እስክንድር በአሳሪዎቹ እጅ ወድቆም ስለ ሌሎች ማሰብ ባለማቋረጡ እየተገረምኩ ቃሊቲን ለቅቄ ወጣሁ። ወዳጆቼ በዚህ ቤት መታሠር ሚያቆሙት መቼ ይኾን ስልም ራሴን ጠየኹ!


በኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን የዛሬ ስድስት አመት የተፈጸመ አሳዛኝ የግድያ ወንጀል ታሪክ

$
0
0

በምዕራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ ከባህር ዳር ከተማ 25 ኪሎ ሜትር አካባቢ ባችማ ቀበሌ ውስጥ አቶ ገብሬ ስንቴ ገደፋው የተባለ ግለሰብ ህይወት በጣም አስቸጋሪ ትሆንበትና ከነገ ዛሬ ቀን ይጣል ብሎ ተስፋ በማድረግ በሰው ቤት ተቀጥሮ ደፋ ቀና ይል ጀመር…. ጊዜያት እየሄዱ ጊዜ ሲተካ እኔም እንደ እኩዮቼ በማለት ሚስት አግብቶ ልጅም ወለደ፡፡

የመጀመሪያ ልጁንም ብርቱካን ገብሬ
ሲል ሰዬማት፡፡ ብርቱካን ግን ከሶስት ዓመታት በላይ በህይወት ለመኖር አልታደለችም፡፡ በጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎችን የጫነች በፌደራል ፖሊስ በታጀበች መኪና ትገጫለች፡፡ አቶ ገብሬ ሁኔታውን ከስድስት ዓመት በኋላ ሲያስታውሱ ‹‹ድምጽ ሰምቼ ወደ መኪናው መንገድ ሄድኩ፤ የማይታመን ነገር ተመለከትኩ፤ በድህነቴ ለፍቼ የማሳድጋት አንዲት ልጄ አንገት ተቆርጦ ብዙ ርቀት ሂዷል፡፡ አካሏ ከሁለት ተለያይቷል፤ ከዚያ በኋላ የሆንኩትን አላውቀውም፡፡›› በማለት ሲናገሩ አሁንም ድረስ ፊታቸው ላይ አደጋው እንዳለ አድረገው ያስታውሳሉ፡፡

ሰኔ 6 ቀን 2000 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 3፡00 አካባቢ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች አንድ ባለስልጣን አጅበው ይጓዙ ነበር፡፡ ብርቱካንን እንደገጩ በአካባቢው ወደ መራዊ ከተማ እየሄዱ የሚማሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መኪናውን ለማስቆም ሲሚክሩ ታጣቂዎቹ ‹‹እናንተንም እንዳንደፋችሁ›› በማለት አስፈራርተው ያልፋሉ፡፡ የአካባቢው ሰዎች ወደ ወረዳው ከተማ መራዊ ፓሊስ ስልክ ደውለው እነኚህ ወፍራም ባለስልጣን ወወንጀለኛ እንዲያዙ ቢናገሩም ከተማውን አልፈው ስለነበር ወደ አዊ ዞን እንጅባራ ይደውላሉ፡፡ አዊ ዞን ላይ ቢያዙም ከፖሊስ ጋር በምን መልኩ እንደተደራደሩ ሳይታወቅ ጉዟቸውን ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ቀይሰው የመኪናዋን ታርጋም ቀይረው ጉዟቸውን ወደ ቻግኒ ከተማ ያደርጋሉ፡፡

የሜጫ ወረዳ የፖሊስ አካላት ወንጀለኛውን ለመያዝ ደፋ ቀና ሲሉ ከቆዩ በኋላ የሰውዬውን ማንነት ያውቃሉ፡፡ ከዚያም ምስኪኑን የሟች አባት ‹‹አርፈህ ተቀመጥ ልንረዳህ አንችልም›› ብለው ያሰናብቱታል፡፡ አባትም ሳይሰለች የልጁን ገዳዮች በህግ እንዲያዙለት በየቀኑ በየደረጃው ያሉ ባለስልጣናትን ደጅ መጥናት ቀጠለ፡፡ ግን የበለጠ መረጃዎቹን እያጠፉበት ሄዱ እንጅ አንዳች ነገር የፈየደለት አካል የለም፡፡ እንደ ደሃዋ መበለት ቢያንስ ሰልችቷቸው መልስ ይሰጡኛል ቢልም ቀናት ቀናት እየቆጠሩ ድካምና ልፋት ብቻ አተረፈ፡፡

የመራዊ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በቁጥር መጤጣ/283/01 በቀን 17/10/2000 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ በሰጠው የህክምና ማስረጃ ሰኔ 06 ቀን 2000 ዓ.ም. ወደ ጤና ጣቢያው የመጣችሁ ህጻን ጭንቅላቷ የተፈረካከሰ፣ አንገቷ የተቆረጠ፣ እጆቿና ወገቧ የተሰባበረ ሲሆን ምንም አይነት እስትንፋስ እንደሌላት ለሜጫ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳወቀ፡፡

ፖሊስ ጽ/ቤቱ ግን በወቅቱ የሟችን አካል የሚያሳየውን ፎቶ ግራፍና ሌሎች ሰነዶችን ሁሉ አጠፋፏቸው፡፡ የሟች አባት ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያና ፍትህ ቢሮ በተደጋጋሚ አመለከቱ፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ በቁጥር ፍቢ/801/አበ.23/2001 በቀን 11/02/2001 ዓ.ም. ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በተጻፈ ደብዳቤ በትራፊክ ፖሊስ የተጀመረው ደብዳቤ ለምን እስካሁን እንደዘገዬና አደጋውን ያደረሰው ሰው ለምን እንደተለቀቀ በዝርዝር እንዲልክ ጠየቀ፡፡ በዚያው ዓመት እስከ የካቲት ወር ከተጓተተ በኋላ ፍትህ ቢሮ ብድጋሚ ለምዕራብ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ በቁጥር ፍቢ/1700/አበ.23/2001 በቀን 04/06/2001 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ‹‹የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 33- 3364 የሆነ ኮብራ መኪና ማንነቱ ባልታወቀ ሰው እተሸከረከረ ሳለ ሰው ገጭቶ ከገደለ በኋላ ማምለጡንና በዚህ ጉዳይ በሜጫ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ምርመራ ተጀምሮ ለውጤት ሳይበቃ በእንጥልጥላ ላይ መሆኑን›› ይገልጻል፡፡  ደብዳቤው አያይዞም ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡ በተደጋጋሚ ማመልከቱንና ምላሽ ያላገኘ ሲሆን በወረዳው ፖሊስ የተጀመረውን ምርመራ እንዲቀጥሉ በማድረግ ለቢሮው ሪፖርት እንዲያደረጉ ተገልጧል፡፡

ከዚያ በኋላ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥር አብክመፖ/መ/7/አደ/መ/80/02 በቀን 7/8/2002 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ከላይ የተጠቀሰውን ታርጋ ቁጥር በመጥቀስ ህጻን ብርቱካንን ገጭቶ እንዳመለጠ ዋና ሳጅን ደሳለኝ አባተ የተባለ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ፖሊስ ቢይዘውም እንዳልገጩ ሲነግሩት ሙሉ መረጃ ሳይዝ ሲለቃቸው ጉዟቸውን ወደ ፓዊ አቅጣጫ እንዳደረጉ ሪፖርት አድርጓል፡፡ ደብዳቤው አያይዞም ዳንግላ ከተማ ላይ ፖሊሶች ሊይዙት ቢሞክሩም ጥሰው እንዳመለጡ ይናገራል፡፡ በመጨረሻም የታርጋ ቁጥሩ በማን ስም እንደተመዘገበ በማጣራት እንዲተባበሩ ይጠይቃል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥር 1/ፌፖኮ211 በቀን 7/11/2002 የመኪናው ንብረትነት በቤኒሻንጉል ክልል መስተዳደር ምክር ቤት የተመዘገበ መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ቢሆንም ግን ለሟች ቤተሰቦች መፍትሄ አልተሰጣቸውም፡፡  የሟች አባት አቶ ገብሬ አሁንም ተሰፋ በለመቁረጥ ለሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አመለከቱ፡፡ ሰመጉም ምንም መፍትሄ ማምጣት ብቻ ሳይሆን መግለጫም ሳያወጣ እስከ 2004 ዓ.ም. ድረስ ቆየ፡፡ እንደ ሟች አባት እምነት የወንጀለኛው ማንነት በዚያው ቀን ታውቆ ነበር፡፡ ነገር ግን የመንግስት ከፈተኛ ባለስልጣን በመሆኑ ለስድስት አመት ተበድበስብሶ ቆየ፡፡

በወቅቱ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ባህር ዳር ላይ ስብሰባ ነበራቸው፡፡ በዚህም ምክንያት አሁን በሙስና ወንጀል በቃሊቲ (በማዕከላዊ) የሚገኙት በዘመኑ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹም ባህር ዳር ሲመለሱ በጸጥታ ሀይሎች ታጅበው ሲሄዱ አደጋውን ያደረሱት የእርሳቸው መኪና አሊያም እርሳቸውን ያጀቡ ወታደሮች መኪና እንደሆነ በጊዜው ይታወቅ ነበር፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አቶ ያረጋል ወደ ማረሚያ ቤት ከተላኩ በኋላ በ2004 ዓ.ም. መግለጫ እንዳወጡ የሟች አባት ቢነግሩኝም መግለጫውን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ በህግ ከተያዘ በኋላ በዚህ አመት እንደገና እንቅስቃሴ የተጀመረ ቢሆንም እስካሁን አቶ ገብሬ መፍትሄ አልተሰጣቸውም፡፡ የምራብ ጎጃም ፍትህ መምሪያ በዞ/ፍ/አቤ/መ/ቁ 92/05 በቀን 19/07/05 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ለሜጫ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በአጭር ጊዜ የነበረው ሁኔታ እንዲገለጽልን ብሎ ቢጽፍም አቶ ገብሬ ፍትህ ለማግኘት አሁንም የማይረግጡት መስሪያ ቤት የለም፡፡

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሁሉም ዜጎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ቢልም ይህ የህገ መንግስቱ አንቀጽ ለሁሉም ዜጎች እኩል እንደማይሰራ ማረጋገጫ መሆኑን የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያምናል፡፡


Viewing all 940 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>