Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

ኢሕአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ሊያስር መሆኑን ፍንጭ ሰጠ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመወጣት ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ …..“ፓርቲው ህገ መንግስቱን በመጣስ በሃይማኖት እጁን መክተቱና በህግ የበላይነት አምናለሁ እያለ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተያዘባቸው ሰዎች በሁካታ ይፈቱልን ማሰኘቱ ተጠያቂ ያደርገዋል” አሉ።

964382_10200726554220184_1320094080_oአቶ ሬድዋን በፍርድ ቤት ሽብርተኛ የተባሉ ሰዎችን ሰማያዊ ፓርቲ እንዲፈቱለት መጠየቁ አግባብ አይደለም ካሉ በኋላ “የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ብሎ ኢህአዴግ ያምናል።” በማለት የፓርቲው ሰዎችን ለማሰር ያለውን እቅድ ፍንጭ ሰጥቷል።

የኢሕአዴግ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት በልምድ እንደታየው ግለሰቦችን ማሰር ሲፈልግ “ሕገመንግስቱን” እንደሚጠቅስ የሚያስታውሱት የፖለቲካ ተንታኞች ኢሕአዴግ ይህን  “ሰማያዊ ያዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተፈለገ አላማ አውሎታል” ሲል መግለጹ እንደተለመደው ሰበብ ፈልጎ ለማሰር ያለውን እቅድ ያሳየ ነው ብለውታል።

አቶ ሬድዋን በመግለጫቸው “በሰልፉ በአብዛኛው የተንጸባረቀው የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ እየተባለ መስተጋባቱ፤ ፓርቲው ህገ መንግስቱን በመጣስ በሃይማኖት እጁን መክተቱና በህግ የበላይነት አምናለሁ እያለ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው የተያዘባቸው ሰዎች በሁካታ ይፈቱልን ማሰኘቱ ተጠያቂ ያደርገዋል” ሲሉ በግልጽ መናገራቸውን የተመለከቱ የፖለቲካ ተንታኞች ስርዓቱ ይህን አይነት መግለጫ የሚሰጠው ከፍራቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ለመንግስታዊ ሚዲያዎች ሰጡት በተባለው አስተያየት በሃይማኖት ውስጥ ችግር አለ እስከተባለ ድረስ እና የታሰሩ ሰዎች እስኪፈቱ ድረስ ፓርቲው ትግሉን ይቀጥላል ብለዋል።  በዛሬው በሰልፉ በቅርቡ በቤንሻንጉል ክልል እንግልት የደረሰባቸው የአማራ ክልል አርሶ አደሮች አደሮች ጉዳይ ፣ በአሸባሪነት ተጠርጥረው የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎችና የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው የተወነጀሉ ጋዜጠኞች ከእስር ይፈቱ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ በየትኛውም አካባቢ ተዘዋውረን የመኖር መብታችን ይከበርልን ፣ ህገ መንግስቱን የሚቃወሙ አፋኝ አዋጆች ይሰረዙልን ብለዋል ሰልፈኞቹ ሲሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሃንም ዛሬ ጠዋትም ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል።



Ethiopian human rights protesters take to streets in Addis Ababa

$
0
0

Demonstrators demand government releases political leaders and journalists, and tackles corruption and economic problems…..

Ethiopian human rights protesters

(The Guardian) — Around 10,000 Ethiopians staged an anti-government demonstration on Sunday in the first large-scale protest since a disputed 2005 election ended in street violence that killed 200 people.

The demonstrators marched through Addis Ababa’s northern Arat Kilo and Piazza districts before gathering at Churchill Avenue in front of a obelisk with a giant red star perched on top, a relic of Ethiopia’s violent communist past.

Some protesters carried banners reading “Justice! Justice! Justice!” or pictures of imprisoned opposition figures. Others chanted: “We call for respect of the constitution.”

A few police officers watched the demonstration, for which the authorities had granted permission.

“We have repeatedly asked the government to release political leaders, journalists and those who asked the government not to intervene in religious affairs,” said Yilekal Getachew, chairman of the Semayawi (Blue) party, which organised the protests.

He said the demonstrators also wanted action to tackle unemployment, inflation and corruption.

“If these questions are not resolved and no progress is made in the next three months, we will organise more protests. It is the beginning of our struggle,” he said.

Ethiopian opposition parties regularly accuse the government of harassment and say their candidates are often intimidated in polls. The 547-seat legislature has only one opposition member.

Though its economy is one of the fastest-growing in Africa, Ethiopia is often criticised by human rights groups for clamping down on opposition and the media on national security grounds, a charge the government denies.

A 2009 anti-terrorism law makes anyone caught publishing information that could induce readers into acts of terrorism liable to jail terms of 10 to 20 years.

Last year, an Ethiopian court sentenced 20 journalists, opposition figures and others to long sentences for conspiring with rebels to topple the government.

At least 10 journalists have been charged under the anti-terrorism law, according to the Committee to Protect Journalists, which says Ethiopia has the highest number of exiled journalists in the world.

Muslims, who form about a third of Ethiopia’s mostly Christian population, staged mosque sit-ins in 2012, accusing the government of meddling in religious affairs and jailing their leaders.

Ethiopia, long seen by the west as a bulwark against radical Islamists in neighbouring Somalia, denies interfering, but says it fears militant Islam is taking root in the country.


ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ሞክረው…

$
0
0

እኔ እኮ ሁልጊዜ ግራ የሚገባኝ አቶ ሽመልስ ከማልን በእንዲህ ያለው ጉዳ ላይ ለምን እንደሚያጋፍጧቸው ነው፡፡ እርሳቸውስ ቢሆኑ አሁንስ አበዛችሁት ራሳችሁ ተናገሩ አይሉም እንዴ…! ውይ የኔ ነገር ቆይማ ነገርን ከስሩ እንዲሉ ለወጋችን ትንሽ መሰረት ብጤ እንጣልላት..

945562_456214187800412_886270627_n

ትላንት ሰማያዊ ፓርቲ ወንድ ሴት እስላም ክርስቲያን ሳትል በደለኛ ሁላ ና አደባባይ ውጣ እና መንግስትን አብረን እንቆጣው ብሎ ጠርቶ አልነበር… ታድያኮ ባማረ እና በደመቀ መልኩ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል፡፡ በእውነቱ ይህ ህዝብ ከመሪዎቹ የሚበልጥ አይደለምን…!

ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የማታ ማታ አስቦ አስቦ ሰልፉን የተመለከተ ዘገባ አቅርቧል፡፡ በዘገባው ላይ የሚመለከታቸው አካል ተብለው ማብራሪያ ሊሰጡ የተጋበዙት አቶ ሽመልስ ከማል ናቸው፡፡

መጀመሪያ ላይ አቶ ሽመልስ ሰልፉን አስመልክቶ የሚነግሩን አለ ሲባል የሰልፉ አስተባባሪ እርሳቸው ነበሩ እንዴ… ብዬ ተደንቄ ነበር፡፡ ኢቲቪ ግን ምንም አይደብረውም… የሰልፉን አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች አንድ ጥያቄ እንኳ ሳጠይቅ ቀጥታ ከመንግስት ወገን ምላሽ እና ማብራሪያ እንዲሰጡ አቶ አቶ ሽሜን የሚጠራቸው…

የሆነ ሆኖ አቶው መጡና “በሰልፉ ላይ ሲንፀባረቁ የነበሩ መልዕክቶች ከህገመንግስቱ ጋር የሚጣረሱ ናቸው” ብለውን እርፍ አሉት፡፡ አቶ ሽመልስ ይሄንን ያሉት ሃይማኖት እና ፖለቲካ መነጣጠል አለባቸው ከሚል መነሻ እንደሆነ ሊያስረዱን ሞክረዋል፡፡ አባባላቸውን ከኢህአዴግኛ ወደ አማርኛ ስንቀይረው፤ የሀይማኖት ሰዎች የፈለገ በደል ቢደርስባቸው ዝም ብለው ዱዓ ያደርጋሉ እንጂ ለመንግስት አቤት አይሉም የሚል ይመስላል፡፡

እኔ የምለዎ አቶ ሽመልስ… ሃይማኖታቸወን ስላራመዱ ሰዎች መታሰር የለባቸውም… ብሎ መጠየቅ ህገ መንግስቱን እንደመናድ ከተቆጠረ፤ እርስዎን በቴሌቪዥን ማቅረብስ ህገመንግስቱን የመደርመስ ያህል ቢቆጠር ምን ይመስልዎታል…!

አሁንስ ይሄ ህገመንግስት አሳዘነኝ ምንድነው ይሄን ያህል በካርቶን ነው እንዴ የተገነባው በሆነው ባልሆነው የሚፈርሰው!

እዝችው ላይ አቶ ሽመልስ፣ ኢቲቪ እና አንዳንድ ስማቸውን ብንጠቅስም ባንጠቅስም ዋጋ የሌላቸው ሰዎች ሰልፉ ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይበዛል አይበዛም እያሉ ጉንጭ አልፋ እና ፌስ  ቡክ አልፋ ንግግር  ሲናገሩ ተደምጧል፡፡ ተነቧልም፡፡ የሚያስቀው እነዚሁ ግለሰቦች ከሰልፉ ቀደም ብለው በሰልፉ ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ አይሳተፍም እያሉ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ናቸው፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ አዎ በብዛት ተሳትፏል፡፡ እንደኔ እምነት እንደውም ሰልፉ በሰላም ለመጠናቀቁ አንዱን አስተዋፅኦ ያደረገው ሙስሊሙ ህብረተሰብ በብዛት በመሳተፉ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከአመት ላለፈ ጊዜ ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ስለነበረ ያንን ልምድ ለሰማያዊ ሰልፈኞች አጋርተዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡

እና ሙስሊሙ ህብረተሰብ በብዛት መሳተፉ ጉዳቱ ምንድነው… ሙስሊሙ በደል ስለደረሰበት ስለሀገሩ ግድ ስለሚለው ተሰለፈ፡፡ ሴቷ በደል ስለ ሀገሯ ግድ ስለሚላት ተሰለፈች፡፡ ወጣቱ በደል ስለደረሰበት እና ስለ ሀገሩ ግድ ስለሚለው  ተሰለፈ፡፡ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱም በደል ስለደረሰባቸው እና ስለሀገራቸው ግድ ስለሚላቸው ተሰለፉ፡፡ ታድያ ይሄ ምን ይገርማል…

አቶ ሽመልስ ሌላው ያሉን ነገር “ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ መንግስት ቀድሞ መልስ ሰጥቶታል” ብለዋል… አይ ጋሽ ሽሜ… እኔ እኮ ሁልጊዜ ርስዎን ለምን እንዲህ እንደሚጋፍጡዎት ነው የሚገርመኝ፡፡ አቶ በረከት ግን አይወዱዎት የምሬን ነው የምልዎ… እንዲህ ሲናገሩ የሰማዎ ሰው ሁሉ እኮ እንደኮሜዲያን እንጂ እንደባለስልጣን አይመለከትዎትም፡፡ አቶ ሽሜ ለማንኛውም ጥያቄው አፋናቃዮቹ ለፍርድ ይቅረቡ ነው፡፡ ይልቅ ከአፈናቃዮቹ ውስጥ ዝርዝርዎ እንዳይኖር ይስጉ…

የጋዜጠኞችን እስር ጉዳይ፣ የፕሬስ አፈናውን እና የኑሮ ውድነቱን አስመልክቶ የተነሱትን ጥያቄዎች፤ ኢቲቪም አቶ ሽሜም ሆን ብለው የረሱት ወይም በአጠቃቀስኩ ያለፉት ይመስለኛል፡፡ ግን እንዲህ በማደባበስ የትም አይደረስም፡፡

ኢህአዴግዬ ብልጥ ከሆነች የተጠየቀችውን በሙሉ ተግባራዊ አድርጋ ተቃዋሚዎቿን አፍ ማዘጋት ነው ያለባት፡፡


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ሉግዲ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

$
0
0

4444444

የወያኔው አምባገነናንዊ ስርዓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን የግፍና የመከራ እንዲሁም የችግርና የሰቆቃ ዘመን ለማሳጠር ስርዓቱን በግንባር እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ሉግዲ በተባለው አካባቢ ከወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ጋር ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት.. በተካሄደው ውጊያ 44 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 66 በማቁሰል እንዲሁም ብዛት ያላቸው ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነሙሉ ትጥቃቸው በመማረክ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሚንቀሳቀስባቸው የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተለይም በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ፣ ወልቃይት፣ ቋራና መተማ ግንባሮች በተለያዩ ጊዜያት በጠላት ላይ በሚሰነዝራቸው ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ በወያኔ የታጠቁ ሀይሎች ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሀገርንና ወገንን የመታደግ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በመነሳት ኢትዮጵያዊ ኩራት መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል።

በወታደራዊ ሀይልና በመሳሪያ ብዛት የተመካው ጎጠኛው ስርዓት አሁንም ከሚሰነዘርበት የሀይል ጡጫ መቋቋም የተሳነው በደረሰበት ሽንፈትና በተከናነበው የሐፍረት ካባ ጀርባውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት እያሳዬ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ መፈርጠጡም ታውቋል።

በመጭረሻም ግንባር የጀመረውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማዳን ተልዕኮ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ እንደሚገፋበት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስታውቃል


ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ የአስቸኳይ ሃገራዊ ጥሪ

$
0
0

መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የዓለም ማህበረሰብ እንደሚገነዘበው ሁሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄም የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ ስርዓት እያከተመ እንደሚገኝ ይገነዘባል፡፡
የዓለማችን ተመሳሳይ ታሪኮች እንደሚዘክሩት ሁሌም በአምባገነኖች መዳፍ ስር የወደቁ ሃገራትና ህዝቦች ጨቋኞቻቸው ባልታሰበ ሁኔታ በሞት ሲሸኙ ቀጣዩ ሂደት በአብዛኛው ጊዜ እጅግ አሳዛኝና ወደባሰ አዘቅት ሲወስድ ታይቷል….፡ በአንፃሩ ደግሞ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ሃገራት በህዝቦች በሳል ትግልና መስዋዕትነት እንዲህ አይነቱን ፈታኝ አጋጣሚዎችን በአግባቡ በመጠቀም ወደ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመቀየር መልካም የታሪክ ትሩፋቶች ሆነው አልፈዋል፡፡
ከዚህም ታሪካዊ እውነታ በመነሳት የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ስርዓት ውድቀትን ተከትሎ የሚፈጠረውን የስልጣን ሽኩቻ ምን ያህል አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችል በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ አበው “ሌባ ሲሰርቅ ይስማማል፣ ሲካፈል ደግም ይጣላል” እንዲሉ ፤ በተለይም ሽኩቻው ላለፉት 21 ዓመታት በዙሪያው ባሰባሰባቸው ፈርጀ ብዙ ዘራፊ ቡድኖች መካከል ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ይገመታል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይህ ዘረኛና እኩይ ሰው በማን አለብኝነትና በእብሪት በጎረቤት ሃገራት ላይ በወሰዳቸው አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችና ወረራዎች ምክንያት ሃገራችንና ህዝባችን ሁሌም ለአደጋ እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡ በዚህ ፈታኝ ወቅት የሚፈጠረውን ባለቤት አልባነት በንቃት የሚከታተሉና ለበቀል ያቆበቆቡ ጎረቤት ሃገራት የሁኔታውን አመቺነት በመጠቀም አሳፋሪ የታሪክ ጠባሳ ሊያሸክሙን ይችሉ ይሆናል፡፡
ከላይ ከተቀመጡት ግልፅ አደጋዎች በተጨማሪ እጅግ ብዙ አሳሳቢ ሁኔታዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ዋና አላማ አደጋዎችን ማመላከት ብቻ ሳይሆን በይበልጥ ይህንን የታሪክ አጋጣሚ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በኢትዮጵያ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በዘላቂነት እንዲገነባ ማስቻል ነው፡፡

ይህንን እውነታ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድና በማስተዋል ከተጠቀምንበት ለእኛ ለኢትዮጵያውያንና ለምንወዳት ሃገራችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ይከፍትልናል ብለን በፅኑ እናምናለን፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በዚህ ፈታኝ ወቅት ለምንመኘው ታሪካዊ ድል በጎ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል የሚላቸውን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድነት የሚያቀናጅ ሃገራዊ ጥሪ ከዚህ እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

1ኛ. ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፆታ፣ እድሜ፣ ሃይማኖት፣ ጎሳና፣ ዘር ሳይለይ ለአለፉት ዘመናት በተለይም በአምባገነኖቹና በጨካኞቹ የመንግስቱ ኃ/ማርያምና የመለስ ዜናዊ ስርአቶች እንደ ባእድ ወራሪ በገዛ ልጆቹና ሃገሩ የግፍ ግፍ ሲፈፀምበት፣ ምድሪቱም በደም ጎርፍ ስትታጠብና፣ ሁሉም በሚችለውና በአቅሙ እነዚህን የሰው አውሬዎች ከላዩላይ ለማስወገድ ሲኳትንና በመራራ ትግሉና በውድ ልጆቹ መስዋዕትነት የመጀመሪያውን ጭራቅ አስወግዶ ሁለተኛውን እኩይ ሲተካ ሃዘኑ ያልጠናበትና ፈጣሪውን ያላማረረ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡
ይሁንና ሁልግዜም ታሪክ እንደሚዘክረውና ድርሳናት እንደሚነግሩን “በጨለማ የነበረ ህዝብ ብርሃን አየ” ነውና በጭቆና ውስጥ ያለን እኛ ኢትዮጵያውያን ይዋል ይደር እንጂ ነፃነታችንን መቀዳጀታችን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ እነሆ ዛሬ የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ጨቋኝ ስርዓት የጀመረውን የግፍና የጥፋት መንገድ ሳያጋምስ በሃያሉ የኢትዮጵያ አምላክ እጅ ለፍርድ ተይዟል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ እኩይ ስርዓት በህዝባችን መካከል የዘራቸው የጥላቻ፣ የበቀል፣ የክህደትና፣ የመለያየት መርዞች ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይም የብሔርተኝነት፣ የጎሰኝነት፣ የጎጠኝነትና፣ ብሎም የመንደርተኝነት መርዙ ምን ያህል የከፋና የከረፋ መሆኑን በአለፉት 21 የሰቀቀንና የጭንቅ ዓመታት እሬት እሬት እያሉን አጣጥመናቸዋል፡፡ ይበልጡንም ወንድማችንና ጋሻችን የሆነውን ጨዋውን “የትግራይ” ህዝብ በስሙ በመነገድ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠልና ሌሎች ብሄረሰቦች በጠላትነት እንዲነሳሱበት ለማድረግ ያልተቆፈረ ጉድጓድና ያልተሸረበ ምድራዊ ሴራ አልነበረም፡፡ ነገር ግን የህዝባችን አንድነትና ፍቅር የተሸረበበት ድር የአለፉት እልፍ አእላፋት ትውልዶች ለአንድነትና ለነፃነት በተሰዋ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ደም በመሆኑ የከፋፋዮቹ ህልም እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ሊሳካ አልቻለም፡፡ የተመኙትንም ኢትዮጵያን የማፍረስና ህዝቧን የማጫረስ ፋሽስታዊ ተልእኮና ህልም ሳያሳኩ ወደ ጥልቁ “በአቦሸማኔ” ፍጥነት እየተምዘገዘጉ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ሰአት በሃገራችን የተፈጠረውን ታሪካዊ ክስተት የአምባገነኖች ቡድን እንዳይቀለብሰውና ወደ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሊደረግ የሚገባውን ታሪካዊ ጉዞ እንደለመዱት ለእኩይ አላማቸው መጠቀሚያነት እንዳያውሉት ህዝባችን ነቅቶ ሊጠብቅ ይገባል፡፡ ሁላችንም ልክ እንደ አባቶቻችን ሃገራችንና ህዝባችንን ከሁሉም ነገር በላይ በማስቀደም፤ በአንድነትና በፍቅር ፀንተን በመቆምና፤ በማስተዋል እኩዩ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የዘራውን የመጠፋፋት መርዝ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከስር መሰረቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማፅዳት ታሪክ የጣለብን አደራና ፈተና ነው ብሎ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በፅኑ ያምናል፡፡
ስለዚህም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶቹ ያቀበሉትን የመለያየት አጀንዳ በማጥፍት፤ ለነፃነቱ መከበር በአንድነት በመቆም ለህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምስረታ በፅኑ እንዲታገልና ከእጁ የገባውን ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ ዳግም ለአምባገነናዊ ስርዓት አሳልፎ እንዳይሰጥ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

2ኛ. ለሃይማኖት ተቋማት
“ኢትዮጵያ የሃይማኖት ደሴት ናት!” የዓለም ታሪክና ታላላቆቹ የየዕምነቱ መሪዎች ከተናገሩልን፤ የሃይማኖት ድርሳናትም በትልቁና በደማቁ ከከተቡልንና ዛሬም የዓለም ህዝቦች በአድናቆትና በግርምት ከሚመለከቱት ማንነታችን መካከል ዋነኛው መገለጫችን ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያውያን በሁሉም ሃይማኖቶቻችን በመከባበርና በመቻቻል በአንድነት የኖርንባትና የምንኖርባት የቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ባለቤቶችና ጨዋ ህዝቦች መሆናችንን በኩራት የምንናገረው ሃቅ ነው፡፡ እንዲሁም ይህን ማንነታችንን በተለያየ ጊዜና ዘመናት ለአደጋ የሚያጋልጡ ክስተቶች እንደነበሩና አባቶቻችን በድል አድራጊነት እንደተወጡት እናውቃለን፡፡ እነሆም ዛሬ በእኛ ዘመን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይህን ኩራታችንን ለመናድ የተለያዩ ትንኮሳዎችን አስተናግደናል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ የሃገሪቱን የመንግስት ስልጣን የያዘው የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አስተዳደደር በሃይማኖት ተቋሞቻችንና ይዞታዎቻችን ቀጥተኛ ትንኮሳ፣ ወረራና፣ ግድያ ሲፈፅምብን ኖሯል፡፡እየፈፀመም ይገኛል፡፡ ይህንንም በእውነተኛና ታማኝ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናንና፣ ተቋማት ላይ ሲፈፀም የነበረውን ግፍና መከራ እስከ አሁን ድረስ በፅናት እየታገልን እንገኛለን፡፡ በዚህም ህዝባችን ድል እንደሚቀዳጅ እርግጠኞች ነን፡፡
ወገኖቻችን ! ዛሬ ሃገራችን ኢትዮጵያ እጅግ አሳሳቢ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ስለሆነም እንደ አንድ ኩሩና ጀግና ህዝብ በዚህ ሰአት ለገጠመን ሃገራዊ ፈተና ቅድሚያ በመስጠት እስከዛሬ በፅናት የታገላችሁላቸውን ሃይማኖታዊ ክብርና መብቶቻችሁን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጋራ ያለምንምና ማንም ተፅዕኖ የምንጎናፀፈው በሃገራችን ሰላም፣ዲሞክራሲና፣ ፍትህ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ለዚህ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ቅድሚያ በመስጠት ትኩረታችሁን፣ ፀሎታችሁንና፣ ድጋፋችሁን በሃገራችን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲመሰረት ለምንፈልገው ሁሉንም ወገኖች በእኩልነት የሚያሳትፍ ስርዓት ምስረታ ታደርጉ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

3ኛ. ለፖለቲካ፣ ለሲቪክና፣ ለግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በሙሉ
ለአለፉት ዘመናት ደከመንና ሰለቸን ሳትሉ ለሃገራችሁ እድገት፣ ለህዝባችሁ አንድነትና ነፃነት፣ እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ህዝባዊ መንግስት ምስረታ ሌት ከቀን የባዘናችሁና በዱር በገደሉ የተንከራተታችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችና፣ የሙያ ማህበራት በሙሉ እነሆ የታገላችሁለትን አላማ አጨናግፎና እናንተንም ለእስር፣ ለአካል ጉዳተኝነት፣ ለስደትና፣ ለሞት ይዳርጋችሁ የነበረው የእኩዩ የመለስ ዜናዊ ስርዓት ህልውና እያከተመ ይገኛል፡፡
ምንም እንኳ ይህ የአምባገነኖች ስርዓት የመጨረሻው ስንብት ላይ ቢሆንም “ሌባ ሲሰርቅ…..” እንደሚባለው ሁሉ እየተፈጠረ ያለው የሃይል ሚዛን መዛባት የዘራፊውን ቡድን እርስ በእርስ እንደሚያባላቸውና አሸናፊው የአውሬው ክንፍ ዝርፊያውን ለማስቀጠል መንበሩን ለመያዝና መሪውን ወደ ፈለገው ለመጠምዘዝ እንደሚሞክር እሙን ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ከህዝቡ ጋር ካለው ቀጥተኛ ግንኙትና ተጨባጭ መረጃ በመነሳት የመለስ ዜናዊ የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሸው ህዝባችን በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ህዘባዊው ቁጣ ሊፈነዳ ጫፍ ላይ የደረሰ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም እስከ ዛሬ ደንቃራ ሆኖ አንድነታችሁንና ህብረታችሁን የተፈታተነውን የንድፈ ሃሳብ ልዩነት ወደጎን በመተው ለማይቀረው ህዝባዊ ቁጣና ለህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አፋጣኝ የጋራ አስተዋፅኦና ድጋፋችሁን ታበረክቱ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

4ኛ. ለመምህራን፣ ለተማሪዎች፣ ለአርሶ አደሩ፣ ለሲቪል ሰራተኛውና፣ ለነጋዴው የህብረተሰባችን ክፍሎች በሙሉ
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ እስከዛሬ ድረስ የህልውናችን መሰረት በመሆን፤ ከትውልድ ትውልድ ታሪካዊ ሃላፊነታችሁን እየተወጣችሁ በተቻላችሁ መንገድና አቅም ሁሉ አምባገነኖችን በመታገል ላሳያችሁት ፅናትና ተጋድሎ ታላቅ አክብሮቱን ይገልፃል፡፡ በተመሳሳይ እንደ ቀደሙት ታሪካዊ ክስተቶች ሁሉ ዛሬም በጨካኙና በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ መወገድ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን አለመረጋጋትና ህገወጥነትን በመገንዘብ አካባቢያችሁን፣ ሃገራችሁንና፣ ማህበረሰባችሁን ከማንኛውም ጥቃትና ምዝበራ ነቅታችሁ ትጠብቁ ዘንድ፤ እንዲሁም ለሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በሚደረገው የህዝብ ትግል ፍፁም ሰላማዊ በመሆ መንገድ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የተለመደውን ታሪካዊ ግዴታችሁንና ሃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

5ኛ. ለሃገር መከላከያና ለፖሊስ ሰራዊቱ አባላት
ለአለፉት 21 ዓመታት አምባገነኑ የመለስ ዜናዊ መንግስት ያደርስባችሁ በነበረው ከፍተኛ ተፅዕኖ ምክንያት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ስታስፈፅሙ እንደነበራችሁ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ዛሬ የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድበት ወቅት መድረሱ እውን ሆኗል፡፡ ስለሆነም ይህ ታሪካዊ ክስተት ከማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ ለእናንተ ኢትዮጵያዊ ወገናችሁን ለመካስ የሚያስችል ልዩና መልካም አጋጣሚ ይዞላችሁ እንደመጣ እናምናለን፡፡
ይኃውም የሃገራችሁን ዳርድንበርና የህዝባችሁን ደህንነት በቅንነትና በታማኝነት የመጠበቅና የማገልገል ታላቅ ሃገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ትወጡ ዘንድ ያስችላችኃል ብለን እናምናለን፡፡ በተለይም በዚህ ወቅት ህዝባችሁንና ሀገራችሁን ከማንኛውም ጥቃትና አደጋ እንድትታደጉና ወደ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገውን ፍፁም ሰላማዊ የህዝብ ትግል ከማንኛውም የአምባገነኖች ጥቃት ነቅታችሁ በመጠበቅና በመከላከል አኩሪ ታሪክ ትሰሩ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

6ኛ. ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አባላት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አባላት ህዝብ የጣለባችሁን ወሳኝ ሃገራዊ አደራ በአግባቡ እንዳትወጡና አምባገነኑን መለስ ዜናዊንና ስርአቱን ለመጠበቅ ሲባል ብቻ በግዴታ የኢትዮጵያን ህዝብ በማሳደድ አስነዋሪ ተግባር ውስጥ እንድትዘፈቁ መደረጉን በአለፉት 21 ዓመታት በህዝባችን ላይ የተፈፀሙት ግፎች ያረጋግጣሉ፡፡ ነገርግን ዛሬ ያ የጨቋኙ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እንደሚወገድና በምትኩም ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚመሰረትበት አዲስ የታሪክ አጋጣሚ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለእናንተም እኩል እየመጣላችሁ መሆኑን እናምናለን፡፡
ስለሆነም እናንተም ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ በአግባቡ በመጠቀም መላው ህዝባችሁንና ኢትዮጵያ ሃገራችሁን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ጥቃት በንቃት በመጠበቅ፣ እንዲሁም አሁን በጨቋኙ የመለስ ዜናዊ ስርዓት ውስጥ የተፈጠረውን የሃይል ክፍተት በመጠቀም በሃገራችን ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን የስርዓት አልበኝነት ትከላከሉ ዘንድ ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን፡፡ በአጠቃላይ ህዝባችን ለሚያደርገው ፍፁም ሰላማዊ የሆነ የህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት ምስረታ ሂደት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ በማበርከት ታሪካችሁን በክብር መዝገብ ላይ ታሰፍሩ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

7ኛ. ለጋዜጠኞችና ለሚዲያው ማህበረሰብ በሙሉ
ከአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አውሪያዊ አገዛዝ ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለእውነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለፍትህና፣ ለነፃነት አኩሪ ተጋድሎ እያደረጋችሁ ለምትገኙት ክቡራንና ክቡራት የኢትዮጵያ ነፃ ሚዲያ አባላት፤ እንዲሁም አቅማችሁ በፈቀደው ሁሉ መረጃ በመስጠትና በማስተለላለፍ ለተሳተፋችሁ “የእውነት ብርሃኖች” ሁሉ ዛሬ በሃገራችን እየተፈጠረ የሚገኘውን አዲስ የታሪክ ክስተት በንቃት እየተከታተላችሁ እንደምትገኙ እናምናለን፡፡
እንደሚታወቀው ምንም እንኳ የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ፍፃሜ የተቃረበ ቢሆንም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሃገራችንን ወደ አዲስ የነፃነት፣ የዲሞክራሲና፣ የፍትህ ምዕራፍ ለማሸጋገር ይቻል ዘንድ በሁሉም አቅጣጫ ብልህነት የተሞላበት አካሔድ እንደሚያስፈልገው አያጠራጥርም፡፡
ስለሆነም ይህንን ታሪካዊ ክስተት ተከትሎ የሚከሰተውን ውጥንቅጥ በማጋለጥና በማጥራት፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለምዓቀፉ ማህበረሰብ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ በወቅቱ በማድረስ ህዝባችን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሚያደርገው የህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትግል የበኩላችሁን አስተዋፅኦ በማድረግ የዜግነት ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

8ኛ. ለመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ አባላትና ደጋፊዎች፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣቶች በሙሉ
ለአለፉት 21 ዓመታት ሲያሰቃየን የኖረው እኩዩ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እያከተመለት እንደሚገኝ እርግጥ ነው፡፡ በመሆንም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወጣት ከፊት ለፊታችን ተሰቅሎ የሚታየንን የአምባገነኖችን ዘላለማዊ የጨለማና የውርደት መቃብር በጉጉትና በተስፍ እየተመለከትን፤ ከውልደታችን ጀምሮ የምንናፍቀውንና የምንጓጓለትን ነገር ግን ልናየውና ልንኖርበት የተከለከልነውን ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት መልካም አጋጣሚ በእጃችን እንደገባ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ይረዳል፡፡ እንዲሁም ከሁሉም በላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ገደብና ቅደመ ሁኔታ በእኩልነት፣ በነፃነትና፣ በፍትሃዊነት የምንኖርባትን ታላቋን ኢትዮጵያ ማየት የወጣቱ ትውልድ ታለቅ ራዕይ መሆኑንና የመገንባቱም ዕጣ-ፋንታ ዛሬ በትክሻው ላይ እንደወደቀ እናምናለን፡፡
ነገርግን እስከ አሁን ድረስ እግር በእግር እየተከተለ የነፃነት፣የፍትህ፣የእኩልነትና፣ የዲሞክራሲ ፍላጎትና ተስፋችንን እያመከ የሚገኘው የአምባገነኖች ርዝራዥ ሃይል ተጠቃሎ ከእነ እኩይ ምግባሩና ሴራው ከሃገራችንና ከህዝባችን ጫንቃ እስኪወገድ ድረስ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ የትግል መስክ እንደ አቅማችንና ችሎታችን ተሰልፈን በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ መስዋዕትነት እየከፈልን የምንገኝ ወጣቶች ሁሉ ወደ ዲሞክራሲያዊ ህዝባዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ጉዞ ግቡን እስኪመታ ድረስ በፅናትና በቁርጠኝነት ትግላችንን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እስከመጨረሻው እንድንቀጥል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ለማሳሰብ ይወዳል፡፡ ስለሆነም በዚህ የታሪክ አጋጣሚ በአምባገነኖች መንደር ሊፈጠር የሚችለውን ትርምስ ተገንዝበን ለውጡ “የጉልቻ መለዋወጥ” ብቻ ላይ ተገድቦ ሂደቱ ዳግም የትውልድ ተስፋችንን እንዳያጨልምብንና ዳግመኛ ሃገራችን በሌላ አምባገነናዊ ስርዓት እንዳትጠለፍ ሂደቱን በንቃት በመከታተልና ባሉት ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች በመሆን ሃገራችንን ወደ ምንመኘው ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር በአንድነት እንድንቆም የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ!


ጦር ሃይሎች ውስጥ የተከሰተው የእርስ በእርስ ፍትጊያ ተሟሙቋል::

$
0
0
ከጦር ሃይሎች መኮንኖች የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው የወያኔ ከፍጠኛ የጦር ጄኔራሎች በመንግስታቸው በኩል የቀረበባቸውን ውንጀላ ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ በመግባት እርስ በእርሳቸው እየተፋተጉ መሆኑን ታውቋል… ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተደረገው እና አሁንም በቀጣይነት በመኮንኖች ክበብ ውስጥ በከፍተኛ መኮንኖች እና የጦር መምሪያ ሃላፊዎች ላይ የቀጠለው ግምገማ ውጠቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የሆነው ሌ/ጄ. ሳሞራ የኑስ ዋናው አትኩሮ ሲናገር የነበረው በመረጃ ንግድ ላይ የተሰማራችሁ የጦር መኮንኖች ምስጢራችንን አሳልፋችሁ ሸጣችኋል እና ብትጠነቀቁ መልካም ነው ካልሆነ የመጨረሻ እርምጃ እንወስዳለን ሲል ዝቷል:: ከመከላከያ ውስጥ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ አላግባብ ጠፍጥቷል የተባለው እና ለወያኔው ምር ቤት የቀረበው የኦዲት ሪፖርት በመኮንኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግብግብ እየፈጠረ ሲሆን ለግምገማው መራዘም ምክንያት መሆኑን ምንጮሹ ለምንልክ ሳልሳዊ ተናግረዋል:: ይህንን ተከትሎ አንዳንድ  የተመረጡ የጦር መኮንኖችን ለመክሰስ የታቀደ ሲሆን አትኩሮት የሚደረግባቸው በሕወሓት ውስጥ በአሁን ወቅት ተከስቶ ያለውን ክፍፍል ተከትለው ከባለስልጣናት በተጻራሪ ወገን ቆመዋል የተባሉ የመለየት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል ምንጮቹ አክለውም ዝርዝር መረጃው በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል::

የወያኔ ፋሽስቶች መሠረትና ዕድገት

$
0
0

በኢትዮጵያ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ዘርን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ ድርጅት በ1942 ዓ.ም ለጣሊያን በባንዳነት አድረው ሲያገለግሉ በነበሩ የትግራይ ጎጠኞች ተመሠረተ… ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ሀገራችን በፋሽስት ጣሊያን ተወራ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ደረታቸውን ለጦር እግራቸውን ለጠጠር ሳይሰስቱ እየሰጡ አገራቸውን ለወራሪ አናስደፍርም ብለው በየጋራውና በየሸንተረሩ ተሰማርተው በኋላ ቀር መሣሪያ ጠላትን ሲፋለሙ ፤ለገንዘብ ወይም ለርካሽ ቁሳዊ ጥቅም ሲሉ ለጠላት አድረው ያገራቸውን ምስጢር የሸጡ፣ከጠላት ጐን ተሰልፈው አገራቸውን የወጉና ያደሙ ባንዳዎች “ቀዳማይ ወያኔ” ብለው በዘር ተደራጁ።

“ቀዳማይ ወያኔ” የሌቦችና የዘራፊዎች ስብስብ ስለነበረ፤በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትዕዛዝ በልዑል ራስ አበበ አረጋይ አማካኝነት በ1943 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። ይሁን እንጂ በ1966 ዓ.ም የተደረገን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ ሌላ ወያኔ በ1968 ዓ.ም በአቶ ስብሃት ነጋ ተፈጠረ። ይህ በአቶ ስብሃት ነጋ የተመሠተው ሀገር በቀል ፋሽስት ማዕከላዊ አቋሙ “አማራ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው” የሚል በመሆኑ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ የአማራን ነገድ ለማጥፋት ዕቅድ አውጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።

አቶ ስብሃት በዘረኝነትና በአልኮል የደንዘዘ ኋላቀር ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተመለከት ባላው የተሳሰተ የፖለቲካ አቋም ይታወቃል። ለአብነት “ገዛ ተጋሩ” በተሰኘው የዘረኞች ውይይት ክፍል ውስጥ አሰብ ወደብና የአማራ ነገድን በተመለከተ የሚከተለውን ዘረኛ አቋም አንጸባርቋል። “አሰብ የኤርትራ ወደብ ነው። በዚህ ወደብ ላይ የባለቤትነት ጥያቄ የሚያነሱ የደርግ ሥርዓት ናፋቂና ነፍጠኞች ብቻ ናቸው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት አማራ መሬት ስንገባ እናድንሃለን እያልነው የአማራ ገበሬ በሙሉ የወጋንም ንቃተ ህሊናው ትንሽ ስለሆነ ነው ብሏል።”

ይህ ከቂምና ከጥላቻ በስተቀር ፍቅርን የማያውቅ የወያኔ ትግሬ በእርጅና ዘመኑ እንኳ ራሱን መግራት ያቃተው በመሆኑ፤ “ስልጣንን ከኦሮቶዶክስና ከአማራ እጅ ነጠቅናት ይህም የትግላችን ውጤት ነው” ማለቱን ሰምተናል። ባለፉት አርባ ዓመታት የትኛው አማራ፤ የትኛው ኦሮቶዶክስ ስልጣን ይዞ ነበር ቢባል ግን መልስ የለውም። የከሃዲው ስብሃት ነጋ አባባል ግን ለአማራ ነገድና ለኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን ያለውን ሥር የሰደደ ጥላቻ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። መለስ ዜናዊም በህይወት ዘመኑ ለቤተክርስትያኒቷና ለአማራ ነገድ ባለው ጥላቻ መሠረት ቤተክርስትያኒቷን ለማፍረስ የቻለውን ሁሉ አድርጓል። የአማራንም ነገድ ለማጥፋት ብዙ አረመኔያዊ ተግባራትን ፈጽሟል።በእርሱ የአገዛዝ ዘመን 2.4 ሚሊዮን በላይ አማራ ከቁጥሩ ጎድሎ የት እንደገባ ሳይታወቅ ቀርቷል።

ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የአማራ ነገድ የት ገባ ተብሎ የተጠየቀው መለስ ዜናዊ ያለምንም ሃፈረትና ታሪክና ሰው ምን ይለኛል ሳይል “በኤድስ አልቋል” ብሎ በድፍረት መልስ ሰጥቷል።ይሄ በጣም አሳፋሪ እና ነውር ነገር ነው። በተለይም አገርን እመራለሁ ብሎ በህዝብ አናት ላይ ከተቀመጠ ሰው አንደበት ሲወጣ። የወያኔ ፋሽስቶች እንዲህ ያለውን አሳፋሪንና ነውር ነገረን ለይተው አያውቁም ማለት አይቻልም። አንድን ነገድ ለይተው “በኤድስ አለቀ” ብለው መናገራቸው በአማራ ነገድ ላይ የፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በግልፅ ያረጋግጣል።

በአጠቃላይ የወያኔ ፋሽስቶች ለአማራ ነገድ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋትና ወንጀል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ተደርሷል።የሩቁን እንኳን ብንተወው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ተፋፍሞ በቀጠለው አማራን ከቤትና ከንብረቱ በግፍ የማፈናቀል ዘመቻ ከ100 በላይ አማሮች ተገድለዋል። በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ጎዳና ላይ ተጥለው በርሃብ ፣በብርድና በበሽታ በመሞት ላይ ይገኛሉ።ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ማስቆምና ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ቢሆንም ዘራቸው በመጥፋት ላይ ያለው የአማራ ነገድ አባላት ራሳቸውን ለማዳን የወያኔ ፋሽስቶችን ማግለልና ከህብረተሰቡ እንዲነጠሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።


አዲስ ፍጥጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ

$
0
0

Untitledበጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ውስጥ የፖለቲካ ፍጥጫ እና የስልጣን ሽኩቻ እየታየ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል:: በሁለት ወገን በሕቡእ እንደተሰለፉ የሚታሙት እንዲሁም ለሕወሓት መረጃ ያቀብላሉ በሚባሉ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ግብግብ መፈጠሩን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል…

ምንጮቹ እንደጠቆሙት ከሆን በረከት ስምኦን የራሱን ቡድን አደራጅቶ ሕወሃቶችን በማለሳለስ ሃይለማርያምን እየመራው እንደሚገኝ የገለጡ ሲሆን ለላኛው ቡድን ደሞ ለሃይለማርያም ድፍረት ለመስጠት እየሰራ የሚገኝ እና የሕወሃት ደህንነቶችን በጥገኝነት የተጠጋ መሆኑን ገልጸዋል:: በረከት ስምኦን በተለያዩ ጊዜያት ከሃይለማርያም ጋር ስምምነት እንዳሌለው ያዩ እና በመካከላቸው አለመግባባት መኖሩን የተመለከቱ የወያኔ የበላይ አመራሮች እስከመቼ ተመሪ ሆነህ ትቀጥላልህ በማለት ሃይለማርያምን የሚያደፋፍሩ ሲሆን በተዘዋዋሪ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማንን ባልሽ እንዲደፍር አበረታችው በማለት የሚጠዘጥዙ ወገኖች እንደተፈጠሩ ምንጮቹ አክለው አስረድተዋል:: በረከት የራሱን ርእዮት አለም የሚደግፉለትን  ከተለያዩ ክልሎች ያሉ የኢህኣዴግ ካድሬዎችን በማደራጀት ላይ ሲሆን ብኣዴንን በተመለከተ ምንም የሚሰራው ድርጅታዊ ስራ እንደሌለ የተጠቆመ ሲሆን ከስልጣኑ ውጭ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት በተለያየ ጊዜ የሞከራቸው ሙከራዎች በአቶ ሃይለማርያም የተደናቀፉ መሆኑን እና ከተደናቀፉ ጉዳዮችም አንዱ ኤርትራውያንን በወያኔ ስር የማደራጀት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዜግነት የመስጠት በማለት ወደ ወያኔ/ኢህኣዴግ ይበልጥ ሰርገው እንዲገቡ ለመመልመል ያደረገው ሙከራ እና ቀጣዩን የወያኔ የስልጣን ርክክብ ለእነዚህ ላሰባቸው የኤርትራውያን ህዋሶች ለመስጠት ያሰበው ተደናቅፎበታል:: ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አከባቢ ፍጥጫ መኖሩን እና እንዳይካረር ያሰጋል ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::



ጠቅላይ ሚንስትሩ የትራንስፎርሜሽ እቅዱ እንዳልተሳካ እቅጩን ነግረውናል!

$
0
0

ጠቅላይ ሚንስትሩ በድፍረትየእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ያህል አልተሳካም:;መንግስት ያሰባቸው እና ያቀዳቸው ከግማሽ በታች እንኳን አልተሳኩም አሉ: ለጀሌዎቻቸው…

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህር ዳር ካሉት በመነሳት ነገሮች ሲወቀጡ በ1ለ5 እየሰበሰቡ የልማታዊ የፖለቲካ ሠራዊት ማደራጀት የተፈጥሮ ሃብት ልማት እያሉ ገበሬዎችን በዘመቻ ለፖለቲካ ፍጆታመጥመድ ልማት የሚባለው አልተሳካም። ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተጓተዋል የገበሬዎች የእርሻ ምርት፣ የእቅዱን ግማሽ ያህል እንኳ አልተሳካም፣ የእድገትና የትራንስፎርሜሽ እቅዱ የታሰበውን ያህል እየተሳካ እንዳልሆነና፣ በታለመለት መጠን እንዳልተሳካ እቅጩን ነግረውናል እርማችንን እንድናወጣ በሚል ።

ግዙፎቹን ፕሮጀክቶች ተመልከቱ። ከሁሉም በላይ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው የህዳሴ ግድብን መጥቀስ ይቻላል። በአምስት አመት ይጠናቀቃል የተባለው የህዳሴ ግድብ፣ አሁን በሚታየው ሁኔታ ከቀጠለ አስር አመት ሊፈጅ ይችላል። በሁለት አመት ውስጥ የተከናወነው ስራ 18 በመቶ ያህል ነውና። ሌሎቹ ትልልቅ ፕሮጀክቶችም ብንመለከት ከዚህ የተሻለ ውጤት አናገኝም። በአምስት አመቱ እቅድ ተገንብተው ስራ ይጀምራሉ የተባሉት 10 የስኳር ፋብሪካዎች፣ ገና በጣም ገና ናቸው። 10 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ይቅርና፤ ከሰባትና ከስምንት አመት በፊት እቅድ ወጥቶላቸው ቢበዛ ቢበዛ በሶስት አመት ይጠናቀቃሉ ተብለው የነበሩት የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎችና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችም እስካሁን ስራ አልጀመሩም።

በ1997ቱ የአምስት አመት እቅድ ውስጥ የተጀመረው የተንዳሆ ፕሮጀክት፣ የሸንኮራ ልማቱም ሆነ የስኳር ፋብሪካው ግንባታው ይሄው፣ ለ2002ቱ የአምስት አመት እቅድ ተሸጋግሮ አሁንም አልተጠናቀቀም። የመተሃራና የከሰም ፕሮጀክቶችም እንዲሁ እየተጓተቱና እየተሸጋገሩ የመጡ ነባር ፕሮጀክቶች ናቸው – በመጪው አመትም ስራ ይጀምራሉ ተብሎ አይጠበቅም። ሊጠናቀቅ ተቃርቧል የተባለው ነባሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እንኳ፤ በሚቀጥለው ወር፣ በሚቀጥለው የመንፈቅ አመት እየተባለ ስንት አመት አስቆጠረ? ይሄው ዘንድሮም፤ በጥቅምት ወር ስራ ይጀምራል ከተባለ በኋላ፤ ስራው ተጓትቶ ለጥር ይደርሳል ተባለ። ከዚያ ወደ መጋቢት ተሸጋገረ።

አሁን ደግሞ ወደ ሰኔ ወይም ወደ ሃምሌ። መንግስት እነዚህ ነባር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ሳይችል፤ ተጨማሪ 10 አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት ይችላል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ፤ “ተአምር” የማየት ረሃብ ይዟችኋል ማለት ነው። ሌላኛው ትልቅ ፕሮጀክት የባቡር ሃዲድ ግንባታ ነው። ይሄኛውም ፈቅ አላለም። ከሁሉም በላይ፣ በጣም ተስፋ አስቆራጭ የሆነው ደግሞ የእርሻ ምርት ብዙም ሲያድግ አለመታየቱ ነው። በአማካይ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ፣ የእርሻ ምርት በየአመቱ በ6% እንዲያድግ ነበር የታቀደው – በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ። የአምናው እድገት ግን፤ 2.5% ገደማ ብቻ ነው። የእቅዱ ግማሽ ያህል እንኳ አልተሳካም። መንግስትና ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ፣ ይህንን ያውቃሉ። በአምስት አመት ውስጥ ይተገበራል ተብሎ የወጣው “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ”፣ የታሰበውን ያህል እየተሳካ እንዳልሆነ ኢህአደግ በግልፅ ባይናገርም፣ የገበሬዎች ምርት የታሰበውን ያህል እያደገ እንዳልሆነ የሚክደው አይመስለኝም።

እንዲያውም፤ የኢህአዴግ ድርጅቶች ሰሞኑን ባካሄዷቸው ጉባኤዎች ጉዳዩ ተነስቷል። የእርሻ ምርት ላይ የሚታየው እድገት ዝቅተኛ እንደሆነ በኢህአዴግ ጉባኤዎች በየጣልቃው ጠቀስቀስ ተደርጎ ሲታለፍ ታዝባችሁ ይሆናል። ለምሳሌ ብአዴን በባህርዳር ባካሄደው ጉባኤ ላይ፤ “የአምናው የእርሻ ምርት እንደተጠበቀው አይደለም” ተብሏል። በሃዋሳው ጉባኤ ደግሞ፣ “የሰብል ምርት ላይ ድክመት አለ” ተብሏል። አሳሳቢነቱ፣ የአምና ምርት ከጠበቀው በታች መሆኑ ብቻ አይደለም። የዘንድሮው የመኸር ምርትም እንደተጠበቀው እንዳልሆነ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ጥናት ያረጋግጣል።

እናም፣ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ፣ የዘንድሮ የግብርና ምርት እድገትም እንደአምናው 2.5 በመቶ ገደማ ብቻ እንደሚሆን ይገመታል። ምን ለማለት ፈልጌ ነው? እንደሌሎቹ ዋና ዋና የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዶች ሁሉ፣ የእርሻ ምርትም የታቀደለትን ያህል እያደገ እንዳልሆነ ሊካድ አይችልም ለማለት ነው። በእርግጥ፣ ታዲያ በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ ለምን በጨረፍታ ብቻ ተጠቅሶ ታለፈ? “አልተሳካልኝም” ብሎ መናገር አስጠልቶት ሊሆን ይችላል። በአራቱም ጉባኤዎች ላይ እጅግ ሲበዛ ተደጋግሞ የተነገረውስ ምንድነው? የኢህአዴግ ድርጅቶች በሙሉ በየፊናቸው ባካሄዱት ጉባኤ፤ በገጠርና በገበሬዎች ላይ ስኬታማ ውጤት እንዳስመዘገቡ ደጋግመው ገልፀዋል። የተመዘገበው ውጤት ግን የምርት እድገት አይደለም። እናስ ምንድነው? “በልማት ሠራዊት ግንባታ” እና “በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” ዙሪያ እጅግ “አስደናቂ ውጤት” መመዝገቡን ነዋ የገለፁት።

አስደናቂውን ውጤት የሚያብራሩ “ድንቅ” መረጃዎችና ሪፖርቶችም ቀርበዋል። በመቶ ሺ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችን በ1ለ5 አደራጅተን ሰፊ “የልማት ሠራዊት” ገንብተናል ብለዋል የኢህአዴግ ድርጅቶች። በመቶ ሺ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ለ”ተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” በዘመቻ አሰልፈናል ተብሏል። በእርግጥም “የልማት ሠራዊት” ተገንብቶ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎች “ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” ለበርካታ ቀናት በዘመቻ ሲሰማሩና በየእለቱ እየጨፈሩ ሲመለሱ የሚያሳዩ የኢቲቪ ዘገባዎችን ተመልክተናል። ግን ምን ዋጋ አለው? የ“ልማት” እና የ“ሃብት” ውጤት አልተመዘገበም። የኢህአዴግ ድርጅቶች የሚያቀርቡት፣ ያ ሁሉ አስደናቂ ውጤትና ሪፖርት፤ በገበሬዎች የእርሻ ወይም የሰብል ምርት ላይ ከወትሮው የተለየ ቅንጣት ለውጥ አላመጣም።

ምን አስታወስኩ መሰላችሁ? ከአምስት አመት በፊት ነጋ ጠባ እንሰማው የነበር የ“ውሃ ማቆር” መፈክር። በ“ውሃ ማቆር” ምን ያህል አስደናቂ ውጤት እንደተመዘገ ለማስረዳት ይቀርቡ የነበሩ ድንቅ ሪፖርቶችን አታስታውሱም? በየክልሉ ምን ያህል እልፍ አእላፍ ገበሬዎች፣ ውሃ ማቆሪያ ጉድጓድ እንደቆፈሩ፣ በላስቲክና በሲሚንቶ ጉድጉዱን እያበጃጁ እንደሆነ በዝርዝር የሚተነትኑ እልፍ ዘገባዎችና ሪፖርቶች ቀርበዋል – ያኔ ከአምስት አመት በፊት። ለውሃ ማቆር ዘመቻ ስንትና ስንት ሚሊዮን ብር እንደተመደበ፣ በመቶ ሺ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችም በዘመቻው እንደተሳተፉ… የሚያብራሩና የሚዘረዝሩ ሪፖርቶች ትዝ አይሏችሁም? ምን ያደርጋል! አገሪቱ በ’ውሃ ማቆር’ ዘመቻ እንደምትለወጥ የሚያበስሩ ድንቅ ሪፖርቶች ሲቀርቡና ሲደመጡ ከርመው፣ ወራት አልፈው አመታት ተተክተው… መጨረሻ ላይ ሲታይ፤ ምንም ጠብ የሚል ውጤት ጠፋ።

በቃ፤ በገበሬዎች ምርት ላይ ምንም የመጣ ለውጥ የለም ተባለ። የኋላ ኋላ፣ የፌደራል ባለስልጣናትና ከየክልሉ የመጡ ርዕሰ መስተዳድሮችና ከፍተኛ መሪዎች በተሰበሰቡበት ነው ፍርጥርጡ የወጣው። በእርግጥ በስብሰባው ላይ፣ እንደወትሮው ድንቅ የውሃ ማቆር ሪፖርቶችና ማብራሪያዎች ቀርበዋል። በዚህ መሃል ነው፣ አንድ ቀላል ጥያቄ ዱብ ያለው… “ግን በገበሬዎች ምርት ላይ ያመጣው ለውጥ ምንድነው?” የሚል ጥያቄ። ጥያቄውን ለፌደራልና ለክልል ከፍተኛ መሪዎችና ባለስልጣናት በአፅንኦት ያቀረቡት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ነበሩ። ከመነሻው “ውሃ ማቆር” የሚለው ሃሳብ የመጣው፤ የገበሬዎችን ምርት የማሳደግ አላማን ለማሳካት ነበር።

አሁን ግን፣ የተነሳንበት አላማ እየተረሳ፣ የውሃ ማቆሪያ ጉድጓዶችን የመቁጠርና የመደመር ነገር… ራሱን የቻለ አላማ እየሆነ መጥቷል ያሉት አቶ መለስ፤ ሥራው የገበሬዎችን ምርት ለማሳደግ በሚጠቅም መንገድ እየተሰራ ነው ወይ? የውሃ ማቆር ዘመቻው ወደ ገበሬው ኪስ ተጨማሪ ገቢ በሚያመጣ መንገድ እየተሰራ ነው ወይ? በማለት አጥብቀው ጠይቀዋል። በእርግጥ፤ የውሃ ማቆር ዘመቻውን በቀዳሚነት ያቀነቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚገምቱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን፤ እዚህ ላይ ዋናው ቁምነገር፣ የሆነ እቅድ የታሰበለትን ውጤት እያስገኘ እንዳልሆነ በተግባር ሲታይ፣ ሳይረፍድበት ቆም ብሎ ማሰብ ማስፈለጉ ነው።

አለበለዚያ፣ ያሸበረቀ ሪፖርት ማዘጋጀትና የተንቆጠቆጠ መግለጫ ማቅረብ፤ በአንዳች ተአምር ወደ ምርት እድገትና ወደ ኢኮኖሚ እድገት እንዲቀየር እየተቁለጨለጩ መጠበቅ ይሆናል። የሆነ ሆኖ፤ “የውሃ ማቆር ዘመቻው ምን አይነት ተጨባጭ ውጤት አስገኘ?” በሚለው ጥያቄ አማካኝነት ነገሩ መቋጫ አገኘ። ከዚያ በኋላማ በየእለቱና በየሰዓቱ በሬድዮና በቲቪ ሲያሰለቸን የነበረው የውሃ ማቆር ነገር ድምፁ ጠፋ። በውሃ ማቆር ፋንታ፤ ባለፉት ሁለት አመታት በመንግስት ሚዲያ የሚቀርብልን የዘወትር ቁርስና እራት፤ “የልማት ሠራዊት ግንባታ” እና “የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ” በሚሉ ሃረጎች የተጥለቀለቁ “ድንቅ ሪፖርቶችና መግለጫዎች” ናቸው – የገበሬዎችን ምርት ለማሳደግ ይጠቅማሉ እየተባለ። ነገር ግን፣ የአምናውና የዘንድሮው ተጨባጭ የምርት መጠን ሲታይ፣ እነዚያ ድንቅ ሪፖርቶች፣ የገበሬዎችን ምርት ለማሳደግ እየጠቀሙ አለመሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል።

በ1ለ5 የተደራጀ ገበሬና በየቀበሌው ለስራ ዘመቻ የተጠራ ገበሬ ምን ያህል እንደሆነ እየቆጠሩ “ድንቅ ሪፖርት” ማቅረብ… ራሱን የቻለ ትልቅ አላማ እየሆነ መጥቷል። ይሄ ግን አያዛልቅም። ገበሬዎችን በተፅእኖ አደራጅቶ በዘመቻ እንዲሰሩ ማድረግ፤ ወደ ገበሬዎቹ ኪስ ተጨማሪ ገቢ አያመጣም። እፍኝ የእህል ምርት ለማሳደግም አይጠቅምም፤ ገበሬዎችን ከእውነተኛው የምርት ስራ ከማስተጓጎል ያለፈ ጥቅም አያስገኝም። አሁን ያለው አንዱ አማራጭ፤ “የሠራዊት ግንባታ” እና “የሥራ ዘመቻ” ሪፖርቶችን እያሳመሩ በመጓዝ ያለመፍትሄ ውድቀትን መደገስ ነው። ሌላኛው አማራጭ ደግሞ፤ የአምስት አመቱ እቅድ እየተሳካ እንዳልሆነ በግልፅ ተናግሮ፤ በሌሎች የኢኮኖሚ መስኮች ላይ እንደሚታየው የመንግስት ገናናነት መልካም ውጤት እንደማያስገኝ ተገንዝቦ መፍትሄ መፈለግ ነው። ኢህአዴግ የትኛውን አቅጣጫ እንደሚመርጥ እስካሁን በግልፅ አይታወቅም።


በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ተቃውሞ አሠሙ

$
0
0

100df95bbd9b152cae7b06a631b12efe_M

“ለአንድ ዲፓርትመንት ብለን የዩኒቨርሲቲውን ካሌንደር አንቀይርም” የዲፓርትመንቱ ኃላፊዎች በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች የወጣውን የፈተና ፕሮግራም በመቃወም ረቡዕ ጠዋት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ… ተማሪዎቹ “መንግሥት በመደበልን ጊዜና በጀት የመማር መብታችን ይከበር” “There is no exam without education” እና የመሣሠሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡ “የዘንድሮው ምዝገባ በሦስት ሳምንት ዘግይቶብናል፣ ከተመዘገብንም በኋላ ሁለት ሳምንት ዘግይተን ነው ትምህርት የጀመርነው” በማለት ቅሬታቸውን ያሰሙት ወደ 300 የሚጠጉት የሲቪል ምህንድስና የሦስትኛ ዓመት ተማሪዎች “አራት ሚድ ተፈትነን ከፋሲካ በዓል ስንመለስ አራት ሜጀር ኮርሶችን አንዳንድ ቻፕተር ብቻ የተማርናቸው አሉ፣ አስተማሪዎች በሥነ-ሥርዓቱ ስለማይገቡ አሁን ጊዜው ሲደርስ ለመጨረስ ቅዳሜ ማታ ሳይቀር እየተዋከብን እንማራለን፣ አንድ ላይ የማይወሰዱ ኮርሶችን በአንድ ላይ እንወስዳለን፣ ቤተ-ሙከራ (ላብ) አናውቅም፤ እስከ አርብ ተምረን ሰኞ ፈተና ልንቀመጥ አይገባም” የሚሉና መሰል ጥያቄዎችን አቅርበው የፈተናው ጊዜ ሊራዘምላቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

“ተሰብሰቡና እናነጋግራችኋለን” ተብለው “ፓርላማ” በተባለው አዳራሽ ውስጥ የተሰበሠቡት ተማሪዎች ከቆይታ በኋላ ሦስት የዲፓርትመንቱ ኃላፊዎች መጥተው ለማነጋገር ሲሞክሩ ብዙ አለመግባባቶች እንደነበሩ በስብሰባ አዳራሹ ተገኝተን ታዝበናል፡፡ የዲፓርትመንቱ ኃላፊ “ችግሩን ለማቅረብ በጣም ዘግይታችኋል” ተመዝግባችሁ ያልጀመራችሁት ኮርስ ካለ ተውት፣ ጀምራችሁ ያልጨረሳችሁት ኮርስ ካለ ጊዜ ፈልገን ትማራላችሁ፣ የዩኒቨርሲቲው ካላንደርና የፈተና ፕሮግራሙ ግን ለአንድ ዲፓርትመንት ተብሎ አይቀየርም በማለታቸው ተማሪዎቹ ቁጣቸውን በጩኸት ገልጸዋል፡፡ “የፈተና ፕሮግራሙ ለአራተኛ ጊዜ ተቀያይሯል፤ ይህ ለምን እንደሆነ አናውቅም” ስምንት ኮርስ እየወሰድን ጊዜው አጥሮብናል” ያሉት ተማሪዎቹ በሌላ ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ፈተና ሰኔ 16 ነው የሚጀምሩት፤ እኛ ግን ገና ተምረን ሳንጨርስ አርብ ጨርሳችሁ ቅዳሜ ውጡ ልንባል አይገባም” በማለት ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ አንድ ተማሪ ተነስቶ ባደረገው ንግግር “ምዝገባን ያዘገየው ሌላ ሰው፣ የችግሩ ሰለባ የሆንነው እኛ ነን ሁሉንም ችግር ያላጠፋነውን ሁሉ እንዲንሸከም የምታደርጉት ተማሪውን ነው” በማለት ቅሬታውን ገልጿል፡፡

ተማሪው አክሎም “እኛ እናንተ ምን ኃላፊነት እንዳላችሁ አናውቅም፤ ምንም ስትከታተሉ አይተናችሁ አናውቅም፣ ችግሩን አዘግይታችኋል የምትሉት ትክክል አይደለም፣ የሚሰማን አጥተን ነው እንጂ ስንጮህ ነው የቆየነው፤” አሁንም ቢሆን ጊዜው ተራዝሞ ኮርሶቻችንን ጨርሰን የምንፈተንበት መንገድ ይፈለግልን” ያለው ተማሪው “በዚህ ሁኔታ ከተፈተንን ኪሳራው የተማሪው፣ የዩኒቨርሲቲውና ብሎም የሀገሪቱ ነው” ሌላ ተማሪ በበኩሉ “እኔ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምህንድስና ተማሪ ማወቅ የሚገባኝን አውቄያለሁ ብዬ አላምንም” ካለ በኋላ በግቢው አስተማሪ ማስተማርም አለማስተማርም መብቱ እንደሆነ፣ አንዳንድ አስተማሪዎች ፈተና 15 ቀን ሲቀረው እየመጡ እንደሚያጣድፉ፣ ዩኒቨርስቲው ይህን እንደማይከታተልና ችግሩ ሰለባ እየሆነ ተማሪው እንደሆነ በአፅንኦት ተናግሯል፡፡ “አሁን ሰኔ ስምንት እንድንወጣ የሚደረገው በበጀት እጥረት ነው፤ እኛ እንደ ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ “ኮስት ሼሪንግ” የምንፈርመው ከመስከረም እስከ ሰኔ 30 ነው፡፡ ስንገባም ጥቅምት አምስት ነው ወደ ጊቢ የመጣነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት የመደበልን ጊዜና በጀት እስከ ሰኔ 30 የሚያቆየን በመሆኑ ቀስ ብለን ተረጋግተን ልንፈተን ይገባል” ብሏል፡፡

ኮስት ሼሪንግ የፈረሙበት ፎቶ ኮፒ እጃችን ላይ ይገኛል፡፡ “ሌላው ዩኒቨርሲቲ የራሱ አካሄድ አለው፡፡ አዳማም በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ካሌንደር ነው የሚሠራው” ያሉት የዲፓርትመንቱ ኃላፊ “አሁን ችግር ያላችሁት የፈተና ፕሮግራሙ ነው፤ እሱ ላይ ተናገሩ እንጂ ጠቅላላ ችግር አታውሩ” በማለት ቁጣ በተቀላቀለው አጽንኦት ተማሪዎቹን ገስፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተማሪው ኃሀላፊውን ቁጣ ወደ ጐን በመተው “አንድ ኮርስ በሳምንት ብቻ የምንጨርስበት ሁኔታ አለ፤ እኛ ዴቨሎፕ ሳናደርግ ነው የምንፈተነው፤ ዜጋን ለማዳን ከተፈለገ የማይለወጥ ነገር የለም፡፡ በትምህርቱና በፈተናው መሀል ክፍተት ተሰጥቶን እንፈተን” በማለት ጥያቄያቸውን ቀጥለዋል፡፡ “እኔ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ መማር የሚገባኝን ያህል አልተማርኩም፣ አስተማሪም ከሆንኩ በኋላ ለተማሪዎቼ በአግባቡ አስተምሬያለሁ ብዬ አላምንም” በማለት ለተማሪዎች ምላሽ መስጠት የጀመሩት ሌላው ኃላፊ፤ ይህ ከእኔም ስንፍና፣ ከዩኒቨርሲቲውም ችግር አሊያም በሀገሪቱ ካሉት በርካታ ገደቦች ሊሆን ስለሚችል አሁን ባለው ሁኔታ ቶሎ ቶሎ ጨርሳችሁ ተፈተኑ” ማለታቸው ተማሪዎችን የበለጠ አስቆጥቶ ነበር፡፡ በአዳራሹ ውስጥ ጭቅጭቁ እየከረረ በመሄዱ አንድ ተማሪ አንድ የተሻለ የሚለውን ሐሳብ አቀረበ፤ “አንድ ኮርስ አሳይመንት ሠርተናል፤ እሱ ከመቶ ይታይና መፈተኑ ይቅርብን፡፡

ይህም የሚጠበውን ጊዜ ይቆጥባል ከዚያ በተረፈ ቢያንስ አንድ ቅዳሜ ይጨመርልንና ትንሽ ጋፕ ይኑረን” በማለቱ ኃላፊዎቹ እየከበዳቸውም ቢሆን ለመቀበል ተገደዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንደሚሉት በዩኒቨርሲቲው ብዙ ችግር እንዳለባቸውና ፕሮፌሰር ማጁንዳ የተባሉ የቢዩልዲንግ አስተማሪ በሰጡት ግሬድ ስላልታመነበት ከአስተዳደር ክፍሉ በተነሳ ጭቅጭቅ አስተማሪው አጠቃላይ የተማሪዎቹን ውጤት ይዞ ወደ ህንድ በመሄዱ ውጤት በጊዜ ሊታወቅ ስላልቻለ ምዝገባው ለሦስት ሳምንት መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡ ኃላፊዎቹም ይህን አምነው አስተማሪውን በኢሜልም በስልክም አነጋግረን ሊታረም ባለመቻሉ ከስራው ማሰናበታቸውንና የምዝገባው ጊዜ መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡ “እኛ በአግባቡ አልተማርም ያልዘሩብንን ሊያጭዱ ይሞክራሉ፡፡ ይኼ ለዚህች አገር ውድቀት ከፍተኛ ቁልፍ ነው” ያሉት ተማሪዎቹ ትምህርት ሚኒስቴርና የሚመለከተው አካል ዩኒቨርሲቲውን እንዲቆጣጠረውና እንዲፈትሸው አሳስበዋል፡፡ “ችግሩ የእኛ ዲፓርንመንት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው” ያለችው አንዲት የዲፓርትመንቱ ተማሪ እኛ ከማወቅ ሳይሆን ከመጨረስ አኳያ ነው እየተዋከብን ያለነው፤ መንግስት ችግራችንን ይወቅልን” ስትል ተናግራለች፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ተማሪዎቹ ያለባቸውን ችግር ችለው እንዲፈተኑና በተባለው ጊዜ ግቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ስብሰባው ቢበተንም ተማሪዎቹ ቅሬታ እንዳለዙ ሲበታተኑ ለመታዘብ ችለናል፡፡


Human rights situations that require UNHRC’s attention – Ethiopia

$
0
0

United Nations Human Rights Council 23rd Session, Geneva, SwitzerlandHRLHA

HRLHA  Oral Statement: by Mr. Garoma Wakessa
Executive Director the Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA) Item 4: Human rights situations that require the Council’s attention – Ethiopia   Thank You Mr. Chairman,
Human rights violations in Ethiopia are gross, are of all kinds and widespread. Due to the limited time allotted to this Oral Statement, I will focus on the most crucial components.

The current Ethiopian Government has continued systematic restrictions on basic rights and freedoms to which all humans are entitled, including freedom of thought and expression, and civil and political rights. The independent media, political opposition parties, and civil societies, are continuously harassed and intimidated by the government; many of them are outlawed, and political leaders are sentenced to long prison terms under the so- called Anti-Terrorism proclamation.

The provisions of Ethiopia’s 2009 Anti-Terrorism Proclamation define terrorist activities so vaguely that they are easily used to criminalize all civil society activists and political opposition leaders, supporters, and peaceful demonstration organizers.
Today, media practitioners in Ethiopia face charges such as treason and terrorism simply because they put information on paper -and publish it. Opposition political party leaders and supporters face the same charge because they exercise their political freedoms.
In the past two years, Muslims who demanded non-interference of government in their religious affairs have been harassed, sometimes killed or imprisoned. University students who staged demonstrations to demand better treatment at their University campuses were beaten or imprisoned under the Proclamation.
Mr. Chairman,
In Ethiopia, the giving away of land to Transnational Corporations and other wealthy states has become a critical and burning issue for millions of family members. Thousands of small land holders in Gambela, (South Ethiopia), in Oromia Regional State ( Central and Western Ethiopia) and Benshangul ( South West part of Ethiopia) have been forcefully evicted from their ancestral lands and become jobless and homeless; those who resisted forced eviction or demanded compensation for their plundered land have been killed. Others were charged as terrorists and now languish in prison.
Mr. Chairman,
Today, children, women, senior citizens in Ethiopia regularly face starvation and are dying every day. They require the attention of the UN Human Rights Council. The Ethiopian Government has the legal obligation to respect and protect human rights set out in the international human rights conventions it ratified. Investors also should abide by the UN Global Compact – the ten principles which clearly explain their responsibilities in the areas of human rights, labor, and environmental rights in the country in which they are investing.
Mr. Chairman,
The Human Rights League of the Horn of Africa is very concerned with the deteriorating situation of human rights in Ethiopia and calls upon the UN Human Rights Council,
  • Urge the Ethiopian authorities to carry out their obligations under domestic, regional and international obligations to protect and promote freedom of expression, by immediately ending the practice of arresting and prosecuting those who hold different political opinions;
  • Call on the government of Ethiopia to allow the Special Rapporteur on the land issue to visit the country to determine the extent to which the government of Ethiopia and the investors are complying with their domestic, regional and international human rights obligations. It is their responsibility to respect human rights.

ኢቲቪ ሰው ምን እንደሚለውም ያውቃል። ታዲያ ሰምቶ እንዳልሰማ ለምን ይሆናል?

$
0
0

በኢሳ አብድሰመድ/ by IssaAbdusemed

ወያኔዎች ጭንቅ ጥብብ ብሏቸዋል ህዝቡን ለማደናገር የሞከሯቸው አሳፋሪ ድርጊቶች አልያዝላቸው ብሎ ሕዝቡ አደባባዩን በመሙላቱ በመደናገጣቸው ምክንያት ፕሮፓጋንዳው ሁሉ ጠፍቶባቸዋል…..መንግስት ስራው ሊሆን የሚገባው በአማኞቹ መካከል ክፍተት ለመፍጠር የእምነቱ  አስተምህሮ ሳይገባቸው አብያተክርስትያናት ላይ ክብሪት የሚለኮሱትን ይህ አንባገነናዊ ድርጊት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይም ተግባራዊ በመደረጉ ምዕመናኑ የመንግስትን ድርጊት በመቃወም ከአንድ አመት ለበለጠ ጊዜ ጠንካራ ሰላማዊ ትግል አድርገዋል፤ እያደረጉም ይገኛሉ፡፡  ሰዎች በማደን ፍርድ ፊት ቢያቀርባቸው ያለው ነገር የተፈጠረው ነገር በረገበ ነበር ፤ ይህን ማድረግ ሲገባው ይህን  ፤ ከውጭ በብር የሚረዱ ሰዎች  እንደሆኑ ደርሶባቸው ሳለ ችግሩን ለህዝቡ ገልጾ ውጤቱን ግን መግለጽ ሲሳነው ተመልክተናል ፤ ግልፅ የመብት ጥያቄዎች ብልሀት የተሞላበት ምላሽ መስጠት ያቃተው የኢህአዴግ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉት ኢህገመንግስታዊ እርምጃዎች ያሳስቡናል፤ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለመድረሱ አሁንም መፍትሄ ሊመጣ  የሚችለው መንግስት ከእምነት ተቋማት ላይ እጁን ሙሉ በሙሉ በማንሳት ነጻ ጋዜጠኞችን በመፍታት   ፤የህዝብእና የአገሪቱን ሃብት እና ንብረት የዘረፉ ባለስልጣናትን  አጋልጦ ፍርድ ቤት በማቅረብ ትክክለኛ ቅጣታቸውን ሲያገኙ ለማህበረሰቡ ያሳይ ፤ ሙስሊሙም ሆነ  ክርስትያኑ የውስጥ ችግሩን በራሱ አካላት እንዲፈታ ያድርግ ፤ በሁለቱም ወገን ተከሰቱ የተባሉ ችግሮች ህዝብ ፊት በማቅረብ ማህበረሰቡን በማወያየት የመፍትሄ አቅጣጫዎቹን ህዝቡ ራሱ እንዲያመላክት ያድርግ ፤ ያለፉትን መልካም ተሞክሮዎች በመውሰድ የማዳበር ስራ የሃይማኖት አባቶች እንዲሰሩ መንገዱን ያመቻች ፤ ከዘመናት በፊት የተደረጉ የእምነት ነጻነት ገፋፈዎችን ነገ ዳግም እዳይፈጠሩ የማድረግ ስራ ይስራ: በአገራችን የነጻ ሚዲያዎች መስፋፋት ይኑር ብዙዎቻችን የኢቲቪን መደጋገም፣ ማጋነን፣ ማጣመም፣ ማሰልቸት እንደ አንድ ትልቅ ችግር እንቆጥራለን።

ያንን ከበቂ በላይ ብዙ ጊዜ አስረድተናል። ግን ደግሞ አይሰለቸንም፤ አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ተመልሰን  ስለዚሁ ነገር እንነጋገራለን። ለመሆኑ ይህንኑ ችግር የምንለውን ነገር ኢቲቪን የሚቆጣጠሩት ሰዎች እንዴት የሚያዩት ይመስላችኋል? እንደችግር  ቢያዩት ኖሮ እስከዛሬ ይቀይሩት ነበር። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ይህን ነገር የሚያዩት ሊያሳኩት ለሚፈልጉት አላማ
ሲባል እንደሚከፈል ዋጋ ነው። ስለዚህ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንዲሉ ኢቲቪ ይህን ጠባዩን እንዲቀይር ከጠበቅን እየተሳሳትን ያለነው እኛው ነን። ስኬታማ የሆነለትን መንገድ ለምን ይቀይራል? ኢ.ቲ.ቪ ከበሩ ላይ እንኳን የሚፈፀመውንም ተግባር ቀጥታ እንደወረደ የማስተላለፍ ችሎታ የለዉም የውሸት ሚደያ ነው :: ሰማያዊ ፓርቲ እንኳአን በ ኢትቪ በር ላይ ያደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ቀረጻውን ለማድበስበስ ቢሞክርም ሃቁ ግን ይህን ይመስል ነበር ወዳጆቼ??  ምን አይነት የቴክኒክ ችግር  አጋጥሟቸዉ ይሆን ይችን እንኳ በመቅረፅ ድምፅ መመዝገብ ያቃታቸዉ ??

(ምንም የመብት ጥያቄ በቁጥር መወሰን ባይኖርበትም) የመንግስት ባለስልጣናትና ደጋፊዎቻቸው የቁጥር ጨዋታ ውስጥ በመግባት ሊያሳንሱትና ሊቀንሱት የፈለጉትን ሰልፈኛ እንደ ረጋ ውሀ ተከማችቶ ይመልከቱት፦

youtube https://www.youtube.com/watch?v=KB34Q2NqlmU]

በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ ያስተላለፈው መልክት እስከ ፫ ወር ለኢትዮዽያ ህዝብ በቂ መልስ እስካልሰጠ ድረስ የተቃውሞ ሰልፉ አንደሚቀጥል ገልፀዋል::

ቸር ያሰማን     ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር


ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

$
0
0

1ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ከወያኔ መከላከያ ጋር በሉግዲ ባካሔደው ውጊያ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል። በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በቀጠለው ውጊያ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከአምባገነኑ አገዛዝ 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊ….ያ በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ፣ጠመንጃ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርኳል። በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የአካባቢው ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ባሳየው ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብድ መደነቃቸውንና ድርጅቱ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቃት ያሳየ መሆኑን ገልፀው ፣ ወጣቶችም በዚህ ሃይል ጠላት ማሽመድመድ የሚችል ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲሉ ተናግረዋል። ለስምንት ዙር ያህል በተካሄደው ውጊያ የአገዛዙ ቅጥረኛ ጦር ቁስለኞች ወደ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ሁመራ የመሳሰሉት ቦታዎች በሚገኙ የጠላት የሕክምና ተቋማት ቁስለኞችን እየጫኑ ማጓጓዝ ላይ ተጠምደው እንደዋሉና ገሚሶቹ ከፉኛ በመቁሰላቸው ሕክምና እርዳታ ሳይጀመርላቸው መሞታቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት አከርካሪው የተሰበረው 35ኛ ክፍለ ጦር በድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ተሸብቦ በመጨነቅ ላይ በመሆናቸው የአካባቢውን ማህበረሰብ ያለስራው እየተንገላታ እንደሚገኝ ታውቋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አሁንም ቢሆን ወያኔው ለሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ ባለመስጠት አቋሙ የሚቀጥል ከሆነና ስለ አባይ ግድብ እያወሩ ሕዝብን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መግዛቴን እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት እንዲሁም በሉግዲ በ35ኛ ክፍለ ጦርና በሚሊሻ ላይ የተወሰደው አኩሪ ወታደራዊ እርምጃ አይነቱን ቀይሮና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል። በግንቦት 24 እና 25-2005 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ በድምሩ 192 ሙት 440 ቁስለኛ ቁጥራቸው የበዛ ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነትጥቃቸው በመማረክ የታሪኩ አካል የሆኑ ተዋጊ አርበኞች እንዳሉት እኛ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ፊት ለፊት በጠመንጃ አረር እየተፋለሙ እንደሚገኙና ትግሉ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን የሁሉም ርብርብና ተሳትፎ አስፈላጊና የውዴታ ግዴታ በመሆኑ የአገራችን ችግር መፍትሔ ለመስጠት በአምባገነኑ የወንበዴ ቡድን በሆነው ወያኔ ላይ እንዝመት ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።


ዘረኛው የወያኔ ስርአትን በህዝብ ሰላማዊ አመፅ እንዴት መገርሰስ ይቻላል?

$
0
0
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ሰላማዊ አመፅን በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ ከታወቁ የሰላማዊ አመፅ ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ተቋማት ጋር በመተባበር የስልጠና ፕሮግራሞችን ነድፎ ለአባላቶቹ የተሳካ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል…. ንቅናቄው የተሳካ የህዝብ ሰላማዊ አመፅ በአባላቶቹ ተሳትፎ ብቻ የሚከናወን ሳይሆን የሁሉንም ህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያካተተ መሆን እንዳላበት ጠንቅቆ ያውቃል:: ይህ ታላቅ ሰላማዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን ህዝቡ የሰላማዊ አመፅን ፅንሰ ሃሳብን በሚገባ መረዳትና ተግባራዊነቱም እንዴት መሆን እንዳለበት እንዲሁም የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን በሚገባ ማወቅና መለየት ይኖርበታል:: ስለሆነም ንቅናቄው ነፃ የሰላማዊ አመፅ አጫጭር የስልጠና ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እያካሄደ ይገኛል::

ስልጠናውን እንዴት መቀላቀል ይቻላል? ስልጠናውን ለመከታተል 3 መሰረታዊ ቅድመሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል::

1. ከሚቀርቧቸውና ከሚያምኗቸው የቅርብ ወዳጆችዎና ጓደኞችዎ ጋር በመሆን : ቢያንስ አስር አባላትን ያካተተ የራስዎን ቡድን ያቋቁሙ::
2. ሰላማዊ አመፅን መሰረት በማድረግ ከአባላትዎ ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት በማካሄድ የቡድንዎን አላማ: ራእይ : እንዲሁም ተግባራትን በመወሰን ዝርዝር መመሪያዎችን ይንደፉ::
3. ከላይ የተዘረዘሩትን 2 ጉዳዮች ከፈፀሙ በኋላ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄን በድህረገጽ በፌስቡክ በኢሜልና በስልክ አድራሻዎቻችን ያግኙ::

ከተዘጋጁት የስልጠና ፕሮግራሞች መካከል:

1.መሰረታዊ የሰላማዊ አመፅ ፅንሰ ሃሳብና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታው
2. የሰላማዊ አመፅ ስኬታማነት በኢትዮጵያና መሰናክሎቹን እንዴት ማጥበብ ይቻላል
3. የሰላማዊ አመፅ ስትራቴጂ ታክቲክና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች
4. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የተሳታፊውን ደህንነት ለመጠበቅ ከመቀላቀል በፊት ሊደረጉ የሚገቡ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች
5. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሰልፉን ሰላማዊነት ጠብቆ እስከመጨረሻው ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስነልቦናዊና ስልታዊ እውቀቶችን ማወቅና መለየት
6. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሚከሰቱ ማንኛውም ክስተቶችን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሰአቱ ለማሳወቅ የሚቀርፁ እንዲሁም በቀጥታ በተለያዩ የሚዲያ ድህረገፆች ላይ የሚያስተላልፉ መሳሪያዎች አጠቃቀምና የቀረፃ ቴክኒኮች

እንዲሁም:-

1. መሰረታዊ የኢንተርኔትና የፌስቡክ አጠቃቀም
2. ከወያኔ የኦንላየን ሃከሮችና ስፓዮች እራስን እንዴት መከላከል ይቻላል
3. በፌስቡክና በኢሜል የሚደረጉ ሚስጥራዊ የመልክት ልውውጦች

ዘረኛው የወያኔ ስርአትን በህዝብ ሰላማዊ አመፅ እንዴት መገርሰስ ይቻላል?</p>
<p>የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ሰላማዊ አመፅን በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ ከታወቁ የሰላማዊ አመፅ ማሰልጠኛ ኮሌጆችና ተቋማት ጋር በመተባበር የስልጠና ፕሮግራሞችን ነድፎ ለአባላቶቹ የተሳካ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል:: ንቅናቄው የተሳካ የህዝብ ሰላማዊ አመፅ በአባላቶቹ ተሳትፎ ብቻ የሚከናወን ሳይሆን የሁሉንም ህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያካተተ መሆን እንዳላበት ጠንቅቆ ያውቃል:: ይህ ታላቅ ሰላማዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን ህዝቡ የሰላማዊ አመፅን ፅንሰ ሃሳብን በሚገባ መረዳትና ተግባራዊነቱም እንዴት መሆን እንዳለበት እንዲሁም የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን በሚገባ ማወቅና መለየት ይኖርበታል:: ስለሆነም ንቅናቄው ነፃ የሰላማዊ አመፅ አጫጭር የስልጠና ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እያካሄደ ይገኛል::</p>
<p>ስልጠናውን እንዴት መቀላቀል ይቻላል? ስልጠናውን ለመከታተል 3 መሰረታዊ ቅድመሁኔታዎችን ማሟላት ያስፈልጋል::</p>
<p>1. ከሚቀርቧቸውና ከሚያምኗቸው የቅርብ ወዳጆችዎና ጓደኞችዎ ጋር በመሆን : ቢያንስ አስር አባላትን ያካተተ የራስዎን ቡድን ያቋቁሙ::<br />
2. ሰላማዊ አመፅን መሰረት በማድረግ ከአባላትዎ ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት በማካሄድ የቡድንዎን አላማ: ራእይ : እንዲሁም ተግባራትን በመወሰን ዝርዝር መመሪያዎችን ይንደፉ::<br />
3. ከላይ የተዘረዘሩትን 2 ጉዳዮች ከፈፀሙ በኋላ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄን በድህረገጽ በፌስቡክ በኢሜልና በስልክ አድራሻዎቻችን ያግኙ::</p>
<p>ከተዘጋጁት የስልጠና ፕሮግራሞች መካከል:</p>
<p>1.መሰረታዊ የሰላማዊ አመፅ ፅንሰ ሃሳብና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታው<br />
2. የሰላማዊ አመፅ ስኬታማነት በኢትዮጵያና መሰናክሎቹን እንዴት ማጥበብ ይቻላል<br />
3. የሰላማዊ አመፅ ስትራቴጂ ታክቲክና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች<br />
4. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የተሳታፊውን ደህንነት ለመጠበቅ ከመቀላቀል በፊት ሊደረጉ የሚገቡ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች<br />
5. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሰልፉን ሰላማዊነት ጠብቆ እስከመጨረሻው ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስነልቦናዊና ስልታዊ እውቀቶችን ማወቅና መለየት<br />
6. በህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የሚከሰቱ ማንኛውም ክስተቶችን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሰአቱ ለማሳወቅ የሚቀርፁ እንዲሁም በቀጥታ በተለያዩ የሚዲያ ድህረገፆች ላይ የሚያስተላልፉ መሳሪያዎች አጠቃቀምና የቀረፃ ቴክኒኮች </p>
<p>እንዲሁም:-1. መሰረታዊ የኢንተርኔትና የፌስቡክ አጠቃቀም<br />
2. ከወያኔ የኦንላየን ሃከሮችና ስፓዮች እራስን እንዴት መከላከል ይቻላል<br />
3. በፌስቡክና በኢሜል የሚደረጉ ሚስጥራዊ የመልክት ልውውጦች” src=”<a href=https://fbcdn-sphotos-b-a.akamaihd.net/hphotos-ak-ash3/q71/s480x480/941942_456572107766480_1610066741_n.jpg&#8221; width=”625″ height=”547″ />

እንግዲህ ለኤልፓና ለቴሌኮም ስንል ጫካ አንገባ?

$
0
0
እናንተ … በገዢው ፓርቲ አባላት የተሞላው ፓርላማ ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ ደፋር የሆነው? (ሰርጐ ገብ ቡድን ገባ እንዴ?) የፓርላማ አባላቱ ስንቱን ቱባ ቱባ የመንግስት ባለስልጣን መሰላችሁ ሲያፋጥጡ የሰነበቱት! አንድ የፓርላማ አባል ስለ ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስተያየት ሲሰጡ “ኮሚሽኑ ጥርስ እንዳለው አሳይቷል” ብለው ነበር፡፡ እኔ ደግሞ “…ፓርላማው ጥርስ እንዳለው አስመስከረ!” ብያለሁ – ለራሴ፡፡ ከምሬ ነው … እንደ ድሮ አጨብጭቦና እጅ አውጥቶ መለያየት ቀረ እኮ! (እንኳን ፈጣሪ ገላገለን!) ባለፈው ጊዜ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ለፓርላማ ሪፖርታቸዉን ካቀረቡ በኋላ ከግራና ከቀኝ እንዴት በጥያቄ እንዳፋጠጧቸው አልነግራችሁም፡፡ አንዱ አባል፤ በተወከለበት አካባቢ የኔትዎርክ መቆራረጥ መኖሩን ሲገልፅ፤ ሌላኛው እሱ በተወከለበት አካባቢ ግን ከእነአካቴው ሞባይል እንደማይሰራ ተናገረ፡፡ (ምን ያድርግ ሃቅ ነዋ!) ሃላፊው ታዲያ ምናቸው ሞኝ ነው፡፡ ጥያቄው እንኳንስ በእሳቸው የስልጣን ዘመን በተተኪው ትውልድም መልስ የሚያገኝ ስላልመሰላቸው ስለ ቴሌኮም ማውራቱን ትተው ስለ አገሪቱ ዕድገት መስበክ ጀመሩ፡፡ (ክሊሼ እኮ ነው!) “ምስቅልቅሎች ይኖራሉ፤ ግን የዕድገት ምስቅልቅሎች ናቸው!” አሉን ሚኒስትሩ፡፡ (አዲስ ነገር ግን አልነገሩንም!) እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ከሁለቱ “ጉልቤ” የመንግስት ድርጅቶች የሚገላግለን እናገኝ ይሆን? እንግዲህ ለኤልፓና ለቴሌኮም ስንል ጫካ አንገባ? እውነቴን ነው … ኤልፓ የዕለት ተዕለት ኑሮአችንን አመሰቃቀለው እኮ! እሱም እንደባልደረባው “ምስቅልቅሉ የዕድገት ምስቅልቅል ነው!” እንዳይለን እሰጋለሁ፡፡ (ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ ይባል የለ!) ይታያችሁ … በአንድ ከሰዓት በኋላ ብቻ ሦስቴ መብራት እየጠፋብን ነው፡፡ ቴሌኮምም ቢሆን እኮ ብሶበታል፡፡ ቅዳሜ ማታ እዚሁ አዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ ለሚኖር ጓደኛዬ የላክሁት ማሴጅ መቼ ቢደርስ ጥሩ ነው? ማክሰኞ ማታ – በአራተኛው ቀን ማለት ነው፡፡ ለዚህ ለዚህማ እኔው ራሴ እቤቱ ሄጄ መልዕክቱን አደርስለት ነበር (ከመንገድ ትራፊክ የቴሌ ትራፊክ ባሰ እኮ!)

Yared Getachew



ግብጾች ተሸወዱ የግብፅ ፖለቲከኞች ስለአባይ በምሥጢር የተነጋገሩት!!

$
0
0

የግብፅ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን ግድብ አስመልክቶ የተንኮል ወይም መሠሪ አድራጎት የመፈፀም ሃሣቦችን አንፀባርቀዋል። የፖለቲካ መሪዎቹ ይህንን ሃሣቦቹን ያሰሙት በግድቡ ግንባታ ላይ ባደረጉት ውይይት ላይ ነው፡…

በአባይ ውኃ ላይ የሚከናወኑ ሥራዎችን በቸልታ እንደማይመለከቱ የተናገሩት የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ የሃገራቸው ተቃዋሚ መሪዎች ሳይቀር ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን አስቀምጠው በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ማሰማታቸው ይታወሣል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዌብ ሣይቱ ላይ ባሠፈረው መልዕክት ግብፅን የሚያሠጋ አንዳችም ነገር የለም ብሏል።


Breaking News: Armoured Vehicles Surround Ethiopian Embassy In Cairo

$
0
0

Awramba Times – The Ethiopian embassy in Cairo is surrounded by heavily armed personnel and armoured vehicles. Ethiopian citizens, both refugees and Ethiopian-passport holders, are savagely harassed and beaten by ordinary Egyptians and the police everywhere they move…

According to our sources, it is very difficult for Ethiopians to move around and many people are starving as they fear for their life to go out and buy foodstuff and drinking water. Egyptians are preparing a massive demonstration against Ethiopia to be held next Friday.

On the other hand, Ethiopian Ambassador to Egypt Mohamed Dirrir met with Egyptian opposition leader and former Secretary General of the Arab League, Amr Moussa in Cairo today. Ambassador Mohamed Drirr has a two hours meeting with Amr Moussa on the recent developments on the Nile and has made clear that Ethiopia has no any intention of harming egypt or affecting its access to the Nile waters


የሰሞኑ የአባይ ግርግር

$
0
0

እስከ ነጻነት ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛዎችና የውጭ ዜና አውታሮች ጭምር ስለ አባይ ግድብ ብዙ ሲሉ ይሰማል፡  ለምን? ለምን አሁን? ምን የተለየ ነገር ተገኘ?

በመሰረቱ አባይ መገደብና ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም መብትም ግዴታም አለባት፡…. እዚህ ላይ ማንም ጥያቄ ያለው አይመስለኝም፡ ጥያቄ የሚነሳው ግን በርግጥ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር የሚመራው ብድን አባይን አገድባለሁ የሚለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ነው ወይ? ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መክሮና ተስማምቶ ነው ወይ? ግድቡስ ለግርጌ ተፋሰስ አገሮች ጉዳት ያመጣል ወይ የሚሉት ጥያቆዎች መመለስ አለባቸው።

ስለ አባይ ጉዳይ ዝርዝር ከመግባቴ በፊት ወያኔ ለምን በተለያየ ዘዴ ስለ አባይ እንዲነሳ ፈለገ? ግብጽስ አሁን ሰለጉዳዩ ለምን አጀንዳ አረገችው? ወዴትስ ሊያመራ ይችላል? የሚሉትን ከወያኔ ምግባርና ጸባይ ተነስቼ ያለኝን አስተያየት አጠር አርጌ ላቅርብ፡

ወያኔ ባሁኑ ሰዓት አቅጣጫ ጠፍቶት በትርምስ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፤ የውስጥ ሽኩቻ አለበት፤ ከውጭ ጫና አለበት፤ ህዝብ ጭቆና አንገፍግፎት በቃኝ እያለ ነው፡ ይህን ሁሉ አቅጣጫ ለማስቀየር አንድ ዘዴ መፍጠር አለበት፡ የግብጹ ሙረሲም ከግብጽ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ የለውም እና አሱም የግብጻውያንን የልብ ትርታ የሚኮረኩር ነገር ይዞ መቅረብ ይፈልጋል፡ ስለዚህ የጋራ ሴራ አየተሸረበ ሊሆን እንደሚችል አገምታለሁ፤ በዚህ ላይ የውጭ አጅ የለበትም ለማለት አልደፍርም፡ ሁኔታው እየባሰ ከሄደ ወደ ጦርነትም ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ግምታ አለኝ፡ በተለይ ኢትዮጵያ ጦር ሃይል ውስጥ የማፈንገጥ አዝማሚያ ያሳያሉ ብለው የሚጠረጥሯቸውን ለማስፈጀት እና እግረ መንገዳቸውንም በመርዝ፤ በጥይት፤ በማፈናቀል አላልቅ ያላቸውን ያማራ ህዝብ ባይሮፕላን ለመደብደብም አይመለሱም የሚል ግምት አለኝ ይህ ደግሞ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር አዲስ ነገር አደለም እንኳን ጠላቴ የሚለውን አማራና ነጻ አወጣሃለሁ የሚለውን ህዝብም ከመጨረስ አለተመለሰም፡

1)  ነጻ አወጣሃለሁ ያሉት ህዝብ ላይ አሲረው የነለገሰ አስፋውንና መንግስቱ ሐ/ማርያምን ደደብነት ተጠቅመው ሃውዜንን በልጆቿ ደም አጨማልቀዋታል፡

2)  ከተሸነፈ ጦር ጋር አብረን አንሰራም ብለው ለልመና የዳረጉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሃገር ፍቅር ስሜቱን ስለሚያውቁና ወደፊት ለሚያቅዱት አገር የማጥፋት ሴራ እንቅፋት ይሆናል ብለው ስለገመቱ ባድሜ የሚል ድራማ ደርሰውና አራግበው በመቶ ሺ የሚቆጠር ወጣት አስጨርሰው፤ ለቤተሰቦቻቸው እንኳ በውል ልጆቻቸው የት እንደወደቁና እና የት እንደሞቱ  አልነገሯቸውም፡

3)  የአሜሪካንን ጦርነትን ለመዋጋት ሶማሊያ ድርስ የተላከው ጦር ሬሳው በመቋዶሾ ጎዳናዎች ላይ ሲጎተት ስንት እንደሞተና ስንት እንደቆሰለ እንኳ አልተነገረም እንደ ርካሽ እቃ ወድቆ ቀርቷል፡

ከዚህ ሁሉ የወያኔ እርኩስ አላማና ዘር አጥፊ ወንጀለኛ ባህሪይ ተነስቼ  በወያኔ ጠባብ ዘረኛ አስተዳደር ላይ ቅሬታ ያላቸውን የጦር ሃይል አባላት ሰብሶቦ ሊማግዳቸው ይችላል የሚል ግምት ባቀርብ የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡  ስለዚህ መጠንቀቅ ያለባቸው ጦሩ ውስጥ ያሉና በህውሃት በጥርጣሬ የሚታዩ የሰራዊቱ አባላት ሊጠነቀቁና አይናቸውን ከፍተው በንቃት ሁኔታወችን መከታተል ያለባቸው መሆኑን አስምሬበት አልፋለሁ።

ስለ አባይ ጥቂት መረጃዎች

የአባይ ወንዝ ናይልን ከሚመግቡ ሶስት ወንዞች አንዱና ዋናው ነው፤ የወንዞቹ ተፋሰስ ስፋትና የፍሰት መጠን ከታች ባለው ሰንጠረዥ ይመልከቱ

Ethiopia's Nile river

ያባይ ወንዝ ከፍተኛው የገባር ወንዝ መነሻው 4250 ሜ ከባህር ጠለል በላይ ሲሆን ሱዳን ድንበር ላይ ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ 490 ሜ ነው፡ (የ3760 ሜትር ልዪነት ማለት ነው)

አባይ ተፋስስ ከፍተኛ የሃይል ማመንጨትና የመስኖ ልማት አቅም ያለው መሆኑን በተፋሰሱ ላይ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን በነዚህ ጥናቶች መሰረት አባይ ተፋሰስ ውስጥ በመስኖ ሊለማ የሚችል እስከ 700,000 ሄክታር የሚደርስ የመሬት ሰፋትና ከፍተኛ ሃይል ማመንጨት ሊመረትባቸው የሚችሉ አራት የግድብ ቦታዎች የገኛሉ (ካርታውን ይመልከቱ)

Ethiopian proposed hydroelectric dams

ለመስኖ ልማት አመቺ የሆነው መሬት የሚገኘው ከመንዳያ ግድብ ግርጌ ጀምሮ እስከ ሱዳን ጠረፍ ድረስ ነው፡

አባይና ደለል

ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘበው የሚገባው ነገር፡  አባይ ወንዝ ባማካይ ባመት 320 ሚሊየን ቶን ደለል ከኢትዮጵያ ኮረብታዎች ሸርሽሮና ተሸክሞ አሰዋን ግድበ መዳረሻ ላይ ይዘረግፈዋል፡ ይህም የግድቡን ውሃ የመቋጠር አቅም ይቀንሳል፡ ሊለማ የሚችለው መሬት በደለል ይሸፈናል፤ ደለሉ የውሃ መጥለፊያ ቦዮችን ይደፍናል እናም ሱዳንና ግብጽን በተለይ ሱዳንን ከፍተኛ ወጭ ያስወጣቸዋል፡ ይህ ትልቅ ችግር የሱዳንና የግብጽ የውሃ ባለሙያዎችን እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ በመሆኑን በብዙ አለም አቀፍ መድረኮች ሲያቀርቡትና ይህንኑ ለማስቆም ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አባይ ተፋስስ ውስጥ ከፍተኛ የጎርፍን መሽርሸር መከላከያ ሰራ መሰራት እንዳለበት ይመክራሉ፡ (Ahemed, 2007; Betrie  et al., 2010.)  ያቀረቡትን መመልከት ይቻላል፡

የተወራለት የአባይ ግድብ

1) ግድቡ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊጠቅም የሚችልና የምግብ ፍላጎት በፍተኛ ደረጃ ሊቀርፍ የሚችለው የመስኖ ልማት አላካተተም

2) ወደ መሃል ሃገር ቀረብ ያሉትንና ለመስኖ ልማት ሊውሉ የሚችሉ ግድቦችን ዘሎ ድንበር ላይ መገደብ ለምን እንደተመረጠና ጠቀሜታውን የሚያረጋግጥ ምንም መረጃ ለህዘብ አልተገለጸም፡ በመስኖ የመጠቀም መብቷንም እስከወዲያኛው የዘጋ ታላቅ ሴራና አገር ክህደት ወንጀል ነው፡

3) ግድቡ የሚያመርተው የመብራት ሃይል ብቻ ነው፡ ከልምድ እንደሚታወቀው ደግሞ የውሃ ሃብት ፐሮጀክቶች ዘርፈ ብዙ እስካልሆኑ ድረስ አትራፊ እንደማይሆኑ ይታወቃል፡ ስለዚህ የአባይ ግድብ በየአመቱ ወደግድቡ የሚገባው 320 ሚሊየን ቶን ደለል ሞልቶት የግደቡ እድሜ አስኪያልቅ ድረስ እንኳን አትራፊ ሊሆን የሚገነባበትን ወጪ ለመመለሱም በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፤ ከህዝብም የተደበቀ የወያኔ ሚስጥር ብቻ ነው፡

4) የተፋሰሱን ጎርፍ ሽርሸራ ለመከላከል ወይም ለመቀነስ የተደረገ የተፋሰስ ልማት ስለመደረጉ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡

5) ውሃው የሚተኛበት መሬት እስከመጨረሻው ከጥቅም ውጭ የሚሆን ነው፡ ደለሉ የሚከማችበት ቦታም እንደዚሁ፡ ይህን በተመለከት የምጣኔ ጥናትና አካባቢ ሁኔታ ጥናት(economic analyses, environmental impact assessment) ስለመደረጉና አዋጭ ስለመሆኑ ምንም የሚታወቅ ምንም ነገር የለም፡

6) ግደቡ ከኢትዮጵያ ይልቅ የሚጠቅመው የግርጌ ተፋስስ አገሮችን ነው፤ ወሃው ከደለል ነጻ የሆነና የተመጣጠነ ውሃ ወደ ግርጌ ተፋሰስ አገሮች ስለሚለቀቅላቸው ዋናው አገልገሎቱ ለሱዳንና ለግብጽ ነው

ማጠቃለያ

ከላይ እንደተገለጸው የአባይ ግድብ በዋናነት የሚጠቅመው ሱዳንን እና ግብጽን መሆኑ ግልጽ ነው፤ ምንም ገንዘብ ሳያወጡ በኢትዮጵያውያን ላብ እና ደም የተሰራላቸውን የደለል መቆጣጠሪያ ግድብ እና የመስኖ ልማት የመጠቀም እደሏን እሰከመጨረሻ ያዳፈነ ፐሮጀክት ሊጠሉት የሚችሉበት እና አባይ ግድብን ለማስቆምም ይሁን አደጋ ለማድረስ የሚያስችል ምንም አይነት ነባራዊ ሁኔታዎች የሉም፡ ራሱ ወያኔ ካላፈረሰው በቀር፤ በዚህ ደግሞ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ተመክሮ አለው፡ አዲስ አበባ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ ፈንጂ ቀብረው ንጹሃን ዜጎችን መጨረሳቸውን ሊዘነጋ አይገባም፡

ስለዚህ ግብጽ ስለ አባይ እንዲህ አለች እንደዛ አለች፡ ሱዳን ይህን አለ የሚባለው ወሬ ሁሉ የወያኔና ግብረ አበሮቹ የተለመደ አኪልዳማ፤ ሃረካት ክፍል መሆኑን መረዳትና ለዚህ ወሬ ትኩረት ሳንሰጥ አገራችንን አገራዊ አመራር እንዲኖራት ማድረጉ ላይ ትኩረት መስጠት አለብን። ስለ አባይ ተፋሰስ ልማት ወደፊት ህዝብ የሚመክርበና የሚወስንበት ጉዳይ ነው፡ ምናልባትም አሁን በመሰራት ላይ ያለው ግድብ ቆሞ ከላይ ላሉት ግድቦች ቅድሚያ ሊሰጥ የሚችልበት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል።፡ከሁሉ የሚቀድመው ግን ነጻነት ስለሆነ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባርን ጠባብ ዘረኛ የግዞት ቀንበር መስበር ያስፈልጋል፡ የተጀመረውን ሁለገብ ትግል ማጋጋልና ማጠናከር አለብን አንጂ ስለአባይ ወያኔ የሚያቀብለንን ጉላንጆ በማላመጥ ጊዜም ጉልበትም ማባከን አይገባንም ብዬ ሃሳቤን አጠቃልላለሁ፡

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊ አመራር ይስጣት

አመሰግናለሁ

እስከ ነጻነት


የኢሕአዴግ መንግስት በጄኔቭ በኢትዮጵያውያን ከባድ ተቃውሞ ገጠመው

$
0
0

በጂኔቭም ሕዝቡ ነፃነትና የሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ ካልተከበረ ገንዘብ የለም አለ። ቪድዮ፦


የአንድነት የወረዳ 19 ምክትል ሰብሳቢ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል

$
0
0

UDJ22

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የወረዳ 19 ምክትል ሰብሳቢ ወጣት ባህሩ ራህመቶ ግንቦት 20/2005 ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ በደህንነት አባላት ከተወሰደ በኋላ የሚገኝበት ፖሊስ ጣብያ ሳይታወቅ ለቀናት መቆየቱንና በማረፊያ ቤቱ እንዲቆይ ያደረገው ፖሊስም እስከ ግንቦት 27/2005 ፍርድ ቤት ሳያቀርበው መቆየቱን መዘገባችን አይዘነጋም…

ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ27/2005 እንዲቀርብ የተደረገው ባህሩ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17/2005 ሊያደርገው የነበረን ሰላማዊ ሰልፍ ስትቀሰቅስ ነበር የሚል ክስ እንደቀረበበት ለመረዳት ተችሏል፡፡የፍርድ ሂደቱን የባህሩ ወዳጆች፣ጋዜጠኞችና ታዛቢዎች በሚገኙበት ግልጽ ችሎት እንዲከናወን አለመደረጉም ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ባህሩ ፍርድ ቤት በቀረበበት ዕለት የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር ተቀዳሚ ፕሬዘዳንትና የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ የሆነው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ለህዝብ ዝግ በሆነ ችሎት ጉዳዩን እንዲከታተል ተደርጓል፡፡

ፖሊስ የእነ ብርሃኑን ክስ ለመምራት የሚያስችለው ስልጣን እንደሌለው በመጥቀስ ሁለት ቀጠሮ የጠየቀበትን ጉዳይ ፍርድ ቤቱ እንዲዘጋለት ቢጠይቅም

ዳኛው የአዲስ አበባ ፖሊስ ክሱን ለፌደራል ፖሊስ እንዲያዞር በማዘዝ ክሱ ለፌደራል ፖሊስ ካልዞረ ግን በ29/5/2005 መዝገቡን በመዝጋት ተጠርጣሪዎቹን በነጻ እንደሚያሰናብቱ አስረድተዋል፡፡የእነ ብርሃኑ ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ‹‹ፍርድ ቤቱ ከፖሊስ የቀረበለትን ጥያቄ በመቀበል ያለ በቂ መረጃ እየተንገላቱ የሚገኙትን ደምበኞቻቸውን በነጻ ማሰናበት ሲገባው ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ እንዳስገረማቸው ገልጸዋል፡፡

የባህሩና የብርሃኑ ቤተሰቦችና የቅርብ ሰዎች ነገ በሚካሄደው የፍርድ ችሎት ሁለቱ ወጣቶች በነጻ ሊሰናበቱ እንደሚችሉ ተስፋ ማድረጋቸውን ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡


Viewing all 931 articles
Browse latest View live