Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

ለአንባገነን መንግስት እርዳታ የሰጠውን የእግሊዝ መንግስትን ለመክሰስ አንድ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ ቀጠረ

$
0
0

በሚሊዮኖቸ ለሚቆጠሩ ስዎች መፈናቀል ምክንያት የሆነውን የኢትዮጵያ የመሬት ፓሊሲ የሚደግፍ 1.3 ቢሊዮን ዪሮ የሰጠውን የእንግሊዝ መንግስት ለመክሰስ አንድ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ መቅጠሩን ለዋሽንግተን ፓስት አስታወቀ..

ሚስተር O በሚል በዋሽንግተን ፓስት ላይ የሰፈረው ይህ ኢትዮጵያዊ የብሪታንያ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉት 40 ሚሊዮን በሚደርሱ ዳሃ ኢትዮጵያኖች ስም እፋረደዋለው ሲል አስታወቀ።ኢትዮጵያዊው የወከለው የለንደኑ የህግ ድርጅት ተወካይ ሌይ ዴይን ዋቢ ያደረገው የልማት ድርጅቱ ይህ ተግባር የራሱን የሰው ሃይል ፓሊሲ እየተፃረረ ነው በማለት የእንግሊዝ መንግስት የ 3 ቢሊዮን ዪሮ እርዳታ አግባብ አለመሆኑን ገልፃል። ይህን በማድረግ የብሪታንያ መንግስት ጨቃኝ እና አፋኝ የሆኑትን መንግስታት በስልጣን እንዲቆዩ እየረዳ ነው በማለት እርዳታው የሚያስከትለውን ውጤት ገልፃል።

በኢትዮጵያ የቀረበው የእንግሊዝ የጥብቅና ድርጅት ለም ከሆነው የዘሩትን ይበቅልበታል እንዲሁም መአድን ይገኝበታል በሚባለው ከጋንቤላ የተፈናቀሉትን ለአብነት ጠቅሳል። ከዚህ ምድራቸው እንዲፈናቀሉና የሰባዊ ጥሰት እንዲደርስባችው የሚያደርግ ገንዘብ መርዳት ወንጀል ነው ሲል አስታውቋል።



የጁምአ የህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ ላይ ግርግር እና ችግር በመፍጠር ግንቦት 25 ይካሄዳል የተባለውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቀረት መታቀዱን ተሰማ፡:

$
0
0

ባሳለፍነው ሳምንት የአፍሪካ ህብረት 50ኛ አመት ክብረ በአል ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደረግ ካስታወቀ ቡሃላ መንግስት ህዝበ ሙስሊሙ በጁምአ ቀን በታላቁ አንዋር መስጂድ የሚያደርገውን ተቃውሞ በመጠቀም ረብሻ በመፈጠር ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማጨናገፍ ሲያሴር እንደነበር የውስጥ ምነጮቻችን አስታወቁ… ሆኖም የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በመኖሩ እና ይህ የመንግስት እቅድ ቀድሞ ደርሶት የነበረው ድምጻችን ይሰማ መንግስት በጉጉት ሲጠባበቀው የነበረውን አጋጣሚ ለማክሸፍ ሲባል በጁምአ ቀን በመላው ሃገሪቱ ተቃውሞ ሲካሄድ በአዲስ አበባ ግን እንዳይካሄድ በማድረጉ የመንግሰት ሴራ ሙሉ ለሙሉ ሊከሽፍ መቻሉን ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡

መንግስት አቅዶት የነበረው በታለቁ አንዋር መስጂድ ግርግር በመፍጠር የሰማያዊ ፓርቲን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ ያደረገው ሴራ ባለመሳካቱ ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ጥሎት የነበረውን የሰላማዊ ሰልፍ እገዳ ለማንሳትና ፈቃድ ለመስጠት ተገዷል፡፡

መንግስት ሰላማዊ ሰለፉ የሚካሄድበትን ቀን ለአንድ ሳምንት እንዲራዘም በማድረግ ለግንቦት 25 እንዲከናወን መፍቀዱ መጀመሪያ አቅዶት የነበረውን ሴራ በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ማቀዱን የውስጥ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በታላቁ አንዋር መስጂድ የሚካሄደውን ሰላማዊ ተቃውሞ በተለያዩ ጊዜያቶች ለማደናቀፍ ጥረት ሲደረጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህም ሳምንት ግንቦት 25 በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማጨናገፍ እና ለመከልከል የህዝበ ሙሊሙን የታላቁ አንዋር መስጂድ ተቃውሞ እነደ ጥሩ አጋጣሚ ዳግም እየተጠባበቀው እንደሚገኝ የውስጥ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡

በታላቁ አንዋር መስጂድ በሚካሄደው የጁምአ የህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ ላይ ግርግር እና ችግር በመፍጠር ግንቦት 25 ይካሄዳል የተባለውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቀረት መታቀዱን ከውስጥ ምንጮች ለመስማት ተችሏል፡፡ይህንንም በማድረጋቸው የሙስሊሙን ተቃውሞ በማስቆም እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፉን በማስቀረት ደረጃ ከፍተኛ አቅድ ይዞ መንግስት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል፡፡


ጎንደር ታምሷል፤ አዲስ አበባ ህዝቡ ተነሳስቷል!

$
0
0

በመተማ ገንዳውሃ ከተማ ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም የእርሻ መሬታቸው የተነጠቁ በርካታ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው የ‹ክልሉ› ም/ አስተዳደር እንደሚገኝ ቢነገርም የተገኙት የሰ/ ጎንደር አስተዳደር ሀላፊ አቶ ግዛት አብዩ ናቸው፡፡

Blue party logo
ስብሰባው የእርሻ መሬታቸውን በተነጠቁት አርሶ አደሮች ጉዳይ ሲሆን ከፍተኛ ክርክር ተካሂዶ ስምምነት ያልተደረሰ ሲሆን አቶ ግዛት ‹‹ መሬቱን መልቀቅ አለባችሁ..›› ሲሉ ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ አድርገዋል፡፡
አያይዘውም አቶ ግዛት ‹‹…እስከ አፍንጫው የታጠቀ መከላከያ ሰራዊት ነው ያለን ሜዳው ያውላችሁ….›› በማለት ዛቻ አሰምተዋል፡፡ አርሶ አደሮችም ‹‹ መሬቱን አንለቅም መከላከያ እገላለሁ ካለም ይግደለን፡፡›› በሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከስብሰባው በኋላ የኢህአዴግ አባላትን ይዘው እስከ ምሽቱ 6፡00 በመሰብሰብ ችግር ይፈጥራሉ ባሏቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዶልተው ሂደዋል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ባለኀብቶችና ነጋዴዎችን የቀበሌ ሹማምንት ‹‹የመለስ ራእይ›› የሚለው ‹‹መፃህፍን›› ከ2000.00- 5000.00 ብር ግዙ በማለት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ነጋዴዎች በምሬት ገለፁ፡፡ እያንዳንዱ ቀበሌ ‹‹መፅሀፉን›› ሽጦ ከ400.000.00- 500.000.00 ብር ገቢ እንዲያደርግ ታዟል፡፡

በሌላ መልኩ ቁጥቸው 500 የሚደርሱ ሚሊሻዎች ከደባርቅ ወረዳ በመሰብሰብ ለልዩ ስልጠና ከ21/ 09/ 2005 ዓ. ም ጀምሮ በድብ ባህር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የስልጠናው ምክንያት በአካባቢው ባሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ የሰሞኑ የአገር ቤት አቢይ ዜና መሆኑ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር የደረሰን መእክት እንዳስተላለፈው፤ የህዝባዊ ስብሰባው አጀንዳ ሀገራዊ በመሆኑ ቀደም ሲል ሁሉም ኅብረተሰብ ‹‹ተቃዋሚ የለም፣ ማን ያስተባብረን፣ ሚጠራን የለም፣…ወዘተ. ›› ጉንጭ አልፋ ወሬዎችን የሰበረ ነው፡፡ ይኸው ‹‹ና›› ተነስ ተቃውሞህን ግለጽ ተብለናል፡፡ በየጓዳው፣ በየካፌው፣ በየባንኮኒው፣ በየወረቀቱ፣ በየ…፣በየ…፣ መትመክመክ ዋጋ የለውም፡፡

ስለዚህ በዚህ ምቹ አጋጣሚ ሁላችንም ተነስተን ‹‹ሆ›› ብለን ተቃውሟችን እንግለፅ፡፡
በስብሰባው መገኘት የግድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆን አይደለም፣
ስብሰባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ይጋብዛል፣
ሁሉንም ተቃዋሚዎች ይጋብዛል፣
ሁሉንም እምነቶች ያካትታል፣
ከቤት ውጭ በመሆኑ በጣም አመችና ገላጭ ነው፣
መፈክር ይዞ ለመውጣት ያመቻል፣
ለረዥም ቀናት/ድል ለመጨበጥ/ ያመቻል፣
ከሁሉም በላይ ወሩ ግንቦት ነው፣
ጥንካሬ፣ ድፍረት፣ ቆራጥነት፣ ፅናት፣ ….ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

የዘገባው መጨረሻ፤ ራሳችን ነፃ ወጥተን ሀገራችንን ነፃ እናውጣ!!!
…..ቱኒዝያ፣ ግብፅ፣ ሊብያ፣ የመኒያ፣……ኢትዮጵያ፣……” ብሏል ርእየ- ሁለንተና – አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ


ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ለሃምሌ ሁለት ተቀጠረ : የፍርድ ቤት ውሎ

$
0
0

ፍርድ ቤቱ የተከሳሽን  ቃል ሲሰማ እና ጠበቆች ስለምስክሮቹ መግለጫ ሲሰጡ ሰዓቱ ስላለቀ ሃምሌ 2 የምስክሮቹን የምስክርነት ቃል ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቷል…. የተመስገን ጠበቃ ምስክሮቹ በምን ጉዳይ ላይ ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡ ከተናገረ በኋላ አቃቢ ህግ የሁለቱ መስካሪዎች እንዳይመሰክሩ በምክንያት አስደግፈው ተቃውመው ነበር::  በዚህም መሰረት አንደኛው ምስክር ዶ/ር ያሬድ ከህገ መንግስቱ እና ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ሃሳብን የመግለፅ መብቶች ከሚደነግጉ ህጎች አንፃር ተመስገን የተከሰሰባቸው ፅሁፎች ከህግ ውጪ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ ::  ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ደሞ ኢሰመጉ ይሰሩባቸው በነበሩበት ወቅት በኢሰመጉ ሪፖርት የቀረቡ በኢትዮጵያ መንግስት ስለተጣሱ ሰብአዊ መብቶች ያቀርባሉ::   አቶ እንዳልካቸው ሃ/ሚካኤል ክስ የቀረበባቸውን ፅሁፎች ከጋዜጠኝነት ስነምግባር እና አሰራር ከሙያ አንፃር እንዴት መታየት እንዳለበት ያቀርባሉ:: አቃቤ ህጎች የሁለቱ ምስክርነት ቃል እንዳይሰማ ብለው ተቃሟቸውን አቅርበው ነበር በ1ኛ እና 2ኛ ምስክሮች ላይ::

394711_184013551696255_1365830121_n

ጠበቆቹ ስለምስክሮቹ መግለጫ ካቀረቡ በኋላ አቃቤ ህጎቹ በ1ኛ እና 2ኛ ምስክር ላይ ተቃሞ እንዳላቸው ተቃሟቸውን አቀረቡ:: 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ የህግ ባለሙያ ቢሆኑም ህገመንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የላቸውም :  ህገመንግስቱን የመተርጎም ስልጣን ያለው የፌዴሬሽን ም/ቤት ብቻ ነው ስለዚ የሳቸው ምስክርነት አያስፈልግም:: 2ኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ኢሰመጉ ሊቀመንበር ሆነው የሰሩ ቢሆንም ከ97 በኋላ ባላቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እና አቋም ገለልተኛ ሆነው መመስከራቸው ያጠራጥረናል ስለዚህ የሁለቱን ምስክር ሆኖ መቅረብ ፍ/ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል::

የተከሳሽ ጠበቆችም ምላሽ ሲሰጡ : 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ ህገመንግስቱን እንዲተረጉሙ ሳይሆን ደንበኛቸው የተከከሰሰባቸው ፅሁፎች ከህገመንግስቱ እና ኢትዬጵያ ከፈረመቻቸው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከሚደነግጉ አለም አቀፍ ህጎች አንፃር እንዴት ትክክል እንደሆኑ ለማስረዳት መሆኑን 2ኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ደግሞ የሚያቀርቡት ኢሰመጉ ሲሰሩ በነበሩባቸው ጊዜያቶች ያዩትን የሰሙትንና ድርጅቱም በሪፖርቱ ያካተታቸውን ጉዳዮች እንጂ ሌላ ነገር አለመሆኑም..የገለልተኝነታቸው ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ በህጉ ምስክሮች ገለልተኛ መሆን አለባቸው የሚል እንዳልተጠቀሰ ..አቀረቡ:: ዳኛውም ግራ ቀኙን ካዳመጡ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላለፉ:: በአቃቤ ህግ ተቃሞ የቀረበባቸው ምስክሮች 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ ህገመንግስቱን መተርጎም እንደማይችል ነገር ግን ከዛ ውጪ ባለው እውቀት ክስ የቀረበባቸውን ፅሁፎች ከህገመነግስቱ እና ሌሎች ህጎች አንፃር እንደማያስከስሱ ብቻ ማቅረብ እንዳለባቸው 2ኛ ፕ/ር መስፍንም ኢሰመጉ ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት የሚያቁትን ብቻ እንዲያቀርቡ፡፡ ገለልተኛ ለተባለው…መስካሪዎች ገለልተኛ እንዲሆኑ የሚል ደንብ ስለሌለ ማንኛውም ሰው ያለምንም ልዩነት የምስክርነት ቃል መስጠት ይችላል::

በፍትሕ ጋዜጣ ላይ፣ የተዘገቡ ”የካቲት 23 2004 ዓ.ም በተሰራጨው የፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 05 ቁጥር 177 እትም የፈራ ይመለስ በሚል” : ”በቅጽ 5 ቁጥር 179 መጋቢት 7 2004 ዓ.ም ዕትም መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ” እና “ ሐምሌ 22 ቀን 2003 ዓ.ም የሁለተኛ ዜግነት ህይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ?”  በሚሉ ርእሶች በወጡ መጣጥፎችን ተከትሎ ”የሕዝብን ሐሳብ ማናወጥ፣ሕዝቡን በሕገ-መንግስቱ ላይ ማነሳሳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት” በሚሉ ሶስት ክሶች ነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተከሰሰው::


Egypt could block Suez Canal to Ethiopian ships over dam

$
0
0

Opposition figure Hamdeen Sabbahi says Egypt could block Suez Canal to Ethiopian ships if tripartite report shows dam will damage water supply…..

Egypt could stop Ethiopian ships passing through the Suez Canal if a tripartite report shows the Renaissance Dam will damage the flow of water along the Nile River, Egyptian Popular Current leader Hamdeen Sabbahi said at a press confereEgypt could block Suez Canal to Ethiopian shipsnce on Wednesday.

Egyptians must support the government in its dispute with Ethiopia over the dam, Sabbahi added in comments reported by Al-Ahram Arabic news website.

On Tuesday, Ethiopia began diverting the course of the Blue Nile, one of the Nile River’s two major tributaries, as part of its project to build a dam for electricity production, a move that raised concerns in Egypt and Sudan that the flow of water could be disrupted.

A final report on the impact of the planned dam by a joint committee of Egyptian, Sudanese and Ethiopian representatives is expected within days.

“We will not accept any pressure when it comes to our water supply,” Sabbahi said. “Solutions must be presented to avoid conflict.”

If Ethiopia continues with projects that harm Egypt, the nation will unite to deter an attack on its interests, he added.

Sabbahi said that while he fully supports Ethiopia’s right to increase its energy production, Egypt would not accept any reductions in its annual water supply.

If matters escalate, he said, a drop of water would exceed a drop of blood in value. The best way to avoid conflict is to open new initiatives for strategic cooperation in the Nile Basin, he added.

During the 21st African Union summit, President Morsi said Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam had vowed to consider Egypt’s interests regarding the dam.

Egypt’s ambassador in Addis Ababa, Mohamed Idris, said Ethiopia’s intention to divert the Blue Nile had been known since November 2012.

According to the state-run National Planning Institute, Egypt will require an additional 21 billion cubic metres of water per year by 2050 – on top of its current annual quota of 55 billion metres – to meet the needs of a projected population of some 150 million.


የግንቦት 7 ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበ

$
0
0

የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ከግንቦት 11 – 19/2005 አ/ም በበርካታ ወቅታዊ፣ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና የድርጅቱን አዲስ ም/ቤት በመምረጥ ወያኔን በማስወገድ ረገድ ሊከተል የሚገባውን ጠቋሚ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን ከተሳታፊው በመውሰድ ወሳኝ የሆነ ውይይት አድርጓል..

ንቅናቄው ከተለያዩ አለማት በአባላት የተወከሉ ጉባኤተኞች እና በተለያዩ የስራ ክፍል የሚገኙትን የድርጅቱን አባላት ያሳተፈ፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉትም ጉባኤዎች እጅግ የላቀ አባላት የተገኙበት ነበር።
ጉባኤው የነበረውን የም/ቤት ሪፖርት፣ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ማናጅመንት ኮሚሽን፣ የግልግልና ዳኝነት ኮሚቴን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዳመጥ ጥልቅ የሆነ ወይይቶች አደርጓል።
የግንቦት 7 ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤ ደርጅቱ የጀመረውን ወያኔን የማስወገድ ትግል በየትኛውም አቅጣጫ አስፈላጊ ሆኖ የታመነበትን ማናቸውም መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘረኝነትን ስርአት ድባቅ መምታት፤ አልፎም ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አስቸኳይና ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ግዴታው አድርጎ መውሰድ ያለበት አጣዳፊ ስራ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አየርና የዲሞክራሲ ጮራ ሁሌም የሚፈነጥቅባት፣ ህዝብ ካለፍርሃትና ሰቀቀን ወጥቶ የሚገባባት፣ ህዝብ በነጻነት የፈለገውን ፓርቲ የሚመርጥበት፣ የሚያወርድበት፣ ስልጣን የህዝብ መሆኑን የሚረጋገጥበት፣ የመንግስት አካላት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ነጻ ሚዲያ ለመልካም አስተዳደር ግንባታ የሚያገለግልበት፣ ፍትህ ለሁሉም በእኩል የሚሰጥበት፣ ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ ቤተሰብ የመመስረት፤ ከቦታ ወደ ቦታ ያለምንም ገደብ የሚንቀሳቀሱበት መብት እንዲኖራቸው፣ እና የሃይማኖት ነጻነት ይኖረን ዘንድ የድርጅቱ ጉባኤተኞች ሙሉ መሰዋእት ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ሲሉ በድጋሚ ቃል በመግባት መራራ የሆነውን ትግል እጅ ለእጅ ተያይዞ ተራራውን ለመውጣት እና ለማቋረጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
ከ4ኛ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ጉባኤተኛው የግንቦት 7ን 5ኛ አመት ምስረታ ታሪካዊ ቀን አስቦ ውሏል። በዚህ በግንቦት 7, 1997 ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተሳትፎ ፍትህ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ በሀገሪቱ ይሰፍን ዘንድ ለዘመናት ተጭኖት የነበረውን ጫና ተቋቁሞ የወያኔን ስርአት በድምጹ የጣለበት ልዩ ቀን ነበር። ግንቦት 7, ሁሌም በታሪክ የሚዘከር ልዩ እለት ነው።
ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያዊ ትውልድ በግንቦት 7 ያሳየውን ልበሙሉነት፣ ጀግንነት፣ መሰዋእትነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት ለዘለአለም ሲታወስ ይኖራል። ይህንኑ በ97 የተጀመረው የትግል ፍሬ፤ ውጤት ያፈራ ዘንድ አስፈላጊ ያላቸውን ትግሎችን እያደረገ እንደሆነ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 5ኛ አመቱን ከአባላቱ ጋር ሆኖ ሲዘክር ተወያይቷል። ይህም ታሪካዊ የህዝብ ድል ቀን፤ በጠመንጃ ሃይል የነጠቀውን ወያኔን ለማስወገድ እና የህዝብን ድምጽ ለማስመለስ ድርጅታችን ማናቸውንም መንገድ በመጠቀም የሚያደርገውን የትግል ጅማሮ ግብ ለመምታት አሁን ከአለንበት በተሻለ በመጠናከር መሆኑንም ስምምነት ተደርሷል። ድርጅታችን ካለፈው ጉባኤ ጀምሮ ድርጅቱ ያደረገውን እንቅስቃሴ በስፋት ገምግሞ፤ በስራ ሂደት የታዩ ድክመቶችን አፍረጥርጦ ተወያይቶ፤ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ የሚጎለብቱበትን ሁኔታ ተመልክቶ፤ በድርጅቱ የእስትራቴጂ አካሄድ ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን አድርጎ፤ እነኝህን የእስትራቴጂ አቅጣጫዎች በተቀላጠፈ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ወሳኝ የመዋቅር ለውጦችን አጽድቆና ይህን አዲስ መዋቅር የሚያስፈጽሙ ያመራር አባላትን መርጦ፤ በከፍተኛ የጓዳዊ መንፈስና ልዩ በሆነ የትግል ወኔ ጉባኤውን በድል አጠናቋል::
በመሆኑም ግንቦት 7፣ በግንቦት 7 የገባውን ቃል ኪዳን ዛሬም ህያው መሆኑን ሲያረጋግጥና ትግሉ ከመቼውም በበለጠ ጽናትና ቁርጠኛነት እንደሚገፋበት ቃል ሲገባ፣ የሀገራችን ህዝብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ; አዛውንት፣ ወጣት፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ ዘር ቀለም ሳይለያችሁ በግንቦት 7/ 1997 የተሰረቀውን፣ የተነጠቅነውን የህዝብ መንበረ-ድምጽ ስልጣን ወደ ትክክለኛ ባለቤቱ እንዲመለስ የምናደረግውን የትግል ጉዞ ትቀላቀሉ ዘንድ ጥሪያችን ይድረሳችሁ!
የሀገራችን ወጣቶች ሆይ፡ ለነጻነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ቱርፋቶች መሰዋእት ሆናችሁ መሰዋእትነታችሁ በጥቁር ህዝብ የኢትዮጵያ ታሪክ ገድል ውስጥ ለዘላለም ተከትቦ ይቀመጥ ዘንድ ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታ አለባችሁ፡፡ ግንቦት 7 ትግሉን ጀምሯል። ኑ ተቀላቀሉ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ሰበር ዜና-የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞርስ ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው አብደል ፋታህ አልስሲን ጋር ስብሰባ ተቀምጡ

$
0
0
”አህራም ኦን ላይን” የተሰኘው የግብፅ የአንግሊዝኛ ጋዜጣ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 22፣2005 (may 30,2013) ከካይሮ እንደዘገበው የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞርስ ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው አብደል ፋታህ አልስሲን…፣የሃገር ውስጥ ሚኒስትራቸውን ሙሐመድ እብራሂምን እና የደህንነት ሚንስትር ራፋት ሸሃታን ይዘው ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ስብሰባ አድርገዋል።

Image

እንደ ፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ኢሃብ ፋህሚ ገለፃ ውይይቱ የተደገው ግድቡ በግብፅ ላይ የሚያመጣውን አይነተኛ ተፅዕኖ ላይ መሆኑን ጠቁመው በመቀጠል ”በጉዳዩ ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በጋራ አጠቃቀም ዙርያ ላይ አሁንም ንግግር እየተደረገ ነው” ብለዋል።
በመጨረሻም እንደ ጋዜጣው ዘገባ ፕሬዝዳንቱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ሙሐመድ ከማል ኦመር ጋር እና ከ ውሃ ሀብት ሚኒስትሩ ሞሐመድ በሃ ኤልድን ጋር መመካከራቸውን እና ”በግብፅ የውሃ አቅርቦት ላይ ማንም እንዲያስፈራራን አንፈቅድም” የሚል መግለጫ ከፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት መሰጠቱን አጥቷል።

ከ”አህራም ኦን ላይን” ዘገባ ውጭ ተጨማሪ


ኢአዴግ የኢንተርኔት ድህረ ገጾችን ለማፈን 26 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለቻይና መንግስት ፈጸመ

$
0
0

ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአስተማማኝ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ የደህንነት ሰራተኛ ባገኘው መረጃ መንግስት ለስርአቱ አደጋ ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን የመገናኝ ብዙሀን ወደ አገር ቤት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ወደ 26 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መክፈሉን ለማወቅ ተችሎአል…

በቁጥር አንድ እንዲታፈን ትእዛዝ የተላለፈበት ኢሳት ሲሆን ድህረገጹ ራዲዮው እና ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ  እንዲታፈን ስምምነት ላይ ተደርሷል።  ፣ የአሜሪካ ድምጽ  እና የጀርመን ድምጽ የራዲዮ ጣቢያዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ዝግጅት ይዘት አይነት አፈና እንዲካሄድባቸው ሲወሰን አሁንም ድረስ ስርአቱን የሚጻረሩ ድረጎች ሙሉ በሙሉ እንደታፈኑ ይገኛሉ።

ኢሳት ድረገጹ ቢታፈንበትም ራዲዮ እና ቴሌቪዥኑ ካለፉት 5 ወራት ጀምሮ ያለ ምንም ችግር እየተላለፈ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሽ አቅጣቻውን በየጊዜው በመቀያየር ኢሳትን በመከታተል ላይ ይገኛል። አንድንድ ባለስልጣናትም ኢሳትን እየተከታተሉ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

በተመሳሳይ ዜናም መንግስት በፊስ ቡክ እየደረሰበት ያለውን ውግዘት እና የለውጥ ማእበል ለመግታት ‹‹ ሬሳው ›› ሲል ስም የሰጠውን የአፈና ቴክኖለጅ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ሙከራው ተግባራዊ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ የፊስ ቡክ ግንኙነቶችን ለመገደብ እድል እንደሚያገኝ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ካለፈው ወር ጀምሮ ስራውን ለማስጀመር የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አለመሳካቱ ታውቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።



መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ – ከግርማ ካሳ

$
0
0

Muziky68@yahoo.com  ግንቦት 22 ቀን 2005. ዓ.ም

ዜጎች ሃሳባቸዉን በነጻነት የመግለጽ፣ የመሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብት አላቸው። ይሄንን መብት በመጠቀም አገር ቤት የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ በአፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል። ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት…. ለባለስልጣናት ሰልፍ እንደተጠራ ማሳወቅ ብቻ ስለሚያስፈልግ፣ የፓርቲዉ አመራር አባላት ማስታወቂያ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር ይሄዳሉ። የአስተዳደሩ ሃላፊዎች ግን ሊያናግሯቸውም ሆነ ማስታወቂያዉን ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀረ። ተደጋግሞ ሙከራ ቢደረግም፣ በሕጉ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲን ማስታወቂያ ተቀብለው፣ አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ የነበረባቸው የኩማ ደመቅሳ ሰራተኞች ግን ዜጎችን ማንገላታት መረጡ።

ዜጎች ሰልፍ በሚጠሩበት ጊዜ ለባለስልጣናት የሚያሳዉቁት፣ ፍቃድ ለመጠየቅ ሳይሆን፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ የኮንስትራክሽን ግንባታዎች የመሳሰሉ ችግሮች ካሉ፣ አስፈላጋዊዉን ዝግጅት ማድረግ፣ ያም ካልተቻለም ደግሞ ሰልፉ የሚደረገበትን ሌላ አማራጭ ቦታ ወይንም ጊዜ በመግለጽ፣ እንዲተላለፍ መጠይቅ ይችሉ ዘንድ ነዉ።

በአዲስ አበባ አስተዳደር እንግልት የደረሰባቸዉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ በፓስታ ቤት፣ በሬኮመንዴ ሰልፍ እንደሚያደርጉ የሚገለጸዉን ደብዳቤ ይልካሉ። ከአስተዳደሩ ግን ምንም አይነት ምላሽ አሁንም ሳይገኝ ይቀራል። የዚህን ጊዜ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንጂ ከማንም ፍቃድ መጠየቅ እንደሌለባቸው ጠንቅቀዉ ያወቁት ብሉዎች፣ ሰልፉ በተባለው ቀን (ግንቦት 17) እና ቦታ እንደሚደረግ ያሳውቃሉ። የዚህን ጊዜ፣ በሰማያዊ ፓርቲ ዉሳኔ ግራ የተጋቡትና የጨነቃቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለስልጣናት፣ በርካታ የዉጭ አገር መሪዎች በአዲስ አበባ በመኖራቸውና ከፍተኛ መጨናነቅ በመኖሩ፣ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ ይጠይቃሉ። ሕግን የሚያከብረው ሰላማዊዉ የሰማያዊ ፓርቲ፣ በቀኑ መለወጥ ተስማምቶ፣ ሰልፉ የፊታችን እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም እንደሚደረግ ይገልጻል።

እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ፣ ለመብት፣ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገዉ ትግል ስር እየሰደደ መምጣቱን ነዉ። በዚሁ በሰላማዊዉ ትግል እንቅስቃሴ ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የኢትዮጵያዉያን መሰባሰባና መተባበር እየታየ ነዉ። ይሄም በራሱ ትልቅ ድል ነዉ።

(የመኢአድ ፕ/ት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል)

የመኢአድ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ወንድሙ ፣ ድርጅታቸው መኢኣድ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ አባላቱና ደጋፊዎች እንዲገኙ ጥሪ እንዳቀረበ፣ ከፍተኛ የማስተባበር ሥራ እንደሚሰራም አስረድተዋል። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ የተከበሩ አቶ ዳንኤል ተፈራ በበኩላቸው ፣ የአንድነት ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ከልብ እንደሚደግፍ፣ አባላቱም ከብሉ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ሆነዉ ድምጻቸውን ለማሰማት እንደተዘጋጁ ገልጸዋል። ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የአንድነት አመራር አባላት የቅርበት ግንኙነት እንዳላቸው የገለጹት ሌላው የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባልና የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ፣ የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘዉዴ « የሰማያዊ ፓርቲ ያናሳቸው ጥያቄዎች የአንድነት ጥያቄዎቹ ናቸው። በአዲስ አበባ በሚገኙ 23 ወራዳዎች ባሉት ሴሎችና ጽ/ቤቶቹ አማክኝነት፣ የቅስቀሳ ሥራ ጀምሯል» ሲሉም የሰላማዊ እንቅስቃሴዉን ግለት ለማሳየት ሞክረዋል።

ከመኢአድና ከአንድነት ፓርቲ በተጨማሪ የባላራዩ የወጣቶች ማህበር የተስኘው የሲቪክ ማህበርም በሰልፉ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፣ የአመራር አባላቱ ከሰልፉ ጋር በተገናኘም ከወዲሁ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ነዉ። የባላራእዩ ወጣቶች ማህበር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ ወጣት ተክለ ያሬድ በአሁኑ ወቅት በአገዛዙ ፖሊሶች ተይዞ በእሥር ቤት ይገኛል። ይሄም የሚያሳየው ምን ያህል በአገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈሉ እንዳለ ነዉ።

ወደ ዉጭ አገር ስንመጣ ደግሞ ኢትዮጵያዉያን በሚሰባሰቡበት በርካታ የፓልቶክ ክፍሎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ፣ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ ያልታወቀ፣ አገር ቤት እየተደረገ ላለዉ ትግል ትልቅ ድጋፍ እየተሰጠ ነዉ። ትላንት የተለያየ መስመር ይዘው እርስ በርስ ሲላተሙ የነበሩ፣ የቃሌ ክፍል፣ ከረንት አፌር፣ ደብትራዉ፣ ሲቪሊቲ ….የመሳሰሉ ክፍሎች እየተግባቡ፣ እየተቀራረቡና ለአንድ አላማ በአንድ ላይ እየተሰባሰቡ ነዉ። ሁሉም ትኩረታቸውን አገር ቤት አድርገዉ፣ እየተደረገ ላለዉ ሰላማዊ ትግል ድጋፋቸውን እየለገሱ ነዉ። እንደ ኢሳት፣ ኢትዮጵያ ሪቪው፣ ዘሃበሻ፣ አቡጊዳ፣ ኢኤምኤፍ ያሉ ሜዲያዎችም፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ዘገባ እያቀረቡበት ሲሆን፣ ተስፋ ቆርጠው ፣ በነበሩት መከፋፈሎች አዝነዉ ፣ ዝምታን መርጠው የነበሩ ሁሉ እየተነቃነቁ ነዉ።

በዉጭ አገር ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ካየን ደግሞ፣ በባህር ዳር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዳደረገ በኢሳት የተዘገበለት የሽግግር ምክር ቤት የተሰኘው ድርጅት፣ እንዲሁም ኢሕአፓ-ዴ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራዉ መኢአድና አንድነትን ለተቀላቀሉት የሰላማዊ ሰልፍ ያላቸዉን ድጋፍ ገልጸዋል። በስምንት የፓልቶክ ክፍሎች፣ በፌስቡክና ትዊተር በመተላለፍ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን ተከታትለውታል በተባለው፣ ግንቦት 17 እና 18 2005 ዓ.ም የሲቪሊቲ ክፍል ባዘጋጀው የአለም አቀፍ የኢትዮጵያዉያን ኮንፍራንስ ላይ፣ የተገኙት የሽግግር ምክት ቤቱ ዋና ጸሃፊ የተከበሩ ዶር ፍስሐ እሸቱ፣ ድርጅታቸው በአገር ቤት ለሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አረጋግጠዋል። «ትግሉ ያለው አገር ቤት ነዉ። አገር ቤት የሚታገሉትን መርዳት አለብን» ሲሉ ነበር ዶር ፍስሐ ለአገር ቤቱ ትግል ያላቸዉን ጠንካራ ሶሊዳሪቲ የገለጹት።

ይሄ ሁሉ እንግዲህ የሚያሳያዉ ጸሎታችን እየተሰማ እንደሆነ፣ እንደ ሕዝብ ለመብታችን፣ ለአገራችን አንድነት መከበር፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህ መስፈን ፣ ለሕግ የበላያነት ፥ ለመታገል በአንድ ላይ እየተሰባሰብን መሆኑን ነዉ።

ሁለት ነጥቦች ጣል አድርጌ ላቁም። በጣም መሰረታዊና ሊሰመርባቸው የሚገባ ነጥቦች !

አንደኛ – እሑድ ግንቦት 25 ቀን የሚደረገዉ ሰልፍ ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ቀጣይነት ያለው፣ የተደራጀ፣ የተጠና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ይቀጥላሉ። በዘጠና ሰባት በግፍ የተገደሉትን ፣ እነ ሽብሬ ደሳለኝ፣ ለማስታወስ፣ የአንድነት ፓርቲ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ዝግጅት ላይ እንዳለ የፍኖት ጋዜጣ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።። ለአንድነት ቅርበት ያላቸው እንደገለጹልኝ፣ የሚደረጉትን ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ሰላማዊ ሰልፎችን የሚያካትቱ ሲሆኑ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በማቀናጀት የሚሰራ እንደሆነም ለመረዳት ችያለሁ። መኢአድም እንደዚሁ የሚያደጋቸው ይኖራል። በአጭሩ ተከታታይ እንቅስቃሴዎች በሁሉም መስክ ይኖራሉ።

ሁለተኛ- የፊታችን ግንቦት 25 የሚደረገዉ ሰልፍ፣ ሰማያዊ ፓርቲ ቢጠራዉም፣ የመኢአድ፣ የአንድነት፣ የሽግግር ምክር ቤቱ፣ የኢሕአፓ_ዴ፣ የባላራዩ ወጣቶች ማሕበር፣ ሰልፉን የምንደግፍ ዜጎች ሁሉ ሰልፍ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰልፍ ነዉ። ሰማያዊ ፓርቲ ለኮሰ። የተለኮሰውን ማቀጣጠል የእያንዳዳችን ነዉ። በድርጅቶች የሚጠሩት እንቅስቃሴዎች ዉጤት የሚያመጡት እያንዳንዳችን ስንተባበር ብቻ ነዉ። አገር ቤት ያለነዉ ወደ ሰልፉ መሄድ ይጠበቅብናል። ሰልፉ ሰላማዊና በሕግ የተፈቀደ ነዉ። «መብታችን ተረገጠ፣ ድህነት በዛ፣ ዘረኝነት በዛ፣ በአገራችን ባርያ ሆንን መኖር መረረን፣ ፍትህ ጎደለ፣ ቀንበርና ግፍ በዛ» የምንል ካለን ፣ እንግዲህ ጊዜው አሁን ነዉ። ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንነሳ። እንጩህ። ድምጻችን እንደ ነጎድጓድ ያስተጋባ። አንፍራ።

በዉጭ አገር ያለነዉ ደግሞ፣ ስልክ እንደዉል፣ ኢሜል እንላክ። ዘመድ ወዳጆቻችንን እናበረታታ። ደብረጺዮን የስልክ መስመሩን እና ኢንተርኔቱን ሊዘጋው ይችላል። ግድ ይለም። መስመሮቹን እንዲዘጋ ማስደረጋችን በራሱ ትልቅ ድል ነዉ።

ያኔ ኢትዮጵያም በልጆቿ ትኩራለች !


ስለደረሱብን በደሎች ከወገኖቻችን ጋር አብረን እንጮሃለን! …

$
0
0

ስለደረሱብን በደሎች ከወገኖቻችን ጋር አብረን አንጮህምን?! …ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 በሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ሙስሊም ኅብረተሰብ እንደ ዜጋም እንደ ሙስሊምም እንዲሳተፍ ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሙስሊሙ እንደዚህች አገር ዜጋ፣ … ከዜጋም በሃይማኖት ነፃነቱ ላይ መጠነ ሰፊ ጥሰቶች እየተፈፀሙበት እንደሚገኝ ዜጋ፣ … በፍትኅ አካላት መጠነ ሰፊ ኢ ፍትኃዊ በደሎች እየተፈፀሙበት እንደሚገኝ የዚህች አገር ዜጋ፣ … ስለ መብቱ መከበር “ድምፃችን ይሰማ!” ብሎ በጮኸ ከአንድ ዓመት በላይ “አክራሪ” ተብሎ እየተብጠለጠለ እንደሚገኝ ዜጋ፣ … “ሕገ መንግሥታዊ መብቶቼና ነፃነቶቼ ይከበሩ!” ብሎ በጮኸ “እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም የሚቋምጡ፣ ስውር አጀንዳ ያላቸው የውጭ ኃይል ቅጥረኛ አክራሪዎች” ተብሎ የዜግነት ክብሩ እንደተነካበት፣ አለግብሩ በክህደት እንደተወነጀለ ዜጋ፣ … “የጋራ ሃይማኖታዊ ተቋሜን አመራሮች የመምረጥ መብቴ ይከበር!” ብሎ በጮኸ ክርስቲያን ወገኖቹ በጥርጣሬ ዓይን እንዲያዩት ክፉ ሤራ እንደተሸረበበት ዜጋ፣ … አንድዬ የጋራ ሃይማኖታዊ ተቋሙን በኃይል እንደተነጠቀና ሰብአዊ ክብሩን በሚዳፈር መልኩ በገዛ ተቋሙ መሣርያነት ‹እምነትህን ልምረጥልህ› እየተባለ እንደሚገኝ ዜጋ፣ … አያሌ እህትና ወንድሞቹ በሃይማኖታዊ ሰብዕናቸው እና በእምነታቸው የታዘዘውን በመተግበራቸው ብቻ /ከእምነታችሁ ወይ ከትምህርታችሁ ምረጡ በሚል/ ከትምህርት ገበታቸው በግፍ እንደተፈናቀሉበት ዜጋ፣ … “ሕገ መንግሥታዊ መብቴ ተነክቷል፣ ለሕጋዊ ጥያቄዎቼ መንግሥትን አነጋግራችሁ መፍትኄ አፈላልጉልኝ” ብሎ በፊርማው መርጦ የላካቸው ምርጥ ወኪሎቹ አለስማቸው ስም ተሰጥቷቸው በአሸባሪነት እንደተከሰሱበት፣ መከሰሳቸው ሳያንስ የዋስትና መብት ተነፍገው በእስር እየተንገላቱበት እንደሚገኝ ዜጋ፣ … መስጂዶቹን እንደተቀማና እየተቀማም እንደሚገኝ ዜጋ … አዎ፣ እነዚህ ሁሉ እና ሌሎችም በርካታ በደሎች እየተፈፀሙበት እንደሚገኝ የዚህች አገር ዜጋ … በአዲስ አበባ የሚኖረው ህዝበ ሙስሊም … ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት … ፍትኅ እንዲሰፍን፣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር፣ የህዝበ ሙስሊሙ ህጋዊ ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ እንዲሰጣቸው፣ የሕሊና እስረኞች ከእሥር እንዲፈቱ፣ … ለዘመናት በሀዘኑም በደስታውም አብረውት ከኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ… ድምፁን እጅግ ከፍ አድርጎ ማሰማት አለበት እላለሁ፡፡ ወሏሁአዕለም፡፡

ምንድነው ጉዱ?

$
0
0

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ምንድነው ይሄ በየሄድኩበት የማየው ሀገራዊ ጉድ? የዚህ ሁሉ አፍዝ አደንግዝ መንስኤ ምን ይሆን? በእውነት ኢትዮጵያ የማን ወይም የነማን ናት? እንታይ ኢዩ ጉዱ! እንታይ ኢዩ’ሞ ብላዕሊ ሕዝቢ ኢትዮጵያ ዝወረደ? መአዝ ኢዩ እዙይ ኩሉ ህማምን ፃዕርን ዝክላዕ ወይን ድማ ዝውገድ..? ብሃፋሽኡ ኩሉ አብዚ ዘመን እዚ ዝርዐይ ዘሎ ኩነት የጭ’ንቅን የስምብድን!ጎይታና ኢየሱስ ክርስቶስ እንተዘይመፀን እንተዘይተራድኣን ብዙኃት ነገራትና ናብ አዲ ሦርያ እንዳወፈሩ ኢዮም …
እውነትም የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው፡፡ ዶክተር ኃይሉ አርአያን ያፈራች ትግራይ፣ ገ/መድኅን አርአያን የፈጠረች ትግራይ፣ አስገደ ገ/ሥላሤን የወለደች ትግራይ፣ ወጣት አብርሃ ደስታን ያፈራች ትግራይ፣ በኢትዮጵያ ሲመጡበትና የመጡበት ሲመስለው አራስ ነብር የሚሆነውንና የደመ ቁጡነቱ የብዕር ወላፈን ከጠላት አልፎ ለየዋሃን ወዳጆቹ የሚተርፈውን የኢትዮሰማይ ብሎግ አዘጋጅ ጌታቸው ረዳን ያፈራች ትግራይ(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጌታቸው ረዳም ስላለ ነው)፣ አብርሃ በላይን የወለደች ትግራይ፣ … ስንቶቹን ዘርዝሬ እጨርሳለሁ … እነዚህን ውድና ብርቅዬ ልጆች ያፈራች ኢትዮጵያዊት ትግራይ ከዚህ በታች የምዘረዝረውን አጸያፊ ተግባር የሚፈጽሙ ምግባረ ብልሹ ልጆችን ትወልዳለች ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በአንድ ሀገር ጉድ ሲወለድ የጉዱን መጠን መተንበይ አይቻልምና የማንም ምድራዊ ፍጡር አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ግፍና በደል የሚሠሩ የትግራይ ልጆች መላዋን ኢትዮጵያን ወርረው በመቆጣጠር አሁን የምነግራችሁንና እናንተም ከዚህ ቀደም የምታውቁትን ግፍ እየሠሩ ናቸው፡፡
[አንድ ጓደኛየ ሁለት ዶሮዎች አሉት - አንዲት ሴት አንድ ወንድ፡፡ ጥሬ ሲበትንላቸው ሴቲቱ ወንዱን አታስበላውም፡፡ እርሷ ብቻ ስትበላ እርሱ አጠገቧ ሣር ቢጤ ይነጫል፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ፡፡ አዘናግቶ ሊለቅም ሲጀምር አርቃ ታባርረዋለች - በመንቆሯ እየነከሰች፡፡ ሌሎች ወፎችና እርግቦች አብረዋት ሲለቅሙ ግን እነሱን ምንም አታደርጋቸውም፡፡ ከራስዋ ጋር በአንድ ቆጥ የሚያድረውን ወገኗን ግን ታሳድደዋለች፡፡ ይህ ነገር ብዙ ካሳሰበኝ በኋላ የዚህን ምግብ ላይ ያለመስማማት ጉዳይ ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ጓደኛየን ጠየቅሁት፤ ከኔው ጋር ተመሳሳይ እሳቤ እንዳለው ተረዳሁ፡፡ የዚህች ዶሮ ችግር የምግብ መኖር አለመኖር አይደለም፤ ችግሯ ማሸነፏን ለማሳወቅ የምታደርገው ጥረት ነው፤ በባዶ ሜዳና ባላስፈላጊ ሁኔታ እንዲህ የምትደክመው ሥነ ልቦናዊ የበላይነቷን ለሚመለከተው ሁሉ በተለይም በ‹ሰብኮንሸሷ› ውስጠኛ ክፍል ተሰንቅሮ ፍዳዋን ለሚያስቆጥራት ‹ኢድ/ኢጎ› ለማሳየት ነው፡፡ እርሷ ጠግባ ብዙ ጥሬ ሜዳው ላይ ፈስሶ እያለ እርሷ እዚያ አካባቢ እያለች ያ ምሥኪን ዶሮ ወደዚያች ምግብ ትውር አይልም - ሌሎች አእዋፋት ግን እንደልባቸው ይለቅማሉ - የሚገርም እውነተኛ የነገር ምስስሎሽ (አናሎጂ)! ፡፡ እሱም አቅሙን አውቆ ይኖራል፤ አሳዳጅና ተሳዳጅ አንዳቸው ባንዳቸው በጎ ፈቃድ ‹አብረው› ይኖራሉ - መኖር ተብሎ፡፡ ]
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዕዝ – ቀደም ሲል በግንቦት ሰባት እንደተገለጠውና እኛ በሀገር ቤት ያለነው ወገኖችም በቅርበት እንደምናውቀው – ለይስሙላና ለታይታ አልፎ አልፎ ከሚስተዋል የታችኛው የዕዝ መስመር ላይ የሚታይ የሌላ ብሔር ተወላጅ ምደባ በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሥልጣኑና የውጊያ አመራሩ የተያዘው በትግሬዎች ነው፡፡ መቶ ወታደር ካየህ – ጨዋነት በተሞላበት ግምት – መላ አመራሩን ጨምሮ ሰማንያዎቹ ትግሬዎች ቢሆኑ አይግረምህ፡፡‹ታዲያ ምን ይጠበስ?› አትበለኝ፡፡ ምንም አይጠበስም፤ እኛው እንደለመድነው በአጋዚም በለው በትርሃስና በሐጎስ እንጠበሳታለን፡፡
አደራ! ወያኔ ወይም ትግሬ ስል መልካሞቹን ሳይሆን በአሁኑ ሰዓት በወያኔ አመራር ሥር ተኮልኩለው ሲያበቁ የኢትዮጵያውያንን ደም እንደመዥገር የሚመጡትን፣ እንደአልቅትና ትኋን የሚመገምጉትን ብቻ ነው፡፡ እርግጥ ነው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ኖሮን ችሎታንና ብቃትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በእኩል የዜግነት መብታቸው የሚቀጠሩ ትግሬዎችን ለመለየት ባለመቻሉ ሁሉም የትግሬ ሠራተኛ እንደወያኔ መቆጠሩ ጊዜው ያመጣብን ፈውስ የለሽ ደዌ ነውና ይህን እውነታ ለመገንዘብ ጊዜና ትግስት እስኪኖረን ድረስ ይቅርታ መጠየቅ የሚገባን ጥቂት ትግራውያን ዜጎች መኖራቸውን ላስታውስ እፈልጋለሁ፡፡ ‹ከኑግ ጋር የተገኘሽ መጭ(ሰሊጥ?) አብረሽ ተወቀጭ› እንዲሉ እነዚህ በችሎታና ብቃታቸው ሊያውም ከሌሎች ጋር ተወዳድረው (በሜሪታቸው) ቦታውን ሊያገኙ ይችሉ የነበሩ ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ሲታሙ ሳይ በግሌ ይሰማኛል – የሚገኙበት ሥነ ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ይገባኛል፤ ህመማቸው ህመሜ መሆኑን ሳልገልጽ አድበስብሼ ማለፍም አልፈልግም፡፡ ችግራቸውን ልንረዳላቸው ይገባል እንጂ እኚህን መሰል ወንድምና እህቶቻችንን ከደናቁርትና ከእጅ እስካፋቸው ብቻ ማሰብ ከሚችሉ አንበጣ ወያኔዎች ጋር አዳብለን በነገርም ይሁን በርግማን መጎሸም እንደማይገባን እንወቅ፡፡ ይህ ችግር ደግሞ መጥፎና ማንም በቀላሉ ሊረዳው የማይችል ስስ ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከፍርደ ገምድልነት እንድንቆጠብ ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ የምናያቸው ብዙ መጥፎ ነገሮች ዕድገታቸውን ጠብቀው ያልፋሉ፤ እንኳን ይህ ዘመን የአህመድ ግራኝና የዮዲት ጉዲትምም የመንጌ ቀይ ሽብርም የዘመነ መሣፍንት ትርምስም … ሁሉም በሰዓቱ አልፏል፡፡ ይህም ያልፋል – ሰንኮፉ ወድቋል፡፡ የቀረው ካልቀረው በእጅጉ ያነሰ ነውና እንዲያው አጃኢብ ከማለትና ከጸሎት ጀምሮ የበኩላችንን ለማድረግ ከመትጋት በስተቀር በስተቀር ብዙም አይሰማን፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ቂም በቀል የሚቋጥር ሰው በተመሳሳይ አረንቋ ለመዳከር ያለመ ነውና ከዚህ አዙሪት ባፋጣኝ እንውጣ፡፡ በነሱም አላማረ፡፡ ስቃያችን እንዳይረዝም ከብቀላና ከሸፍጥ ነጻ ሆነን ፈጣሪ ሀራ እንዲያወጣን ከልብ እንለምነው – ይቻለዋል፡፡ እየሆነ ያለውን የፈቀደው ሆን ብሎ እኛን ለመፈተን መሆኑን እንረዳ፡፡ አለበለዚያማ እነኚህ ጉዶች ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ እንደከብት ሊነዱት እንዴት ይቻላቸዋል? …
በተረፈ ግን ሀገራችሁ እንዲህ ሆናላችኋለች፡፡ አዲስ ነገር እየነገርኳችሁ እንዳልሆነ እኔም አውቃለሁ፡፡
የምነግራችሁ በጥቅስና በምንጭ የተዥጎረጎረ ጥናታዊ ዘገባ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሆን ብዬና በሥራዬ አጋጣሚ በመዘዋወር ያገኘሁት መረጃ ነው፡፡ መረጃየ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ በቀላሉ የሚያኮርፍ ትግሬ ይህን ትንግርተኛ ጉድ የያዘ መጣጥፍ ባያነብ ይሻለዋል፡፡ በኋላ እኔ ላይ የሚለጥፈውን ታርጋ በመፈለግ እንዳይንገላታ ቀድሞውን አያንብ ዌም ድረ ገጽም ከሆነ አይለጥፈው፡፡ እዚያው በጠቡሉ እኔም እዚችው በጠበሌ፡፡ ያልተበረዘ ያልተከለሰ እውነቱ ግን ይሄውና፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/03/defence-minster.jpg

የመከላከያ ሠራዊት ሕንጻ

መከላከያ ሚኒስቴር ሄድኩ፡፡ ከበር ጀምሬ ስታዘብ ከሞላ ጎደል ሁሉም ትግሬ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ለመግባት ምክንያቴን ገልጬ ተረኛው ዘብ ለውስጠኛው ሰው የይለፍ ፈቃድ ሊጠይቅልኝ በስልክ ሲያናግር የተጠቀመው ቋንቋ ትግርኛ ነው – አውቃለሁ፡- ከተጓዳኝ ፍካሬያዊ መልእክቱ ባለፈ ይህ ክስተት በራሱ ክፋት የለውም – የራስን ቋንቋ መጠቀምም የሚበረታታ እንጂ የሚያስነቅፍ አይደለም – መቼና የት ለምን የሚሉትን ጥያቄዎች ማጤን ግን የብዙ ልጆች እናት የሆነችን አንዲት ‹ፌዴራላዊት› ሀገር በ‹እኩልነትና በፍትህ› የሚያስተዳድሩ ወገኖች ሊያስቡበት ይገባቸው የነበረ ጉዳይ መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ – በዚያ ላይ የሚታሙበትን ብዙ ነገር መገንዘብና ለተጨማሪ ሃሜት በር መክፈትም ተገቢ አይደለም ፡፡ ብቻ እኔም በትግርኛ አናግሬው – በዚያም ምክንያት በጣም ተደስቶ – ገባሁ፡፡ በአገዛዙ ውስጥ በወያኔነት የተገጠገጡ ትግሬዎች – አዝናለሁ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልክ – የዋሆች ናቸው- በቋንቋ የሚያመልኩ፣ ለጎሣዊ አንድነት በቀላሉ የሚንበረከኩና ለወያኔያዊ ማንነት የሚሰግዱ ጅሎች ናቸው፡፡ ትግርኛ ጥርት አድርገህ ከተናገርክ ብዙ ሥራ ልትሠራ ትችላለህ – ከደረሱብህ ግን አንተን አለመሆን ነው(ትግርኛ በመናገሩ ምክንያት አምባሳደር ሊያደርጉት የመለመሉት ሰው ኋላ ላይ ትግሬ አለመሆኑን ሲያውቁ መሸወዳቸው ገባቸውና ሥልጠናውን ጨርሶ ሊመደብ ሲል እንዳባረሩት ቀደም ሲል ሰምቻለሁ – ከዓለም በዘረኝነታቸው የሚስተካከላቸው የነበረና የሚኖር አይመስለኝም – ከአፓርታይድም ይብሳሉ፡፡ በሀገር የጋራ ሀብት እንደልባቸው የሚፏልሉ የአሁን ጅሎች የነገ የታሪክ ዝቃጮች መሆናቸውን በድፍረት የምመሰክረው የነገ ዕጣ ፋንታቸውን ከወዲሁ ቁልጭ አድርጌ እያየሁ ለነሱና ለጠፋው ትውልዳቸው ከልቤ በማዘን ነው)፡፡ ምን አለፋህ – ወያኔዎች ቂሎች ናቸው – ብልጥነት ሲበዛ ሰውን የሚያጃጅል ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ይሉኝታና ሀፍረት የሚባል ጨርሶውን የሌላቸው፡፡ እነዚህ ወያኔ ትግሬዎች 0.000…1 በመቶ ይሉኝታ የላቸውም፡፡ የጅልነታቸው መሠረትም ይሄው ‹ሰው ምን ይለኝ ይሆን? ታዛቢ ምን ይለኛል? › ማለት አለመቻላቸው ነው፡፡ ሀገሪቱን እኮ የአንድ ቤተሰብ ንብረት ያህል ነው የቆጠሯት! አይገርምም? ‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›ና እንደልቤ መናገሬን ከጥፋት ላለመቁጠር ሞክር፡፡

[አማራ እንደወይራና ደሬ ፍልጥ ሥጋውና አጥንቱ ወያኔዎች በሚለኩሱትና በሚያስለኩሱት እሳት እየነደደ ሳለ በደስታ እየቦረቃችሁ ይህን እሳት የምትሞቁ ትግሬዎችም ሆናችሁ ሌሎች ዜጎች ወዮላችሁ! እሳት በባሕርይው ተዛማች ነው፡፡ በሰው ስቃይ የምትደሰት ሁላ ነገ ወር ተራህ ሲደርስ አንተም አይቀርልህም፡፡ ይህን ፍርድ ሰው አይደለም የሚጥልብህ፡፡ ተፈጥሮ ራሷ ናት - እግዚአብሔርም ልትል ትችላለህ፡፡ … አንድ ጉብታ ቦታ ላይ ቤቶች በእሳት መቀጣጠል ይጀምራሉ፡፡ ሰዎች በኅብረት ሆነው ውሃ ያለው በውሃ፣ ሌሎች በአፈርም በቅጠልም ያን እሳት ብዙ ውድመት ሳያስከትል ለማጥፋት ይሞክራሉ፡፡ ከጉብታው ወረድ ብሎ በሚገኝ ረግረጋማ ኩሬ ውስጥ ዕንቁራሪቶች አሉ፡፡ አንዲት ቀበጥና የሰው ችግር የማይገባት ኮረዳ ዕንቁራሪት የእሳቱ ነበልባልና ጪስ በሚሰጣት የደስታ ስሜት ተውጣ የእልልታ በሚመስል ዕንቁርቁርታ ጩኸቷን ታስነካው ያዘች፡፡ እናቷ ግን ‹ተይ ዕረፊ፤ አያድርስ ነው› ብላ ብትመክራትም ‹እንዴ እማዬ! እዚህ ውሃ ውስጥ ሆኜ ምን እሆን ብለሽ ነው› በማለት የደስታ ቡረቃዋን ትቀጥላለች፡፡ … መንደርተኛው ባለው ‹ሪሶርስ› እሳቱን ለማጥፋት ያደረገው ጥረትና ሙከራ ሁሉ አልሳካ ይለውና እንሥራ ያለው በእንሥራው ቅል ያለው በቅሉ ውሃ እየቀዳ ያን ጠንቀኛ እሳት ለማጥፋት ወደኩሬው ይወርዳል፡፡ ሁኔታው ያላማራት እናት ወደታች ወርዳ ትመሽጋለች፤ ልጅ በሰው ስቃይ እየተደሰተች በኩሬው የላይኛው ክፍል ቡረቃዋን ትቀጥላለች፡፡ እንደተባለው አያድርስ ነው ያኔ በአንዱ ቅል ውስጥ ትጠለፍና እሳት ማጥፊያ ሆና አርራ ትሞታለች፤ እናትም ብዙ አላዘነችም - ቀድማ አስጠንቅቃለችና፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ የለም ወንድሜ፡፡ ዘመነ መርዓ እንዳለ ሁሉ ዘመነ ፃማ ወብካይ እንዳለም ማወቅ ተገቢ ነው ያገሬ ልጅ፤ ሁልጊዜ ጅልነት ከጥቅሙ ጉዳጡ ያመዝናል እህቴ፡፡ ጥጋብንና ቂላቂልነትን ገታ አድርጎ ወደኅሊና መመለስ ለሟች ብቻ ሳይሆን ለገዳይም የሚተርፍ እርባና አለውና ጎበዝ ነቃ እንበል፡፡]

መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሀብት ነው፡፡ አሁን ግን የወያኔ ትግሬዎች ብቻ ነው፡፡ ማንም ሌላ ኢትዮጵያዊ ‹የኔ መከላከያ ሠራዊት› ብሎ የሚቀበል አይመስለኝም – ፖሊሱንም፣ ቤተ መንግሥቱንም፣ ባንዲራውንም፣ ብሔራዊ መዝሙሩንም እንዲሁ ‹የኔ ነው› ብሎ የሚቀበል የለም፤ ባይገርማችሁ ኢትዮጵያንም የኔ ናት ብ የሚቀበላት እየጠፋ ነው፡፡ ‹እነሱው እንደፍጥርጥራቸው ያድርጓት› ብሎ አብዛኛው ሰው ትቷታል – መጥፎ የነገሮች ሂደታዊ ዕድገት! (ባንዲራ ሲሰቀልና ሲወርድ ሰዓቱ ካለመጠበቁም በላይ አክብሮ የሚቆምነና ሰላምታ የሚሰጥ ወታደር አላይም፤ ጎበዝ እንደሕዝብም እንደሀገርም አልሞትንም ብለን እንዳንወሽ!) በአመራር ሳይሆን በሌሎች ድጋፍ ሰጪ የሥራ ክፍሎች የሚገኙ ሌሎች ወገኖች እንዴት በመሰለ ፍርሀትና መሽቆጥቆጥ እንደሚኖሩ አትጠይቁኝ፡፡ በደርግና በአፄው ዘመነ መንግሥቶች ሥልጣን ላይ የነበሩ ትግሬዎች ወንበራቸው የፈቀደውን የሥራ ኃላፊነት ያለመሸማቀቅ ሲያከናውኑ የዛሬው የይስሙላ ኮሎኔል ተብዬ ‹አዛዥ› ከተላላኪ የትግሬ ወያኔ ፈቃድ ሳያገኝ አንዳችም ነገር አይሠራም፤ አስገራሚና ከአእምሮ የመቀበል አቅም በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዘመን! ኧረ በኢትዮጵያ ጉድ ፈልቶላችኋል! የት ነበርክና ዛሬ እንዳዲስ እንዲህ ያንዘረዝርህ ያዘ እንዳትሉኝ ብቻ፡፡ አጠቃላይ ነገረ ሥራቸውና እያደር ጥሬነታቸው ደም ፍላቴን ቀስቅሶብኝ ነው አሁን በብዕር የማወጋችሁ፡፡

ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌዴራል ፖሊስ ሄድኩ፡፡ ዘብ አካባቢ ጥቂት ኢትግሬዎችን አየሁ፤ ወደውስጥም ገባሁ – ግን ያው እንደመከላከያው የተሞላው በአብዚ አብዚ ነው፡፡ በጥልቀት ለተመለከተው ወያኔ ትግሬዎች ያሳዝናሉ፡፡ ይህን ሁሉ ሀገራዊ ሥልጣን ለብቻቸው የያዙት እኮ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የሚጨነቅ ከሌላው ብሔር ሰው ስላልተገኘ ነው! ሸክማቸው ከበደ፤ አጋዥም አልፈለጉ፤ ብቻቸውን ይዳክራሉ፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ ብቻቸውን ሲባዝኑ ስታዩዋቸው አንጀታችሁን ይበሏችኋል፡፡ እናግዛችሁ ብትሏቸው ‹በገዛ ሀገራችን አንተን ምን አገባህ?› ከሚል ይመስላል አይፈቅዱልህም፡፡ አንድ ጊዜ በአንድ መሥሪያ ቤት አንድ ባለዲግሪ ሰው አወዳድራችሁ ላኩልን የሚል ትዕዛዝ ይወርዳል፡፡ ትግሬው አለቃ ትግሬ ባለዲግሪ ቢያፈላልግ ያጣል፡፡ ነገሩን የሚያውቅ አማራ ባለዲግሪ ቢጠይቀው በለበጣ ስቆ ‹ያንተን ዲግሪ እንጨት ስበርበት፤ ውሃ ቅዳበት› በሚል ምፀታዊ የምልክት ቋንቋ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረገበትና ባለዲፕሎማ ትግሬ እንደላከ አጫውቶኛል – ልጆቼን ይንሳኝ የምነግራችሁ እውነቴን ነው፡፡ ቢሆንም ይህም ያልፋልና በግብዞች ተናድዳችሁ ግብዝ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ፡፡ ሆድ ብዙ ይችል የለም? ባይሆን በዚሁ ይብቃችሁ እንዲለንና እንዲምረን ጌታን መማፀን ነው፡፡ በመሠረቱ የመንግሥት ሥልጣንና ደመወዝ የሚቀኑበትና የሚጎመዡለት ሆኖ አይደለም፡፡ ሊስትሮ ሆኖ መኖር ይሻላል፡፡ የሚያናድደን ግን ካለችሎታቸውና ካለዕውቀታቸው ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን በዐይነ ዐዋጅ ሁሉንም ነገር እየያዙ ሥራ ስለሚያበላሹ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በበኩሌ ሀገራዊ ሥራ እስከተቃና ድረስ፣ አስተዳደራዊ ግፍና በደል እስከተወገደ ድረስ እንኳንስ አንድ ብሔር አንድ ቤተሰብም ሀገሪቱን ቢገዛ ጉዳየ አይደለም፡፡የነዚህ ግን ለዬቅል ነው፡፡ ከዘበኝነት በቀጥታ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ሲመደብ ብታይ፣ ከጽዳት በቀጥታ የመኪና አሽከርካሪ አሰልጣኝነት በአንዲት ቀላጤ ተመድቦ ብታይ ከመገረም ባለፈ የምትለው ነገር የለህም – ኢትዮጵያ የነሱ እንጂ የአንተ ሀገር አይደለችማ! ለካንስ ዜጎች በነቂስ ከሀገር ለመውጣት የሚጥሩት ለዚህ ኖሯል?

የመኮንኖች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ሄድኩ፡፡ የግቢው ኦፊሴል ቋንቋ ከበር ጀምሮ ትግርኛ ነው፡፡ ቤተ መጻሕፍትም ግባ መስተንግዶም ግባ የትም ግባ የትም የምታገኘው ትግሬ ነው፡፡ አደራችሁን ጥሩዎች ትግሬዎች በጉዱ ካሣ ‹ዕብደትና ምቀኝነት› የተሞላበት ንግግር እንዳትከፉብኝ፤ የመንታ እናት ተንጋላ ታጠባ ዓይነት ሆነብኝ፡፡ ራሴው ፈርቼ ሰውን አደራ ማለት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው እባካችሁን? ግን ለምን ፈራሁ? አሃ – በይሉኝታ ባህል ነዋ ያደግሁት፡፡ እነሱ ቢተውት እኔም ልተው?

ምግባረ ሠናይ ወደተባለው ሆስፒታልም አመራሁ፡፡ ከዘበኛ እስከ ላይኛው ሜዲካል ዳይሬክተር ትግሬ ነው – በነገራችን ላይ የአሁኑን አታስዋሹኝ ማን እንደሆነ አላውቅም – እኔ በሄድኩ ሰሞን ግን ሁሉም ትግሬዎች ነበሩ፡፡ በጣም አልፎ አልፎ ጽዳቶችና ዕቃ አቀባባዮች ከሌሎች ጎሣዎች አይቻለሁ – የሄድኩበት ጊዜ ራቅ ስለሚል ነው የአሁኑን አለማወቄን የተናዘዝኩት፤ ለነገሩ ገዢዎቻችን ይሉኝታቸውን ቀቅለው የበሉ ወይም ባወጣ የሸጡ በመሆናቸው ለውጥ ይኖራል ብዬ አልጠብቅም፡፡ ሰው በጊዜ ሂደት ይማራል እነሱ ግን እየባሰባቸው ነው የሚሄድ፤ ሰዎች አልመስልህ እያሉኝ ነው ወገኖቼ፡፡

እዚያው ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘውን የመኮንኖች መኖሪያ ካምፕ ውጪ ሆኜ ወጪ ገቢውን ታዘብኩ፡፡ እንደወያኔ የምርጫ ውጤት 99.98 የሚሆነው ወጪ ገቢ ያው ትግሬ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአንድ የወታደር ሚኒባስ ወይም የራሽያ ዋዝ ሊፍት አግኝተህ ብትሳፈር ከአሥሩ ወታደራዊ መኮንኖች የሌላ ጎሣ የምታገኘው – ለዚያውም ዕድለኛ ከሆንክ – አንድ ቢሆን ነው፤ አንድ ጊዜ ይህን ዕድል አግኝቼ ሾፌሩ ብቻ ኢትግሬ ሆኖ ታዝቤያለሁ፡፡ እኛ በትግርኛችን ወሬያችንን እስከጣራ ስናቀልጠው ሾፌሩ ከሃሳቡ ጋር ነበር የቤቱን ጣጣ ያወጣ ያወርድ የነበረው – ያልታደለ፡፡ ምን ቅብጥ አድርጎት አማራ ሆነ?

ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ሄድኩ – ይገርማችኋል አሁን አሁን እርሱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ብዙ ተቀጣሪ ኢትግሬዎች አየሁ፡፡ የኃላፊነት ቦታዎችን ግን አትጠይቁኝ፤ ግቢው የተጥለቀለቀው የሚመስላችሁ በ‹ጌትነታችን ይታወቅልን› ሥነ ልቦናዊ ደንባራ ስሜት እየተነዱ ጮክ ብለው በሚያወሩ ወያኔ ትግሬዎች ነው፡፡ ይሄ ‹ምቀኝነቴ› ዛሬ የት እንደሚያደርሰኝ አይቼው፡፡ በነገራችን ላይ ቦታው ለመንግሥት ሥልጣን አሰጋም አላሰጋም በተለይ የሚበላበትና የሚጠጣበት የሥልጣን ቦታ ላይ ወያኔ ትግሬ ይጠፋል ማለት ዘበት ነው – ዋና ቦታ ለይምሰል ኢትግሬ የያዘው ቢመስል ጉዳዩ ሌላ ነው፡፡ ሀገሪቱ በአንድ ብሔር ሥር በጥገትነት ስለተያዘች ትግሬ በሥልጣን የሌለበትን መሥሪያ ቤት ለማግኘት እንደዲዮጋን ጠራራ ፀሐይ ላይ ፋኖስ ጨምረህ ብትዞር አታገኝም – እንዴት ብሎ? ሀገርን የፊጥኝ አሥሮ የመምራት ታሪካዊ ኃላፊነት በትግሬዎች ጫንቃ ላይ ወድቆ ትግሬን ከማንኛውም የሥልጣን ቦታ ማጣት በፍጡም አይታሰብም፡፡ ማንንስ ያምናሉ? ማንንም! ‹ሌባ እናት ልጇን አታምንም› ይባላል፡፡

የዚህ ሁሉ ከንቱ ተግባራቸው መንስኤ ሌሎችን ያለማመን ችግር ነው፡፡ ማይም ወያኔ ትግሬ የቢሮ ኃላፊ ሆኖ ሲሾም የተማረ ኢትግሬ አስፋልት ለአስፋልት ጫማውን ሲጨረስ እሚውለው ሀገሩ የርሱም ስላልሆነች ሳይሆን ወያኔዎች ‹ጥቅማችንን ይጋራብናል፤ ንግሥናችን ይጨናገፍብናል› ብለው ስለሚያምኑ ማንንም ወደመንግሥት የኃላፊነት ቦታ ማስጠጋ ስለማይፈልጉ ነው፡፡ የቬንዞላው ኒኮላስ ማዱሮ ከአውቶቡስ ዘዋሪነት በቀጥታ ወደ ምክትል ፕሬዚደንትነትና ከዛም ሳይታሰብ ወደ ዋና ፕሬዚደንትነት የተሸጋገረው በችሎታው ሳይሆን በአምባገነኖች በጎ ፈቃድ መሆኑን ለሚገነዘብ ሰው የወያኔ ደናቁርት፣ ማይምና ነቀዝ ባለሥልጣናትን የሹመት ሂደት መረዳት አያቅተውም – ወዮ ለሀገራቱ ሕዝቦች፡፡ የመማር ያለመማር ጉዳይ አይደለም፤ በመታመንና ባለመታመን መሀል ያለው ክፍተት በታሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ በበላዮች ለማመን የመፈለግና ያለመፈለግ ጉዳይ ነው ዋናው ወሳኝ ነገር፡፡ ለአፍሪካዊ የፖለቲካ ሥልጣን መማር እንዲያውም አስፈላጊ አይደለም፡፡ ከተማርክ ለምን ትላለህ፤ ካልተማርክ ግን ለምሳሌ ግደል ብትባል ስንት እንጂ ለምን ብለህ አትጠይቅም፡፡ ሆድ እንጂ ራስ እንዲኖርህ አይፈለግም፡፡ የዘር ራ እንጂ የዕውቀት ምጥቀት የትም አያደርስህም፤ ደምህ እንጂ ችሎታህ አያዋጣህም፤ አጭበርባሪነትና መስሎ አዳሪነት እንጂ ለኅሊናና ለሀገር ታማኝነት ዘብጥያ ሊያወርድህ ይችላል፡፡

[ኢትዮጵያ የጉድ ሀገር ናት፡፡ ሕገ መንግሥት ተብዬውን ጨምሮ እያንዳንዱ ሕግ ሁለት ‹ቨርዥን›/መልክ አለው፡፡ አንዱ የተጻፈውና ይበልጡን ለኢትግሬዎች የሚሠራው ነው፤ ሌላው ያልተጻፈውና ለወያኔ ትግሬዎች ብቻ የሚሠራው ነው፡፡ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቁ አንደኛው የእንጀራ ልጆችን የሚያሰቃይ ሌላኛው የአብራክ ልጆችን የሚያስተዳደር ሁለት መንግሥታት በአንድ መንግሥት ሥር ይሉሃል እንዲህ ነው፡፡ ትግሬም ሁን ትግሬም አትሁን ወያኔ ትግሬን በሕግ አስተዳድራለሁ ብለህ ከተነሣህ መዳረሻህ ቃሊቲ ነው - እነሱ ሕግና ሥርዓት ጠላታቸው ነው ወንድሜ፡፡ ዘብጥያ የምትወርድበት ሰበብም አሸባሪነት፣ ሙሰኝነት፣ ነፍጠኝነት… ብዙ የክስ ቻርጅ ሞልቶልሃል፡፡ በአንጻራዊ ሁኔታ ደህና ልትኖር የምትችለው ያገኘኸውን እንደከብት እያመነዠክህ እንደነሱው እንደከብቶቹ ለመኖር ከወሰንክ ነው፡፡ ያ ደግሞ ለብዙዎች ስለማይስማማ ብዙው ሕዝብ ከቀን ቀን ወደዕብድነት እየቀየረ ነው፡፡]

ወደ ጥቁር አንበሣ ሆስፒል ተጓዝኩ፤ እዚያ ይልቅ የተሻለ ነገር አየሁ፤ በግቢው በአማርኛ የሚነጋገሩ ሠራተኖችን ተመለከትኩ – ያኔም የኢትዮጵያዊነት ስሜቴ በውስጤ ሲያንሠራራ ተሰማኝ፡፡ ትግርኛችን ከሰማንያ በላይ ከሚገመቱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎቻችን አንዱ እንጂ ሁሎችንም በጋራ ቋንቋነት ሊያግባባ የሚችልን የጋራ መግባቢያ በ‹ፌዴራል› ደረጃ እንዲተካ ሕገ መንግሥቱም አያዝምና በትምክህተኝነት የሚከሰኝ ሰው ቢኖር እኔ የለሁበትም – ራሱ ይኮነንበታል፡፡ በኃላፊነት ደረጃ አሁንም አትጠይቁኝ፡፡ ከትግሬ እጅ የሚወጣ የሀገሪቱ ሥልጣን የለም – የነብርን ጅራት አይዙም ፤ ከያዙም አይለቁም ወዳጄ፡፡ ከንቱነታቸው ግን አሁንምና መቼም ያሳዝናል፡፡ ልበ ውልቆች! ጥንጥዬ ይሉኝታ እንዴት አጡ? በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ከሚተራመስ ከዚያ ሁሉ የወያኔ ትግሬ ሠራተኛ ውስጥ ‹ኧረ ጎበዝ ይሄ አካሄዳችን የኋላ ኋላ መዘዝ ያመጣብናል! ይሄ ጥጋባችን ወደርሀብ እንዳይነዳን ብዙ ሳይመሽ ቆም ብለን እናስብ!› ብሎ በዝግ ስብሰባቸው ላይ የሚያስታውስ አንድ ቆራጥ ወያኔ እንዴት ይጥፋ? እንዴት ነው ሁሉም እንደተራበ ጅብ የሚሰለቅጠውን እየሰለቀጠ፣ የሚግጠውን እየጋጠ ተያይዞ ለማለቅ የወሰነው? ምን ዓይነት አጥፍቶ የመጠፋት ቃል ኪዳን ነው? የሰውስ ይቅር የፈጣሪ ፍርድ እንዴት ተዘነጋ? ይህ ሁሉ ጉድ አልፎ አይቼው መቼስ!

ለናሙናነት እንዲሆኑኝ ወደጥቂት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ሄድኩ፡፡ ድፍን ያልተማረ ትግሬና አጨብጫቤ ኢትግሬ በብቃት ሳይሆን በታማኝ አገልጋይነት ከሚሰገሰጉባቸው የመንግሥት ተቋማት መካከል እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ እንደጣሊያን ሶላቶ እዚህም እዚያም እንደልቡ ሲጮህና ሲያናፋ የምታዩት የወያኔ ትግሬው ባለሥልጣን ነው – ቀላልነታቸው ሲታይህ ውስጥህ በሰዎች ማንነትና ሰዎች ስንባል አንድ ያልተጠበቀ ነገር ስናገኝ ከሚታይብን ብርቅ ድንቃዊ ጠባይ አኳያ የማንነታችን ትርጓሜ ከእንደገና ይደነፈይ(to be redefined) ዘንድ ትመኛለህ፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ጥቂት የማይባሉ ኢትግሬዎች ቢኖሩም በሥልጣናቸው የሚያደርጉት ነገር ከስንት አንድ ነው፤ ሁሉም ለትግሬዎች እጁን ሰጥቷል፡፡ የቀበሌ ምርጫ እንኳን ሲኖር ኢትግሬዎች ራሳቸው የሚጠቁሙት ታሪክ ‹ኢትዮጵያን አደራ› ያላቸውን የወያኔ ትግሬዎችን ነው – እነሱው እንዳቦኩት እነሱው ይጋግሩት› ለማለት ይመስላል፤ ሌላው በሀገሩ ውስጥ የሚኖር መስሎ ከሀገሩ ወጥቷል – ይህን ደግሞ ትግሬዎቹ አይረዱም ወይም መረዳት አይፈልጉም፤ የሌሎቸ ዜጎችን የ‹ሬዚግኔሽን› ወይም ‹ዊዝድራዋል› ስሜት ወያኔዎች የሚወስዱት እንደሽንፈትና እንደመንበርከክ እንደበጎ አጋጣሚም ነው፡፡ ብቻ የትም ቀበሌ ሂዱ ፈላጭ ቆራጩ ባብዛኛው ያው ታሪክ የፈረደበት ሀፍረተቢሱ ወያኔ ትግሬ ነው፡፡

ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲሄድ የምናብ ሳይሆን እውነተኛ ፈረሴን ኮለኮልኩ፡፡ ይዘገንናችኋል፡፡ ለነገሩ ከሀገሪቱ ስድስት በመቶ ከሚሆን ሕዝብ በብቃታቸውና በደም ጥራታቸው ተመርጠው የአንዲትን የ87 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ለብቻቸው ቢቆጣጠሩ እነሱን ካላደከማቸው ምን ችግር አለው? በዚህ ጉዞየ ለነሱ ተሳቀቅሁላቸው፤ ክፉኛ አፈርኩላቸው፡፡ በተወሰነ ዲግሪም ቢሆን በደሜ ውስጥ ያለችውን ትግሬነት አውጥተህ ጣላት የሚለኝ እርኩስ መንፈስ አንሾካሾከብኝ፡፡ ወንድሞቼ – ማርም ሲበዛ ይመራል፡፡ ሰው ባይቆጣ፣ ተቆጥቶም ባይናገር፣ ተናግሮም ባይደመጥ… ፈጣሪ ምን ይለኛል ተብሎ ሀፍረተቢስነትን በትንሽ ይሉኝታ ሸፈን ማድረግ ማንን ገደለ? በዚህ ሆስፒታል የትም ግባ የትም ካለትግሬ ሌላ የሆስፒታል ሠራተኛ ለማግኘት ያለህ የመቶኛ ስሌት ዕድል በዜሮና በአንድ መካከል ነው ቢባል ከእውነቱ አንጻር ሲታይ ግነቱ እጅግ ጥቂት ነው፡፡ በተለይ አንተ ጤናማ ትግሬ ሆነህ ወደዚያ ቦታ ለጉብኝትም ሆነ ለሥራ ወይም ለህክምና ጎራ ብትል በሀፍረት ተሸማቀህ የጎሣ አባሎቼ ናቸው በምትላቸው ሰዎች በሚሠራው ያልተገባ ሥራ በመናደድ ራስህን ልትሰቅል ትደርሳለህ፡፡ የነፍጠኛ ሥርዓት ናፋቂ እንዳትባልና መቀበሪያም እንዳታጣ በመሥጋት ግን ትተሃቸው ትወጣና ወደሚመስሉህ ወገኖችህ ትቀላቀላለህ፡፡ በዚህ ሆስፒታል በዝቅተኛ ሥራ ላይ የሚገኙ ጥቂት ኢትግሬዎችን አይቻለሁ፡፡ በተረፈ ንግግራቸው ብቻ ሳይሆን ሳቃቸው ሁሉ ትግርኛ የሆነ የ‹ፌዴራል ሪፈራል የመከላከያ› ሆስፒታል ነርሶችን፣ የጤና መኮንኖችንና የህክምና ዶክተሮችን ለማየት ወደዚህ ቦታ አምራ – የሆነ ቀጭን ሰበብ ፈልግና፡፡ ግን አትናደድ – ሁሉም ሊሆን የግድ ነውና በሞኝነታቸው ለነሱው ከማዘን በስተቀር ቂምና በቀልም አትያዝባቸው፡፡ አትፍረድባቸው – እየፈሩ ነው እንዲህ ያለ የነሱን ኅሊና ሳይቀር ሊረብሽ የሚገባው መጥፎ ሥራ ውስጥ (ወጥመድም ብለው እችላለሁ) የገቡት፡፡ እልሁንና ለሥልት የሚጠቀሙበትን የዘር ጥላቻ ለጊዜው ወደጎን ትተን ለመሆኑ አንድ ወያኔ ትግሬ ከኔ የበለጠ ሆድ አለው? ለዚህች ከአንድ እንጀራ ለማታልፍ ለቆታስ ይህን ያህል ርቀት ተጉዘው ለታሪክና ለሕዝብ ትዝብት መዳረግ ነበረባቸው? አልፎ አይተነው!

ቦሌ ካርጎ ማራገፊያም ሄድኩ፡፡ ያው ነው፡፡ ትግሬ ብቻ! ወይ ዕዳቸው፡፡ በየትም ሊገጥምህ የሚችል ነገር ደግሞ ላስታውስህ፡፡ በጦርነትም ይሁን በግል ጠብ፣ በጥይትም ሁን በጎራዴ እጁ የተቆረጠ ወይም ሌላ አካሉ የጎደለ የትግሬ ሠራተኛ በብዙ ቦታ ማግኘት የተለመደ ነው – አሃ! እሱ እኮ ‹የነሱው› ነው – ደሙን ለሕወሓት ያፈሰሰ ጅግና ተጋዳላይ፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕድል ለኢትግሬ እንደሚሰጠውና እንደማይሰጠው ለማወቅ ‹ያደረግሁት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም›፡፡ በዚህም ቦታ አዛዥ ናዛዡ ትግሬ ነው፡፡ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂድ፣ ቤተ መንግሥት ግባ፣ ፓርላማ ሂድ፣ በማንኛወም የሚኒስቴርና የኮሚሽን መሥሪያ ቤቶች ግባ፣ ኢቲቪና ዋልታ ሂድ፣ ኢዜአም ሂድ፣ ጅምሩክ ሂድ፣ ባቡር ጣቢያ ግባ፣ አየር መንገድ ግባ፣ ሲቪል አቪየሽን ሂድ፣ ቴሌ ግባ፣ ኤልፓ ሂድ፣ ቤተ ክርስቲያን ግባ ፣ መስጊድ ሂድ፣ የትም ግባ አብዛኛውን የሀገሪቱን ሥልጣንና የጥቅም ቦታ የያዙት እነሰውና እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ አዲ አበባ ላይ በንግዱም በፖለቲካውም ትግሬዎች ከመብዛታቸው የተነሣ መቀሌ ላይ እንዳለህ ቢሰማህ ወቅቱ የፈቀደው ፖለቲካዊ ፋሽን ውና ብዙ አትደነቅበት፡፡ መዝናኛማ በአብዛኛው የነሱ ርስተ ጉልት ነው፡፡ ሌላው ገንዘቡን ከየትአባቱ አምጥቶ ይዘባነናል? አይ ያለው ማማሩ! (የሌለው ደግሞ መደበሩ)፡፡ ወዩ አንቺን በጎጥና በሸጥ እየከፋፈለ በነገርና በቡጢ ሲያደባድብሽ፣ ለስደትና ለእንክርት ሲዳርግሽ፣ የጋራ ሀገርሽን ሲመዘምዝልሽ… እያንዳንድሽ በ‹ከነገሩ ጦም እደሩ› የማምለጫ መንገድ ራስሽን ለማዳን አላስካና ሶሎሞን ደሤቶች ድረስ እግር አውጪኝ ትያለሽ፡፡ እዚህ ያለው ደግሞ ሰማይ ምድሩ ተደፍቶበት እንደክርስቶስ ኤሎሄ ይላል፡፡ ምን ይበጃል? መጠበቅ ነው፡፡

አንድ ቀበሌ ለንግድ ከገነባቸው አሥራ ሦስት ክፍሎች ውስጥ ለላንቲካ አንዱ ብቻ ለኢትግሬ ሲከራይ አሥራ ሁለቱ ለትግሬ መከራየታቸውን የማረዳህ ይህ ሸፋፋ አካሄድ ነገ ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ ዳፋ በዓይነ ቁራኛ አጮልቄ እየተመለከትኩ በሚሰማኝ ከፍተኛ ሀዘን ተውጬ ነው – ያን ሰውዬ ከሠልፉ ለማስወጣትም ጥረት እየተደረገ እንደነበር ራሱ አጫውቶኛል፡፡ ወያኔ ትግሬ ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ ነው፤ ያልተሞዳሞደ ኢትግሬ ዜጋ ግን በግብር ቁልል፣ በኪራይ ቁልል፣ በ‹እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው› ዘዴ ከንብረትም ከሀብትም ከቤትም ከትዳርም እንዳይሆን እየተደረገ ሜዳ እንዲወድቅ ሁኔታዎች ሁሉ ይመቻቻሉ፡፡ አንድ ወያኔ ትግሬ ያለውን መብት አንድ መቶኛ ያህል እንኳን አንተ የለህም፡፡ ኢ. ቅጣው ሰባተኛ ዜጋ እንደሆንን የገለጸውን አሁን በሕይወት ኖሮ የመከለስ ዕድል ቢገጥመው ወደ ዐርባና ሃምሳ የዜግነት ደረጃ ያወርደው ነበር፡፡ እየተሠራ ያለው ግፍ ሰማይና ምድር አይችሉትም፡፡ ክፍያውን ግን ማን ሊችለው ይሆን?

አንድ ነገር ትዝ አለኝ፤ የዛሬ 23 ዓመታት ገደማ በፊት ከሬዲዮ የሰማሁት ነው፡፡ በዚያ የሬዲዮ መጣጥፍ ላይ የተገለጸው ትንቢታዊ ቃል አሁን ድረስ ከጆሮየ አልጠፋም፡፡ እንዲህ ነበር ሲባል የሰማሁት – እጠቅሳለሁ -‹ወያኔ የሚቃዥባትን የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ከተቆጣጠረ አማራን እንኳንስ ለኃላፊነት ቦታ ለዘበኝነትም አያበቃውም› የጥቅሱ መጨረሻ፡፡ ትንቢት ይቀድሞ ለነገር ይላሉ ካህናት፡፡ ትክክለኛ ግን መጥፎ ትንቢት፡፡

ለኢትግሬዎች ታዲያ ምን ቀራቸው ብሎ መጠየቅ ከብልህ አንባቢ ይጠበቃል፡፡ ለቀሪው ሕዝብ የተረፈው በስደት ዓለምን መዞርና ዕድል ካልቀናም በመንከራተት ሕይወትን በጨለማ አዘቅት ውስጥ ሆኖ መግፋት፤ በሀገር ውስጥ ለእሥርና እንግልት መዳረግ፤ በአማራነት ሰበብ ከምድረ ገጽ መጥፋት፣ ወያኔ ትግሬ በሀገርና ከሀገር ውጪ እየተንደላቀቀና እየተንፈላሰሰ ሲኖር በበይ ተመልካችነት መታዘብ፣ ከሲዖል ለመውጣት በሚደረግ ጥረት በየበረሃው የአውሬና የሰውነት ክፍልን በቁም እየበለቱ ለሚሸጡ ጨካኞች ሲሳይ ሆኖ መቅረት፣ (ፀረ-አማራ ፍሊት ከየት እንደሚገዙ አላውቅም ያን ወዳማራው ክልል በብዛት ሲልኩ ወደትግራይ ደግሞ ኢንኪውቤተር የሚልኩ ይመስለኛል – ሊያውም ማርገዝ፣ መውለድ፣ ማሳደግና ማስተማር ሳያስፈልግ ሰውን ያህል ፍጡር ትልቅ አድርጎ ለአቅመ አገዛዝ አድርሶ የሚፈለፍል ኢንኪውቤተር፤ አለበለዚያ ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሞላ ትግሬ ወያኔ በነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከየት አፈለቁት ሊባል ነው? አማራን መፍጀት – በምትኩ ትግሬን ማብዛት! ትልቅ የሚሌኒየሙ የወያኔ ዕቅድ፡፡ ወዮ ለመጨረሻው የ‹ቂያማ ቀን›!)

ምን ቀረኝ? ሁሉንም ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ ስለዚህ ተመራርቀን እንለያይ፡፡ ወያኔዎች ሆይ መልካም የደስታና የሥልጣን ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ ለሌላውም ልብ ይስጠው፡፡ ፈጣሪ ለሁሉም ጊዜና ዕድልን አመቻችቶ ይሰጣል፡፡ አንዱ ከአንዱ እየተማረ ይህችን አጭር ግን አሰልቺ የምድር ሕይወት ማጣፈጥ ሲቻል እያመረሩ መጓዝ ለምንም ለማንም አይጠቅምምና ሁላችንም እያሳለፍነው ካለነው የመከራና የስቃይ አዙሪት ተምረን መልካም ሰዎች እንድሆን ፈጣሪ ይርዳን፡፡

እግዚአብሄር ሆይ ና፤ የቅድስቲቱን ምድርም ባርክ፤ ሕዝብህንም ከብዔልዘቡሎች የእሳት ጅራፍ አድን፡፡ አሜን፡፡

ምንድነው ጉዱ?

(ሰበር ዜና፡- ይህን ወረቀት ጽፌ ከጨረስኩ በኋላ የሰማሁት ነገር ነው፡፡ የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ነጩ ብር 2200 ሲገባ ጥቁሩ 2000ን ዘለቀ አሉኝ – ከገዛ ሰው ነው የሰማሁት፡፡ ወያኔ ዕድገታችንን ማለቴ ሞታችንን በየአቅጣጫው እያፋጠነልን ነው፡፡)


የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪዎች 60 የክስ መዝገቦች መቋረጣቸውን አስታወቀ

$
0
0

- የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት     ሁለት ተጠርጣሪዎች በምርመራ ወቅት መደብደባቸውን ተናገሩ   ተያዘ የተባለው ሰነድ ሁሉ በሀብት ምዝገባ ያስመዘገብኩት ነው›› አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ቡድን….፣ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዲቋረጡ ከተደረጉት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 ያህሉን መሰብሰቡን ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

መርማሪ ቡድኑ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ እንዳስረዳው፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባለፉት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ላይ የሠራውን የምርመራ ሥራ እንዳብራራው፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ሰብስቧል፡፡ ከተለያዩ ባንኮች በተወሰኑ ተጠርጣሪዎች ላይ ከአራጣ ብድር ጋር የተያያዙ ማስረጃዎችን፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ (መኒ ላውንድሪንግ) መጠቀምን የሚያሳዩ ሰነዶችን መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ጨምሮ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በአራጣ ብድር የተከሰሱ ሰዎችን ክስ ያቋረጡባቸውን የክርክር መዝገቦችን መሰብሰቡንና በኮንትሮባንዲስቶች ላይ በፍርድ ቤት ተጀምረው ከነበሩትና በሕገወጥ ጥቅም ከተቋረጡት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 የሚሆኑት መሰብሰቡንም ገልጿል፡፡

በአንድ የንግድ ድርጅት ላይ ተወስኖ የነበረን ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ግብር ወደ ሦስት ሚሊዮን ብር የተቀነሰበትን ሰነድ፣ እንዲሁም 87 ሚሊዮን ብር ግብር እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረን ድርጅት፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ ስምንት ሚሊዮን ብር ዝቅ የተደረገበትን ሰነድም መሰብሰቡን ቡድኑ ለችሎቱ ተናግሯል፡፡

ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲት ሊያደርጋቸው የሚገቡ ስምንት ኩባንያዎች መኖራቸውን ማረጋገጡን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ፣ ኦዲት የሚደረጉትን ለይቶ መጨረሱንና ለመሥሪያ ቤቱ ደብዳቤ መጻፉን አሳውቋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ የምስክሮችን ቃል በከፊል መቀበሉንና የንብረት ጥናትም በከፊል መሥራቱን ገልጾ፣ የቀሩትንም የምርመራ ሥራዎች ጠቁሟል፡፡

ያላግባብ ክሳቸው የተቋረጡ 40 የክስ መዝገቦችን መሰብሰብ፣ በሕገወጥ መንገድ ግብር እንዲቀነስ የተደረገባቸውን ሰነዶች፣ ሕጋዊ በማስመሰል ሕገወጥ ገንዘብን ለመጠቀም የተዘጋጁ ሰነዶችን መሰብሰብ፣ የስምንት ኩባንያዎችን ግብር ማጣራት፣ የኦዲተሮችን ቃልና የቀሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ላለፉት 14 ቀናት በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሠራቸውንና የሚቀሩትን ሥራዎች ለችሎቱ ካሳወቀ በኋላ፣ በጠየቀው ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜን በሚመለከት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በችሎቱ የተፈቀደላቸው፣ በኢትዮጵያ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ኃላፊ የምርመራ መዝገብ ሥር ያሉ 12 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡

መርማሪ ቡድኑ በጥቅል ከመግለጽ ባለፈ እያንዳንዱ ተጠርጣሪ ምን እንደሠራ፣ ተጠርጣሪው ከሠራው ወይም ካጠፋው ነገር አንድም እንኳን እንዳልተነገረው፣ ምን ሠርቶ ምን እንደቀረው እስካሁን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለፍርድ ቤቱ ያስረዱት፣ የአቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ጠበቃ ናቸው፡፡ ደንበኛቸው ተጠርጥረው የታሰሩት ክስ በማቋረጥና ባልተፈቀደ የፍራንኮቫሉታ ፈቃድ ሲሚንቶ ማስገባት እንደነበር ያስታወሱት ጠበቃው፣ መርማሪ ቡድኑ 14 ቀናት የምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ ያልተናገራቸውና ለደንበኛቸው ያልተገለጹላቸው ሰነዶችን ማሸሽ፣ ንብረት ከተገቢው በላይ ማፍራትና ከባለሥልጣናት ጋር መመሳጠር፣ ሕገወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም፣ አራጣ ማበደርና ግብር ያላግባብ መቀነስ የሚሉት የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስና ያላግባብ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት ስለተጠረጠሩበት ወንጀል በተያዙበት ወቅት ሊነገራቸው ይገባ እንደነበር የገለጹት ጠበቃው፣ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መርማሪ ቡድኑ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ ያስመዘገባቸው፣ ‹‹የሲሚንቶው ጉዳይ ምን ሆነ? ሰነድ ጠፋ ወይስ ምን ሆነ? ሊገለጽልን ይገባል፤›› ካሉ በኋላ፣ በወቅቱ ያልተገለጹና እንደ አዲስ ክስ የቀረቡት ጉዳዮች ተገቢ ጥያቄዎች ባለመሆናቸው የ14 ቀናት ተጨማሪው የጊዜ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ገብረ እግዚአብሔር እንዲናገሩ ችሎቱን ጠይቀው ሲፈቀድላቸው እንደተናገሩት፣ በምን ተጠርጥረው እንደታሰሩ አያውቁም፡፡ ለምርመራ ሲቀርቡ በተደጋጋሚ የሚቀርብላቸው ጥያቄ ስለንብረታቸው ነው፡፡ የልብ ሕመምተኛ መሆናቸውንና ንብረታቸውም የተመዘገበ መሆኑን በመግለጽ፣ ማወቅ የሚፈልገው አካል በፈለገ ጊዜ ሊያውቅ እንደሚችል ገልጸው፣ እሳቸው ግን በአንድ በተዘጋ ክፍል ውስጥ መሆናቸው አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

እምባና ሳግ እየተናነቃቸው ዝቅ ባለ ድምፅ መናገር የቀጠሉት አቶ ነጋ፣ በታሰሩበት ክፍል ውስጥ ሁለት ጊዜ ራሳቸውን ስተው ወድቀው እንደነበርና መደብደባቸውንም ገልጸዋል፡፡

ነጋዴ በመሆናቸው ሀብት ማፍራት እንደሚችሉ የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ ምርጥ ታክስ ከፋይ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ መሆናቸውን፣ ለአገራቸው 33 ሚሊዮን ብር መድበው በ23 ሚሊዮን ብር ያስገነቧቸውን ፖሊ ቴክኒክ ትምህርት ቤቶችን ለሕዝብና ለመንግሥት ማስረከባቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

‹‹አገሬን ያወቅኋት አሁን ነው፤ ዜጋ ነኝ ለማለት አይቻልም፤›› ያሉት አቶ ነጋ፣ ሲደበደቡ ራሳቸውን ስተው እንደሚወድቁ አስታውቀው፣ ኢሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው ጠቁመዋል፡፡ የደም ግፊትና የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውንና የልብ ቱቦ ተገጥሞላቸው ያሉ ታማሚ በመሆናቸው ክትትል ካልተደረገላቸው ለሕይወታቸው አስጊ መሆኑን ጠበቃቸው አክለዋል፡፡

የመርማሪ ቡድኑን በጥቅል የመግለጽ ሁኔታ እንደ አቶ ነጋ እሳቸውም እንደሚቃወሙት የተናገሩት የባለሥልጣኑ ሠራተኛ አቶ ጥሩነህ በርታ ሲሆኑ፣ መርማሪዎች ወደ ምርመራ ክፍል በመውሰድ የሚጠይቋቸው ከሥራቸው ጋር የማይገናኝ፣ መረጃ እንደሚያውቁ ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደሚቀርብላቸውና በማያውቁት ጉዳይ ላይ መረጃ ሰብስበው ክስ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እሳቸው ተጠርጥረዋል በተባሉበት ክስ የማቋረጥ ወንጀል መጠየቅ ያለባቸው እሳቸው ሳይሆኑ ከእሳቸው በላይ ያሉ ኃላፊዎች እንደሆኑ የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ እነሱ ሳይጠረጠሩ እሳቸውን አስሮ ማሰቃየት ኢሰብዓዊ ድርጊት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሱሪያቸውን ከፍ በማድረግ እግራቸውን ለችሎቱ እያሳዩ መደብደባቸውን የገለጹት ተጠርጣሪው፣ ውኃ እየተደፋባቸው እንደተገረፉ ለበላይ ኃላፊ ቢያመለክቱም፣ መርማሪዎቹ በድጋሚ ሲያገኟቸው ‹‹እንኳን ለኃላፊ ለማንም ብትናገር አንተውህም›› እንዳሏቸው ሲገልጹ መርማሪ ቡድኑ አቤቱታቸውን ተቃውሟል፡፡ የተቃወመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ፍር ቤቱ ሲፈቅድለት፣ ተጠርጠሪው የሚያነሱት ጉዳይ አስተዳደራዊ መሆኑን በመጠቆም፣ ፍርድ ቤት ሊቀርብ እንደማይገባ አመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ ‹‹አስተያየታቸው ሊደመጥ ይገባል፡፡ ኮሚሽኑ ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ አቤቱታዎችን እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ቢታዘዝም ሊታረም አልቻለም፤›› በማለት ተጠርጣሪው አቤቱታቸውን እንዲቀጥሉ አዟል፡፡

ተጠርጣሪው ቃላቸውን እስካሁን የተቀበላቸው እንደሌለ በመግለጽ፣ ቢሮአቸውንም ሆነ ቤታቸውን ቡድኑ በርብሮ ምንም አለማግኘቱን፣ እያንገላታቸው ያለው አዲስ ማስረጃ ለማሰባሰብ እንጂ በእሳቸው ላይ ምንም ዓይነት ጭብጥ እንደሌለው ፍርድ ቤቱ እንዲገነዘብላቸው አመልክተዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ኦዲተር መሆናቸውንና ደመወዛቸው ከአሥር ሺሕ ብር በላይ መሆኑን፣ የተጣራ 5,600 ብር አካባቢ እንደሚያገኙና ሥራ የሌላቸውን ባለቤታቸውን ጨምሮ፣ ልጆቻቸውንና የእህታቸውን ልጅ ጭምር የሚያስተዳድሩት እሳቸው መሆኑን የተናገሩት አቶ በላቸው በየነ ሲሆኑ፣ መርማሪ ቡድኑ የልጃቸው ላፕቶፕ ጨምሮ በመሥሪያ ቤታቸውና በቤታቸው ያለውን ሁሉንም ሰነድ ስለወሰደ በዋስ እንዲለቃቸው ጠይቀዋል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በጥቅሉ ሳይሆን እያንዳንዱ ተጠርጣሪ የተጠረጠረበትን ወንጀል ለይቶ ማቅረብ እንደሚገባው የገለጹት ተጠርጣሪው፣ መንግሥት በመደባቸው በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ለ27 ዓመታት መሥራታቸውን፣ አብዛኛው ሥራዎቻቸውን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጭምር ያውቁት እንደነበር፣ ቤተሰብንም ሆነ ሌላ አካል ወይም ማንንም ለመጥቀም በሚል ሕገወጥ ሥራ ሠርተው እንደማያውቁ አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ ለዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ሥልጠና ለመስጠት እሳቸውና ሌላ አንድ ሰው ተመርጠው እንደነበር የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ መርማሪ ቡድኑ ኩባንያዎችን ኦዲት እንዲያደርጉለት ለዋና ኦዲተሩ ደብዳቤ መጻፉን አስታውሰው፣ ‹‹ኦዲት የሚያደርጉት ሠልጥነው ነው ወይስ?›› ሲሉ ፍርድ ቤቱ ‹‹ይኼ በማስረጃ ጊዜ የሚታይ ነው፤›› በማለት አስቁሟቸዋል፡፡

አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ ሁለት ሕፃናት ልጆቻቸው እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ፣ የሚረዳቸው ወይም የሚቀልባቸው ሰው ባለመኖሩ ሥጋት ላይ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፣ ባለቤታቸው ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይና እህታቸው ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋይ፣ እንዲሁም በውጭ አገር ለሰባት ዓመታት ቆይቶ ከመጣ አራት ወራት ብቻ የሆነው የወ/ሮ ንግስቲ ልጅ አቶ ሀብቶም ገብረመድኅን በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

እሳቸው የተጠረጠሩበትን የወንጀል ሰነድ አሽሽተዋል በሚል ቤተሰቦቻቸው መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ ዋህድ፣ ሸሽቷል የተባለው ሰነድ ኮሚሽኑ ባወጣው የሀብት ማስመዝገብ አዋጅ የተመዘገበና ኮሚሽኑ የሚያውቀው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የባለቤታቸው እህት የ60 ዓመታት አዛውንት መሆናቸውን፣ ከአቅም በላይ በሆነ ውፍረት ክብደታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ዕርዳታ እንደሚፈልጉና የደም ብዛትና የስኳር ሕመምተኛም ስለሆኑ ከተቻለ በነፃ ካልሆነም በዋስ አንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ የቀረው መደበኛ ሥራው መሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ ዋህድ፣ ከእሳቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በዋስ እንዲለቀቁ ወይም የምርመራ ጊዜው አንዲያጥር አመልክተዋል፡፡

የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ ምሕረተ አብ አብርሃ ባቀረቡት አቤቱታ እንደገለጹት፣ የሚተዳደሩት በንግድ ነው፡፡ ከ1993 ዓ.ም. እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ በታሰሩበት ወቅት ንብረታቸውን ያስተዳድር የነበረው ኮሜት የሚባል ድርጅት ነበር፡፡ ንብረታቸውን በሚመለከት ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር አለመግባባት ላይ ደርሰው፣ መብታቸውን ያስከበሩት በፍርድ ቤት ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ‹‹ተጠርጥረሃል›› ከተባሉበት ክስ ማቋረጥ፣ ኮንትሮባንድ፣ አራጣና ሌሎች ጉዳዮች ጋር እንደማይገናኙ ተናግረዋል፡፡ ከነበሯቸው ከ15 በላይ ተሽከርካሪዎች ልጆቻቸውን እያስተዳደሩ ያሉት በሁለት ተሽከርካሪዎች በሚያገኙት ገቢ ብቻ መሆኑን የገለጹት አቶ ምህረተ አብ፣ ባለሥልጣኑ ከፍተኛ ግብር ጭኖባቸው ከ1999 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ በፍርድ ቤት ባደረጉት ክርክር መብታቸውን ማስከበራቸውን ገልጸው፣ አሁን የተጠረጠሩበትን ምክንያት ስለማያውቁት ዋስትና እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በአጠቃላይ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበው የምርመራ ውጤት ወንጀሉ ጥቅል መሆኑን፣ በተያዙበት ወቅት ያልተነገራቸው የወንጀል ክስተት እየቀረበባቸው መሆኑን፣ ማስረጃ ተሰብስቦ ቢያልቅም መብታቸው አለመከበሩን፣ ጥርጣሬዎቹ ከሰነድ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ታስረው ሊቆዩ እንደማይገባና ዋስትና ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደማያስፈልግ የሚሉትን ሐሳቦች ሁሉም ያነሱ ሲሆን፣ በተናጠል ደግሞ የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን፣ የጤና ችግር እንዳለባቸው፣ የመብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን፣ ከተያዙ ጀምሮ ቃላቸውን አለመስጠታቸውን ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ በምርመራ መዝገቡ የቀረቡት 12 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ፣ የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በተናጠል ሳይሆን በቡድንና ውስብስብ በሆነ መንገድ መሆኑን ገልጿል፡፡ ጉዳዩ አገራዊ በመሆኑ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑንም አስገንዝቧል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች መሆናቸውን በመጠቆም፣ ሥልጣንንና ገንዘብን ተገን በማድረግ ውስብስብ በሆነና በጥቅም በመመሳጠር በአገር ገቢ ላይና በሌሎች የሕዝብ ጥቅሞች ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን አስረድቷል፡፡ ክስ እንዲቋረጥና ከውጭ የሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ቀረጥ እንዳይከፈልባቸው ሲደረግ፣ ለጠቋሚዎች የሚከፈል አበል ለራስ ጥቅም ሲደረግ፣ አንድ ተጠርጣሪ ብቻ የሚሠራው ሳይሆን በቡድንና በመመሳጠር የሚሠራ መሆኑን መርማሪ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ድርጊቱ በአጠቃላይ በትብብር የተሠራ መሆኑንና ለቀሪ የምርመራ ጊዜ ተጨማሪ 14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት በድጋሚ አመልክቷል፡፡

ቃል አልሰጠንም ያሉት ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን መስጠታቸውን በተለያየ መንገድ መግለጻቸውን፣ ሰብዓዊ የመብት ረገጣ ደርሶብናል ያሉት ተጠርጣሪዎችም በማስረጃ የቀረበ ባለመሆኑ ሊታመን እንደማይችል መርማሪ ቡድኑ ገልጾ፣ ዋስትና ቢፈቀድ የሰነድና የምስክሮች ቃል ሊያጠፉበት እንደሚችሉ በመናገር ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

መርማሪ ቡድኑ በተሰጠው ጊዜ በማን ላይ ምን እንደተሠራ፣ በማን ላይ ምን እንደቀረው በግልጽ አለማስቀመጡን፣ ይኼም ለክርክር በር መክፈቱን፣ በርካታ ምስክሮች የቀሩት በማን ላይ እንደሆነና ሰነድም ሆነ ሌላ መረጃ ለማጣራት የተፈለገው በማን ላይ እንደሆነ ግልጽ አለመደረጉ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ በቀጣይ ቀጠሮ በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ላይ በተናጠል የተሠራው ተዘርዝሮ እንዲቀርብ አዟል፡፡

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ከድርጊቱ ውስብስብነት አንፃር የተጠርጣሪዎች ዋስትና ጥያቄን አለመቀበሉን፣ የመርማሪ ቡድኑን 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜያት መፍቀዱን አስታውቆ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ኮሚሽኑ አጣርቶ እንዲያቀርብ በማዘዝ ለሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዕለቱ መቅረብ የነበረበት የእነ አቶ መላኩ ፈንታ የምርመራ መዝገብና የእነ አቶ መሐመድ ኢሳ የምርመራ መዝገብ በመሆኑ፣ መዝገቡ የቀረበ ቢሆንም ቀኑ በመምሸቱ ለግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በይደር ተቀጥሯል፡፡ በእነ መሐመድ ኢሳ የምርመራ መዝገብ ፍሬሕይወት ጌታቸው የተባሉ ተጠርጣሪ በመካተታቸው ጠቅላላ የተጠርጣሪዎች ቁጥር 55 ደርሷል፡፡

ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሹማምንት፣ ታዋቂ ነጋዴዎችና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ችሎት ለመታደም በፍርድ ቤት የተገኙ ታዳሚዎች ከችሎቱ አቅም በላይ ስለነበሩ በርካቶች ችሎቱን መከታተል አልቻሉም፡፡

Source: Ethiopian Reporter

Federal_court

 


ሰበር ዜና: በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

$
0
0

Limited demonstration erupts outside Ethiopian embassy in Cairo as activists protest perceived infringement on Egypt’s traditional share of Nile water….

FFF

Protest outside Ethiopia’s Cairo embassy about Blue Nile dam move

Dozens of Egyptian protesters gathered outside the Ethiopian embassy in Cairo on Friday to protest Addis Ababa’s decision earlier this week to temporarily divert the course of the Blue Nile as part of a project to build a series of dams on the river.

Protesters held banners aloft reading, “We reject attempts to take our Nile Water.” Others chanted: “We are the source of the Nile Basin.”

“After Ethiopia’s surprising decision, bilateral relations have now been put to the test,” according to a statement by the ‘Copts without Borders’ group, one of the protests’ main organisers.

The statement added: “Any agreement between President Mohamed Morsi’s government and its Ethiopian counterpart will not be recognised, since Morsi has lost all legitimacy before the Egyptian people.”

The statement went on to call on Egyptians to take part in a planned anti-Mors rally on 30 June to call for snap presidential elections.

Other participants at Friday’s protest included members of the ‘Lawyers Union for the Nile Basin’ and the ‘Egyptians against Injustice’ movement.

Within the context of a plan to build a series of new dams for electricity production, Ethiopia on Tuesday began diverting the course of the Blue Nile, one of the Nile River’s two main tributaries. Most Nile water that reaches Egypt and Sudan originates from the Blue Nile.

Ethiopia’s ‘Renaissance Dam’ project – one of four planned hydro-electric power projects – has been a source of concern for the Egyptian government, amid ongoing sensitivities regarding the project’s possible effects on Egypt’s traditional share of Nile water.

According to the state-run National Planning Institute, Egypt will need an additional 21 billion cubic metres of water per year by 2050 – on top of its current quota of 55 billion metres – to meet the needs of a projected population of some 150 million.

Source:www. Sodere.com


ሃምሳም ሰውም ይውጣ ሃምሳ ሺህ ግን አንድ ፀባይ እሱም “ፍፁም ሰላማዊ!”abetokichaw

$
0
0

935293_421802944584325_731290226_n

አቤት የርዕሴ ርዝመት… ደግሞ በዛ ላይ ቀጥሎ የምናገረውን ማሳበቁ! “ቢወዳት ነው ቢጠላት ባሏ በሻሽ አንቆ ገደላት” አይነት ሆነኮ…

ለማንኛውም ቀጥሎ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ጥቂት ልናወጋ ነው፡፡ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ እና በጥቅሉ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስለ ሰላማዊ ትግል ስናወራ ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውን በማውራት ብንጀምር የወጋችንን ደረጃ ከፍ ደርገዋል ሞገስም ይሰጠዋል እና  እንቀጥል…

መንግስታችን በዛን ሰሞን በገዛ ቴሌቪዥኑ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ተቃውሞ በሌላው ህብረተሰብ ላይ የተቃጣ ትንኮሳ አስመስሎ ኮሳሳ የሆነ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲሰራ አይተን ታዝበን ታዝበን ታዝበን አልወጣልንም፡፡

በተደጋጋሚ እንዳየነው ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከአመት በላይ በመስጂዳቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ያሳዩን ጨዋነት ገዢዎቻችንን ያሳፈረ ነበር የሚለው ቃል አይገልፀውምና “አፈር ያስበላቸው ነበር” ማለት ይሻላል፡፡ (አረ እንደውም አፈር ደቼ እንበል እንጂ… ሃሃ… “ደቼ” የምትለውን ቃል ትርጓሜ ከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላትን ላይ ባገላብጥም፤ ደቸር፣ ደቻሪ ደቻራ፣ ደችሮ ብሎ ይዘላታል እንጂ ትርጉሟን አላስኮርጅ አለኝ…) የምር ግን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጨዋነት የተላበሰ ተቃውሞ ገዢውን እና አሳሪውን መንግስታችንን አፈር ደቼ ያበላ ነበር ከሚለው ውጪ ገላጭ ቃል ከየት ይገኝለታል?

የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሌላው ኢትዮጵያዊም ጥያቄም ነው፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፤ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይግባ” ይላሉ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ፤ “አዎን እንኳንስ በሀይማኖት እና በታክሲ ወረፋም ጣልቃ መግባት ነውር ነው” ይላል፡፡ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፤ “መንግስት የምንጠይቀውን ጥያቄ በእስር እና በጠብ መንጃ አይመልስልን” ይላሉ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ “አዎ ሰው ማሰርን በሬ እንደማሰር አታቅልሉት ሰው ለመጥመድም በሬ እንደመጥመድ አትቸኩሉ” ይላል፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች “ድምፃችን ይሰማ” ይላሉ፡፡ ሌላው ኢትዮጵያዊም፤ “ጮክ ብሎ ዜና እናሰማለን ማለት ብቻ ዋጋ የለውም የእኛንም ድምፅ መስማት ልመዱ” ሲል በየአጋጣሚው ሁሉ ይጮሃል፡፡

እስከ አሁን ኢትዮጵውን ሙስሊሞች በአንድ ላይ ሆነው በየሳምንቱ በየ መስጂዳቸው ድምፃችን ይሰማ ሲሉ የቆዩ ሲሆን፤ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ደግሞ በጋራ ሆኖ ኡኡ የሚልብት አማካይ ቦታ ተቸግሮ “የት ሄጄ ልፈንዳ” እያለ ይገኛል፡፡

አሁን እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ፤ ሁሉን በጋራ የሚያሰባስብ አንድ መድረክ ተፈጥሯል፡፡ እሁድ ግንቦት 25 ዋቄፈታውም፣ ኦርቶዶክሱም፣ ሙስሊሙም፣ ፕሮቴስታንቱም፣ ካቶሊኩም በአንድ የሚሰባሰቡበት መድረክ ተፈጥሯል፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምፅ ተባብረው “ድምፃችን ይሰማ” ይላሉ፡፡ መንግስት ሊሰማም ላይሰማም ይችላል፡፡ የጋራ የሆነው የሰማዩ አምላክ ግን እንደሚሰማ ግን በጣም ርግጠኛ ነን!

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤

እስከ አሁን በደረሰኝ ወሬ ከቢሸፍቱ (ደዘዎች) እና ከአዳማ (ናዝሬት) በርካቶች በሰልፉ ለመታደም ተነሳሽነት አሳይተዋል፡፡ እንደ ቅንጅት ጊዜው በክልላችሁ ተሰለፉ ካልተባሉ በስተቀር፤

በመጨረሻም

ፖሊስ እና ወታደሩ የተሰላፊው ወገን መሆኑን መርሳት ራስን ከመርሳት ጋር እኩል ነው፡፡ ተሰላፊዎች ሃምሳም ሁኑ ሃምሳ ሺህ አንድ ፀባይ ግን ያስፈልጋል እርሱም ፍፁም ሰላማዊ መሆን! ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚሊዮን ሆነው አቤት ሲሉ የአቤቱታው ፀባይ አንድ ነበር ፍፁም ሰላማዊ! (ይቺን ነው መኮረጅ!)

በመጨረሻው መጨረሻ

ለሰላማዊ ተቃዋሚዎች፤ ሰላሙን ያብዛ! ብለን እንመርቃለን!

አሜን!

abetokichaw


የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን (SMNE) በኅብረት ስራ ጀመሩ! ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ

$
0
0

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ… አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።

(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።

ከወር በፊት በተካሄደ የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዲያደርጉላቸው በተጋበዙት መሰረት አቶ ኦባንግ ህግን እየተንተራሰ ዜጎችን በቁም እስርና በወህኒ ቤት እያሰቃየ ስላለው የኢህአዴግ አገዛዝ በስፋት ባስረዱበት ወቅት ማህበሩ እሳቸው ከሚመሩት ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃዱን አሳይቶ እንደ ነበር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍና ወንጀል፣ ለአፈና ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎችን በማውጣት ዜጎችን ለወህኒ ቤትና ለቁም እስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ገለልተኛ አካሎች ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ የሚጠቀምባቸው የፖለቲካው መሳሪያዎቹ ስለመሆናቸው፣ በመዘርዘርና ማስረጃ በማጣቀስ አቶ ኦባንግ ለጉባኤው መናገራቸውን አመልክተዋል።

ቀደም ሲል ጀምሮ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚዎች የሚታወቁትም ሆነ ሚዲያው የዘነጋቸው ዜጎች ጉዳያቸው ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ በያቅጣጫው እየተደረገ ካለው የተለያየ ጥረት በተጨማሪ ሲመክርበት የነበረው ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉት አካላት በራሳቸው ሰዎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ታላቅ ተግባር ነው። ድርጅታችን እንደ ስኬት ይቆጥረዋል። ዓርብ በዝርዝራችን ካገኘናቸው የታዋቂ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪ ጠበቆች ጋር የስካይፕ ስብሰባ ይካሄዳል። በቀጣይ አገር ቤት በመሄድ ባመቻቸው መንገድ ስራቸውን ያከናውናሉ” ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩት ወገኖች፣ ወዘተ ጠበቆች ጋር በስካይፕ ንግግር እንደሚደረግ አቶ ኦባንግ አስታውቀዋል። እስከዛሬ ጆሮ ያልተሰጣቸው ወገኖች ጉዳይ አደባባይ ከማውጣት በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ባቋቋማቸው ግብረኃይሎች አማካይነት ወደ ህግ የሚሄዱ፣ ሌሎች አብረው መስራት የሚፈልጉ አካላት የሚያቀርቧቸውን አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክስ መስርቶ ለመሟገት ማህበሩ ዝግጁ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ለጋራ ንቅናቄው ማቅረብ ይችላሉ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ማህበሩ መንግስትን የሚያማክሩ፣ የሚመክሩ፣ ፖሊሲ በማርቀቅ ስራ ላይ የተሰማሩ ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ለዓለም ዓቀፍ ሚዲያና ኔትወርኮች ቅርበት ያላቸውና ተሰሚነታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲህ ካሉ አካላት ጋር በጨዋነት መስራት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለማስተጋባት መልካም አጋጣሚ ማመቻቸት እንደሆነም አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።

“… ኢህአዴግ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን በስርዓቱ የተገፉ በማስመሰል የሃሰት ማስረጃ እያስጨበጠ በአሜሪካ፣ በካናዳና በተለያዩ የምዕራብ አገራት ያሰማራቸውና በተቀነባበረላቸው መረጃ የስደት መኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ስደተኛውን እንዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑ፤ በተለያዩ አገራት በገቢር የተያዙ መረጃዎችና ዋቢ ክስተቶች መኖራቸውን የተረዳው የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል” በማለት ከዚህ ቀደም ለጎልጉል ስለተናገሩት አስተያየት እንዲሰጡ አቶ ኦባንግ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

“ኢህአዴግን የሚደግፉ ዜጎችም ቢሆኑ ለጋራ ንቅናቄያችን ልጆቹ ናቸው” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አቶ ኦባንግ “ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ምስጢረኛ ለመሆን እገደዳለሁ። አንድ ነገር ለማስታወስ ያህል ግን ምዕራባውያን አሠራራቸው መጭበርበሩን ካረጋገጡ ምህረት የላቸውም። ከሰብአዊነትም አንጻር ቢሆን አገሩ መኖር ያልቻለን ዜጋ ስደት አገር ድረስ እየተከታተሉ ማሳደድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በህግም አይፈቀድም። እንደዚህ ካሉት ጋር የሚተባበሩ አገሮችን ህግ ፊት በማቆም በህግ ስለፍትህ እንከራከራል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ABA የሚባለው የህግ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሲያከብር ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ፣ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት አርብ የሚደረገው ንግግር የድጋፉና አብሮ የመስራቱ ሂደት መጀመሪያ ነው። ሥራው ጊዜ የሚወስድና እልህ የሚያስጨርስ መሆኑን ሁሉም እንዲያስተውለውና ፈጣን ውጤት በመጠበቅ ቶሎ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሁሉም ዜጋ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጋራ ንቅናቄው በመላክ ትብብሩን እንዲቀጥል ጨምረው ገልጸዋል፡፡



ግብጽ በዲፕሎማሲያዊ ኢትዮጵያ ላይ ካልጫንኩ በሚሳኤልም፣ በኮማንዶም፣ በጄትም ልታጠቃ አሰበች ዊኪሊክስ

$
0
0

ባፈው ሰሞን ወሬና “ሚስጢር” አሹላኪው ዊኪሊክስ ከአሜሪካው የደህንነት ድርጅት ስትራትፎር ሾልኮ እጄ የገባው የበየነ መረብ መልዕክት መሰረት ግብጽ….. በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች የምፈልገውን በእነ ኢትዮጵያ ላይ ካልጫንኩ በሚሳኤልም፣ በኮማንዶም፣ በጄትም በመጠቀም በሰዓታት ልታጠቃን አንዳሰበች በሊባኖስ የሚኖሩ ዲፕሎማቷን ጠቅሶ ገልጾልናል፡፡

የግብፃውያን ከአባይ ጋር በተያያዘ ዋናው ችግራቸው በማስፈራራት እና ኃይል በመጠቀም የራሳቸው የሚያደርጉት ይመስላቸዋል፡፡ ይህም የሆነው በዋናነት የአባይ ወንዝ መነሻና ብዙውን ውሃ አበርካች የሆነችው ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ በጦርነት በመኖሯ እና አቅሟን የማጠናከር ጉዞዋ ያልተስተካከለ በመሆኑ ለውስጥ የደህንነት ጉዳዮች ትኩረት መስጠቷ ውሃውን እንዳትጠቀም እንቅፋት መሆኑ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ግብጽ ሱዳንን በመዛት ማስበርገግ መቻሏ እና ከካምፕ ዴቪድ ስምምነት በኋላ ከአሜሪካ የሚጎርፍላት ረብጣ ዶላር እና ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ልቧ እንዲያብጥ ስላደረገው ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው የጦርነት ክዋኔ በዘመናት ይለያያል እንጅ ባህሪው ባለመለወጡ ምንም መሳሪያ ብታከማች ግብጽ በታሪኳ አትዮጵያን አንድም ጦርነት አሸነፍ አታውቅም፡፡  ከዚህ አንጻር ስንመለከተው በዊኪሊክስ በኩል የሾለከው ጦማር ተራ ወሬ ሊባል የሚችል ነው፡፡ ሆኖም ግን ስንገጣጥማቸው ሙሉ ትርጉም የሚሰጡን ክስተቶችን ስላየን ይህን ጦማር ማቅለል ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል በአንክሮ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ምንአልባት ምንአልባት አንዳች ክፉ ነገር የህዳሴ ግድቡ ላይ ብታደርስ የማያቋርጥ የውሃ ጥማትን ለሚመጣው የግብጽ ትውልድ ትተዋለች፡፡ እጅግ በጣም ውስብስብ በሆነው መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ እየኖረች የእስራኤል እና የአረቦች ጉዳይ ባልለየለት ሁኔታ እንዲህ አይነት እስጣ ገባ ውስጥ መግባት የሚበላው ራሷን ግብጽን ነውና፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ግብጽ ኢትዮጵያን በሽርክ ለማጥቃት ኩርሲ በተባለች ዳርፉር ሱዳን ውስጥ በምትገኝ ቦታ የሚስጢራዊ ወታደራዊ ማዘዣ እያቋቋመች እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ይህ ምን ያክል እውነት ነው? ወደፊት የምናየው ጉዳይ ይሆናል፡፡


የነመላኩ ፈንታን የሙስና ጉዳይ ከማጣራት ቢላደንን ማግኘት ይቀል ነበር ማለት ነው?

$
0
0

የኢትዮጵያ ታሪክ መቼም አያልቅም፡፡ ታዲያ በዚህ በማያልቀው ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ የሰማሁች ታሪክ ቢኖር በኢህአዴግ ዘመን ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ኢህአዴግ ስልጣን ከጨበጠ 22 አመት ሞልቶታል…. ታዲያ በዚህ ወቅት ላይ “ትልቅ ሙስና” ብሎ ታላላቅ ባለስልጣናትን ወደ ማረሚያ ቤት አወረደ፡፡ መቼም ይህንን በማድረጉ ኢህአዴግ “ዴሞክራት ነው” የዚህ አይነት እርምጃ የሚወስድ መንግስት የለም ሊባል ይቻላል፡፡ ግን የኢህአዴግ የሙስና ጉዳይ ልክ እንደ ቼዝ እየዘገየ የሚደረግ ነገር ነው፡፡ በአለማችን ረጅም ጊዜያት የሚቆይ ጨዋታ ቢኖር ቼዝ ነው፡፡

 

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/05/Woyyane.jpg

የአለማችን የቼዝ ሻምፒዮን ሩሲያዊው ሰው ለሰባት አመት በቆየ የቼዝ ጨዋታ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ታዲያ ከዚህ ቀደም በ1987 ዓ.ም. የቀድሞ ታምራት ላይኔ ከሙስና ጋር በተያያዘ ወደ ዘብጥያ ወረዱ፡፡ ከሰባት አመት በኋላ ደግሞ በ1994 ዓ.ም. ላይ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትሮችና ስዬ አብርሃ ከቤተሰባቸው ጋርና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ወህኒ ወረዱ፡፡ ይህ ሲሆን መቼም ያልተገረመና ያልተደነቀ ሰው የለም፡፡ ይሁንና ታዲያ ከአስር አመት በኋላ ግን ዳግም የሙስናን ጉዳይ ሰማን ወይም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሙስና ጋር መታሰራቸው ነበር፡፡ በርካቶች የኢህአዴግ ጠንካራ እርምጃ በሙስና ላይ ወሰደ ሊሉ ይችላሉ፡፡ከሙስና ጋር በተያያዘ ግን የታሰረው ወገን ስንናገር “ይሄ ቼዝ አውራዎቹንና ዋናዎቹን” ብለን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ግን የገረመኝና ያስደነቀኝ ነገር ቢኖር እነዚህ ሰዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ወደ ወህኒ ከወረዱ በኋላ የፀረ ሙስና ኮሚሽነሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ያሉት ነገር ነው፡፡ “ይህ ጉዳይ ጠ/ሚ መለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ከአንድ አመት ከስምንት ወር በፊት የተጀመረ ነገር መሆኑን” ገለፁ፡፡ በዚህን ያህል ጊዜ ውስጥ ደግሞ እርምጃዎች ያልተወሰዱት ጠ/ሚ መለስ ተረጋግታችሁ በስህተት ሰውን እንዳታገላቱ ብለው በማለታቸው እንደሆነ ተናገሩ፡፡ ይህ የእሣቸው አነጋገር ግን አንድ ነገር በአእምሮዬ ውስጥ እንዳስብ አደርገኝ፡፡ ሙስኛን ወይስ አሸባሪን መያዝ ይከብዳል የሚል፡፡ መቼም ሙስናን የሚፈፅምን ሰው በርግጠኝነት በሕብረተሰቡ ዘንድ መረጃ ከተገኘበት ቀላል ነገር ነው፡፡ የሽብር ተግባር የሚፈፅምን ሰው መያዝ ግን በአሁን ሰአት እንኳን ለኛ ለአሜሪካ የከበደና አሜሪካንን ሆድ ያስባሰው ቢላደን እንኳን ከስንት አመት በኋላ እንደተገኘና እንደሞተ የምናውቀው ነገር ነው፡፡ ታዲያ አሁን ምን ታዘብን ብትሉ ከሽብርተኛ ሙስና በለጠ የሚለውን ነገር ነው፡፡ ይህንን ነገር ደግሞ በምንም ሣይሆን ከባለፈው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊቀመንበር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መግለጫ ማወቅ የምንችለው ነገር ሆኗል፡፡ ታዲያ ምናልባትም እሣቸው አንድ የገለፁት ነገር አለ፡፡ ይህ ነገር ወይም ክትትሉ የተጀመረው ጠ/ሚ መለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑንና በፍጥነት ሄዳችሁ ሰው ማጉላላት የላባችሁም ማለታቸውን ገለፀ፡፡ ስለጠ/ሚ መለስ ራእይ ምናልባትም ተራው ለመናገር የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ከሽብርተኛና ከሙስኛ የትኛውን ወገን መያዝ ወይም በፍጥነት ማወቅ ይቻላል የሚለውን እናስብ ይህንን ነገር ስናስብ ደግሞ ጉዳዩን የምንመለከተው ከሰብአዊ ወይም ከምርመራና ከውሣኔ አንፃር ሊሆን ይችላል፡፡ መቼም ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይ ሀገር ናትና ከአሜሪካ ጀምረን ወደኛ እንመለስ፡፡ ባራክ ኦባማና ኦሳማ ቢላደን በ2000 ወይም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም በአሜሪካ የደረሰው ነገር መቼም ለመላው አለም ይዞት የመጣው ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ በአሜሪካን የሽብር ጥቃት ደረሰ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸው አለፈ፡፡ አሜሪካ የምትታወቅበት የኒውዮርክ መንታ ህንፃዎች ሣይቀር የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆኑ፡፡ አለም ሽብርተኝነት የሚለውን ትርጉም ወይም “አሸባሪ” የሚለውን ነገር ያወቀው በዚህ ጊዜ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይሁንና ግን ታዲያ ይህንን የሽብር ተግባር ማን ፈፀመው የሚለው ነገር ሲነሣ “ኦሣማ ቢላደን” መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ ከሽብርተኝነትም በላይ የድፍረትም ያህል የቆጠረችው አሜሪካ ከሁልጊዜ ሸሪኳ እንግሊዝ ጋር በመሆን አልቃይዳ ይገኘበታል ያላቸውን አፍጋኒስታን ላይ ጥቃት ለማሰንዘር “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት” ተ.መ.ድ አማካይነት ዘመቻ ጀመረች፡፡ ይህ ሁኔታ ሁሉም ዜጋ የሞተበትና የተፈፀመው የሽብር ጥቃት ከዚህ ቀደም የማይታወቅ በመሆኑ ድምፀ ተአቅቦ ማድረግ ሽብርተኝነትን ማበረታታት በመምሰሉ ውሣኔው ፀደቀ፡፡ ይሁንና የአሜሪካና እንግሊዝ ጦር ወደ አፍጋኒስታን ዘልቆ ገባ፡፡ የታሊባን ኃይሎች ወይም ለአልቃይዳ ቦታ ሰጡ የተባሉት ኃይሎች እየተሸነፉ ጭምር የተባበሩት ኃይሎች ድል እያገኙ መጡ፡፡ ግን ይህ ድል ለአሜሪካ አንጀት የሚያርስ አይደለም፡፡ ለአሜሪካዊያንም ሆነ ለሌሎች ወገኖች ደስታው ይህን የሽብር ጥቃት በመንደፍ የአሜሪካ መለያ የነበሩትን መንታ ፎቆች ሣይቀር ያወደመውን አሸባሪው ኦሳማ ቢላደንን መያዝ ነበር፡፡ ይህ ግን አልሆነም፡፡ በአፍጋኒስታን ታሊባን ወርዶ የሽግግር መንግስት ቢቋቋምም ቢላደን አለመገኘቱ የኪሳራ ያህል ነበር፡፡ የሪፖብሊካኑ የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ጥሮ ምንም ሣይሣካ ወረደ፡፡ ከዛ በመቀጠል የኦባማ አስተዳደር ተተካ፡፡ ይሁንና ኦባማ ሙሉ ትኩረታቸውን በዚህ ጉዳይ ሣያደርጉ ስራ ጀመሩ፡፡ ይሁንና ግን በ2010-11 ላይ አንድ ያልተጠበቀ ዜና ተሰማ፡፡ ይህ ዜና ደግሞ አሜሪካ ትፈልገው የነበረው አሸባሪው ኦሳማ ቢላደን መገደሉንና ይህንን ያደረገው የአሜሪካ ጦር መሆኑን ተናገሩ፡፡ የኦባማ ቃል ለአለም አስገራሚ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኦባማ ሲገልፁ ኦሣማ ቢላደን ያለበትን ቦታ አውቆ በእሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የአንድ አመት ጊዜ መውሰዱን ጭምር ገልፀው ነበር፡፡ ኦሣማ የሚኖርበት ቦታ ላይ ማስረጃ /መረጃ/ ካገኘን በኋላ የዚህን ያህል አንድ አመት የቆየው እሱና ቤተሰቡ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማግኘት ስለነበረብን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አንድ አመት መቆየቱን ግን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ሊያውም አቅም ያለው አሸባሪን በሚመለከት፡፡ ታዲያ በኛ ሀገር ባለፈው ሰሞን የፀረ ሙስና ኮሚሽነር የሆኑት አሊ ሱሌይማን ሲገልፁ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሆኑት አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የሆኑት ሰዎችን ለመያዝ አንድ አመት ከስምንት ወር መፍጀቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ ስራ የተጀመረው ጠ/ሚመለስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑንና መለስም ዝም ብላችሁ የራሣችሁን ነገር አታድርጉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ ማለታቸውን ገልፀዋል፡፡ ምናልባትም የእሣቸው ጉዳይን ከመለስ ጋር ማያያዝ ምናልባት ከውለታ ጋር እናገናኝ፡፡እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሙስና ተግባራት ይከናወናል ተብሎ ከሚጠበቅባቸው ተቋማት መካከል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ነው፡፡ በየአመቱ የየሀገራችን የሙስና ጉዳይ የሚመረምረው ተቋም የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ ሙስና የተፈፀመበትና ከባድ ምዝበራ የሚከናወነው የገቢዎችና ጉምሩክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ ነገር ደግሞ መቼም በስልጣን ላይ ለሚገኘው መንግስት የማንቂያ ደውል ሊሆን ይችላል፡፡ በዛው መጠን መለስ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መ/ቤት ላይ ትኩረት አደረጉ፡፡ ታዲያ የአለም ባንክ ሪፖርት ግን አስር አመት ነው፡፡ አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት መላኩ ፈንታና “ግብረ አበሮቻቸው” ሣይሆን የስራ ባለደረቦቻቸው ከተሾሙ ደግሞ ገና ሦስት አመታቸው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በፍርድ ላይ የተያዘ ነው፡፡ ምናልባት የፍርድ ሂደቱን ተከትሎ ብዙ ነገር ማለት ቢቻልም ስናየውና ስንገነዘበው ገና ውሣኔያቸው አልታወቀም፡፡ በኢትዮጵያ ወይም በኢህአዴግ አሠራር ከሆነ ግን አሜሪካ ወይም ኦባማ መኖሪያውን አረጋግጠው ከያዙት ቢላደን ይልቅ ጠ/ሚ መለስ ጀምረው የእሣቸው ሕይወት ካለፈ ወይም በሕይወት ጀምረውት አንድ አመት ከስምንት ወር የፈጁት መላኩ ፈንታ በለጡ ማለት ነው፡፡ ይህ ነገር መቼም በጣም የሚገምር ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አሜሪካ በየአመቱ ከምታወጣውና ለሌሎች ሀገሮች የምትረዳው የሽብር ጉዳይን ለመከላከል ይህ ሆኖ እንኳን በቅርቡ በቦስተን ማራቶን የሽብር ጥቃት ደርሷል፡፡ሙስና ደግሞ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሙሰኛው ሰው ላይ ለቀናት የሚደረግ ትኩረት ግለሰቡን ያጋልጣል፡፡ ሌለው ቢቀር አካውንቱን በማስመርመር ብዙ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ ታዲያ አሁን የገቢዎችና ጉምሩክ ሰዎች መታሰርን ከዛም ይህን እርምጃ ለመውሰድ የፈጀውን አንድ አመት ከስምንት ወር ስናስብና አንድ አመት የፈጀውን የቢላደን መኖሪያን ስንጨምርበት የትኛው በለጠ ብለን እንድስብ ያደርገናል፡፡ ገና ያደረጉት ነገር ያልተረጋገጠው ክስ የተመሠረተባቸው እነ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ለማወቅና ለማግኘት ኦባማ ካደረጉት የቢላደን ዘመቻ በለጠ ማለት ነው፡፡


በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ተቃውሞ አሠሙ

$
0
0

ለአንድ ዲፓርትመንት ብለን የዩኒቨርሲቲውን ካሌንደር አንቀይርም” የዲፓርትመንቱ ኃላፊዎች በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች የወጣውን የፈተና ፕሮግራም በመቃወም ረቡዕ ጠዋት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ….. ተማሪዎቹ “መንግሥት በመደበልን ጊዜና በጀት የመማር መብታችን ይከበር” “There is no exam without education” እና የመሣሠሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ተቃውሞ አሠሙ

 

“የዘንድሮው ምዝገባ በሦስት ሳምንት ዘግይቶብናል፣ ከተመዘገብንም በኋላ ሁለት ሳምንት ዘግይተን ነው ትምህርት የጀመርነው” በማለት ቅሬታቸውን ያሰሙት ወደ 300 የሚጠጉት የሲቪል ምህንድስና የሦስትኛ ዓመት ተማሪዎች “አራት ሚድ ተፈትነን ከፋሲካ በዓል ስንመለስ አራት ሜጀር ኮርሶችን አንዳንድ ቻፕተር ብቻ የተማርናቸው አሉ፣ አስተማሪዎች በሥነ-ሥርዓቱ ስለማይገቡ አሁን ጊዜው ሲደርስ ለመጨረስ ቅዳሜ ማታ ሳይቀር እየተዋከብን እንማራለን፣ አንድ ላይ የማይወሰዱ ኮርሶችን በአንድ ላይ እንወስዳለን፣ ቤተ-ሙከራ (ላብ) አናውቅም፤ እስከ አርብ ተምረን ሰኞ ፈተና ልንቀመጥ አይገባም” የሚሉና መሰል ጥያቄዎችን አቅርበው የፈተናው ጊዜ ሊራዘምላቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

“ተሰብሰቡና እናነጋግራችኋለን” ተብለው “ፓርላማ” በተባለው አዳራሽ ውስጥ የተሰበሠቡት ተማሪዎች ከቆይታ በኋላ ሦስት የዲፓርትመንቱ ኃላፊዎች መጥተው ለማነጋገር ሲሞክሩ ብዙ አለመግባባቶች እንደነበሩ በስብሰባ አዳራሹ ተገኝተን ታዝበናል፡፡ የዲፓርትመንቱ ኃላፊ “ችግሩን ለማቅረብ በጣም ዘግይታችኋል” ተመዝግባችሁ ያልጀመራችሁት ኮርስ ካለ ተውት፣ ጀምራችሁ ያልጨረሳችሁት ኮርስ ካለ ጊዜ ፈልገን ትማራላችሁ፣ የዩኒቨርሲቲው ካላንደርና የፈተና ፕሮግራሙ ግን ለአንድ ዲፓርትመንት ተብሎ አይቀየርም በማለታቸው ተማሪዎቹ ቁጣቸውን በጩኸት ገልጸዋል፡፡ “የፈተና ፕሮግራሙ ለአራተኛ ጊዜ ተቀያይሯል፤ ይህ ለምን እንደሆነ አናውቅም” ስምንት ኮርስ እየወሰድን ጊዜው አጥሮብናል” ያሉት ተማሪዎቹ በሌላ ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ፈተና ሰኔ 16 ነው የሚጀምሩት፤ እኛ ግን ገና ተምረን ሳንጨርስ አርብ ጨርሳችሁ ቅዳሜ ውጡ ልንባል አይገባም” በማለት ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ አንድ ተማሪ ተነስቶ ባደረገው ንግግር “ምዝገባን ያዘገየው ሌላ ሰው፣ የችግሩ ሰለባ የሆንነው እኛ ነን ሁሉንም ችግር ያላጠፋነውን ሁሉ እንዲንሸከም የምታደርጉት ተማሪውን ነው” በማለት ቅሬታውን ገልጿል፡፡

ተማሪው አክሎም “እኛ እናንተ ምን ኃላፊነት እንዳላችሁ አናውቅም፤ ምንም ስትከታተሉ አይተናችሁ አናውቅም፣ ችግሩን አዘግይታችኋል የምትሉት ትክክል አይደለም፣ የሚሰማን አጥተን ነው እንጂ ስንጮህ ነው የቆየነው፤” አሁንም ቢሆን ጊዜው ተራዝሞ ኮርሶቻችንን ጨርሰን የምንፈተንበት መንገድ ይፈለግልን” ያለው ተማሪው “በዚህ ሁኔታ ከተፈተንን ኪሳራው የተማሪው፣ የዩኒቨርሲቲውና ብሎም የሀገሪቱ ነው” ሌላ ተማሪ በበኩሉ “እኔ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምህንድስና ተማሪ ማወቅ የሚገባኝን አውቄያለሁ ብዬ አላምንም” ካለ በኋላ በግቢው አስተማሪ ማስተማርም አለማስተማርም መብቱ እንደሆነ፣ አንዳንድ አስተማሪዎች ፈተና 15 ቀን ሲቀረው እየመጡ እንደሚያጣድፉ፣ ዩኒቨርስቲው ይህን እንደማይከታተልና ችግሩ ሰለባ እየሆነ ተማሪው እንደሆነ በአፅንኦት ተናግሯል፡፡ “አሁን ሰኔ ስምንት እንድንወጣ የሚደረገው በበጀት እጥረት ነው፤ እኛ እንደ ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ “ኮስት ሼሪንግ” የምንፈርመው ከመስከረም እስከ ሰኔ 30 ነው፡፡ ስንገባም ጥቅምት አምስት ነው ወደ ጊቢ የመጣነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት የመደበልን ጊዜና በጀት እስከ ሰኔ 30 የሚያቆየን በመሆኑ ቀስ ብለን ተረጋግተን ልንፈተን ይገባል” ብሏል፡፡

ኮስት ሼሪንግ የፈረሙበት ፎቶ ኮፒ እጃችን ላይ ይገኛል፡፡ “ሌላው ዩኒቨርሲቲ የራሱ አካሄድ አለው፡፡ አዳማም በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ካሌንደር ነው የሚሠራው” ያሉት የዲፓርትመንቱ ኃላፊ “አሁን ችግር ያላችሁት የፈተና ፕሮግራሙ ነው፤ እሱ ላይ ተናገሩ እንጂ ጠቅላላ ችግር አታውሩ” በማለት ቁጣ በተቀላቀለው አጽንኦት ተማሪዎቹን ገስፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተማሪው ኃሀላፊውን ቁጣ ወደ ጐን በመተው “አንድ ኮርስ በሳምንት ብቻ የምንጨርስበት ሁኔታ አለ፤ እኛ ዴቨሎፕ ሳናደርግ ነው የምንፈተነው፤ ዜጋን ለማዳን ከተፈለገ የማይለወጥ ነገር የለም፡፡ በትምህርቱና በፈተናው መሀል ክፍተት ተሰጥቶን እንፈተን” በማለት ጥያቄያቸውን ቀጥለዋል፡፡ “እኔ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ መማር የሚገባኝን ያህል አልተማርኩም፣ አስተማሪም ከሆንኩ በኋላ ለተማሪዎቼ በአግባቡ አስተምሬያለሁ ብዬ አላምንም” በማለት ለተማሪዎች ምላሽ መስጠት የጀመሩት ሌላው ኃላፊ፤ ይህ ከእኔም ስንፍና፣ ከዩኒቨርሲቲውም ችግር አሊያም በሀገሪቱ ካሉት በርካታ ገደቦች ሊሆን ስለሚችል አሁን ባለው ሁኔታ ቶሎ ቶሎ ጨርሳችሁ ተፈተኑ” ማለታቸው ተማሪዎችን የበለጠ አስቆጥቶ ነበር፡፡ በአዳራሹ ውስጥ ጭቅጭቁ እየከረረ በመሄዱ አንድ ተማሪ አንድ የተሻለ የሚለውን ሐሳብ አቀረበ፤ “አንድ ኮርስ አሳይመንት ሠርተናል፤ እሱ ከመቶ ይታይና መፈተኑ ይቅርብን፡፡

ይህም የሚጠበውን ጊዜ ይቆጥባል ከዚያ በተረፈ ቢያንስ አንድ ቅዳሜ ይጨመርልንና ትንሽ ጋፕ ይኑረን” በማለቱ ኃላፊዎቹ እየከበዳቸውም ቢሆን ለመቀበል ተገደዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንደሚሉት በዩኒቨርሲቲው ብዙ ችግር እንዳለባቸውና ፕሮፌሰር ማጁንዳ የተባሉ የቢዩልዲንግ አስተማሪ በሰጡት ግሬድ ስላልታመነበት ከአስተዳደር ክፍሉ በተነሳ ጭቅጭቅ አስተማሪው አጠቃላይ የተማሪዎቹን ውጤት ይዞ ወደ ህንድ በመሄዱ ውጤት በጊዜ ሊታወቅ ስላልቻለ ምዝገባው ለሦስት ሳምንት መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡ ኃላፊዎቹም ይህን አምነው አስተማሪውን በኢሜልም በስልክም አነጋግረን ሊታረም ባለመቻሉ ከስራው ማሰናበታቸውንና የምዝገባው ጊዜ መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡ “እኛ በአግባቡ አልተማርም ያልዘሩብንን ሊያጭዱ ይሞክራሉ፡፡ ይኼ ለዚህች አገር ውድቀት ከፍተኛ ቁልፍ ነው” ያሉት ተማሪዎቹ ትምህርት ሚኒስቴርና የሚመለከተው አካል ዩኒቨርሲቲውን እንዲቆጣጠረውና እንዲፈትሸው አሳስበዋል፡፡ “ችግሩ የእኛ ዲፓርንመንት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው” ያለችው አንዲት የዲፓርትመንቱ ተማሪ እኛ ከማወቅ ሳይሆን ከመጨረስ አኳያ ነው እየተዋከብን ያለነው፤ መንግስት ችግራችንን ይወቅልን” ስትል ተናግራለች፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ተማሪዎቹ ያለባቸውን ችግር ችለው እንዲፈተኑና በተባለው ጊዜ ግቢውን እንዲለቁ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ስብሰባው ቢበተንም ተማሪዎቹ ቅሬታ እንዳለዙ ሲበታተኑ ለመታዘብ ችለናል፡፡

Source: Addisadmassnews.com


ከኢሳት የአዲስ አበባውን ሰላማዊ ሰልፍ የተመለከተ ልዩ ዘገባ

$
0
0

Special Report on the Protest rally Semayawi Party June 02,


Ethiopian gov’t pays China 26billion birr to block sites, media

$
0
0

Special dish for up to 16 satellite positions ...

The Ethiopian government has paid China $1.2 Billion (26 Billion Birr) for the later to block websites and media that the regime considers “critical and a danger…” to its administration, a reliable source in the Ethiopian Internet Security told ESAT.
The two sides have agreed that the Website, Radio and Television transmission of Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT) should first be blocked of all. A decision has also been reached to block selected programs of the Voice of America Amharic Service and Deutsche Welle Amharic Service. Websites that are critical of the government are still inaccessible in Ethiopia.
Although ESAT’s Website has been blocked in Ethiopia, its Radio and Television transmissions have been reaching Ethiopia for the past five months. Audiences in Ethiopia have been accessing ESAT by changing the directions of their Satellite Dishes. ESAT has also been receiving reports that some Ethiopian government officials have been taking actions after watching some of ESAT’s reports.
In related News, in an attempt of restraining the condemnation and pressures of change that it has been facing on Facebook, the Ethiopian government is preparing to apply a new blocking technology that it dubs “RESAW”. If the pilot scheme succeeds, there are possibilities that the government could block all connections in Facebook. Although there have been attempts to apply the new technology since last month, it has not been successful.
Ethiopian government officials whom ESAT phoned to get their opinion on the issue were unreachable.

Viewing all 931 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>