Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

ለምን የኢትዮጵያ ብር ወደ ጥቁር ገበያ ይላካል?

$
0
0

በሙስና ውስጥ የተዘፈቁ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተባባሪ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚያገኙትን የኢትዮጵያ ብር በአዲስ አበባ ጥቁር ገበያ ውስጥ በዘረጉት ሰንሰለት ወደ አሜሪካ ዶላር ለውጠው ወደ ውጭ ሀገር እንዲወጣ በማድረግ ተጠቃሚ በመሆናቸው መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል…

በተለይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዚህ መልኩ የሰበሰቡትን የአሜሪካ ዶላር በተሰጣቸው ያለመፈተሸ መብት በመጠቀም እና በገቢዎችና ጉምሩክ በዘረጉት የኪራይ ሰብሳቢ ሰንሰለቶች አማካይ ወደ ውጭ ይዘውት የሚወጡበት አሰራር ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የሰበሰቡትን የአሜሪካ ዶላር በሳምሶናዊት ቦርሳቸው ውስጥ በመጨመር እና ቦርሳውን ላይ ያለመፈተሽ መብት የሚያጎናጽፋቸውን ልጣፍ በመለጠፍ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ዶላሩን ይዘው የሚወጡበት ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን ተናግረዋል።
በአስረጅነት ግምታቸውን ሲያስቀምጡ የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት የተገኘው 26ሺ የአሜሪካ ዶላር እና 19ሺ ዩሮ የአውሮፓ ሕብረት የመገበያያ ገንዘብ በዚህ መልኩ የተሰበሰቡ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ግምት ገልፀዋል። አያይዘውም አንድ ግለሰብ ከ200 የአሜሪካ ዶለር ምንዛሪ ውጪ ይዞ መገኘት እንደማይችል በኢትዮጵያ ሕግ መስፈሩንም አስታውሰዋል። እንዲሁም በአቶ አስመላሽ ወ/ማሪያም መኖሪያ ቤት የተገኘውም አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር ለመቀየር የተቀመጠ ገንዘብ ሊሆን እንደሚችል ከጥቁር ገበያ ያገኘነው ግምታዊ መረጃ ያሳያል።
ይህን መሰል ተግባር መፈጸም ትርጉሙ ብዙ ሊሆን ይችላል። በተለይ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት መኖሩ እያወቀ የኢትዮጵያን ብር በዶላር እየመነዘረ ወደ ውጭ ሀገር በማስወጣት ተግባር ላይ ከተሰማራ እንደሀገር ትልቅ በደል መሆኑን መገንዘብ ሮኬት ሳይንስ አይሆንም። በዚህ መልኩ የተሰማሩ የመንግስት ባለስልጣናት በወፍ በረር ሲታይ፣ ዶላር ማሸሽ ቢመስልም በተግባር ግን ሲመነዘር የኢትዮጵያ መንግስትን እና ሥርዓቱን ቀስ በቀስ እየሸራረፉ ሊጨርሱት መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ ነው። የፓርቲ ሹመኞቹን የመንግስትን ስርዓት ለዘረጋው ገዥ ፓርቲ ቢተውም፣ ተግባራቸው ግን ሕገ መንግስቱን በጠራራ ፀሐይ እየበጣጠሱት ስለመሆኑ አስረጂ አያስፈልገውም።
የገንዘብ ምንጩ ስትራቴጂ
እ.ኤ.አ. የሴፕቴምበር 11 ቀን 2001 የአሜሪካኑን የሽብር ጥቃት ተከትሎ ትንሹ ቡሽ ሴፕቴምበር 20 ቀን 2001 “WAR ON TERROR” በሚል መጠሪያ ዓለም ውስጥ የሚገኙ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ ያስችላል በሚል አዲስ ስትራቴጂ ይዘው ብቅ አሉ። ቡሽ ቀጠል አድርገው በአሸባሪዎች ላይ የምንከፍተው ዘመቻ ‘የመስቀል ጦርነት’ ነው በማለት ለዓለም ሕዝብ በይፋ ተናገሩ።
ቡሽ ብዙም ሩቅ ሳይጓዙ በአደባባይ “የመስቀል ጦርነት” የሚለውን ቃል ተገቢ አይደለም፤ ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር አወዛጋቢ ፍቺ ያመጣል በማለት በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጦርነቱን የምንጀምረው በአልቃይዳ እና በእሱ የሽብር መረብ ከተያያዙ አሸባሪዎች ጋር ነው ሲሉ አቋማቸውን በግልፅ አስቀመጡ። ዓለም ከአሜሪካ ጎን ቆመ። ቡሽም፣ ‘ወይ ከእኛ ወይም ከእነሱ’ ጋር መሆንን ምረጡ ብለው ለዓለም ዓቀፉ ሕብረተሰብ ጥሪ አቀረቡ። ዓለምም በወቅቱ በጐ ምላሽ ሰጣቸው። ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ኦሳማ ቢላደን ግን ከአስር ዓመት በኋላ ተገድሏል።
እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ቁምነገር፤ እንደቡሽ የመጀመሪያ አቀራረብ ቢሆን የተቀደሰውን የእስልምና እምነት ከሽብር ተግባር ጋር ጨፍልቆ ለማየት ያለመ ነበር። ሆኖም ቡሽ ፈጥነው አባባላቸው ስህተት መሆኑን አርመው በይፋ ይቅርታ ጠየቁ። ስለዚህም ነገሮች ለያይቶ ማየት እንጂ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ወርውሮ አንድ መለያ መስጠት ተገቢ አለመሆኑ ከዚህ መረዳት ይቻላል።
በተነፃፃሪነት ሲታይ ደግሞ ገቢዎችና ጉምሩክ በቀድሞ ከፍተኛ አመራሮቹ በኩል የኢትዮጵያ ነጋዴዎችን በተለይ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን ነጋዴዎች በግብር ስም ሁሉም ነጋዴ ግብር አጭበርባሪ ኪራይ ሰብሳቢ በማድረግ ሽብር “TERROR on tax” በነጋዴው ላይ ረጩ። ነጋዴውም ግብር መክፈሉን ሳይሆን ለኪራይ ሰብሳቢ ወይም ለግብር አጭበርባሪ ታፔላን ላለመጋለጥ በሚል ብቻ የገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተገዢ መሆኑ አረጋገጠ። በመጨረሻም በተፈበረከው የሽበር ማዕቀፍ ውስጥ ነጋዴው ወደቀ። ፍርሃት፣ ስጋት መለያው ሆነ።
ከዚህ በኋላ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮቹ ጋር ተባብሮ መስራት የኪራይ ሰብሳቢዎች የህግ የበላይነትን ማረጋገጫ አድርጎ ተቀበለው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው መንግስት ከፍተኛውን የሙስና ወንጀል በራሱ መንገድ ደረሰበት እንጂ በአደባባይ በመውጣጥ ለማጋለጥ የደፈረ ታዋቂ ባለሃብት አንድም አልነበረም። በሕግ የማይነኩ በሚመስሉ የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር ሲራኮቱ የነበሩ ታዋቂ የከተማችን ባለሃብቶች ሕግ በራቸው ደጃፍ ሲመጣ ሌላ የፖለቲካ ዓላማ ያለው ተግባር እንጂ ሙስና አይመስለንም ሲሉ በአደባባይ በዘረጉት የኪራይ ሰብሳቢዎች የሙስና ሰንሰለት በመጠቀም ከተማውን እያሟሟቁ ይገኛሉ። እውነቱ ግን ሌላ ሆኖ ነው እየታየ ያለው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በባሕርዳር በተደረገ የኢሕአዴግ 9ኛው ጉባኤ ላይ ከተጋበዙ ባለሃብቶች መካከል አንዱ የከተማችን ባለሃብት ለጉባኤው ያቀረበው ጥያቄ አጠቃላይ መንፈሱ ሲታይ “የኪራይ ሰብሳቢ” መሰረታዊ ይዘት በመቀየር ወደ ‘ሽብር’ መለወጡን አመላካች ነው። ባለሃብቱ ጉባኤውን የጠየቀው እንዲህ ሲል ነበር፣ “የኪራይ ሰብሳቢ ፍቺው በጣም የተለጠጠ ነው። በትክክልም ምን እንደሆነ እንኳን ለመረዳት አዳጋች ነው። በጅምላ ሁሉም ነጋዴ በገባበት ቢሮ ውስጥ ኪራይ ሰብሳቢ እየተባለ ይሸማቀቃል። እኔ እራሴ አሁን ኪራይ ሰብሳቢ በሚባለው ፍቺ ኪራይ ሰብሳቢ ልሁን፣ አልሁን ማረጋገጥ እንኳን አልችልም” ሲል በነጋዴው ላይ የተለቀቀውን ሽብር ለጉባኤው አስረድቷል።

ቡሽም በጅምላ የሚካሄደው ጦርነት የመስቀል ጦርነት ነበር ያሉት። እሳቸው ግን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር የበለጠ በመቀራረብ ለኪራይ ሰብሳቢዎች የተጋለጠውን የንግዱን ሕብረተሰብ ከሌላው ጤነኛ የንግዱ ሕብረተሰብ መለየት አለበት። ሁሉም ነጋዴ የኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያም ተባባሪም ሊሆን ስለማይችል ነው። ንግድም ዓለምን የለወጠ የተከበረ ተግባር ከመሆኑ አንፃር መንግስት ከዚህ በፊትም ሲያደርገው እንደነበረው አሁንም አጋርነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል። ስለዚህም መሰረታዊ የመንግስትን የገቢዎችና ጉምሩክ ፖሊሲን “በሽብር”፣ “በፍርሃት” ቆፈን ቀይረው ለራሳቸው ጥቅም ያደሩ የመንግስት ባለስልጣናት በፈጠሩት የተሳሳተ የኪራይ ሰብሳቢ ፍቺም በተቻለ ፍጥነት ለንግዱ ማሕበረሰብ መሰረታዊ ዕሳቤውን ማቅረብ ያስፈልጋል። በአንድ ቅርጫት ውስጥ የተቀመጠው የንግዱ ማሕበረሰብ ስምም ተገቢውን ስፍራ ሊያገኝ ይገባል። በመንግስትም በበኩሉ ኪራይ ሰብሳቢዎችን መያዙ ምርጫው ሳይሆን ግዴታው መሆኑን ግንዛቤ መውሰዱም ይጠቅማል። በተረፈ መንግስትና ጤናማው የንግዱ ማሕበረሰብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጸች መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር በመሆኑ ብዙ ማለት   አይቻልም።¾(ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 402 ረቡዕ ግንቦት 14/2005)

posted by Aseged Tamene

Like this:

የአንድነት እና የመድረክ ውዝግብ ቀጥሏል

“ቆብ ቀዶ መስፋት የስንፍናና ሥራ ፈትነት እንጂ የችሎታና የብቃት ማሳያ ተግባር ሊሆን አይችልም”
ከጥላሁን እንደሻው (የመድረክ ሊቀመንበር)
በአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላት በመድረክ ላይ ሰሞኑን የተከፈተውን አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ በሚመለከት የቀረበ ማብራራሪያ፡-
በቅድሚያ በመድረክ ላይ ሰሞኑን በየሚዲያዎቹ እየተካሄደ ያለው አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ በአንድ ግለሰብና በሌሎች ደጋፊዎች አማካኝነት ቢመስልም በመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአንድነት ተወካዮች የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አሥራት ጣሴ ግንቦት 7 ቀን 2005 ዓ.ም በተካሄደው የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እውነቱን አውጥተው ተናግረዋል። በዚሁም መሠረት አቶ ሃብታሙ አያሌው የሚባለው ግለሰብ በየሚዲያዎቹ መድረክን ስለማፍረስ ፕሮፓጋንዳ የጀመረው በራሱ ተነሳሽነትና ውሳኔ ሳይሆን የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አመራሮች በተለይም የም/ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ና የግምገማ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ በላይ ፈቃደ በሰጡት ፈቃድና ትዕዛዝ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁንም ቢሆን የብሔራዊ ም/ቤቱ ግለሰቡ የሚያካሂደውን አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ የሚያስተባብል መግለጫ ለማውጣትም ሆነ የእርማት እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ አለመሆኑን ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት በመድረክ ሥ/አ/ኮ የአንድነት ተወካዮች በስብሰባ ላይ በግልጽ አስረድተውናል። ስለዚህ ሁሉም የብሔራዊ ም/ቤት አባላት ይህንን አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ይደግፋሉ ብሎ ማጠቃለል የማይቻል ቢሆንም ነገሩ የግለሰብ ጉዳይ አለመሆኑንና በብሔራዊ ም/ቤት መሪዎች ግለሰቡ የጀመረውና የቀጠለበት ጉዳይ መሆኑን አንባቢያንና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳልኝ እፈልጋለሁ። እውነቱን ለነገሩን የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች በወቅቱ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ምስጋናዬን ያቀረብኩ ሲሆን አሁንም ደግሜ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። እኔም ነገሩ የግለሰብ ይሆን እንዴ? ብዬ በትዕግሥት ስከታተል ከቆየሁ በኋላ በብሔራዊ ም/ቤት አመራር ደረጃ እጃቸውን ያስገቡበት ጉዳይ መሆኑን ስለተረዳሁ በመድረክ ውስጥ የተሠራውን እውነተኛ ሥራ በማስረዳት ሕብረተሰቡን በሐሰትና አፍራሽ በሆነ ፕሮፓጋንዳ ለማወናበድና ለማሳሳት እየተንቀሳቀሱ ያሉትን እነዚህ ግለሰቦች የሚያካሂዱትን መሠረተ ቢስ ፓሮፓጋንዳዎች ለመከላከል እንደመድረክ ሊቀመንበርነትም ሆነ እንደ አንድ እውነትን ደጋፊ ዜጋ የበኩሌን ድርሻ መወጣት ግዴታ ስለሆነብኝ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ብዕሬን ማንሳቴን ለአንባብያን በቅድሚያ መግለጽ እፈልጋለሁ። እውነት እስኪታወቅ ድረስ ሐሰት እውነት መስላ ብዙ ሰዎችን ልታሳስት ስለምትችል ሁሉም ስለመድረክ ትክክለኛውን እውነታ የሚያውቅ የመድረክ አባልም ሆነ ደጋፊ ሁሉ በመድረክ ላይ የተከፈተውን አፍራሽና ጐጂ ፕሮፓጋንዳ በማጋለጥ የድርሻውን እንዲያበረክትም በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። በመቀጠል ወደ ርዕስ ጉዳይ እገባለሁ።
በሀገራችን ሰነፎችና ሥራ ፈቶች የሚሠሩትን ፋይዳቢስ ሥራ ለመግለጽ ሕዝባችን በድሮ ጊዜ የሚጠቀመው ምሳሌአዊ አነጋገር “ሥራ የፈታ መነኩሴ ቆብ ቀዶ ይሰፋል” የሚል ነበር። ይህ አባበል በአሁን ጊዜ መነኩሴዎቻችን ሥራ ፈቶች መሆናቸው ቀርቶ ሥራ አክባሪዎችና ብርቱ ሠራተኞች ሆነው በየገዳማቱ በሚያመርቱት ምርት ለሌላውም ሕብረተሰብ ጥሩ አርአያ እየሆኑ ስለመጡ ከመነኩሴዎቻችን ጋር የማይገናኝ ተረትና ምሳሌ ሆኖአል። ምክንያቱም መነኩሴዎቻችን እጅግ በጣም ብዙ ሥራዎችን በየገዳማቱ በመፍጠር በሥራ እየተጠመዱ ጥሩ ጥሩ የሥራ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ ስለሆኑ በአሁኑ ጊዜ ቆብ ቀደው የሚሰፉበት ጊዜ ስለሌላቸው ነው::
ይሁን እንጂ ይህ መጥፎ የሥራ ፈትነትና ስንፍና ባህርይ በጠቅላላው ከሕብረተሰባችን ጠፍቷል ማለት ግን አይደለም። እንዲያውም አንዳንድ ፖለቲከኞች ነን ባዮች ለራሳቸው ሥራ መፍታትና የስንፍና ባሕሪ ማሳየት ብቻ ሣይሆን በሥራ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሚጥሩትን ዜጎችንም በሥራቸው ላይ እንዳያተኩሩ በፋይዳቢስ ፕሮፓጋንዳቸው ለማስተጓጎል ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያውቀው በሀገራችን የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ፓርቲዎቹ በፖለቲካ አመለካከትና የአደረጃጀት ቅርፅ መለያየት ብቻ ሣይሆን በርካታ የሚጋሩዋቸው ጉዳዮችም አሉዋቸው። በብሔርም ሆነ በሕብረ ብሔር ቢደራጁም የሚታገሉት ለአንዲት የጋራ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ስለሆነና ሀገራቸውም ደግሞ በውስጡዋ ብሔር ብሔረሰቦች ያሉዋት በመሆንዋ ለሀገራቸው ሲያስቡና ሲታገሉ በውስጡዋ ለሚገኙና የየራሳቸው ባህልና ቋንቋ እንዲሁም የማንነት መግለጫ ላላቸው ሕዝቦች መብት አብሮነትና የጋራ ዕድገትም ያስባሉ፤ ይታገላሉም። ስለዚህ በብሔር ወይም በሕብረ ብሔር የመደራጀት ጉዳይ የአደረጃጀት ቅርጽ እንጂ የዓላማ ልዩነት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም።
አንዳንድ ይህንን እውነታ በሚገባ ያልተረዱ ወይም ሆን ብለው በመከላከላቸው ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና ለገዢው ፓርቲ የከፋፍለህ ግዛ ተልኮ መሳካት አስተዋጾአቸውን ለማበርከት የተሰለፉ ግለሰቦች በብሔር ብሔረሰብ የተደራጁ ፓርቲዎች ለራሳቸው ብሔር ወይም ብሔረሰብ ብቻ የቆሙ፣ ለኢትዮጵያ ሕልውናና አንድነት የማይጨነቁ፣ እንዲያውም ሀገርን ለመገነጣጠል የተሰለፉ አድርገው በሌላ በኩል በሕብረ ብሔር የተደራጁት በአደረጃጀት ቅርጻቸው ምክንያት ብቻለሀገር ሕልውናና አንድነት ብቸኛ ጠበቆችና ባለአደራራዎች እንዲሆኑ አድርገው ከተጨባጩ እውኔታ ውጭ በሆነ አቀራረብ ሲዘባርቁ ይታያሉ። አንዳንዶች ደግሞ በሕብረ ብሔር የተደራጁት ሁሉ የብሔር ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን መብቶች በጭራሽ እንደማይቀበሉ አድርገው ይፈርጃሉ። አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም እነዚህኑ ቁንጽል አስተሳሰቦች በማስተጋባት በብሔር ብሔረሰብ የተደራጁና በሕብረብሔር የተደራጁ ፓርቲዎች ጭራሽ ሊያገናኛቸው የሚችል ጉዳይ በመካከላቸው እንደሌለ በመቁጠር አብሮ ለመሥራት የሚያደርጉት እንቅስቃሴና የጋራ ትግላቸውን ሲያጥላሉ ይታያሉ።
ከዚህ በላይ የተገለጹት የተዛቡ አመለካከቶች ትክክል አለመሆናቸውን የተረዱት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አባል የሆኑ በብሔር ብሔረሰብ የተደራጁና ሕብረ ብሔር የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተዛባውን አስተሳሰብ በመስበር ተቀራርበው በመወያየት የሚያስማማቸውንና የሚለዩበትን ጉዳዮች በሰከነ ውይይት በመለየትና ከሚለያያቸው ጉዳዮች ይልቅ በሚያግባባቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር በጋራ ተቀናጅተውና ግንባር ፈጥረው ለሀገራችን የዴሞክራራሲ ሥርዓት ግንባታና ለልማቱዋ የጋራ ዓላማዎችን በጋራ ለማሳካት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በዚህም ጥረታቸው ከ2000 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ “መድረክ ለዴሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል የጋራ የውይይት መድረክ ከፍተው ውይይታቸውን ለአንድ ዓመታት ያህል ጊዜ አካሂደው በመጀመሪያ የጋራ መርሖችን አውጥተው በነዚሁ መርሖዎች የሚሰማሙ ሌሎች ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በመድረኩ እንዲሳተፉ በመጋበዝ ተንቀሳቅሰዋል።
በመጀመሪያ እንቅስቃሴውን የጀመሩት በብሔር የተደራጁት የኦሮሞ ሕዝቦች ኮንግረስ፤ አረና ትግራይና የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት፤ በክልልና ሕብረ ብሔር አደረጃት የተደራራጀው ደቡብ ሕብረትና በሕብረብሔርና ሀገር አቀፍ አደረጃጀት የተደራጁት የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከሁለት ታዋቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ነበር። መድረኩን ከፈጠሩበት መሠረታዊ መርሖዎች አንዱና ዋነኛውም “ትግላችንን በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ሥር እናካሂዳለን” የሚል ነበር።
እንግዲህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት አካላት በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ሥራ ለመታገል የተስማሙባቸው በርካታ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መርሖዎች የሳባቸው ሌሎች ሕብረ ብሔራዊ ፓርቲዎች ማለትም የኢትዮጵያ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሚባሉ ፓርቲዎችም በመድረኩ የተቀላቀሉ ሲሆን መድረኩን ከውይይት መድረክ ወደ ሕጋዊ የቅንጅት አደረጃጀት ለማሸጋገር ከስምምነት ስለተደረሰ ለዚህ አደረጃጀት የሚያበቃንን የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የጋራ የስምምነት ሰነድ ለማዘጋጀት ይህንኑ የሚያዘጋጅ ግብረሃይል በማቋቋም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሰፊና እጅግ አድካሚ ውይይቶችን አካሂደናል። በሳምንት ከሶስት እስከ አራት ቀናት ስብሰባዎችን በማካሄድና በእያንዳንዱ ቀናትም ከሶስት እስከ አምስት ሰዓታት ያህል ሳናቋርጥ በውይይት ላይ እየቆየን ነው ለአንድ ዓመት ያህል ጊዜ ያሳለፍነው። ግብረሃይሉ የሚያካሂዳቸውን ውይይቶች በየ15 ቀናት ለጋራ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት እያደረገ ከየድርጅቶቹ የተወከሉትን ሁለት ሁለት ግለሰቦች ያቀፈው የመድረክ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እየገመገመው ቀጣይ ውይይቶች በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንዲካሄዱ በማድረግ ስፋትና ጥልቀት ያላቸው የፖሊስ ጉዳዮች ላይ በመወያየት አጠቃላይ የፖለቲካ የኤኮኖሚና የማሕበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ብቻሳይሆኑ ዝርዝር የሴክተር ፖሊሲዎች ላይ ጭምር ከስምምነት ላይ ሊደረስባቸው ችሎአል። ውይይቶቹ በተወካዮች አማካኝነት ብቻ ሣይሆን ለድርጅቶችም እየተላኩ በየድርጅቶቹ የአመራር አባላትና አካላት ጭምር ውይይቶች እየተካሄዱ አቋም ይወሰድባቸው ነበር።
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ የሚዳስስ መግቢያ፤ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከስምምነት የተደረሰባቸው አጠቃላይ መርሖችና አቋሞች ፖለቲካዊ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጉዳዮችን በሚመለከትና የኤኮኖሚና ማሕበራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ያሉትን በርካታ ችግሮች ነቅሶ በማውጣት የመፍትሔ ሀሳቦችን የሚያስቀምጡ አንቀጾች በግልጽ የተቀመጡባቸው ባለ 65 ገጽ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በጋራ ጉባኤ ሊጸድቅ ችሎአል። በወቅቱ የኢትዮጵያን አንድነትም ሆነ በኢትዮጵያ አንድነት ሥር ሊከበር ስለሚገባው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት አከባር ላይ በጋራ ስምምነት በርካታ አንቀጾች ያለልዩነት የጸደቁ መኖራቸውን አንባቢያን ፕሮግራሙን ራሱን በማንበብ ሊረዱ ይችላሉ ብዬ አምናለሁ።
ለምሳሌ በፕሮግራሙ አጠቃላይ መርሖዎች መጀመሪያ ላይ “ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት በጽናት እንቆማለን፣ በቀድሞ የነበሩትንና አሁንም ያሉትን ኢፍትሐዊና አድሎአዊ አሠራሮች የተወገዱበት በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነት እንዲጠናከር በጽናት እንቆማለን፤ በመሆኑም መገንጠልን አንደግፍም” የሚል መርሖ ቅድሚያ ተሰጥቶ ሰፍሮ ይገኛል።
የመድረክ አባል ድርጅቶች ብሔራዊም ሆኑ ሕብረ ብሔራዊ በምንም ሳይለያዩ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ስለሕዝቦቿ አብሮነት ያላቸው ጽኑ አቋም ከዚህ በላይ የጠቀስኩት ሆኖ ሳለ አንዳንድ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባላት የሆኑ ግለሰቦችና አንዳንድ ሚዲያዎች በተለይም ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ አንድነትና በሕዝቦች የመብት ጥያቄ ላይ የሰፋ ልዩነት በመድረክ አባል ድርጅቶች መከላከል እንዳለ በማስመሰል የራሳቸውን የፈጠራ ወሬ ከማስተጋባታቸውም በላይ ውይይት ያልተካሄደበትና አቋም ያልተወሰደበት ጉዳይ ያለ ይመስል የመድረኩ አባል ድርጅቶችን ግንኙነት አፍራሽ በሆነ መልኩ ደጋግመው ሲተቹ ታይቷል።
መድረክ ወደ ግንባር የተሸጋገረብትን ሂደት አስመልክተውም በመድረክ አባል ድርጅቶች መሪዎች ብቻ በችኮላ እንደተፈጸመ አስመስለው ከእውነት የራቀ አሉባልታ ሲያስተጋቡ ይደመጣሉ። ይህንን ከሀቅ የራቀ ፕሮፓጋንዳቸው” ለገዥው ፓርቲ ፕሮፓጋንዲስቶች በማቀበልም በመድረክ አባላትና ደጋፊዎች የትግል ሞራል ላይ ጥቃት የሚያደርስ ዘመቻ እንዲያካሂድበት በማድረግ ለገዥው ፓርቲ አገልጋይነታቸውን በተግባር በማሳየት ላይ ይገኛሉ። እውነቱ ግን ከመጀመሪያውኑ የፕሮግራሙና የደንቡ ዝግጅት እንደተጠናቀቀ ሰነዶቹ ከቅንጅት አልፎ ለግንባር ምስረታም ቢሆን በቂ የሆኑ ሰነዶች መሆናቸው በሁሉም የመድረክ አባል ድርጅቶች ታምኖበት የነበረ ቢሆንም በሀገራችን ባላው የግንባር ምሥረታ ሕግ መሠረት የሚመሠረተው ግንባር ከሆነ ሰነዶቹ በእያንዳንዱ አባል ድርጅት ጉባኤ ጭምር መጽደቅ ያለበት ስለሆነ ሁሉም ድርጅቶች በአመራር አካላት ብቻ ሣይሆን ጉባኤ ጠርተው በየጉባኤዎቻቸው እንዲያፀድቋቸው ተደርጐአል። ታዲያ ከእነዚህ የሁሉም አባል ድርጅቶች አባላት በስፋት ከተሳተፉባቸው ጉባኤዎች በኋላ ሁሉም ድርጅቶች የተስማሙበት የጠቅላላ ጉባኤዎች ቃለ ጉባኤና የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ የሰነዱ አጸዳደቅ በአመራር አባላት ብቻ እንዳልሆነና በዴሞክራሲያዊ አሰራር የድርጅቶቹን አባላት በበቂ ሁኔታ በማሳተፍ የተሰራ ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው።
የግለሰብና የብሔር ብሔረሰብና ቡድን መብቶች አከባበር በሚመለከትም ጉዳዩ ከስምምነት ያልተደረሰ አይደለም። በዚህና በሌሎችም የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በመጀመሪያ ለውይይት መነሻ የሆኑ ጥናታዊ ጽሑፎች በግብረ ሃይሉ አባላት እኔም ራሴ በተሳተፍኩበት ተዘጋጅተው ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ከመድረክ አባል ድርጅቶች አባላት ጋር ጭምር ሰፊ ውይይት ከመደረጉም በላይ የግብረ ሃይሉ አባላትም በጥልቀት ተወያይተው “የግለሰብ፤ የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦችና ቡድኖች መብቶች እኩል እንዲከበሩ ሳንታክት እንሰራለን።” በሚለው መርሕ ላይ ካለአንዳች ልዩነት ተስማምተን በፕሮግራሙ ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል። በዚህም መሠረት የግለሰብና የቡድን መብቶች አንዳቸው ሳይከበር ሌላው ሊከበር ስላማይችሉ ሳይነጣጠሉ በተግባር እንዲውሉ ነው የተስማማነው። በወቅቱ ከቡድን መብት ይልቅ የግለሰብ መብት ቅድሚያ ይኖረዋል የሚል አቋም የነበራራቸው የአንድነት አባላትም በውይይቱ በቀረቡት ሀሳቦች በማመናቸው ወደ ጋራ ሃሳብ ማለትም ሁለቱም በእኩልነት ሳይነጣጠሉ በተግባር ላይ እንዲውሉ እናደርጋለን፣ ወደሚለው ሃሳብ መጡ እንጂ ማንም ያስገደዳቸው ወይም ያሳሳታቸው የለም። ወደዚህ ሃሳብ መምጣታቸውንና ፕሮግራሙን መቀበላቸውንም በፊርማቸውና በማሕተማቸው አረጋግጠዋል።
የብሔር ብሔረሰቦች መብትን እስከመገንጠል በፕሮግራሙ አስቀምጦ የነበረው አረና ትግራራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነትም ይህንን ሀሳብ ከፕሮግራራሙ ለማስወጣት በራሱ ፈቃድና ተነሳሽነት በጉባኤው አጽድቆ “መገንጠልን አንደግፍም” ከሚለው የመድረክ ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ አቋም መያዙን በመግለጹ ሁላችንም በመድረክ ፕሮግራም የተቀመጠውን የግለሰብና የቡድን እንዲሁም የብሔር ብሔረሰቦችን መብቶች ካለልዩነት ተስማምተን ነው ያሰፈርነው። ይህ ወደ ሚያቀራርብ መካከለኛ ሀሳብ መሰባሰብና መስማማት ደግሞ ትክክለኛና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ የዴሞክራሲያዊ ድርድር ሂደት መግለጫ ነው ብዬ አምናለሁ።
ከዚህ በላይ በተጠቀሱና በመሳሰሉ በርካታ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያለልዩነት ከስምምነት የተደረሰበት ቢሆንም በሁለት ጉዳዮች ላይ ግን ብዙ ጊዜ ወስደን ብንወያይም ስምምነት ለመድረስ አልቻልንም። እነዚህም ሁለት ጉዳዮች የመሬት ጉዳይና የፌዴራላዊ ክልሎች አከላለልን የሚመለከቱ ነበሩ። በመሬት ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አርሶ አዶሮችና የከተማ ነዋሪዎች መሬት በባለቤትነት የመያዝና የመጠቀም፤ የሚከራዩትና ለፈለጉት ሰው በውርስ በማስተላለፍ መብቶች ላይ ከስምምነት ተደርሶ በፕሮግራሙ ተካትቷል። አርብቶ አደሮችም መሬትን በጋራ ባለቤትነት በመያዝ የመጠቀም መብታቸው በፕሮግራሙ ተካቷል። መሸጥን በሚመለከት ግን አንድነት ለዴሞክራሲያዊና ለፍትህ ፓርቲ መሸጥን ሲደግፍ ሌሎች ፓርቲዎች ግን በአሁኑ የሀገራችን የኤኮኖሚ ዕድገትና ተጨባጭ ሁኔታ መሬትን መሸጥ በተለይም አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮችን ከመሬታቸው ውጭ ሆነው ሌላ የሥራ መስክ ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ወደ ጭሰኝነት ተመልሰው መሬትን በስፋት ለሚገዙ ሰዎች የሥራ ውጤታቸውን እየገበሩ እንዲኖሩ ሊያደርግ ስለሚችል በሕዝቦች ትግል የተወገደውን ፊውዳላዊ ሥርዓት የመመለስ አደጋ ስላለው አንደግፈውም በማለታችን ሳንስማማ ቀርተናል። ስለዚህም ይህ ጉዳይ በልዩነት ተቀምጦ ከተቻለ ወደፊት በውይይት ለመቀራረብና በፕሮግራማችን ለማካተት፣ መቀራራረብ ካልቻልን ደግሞ ሥልጣን በምንይዝበት ወቅት ቅድሚያ ተሰጥቶት ከሌሎች የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሀሳቦች ጋር ለሕዝባችን ቀርቦ ውሳኔ እንዲያገኝ ለማድረግ ተስማምተናል። ሕዝቡ የሚሰጠውን ውሳኔ በፀጋ ለመቀበልም ተስማምተናል።
የፌዴራል ክልሎችን ማካለል በሚመለከትም አንዳንዶች በመልክዐ ምድር ላይ እንዲመሠረት ሲሉ፤ አንድንዶች ደግሞ በሕዝቦች ቋንቋ፣ ባሕላዊና ማህበራዊ ገጽታዎች ላይ የሚል ሌሎች ደግሞ ሁሉንም ማለት መልከዓ ምድራዊ፣ ባህላዊና ማሕበራዊ እንዲሁም ለአስተዳደር ያለውን አመቺነት ባገናዘበና የሕዝቦችን ፈቃደኝነትም ባረጋገጠ መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል የሚሉ አማራጮችን በማቅረብ ሰፊ ውይይቶች ተካሂደው ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቀርተዋል። ይህንንም ጉዳይ ከመሬት መሸጥ ጉዳይ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ከተቻለ ወደፊት በሚደረግ ውይይት በማቀራረብ ወደ ስምምነት ለመድረስና በፕሮግራም ለመካተት ካልተቻለ ግን ለሕዝብ ውሳኔ ለማቅረብ ከስምምነት ተደርሷል። ይህ ሲባል ግን የመንግሥት አወቃቀርን በሚመለከት ምንም ስምምነት አልተደረሰም ማለት አይደለም። በበርካታ የመንግሥት አወቃቀር ጉዳዮችም ላይ ከስምምነት ላይ ተደርሶአል። ለምሳሌም በፕሮግራሙ አንቀጽ 7 ላይ “ሀገራችን የምትከተለው የመንግሥት አወቃቀር በፌዴራልና በክልል መንግሥታት የተመሠረተ ፌዴራላዊ አወቃቀር እንደሚሆን፤ መድረክ በፌዴራል መንግሥትና በክልል መንግሥታት መካከል የሚኖረው የሥልጣን ክፍፍል እና ግንኙነት ትክክለኛውን የፌዴራሊዝም መርሕ የተከተለና በትክክልም ሥራ ላይ የሚውል እንዲሆን ያደርጋል፤ የፌዴራል መንግሥት የሕግ አውጭ አካል በሁለት ም/ቤቶች (Bicameral) ይሆናል፤ በዚህም መሠረት የሕግ መምሪያ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የሕግ መወሰኛ የፌዴሬሽን ም/ቤት የሚባሉ አካላት ያሉት በሕዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች እንዳቋቋሙ ይደረጋሉ፤ የፌዴሬሽን ም/ቤት ከሚሠራቸው ሥራዎች አንዱ በተወካዮች ም/ቤት የሚወጡ ሕጐች ሕግ ሆነው ከመውጣታቸው በፊት በሕገ-መንግሥቱ መሠረት የወጡ መሆናቸውን መርምሮ ማጽደቅ ይሆናል፤ በዚሁም መሠረት በሕግ ማውጣቱ ሥራ የሚሳተፍ አካል ይሆናል፤ ሕገ-መንግሥቱን የመተርጐም ሥራ ከፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ሥራ ይወጣል። በምትኩ ይህንኑ ሥራ የሚሠራ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ይደራጃል የሚሉና የመሳሰሉ በርካታ አሁን ያለውን ሕገ-መንግሥትና አሠራሮችን የሚያሻሽሉ የመንግሥት አወቃቀርን የሚመለከቱ ሀሳቦች ቀርበው በሙሉ ስምምነት በፕሮግራማችን ውስጥ ተካተዋል።
የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች መብት በሚመለከትም ከተደረሰባቸው ስምምነቶች የሚከተሉት ይገኛሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔር ሀገር ነች ቀደምት የሀገራችን አገዛዞች የብሔር ብሔረሰባችን ሕልውና ባለመቀበልና ባለማክበር አምባገነናዊ አሃዳዊ አገዛዝ በማስፈናቸው አገዛዞቻቸው ለሀገራችን ሰላም መታጣትና አለመረጋጋት አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ አገዛዝም በአፋኙ አሃዳዊ አገዛዝ ፋንታ መገንጠልን ጨምሮ የብሔር ብሔረሰቦች መብቶች የሚከበሩበት ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ እውን አደርጋለሁ ቢልም በተግባር ግልጽ ሆኖ የታየው ግን ሥርዓቱ እውነተኛ ፌዴራላዊም ዴሞክራሲያዊም አለመሆኑ ነው፤ በብሔር ብሔረሰብ መብት መከበር ሽፋን ተግባራዊ እየሆነ ያለው ከፋፍሎ መግዛት ነው፤ በዴሞክራሲ ስም በሀገሪቱ ሰፍኖ ያለውም የዜጎች መብቶች አፈና ነው፤ ቀደምቶቹም ሆኑ የአሁኑ የአፈና አገዛዞች የብሔር ብሔረሰቦች መብት የተከበረበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሀገራችን እንዳይኖር ማድረጋቸው የሀገራችን አንድነት ስጋት ላይ እንዲወድቅ አድርገዋል፤ በመሆኑም በዚህ መድረክ የተሰበሰብነው ሃይሎች እስካሁን ከታዩት አካሄዶች በመማር እና የታዩትን ስህተቶች በማረም በሀገራችን የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትና መከባበር የሰፈነበት ዘላቂ አንድነት ይረጋገጥ ዘነድ እንታገላለን የሚሉና የብሔር ብሔረሰቦች ማንነታው ቋንቋቸውና ባህላቸው እንዲሁም ታሪካቸው በእኩልነት የሚከበሩባቸው መርሖዎች እንዲሁም በአካባቢያቸው ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር ያላቸው መብት የሚከበር መሆኑን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲንም ጨምሮ ያለአንዳች ልዩነት በሙሉ ስምምነት አጽድቀነዋል። በዚህ ላይ ከስምምነት ሳይደርስ የቀረ አንድም ነጥብ የለም። ምናልባት አሁን ከተስማማንበት አቋም ለመንሸራተትና የአቋም ለውጥ ለማድረግ ካልታሰበ በስተቀር።
ታዲያ እውነቱ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይቶች ተደርገው ስምምነት የተደረገበት ሆኖ ሳለ እጅግ በርካታ መሠረታዊ በሆኑ የሀገራችን ጉዳዮች ላይ በስምምነት ተግባብተው ለመሥራት የወሰኑ ብሔራዊና ሕብረ-ብሔራዊ ፓርቲዎችን ተስማምተው ሊሠሩ የማይችሉ “ውሃና ዘይት ናቸው” በማለት ለአንድነት ለዴሞክራሲያዊ ለፍትሕ ፓርቲ ይጠቅማል ብለው አንዳንድ የፓርቲው የብሔራዊ ም/ቤት አባላት ከመድረክ የመውጫ (Exit) ስትራራቴጂ  ሚያዝያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም በታተመው የፍትሕ ጋዜጣ “የመድረክ ከየት ወዴት” በሚል አርእስት ሥር በተዘጋጀው ፅሁፍ ጠቁመው ነበር። በወቅቱ ጋዜጣውን ፎቶ ኮፒ አድርጌ ለአንድነት ተወካዮች ሰጥቼ ነበር። ሚያዝያ 23/2005 በታተመው የሰንደቅ ጋዜጣ ደግሞ ስለመድረክ መፍረስ ከንቱ ሕልም በማለም እንዲሁም ሰሞኑን በታተሙት የቆንጆ መጽሄት ላይና በኢትዮ ምሕዳር ጋዜጣ እትሞች መድረክ መፍረስ አለበት እያሉ የባጥ የቋጡን በማውራራት ላይ ይገኛሉ። የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የብሔራዊ ም/ቤት አባላት አዲስ የጥናት ግኝት ያገኙ ይመስል ለገዥው ፓርቲ ለኢሕአዴግ ካልሆነ በስተቀር ለመድረክ፣ ለአንድነትም ሆነ ለሀገራችን ሕዝቦች በአጠቃላይ የማይጠቅም ወሬ ሲያናፍሱ እየተመለከትናቸው ነው። እርግጥ መድረክ ሁሉም አባል ድርጅቶች በፈቃዳቸው አባል የሆኑበት ግንባር ስለሆነ ማንኛውም አባል ድርጅት አንድነትንም ጨምሮ ከመድረክ ለቆ መውጣት ከፈለገ መብቱ የተጠበቀ ነው። ከዚህ አልፎ ግን “መድረክ መፍረስ አለበት” ብሎ ማቅራራታቸው “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ያለችው እንሰሳ አይነት አስተሳሰብ ይመስላል። ሚያዝያ 2004 ዓ.ም የጠቆሙትና ከሚያዝያ 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሰሞኑን በማካሄድ ላይ ከሚገኙት አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ግልጽ የሆነው ነገር የመውጫ ስትራቴጂያቸው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሥርዓት ባለው መልኩ በሰላም ከመድረክ የመሰናበት ሳይሆን በእኩልነት ተደራድረን ከደረስንባቸው ስምምነቶች ውጭ ልክ እንደ ሕወሐት የራሳቸውን ሙሉ ፕሮግራም በመድረክ አባል ድርጅቶች ላይ መጫን ካልተሳካላቸው መድረክን አፍርሰው ለመሄድ በፍጹም የማይሳካላቸውን ምኞት እየተመኙ እንደሆነ ነው። ይህ መቼም ምን ያህል ትዕቢት የተሞላበት ብልግና እንደሆነ አንባቢያን ይረዱታል ብዬ አምናለሁ።
መድረክ እንደ ኢሕአዴግ አንድ አምባገነን የፖለቲካ ፓርቲ ሕወሐት ከሥሩ ተቀጥላ ፓርቲዎችን ፈጥሮ የራሱን የፖለቲካ ፕሮግራም ከሀ እስከ ፐ አስገልብጦ በመስጠት ለጋራ ግንባራቸውም የዚያው አምባገነን ፓርቲ ትክክለኛ ግልባጭ ከስሙ በስተቀር ማለት ነው በማስጨበጥ የተፈጠረ ግንባር አለመሆኑና ነፃና የየራሳቸው አደረጃጀትና አመለካት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ነፃ ፍላጎት ተቀራርበው በሚስማሙባቸው ፖሊሲዎችና የጋራ ሀገራችን ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት የፈጠሩት ግንባር መሆኑን መቼም አንዳንድ የትናንትናዎቹ የኢህአዴግ የወጣት ክንፎችና የአሁኖቹ የአንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትሕ ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባላት ሳይቀሩ በሚገባ ያውቃሉ ብዬ አምናለሁ። ታዲያ ከገዥው ፓርቲ ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ መግባት መብታቸው መሆኑን ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በታተመው በሰንደቅ ጋዜጣ የገለጹትና እኛም ይህንኑ መብታቸውን በጥብቅ የምናከብርላቸው እነዚህ ሰዎች ሊያውቁት የሚገባቸው መሠረታዊ መብት እኛም ከኢህአዴግ የተለየ ማለትም ፕሮግራምን ከአንድ አምባገነን ፓርቲ ሙሉ ቅጂ ያልወሰደ ግን የምንስማማባቸውን አብዛኛዎቹን ጉዳዮች ያካተተና የተለያየንባቸውን ጥቂት ጉዳዮች ደግሞ በተመቸን ጊዜ በዴሞክራሲያዊ“ እኩልነታችንና ነፃነታችን በተከበረ መልኩ በረጋ ሁኔታ ተወያይተን ከተቻለን ለመስማማቱ ካልተቻለን ደግሞ ለሕዝብ ውሳኔ አቅርበን ሕዝቡ በሚወስነው ለመገዛት ተስማምተን ሕብረ ብሔራዊና ብሔራዊ ፓርቲዎችን ያቀፈ ከኢህአዴግ በይዘትም ሆነ በቅርጽ የተለየ ግንባር ለመፍጠር ዴሞክራሲያዊ መብት ያለን መሆናችንን ነው። ስለዚህ ይህንን ነፃ መብታችንን በመጣስ በኢህአዴግ የግንባር ምሥረታ ሞዴል እንድንመራ ሊያስገድዱንና ከኢሕአዴግ ሞዴል የተለየ የግንባር ምሥረታ ሁሉ ስህተት እንደሆነ በማስመሰል በሚያወሩት መሠረተ ቢስ ፕሮፓጋንዳቸው ሕብረተሰቡን ለማሳሳት መሞከር የለባቸውም ብዬ አምናለሁ። እነርሱ በኢሕአዴግ ሞዴል ለመምራት ፍላጎት ካላቸው ግን ለራሳቸው ብቻ ሊመርጡትና ሊጠቀሙበት መብታቸው ነው። በአለም ዙሪያ ተደራጅተው የሚንቀሳቁ ፓርቲዎች ግንባር ሲፈጥሩ የሚስማሙባቸውንና የሚለያዩባውን ጉዳዮች ለይተው ያልተስማሙባቸውን ወደጎን በመተው የተስማሙባቸው” ጉዳዮች በጋራ ሥራ ላይ ለማዋል እንደሚንቀሳቀሱ ግንዛቤ የሌላቸው ወይም ሆን ብለው ሕዝብን ለማሳሳት የመድረክ ግንባርነትን የሚተቹ እነዚህ ሰዎች መድረክ ለምን እንደ ኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና ግንባር በሁሉም ነገር አንድ ግልባጭ ፕሮግራም አይኖረውም? ይህ ካልሆነ ወደ ግንባር መሸጋገሩ ስህተት ነውና መፍረስ አለበት በሚል አስተሳሰብ ስለግንባር አመሠራረት ባላቸው ቁንጽልና የተሳሳተ ግንዛቤ ሕዝባችንን ግራ ለማጋባት ያዙን ልቀቁን ሲሉ ይታያሉ። በዚህ አስተሳሰብና አቀራራረባቸው ከሚወሰኑ ይልቅ የኢህአዴግን ብቻሣይሆን በተለያዩ ሀገሮች ፓርቲዎች የሚፈጥሩዋቸውን ግምባሮች በሚመለከት ሰፊ ጥናት አድርገው ሰፋ ያለ ዕውቀት ለራሳቸውም ሆነ ለሕዝባችን ለማቅረብ ቢዘጋጁ የተሻለ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ሰለ ግንባር ምንነት ያላቸውን ግንዛቤ ትንሽ ሰፋ ቢያደርጉ የኢህአዴግን የመሰለ ግንባር ካልፈጠራችሁ መፍረስ አለባችሁ ከሚለው ፀረ ዴሞክራሲያዊ አቋማቸው ይታረማሉ ብዬም እገምታለሁ።
ግንባር መመሥረት የሚያሳየው መጀመሪያውኑም ቢሆን የተወሰኑ ከስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች መኖርን ነው እንጂ በሁሉም ጉዳዮች መስማማትን አይደለም። በሁሉም ነገሮች ከተስማሙ በኋላ መነሳት ያለበት የውሕደት ጥያቄ ነው። የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላትም ሆኑ መላው ሕዝባችን እንደሚያውቀው የመድረክ አባል ድርጅቶች በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ተስማምተን በጥቂት ጉዳዮች ላይ አሁንም ልዩነታችንን እስከያዝን ድረስ መመሥረት ያለብን ትክክለኛው ጥምረት ግንባር ነው መሆን ያለበት። የተስማማንባቸው ጉዳዮች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ተሠርተው የሚጠናቀቁ ሥራዎች ሳይሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ በጋራ ተሰልፈን እንድንታገል የሚጠይቁን ስለሆነ ከቅንጅት ይልቅ የግንባር አደረጃጀትን የሚሹ ናቸው። እኛም በዚህ እውነታ ላይ ተመሥርተን ነው ከቅንጅት ይልቅ የግንባር አደረጃት ለጋራ ዓላማዎቻችን መሳካት  የሚመጥን ስለሆነ ግንባርን የፈጠርነው። ስለዚህ መድረክ በተወሰኑ ጥቂት ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ሳይደርስ ግንባር መሆኑ ትክክለኛና ከኢሕአዴግ በስተቀር ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችም የሚያረጋግጡት የግንባር አደረጃጀት ጉዳይ ነው። ሙሉ በሙሉ በምንስማማበት ወቅት ወደውሕደት እንደምንደርስና ለዚህም ደረጃ በደረጃ እየሠራራን እንደምንቆይ የመድረክ አባል ድርጅቶች እምነት ነው። በእኛ በኩል “ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።” እንደሚባለው በችኮላ ሳይሆን ቅድሚያ የሚሰጡ የጋራ ሥራዎችን ቅድሚያ እየሰጠን በዚህም ጉዳይ ላይ በሰከነ መንፈስ መወያየታችንን አልተውንም። የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላትም እንደሚያውቁት በቅርቡ የተካሄደው የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ትኩረት ሰጥቶ ከተወያየባቸውና ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መመሪያ ከሰጠባቸው አበይት ጉዳዮች ዋነኞቹ የሀገራችን መሠረታዊና ወቅታዊ ችግሮችን ለመፍታት አቅጣጫ ጠቋሚ ሆኖ ተዘጋጅቶ የቀረበውን ማነፌስቶ አጠናቆ ሕዝቡን በማወያየት የትግል እንቅስቃሴ እንዲደረግበትና ከዚህ ጐን ደግሞ በሚገኘው ጊዜ ውስጥ ባልተጠናቀቁ የፕሮግራም ልዩነቶችም ላይ ውይይት እየተደረገ ለማቀራረብ ሙከራ እንዲደረግ ነው።
መተዳደሪያ ደንባችንን በሚመለከት ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተካሂዶባቸው ከስምምነት ላይ የተደረሱ ጉዳዮች ተካተውበት ደንቡ በጉባኤው ውሳኔ መሠረት እንዲሻሻል ተደርጐ ለምርጫ ቦርድ ከገባ የተወሰኑ ወራቶችን አስቆጥሮአል። ለወደፊትም በሚካሄዱ ውይይቶች ተጨማሪ ማሻሻያዎች ይደረግበታል የሚል እምነት አለኝ። በሰከነ ውይይት ለመፍታት የምንሞክራቸውን ልዩነቶች አሁኑኑ በጥብጠው በማጠጣት ሊያስወጡን ስሜታዊና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ፉከራ የሚያሰሙት የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላት የሆኑ “አለን አለን” ባዮች ስሜታዊ ሩጫዎች አፍራሽ እንጂ ገንቢ አይደለምና ከአፍራሽ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል። የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የተግባር ኮሚቴዎች ይህንን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ ደፋ ቀና በሚሉበት ጊዜ ውስጥ እኛና ሕዝባችን በማኒፌስቶአችን ሀሳቦች ላይ አተኩረን እንዳንቀሳቀስ ለማድረግ አዲስ የጥናት ግኝት ያገኙ ይመስል ጋዜጦችንና መጽሄቶችን እኛ ለብዙ ጊዜ ስንወያይበት በቆየነውና አሁንም ባላቋረጥነው ጉዳይ በመሙላት የአደናቃፊነት መራወጥ ማሳየት ቆብ ቀዶ ከመስፋት ያለፈ ፋይዳ ያለው ሥራ አይደለምና ዓላማውም መድረክ ከተያያዘው ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ላይ የሕዝብን አመኔታ ለመሸርሸርና ለማደናቀፍ የማይሳካ ሙከራ ማድረግ ብቻነው የሚመስለኝ።
በበኩሌ እኔ መድረክ ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ በአመራርውስጥ ያለሁና በተለይም ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ግብረሃይል ፀሐፊ ሆኜ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ቃለ-ጉባኤዎች” በመያዝ በውይይት ወቅት የተከናወኑ ሥራዎችን ስለሚያውቅ እነዚህ የተረሱ ጉዳዮችን ያስታወሱን ይመስል ዛሬ “መድረክ መፍረስ አለበት” እያሉ ቡራ ከረዩ የሚሉ የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላት የሚያነሷቸው ጉዳዮች ስሰማ በጣም ይገርመኛል። ምክንያቱም ጉዳዮቹ በቂና ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው በስምምነትና ልዩነት የተቀመጡ እንጂ ዝም ብለው ወይም ተረስተው የተዘለሉ አይደሉምና ነው። ከላይ እንደ ጠቆምኩትም በመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ተገምግመው ውሳኔ የሰጠባቸውና ቀጣይ የአፈጻጸም ጥረት ብቻ የሚጠይቁ እንጂ ምንም አዲስ ግምገማና ጥናት የሚያስፈልጋቸውም አይደሉም። ምክንያቱም የታወቁና በጠቅላላ ጉባኤም የተገመገሙ ናቸውና። ሳይገመገም የቀረ ነገር አለ እንኳ ቢባል በተወካዮቻቸው አማካይነት ለሚመለከተው የመድረክ አካል በማቅረብ የሌሎችም አባል ድርጅቶች ተወካዮች ባሉበት በጋራ ማስገምገም ሲገባ ከመድረክ ጀርባ ግምገማ ለምን ያስፈልጋል? ታዲያ ተገቢውን የመድረክ የግምገማ አሰራር ሳይከተሉና ሳይገመግም የቆየ አንዳች ጉዳይ እንኳ ሳይዙ ሚዲያ ላይ በመውጣት በመድረክ ላይ አፍራሽ ትችቶችን እያስተጋቡ እዩኝ እዩኝ ማለት ቆብ ቀዶ በመስፋት የሥራ ችሎታንና ብቃትን ለማሳየት የሚቻል መስሎአቸው የሚያደርጉት ከንቱ ሙከራ ነውና ፋይዳ የሌለውና ገንቢ ሊሆን የማይችል ሥራ ነው።
ይልቁንም እነዚህ ሰዎች የራሳቸውንና የእኛንም ወርቃማ ጊዜ በከንቱ ከሚያባክኑብንና ሕዝባችንንም ግራ በማጋባት ሥራ ላይ ከሚሠማሩ በጋራ ጠቅላላ ጉባኤአችን የፀደቀውን የትግል አቅጣጫ አመላካች ማኒፌስቶአችንን ለሕዝባችን አቅርበን ለማወያየትና ሥራ ላይ ለማዋል ገዥው ፓርቲ ከፊታችን የደቀነብንን መሰናክሎች ተባብረን በመጋፈጥ ተጨባጭ የትግል ውጤት በሚያመጡ ሥራዎች ላይ የሚሰማሩበት ወኔ ቢኖራቸውና ለዚህም ቢዘጋጁና ቢሠማሩ ቁም ነገር መሥራት ይሆናልና ለዚሁ ቀና ሥራ እንዲሰለፉ የበኩሌን ሀሳብ አቀርብላቸዋለሁ:: ይህንን ቀና ሀሳብ የማትቀበሉና ከአፍራሽ ፕሮፓጋንዳችሁ የማትታቀቡ ከሆነ አገልግሎታችሁ ለማን እንደሆነ ግልጽ ነውና ምርጫችሁን ብታስተካክሉና ግልጽ ብታደርጉ ጥሩ ይመስለኛል የመድረክ ትግል በእኛ መኖር አለመኖር ይወሰናል ብላችሁ ገምታችሁ ከሆነ በጣም ተሳስታችኋል:: መድረክ ያለእናተም ቢሆን የያዘውን ሕዝባዊ ዓላማ ይዞ በጽናት ትግሉን እንደሚቀጥል በፍጹም ጥርጥር ሊገባችሁ አይገባም። ምክንያቱም አንድ ድርጅት ከውስጡ የሚታረሙ ቦርቧሪዎችን በጸዳ ቁጥር የበለጠ እየተጠናከረ ይሄዳል እንጂ አይዳከምምና። መድረክም ዓላማውንና ፕሮግራሙን እናንተ ብትለዩት ሜዳ ላይ ጥሎ የሚጠፋ ድርጅት አይደለምና።
ይህንን የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላት አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ስላገኛችሁ ሰሞኑን ልባችሁ ቅቤ ጠጥቶ መድረክ አይሰነብትም በማለት ጮቤ እየረገጣችሁ የማይሳካ ሟርታችሁን በማሰራጨት ላይ ያላችሁ የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዲስቶችም የራሳችሁ ድርጅት በየጊዜው የገባበትን ከዚህ ችግር እጅግ የባሰ ማጥና ከዛ ለመውጣት ያደረጋቸውን መፍጨርጨሮች ብታስታውሱ እንደዚህ አይነት ጉዳዮች በናንተም ሆነ በማንኛውም ድርጅት የሚከሰት መሆኑን ትረዳላችሁ። በአምባገነንነተና በአንድ ድርጅት የበላይነት የሚፈጠር የእናንተ አይነት ግንባር ካልሆነ በስተቀር ሌላው ሁሉ የሚፈርስ መስሏችሁ ከሆነ ሟርታችሁ መና ሲቀርና መድረክ የበለጠ ተጠናክሮ ጉዞውን ሲቀጥል ተገቢውን ትምህርት ትቀስማላችሁ ብዬ እተማመናለሁ። ከተጨባጭ ሁኔታ መማር የምትችሉ ከሆነ ማለቴ ነው። እስካሁን ያልተረዳችሁትና በዚህ አጋጣሚ በሚገባ የምትረዱት ይሆናል ብዬ የማስበው ነገር ቢኖር መድረክ ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ከተሰባሰቡት የኢሕአዴግ አባላት እጅግ የላቀ የዓላማ ጽናትና የሞራል ጥንካሬ ያላቸው ታጋዮች ባለቤት የሆነ ድርጅት መሆኑን ነው። ስለዚህ እናንተ እንደምትገምቱትና እንደምታሟርቱበት ሳይሆን ዓላማቸውን በሰላማዊ ትግል ከግብ ለማድረስ ፀንተው በመታገል በእንደነዚህ አይነት ክስተቶች የማይበገሩ አባላት ያሉበት ድርጅት ችግሮች ሲያጋጥሙት የበለጠ ይጠናከራል ባትሳሳቱ ጥሩ ነው። ስለዚህ መድረክ አይሰነብትም በማለት የማይሆን ሟርት በማሰራጨት ጊዜአችሁን ብታባክኑም አይሳካላችሁምና ሌላ ሥራ ብትሠሩ ይሻላል እላለሁ።
ሌላው እነዚሁ የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላት በመድረክ ላይ የከፈቱት አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ስለግንባሩ መተዳደሪያ ደንብና ስለአመራሩ ዴሞክራሲያዊ አለመሆን ነው። እንዲያውም “ኢዴሞክራሲያዊ ነው” በማለት የሚያናፍሱት ፕሮፓጋንዳም ውስጡ ባዶ የሆነ ፕሮፓጋንዳቸው ነው። በመድረክ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የግንባሩ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ከየድርጅቶቹ የሚወከሉ አሥር አሥር አባላት የሚሳተፉበት ሲሆን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ደግሞ ከየድርጅቶቹ የሚወከሉ ሁለት ሁለት ሰዎች የሚሳተፉበት ነው።
የጉባኤውና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ለወደፊቱ ቢያንስ በእጥፍ እንዲጨምር ለማድረግም እየተወያየንበት ነው። ከዚህ የበለጠ ለማድረግ በሁላችንም በኩል ፍላጐቱ ያለ ቢሆንም ችግራችን ጉባኤአችን ለማካሄድ የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ መሆኑን ብቻነው። አባል ድርጅቶች በማንኛውም ወቅት ተወካዮቻቸውን መቀየር ይችላሉ። የግንባሩ ሊቀመንበር ብቃትና ችሎታን መሠረት ባደረገና የአባል ድርጅቶችን እኩል ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ በየዓመቱ ይመረጣል ይላል። ደንቡ አንድ ሊቀመንበር ጉባኤው ከፈቀደለት ለአንድ ዓመት ለአንድ ጊዜ ብቻ ኃላፊነቱን ይዞ ሊቀጥል ይችላል። ከዚያ በላይ ሊቀመንበር ሆኖ መቆየት አይችልም። መጀመሪያውንም ብቃቱ በራሱ ድርጅት ተገምግሞ በድርጅቱ አማካይነት በዕጩነት ይቀርባል። ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ ቆይቶ አምባገነን ሊሆን የሚችልበት ዕድልም በደንቡ ውስጥ በጭራሽ የለም። ታዲያ ይህ ከዚህ በላይ የተገለጸው አሰራር በምን ተአምር ነው ፀረ -ዴሞክራሲያዊ ተብሎ የሚነገረው። እነዚህ ተችዎች በድርጅታቸው ውስጥ በሚያሳዩት ሐቀኛና ቅን ተሳትፎ በራሳቸው ድርጅት አማካኝነት ብቁ ናቸው ተብለው በዕጩነት ሳይቀርቡ የመድረክ ሊቀመንበር ወይም ሥ/አ/ ኮሚቴ አባል ሊሆኑ የሚችሉበት አድል በእርግጥ የለም። በመጀመሪያም ሐቀኛና ቅን ታጋዮች መሆናቸውን በተግባራዊና ቅን ተሳትፎ በድርጅታቸው ውስጥ ማሳየት የተሳናቸው ሰዎች በአቋራጭ ሊቀመንበር ወይም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆንና ለረጅም ጊዜም በአመራር ላይ ለመቆየት ተመኝተው ከሆነ መንገዱ የትግል እንጂ በብልጣብልጥነት ሥልጣን ላይ ወጥተው የሚኮፈሱበት አይደለም። ሥልጣን ይዘው ለረጅም ጊዜ ለመቆየትና አምባገነናዊ አመራር ለመፍጠርም ዕድል አይሰጥም። ይህንን መንገድ መከተልን ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ነው፤ እንደ ኢህአዴግ መሪዎች ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ አይቆይም የሚሉ ከሆነ ስለዴሞክራሲያዊ ግንባር አደረጃጀትም ሆነ አመራር ተገቢ ግንዛቤ የሚጎድላቸው ስለሆነ ራሳቸውን ሊያስተካክሉና በትክክለኛው የታጋይነት አቅጣጫ ሊመጡ ይገባል። በትክክለኛው አቅጣጫ ከመጡና የድርሻቸውን አበርክተው ለሌላ ለማስረከብ ከተዘጋጁ ግን በሩ ለእነርሱም ቢሆን ክፍት ነው።
ከዚህ አልፈው ደግሞ በመድረክ ውስጥ ያልታየና የማይታወቀውን በልመና ሊቀመንበር ስለመሆን በሰንደቅ ጋዜጣ አንስተዋል። ይህ መቼም ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ በትክክል በመድረክ ውስጥ ቢኖር ኖሮ እውነት ሊመስል ይችል ነበር። ነገሩ ግን የመድረክን ሁኔታ በትክክል የሚያውቁትን ሰዎች ለማጭበርበር ተብሎ የቀረበ መሠረተ ቢስ ወሬ ነው። ምክንያቱም የመድረክ አመራር አባልነት ወይም ሊቀመንበርነት ታጋዮች ለቆሙለት ዓላማ ዕውቀታቸውን ጉልበታቸውንና ጊዜአቸውን ገንዘባቸውንም ጭምር መስዋዕት የሚያደርጉበት በተለይም ድርጅቶቻቸው የሚሰጡአቸውን የውዴታ ግዴታ ውክልና መወጣት ግዴታቸው ሆኖ የሚቀበሉት ጉዳይ እንጂ ቅንጣት ታህል የራራሳቸው ጥቅም የሚያገኙበት ቦታ አይደለም። ስለዚህ ካለአንዳች ክፍያ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡበት እንጂ የሚቀራመቱት ጥቅም ኖሮ አንዱ ለማኝ ሌላው ተለማኝ  የሚሆንበት ቦታ አይደለም። ለመሆኑ ማን ማንን ይለምናል? ለምንስ ብሎ ይለምናል? የሚለመነውስ ምን ሊሰጥና ሊጠቅም ወይም ምን ስለሆነ ነው? የሚለመነው? አንዳች የጥቅም መቀራመት በሌለበት ቦታ ፈቃጅና ከልካይ የሆነ የተለየ ስልጣን ወይም ሃይል ያለው አካል በሌለበት ቦታ ለማኝም ሆነ ተለማኝ በፍጹም ስለማይኖር መድረክ ውስጥ እንደዚህ አይነት ነገር በፍጹም ሊኖርም አይችልም። የለምም። ከዚህ ሌላ አንድም ለሊቀመንበርነት የታጨ ሰው እርሱ ብቃት የለውም ተብሎ “እባካችሁ ምረጡኝ” ብሎ የላመነበት ጊዜ የለም። እኔ በተመረጥኩበት ዕለት ስለመተዳደሪያ ደንቡ መሻሻል ቤቱ በስፋት ከመነጋገሩ በስተቀር በግለሰብ ደረጃ ስለእኔ ብቃት ተነስቶ የተተቸበት ሁኔታ በፍጹም አልነበረም። ለመተቸት ግን የሚከለክል ነገር አልነበረም። ከዚህም ሌላ አንድ ሊቀመንበር በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ በአመራሩ ደካማ ሆኖ ከተገኘ በዓመቱ አጋማሽ ላይ በሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ተገምግሞ በሌላ ሊተካ ይችላል። የአንድነት ም/ቤት አባላት ይህንን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ ቢጠቀሙበት እንጂ በጋዜጦች ላይ መሠረተቢስ ወሬ ቢያወሩ ብቃት ያላቸውም ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ሊያሰኛቸው አይችልም። በዕለቱ የተተቸው መተዳዳሪ ደንቡ ስለነበር በራሱ ሰብሳቢነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከጠቅላላ ጉባኤው በተሰጠው መመሪያ መሠረት አሻሽሎት በዓመቱ አጋማሽ ላይ ለተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ማሻሻያው ሊፀድቅና ለምርጫ ቦርድም ሊተላለፍ ችሎአል። ደንቡን ለወደፊቱም ጉባኤው ለማሻሻል የሚያግደው ነገር የለም። በዚህ መሠረት በመድረክ ውስጥ የመተዳዳደሪያ ደንብ የአመራርውክልና አመራረጥም ሆነ አሰራር ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ችግር ሳይሆን እነዚህ ግለሰቦች የሚያወሩት የራሳቸውን ሕልምና ቅዠት ነው።
ሌላው የድርጅት አባልነትን በሚመለከት በአባል ድርጅቶች ሙሉ ስምምነት የሚለው ሀሳብም እስካሁን ሐቀኛና ብቃት ያለው ተቃዋሚ ድርጅት አባል ሆኖ ለመመዝገብ ሲጠይቅ አንድ ድርጅት ብቻውን ውድቅ ያደረገበት አሰራርና ወቅት እስካሁን በፍጹም አልተከሰተም። ፎርማል የሆነ የአባልት ጥያቄ ጠይቆና የአባልነት መመዘኛዎችን አሟልቶ ከላይ በተጠቀሰው የድምፅ አሰጣጥ ምክንያት አባል ሳይሆን የቀረ ድርጅት በሌለበት ዝም ብሎ ለወሬ ብቻ ይህ ደንብ መድረክ በአንድ ድርጅት ድምፅ መወሰን አቅቶት አባላትን እንዳይጨምርና እንዳያድግ አድርጓል ብሎ ማውራት “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” ነውና አሁንም እነዚህ ሰዎች ወደተጨባጩ ዓለም መጥተው ቁም ነገር ላይ በማተኮር ተጨባጭ የሆኑ የመድረክም ሆነ የአባል ድርጅቶች ችግሮች የሚቀረፍበት ሁነኛ ስራ ላይ ቢሠማሩ ይጠቅማቸዋል ብዬ አምናለሁ። በዚህ ረገድ በተጨባጭ ችግር በሥራ ላይ ቢያጋጥም ግን ችግሮችን ገምግመን ደንቡን ለማሻሻል የሚያግዳቸው ነገር የለም። ስለዚህ በተግባር ያልታየን ችግር አየር በአየር ማውራቱ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም።
የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት አባላት ሰሞኑን የግምገማ ሪፖርት ብለው ባዘጋጁት ሰነድም ቀደም ብሎ ድርጅቱ በድርድር የተስማማባቸውን ሀሳቦች ሁሉ የሚንዱና ስምምነቶቹን ሁሉ በሚያፈራርሱ መከራከሪያዎች የታጨቀ የመድረክ የግምገማ ሪፖርት የሚባል ሰነድ ከመድረክ አባል ድርጅቶች በስተጀርባ ሠርተው ካጠናቀቁ በኋላ ይፋ አድርገዋል። መድረክ ራሱ አንድነትም በሚሳተፍባቸው አካላቶቹ አማካይነት የሚገመግምበት አሰራር እያለ ያንን መጠቀም ትተው ለብቻቸው ለመገምገም የፈለጉበት ምክንያት ከሰዎቹ የግልጽነት ጉድለትና በራስ ያለመተማመን ችግራቸው የመነጨና ለገዥው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ ለማቀበል ከመጣደፋቸው ጋር የተያዘ ነው። ስለዚህ ከመድረክ በስተጀርባ ተሠርቶ “ቆብ ቀዶ የመስፋት” አይነት ወሬ ከሚዘበዝበው ሪፖርታቸው ፋይዳ ያለው አዲስና ገንቢ ሀሳብ ስለማይገኝ መድረክ እስከአሁን ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ ለወደፊቱም እራሱን የሚገመግምበት አሰራር ሥራ ላይ በማዋል ያሉበትን ጠንካራ ጐኖች በማጐልበት ደካማ ጐኖችን ደግሞ በማረም የተያያዘውን የዴሞክራራሲና የፍትሕ ሥርዓት የመገንባት ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል። የመድረክ ግምገማ ባሉት ሪፖርቸው ውስጥ ስለታጨቁት አፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎች ወደፊት በዝርዝር ስለሚጻፍበት ለዛሬው በጋዜጦችና መጽሔቶች ሰሞኑን በመድረክ ላይ ስለተነዛው መሰረተ ቢስ ወሬ ብቻ በማብራራት ጽሑፌን ለማብቃት እፈልጋለሁ።
የተከበራችሁ አንባቢያንና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በእነዚህ ግለሰቦች አማካይነት መድረክ በሕዝባችን ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ለመሸርሸር በማለም በመድረክ ፕሮግራሞች መተዳደሪያ ደንብና በአመራሩ ላይ እየተካሄደ ያለውን መሠረተቢስ ፕሮፓጋንዳ ብናወግዝም በመድረክ ላይ የሚታዩትን ትክክለኛና ተጨባጭ የሆኑትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት ድክምታችንን እንድናርም በጥንካሬአችንም እንድንበረታ የሚሰጠንን ገንቢ አስተያየት በአክብሮት የምንቀበል መሆናችንን እየገለጽኩ እንደዚህ አይነት አፍራሽ ሥራዎች ላይ የሚሰማሩ ሰዎችና ሥራቸው በትግል ሂደት የሚከሰቱ ጉዳዮች ስለሆኑ በፕሮፓጋንዳቸው ግራ ሳትጋቡ መድረክ የሀገራችንን መሠረታዊና ወቅታዊ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫዎች ማኒፌስቶ ላይ ያስቀመጣቸውን የመፍትሔ ሀሳቦች ከግብ ለማድረስ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ ማበርከታችሁን በጽናት እንድትቀጥሉበት በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።


አያት አክሲዮን ማህበር ላይ የ90 ሚልየን 81 ሺህ 270 ብር ቅጣት – አመራሮቹ ከ10 እስከ 12 አመት እስራትና እስከ 90 ሚልየን ብር ተቀጡ

$
0
0

በ21 ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈበት የአያት አክስዮን ማህበርና አመራሮቹ ዛሬ ከ10 እስከ 12 አመት በሚደርስ ጸኑ እስራትና እስከ 90 ሚልየን ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ተጣለባቸው።

ከዛሬ ሶሰት ዓመት በፊት የተከሰሱት 1ኛ ተከሳሽ አያት አክስዮን ማህበር ፣ የማህበሩ ስራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢው አቶ አያሌው ተሰማ ፣… ዶክተር መኮንን አካሉ እና አቶ ጌታቸው አጎናፍር ናቸው የተቀጡት። ከክሶቹ መካከል የገንዘብና የባንኮችን አዋጅ መጣስ የሚለው ቀዳሚው ነው ።

ማህበሩ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማትን በተደራጀ መልኩ በመተካት የዱቤ ቤት ሽያጭ አገልግሎት አከናውኗል የሚለው በክስ መዝገባቸው በዝርዝር ቀርቧል። በመሆኑም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርደ ቤት 8ኛው የወንጀል ችሎት በእነዚህና በሌሎች ጥፋቶች ፥ አያት አክሲዮን ማህበር ላይ የ90 ሚልየን 81 ሺህ 270 ብር ቅጣት ወስኖበታል።

እንዲሁም የማህበሩ ስራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አያሌው ተሰማ ደግሞ ፥ በ12 አመት ጽኑ እስራተ እና ከ3 ሚልየን ብር በላይ የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

ዶክተር መኮንን አካሉ በ12 አመት ጽኑ እስራትና ከ436 ሺህ ብር በላይ ፥ እንዲሁም አቶ ጌታቸው አጎናፍር ላይ ፍርድ ቤቱ የ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና የ411 ሺህ 969 ብር ቅጣት ወሰኗል።

ችሎቱ ድርጅቱ ያለአግባብ ሰብስቦ ከአከማቸው ገንዘብ ከ86 ሚልየን ብር የሚበልጠው እንዲወረስም ወስኗል።

አክስዮን ማህበሩና ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አያሌው በ21 ክሶች ያካበቷቸው 15 የሚሆኑ የተለያ አገልግሎት የሚሰጡ የግንባታ መሳሪያዎች እንዲወረሱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል። አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ)


Woolwich attack: Watch brave mum tell how she confronted terrorist after soldier had been hacked to death

$
0
0

Ingrid Loyau-Kennett was passing the  scene on a bus but jumped off to rush to the aid of the murdered soldier…..

Courageous: Ingrid Loyau-Kennett talks to knifeman

Courageous: Ingrid Loyau-Kennett talks to  knifeman
Twitter/@dannymckiernan

A mum-of-two has told how she confronted one of the Woolwich  terrorists and tried to persuade him to hand over his weapons.

Courageous Ingrid Loyau-Kennett was passing the scene on a bus but jumped off  to rush to the aid of the stricken soldier.

The 48-year-old told ITV’s Daybreak she initially thought the victim had been  injured in a car crash after spotting a badly damaged vehicle on a pavement at  the scene.

She said: “I went to the guy and when I approached the body there was a lady  cradling him. And then (one of the killers), the most excited one of the two,  said, ‘Don’t go too close to the body’.

“I thought, okay. And because I was down I could see a butcher’s knife and an  axe – that’s what he had – and blood. I thought, what the heck? I thought  obviously he was a bit excited and the thing was just to talk to him.”

 Ms Loyau-Kennett said she tried to reason with the killer in an effort to  focus his attention away from other potential victims, as large crowds began to  huddle at the scene.

She said: “I know it’s big today but for me it was just a regular guy, just a  bit upset. He was not on drugs, he was not drunk.

“He said, ‘Don’t touch, I killed him’. I said, ‘Why?’ He said: ‘He’s a  British soldier. He killed people. He killed Muslim people in Muslim  countries.’

“And I said: okay. So what would you like? I tried to maker him talk about  how he felt. He said all the bombs dropping and blindly killing women,  children…

“More and more people were starting to come. There were so many people  around. I just looked around and I found it so daunting.”

However, Ms Loyau-Kennett said her thoughts were to “just carry on” talking  to the man, while several woman arriving at the scene tried to shield the  victim.

She said: “I wanted him to concentrate on me and make sure he doesn’t have a  funny idea.

“He (the killer) told me he was a British soldier – he didn’t look like a  British soldier to me, he wasn’t in uniform. But I thought if another one passes  by, or is in the area…”

Asked if she was scared, the woman replied: “No – better me than a child.

“Unfortunately there were more and more mothers with children stopping  around, so it was even more important I was talking to him and ask him what he  wanted.”

Woolwich and Greenwich MP Nick Raynsford today praised the “extraordinary”  bravery of members of the public who approached the killers. The men are  currently in separate London hospitals being treated for injuries after they  were shot by police at the scene.

Relatives of the dead soldier are believed to have been informed though he  has yet to be

Check out all the latest News, Sport & Celeb gossip at Mirror.co.uk http://www.mirror.co.uk/news/uk-news/woolwich-attack-watch-brave-mum-1905504#ixzz2U72ENkmq Follow us: @DailyMirror on Twitter | DailyMirror on Facebook


Ethiopia Amnesty International Annual Report 2013

$
0
0

The state stifled freedom of expression, severely restricting the activities of the independent media, political opposition parties and human rights organizations….. Dissent was not tolerated in any sphere. The authorities imprisoned actual and perceived opponents of the government. Peaceful protests were suppressed. Arbitrary arrests and detention were common, and torture and other ill-treatment in detention centres were rife. Forced evictions were reported on a vast scale around the country

amn

Background

In August, the authorities announced the death of Prime Minister Zenawi, who had ruled Ethiopia for 21 years.

Hailemariam Desalegn was appointed as his successor, and three deputy prime ministers were appointed to include representation of all ethnic-based parties in the ruling coalition.

The government continued to offer large tracts of land for lease to foreign investors. Often this coincided with the “villagization” programme of resettling hundreds of thousands of people. Both actions were frequently accompanied by numerous allegations of large-scale forced evictions.
Skirmishes continued to take place between the Ethiopian army and armed rebel groups in several parts of the country – including the Somali, Oromia and Afar regions.
Ethiopian forces continued to conduct military operations in Somalia. There were reports of extrajudicial executions, arbitrary detention, and torture and other ill-treatment carried out by Ethiopian troops and militias allied to the Somali government.
In March, Ethiopian forces made two incursions into Eritrea, later reporting that they had attacked camps where they claimed Ethiopian rebel groups trained (see Eritrea entry). Ethiopia blamed Eritrea for backing a rebel group that attacked European tourists in the Afar region in January.

Freedom of expression

A number of journalists and political opposition members were sentenced to lengthy prison terms on terrorism charges for calling for reform, criticizing the government, or for links with peaceful protest movements. Much of the evidence used against these individuals consisted of examples of them exercising their rights to freedom of expression and association.
The trials were marred by serious irregularities, including a failure to investigate allegations of torture; denial of, or restrictions on, access to legal counsel; and use of confessions extracted under coercion as admissible evidence.
  • In January, journalists Reyot Alemu, Woubshet Taye and Elias Kifle, opposition party leader Zerihun Gebre-Egziabher, and former opposition supporter Hirut Kifle, were convicted of terrorism offences.
  • In June, journalist Eskinder Nega, opposition leader Andualem Arage, and other dissidents, were given prison sentences ranging from eight years to life in prison on terrorism charges.
  • In December, opposition leaders Bekele Gerba and Olbana Lelisa were sentenced to eight and 13 years’ imprisonment respectively, for “provocation of crimes against the state”.
Between July and November, hundreds of Muslims were arrested during a series of protests against alleged government restrictions on freedom of religion, across the country. While many of those arrested were subsequently released, large numbers remained in detention at the end of the year, including key figures of the protest movement. The government made significant efforts to quash the movement and stifle reporting on the protests.
  • In October, 29 leading figures of the protest movement, including members of a committee appointed by the community to represent their grievances to the government, and at least one journalist, were charged under the Anti-Terrorism Proclamation.
  • In both May and October, Voice of America correspondents were temporarily detained and interrogated over interviews they had conducted with protesters.
The few remaining vestiges of the independent media were subjected to even further restrictions.
  • In April, Temesgen Desalegn, the editor of Feteh, one of the last remaining independent publications, was fined for contempt of court for “biased coverage” of the trial of Eskinder Nega and others. Feteh had published statements from some of the defendants. In August, he was charged with criminal offences for articles he had written or published that were deemed critical of the government, or that called for peaceful protests against government repression. He was released after a few days’ detention and the charges were dropped.
In May, the authorities issued a directive requiring printing houses to remove any content which could be defined as “illegal” by the government from any publications they printed. The unduly broad provisions of the Anti-Terrorism Proclamation meant that much legitimate content could be deemed illegal.
  • In July, an edition of Feteh was impounded after state authorities objected to one cover story on the Muslim protests and another speculating about the Prime Minister’s health. Subsequently, state-run printer Berhanena Selam refused to print Feteh or Finote Netsanet, the publication of the largest opposition party, Unity for Democracy and Justice. In November, the party announced that the government had imposed a total ban on Finote Netsanet.
A large number of news, politics and human rights websites were blocked.
In July, Parliament passed the Telecom Fraud Offences Proclamation, which obstructs the provision and use of various internet and telecommunications technologies.

Human rights defenders

The Charities and Societies Proclamation, along with related directives, continued to significantly restrict the work of human rights defenders, particularly by denying them access to essential funding.
  • In October, the Supreme Court upheld a decision to freeze around US$1 million in assets of the country’s two leading human rights organizations: the Human Rights Council and the Ethiopian Women Lawyers Association. The accounts had been frozen in 2009 after the law was passed.
  • In August, the Human Rights Council, the country’s oldest human rights NGO, was denied permission for proposed national fundraising activities by the government’s Charities and Societies Agency.
It was reported that the Agency began enforcing a provision in the law requiring NGO work to be overseen by a relevant government body, severely compromising the independence of NGOs.

Torture and other ill-treatment

Torture and other ill-treatment of prisoners were widespread, particularly during interrogation in pre-trial police detention. Typically, prisoners might be punched, slapped, beaten with sticks and other objects, handcuffed and suspended from the wall or ceiling, denied sleep and left in solitary confinement for long periods. Electrocution, mock-drowning and hanging weights from genitalia were reported in some cases. Many prisoners were forced to sign confessions. Prisoners were used to mete out physical punishment against other prisoners.
Allegations of torture made by detainees, including in court, were not investigated.
Prison conditions were harsh. Food and water were scarce and sanitation was very poor. Medical treatment was inadequate, and was sometimes withheld from prisoners. Deaths in detention were reported.
  • In February, jailed opposition leader, Andualem Arage, was severely beaten by a fellow prisoner who had been moved into his cell a few days earlier. Later in the year, another opposition leader, Olbana Lelisa was reportedly subjected to the same treatment.
  • In September, two Swedish journalists, sentenced in 2011 to 11 years’ imprisonment on terrorism charges, were pardoned. After their release, the two men reported that they were forced to incriminate themselves and had been subjected to mock execution before they were allowed access to their embassy or a lawyer.

Arbitrary arrests and detentions

The authorities arrested members of political opposition parties, and other perceived or actual political opponents. Arbitrary detention was widespread.
According to relatives, some people disappeared after arrest. The authorities targeted families of suspects, detaining and interrogating them. The use of unofficial places of detention was reported.
  • In January the All Ethiopian Unity Party called for the release of 112 party members who, the party reported, were arrested in the Southern Nations, Nationalities and Peoples (SNNP) region during one week in January.
Hundreds of Oromos were arrested, accused of supporting the Oromo Liberation Front.
  • In September, over 100 people were reportedly arrested during the Oromo festival of Irreechaa.
Large numbers of civilians were reportedly arrested and arbitrarily detained in the Somali region on suspicion of supporting the Ogaden National Liberation Front (ONLF).
  • The authorities continued to arbitrarily detain UN employee, Yusuf Mohammed, in Jijiga. His detention, since 2010, was reportedly an attempt to get his brother, who was suspected of links with the ONLF, to return from exile.
Between June and August, a large number of ethnic Sidama were arrested in the SNNP region. This was reportedly in response to further calls for separate regional statehood for the Sidama. A number of arrests took place in August around the celebration of Fichee, the Sidama New Year. Many of those arrested were detained briefly, then released. But a number of leading community figures remained in detention and were charged with crimes against the state.
There were reports of people being arrested for taking part in peaceful protests and publicly opposing certain “development projects”.

Excessive use of force

In several incidents, the police were accused of using excessive force when responding to the Muslim protest movement. Two incidents in Addis Ababa in July ended in violence, and allegations included police firing live ammunition and beating protesters in the street and in detention, resulting in many injuries. In at least two other protest-related incidents elsewhere in the country, police fired live ammunition, killing and injuring several people. None of these incidents was investigated.
  • In April, the police reportedly shot dead at least four people in Asasa, Oromia region. Reports from witnesses and the government conflicted.
  • In October, police fired on local residents in Gerba town, Amhara region, killing at least three people and injuring others. The authorities said protesters started the violence; the protesters reported that police fired live ammunition at unarmed people.
Security forces were alleged to have carried out extrajudicial executions in the Gambella, Afar and Somali regions.

Conflict in the Somali region

In September, the government and the ONLF briefly entered into peace talks with a view to ending the two-decade long conflict in the Somali region. However, the talks stalled in October.
The army, and its proxy militia, the Liyu police, faced repeated allegations of human rights violations, including arbitrary detention, extrajudicial executions, and rape. Torture and other ill-treatment of detainees were widely reported. None of the allegations was investigated and access to the region remained severely restricted.
  • In June, UN employee Abdirahman Sheikh Hassan was found guilty of terrorism offences over alleged links to the ONLF, and sentenced to seven years and eight months’ imprisonment. He was arrested in July 2011 after negotiating with the ONLF over the release of two abducted UN World Food Programme workers.

Forced evictions

“Villagization”, a programme involving the resettlement of hundreds of thousands of people, took place in the Gambella, Benishangul-Gumuz, Somali, Afar and SNNP regions. The programme, ostensibly to increase access to basic services, was meant to be voluntary. However, there were reports that many of the removals constituted forced evictions.
Large-scale population displacement, sometimes accompanied by allegations of forced evictions, was reported in relation to the leasing of huge areas of land to foreign investors and dam building projects.
Construction continued on large dam projects which were marred by serious concerns about lack of consultation, displacement of local populations without adequate safeguards in place, and negative environmental impacts.

Amnesty International


ኢሳት ጋዜጠኞች ጆሮ ላይ ስልክ ለምትዘጉ ባለስልጣኖች ማሰጠንቀቂያ

$
0
0

እስከ ነጻነት  መረጃ የማግኘት መብት የስብዓዊ መብት ዋናው መሰረት ነው፡ መረጃ የማግኘት መብት ዋናው የሰብዓዊ መብት ምሰሶ መሆኑን የሃገራት ደርግ (League of Nations) የደነገገው በ1946 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነበር… ያደጉ ሃገራት ይህንን መብት በሚገባ ይጠቀሙበታል፡ ገልብጦ መጻፍ እንጂ ማንበብ የማይችልው የወያኔ ዘረኛ ስርዓትም ይህንኑ መብት በህገመንግስቱ ላይ አሰቀምጦታል። ለነገሩ ያላሰቀመጠው ነገር የለም ግን ማን አንብቦት ተግባራዊ ያደርገዋል እንጂ። ተግባራዊ እየሆነ ያለው ዘርን ለማጥፋት የተወጠነው የጫካው ህጋቸው ብቻ ነው።

ይህን እዚሁ ላይ ላቁምና ወደተነሳሁበት ልመለስ፤ የውነትም ይሁን የውሸት ስልጣን ይዛችሁ መረጃ ስትጠየቁ ስልክን ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ የምትዘጋ፤ የምትዘጊ፤ የምትዘጉ ግለሰቦች ወንጀል መሆኑን ካልተገነዘባችሁ እንድትገነዘቡት ላስታውሳችሁ አወዳለሁ፡የእሳት ጋዜጠኛ መረጃ ሲጠይቃችሁ ጆሮው ላይ ስትዘጉ፡ የዘጋችሁበት መሳይ፤ ፋሲል፡ ሲሳይ ወይም፡አንድ የእሳት ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ሳይሆን የ90 ሚሊየን የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ ላይ መሆኑን ልብ ካላላችሁ ላስታውሳችሁ፡ ለያንዳንዷ ለዘጋችሗት ስልክ የምትጠየቁ መሆኑን ደግሜ ደጋግም ላስገነዝባችሁ እወዳለሁ።

በእርግጥ አማራ ነን ብላችሁ አማራ ህዝብን የምታስፈጁት፤ ኦሮሞ ነን ብላችሁ የኦሮሞን ደም የምታፈሱት፤ ኢሳ ሆናችሁ የኢሳን ህዝብ የምታስፈጁት ሌሎቻችሁም የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ካድሬ ከላይ ተጭኖ እንደሚያዛችሁ አለም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡ ምናልባትም ለእሳት መረጃ ለመስጠት የፍርሃት ቆፈን ቀፍድዷችሁ ሊሆን ይችላል። ፈቃደኝነቱ ኖሮ ችግራችሁ ፍርሃት ከሆነ መረጃውን ለሌላ ለምታምኑት ሰው አቀብላችሁ መረጃ የሰጣችሁትን ስው ስልክ ቁጥር ለእሳት ጋዜጠኛ ልትነግሩ ትችላላችሁ፡ ሲሆን ሲሆን አንድ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ጨባጣ ካድሬ እንደ አውራ ዶሮ ሲንቀባረርባችሁ እንደ ሲካካ ዶሮ እኔ እኔ እያላችሁ ከመሽቀዳደም በጋራ ማሰወገድ ትችሉ ነበር፡ይህ ባይሆን እንኳ የወገናችሁን ሰቆቃ እና የወያኔን ሚስጥራዊ ወንጀል ማጋለጥ ከናንተ የሚጠበቅ ትንሹ ተግባር መሆን ሲገባው ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ ትዘጋላችሁ።

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ በተለይ አማራ ነን ያላችሁ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር መጋዣዎች፤ አማራን ለማጥፋት በተግባር እቅዱ ላይ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት እናንተን እንደማይበላችሁ ማረጋገጫችሁ ምንድነው? መረጃውን እዚህ ላይ አንብቡት አሁን በሙስና ተብለው የታሰሩት በርግጥ በሙስና ነው? እናነተስ ነገ ወደቃሊቲ ላለመላካችሁ ዋስትናችሁ ምንድነው? ስለዚህ ቀኑ ሳይመሽ ወደ ህሊናችሁ ተመልሳችሁ ወደ ወገናችሁ ተደባለቁ። ይህ ጥሪ ላማራ ብቻ አደለም፤ ለኦሮሞ፤ ለሲዳማ፤ ለኦጋዴን፤ ለአፋር፤ ለሲዳማ፤ በአጠቃላይ ወያኔ በየቦታው የወዘፋችሁ ባለስልጣናትን ሁሉ ይመለከታል፡ ይህ ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ፤ ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ እየዘጋችሁ የወያኔን ወንጀል ደብቃችሁ ቀኑ ከመሸ እያንዳንዳችሁ ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ መረዳት አለባችሁ፡ ወያኔ እንኳን የናንተን ገመና ሊሸፍን የራሱን ገመና መሸፈን የማይችል የፍየል ጅራት መሆኑ አይናችሁን ካልጨፈናችሁ በስተቀር በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው።

በህግ ስላላወቅሁ ነው የሚባል ነገር እንደሌለና ለሰራችሁት ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ መሆናችሁን አስረግጬ እዚህ ላይ ላብቃ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

ECADF NEWS


በህብረቱ 50ኛ ዓመት በዓል ላይ የአፍሪካ መሪዎችና 20 የዓለም መሪዎች ይሳተፋሉ

$
0
0

በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት በዓል ላይ የአፍሪካ መሪዎችና የብራዚል፣ ኩባ፣ ጃማይካ፣ ሃይቲ፣ አየርላንድ፣ ሩስያ፣ ስዊድን ጨምሮ 20 የዓለም ሀገራት መሪዎች  ይሳተፋሉ …..

 

http://www.ertagov.com/amharic/media/k2/items/cache/b221b486bfa5e70a3ef7b7059063a568_XL.jpg

እንዲሁም የቻይና፣ ህንድ፣ ፍልስጤም፣ ብሩኔ፣ ኒውዝላንድ፣ ኢራን፣ ኢንዶኔዥያ እና የሌሎች ሀገራት ከፍተኛ ልዑካን ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባንኪሞን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም፣ የአለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮች ፣የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀሀፊዎች ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ እና ኮፊ አናን ፣ የመንግስታቱ የቀድሞው ምክትል ጸሀፊ አሻ ሮዝ ሚጊሮ በህብርቱ 50ኛ አመት በዓል ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃለ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ  የቀድሞዎቹ የአፍሪካ ህብረት ድርጅት ዋና ፀሀፊዎችና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበሮች ፣ ሌሎች ተጋዥ የአፍሪካ አካባቢያዊ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ፣ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ፣ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኢጋድ፣ ኮሜሳ፣ኤካስ፣ ኢኮዋስና ሌሎችም ይሳተፋሉ ተብም ይጠበቃል፡፡

በህብረቱ የወርቅ እዮቤልዩ በዓል ላይ የተጋበዙት እንግዶች በፓን አፍሪካኒዝም፣ በአፍሪካ ህዳሴ እና በአፍሪካ የነጻነት ትግል ላይ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ መሰረት ያደረገ ነው ፡፡

የህብረቱን 50ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የተለያዩ ዝግጅቶች፣ ኮንፈረንሶች እና አውደ ርእዮች  ይካሄዳሉ፡፡

 

——————//———————//—————————//————————

 -የአፍሪካ ህብረት መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጊኒ ቢሳዉና ማዳጋስካር ከግንቦት 18¬-19 በሚካሄደዉ 21ኛዉ የህብረቱ ስብሰባ ላይ እንዳይሳተፉ አገደ…

ለህብረቱ ቅርብ የሆነ ምንጭ እንዳስታወቀዉ ሶስቱ ሀገሮች የታገዱት በኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ የስልጣን ሽግግር በማካሄዳቸው ነዉ:: ማዳጋስካር እ.አ.አ በ2009 በፕሬዝዳንት ማርክ ራቫሎማናናን በመፈንቅለ መንግስትከስልጣናቸው አንስታለች::

እንደ ኢሬቴድ ዘገባ ጊኒ ቢሳዉ የታገደችው ባሳለፍነዉ ዓመት በተካሄደው መፈንቅለ መንግስትምክንያት ሲሆንመካከለኛዉ አፍሪካ ሪፐብሊክ ደግሞ በያዝነዉ ዓመት የታጠቁ ሀይሎች በፕሬዝዳንቱ ላይነፍጥ ማንሳታቸዉን ተከትሎ ነው::

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 15/2005 (ዋኢማ)  ምንጭ፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር


ሰማያዊ ፓርቲ አስደናቂ መግለጫ አውጥቷል።

$
0
0

መንግስት እንደለመደው ሰልፉ እንዳይካሄድ ይፈልጋል። ፓርቲው ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም ሰልፉን ለማድረግ መወሰኑን አስታውቋል። ፓርቲው በያዘው ጠንካራ አቋም ብቻ መንግስትን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል… የአዲስ አበባ መስተዳድር ለፓርቲው ደብዳቤ መልስ የሚሰጥ አይመስለኝም። መንግስት እንዲህ አይነት የማፍያ ስራ የሚሰራው ሁሌም ጠመንጃውን ተማምኖ ነው። የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ የመንግስትን ጠመንጃ ባለመፍራት ሰልፉን ለማካሄድ በመወሰናቸው ብቻ ሊደነቁ እና ሊደገፉ ይገባል። እነዚህን ደፋር መሪዎች በሰልፉ እለት በእስር ወይም በሌላ መንገድ እንዳናጣቸው፣ ሁለት ነገሮችን ማድረግ ይገባል እላለሁ። አንደኛው ህዝቡ በነቂስ መውጣት አለበት። ከ10 ሰዎች ይልቅ 100 ሰዎች ፣ ከ100 ሰዎች ይልቅ ሺዎች የተሻለ “የመፈራት ጉልበት” ይኖራቸዋል። ህዝቡ በነቂስ መውጣት ከቻለ፣ ፌደራሎች ሊገድሉም ሊያስሩም አይችሉም። መንግስት ሊያደርግ የሚችለው፣ ከህብረቱ ስብሰባ አንድ ቀን በፊት፣ መሪዎችን በየቤታቸው እየሄደ ማሰር ነው፤ ለዚህ መፍትሄው ደግሞ ከተቻለ ከአንድ ቀን በፊት የድርጅቱ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ውሎ እና አዳራቸውን በጽህፈት ቤታቸው ውስጥ ማድረግ ነው፣ ከተቻለ ከአሁን ጀምሮ! የፌደራል ፖሊሶች ሊያሰሩዋቸው ሲመጡ ደጋፊዎቹና አባሎቹ በመጮህ መቃወም። ጩኸት ብዙ ነገሮችን ይጋብዛል፤ ብዙ ሰዎች ይሰባሰባሉ፣ ሚዲያው ይመጣል፣ አለምም አይኑን ኢትዮጵያ ላይ ይተክላል። መንግስት ስብሰባውን ያለምንም ኮሽታ ማስኬድ ቢፈልግም ያልጠበቀው ጨኸት ስለሚገጥመው የሚኖረው አማራጭ መደራደር ነው። መንግስት ግን ያን የማድረግ ተፈጥሮ የለውም።
እንደኔ እንደኔ ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ አቋሙ ከቀጠለና መጠነኛ የብልጠት ስራዎችን ከሰራ ታሪካዊ ድል ይቀዳጃል። የፓርቲው ደጋፊዎች፣ አባላትና አመራሮች ከአሁን ጀምሮ እጅ ለጅ ቢያያዙ፤ አብረው ቢውሉ፣ ቢያመሹ፣ ከተቻለ ሌሎች ፓርቲዎችም አባሎቻቸውን፣ ደጋፊዎቻቸውን እና አመራሮቻቸውን ይዘው በድርጅቱ ጽህፈት ቤት ቢከትሙ ታሪካዊቷ “ታህሪር”ን በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ውስጥ ተመሰረት ማለት ነው።
እባካችሁ ሌሎችም ሀሳብ አዋጡ


ሰበር ዜና ፀረሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን የሀብት ዝርዝር ላለማሳወቅ እያንገራገረ ነው

$
0
0

musenaፍኖተ ነፃነት  የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣኖችን የሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታቱ በፓርላማ መነጋገሪያ ሆነ፡፡የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ባለፈው ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም…. ለፓርላማ ባቀረቡት የ2005 በጀት የአስር ወር የዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ኮሚሽነሩ ባለፈው አመትም ተመሳሳይ ሪፖርት ሲያቀርቡ “በቅርቡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ እናደርጋለን” ቢሉም በያዝነው አመትም ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ኮሚሽነሩ ሲመልሱም በአስደንጋጭ ሁኔታ “የሚገለፅና የማይገለፅ አለው” ብለዋል፡፡ ብቸኛው የተቃዋሚ ወኪል የሆኑ አቶ ግርማ ሰይፉ “የተሽዋሚዎች ሀብት የሚገለጽና የማይገለፀው ምንድነው?” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቂ ምሳሽ እንዳላገኙ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም “ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሁንም የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብትና መረጃ ይፋ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ መውሰድ የለበትም” ካሉ በኋላ፣ ባለስልጣናቱን በሚመለከት የሚገለፅና የማይገለፅ መረጃ ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡



ግንቦት 7, 97 የታየውን የለውጥ መነሳሳት ለመድገም ጠንካራ ሰላማዊ ትግል የግድ ይላል

$
0
0

ግንቦት በሀገራችን ታሪክ ወሳኝ ፖለቲካዊ ሁነቶች የተከሰቱበት ነው፡፡ ከሌሎቹ ፖለቲካዊ  ሁነቶች መካከል፣ ኢትዮጵያን ከአምባገነኖች መዳፍ ነፃ ለማውጣት የተስፋ ጭላንጭል የታየበት የግንቦት 7, 97 ምርጫ ጎላ ብሎ የሚጠቀስ ነው… በወቅቱ ገዢው ፓርቲ በአንፃራዊነት ከፍቶት በነበረው የውድድር ሜዳ የተጠቀሙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዳር እስከዳር ህዝቡን ለማስተባበር የቻሉበት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ለውጥ እንደሚፈልግና የሰለጠነ ፖለቲካ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ለኢህአዴግም ሆነ ለመላው የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ያረጋገጠበት ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት

selef

 

ግንቦት 7 ተደርጎ የነበረው ታሪካዊ ምርጫ በኢህአዴግ አምባገነናዊ አፈናና በተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ፖለቲካዊ ብስለት ማጣት ምክንያት ለውጤት አለመብቃቱ የሚያስቆጭ ነው፡፡ ሆኖም ከስምንት አመታት በኋላም የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት የመጨመር እንጂ የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም፡፡

ኢህአዴግ በግንቦት 97ቱ ምርጫ ያጋጠመውን ኪሳራ ካሰላ በኋላ በሀገር አቀፍም ሆነ በወረዳና በከተማ ደረጃ ካሄዳቸውን ምርጫዎች ሙሉ ለሙሉ ለውድድር የማይመቹ እንዲሆኑ በማድረግ በህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ቸልሷል፡፡

በዘንድሮው የአካባቢና የከተማ ምክር ቤት ምርጫም ኢህአዴግ በከፍተኛ ውጤት ማሸነፉን ገዢው ፓርቲ እንዳሻው የሚዘውረው ብሔራዊው ምርጫ ቦርድባሳለፍነው ሳምንት ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ ኢህአዴግ ያለተፎካካሪ ብቻውን የሮጠበትን የምርጫ ሂደትና ያገኘው ውጤት ከግንቦት 7, 97 ምርጫ ጋር ሲተያይ የሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ምን ያክል ወደ ኋላ እንደተመለሰ ያመላክተናል፡፡

የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ጉዞ የተሳካ እርምጃ እንዲሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም ዜጎች፣መንግስት፣ገዢው ፓርቲ፣ምርጫ ቦርድ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የሲቪክ ተቋማትና የሌሎች የጋራ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡ መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ፀረ ዴሞክራሲያዊ እርምጃዎችን ሲያደርጉ፣ ብሔራዊው ምርጫ ቦርድም የድርጊቱ ተባባሪ ሲሆን ሌሎቹ ባለድርሻ አካላት በዝምታ መመልከት የለባቸውም፡፡ በሀገራችን በገሀድ እየታየ ያለው ሀቅ ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መንግስትና ገዢው ፓርቲ የሚያደርጉትን ፀረዴሞክራሲያዊ ተግባራት ከማውገዝ ያለፈ ተግባራዊ ስራ፣  ሲሰሩ አይታዩም፡፡ ይልቁኑም ገዢው ፓርቲ ያሻውን እንዲያደርግ የተውት እስኪመስል ድረስ ከመግለጫ ያለፈ ተግባራዊ ሰላማዊ ትግል ከማድረግ ተቆጥበዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በምንም አይነት መቀጠል የለበትም፤ በመሆኑም የኢህአዴግን በተለይም የገዢውን ቡድን አምባገነናዊ አፈና ከማማረር ባለፈ ግንቦት 7, 97 የታየውን የለውጥ መነሳሳት ለመድገም ጠንካራ ሰላማዊ ትግል ይኖርበታል፡፡ግንቦት 7, 97ቱን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመድገም ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ለመረዳት የሀገራችንን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ መመዘን ያስችለናል፡፡

ሀገራችን የገባችበት የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ከስምንት አመት በፊት ከነበረው እጅግ የባሰ ነው፡፡ ህዝባችን የእምነት፣የመደራጀት፣የመናገር፣በፍትሀዊነት የመዳኘት መብቶቹን ከ1997ዓ.ም በባሰ መልኩ በገዢው ቡድን ተነጥቋል፡፡ የሲቪክ ተቋማትና መንግስት ባወጣው አሳሪ ህግ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ አስተዋፅኦ እንዳይኖራቸው ተደርገዋል፡፡ ነፃውን ፕሬስ በአፋኝ የፕሬስ ህግ በማዳከም እንዲሁም ጋዜጠኞች በፀረሽብርተኝነት ህግ ሰበብ የሚጠበቅባቸውን ያህል እንዳይሰሩ ተደርገዋል፣ በርካታ ጋዜጠኞች በተቀነባበረ የሽብር ክስ ታስረዋል፣ ጋዜጦች አታሚ በማጣት ከገበያ እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች ከደጋፊዎቻቸውና ከህዝብ ጋር እንዳይወያዩ አዳራሽ ከመከልከል ጀምሮ አመራሮቻቸውን በተፈበረከ ክስ ታስለውባቸዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ አፈናዎች በ1997 ዓ.ም ከነበረው አፈና ጋር ሲተያይ የአሁኑ እጅግ የከፋ ነው፡፡ ይህ ዘርፈ ብዙ አፈና በህዝቡ ውስጥ የፈጠረውን ብሶት ወደ ሰላማዊ ህዝባዊ ዕምቢተኝነት መለወጥ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡


ሰማያዊ ፓርቲ በግንቦት 17፥ 2005 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍ ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተሰጠ አቋም መግለጫ!

$
0
0

የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ጥቁር በመልበስ እና ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱ ይታወቃል በመሆኑም እንዲህ አይነት ሰላማዊ የህዝብ የመብት… የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሚደግፈው መሆኑን ስንገልጽ::

በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ “በአገዛዙ ምላሽ የተነፈጋቸው የተለያዩ አንገብጋቢና መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብ ትኩረት እንዲሰጣቸው በሚል ሃሳብ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት በዓልን አጋጣሚ በመጠቀም ድምፃቸውን ለአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ለሃገር መሪዎች እና ለታላላቅ ሚዲያዎች ለማሰማት በማቀዳቸው ከጎናቸው ሆነን ድጋፋችንን እንገልፃለን::

እንደሚታወቀው የወያኔ አገዛዝ ባፀደቀው ህገመንግስቱ ላይ የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የተደነገገ ሲሆን፥ ከ1997 ምርጫ በኋላ በግልፅ በከፍተኛ ደረጃ በውርደት የተሸነፈው የወያኔ አገዛዝ በአቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ብቻ ለራሳቸው በሚያመች ሁኔታ ያረቀቁት ህገመንግስቱ ከተሻረ በኋላ የዜጎች የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማረግ እንዲሁም ተዛማች መብቶች ከተገፈፈ እነሆ ስምንት አመታት ተቆጥሯል::

በመሆኑም ይህንን አንገብጋቢና መሰረታዊ የሆነ የመብት፣ የፍትህ እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁሉም ነጻነት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊደግፈው ይገባል ብለን እናምናለን፣ ሰለሆነም ሙሉ አጋርነታችንን ለማሳየት የየዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ የሥራ አስፈጻሚዎች፣ አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች ቀኑን የጥቁር ልብስ በመልበስ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ ድጋፍችንን እናሳያለን፣ በማያያዝም በኖርዌይ ለሚኖሩ መላ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ቀኑን የጥቁር ልብስ በመልበስ ለሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ ድጋፋችሁን እንድታሳዩ ድርጅታችን ጥሪውን ያቀርባል::

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ


ሰበር ዜና፣ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ እውቅና ተሰጠው!

$
0
0

ፓርቲው “በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ ለመፈለግ…” በሚል ባስተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን… የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት

protest in Addis Ababa, semayawi party

ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ” ሲል አሳስቧል።


የዛሬው የሸዋበር መስጂድ ደማቅ ተቃውሞ ውሎ!

$
0
0

ዛሬ የደሴ ሙስሊም በመንግስት ከፍተኛ የሆነ በደል ቢፈፀምበትም የበላይነቱን አሳይቷል፡፡ የመንግስት ተላላኪ የሆኑት ኢማሞች በጊዜ አሰግደው ተቃውሞውን እንዳያኮላሹት በወጣው መርሀ ግብር መሰረት ሙስሊሙ በጊዜ መስጂዱን ሞላው… ኹጥባ ከመደረጉ በፊት በመንግስት ኃይል የመስጂድ ኮሚቴ ተደርገው የተሾሙት ግለሰብ መንግስትን ማሞካሸት እና ሙስሊሙን ለማስፈራራት ሲሞክሩ ውስጡ የተቃጠለው የደሴ ሙስሊም በተክቢራ ያስቆማቸዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ ንግግራቸው በተክቢራ ቢቋረጥም መልሰው ‹እኛ ረብሻ አንፈልግም፡፡ ረብሻለሁ የምትሉ ከሆነ ግን ይሄው በውጨኛው ማይክ ነው የምንናገረው ፖሊሶች እርምጃ እንዲወስዱ እንፈቅድላቸዋለን› የሚል አሳፋሪ ንግግራቸውን በአላህ ቤት ውስጥ ተናግረው ጨረሱ፡፡ … ኢማሙ የመጀመሪያውን ኹጥባ አድርገው ሁለተኛውን ኹጥባቸውን ሲጀምሩ ሙስሊሙ የዝሁርን ሶላት መስገድ ይጀምራል፡፡ ኹጥባው አልቆ ሶላት ተቆመ፡፡ የሙስሊሙም ልብ ተክቢራ ለማሰማት ይደልቅ ጀመር፡፡ በመጨረሻም የብሶት ማሰሚያ ሰዓቱ እንደደረሰ ኢማሙ አሰላምተው ሲጨርሱ የጌታችንን ታላቅነት በምንመሰክርበት ቃል ተክቢራ ሁሉም በአንድ ላይ ‹አላሁ አክበር!› በማለት የሸኽ ያቁት መስጂድን አናወጡት፡፡ ከመስጂዱ ውስጥና ከመስጂዱ የውጭ ክፍል የብሶት ድምፆች ተስተጋቡ! ከባድና አስፈሪ የሆነው የደሴ ሙስሊሞች ድምፅ መስጂዱን አናወጠው፡፡ ይህ የተቃውሞ ድምፅ ኃይሉ በጨመረ ጊዜ ሰላም የማይወዱት የእነ ‹እሾህ ኑሩ› ቡድኖች ከውስጠኛው መስጂድ ከመንግስት የተሰጣቸውን ዱላ በመያዝ በሰላማዊው ሙስሊም ላይ እጃቸውን አነሱ! ዱላ አንስተው ሙስሊሙን መማታት የጀመሩት አቶ አሊ እና አቶ እሸቱ የሚባሉ የመንግሰት ቅጥረኞች ነበሩ፡፡ ረብሻ አንፈልግም በሚል ሰበብ ራሳቸውን ረብሻውን ቀሰቀሱት! ሙስሊሙ የሚደርስበትን በደል በውስጡ እንደያዘ የተክቢራ ድምፁን ማሰማቱን ቀጠለ፡፡ ተቃውሞው በበረታባቸው ጊዜ ዲንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡ በደሉ ከልክ ባለፈ ጊዜ ፍርሀት እንዳይመስል ሙስሊሙ ራሱን መከላከል ጀመረ! ዱላቸውን በመቀማት ባዶ እጃቸውን አስቀሯቸው፡፡ ይህን ተከትሎ ‹እሾህ ኑሩ› የድረሱልን ጥሪውን አስተላለፈና ፖሊሶች መስጂዱን ጥሰው ገቡ፡፡ ይህን ጊዜ የአላህ ቤት ነውና የደሴ ሙስሊም መስጂዱን ለቆ በመውጣት በሸዋበር አደባባይ ላይ መፈክሩን ከፍ አድርጎ ያሰማ ጀመር፡፡ ‹ባገራችን ሰላም አጣን! በቤታችን መስገጃ አጣን! በሱቃችን መስገጃ አጣን!› የሚሉትን መፈክሮች አስተጋባ፡፡ የአድማ በታኞች በቦታው ደርሰው ሙስሊሙን ይማቱ ጀመር! የደሴ ሙስሊም እየተደበደበም፣ ደሙ እየፈሰሰም ተቃውሞውን ቀጠለ፤ ጥንካሬውንም አስመሰከረ! ደም የጠማቸው የመንግስት ውሾች በሙስሊሙ ላይ ድብደባቸውን ሲፈፅሙ ሁሉም ወደ ቤቱ መሄድ ጀመረ፡፡ ለውሻ መልስ አይሰጥምና ጀርባውን ሰጥቷቸው ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ይህ ጊዜ “ለምን ተሸነፍኩ?” በሚል ይመስላል እየተከተሉ መደብደብ የጀመሩት፡፡ የጥይት ቃታቸውንም ሳቡ፡፡ ነገር ግን የደሴ ሙስሊም ሌላም ቀን አለና ቀጠሮ ሰጥቷቸው ይህ የመጨረሻ አለመሆኑን አሳይቶ የቤቱን በራፍ ፊታቸው ላይ ዘጋባቸው! በሙስሊሙ የተናቁትም የመንግስት ውሾች በየቤቱ እየዞሩ አንዳንድ ወንድሞቻችንን አፍሰው ወሰዱ! የዚህ ዓይነት የመንግሰት ትንኮሳና ህግ ጥሰት የነበረ ቢሆንም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን የዛሬውን ተቃው በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ኢንሻአላህ ዛሬ በድል እንደተወጣነው ሁሉ ነገም እንደግመዋለን! “ጅራፍ እራሱን ገርፎ እራሱ ይጮኻል” እንደሚሉት ድብደባ የደረሰባቸው ወንድሞቻችንን ደሴ ሆስፒታል ለህክምና የሄዱትን እዛው በፖሊሶች በመክበብ አስታማሚውንም ሆነ ሊጠይቃቸው የሚመጣውን ሰው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን በመሳሪያ በማስፈራራት እየመለሱ ይገኛሉ፡፡ መቼም ቢሆን ተሸንፈን አናውቅም! ወደፊትም ኢንሻአላህ አንሸነፍም! ድል ለተጨቆነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች! አላሁ አክበር!See more


ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት ወያኔ በሚስጥር እየሰራ ነው፤

$
0
0

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋትና አለመተማመን ያሰጋው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት የሲዳማን ህዝብ የማሳመን ስራ ጀምሯል…ታማኝ ምንጮች እንዳሉት አቶ ሽፈራውን እንዲተኩ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ታጭተዋል።

shiferaw-shigute

ባለፈው ወር በክልሉ በተካሄደ ግምገማ ፕሬዚዳንቱ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በኪራይ ሰብሳቢነትና በሙስና ተፈርጀው ለህግ ተላልፈው እንዲሰጡ ሲወሰን “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” በማለት መልስ ሰጥተው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በስፍራው የሚገኙትን ምንጮች ጠቅሶ መዘገቡ የሚታወስ ነው። በክልሉ አብላጫ የህዝብ ብዛት ካለው የሲዳማ ብሔረሰብ የተወለዱት አቶ ሽፈራው፣ከስልጣናቸው ተወግደው ለፍርድ እንዲቀርቡ ቢወሰንም ውሳኔው ተግባራዊ ያልሆነው በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው።የመጀመሪያው ምክንያት ፕሬዚዳንቱ በተገመገሙበት የሙስና ወንጀል የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት መካተታቸው ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ የሲዳማ ህዝቦች ያምፃሉ በሚል ፍራቻ ነው። “የሙስና መሸሸጊያና የሙስና እናት”በሚል ስያሜ የሚታወቁት የአቶ መለስ ባለቤትና የትግል አጋር ተካተውበታል በተባለው የሙስና ወንጀል በኩል ከፍተኛ ቅሬታ ነግሷል።ፕሬዚዳንቱን አስመልክቶ ግን ለጊዜው ተግባራዊ እንዳይሆን የተያዘው ጉዳይ በሚስጢር ቅድመ ሁኔታዎች እየተካሄዱበት ነው። ጉዳዩን የሚከታተሉት ምንጮቻችን አቶ ሽፈራውን ህግ ፊት ለማቅረብና ከሃላፊነታቸው ለማባረር በመጀመሪያ የሲዳማን ህዝቦች ማሳመን አግባብ ሆኖ ተገኝቷል።በዚሁ መሰረት ከላይ በወረደ ትዕዛዝ በወረዳ ደረጃ አቶ ሽፈራው በህዝብ እንዲጠሉና ድጋፍ እንዲያጡ ለማድረግ የሚያስችል ዘመቻ ተጀምሯል። “ማስተፋት”በሚለው የወያኔ ጥበብ በህዝብ እንዲጠሉና እንዲገለሉ ዘመቻ እየተካሄደባቸው ያሉት አቶ ሽፈራው በበኩላቸው በሚያምኗቸውና እሳቸው በዘረጉት የሲዳማ መዋቅር አማካይነት ከፍተኛ ዘመቻ መጀመራቸው ታውቋል።ዘመቻው እሳቸው ከተነኩ የሲዳማ ህዝብ ዳግም ወደ ሃላፊነት ሊመጣ ስለማይችል በጥንቃቄ እንዲጠባበቅ ነው። ይህንን የተረዳው ወያኔ አቶ ሽፈራውን በሌላ የሲዳማ ተወላጅ ለመተካት ዝግጅቱን እያጣደፈ ይገኛል።በዚሁ መሰረት በጃፓን አምባሳደር ሆነው እየሰሩ ያሉትን አቶ ማርቆስ ተክሌን የሲዳማ ህዝብ “መሪዬ”ብሎ እንዲቀበላቸው የ“የስር ለስር ”ስራ እየተሰራ ነው።የሲዳማ ህዝቦች አቶ ሽፈራውን እየጠሉ አቶ ማርቆስን እንዲወዱ ለማድረግ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የሚከናወነው በወረዳ የተለያዩ መዋቅሮች ላይ ባሉ የሲዳማ ብሄር አባላት አማካይነት በመሆኑ ሚስጥር የተባለውን ጉዳይ ገሃድ እንዳያወጣውና ብጥብጥ እንዳይፈጠር ስጋትም አለ። በ 1993 ዓ ም ውህዳኑን በመደገፋቸው ክልሉን ከጀርባ ሆነው ይመሩ ከነበሩት አቶ ቢተው በላይ ጋር በሙስና ወንጀል ሰበብ የታሰሩት አቶ አባተ ኪሾ ከሰባት ዓመት በሁዋላ ያለ ወንጀል በነፃ የተለቀቁት የሲዳማ ህዝብ ባቀረበው ማስጠንቀቂያ ነበር። በተመሳሳይ ዜና የከተማ መሬት ወረራ ጋር በተያያዘ እስከ የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ ም ድረስ ከሁለት መቶ ሃምሳ የሚጠጉ ሰዎች ታስረው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተዛውረዋል።ከከተማ አስተዳደር፣ማዘጋጃ ቤቶችና የዞን አስተዳደሮች ተለቅመው የታሰሩት ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋትና ህገወጥ የመሬት ደላሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በሚል ነው። “ህገወጥ የመሬት ደላሎችን ለመግታት”ተብሎ በተካሄደ ግምገማ በመድረክ በዋናነት የክልሉን መሬት እየቸበቸቡ ያሉት የህወሃት ሰዎች እንደሆኑ ቢገለፅም የተወሰደው ርምጃና እስር እነሱን ባለማካተቱ በግምገማው ላይ በግልፅ የተናገሩትን ክፍሎች ስጋት ላይ እንደጣለ ምንጮቻችን ያነጋገሩዋቸው የድርጅት አባላት ተናግረዋል። እንዲህ ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀመው ኢህአዴግ በቅርቡ ያወጣውን አፋኝ የከተማ መሬት ሊዝ አዋጅ ለመተግበር መሆኑ ዘግይቶ እንደገባቸው የሚገልፁት የግምገማው ተሳታፊዎች “እንዲህ አይነቱ ተግባር አቶ መለስ አገር ትግራይ የማይተገበር ነው”ሲሉ ቅሬታቸውንና ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። በዚህም ሳቢያ የተፈጠረው ቅራኔና አለመግባባት፣ወደ ፖለቲካ አለመተማመን መሸጋገሩን ያስረዱት ምንጮች፣ከ 45 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩበት የደቡብ ክልል በአንድ ተረግጦ በሞግዚት አስተዳደር አንዲተዳደር አድርጓል።ክልሉ የራሱ አስተዳደር መዋቅር ቢኖረውም አሁን እየተመራ ያለው በህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጥብቅ ክትትልና መመሪያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።ስም ያልጠቀሱት ምንጮች እንዳሉት ወያኔ በደቡብ ክልል ሊገጥመው የሚችለውን ተቃውሞ በመገመት ሙሉ በሙሉ

የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በስለላ መዋቅር ውስጥ ለማስገባት ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ይገኛል።አንዳንድ ጠንካራ ቀበሌዎች ላይ ህዝቦችን በብድር፣በማዳበሪያና በምርጥ ዘር አቅርቦት እየቀጣ ይገኛል።

(በመምህሩ መልካሙ)   source: amnewsupdate.file


ኢህአዴግ ግንቦት 20ን የአባይን ወንዝ አቅጣጫ በማስቀየር ሊያከብር ነው

$
0
0

ኢሳት ዜና:- ኢህአዴግ አዲስአበባን የተቆጣጠረበትን 22ኛ ዓመት ክብረበአል የአባይን ግድብ አቅጣጫ በማስቀየር ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል…

ስነስርዓቱ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጉባ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሚገኙበት እንደሚካሄድ ታውቋል። ኢህአዴግ የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር የኢትዮጵያን ህዝብ በእለቱ ለማስደመም ማቀዱን ለማወቅ ተችሎአል።

 

የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየር ሥራ ክንውን አስመልክቶም የፊታችን ሰኞ ግንቦት 19/2005 ዓ.ም ከ10:30 ጀምሮ በብሔራዊ ቲአትር የሙዚቃዊ ድራማ ዝግጅት መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡

የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየሩ ስራ የፊታችን ማክሰኞ ቢካሄድም መንግስት አጠቃላይ ግንባታው በተያዘለት እቅድ መሰረት ለመከናወን እንደማይችል ፍንጭ ሰጥቷል።

ከአማራ ክልል መንግስት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የመንግስት ሰራተኞች ለአባይ ግድብ መዋጮ አንዲከፍሉ የተጠየቁትን ገንዘብ ከ90 በመቶ በላይ የከፈሉ ሲሆን ፣ የክልሉ ነጋዴዎች ደግሞ 1 ቢሊዮን ብር እንዲከፍሉ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ለመሰብሰብ የተቻለው 16 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። መንግስት ገንዘቡን በሚቀጥሉት አስር አመታት ለመሰብሰብ ማቀዱንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ከተጀመረ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘውና የግንባታው ስራ ከ11 በመቶ በላይ ተጠናቋል የተባለው የዚህ ግድብ መገንባት በሌሎች የተፋሰሱ አባል አገራት በተለይም ስምምነታቸውን በይፋ ባልገለጹት ግብጽና ሱዳን ላይ ተጽዕኖ ማምጣት አለማምጣቱን ከአንድ ዓመት በላይ ሲመረምር የቆየው ዓለምአቀፍ የኤክስፐርቶች ቡድን ሪፖርቱን በዚህ ወር ያቀርባል ተብሎ በሚጠበቅበት በዚህ ወቅት የግድቡ ሥራ ትልቁ አካል የሆነው የአባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀየር ሥራ መገባቱ አነጋጋሪ መሆኑ አልቀረም፡፡

በቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በጎ ፈቃድ የተመሰረተው ዓለም አቀፍ የኤክስፐርቶቹ ቡድን የሚያቀርበው ሪፖርት ለኢትዮጽያ የማይጠቅም ከሆነ በግብጽና ሱዳን ብቻም ሳይሆን በተፋሰሰ አባል አገራት ጭምር የታየው ትብብር መሰረቱን ሊያናጋው እንደሚችል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ሥጋታቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጽያ በበኩሏ ጥናቱ ሌሎች አገራት እንደማይጎዳ ማረጋገጫ አገኝበታለሁ በማለት ተስፋ የጣለች ሲሆን ይህ ባይሆንም ግን ከግንባታው የሚያግደኝ አይኖርም ስትል በተደጋጋሚ መናገሯ የጥናቱን ውጤት የምትቀበለው አስከጠቀማት ብቻ መሆኑ ግን ሌላ ዙር ቀውስ ውስጥ እንዳይከታት ተሰግቷል፡፡

97 በመቶው የግብርና ምርቱን በአባይ ውሃ ላይ ጥገኛ ያደረገችው ግብፅ ከግድቡ መገንባት ጋር በተያያዘ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖን ሊፈጥር ይችላል በሚል ሥጋቷን በተለያየ መንገድ ስትገልፅ ቆይታለች።

ኢትዮጵያ በአንፃሩ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የታችኞቹን ተፋሰስ ሀገራት ከመጉዳት ይልቅ እንዲውም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በተደጋጋሚ ስትገልፅ ቆይታለች። በኢትዮጵያ በኩል ግድቡ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ባልተጠበቀ ጐርፍ እንዳይጥለቀለቁ፣ ግድቦቻቸው በደለል እንደይሞላና የወሃ ትነቱንም ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው  ሲገለፅ ቆይቷል። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በተለይ ግብፅና ሱዳን በግድቡ ግንባታ ላይ ሥጋት ካላቸው አጠቃላይ የግድቡን ሁኔታ የሚመረምር የኤክስፐርቶች ቡድን ተቋቁሞ የራሱን ሞያዊ ሪፖርት እንዲያቀርብ ፈቃደኝነቷን ገልፃለች።

በዚህም መሠረት International Panel of Experts በሚል አንድ ቡድን ተቋቁሞ በህዳሴው የግንባታ ቦታ በመገኘት የራሱን ጥናት ሲያደርግ ቆይቷል። ቡድኑ ስድስት አባላትን ያቀፈና ከኢትዮጵያ፣ ከግብፅና ከሱዳን ሁለት ሁለት ኤክስፐርቶችን አካቷል፡፡ ከዚህ ውጪም አራት ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ኤክስፐርቶችን እንዲይዝ የተደረገ ነው። የኤክሰፐርት ቡድኑ ባለፈው ኣመት ግንቦት ወር ላይ የመጀመሪያውን ጉብኝት በግድቡ አካባቢ በመገኘት ያደረገ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ስብሰባውንም በሰኔ ወር 2004 ላይ አድርጓል። ቡድኑ በያዝነው ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም የመጨረሻ የግድቡን የአንድምታ ተፅዕኖ ጥናቱን ውጤት ለሦስቱም መንግሰታት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።


አንድነት ፓርቲ የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በህዝባዊ ንቅናቄ ሊዘክር መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ

$
0
0

UDJፍኖተ ነፃነት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የግንቦት 97ን ምርጫ ተከትሎ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉትን ኢትዮጵያውያን ለመዘከር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመላክቷል… ፓርቲው በአዲስ አበባ መዋቅሩ ጭፍጨፋው የተፈፀመበትን እለት በህዝባዊ ንቅናቄ ለመዘከር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የፓርቲው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ ምንጮቹ የህዝባዊ ንቅናቄው ዝርዝር አፈጻፀም በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የግንቦት 97ን ምርጫ ተከትሎ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉትን ኢትዮጵያውያን ለመዘከር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመላክቷል፡፡ ፓርቲው በአዲስ አበባ መዋቅሩ ጭፍጨፋው የተፈፀመበትን እለት በህዝባዊ ንቅናቄ ለመዘከር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የፓርቲው ምንጮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ ምንጮቹ የህዝባዊ ንቅናቄው ዝርዝር አፈጻፀም በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

zehabesha.com



አባ መላ ልብ ሲበላ ! በእንግዳ ታደሰ

$
0
0

Aba Mela (Ato Birhanu Damte)

በእንግዳ ታደሰ

ተረት ሲጀምር ከዕለታት አንድ ቀን ተብሎ አይደል የሚጀመረው ? በኔ እና በአባ መላ የወጣትነት ዘመን  አንድ ድምጻዊ ዘፋኝ ነበር ፡፡  በሃይሉ እሸቴ የሚባል ፡፡  « ገሳጭ እንበለው ? ወይስ  ነቃፊ ዘፋኝ ? »  ብቻ ልማታዊ ዘፋኝ አልነበረም … ምጸተኛ ዘፋኝ ብለው ይሻላል ፡፡ ውሻን ወደ ግጦሽ … የዋኋን እንስሳ ደግሞ ወደ ሊጥ ቡሃቃ ያስጠጋ ፡፡ አባ መላ ደግሞ እንደሰማሁት ከሆነ ትውልዱ መርካቶ ዙርያ ስለነበር ፣ ኮልፌ አካባቢ ያለውን የፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ሰፈር ጠንቅቆ ስለሚያውቀው በሃይሉ እሸቴንም ያውቀዋል የሚል እምነት አለኝ ፡፡

በሃይሉ በዘፈኑ ሲሸነቁጥ የተሰደቡትም ሳይቀር  በዘፈኑ እየሳቁ እንደገናም ከምር ይጠሉት ነበር ፡፡ አባ መላ ልክ እንደ በሃይሉ እሸቴ ፣ ከሰሞኑ የወያኔን ሰፈር ፣ በብላኔ*  ይሁን ወይም በዉነት ስላደበላለቀው ፣ እንስሶቹ ሰፈራቸው ሁሉ ተደበላልቆባቸው የግጦሹ እንስሳ ወደ ሊጥ ወረዳ ፥ የሊጡ እንስሳ ደግሞ ወደ ግጦሽ መንደር ገብተው እየተተራመሱ፣ አንዴም በአባ መላ የአራዳ ቋንቋ ሲስቁ ፣ በሌላም በኩል በጥላቻ እየወረዱበት ይገኛሉ ፡፡ ብላኔ የመርካቶ ቋንቋ ናት- ዕውነተኛ ያልሆነች ሲሉ የሚጠቀሙባት ፡፡

አንድ የቡሽ ጥቅስ ትዝ አለኝ ፡፡ የአባትየው ሳይሆን ፣ የጀርጀራው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ፡፡ ልክ እንደ አገራችን ቀዳማዊት እመቤት አፉ እንዳመጣለት የሚዘባርቀው ጆርጅ ቡሽ ፣ ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ ፣ ጥሩ ጥቅሶች ተብለው ከተመዘገቡለት ውስጥ የመስከረም አስራ ሃንድን የሽብርተኞችን ጥቃት አስመልክቶ የተናገረው ንግግር ነበር ፡፡

« ሽብርተኞች ላይ ርምጃ በምወስድበት ወቅት ፣ አስር ዶላር ለሚያወጣ ባዶ ድንኳንና  በድንኳን ውስጥ ለተጎለቱት ግመሎች  ስል የሁለት ሚልዮን ዶላር ሚሳይል እንዲተኮስ አላደርግም ፡፡ ወሳኝ የሆነ ርምጃ ነው የምወስደው ብሎ  ነበር » ፡፡ ”When I take action, I’m not going to fire a $2 million missile at a $10 empty tent and hit a camel in the butt. It’s going to be decisive.”

በጥሩው ፍቅራቸው ጊዜ ፣ ከአቶ መለስ ጥሩ አቀባበልና ፣ መስተንግዶ ይደረግለት ነበር የሚባለው አባ መላ ፣ አሁን ፥ አሁን ግን በአስር ብር ድንኳን ውስጥ ለተጎለቱት የመለስ ግመሎች ሚሳይሌን ከማስወነጭፍ ፣ ከትላልቆቹ ልጀምር ብሎ የጀመረው ሚሳይል የማስወንጨፍ ርምጃ – ከገዛ ተጋሩ እስከ እነ ግርማ ብሩ ኤምባሲ ግቢ ውስጥ ያሉ ወያኔዎችን ሁሉ አበሳጭቶ ፣ አባ መላን ይሄ ከሃዲ እያስባለው  ነው ፡፡

ከአባ መላ ጋር ያደጉና ቅርሌ የለጉ አብሮ አደጎቹ ፣ አባ መላ ከልጅነቱም ጀምሮ ፣ ባህላተ ቃላት ያለው ወይም አፈ ቀና እንደሆነ ይመሰክሩለታል ፡፡ አባ መላንም ፣ በቦታ ፥ በጊዜ ፥ እንደሁኔታው መሆን የሚችልም ነው ይሉታል ፡፡ እሱም አልካደ ! በአራዳ ቋንቋ ፖለቲካን ማን ነው እንደተርኪስ ባቡር አንድ ቦታ ላይ ያቆመው ? ተለዋዋጭ ነው ብሎናል ፡፡አባ መላ ይህን እንደ ተርኪስ ባቡር  ማን ነው አንድ ቦታ ያቆመው ያለውን ፖለቲካ ፣ አቶ መለስ ከሞቱ  በኋላ ማድረጉ ነው አጠያያቂው ጉዳይ ? አራዳ ሁሌ ሲወሳ ! ያውም ፒያሳ- ያውም ፒያሳ የሚል ዘፈን የሰማሁ ይመስለኛል ፡፡ ዉነቱን ነው አባ መላ ! በአቶ መለስ ለሳኝነት በአህያ ቆዳ የተሰራው ቤት ፣ ጅብ ሲጮኽበት ፈረስኩ ፣ ፈረስኩ ሲል እያየ ! ማን አብሮ እዚያ ቤት ይከርማል ? አራዶቹ እነ አባ መላ ድሮ « ላስ እንደ አየር ላንስ ይሉ አልነበር መርካቶ ! »

ግን አባ መላ ! ይህ ፖለቲካ ተለዋዋጭ ነው ! አንቀጹ መሻሻል አለበት ! የዘር ፖለቲካውም ጦዘ ! በየኤምባሲዎቻችንም አንገቱ ላይ ከረባት ያንጠለጠለ ገበሬ በዛበት ፥ ሻንጣ ተሸካሚውም በዛ ፣ የተባለውን ፊልም ያየውና የባነነው አቶ መለስ ከሞቱ  በኋላ ነው ወይስ ድሮም በብልጥጤ አይ ነበር ሊለን ነው ? ዉነቱን ነው አራዳው ሁሉ ወረዳ በሆነበት ዘመን ! አባ መላ ፊልም ቢሠራብን ሊደንቀን አይገባም ፡፡

ባለፈው ፕሮፌሰር መስፍን ፓል ቶክን በሚመለከት በጻፉት ጽሁፍ ላይ ያላስተዋልኩትን ነገር እንደገና ሄጄ እንዳይ አድርገውኛል ፡፡ የዚህ ፓልቶክ ሰለባ የሆኑት የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ሰዎች ሲሆኑ ፣ ከፍተኛውን ቁጥር ሱማልያ ስትዘግን ሁለተኛውን ደግሞ ኢትዮጵያ ታፍስና ፣ ሶስተኛውን ደግሞ ኤርትራ ትቆነጥራለች ያሉትን በትክክል አየሁ ፡፡

ናይጄርያ በአፍሪቃ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ያላት አገር የከፈተችው የፓልቶክ ክፍል አንድ ነው ፡፡ እሱም ሙዚቃ ብቻ ነው የሚያሰማው ፡፡ ከዚያም ከዘለለ ምናልባት ቢያስተዋውቅ የፉፉ ዱቄት ሊሆን ይችላል ፡፡ እንደ አፍሪቃ ቀንዱ የፖለቲካ ዲዲቲ አይረጭም ፡፡

ከዘጠና ሰባት ምርጫ ወዲህ ፓልቶክ የሚባለውን ጣቢያ ከኮምፒዩተሬ ውስጥ አውጥቼ  በሰላም እኖር ነበር ፡፡ ከሰሞኑ አንድ ጸሃፊ ለዚህ ፓልቶክ ጥሩ ስም አውጥቶለት አንብቤአለሁ – ቡል ቶክ ! ብሎታል ፡፡ አንድ ወዳጄ ኧረ እባክህ አባ መላን ግባና አድምጠው ብሎ ቢጨቀጭቀኝ ፣ ይህን ፓልቶክ የሚባል ጭነት ኮምፒዩተሬ ውስጥ ጭኘ  እንደ ቦኖ ወሃ ጠባቂ ሴት ተራዬን ጠብቄ ውዬ ፥ ውዬ እድሉን አገኘሁና አባ መላ ድንኳን ጎራ አልኩ ፡፡

ዉነትም አባ መላ ! አፉ እንደ አሜሪካን ዶላር ነው ፡፡ ይለዋል ! ይመነዝረዋል ፡፡ አበባ ይረጭለታል ! በርታ የሚልም የጅ ጠአት ይቀሰርለታል- ኧረ ስንቱ ! እጅግ የገረመኝ አባ መላ የማረከው የሚመስል የእጅ ምስል ለመናገር ተራ እየጠበቀ እጁን የሰቀለው ሰው መብዛቱ እጅግ ድንቅ የሚል ነው ፡፡ በዚህ መሃል አንድ እጅግ ከልቤ ያሳቀኝ አንድ ተረበኛ ሰው ከጽሁፍ ገበታው ላይ አንድ የሚያስቅ ጽሁፍ ከተበ ፡፡ አቤት ! አቤት ! ይሄ ሁሉ እጅ ፣ አንዳንድ ጠብመንጃ ቢይዝ ኖሮ ወያኔ የሚባል አይኖርም ነበር ፡፡ ወሬኛ ሁላ አለ ! አባ መላም የሚስቅ ምስል ለቀቀለት ፡፡ አባ መላ ውነትም የፓልቶክ አባባ ታምራት ገለታ ነው ፡፡

እጅግ የሚገርመው እዚያው አዲስ አበባ ላይ ሆኖ  ወያኔን በተባ ብዕሩ እንቅልፍ የሚነሳውን ፣የተመስገን ደሳለኝን ጽሁፍ የማያነብ ዲያስፖራ ! አሳጥረህ ብቻ አንቆርቁልኝ የሚል ብዙ ሰው በአባ መላ ተሞለቀቀ ፡፡ ሞለቀቀ በከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት ብዙ ትርጉሞች ቢኖሩትም ፣ በዚህ አግባብ ግን ብዙ ሰው በአንድነት አብሮ ሄደ ነው ትርጉሙ ፡፡ እስከዛሬ ግንባራቸውን ሳያጥፉ የወያኔንን ካምፕ ሲያራውጡ የነበሩ የፓልቶክ ክፍሎች ሁሉ ሳይቀር ቀፎአቸውን ነቅለው አብረው ሊቀላቀሉ እስኪመስል ድረስ ቤታቸውን አቀዘቀዙ ፡፡ አባ መላም አለ ! በሶስት ክፍል የከፈትኩትን ክፍል ለወደፊት በሬድዮ ጣቢያም አጎለብተዋለሁ አለ ፡፡ ማን ያውቃል ፟? ቀጥሎም ኢሳትን የሚገዳደር ቴሌቪዥንም ሊከፍት ይችላል ፡፡

ይህን ሞገደኛ የዲያስፖራ ኃይል በአራዳ ስልትና በወያኔ ቆረጣ ለመሰንጠቅ ፣ የሚደረግም ጨዋታ ሊሆን ይችላል ብሎ መገመትም የዋህነት አይመስለኝም ፡፡ በእባብ የደነገጠ በልጥ ሆኖብን ብንጠራጠር  አባ መላ ይቀየመን ይሆን ?

ልደቱ ሸዋ ሮቢት ታስሮ ወያኔ  በአይነ ምድር ላይ በባዶ እግሬ እንደ ጭቃ ረጋጭ አስረገጠኝ ሲለን አዝነን ማንዴላችን አልነው ፡፡ ቀጥሎም በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ወያኔ ቢሮዬ ውስጥ ቆልፎብኝ ፣ ይኽው ሶስተኛ ቀኔ ብሎ ፣በአሜሪካን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም በስልክ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ! እንዴት ወያኔ ስልኩን ሳይቆርጥበት ባዶ ቢሮ አስቀመጠው  ብለን ሳንጠይቅ ልደቱ ልባችንን በላው ፡፡ ይህ ሁሉ ደርሶብን ! አባ መላ አንተንም እንደ ታምራት ገለታ ብንጠረጥር ትቀየመን ይሆን ?

ግምቴን ላስቀምጥ ፡፡ አባ መላ አሁንም የኢሃዴግ ደጋፊ ነኝ ይለንና ፣ የተማረኩት በወያኔ ፎቅና መንገድ ነው ይለናል! እኛም እንለዋለን ! ጥልያንም ጣዝማ በርንም ፥ ጅማንም ፥የቀበና ድልድይንም ገንብቶልናል እና ጥላያን ተመልሶ ይግዛን ማለትህ ነው እንለዋለን ? ፡፡ ስለ ሃብት ክፍፍሉ ፍትሃዊ አለመሆንና ፣ ባዶ አንገታቸው ላይ ክራባት ያሰሩ የአንድ ክልል ተወላጅ  ገብሬዎች ፣ ኤምባሲያችንን ሞልተውታል እያለን ፣ በዘረኝነትና በሙስና የተበከለን መንግስት እደግፈዋለሁ ሲለን ሃሳቡ አይጋጭም  ?

አባ መላ! ምናልባት አቶ መለስ ያዋቀሩት በአህያ ቆዳ የተለበጠው ቤታቸው ከርሳቸው ህልፈት በኋላ እንደማይቆይ ቀድሞ ነቄ ስላለ ፣ፖለቲካ ዳይናሚክ ነው ፣ መገለባበጥ ነው በሚልም እሳቤ ይህን ርምጃ እንደወሰደ በገሃድ ነግሮናል ፣የአባ መላን አመል ለማወቅ ራጅ ወይም ኤክስሬይ እስካላገኝንለት ድረስ ከአባ መላ ጋር አብሮ ለመሥራት ከሌሎች ፓልቶክ ቤቶች የአድሚንነት ስራ ለማግኘት cv ያቀረቡ አድሚኖች የአባ መላን ዘላቂነት የት ያህል ተረድተዉታል ?

አባ መላ እንደሚለው ብዙ ሰነዶች በእጁ እንዳሉና ፥ በራሱ በኢሃዴግም ውስጥ ጥገናዊ ለውጥ የሚፈልጉ አመራሮች እንዳሉ ስለነገረን ፣ ይህን ነውጠኛ የዲያስፖራ ህዝብ ፣አባ መላ ከሚያውቀው የጥገና ለውጥ አቀንቃኝ የኢሃዴግ መስመር ጋር ለማዛመድ የሚወሰድ ርምጃ እንደሚሆን መገምት ቢቻልስ ፥

በመጨረሻም በወያኔያዊ ቆረጣ ፣ ይሄ አልበገር ያለውን ፣ የአባይ ቦንድን ገንዘብ አትበሏትም ብሎ ባዶ አቁማዳዎቻቸውን ይዘው እንዲመለሱ ያደረጋቸውን የዲያስፖራ ህዝብ ፣ በሚጥመውና ፥ ደስ በሚለው አራዳዊ ቋንቋ እንደ ታምራት ገለታ አነሁልሎ ፣ የወያኔን ቀላል ሚዛን ቦክሰኞች እና የገዛ ተጋሩን ሰዎች አስደንብሮ ከክፍሉ ካስወጣ በኋላ ! ኑ የሌሎች ፓልቶክ ቤት አድሚኖች ፣ እንደውም ታላቅ የፈውስ ኮንፍረንስ ለመጀመርያ ጊዜ ፣ በሳይበር አለም ከአዲስ አበባና ክምድረ አሜሪካ ያሉ ታዋቂ ተቃዋሚዎችን ስለጋበዝኩ  ዛሬና እሁድን ከኔ ጋር አሳልፉ የሚለው ግብዣ ስንቱን ጠርጎ ይወስደው ይሆን ፟? ጠርጥር ከጥህሎም አይጠፋም ስንጥር ሆኗል ተረቱ ተቀይሮ አባ መላ ! ለማንኛውም ፖለቲካ ዳይናሚክስ ነው ! አባ ድሉን ግን ትወዳቸዋለህ እንጂ ! እሳቸው እንኳ የሚከረበቱ አይመስለኝም…ለቀልድ ነው

ከአንተ ቀጥሎ በፓልቶክ ንግግር የምወዳቸው አባት ናቸው ፡፡ በተለይ ከግዕዙ ጋር ሲያዋዙት አቤት ደስ ሲል፡፡

እንግዳ ታደሰ


የታሰረው ሦስት ትውልድ

$
0
0

ትላንት ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ሲል የአውራምባ ልጆች (እኔ፣ አቤል አለማየሁ እና ኤልያስ ገብሩ) ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተገኘን፡- ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ለመጠየቅ፡፡ ርዕዮትን ከሰኞ እስከአርብ ለ10 ደቂቃ መጠየቅ ይቻላል… በዚያች 10 ደቂቃ ከሴቶች ክልል ለጥየቃ የሚወጡት ሁለት እስረኞች ብቻ ናቸው፡፡ ርዕዮት ዓለሙ እና ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ፡፡ እናም ታሳሪዎቹ ከውስጥ ወደ መጠየቂያው አጥር መጡ፡፡ በተወሰነ ርቀት ቆመው ጠያቂዮቻቸውን ያነጋግሩ ጀመር፡፡

ከርዕዮት ዓለሙ በስተግራ በኩል ፈንጠር ብለው ጠያቂዎቻቸውን የሚያነጋግሩት ወ/ሮ እማዋሽ “ከግንቦት 7 ፓርቲ ጋር በመመሳጠር ሕገ-መንግስታዊውን ሥርዓት ለመናድ” አሲረዋል ከተባሉት የኢህአዴግ ጄኔራሉች ጋር የተከሰሱ ናቸው፡፡ በዚህ ክስ የተነሳ ነው ሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓም የ25 ዓምት እስር የተፈረደባቸው፡፡

Photo

 

እናም ትናንትም የዘወትር ጠያቂዎቻዋው ከፊት ለፊታቸው ቆመዋል፡፡ አንደኛዋ ጠያቂያቸው እማሆይ ናቸው፤ የመነኩሴ ቆብ አድርገዋል፣ ነጠላቸውን እንደነገሩ አጣፍተዋል፣ መቋሚያ ተመርኩዘዋል፡፡ በግምት ዕድሜያቸው ወደ 90 ዓመት ይጠጋል፡፡ የታሳሪዋ የወ/ሮ እማዋይሽ ወላጅ እናት ናቸው፡፡ ከእሳቸው ጎን “የወርቅ ፍልቃቂ” የምትመስል ለጋ ወጣት ቆማለች፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን ትባላለች፡፡ (ፎቶዋን ይመልከቱ፡፡) እማሆይ እና ናርዶስ ያለቅሳሉ፡፡ ታሳሪዋ ወ/ሮ እማዋይሽ እንባቸውን ወደውስጥ እያመቁ እነሱን ያፅናናሉ፡፡፡፡ እናት፣ ልጅ እና የልጅ ልጅ በቃሊቲ ቅጥር ግቢ በዚህ መልኩ ማዶ ለማዶ ቆመው ሲላቀሱ ማየት ልብ ያደማል፡፡ እናም ሃዘናቸውን እያየሁ ለራሴ “እነዚህ ሰዎች የታሰረው ሦስት ትውልድ ተምሳሌት ናቸው” አልኩ፡፡ ( በወቅቱ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ በሌላ ቀን “የታሰረው ሦስት ትውልድ” በሚል ርዕስ በዝርዝር ተርከዋለሁ- አሁን ወደ ተነሳሁበት ዋንኛ ጉዳይ ላምራ)

ከላይ እንደነገርኳችሁ የተመደበልን የጥየቃ ደቂቃ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂያ ያህል ሲቀር የ25 ዓመቷ ፍርደኛ ወ/ሮ እማዋይሽ፣ ለልጃቸው ናርዶስ ሙሉጌታ የጆሮ ጌጥ በስጦታ አበረከቱላት፡፡ እናም “መልካም ልደት!” አሏት፡፡ ናርዶስ ስጦታዋን ተቀብላ እንባዋን እንደጅረት ለቀቀችው፡፡ አ…..ህ!! ከዚህ በኋላ የተሰማኝን ስሜት ለመናገር ቃል ያጥረኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ትናንት ግንቦት 16 ቀን 2005 ናርዶስ 19ኛ ዓመት የልደት በዓሏን የምታከብርበት ቀን ነበረ፡፡ እሷ ግን “መልካም ልደት” የማይባልበት ቃሊቲ ናት፤ እያለቀሰች፡፡

እናም ለዚህች ለጋ ወጣት ምንድነው የሚባለው!? መልካም ልደት!?….እን…ጃ!? ከዚህ በኋላ ስንት ልደት ይሆን በዚህ መልኩ የምታከብረው?! አላውቅም! ማንም አያውቅም!…እናም ለዚች ልጅ ልደት ምንድነው!? ወዘተ…. ይኼ ለራሴ ያቀረብኩት ጥያቄ ነው፡፡
ለማንኛውም ወግ ነውና “መልካም ልደት!” ማለት ነው የሚሻለው!!

(በነገራችን ላይ በትናንትናው ዕለት በመብራት መጥፋት ምክንያት ይህንን ማስታወሻ ልፅፍ አልቻልኩም ነበር፡፡ ፎቶዋን ብቻ ነበር በሞባይል ፖስት ያደረኩት፡፡ እናም ፎቶዋን ብቻ አይታችሁ ለናርዲ መልካም ልደት ለተመኛችኋላት የፌስቡክ ሸሪኮቼ ሁሉ በእሷ ስም ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡)
መ – ል – ካ – ም ልደት ናርዲ!!!!

የሚቀጥሉት ዓመታት የደስታ ልደት በዓል የምታከብሪበት ይሆኑልሽ ዘንድ በፅኑ እመኝልሻለሁ!!


እኛና ገዥዎቻችን – በቢርደያ ይሃማክ

$
0
0

(ፀሐፊ፡- ቢርደያ ይሃማክ   e-mail: aklilhabte@gmail.com)

ሰኞ ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. 5 ሰዓት አካባቢ ወደ ደንበል ለመሄድ ከጥቁር አንበሳ ሼል ስነሳ በየቀኑና በየቦታው እንደተለመደው ታክሲ አጣሁ፡፡ ሞልተው የሚያልፉ ታክሲዎችን በመሸኘትና የመለስ ዜናዊ ፎቶ የተለጠፈበትን ጥቁር ከነቲራ የለበሱ አንዳንድ ባልቴቶችን በማየት ብዙ ደቂቃዎችን በክብር ከሰዋው በኋላ በእግር ጉዞዬን ጀመርኩ… እነዚህን ባልቴቶች ሳይ የወጣቶች ሊግ፣ የሴቶች ሊግ እና የቀበሌ ሸማቾች ማህበር ትዝ አሉኝና ተናደድኩ፤ ለምን እንደተናደድኩ የገመተ አለ@ በጣም ጥሩ፤በደርግ ጊዜ የነበረው የአገልግሎት ሱቅ (የቀበሌ ሱቅ) ስኳር፣ አሻቦ፣ ቡና የሚሸጥበት ዋጋ ውጭ በገበያ ላይ ከነበረው ዋጋ ምን ያህል ይቀንስ እንደነበርና ከቀበሌ መግዛት በርግጥ ሰውን እንዴት ይገላግል እንደነበር ያየሁ ሰው ዛሬ የወያኔ ባላባቶችና ቁልፍ ነጋዴዎች ዋጋን እንቆጣጠራለን በማለት የሆነ ውዥንብር ፈጥረው ወይም የነሱ ብቻ በሆኑት ግዙፍ ጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶቻቸው ምርትን ሆን ብለው ደብቀውና አከማችተው የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ካደረጉ በኋላ ጅንአድ፣ ሸማቾች ወዘተ በሚሏቸው ቱቦዎቻቸው በኩል ገበያ ላይ ካለው ዋጋ አንድ ብር ወይም ሁለት ብር ብቻ በመቀነስ በውድ እየቸበቸቡ ሲከብሩ አያለሁ፡፡ የሚገርመው የአንድ ብር ቅናሽም ተስፋ የሆነችበት ይህ ምስኪን ሕዝብ ከነሱ ለመግዛት ቀኑን ሙሉ በቀበሌዎችና በሸማቾች ደጃፍ ተሰልፎ ይውላል፡፡ በነፍስም በሥጋም የሞተው የሟቹ የለገሰ ዜናዊ የሞተ መንግሥት ለምን በህዝቤ እንደሚጫወት አይገባኝም፡፡ ለምንስ የህዝቤን ሰዓት ያቃጥላል@ ይኸ እኮ ነው ወገኖቼ የዛሬ ሸማቾች፣ ቀበሌ፣ሊግ ትዝ ሲሉኝ በቶሎ የሚያናድደኝ፡፡

ጥቁር አንበሳን ሆስፒታል በስተቀኝ እያየሁ ቁልቁል ስወርድ በስደተኞችና ዜግነት ጉዳይ መሥሪያ ቤት (ኢሚግሬሽን) ለመስተናገድ የሚተራመስ ሕዝብ ታየኝ፡፡ አቤት ብዛቱ! የሰማይ ኮከብ፣ የባህር አሸዋ ወይስ ምን@ ይኸ ሁሉ ሰው ነው@ ውጭ ለመሄድ የተሰለፈ ሰው! ‰ረረ በዚህ ከቀጠለ ወደፊት ወያኔ የሚገዛው ሕዝብ እንዳያጣ ያሰጋዋል-ሰው ሁሉ ሄዶ ያልቅበታላ!

ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ 21 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያ በጎሣ ትሸንሸን በሚለው ከሰሜናዊው አባቴ ከኢሳያስ አፈወርቂ በቀሰምኩት አስተሳሰቤ ለምን ከክርስቶስ አሳንሳችሁ ታዩኛላችሁ በማለት ሲሰድበን፣ሲያዋርደንና ሲገድለን የኖረው የወያኔ አምበል ፈርኦን ለገሰ ዜናዊ በመሞቱ የተደናበሩት የሱ ደቀ-መዛሙርት ዛሬ በአደባባይ በሬዲዮና በቴሌቪዥን አንደሚነግሩን በአንድ ግለሰብ ብቻ ሲነዱ የባጁ፣ የኖሩ፣ ያረጁ የአንድ አውራጃ (የአድዋ) ሰፋ እናርግላቸው ካልንም የ3 አውራጃዎች (አሽአ-አክሱም፣ሽሬ፣ አድዋ) ዘመናዊ ነገሥታት የሥልጣኑን ቁልፍ ጨብጠው በፈጠሩት ውጥንቅጥ ኢህአዲግ የሚባለው ጭራቅ ድርጅት አባል የሆኑ ሰዎች በየቀበሌው ተደራጅተው፣ በተለያዩ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች ተቀጥረው እየጨፈሩ፣ እየሰከሩ አንዳንድ ጊዜም አንዳንዶቹ ምስኪኑን እያሰሩ ሲኖሩ፤ እየተራቡ የበይ ተመልካች የሆኑትና አገሬ ላይ በራብ ከምሞት፣ ቤተሰቦቼና ዘመዶቼ በራብ ሲሞቱ ከማይ፤ አረብ አገር ሄጄ ከፎቅ ተወርውሬ፣ በፖሊስ ተደብድቤ ወይም ትንሽ ካየሁትና ለውጥ ከሌለ ታንቄ ልሙት፤ ፈጣሪ ብሎልኝ ካልሞትኩም ለራሴና ለቤተሰቤ ትንሽ ገንዘብ አገኛለሁ በሚል በሕይወታቸው ፈርደው ወደውጭ ለመሄድ ሰልፍ የያዙትን ምስኪንና ቆነጃጅት ያገሬ ልጆች ከብዛታቸው የተነሳ ማየትና መቁጠር አቅቶኝ እግዚኢ-አቤት የፈጣሪ ያለህ፣ የመንግሥት ያለህ፣ ያገር ያለህ፣ የሕዝብ ያለህ እያልኩ ከግፊያው በመከራ ወጥቼ ቸርችል ጎዳና ገባሁ፡፡ በዐይኔ ይኸን እያየሁ አሁን ይህን ጊዜ የወያኔ ሬዲዮዎች (ቱልቱላው ፋና 98.1፣ የቀንደኛዋ ካድሬ ንፋው ዛሚ 90.ምናምን፣ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) ስለ መለስ ተዐምራትና ገድል ያወሩ ይሆናል፡፡ ምን ዐይነት ዓለም! ይህን ጊዜ እኮ በጥበብ፣ በዕውቀት፣ በሥልጣኔ የተራቀቁት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲየን ቁንጮ ላይ ዶላር ጎዝጉዘው የሚደንሱት የአሽአ (አክሱም-ሽሬ-አድዋ) ቀሳውስት፣ ሊቃውንት፣ኤጲስ ቆጶሳት፣ ጳጳሳት – – በአስደናቂ ራዕይ እየተመሩ፣ ክንፎቻቸው እያበሩ ስለ ቅዱስ፣ ሰማዕት- በስመ ድንጋጤ ወአንቅጥቅጤ፣ ልክፍተ ቡዳ በአበበ ገላው ዘጎጃም ወጎንደር ዘነገደ ይሁዳ – ለገስ መለስ – ገድል በወርቅ ብዕር እየፃፉ ይሆናል፡፡ አዎ፣ ይሁን ያርገው ይገባል፡፡ የቅዱስ ለገስ አባ መለስ ገድል ተፅፎ በስማቸው ለሚቀረፀው ታቦት ማደሪያ- ማህደር በሚሆነው ደጀ-ሰላም ውስጥ ቅዳሴ ይቀደስበታል፡፡ ውዳሴ ይወደስበታል፡፡ ልጋሴ ይለገስበታል፡፡ ህዳሴ ይኸደስበታል፣ ይታደስበታል፡፡ አሃሃሃሀ—እውነቱን ለመናገር ርካሴ፣ ርኩሰት ይረከስበታል፡፡

እየተጓዝኩ ነው፡፡ በቸርችል ጎዳና ትንሽ ከወረድኩ በኋላ ዋናው ፖስታ ቤት አካባቢ ስደርስ ወደ ግራ በመታጠፍ ወደ አምባሳደር ሲኒማ ቤት ወረድኩ፡፡ በስተቀኝ የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አላሳልፈኝ አለ፡፡ በሕንፃው ላይ የተለጠፉትን የመለስ ፎቶዎችና አብረው የተፃፉትን ተዐምራት እንደምንም ተቋቁሜ ቀጠልኩ፡፡መስቀል አደባባይማ የኢትዮጵያውያን አደባባይ መሆኑ ቀርቶ የመለስ ዜናዊ አደባባይ ሆኗል፡፡ ወይ የባንዳ ዘመን! ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነን ሰው ፎቶ በአደባባይ በመስቀል ኢትዮጵያዊያንን አንገት ማስደፋት ምን የሚሉት ኢትዮጵያዊነት ነው@ እህህህ!! ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነን ሰው ፎቶውን በመስቀል ከሞተ በኋላ ኢትዮጵያዊ ማድረግ የሚቻል መስሏቸው ይሆን@ ምስኪን አጎብዳጆች!

ከጥቁር አንበሳ እስከ ኦሎምፒያ ድረስ ያየሁትን ነገር ሳሰላስል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሳይሆን የመለስ ቤተሰቦች ለሟቹ መታሰቢያ ባሰሩት ትልቅ መቃብር ቤት ውስጥ ያለሁ መስሎኝ ደገነጥኩ፡፡ መቃብር ቦታ ሰይጣን አይጠፋም፣ መቃብር ቦታ ይከብዳል እየተባልኩ ያሳለፍኩት አስተዳደጌ ትዝ ብሎኝ በድንጋጤ ላማትብ ስል አበሩስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ወዳለው ጉዳዬ ለመውጣት የደረጃውን የመጀመሪያ መካን መርገጥ እንደጀመርኩ ተገነዘብኩ፡፡

በደርግ መንግሥት የመጨረሻ ዘመን አካባቢ የሚዘወተረው ወቅታዊ ዜና የሚከተለውን መልዕክት የያዘ ነበር- ‹‹ ገንጣዩ ሻዕብያ እና በአምሳሉ የፈጠረው ውላጁ ወያኔ በሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች መሣሪያና ገንዘብ ሰክረው፤ ኤርትራን ከእናት አገሯ ኢትዮጵያ ለመገንጠል፣ የሃገራችንን ታሪክና ቅርስ ለማጥፋት፣ የባህር በራችንን ለመዝጋት፣ ዳር ድንበራችንን ለመቆራረስና ባጠቃላይ አንድነታችንን ለመናድ እንዲሁም ሕዝቡን በጎሣና በዘር ከፋፍለው ርስበርስ እያናቆሩ አዳክመው ለመግዛት የከፈቱብንን ጦርነት ሕዝቡ በቆራጥነት እየመከተ ይገኛል›› ዛሬ ዘይት ከከተማ ሲጠፋ በቴሌቪዥን ጀሪካን ይዘው ‹‹ዘይት ሞልቷል››፣ ሕዝቡ ትራንስፖርት አጥቶ ሲሰቃይ ‹‹የትራንስፖርት ችግር የለም›› እያሉ የወያኔን የፈጠራ ወሬ በማስተጋባት የውሸት ምስክርነት የሚሰጡ ግፈኛ ፍርፋሪ ለቃሚ ካድሬዎች የሚያቃጥሉኝን ያህል በደርግ ዘመን ከያንዳንዱ ዜና ጋር የምንትሴ አስተዳደር ክልል የኢሰፓ ዋና ፀሐፊ፣ ምንትሴ እያሉ በሃገሪቱ ያለ ኢሰፓ አባል ሰው የሌለ ሲያስመስሉ ያተክኑኝ ነበር፡፡

ይሁንና ያኔ በደርግ ጊዜ ለመገንጠልና ለማስገንጠል፣ ዳርድንበር ለመቆራረስ፣ እንዲሁም የባህር በራችንን ለመዝጋት ይታገሉ ስለነበሩት ጎጠኛ ቡድኖች ይባል የነበረውን ዛሬም ስመዝነው ውሸት ላገኝበት አለመቻሌ ይገርመኛል፡፡ ርግጥ አልፎ አልፎ ጊዜ በራሱ የሚፈጥረው ተዐምር መኖሩ አይቀሬ በመሆኑ አስገንጣዩ ቡድን (ወያኔ) ፈጣሪውና አለቃው የነበረውን ቡድን (ሻዕብያን) ካጣ በኋላ ከሻዕብያ ሌላ በምድር በሰማይ ጠላት የለኝም በማለት አገር ይያዝልኝ ሲልና ተስፋ በማጣት ከመሸ በኋላ ኢትዮጵያዊ ለመምሰል በተወነው የ10 ዓመታት አድካሚ ትያትር ሲወድቅ፣ ሲነሳ፣ ሲንፈራገጥ ጀርባው ሲገጣጠብ ለማየት በመብቃታችን ወይ ዕድሜ ደጉ ብለናል፡፡ የትያትሩ ደራሲ ራዕይ ይቅርና አቋም የሚባል ነገር ያልተፈጠረበት ለፖለቲካ ጥቅምና ለሥልጣን ሲል ዛሬ በግራ ነገ በቀኝ መሰለፍ የማያሳፍረው መለስ ዜናዊ እንደነበር ‹‹ገድለ-መለስ ወለገስ የህዳሴው መሀንዲስ›› በሚለው መጽሐፍ መለሲዝም የሚለው እምነት ተከታዮች በሆኑት አብዮታዊ ካድሬዎች ተተርኮለታል፡፡ እባካችሁ ለጊዜው መሳቅ ክልክል ነው፤ እሺ@ ከሞተ ገና ዓመቱ እኮ ነው-አይሳቅም፡፡

የሆነ ሆነና በ2004 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ የሞተው መለስ ዜናዊ በርግጥ ኢትዮጵያን ሊወክል የሚችልና ለኢትዮጵያዊያን የመጣ ሰው ነበርን@@@   ይህ ጥያቄ እንቅልፍ ባይነሳኝ ኖሮ ይህን ፅሑፍ መጻፌን ትቼ አርፌ በተኛሁ ነበር፡፡

(ክፍል አንድ በሚቀጥለው ይቀርባል)


በሲዳማ ዞን ሙሰኞችን ለማጋለጥ የተጠራው ስብሰባ ተቀለበሰ

$
0
0

የሲዳማ ዞን አስተዳደር ‹‹ የመልካም አስተዳደር ችግርንና ሙሰኝነትን ለመዋጋት ›› በሚል ርዕስ በአለታ ወንዶ ከነዋሪዎችር ለመወያየት በማሰብ በአደባባይ የጥሪ ወረቀት ይለጥፋል፡…. ነገር ግን የስብሰባው ሰዓት እየተቃረበ በመጣበት ሰዓት በአደባባይ የተለጠፈው የጥሪ ወረቀት እንዲነሳ ይደረግና የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች የጥሪ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡ የተለጠፈው ወረቀት መነሳቱን ያላወቁና ስለ ከተማቸው መልካም አስተዳደር ችግርና ስለ ሰፈነው ሙሰኝነት የዞኑን አመራሮች ለማነጋገር የተዘጋጁት የአለታ ወንዶ ነዋሪዎች ስብሰባው የሚደረግበትን የሚሊኒየም አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደፉ ይሞሉታል፡፡

Shiferaw Shigute, Head of SNNP

ከስብሰባው መሪዎች አንዱ የሆኑት የሲዳማ ዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሚልዮን ማቲያስ በድንገት የድምጽ መነጋገሪያ መሳሪያውን በመጠቀም ‹‹በስብሰባው እንድትሳተፉ የጥሪ ደብዳቤ ከደረሳችሁ ሰዎች ውጪ ያላችሁ በሙሉ አዳራሹን ለቅቃችሁ እንድትወጡ ይህንን ባታደርጉ ግን ሁከት ለመፍጠር እንዳሴራችሁ በመንገር በፌደራል ፖሊስ በኃይል አዳራሹን
ለቅቃችሁ እንድትወጡ አደርጋለሁ›› በማለቱ ህዝቡ ግርግር ከመፈጠሩ በፊት አዳራሹን ለቅቆ ወጥቷል፡፡ በአዳራሹ የቀሩት ጥቂት ሰዎች ዞኑ ምንም አይነት የመልካም አስተዳደርና የሙሰኝነት ችግር እንደሌለበት በመነጋገር ስብሰባውን ማጠናቀቁን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልጸዋል፡፡


በነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ትንተና የት ያደርሰን ይሆን?

$
0
0

በቴዎድሮስ በላይ  አቶ ጁዋር ሲራጅ መሃመድ በቅርቡ ከአቶ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ በአጽንኦት ተከታትያለሁ። የሰውየው ግለ ታሪክና ያደረጋቸው ጉዞዎች መሳጭ ቢሆኑም አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው የተሳሳቱና የተዛቡ ታሪኮችን እንደገና እንዲፈትሽ፤ ሆን ብሎ እያራገበው ከሆነም ቆም ብሎ እንዲያስብበት ለመጠቆም ወደድኩ… የተሳሳተ መረጃ መረጃ ራስንም ሌላውንም ክፉኛ ይጎዳል። ሊዘህ መነሻ የሆነኝ፤ ስለ ኦሮሞ ጭቆና መነሻውን ሲገገልጽ፤ አማራዎቹ የአውሮፓን መሳሪያ ቀድመው ስላገኙ የሚል፤ መሰረት የለሽ ውንጀላው ነው።

ጋዜጠኛ ደረጀ ስለ ኦነግ አመሰራረት ሲጠይቀው፤ ጁዋር እንዲሚከተለው መለሰ።  “እንግዲህ በመቶ አመታት ወደዃላ ሂደን ስናይ አካባቢው በቡድን ግጭት የተሞላ ነበር-በተለይ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ። ከዚያ በፊት አብዛኛው የሐይማኖት ነበር። በሐይማኖት ስር የተደራጁ መንግስታት ነበር ሲጋጩ የነበሩት። ከዚያ በዃላ ግን የብሔር ግጭቶች ነበሩ። ይህ የብሔር ግጭት፤ በአማራ፣ በኦሮሞና በትግሬ የተካሄደው ነው-ኢትዮጵያን የወለደው። በዚህ ግጭት ውስጥ ቀድሞ የአውሮፓን መሳሪያ ሊያገኝ የቻለው የአማራው ሀይል አሸንፎ፤ በበላይነት አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያን ፈጠረ። “  እጅግ በጣም የገረመኝ መልስ ነው። በእርግጥ አቶ ጁዋር ብቻ አይደለም ፤ በቅርብ ጊዜ የምሰማው ከመሰሎቹ የኦሮሞ ወንድሞቼ የዕለት ከዕለት ውንጀላ ሆኗል። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፤ እንዲሉ የዚህ አይነቱን ነገር እንደ እውነት ሳይወስዱት አልቀረም።

ይሄ መልስህ፤ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሮብኛል፡

  • በውኑ ኢትዮጵያን የወለደ ከ14ኛው አመት በዃላ ያለው የብሔር ግጭት ነው?
  • ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት የሐይማኖች ግጭቶች፤ የኦሮሞ ሕዝብ የት ይሆን የነበረው?
  • በውኑ አማራው ነው የውጭዎቹን መሳራያውን ቀድሞ ያገኘው? ማረጋገጫ ልትሰጠኝ ትችላለህ? እኔ ያነበብሁትና የማውቀው ሌላ ነው።

ለምን የፈጠራ ውንጀላ ውስጥ በተለይ ማንበብና መጻፍ ከምንችል ሰዎች መካከል እንደምንዘፈቅ አይገባኝም። ሁለቱን ጥያቄዎች ለአቶ ጁዋር ትቼ፤ ለውንጀላ የተጠቀምህበትን ሶስተኛውን ጥያቄ እኔው ካነበብሁት እመልሳሃለሁ። ስህተት ከሆነ ማስረጃ ያቅርብና እንከራከርበት። ኢትዮጵያውያን እርስ በራሳቸው፤ በአካባቢያቸው በሰሩት መሳሪያ ይዋጉና አሸናፊው ይገዛ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በዚህ እርሱ እና እኔም እንስማማለን።  እንዲህ አይነቱ ልማድ በሌሎቹም አለም ሲደረግ የኖረ ሃቅ ነው። ነገር ግን የአለም ሁኔታ ተቀይሮ፤ አንዱ የሌላውን  ሃብት ድምበር አቋርጦ ለመዝረፍ ሲባል፤ ጠመንጃ መሳሪያን ይዘው ብቅ አሉ።   በመሰረቱ የጠመንጃ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው  በ14ኛው ክፍለ ዘመን በቻይናዎች ነው። ወዲያውኑም ወደ ሩቅ ምስራቆችና አውሮፓዎቹ ተዛመተ። አውሮፓውያንና ሩቅ ምስራቆች፤ በሐይማኖት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭትን አስነሱ፤ የጠበንጃ መሳሪያውንም ይዘው ተነሱ። በኢትዮጵያም ይኸው ሆነ። በወቅቱ፤ ከክርስቲያኖች ጋር ለተጣላው ግራኝ አህመድ፤ ቱርኮቹ ልዩ ሰልጠና ሰጥተው የጦር መሳሪያ አስታጥቀው፤ ከሰለጠነ ወታደር ጋር  ወደ ኢትዮጵያ አስገቡት፤ በ11529 ጀምሮ ኢትዮጵያን በይፋ ወረረ። በጦርና በጨበጣ ብቻ የመዋጋት ልምድ የነበራቸው ኢትዮጵያውያን፤ የጠመንጃ መሳሪያ የታጠቀውን መሃመድን በምንም መልኩ ሊቆጣጠሩት አልቻሉም። ብዙ የሰው ህይወትና የአገር ሃብት አወደመ። በወቅቱ የነበሩ ገዥዎች፤ እርሱን ለመቋቋም፤ ክርስቲያን ክፍል የሆኑትን ፓርችጋሎችን በመማጸን የመሳሪያና የሰው ሃይል እርዳታ አግኘተው፤ ተዋግተው አሸነፉ። ይህ ነው የጠመንጃ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ አመጣጡ። ይሄን እውነታ ቀይሮ አማሮቹ መሳሪያ ቀድሞ ስላገኑ የሚለው አካሄድ፤ ምን አይነት የፓለቲካ ትርፍ ያመጣ ይሆን? በመሰረቱ፤ የግራኝ ጦርነትን ተከትሎ ሰሜኑን የወረረው ማን ነው። የኦሮሞዎች ወረራና በቀላሉ ሰፊውን የሃገሪቱ ክፍል የመያዝ ውጤቱ፤ በግራኝ አማካኝነት የተካሄደው ጭፍጨፋ ከፍተኛ የሆነውን የአማራ  ሕዝብ ስለጨረሰ ነው። ለዚህ መከራከሪያ ምላሹን ከአቶ ጁዋር እፈልጋለሁ። የኦሮሞ ማህበረሰብ በወቅቱ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም፤ የሰሜኑን ክፍል ወርሮ ያሸነፈው ብቸኛው ምክንያት ይሄው ነው። የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጠቀመው፤ አቶ ጁዋር  እንደጠቀሰው አማራውን ሳይሆን ኦሮሞውን ነው። ከቆላማው ወደ ደጋማውና ለም የሃገሪቱ ክፍል እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎላቸዋል።  ይሄን ጥሬ ሃቅ ክዶ፤ በወቅቱ የተሰራን ግፍ ወደ ሌላው መለከክ፤ ከአንድ የፓለቲካ ተንታኝ፣ ያውም ሌሎቹን እያሰለጠነ ካለ በፍጹም አይጠበቅም።

በወንድሜ፤ በአቶ ጁዋር አካሄድ ቢተነተን፤  እስላምና በኢትዮጵያ ምድር ለመስፋፋት አስተዋጽኦ ያደረገው፤ የጠመንጃ መሳሪያ የሙስሊሞቹ መሪ የነበረ በመጀመሪያ በእጁ በቱርክ በኩል ከልዩ ስልጠና ጋር ስለገባ፤ ብዙውን ሰው አሰለመ ወደሚለው ያደርሰናል። እናም፤ ሙስሎሞች ጥፋት ስላጠፉ…..የሚል ጭልጥ ያለ ውንብድና ውስጥ ይከተናል። እኔ ግን ይሄን አልቀበለውም። ምንም ይሁን ምን፤ ደካማ ጎናችንን በመጠቀም፤ የውጭ ሃይሎች የጫኑብን መከራ ነበር ብዬ ነው የማልፈው። ለዛሬ ችግራችንም መጥቀስን አልፈልግም። ምክንያቱም፤ በእነሱ ተንኮል ስር እንደገባሁ ስለምቆጠርው። እናም ጁዋር፤ የኦሮሞ ችግር በውኑ በአማራው የደረሰብት መከራ ነበርን ለማት ታሪኩን፤ መሳሪያ ከመግባቱ በፊት የነበረውን ሁኔታ በጥልቅ እንዲያነቡና ለሁላችን የሚያስማማ፤ እያንዳንዱ ዜጋ የተከበረባት ኢትዮጵያን ለማዬት እጅግ ወሳኝ ነው እላለሁ።

አበቃሁ።


Viewing all 931 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>