Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የ8 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ካሳ የተጠየቀበት የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ክስ መዝገብ እንዲዘጋ ተደረገ፡፡

$
0
0

ሰበር ዜና

የስምንት ሚሊዮን አንድ መቶ ሽህ ብር ካሳ የተጠየቀበት የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ክስ መዝገብ እንዲዘጋ ተደረገ..

በያዝነው ሳምንት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህዝበ ሙስሊሙን የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ በደረሰው የስም ማጥፋት ወንጀል የመንግስት አካላትና ባለስልጣናትን ጨምሮ የተከፈተው የክስ ፋይል መዘጋቱን የኮሚቴዎቻችን ጠበቆች አስታወቁ፡፡

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ ዋና አስተባባሪ አቶ ተማም አባቡልጉ እንደ ገለፁት የ8 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር የሞራል ካሳ ለኮሚቴዎቹ ይገባል በማለት በ83 ሺህ ብር የከፈቱት መዝገብ መዘጋቱ አግባብ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

መዝገቡን ለመክፈት ከዚህ ቀደም የተለያዩ እንግልቶች እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ጠበቃው ጉዳዩ የማይመለከታቸው የፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ባልታወቀ ምክንያት መዘገቡን እንደዘጉት ይገልጻሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ መዝገቡ ለፍ/ቤቱ ዳኛ ቀርቦ ያስከስሳል አያስከስስም ሳይባል እኛም በፍ/ቤቱ ሳንጠራ መዝገቡ መዘጋቱ መነገሩ ፍጹም ህገወጥ ተግባር ነው በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡

ፍትህ ባለበት ሀገር ይህንን መሰል ተግባር መፈፀሙ እጅጉን እንዳሳዘናቸው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ተናግረዋል፡፡

ፍትህ በኢትዬጲያ በቁሙ ተቀበረ!!!

አላህ ይድረስልን!!!

Abu Dawd Osman


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>