አዲስ አበባ ግንቦት 10 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞኑን በሙስና ወንጀል ተጠርጥርጥረው ሲፈለጉ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል በድለላ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ዳዊት መኮንን በሻሸመኔ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ..
የፌደራል ፖሊስ ለኢትዮጱያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እንደሚፈለጉ ሲያውቁ ሸሽተው ወደ ኬንያ ለመግባት ጥረት ላይ ነበሩ፥ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የፌደራል ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪው ሻሸመኔ ላይ በቁጥጥር ስር አውሎአቸዋል፡፡
ተጠርጣሪው በአዲስአበባ እና አዳማ በሚገኙ የግምሩክ ጣቢያወች የድለላ ስራ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል፡፡![]()

Related articles
- Ethiopian Youth Initiative: Nurturing the Culture of Giving Back (kweschn.wordpress.com)
