Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ህወሓት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ፈቃዱ ታገደ

$
0
0

የቦርድ ትእዛዝ አክብሮ ካልተገኘ ከሶስት ወር በኋላ እንደሚሰረዝ ተገልጿል

የምስረታ 50ኛ በዓሉን ለማክበር ቀናት የቀሩት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ህጋዊ ፈቃዱ መታገዱን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰአታት በፊት ይፋ ባደረገው መግለጫ አስታወቀ።

ቦርዱ የህወሓትን የፓርቲ ፈቃድ የሰረዘው በልዩ ሁኔታ ተመዝግቦና የኢትዩጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ህግ፣ መመሪያና ውሳኔዎችን አክብሮ መንቀሳቀስ ሲገባው በአዋጅ ቁጥር 1232/2016 አንቀጽ 3(11) ሀ እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመሪያ አንቀጽ 16(6) ድንጋጌን ጥሷል በሚል ነው።

ነገር ግን ህወሓት ለዕግዱ ምክንያት የሆነውን ጥሰት በማረም አዋጁን፣ መመሪያውንና የቦርዱን ውሳኔዎችና ትዕዛዝ በማክበር ፓርቲው ሊያደርግ የሚገባውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ የሚያስችለውን የጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ለመስራት ለቦርዱ በጽሁፍ ሲያሳውቅና ቦርዱ ይህንኑ ሲያረጋግጥ በመመሪያው አንቀጽ 18(2) መሠረት እግዱን የሚያነሳለት መሆኑን አስታውቋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>