Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 944

በቻይና ከሚመረቱት ርካሽ ልብሶች ጀርባ ያለው እውነታ

$
0
0

በቻይናዋ ከተማ በጉዋንዡ የልብስ ስፌት ማሽን ድምጽ መስማት የተለመደ ነው። ከጠዋት እስከ ማታ ከፋብሪካዎች ድምጹ በመስኮት በኩል ይሰማል። ካናቴራ፣ ሱሪ፣ ሹራብ፣ ቀሚስ ይሰፋል። ከ150 አገራት በላይ የሚላክ ምርት ነው። ፓንዩ የተባለው ሰፈር ሼን የሚባል መንደር አለ። በዓለም በፋሽን ውስጥ የሚታወቁ ልብሶች መነሻ ነው። አንድ የፋብሪካው ሠራተኛ “በወር ውስጥ ባሉት ቀናት እሠራለሁ” ትላለች። አብዛኞቹ ሠራተኞች ቢበዛ አንድ ቀን እረፍት ነው የሚያገኙት። ቢቢሲ በጎበኛቸው 10 ፋብሪካዎች፣ ከአራት በላይ አስተዳዳሪዎችን እና ከ20 በላይ ሠራተኞችን አነጋግሯል። የጨርቃ ጨርቅ እና ልብስ ገበያ ላይም ቢቢሲ ቅኝት አካሂዷል። የቅንጡ ፋሽን ልብሶች መነሻው በሳምንት 75 ሰዓት የሚሠራበት ፋብሪካ ነው። ድርጊቱ በቻይና ሕግ ተከልክሏል። ሆኖም ግን ፋብሪካዎች ሥራ ለማግኘት የሚጣጣሩ ሰዎችን በመቅጠር ለሰዓታት ማሠራት አላቆሙም። ሼን መንደር ቀድሞ እምብዛም አይታወቅም ነበር። ባለፉት አምስት ዓመታት ግን በክፋት በመሞላቱ የሚነሳ መንደር ሆነ። የግለሰቦች ንብረት የሆነው ሰፈር ወደ 66 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ ይገመታል። ሠራተኞችን በመበዝበዝ እና በግዳጅ በማሠራት ክስ ይቀርብበታል። አምና ልጆች ሠራተኞች በፋብሪካው መገኘታቸውን ተቋሙም አምኗል። “በተቋማችን በማንኛውም እርከን የሚሠራ ሰው በፍትሐዊ መንገድ እና ክብሩ ተጠብቆ ነው የሚሠራው” የሚል መግለጫ ከመስጠት ውጭ ለቢቢሲ ጥያቄዎች ለመመለስ አልፈቀደም። ተቋሙ አመራርን ለማጠናከር “በአሥር ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ኢንቨስትመንት” እንደሚያወጣና አብረውት የሚሠሩ ተቋማት “በፍትሐዊነት እንደሚሠሩ ለማረጋገጥ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን” እንደሚሠራም አክሏል። በሼን መንደር የሚሠሩ ቀሚሶች 10 ፓውንድ፣ ሹራቦች 6 ፓውንድ የሚሸጡ ሲሆን፣ አማካይ የሽያጭ ዋጋው 8 ፓውንድ ነው። የሚያገኘው ትርፍ በጣም ጨምሯል። ትርፋማነቱ ታዋቂ የልብስ አምራች ከሆኑት ከኤችኤንድኤም፣ ዛራ እና ፕሪማርክ በልጧል። ሼን መንደር 5,000 ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን፣ አስፈላጊ ግብዐቶች በዚያው በመንደሩ ይገኛሉ። መንደሩ እና በውስጡ ያሉ ክፍሎችም በልብስ እና በጨርቅ ቁርጥራጭ ይሞላሉ። ሌሊቱ ቢጋመስም ሠራተኞቹ ከልብስ በስፊያ ማሽን ላይ አይነሱም። የ49 ዓመቷ የፋብሪካው ሠራተኛ “ከ10 እስከ 12 ሰዓት እንሠራለን። በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ሦስት ሰዓት ይሰጠናል” ትላለች። በሼን መንደር ያሉ ፋብሪካዎች የልብስ ትዕዛዝ ተቀብለው ይሠራሉ። ቀድሞ ተሠርተው የተወደዱ ልብሶች ካሉ ፋብሪካው በብዛት ያመርታል። በቋሚ ሠራተኞቹ ኃይል ሥራው የማይጠናቀቅ ከሆነ ጊዜያዊ ሠራተኞች ይቀጥራል። ከአካባቢው ከተሞች ተሰደደው በፋብሪካው የሚሠሩ ብዙ ናቸው “በጣም ትንሽ ነው የሚከፈለን። ኑሮ ግን ውድ ነው። ለሁለት ልጆቼ የምልከው በቂ ገንዘብ ማግኘት እፈልጋለሁ” ትላለች ከሠራተኞቹ አንዷ።ሠራተኛዋ እንደምትለው የሚከፈላቸው በሚሰፉት ልብስ መጠን ነው።”በቀላሉ የማይሰፋ ልብስ ከሆነ ሁለት ዩዋን ይከፈለናል። በአንድ ሰዓት አሥር ልሠራ እችላለሁ” ትለላች። ክፍያው ከሁለት ዶላር ያነሰ ነውምን ያህል ልብስ ቀዶ ምን ያህል መስፋት እንደሚቻል ሠራተኞቹ ያሰላሉ። በሰዓት ውስጥ ስንት እንደሚከፈላቸውም ያስባሉ። ፓኑዩ የተባለው አካባቢ ገበያ ይበዛዋል። ሠራተኞች እንቁላል፣ ዶሮ እና ወተት ከዚህ ይሸምታሉ። ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ምሽት 5 ሰዓት እንደሚሠሩ ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል። የስዊትዘርላንድ የመብት ተሟጋች ተቋም 13 የፋብሪካው ሠራተኞችን አነጋግሮ ባወጣው ሪፖርት ያስቀመጠው ግምትም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። በሼን መንደር ተጨማሪ ሰዓት የሚሠሩ በርካታ ናቸው። ያለ ትርፍ ጊዜ ክፍያ የሚሰጥ ደመወዝ ከ 2,400 ዩዋን (327 ዶላር) የሚጀምር ሲሆን፣ በእስያ አነስተኛ ክፍያ ወለል ከተቀመጠው በ6,512 ያንሳል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሠራተኞች በወር የሚያገኙት ክፍያ ከ4,000 እስከ 10,000 ዩዋን ነው። የስዊትዘርላንድ የመብት ተሟጋች ተቋም ባለሙያ ዴቪድ ሀችፊልድ “በጣም ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ መሆኑ መታወቅ አለበት” ይላል። የቻይና ሠራተኞች ሕግ በሳምንት ከ44 ሰዓት በላይ መሥራትን አይፈቅድም። ሠራተኞች በሳምንት ቢያንስ አንድ የእረፍት ቀን እንዲኖራቸውም ይደረጋል።

ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ምሽት 5 ሰዓት እንደሚሠሩ ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል
የምስሉ መግለጫ,ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ምሽት 5 ሰዓት እንደሚሠሩ ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል

ቀጣሪ ይህንን የእረፍት ጊዜ መጨመር ካስፈለገው በልዩ ሁኔታ ይስተናገዳል። የሼን ፋብሪካ ዋና መቀመጫ ሲንጋፖር ቢሆንም አብዛኛው ምርቶቹ የሚሠሩት ግን ቻይና ነው። የቻይና ተቋማትን ሁሌም በጥርጣሬ የምታየው አሜሪካ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለች ትገኛለች። ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አድርገው የሾሟቸው ማርኮ ሩቢዮ ስለ ሼን “ከፍተኛ የሥነ ምግባር ጥያቄ አለኝ” ብለዋል።”በባርነት ሰዎች ተይዘው የጉልበት ብዝበዛ ይፈጸማል። ከሼን ጀርባ ያለው ምሥጢር ይሄ ነው” ሲሉም አክለዋል። የሰብአዊ መብት ተቋማት እንደሚሉት በሼን ሠራተኞች ለረዥም ሰዓታት መሥራታቸው የመብት ጥሰት ነው። ሠራተኞቹ ለምሳ እና እራት ብቻ ነው ጥቂት እረፍት ያላቸው። መቀመጫ ቦታ ስለሌለ መንገድ ላይ ይመገባሉ። “ከ40 ዓመታት በላይ በዚህ ፋብሪካ ሠርቻለሁ” ትላለች አንድ በ20 ደቂቃ ምሳ ለመብላት የምትጣደፍ ሠራተኛ። በፋብሪካዎቹ ያለው መብራት ትልቅ ነው። በውስጡ በተለጠፈ ማሳሰቢያ ከዕድሜ በታች ያሉ ሠራተኞች ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ይጠይቃል።

ሼን መንደር
የምስሉ መግለጫ,ሼን መንደር 5,000 ፋብሪካዎች አሉት

አምና ሁለት ከዕድሜ በታች የሆኑ ሠራተኞች መገኘታቸውን ተከትሎ ነው ማሳሰቢያው የተለጠፈው። በአሜሪካው ዴላዌር ዩኒቨርስቲ የፋሽን ጥናት ባለሙያ ሸንግ ሉ “ገጽታቸውን ለመጠበቅ እየሞከሩ ነው” ይላል። “ሼን ስኬታማ ከሆነ ሽያጩን ማስፋት ይችላል። ኢንቨስተሮች ሊያምኑበት እና ኃላፊነቱን ሊወስዱም ይችላሉ” ይላል። ፋብሪካው በለንደን የስቶክ ገበያ ለመሳተፍ እየተጠባበቀ መሆኑን ቢቢሲ ተረድቷል። ከቻይናዋ ዢንዢግ ግዛት ጥጥ ያስመጣል የሚል ክስም በፋብሪካው ላይ ቀርቧል። ቻይና ብታስተባብልም፣ ይህ ግዛት የኡግሁር ሙስሊሞች በግዳጅ ለሥራ የተዳረጉበት እንደሆነ ተገልጿል። “በፋብሪካው ውስጥ ያለው መረጃ በዝርዝር ይፋ መሆን አለበት። የመጓጓዣ መስመርን ጨምሮ ሁሉም መረጃ ይፋ ካልተደረገ ለሼን ፈታኝ ይሆናል” ይላል የፋሽን ጥናት ባለሙያው ሸንግ ሉ።

ሼን መንደር
የምስሉ መግለጫ,በሼን መንደር ያሉ ፋብሪካዎች የልብስ ትዕዛዝ ተቀብለው ይሠራሉ

የፋብሪካው ተገዳዳሪ የሆኑ ተቋማት በቬትናም እና በባንግላዲሽ ይገኛሉ። ከቻይና ግብዐት በመግዛት ልብስ ያመርታሉ። ቻይና ውስጥ የሚመረው ልብስ ግን ሙሉ በሙሉ የሚሠራው በቻይና ግብዐት ነው። በፍጥነት የተለያየ ሥሪት ያላቸው ጨርቆችን ማግኘት ይቻላል። እንደ ሼን ያሉ ፋብሪካዎች የሚጠቀሙት ይህንን መንገድ ነው። ገዢዎች አንድን ልብስ በበይነ መረብ ሲያዙ ወይም አንድ ዓይነት ልብስ እያዩ ረዥም ጊዜ በበይነ መረብ ላይ ሲያጠፉ መረጃው ወደ ፋብሪካው የሚተላለፍበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ፋብሪካው የትኞቹን ምርቶች በብዛት ማዘዝ እና መሥራት እንዳለበት የሚያውቅበት መንገድ ነው።

ቅንጡ የፋሽን ልብሶች መነሻ በሳምንት 75 ሰዓት የሚሠራበት ፋብሪካ ነው
የምስሉ መግለጫ,ቅንጡ የፋሽን ልብሶች መነሻ በሳምንት 75 ሰዓት የሚሠራበት ፋብሪካ ነው

አንድ የፋብሪካ ባለቤት “ሼን መንደር ውስጥ ያለው ጥሩ ነገር የሚታዘዙ ምርቶች ብዙ መሆናቸው ነው። የሚገኘው ትርፍ ግን ውስን ነው” ብሏል። ፋብሪካው ገበያ ላይ ይዞት የሚወጣውን ልብስ ከሌሎች ፋብሪካዎች ባነሰ ገንዘብ በመሸጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ስለሚሞክር ለሠራተኞች የሚሰጠውን ክፍያ መጠን ይቀንሳል።ሦስት ፋብሪካ ያለው ኃላፊ “ሼን መንደር ሳይኖር በፊት በግላችን ነበር ልብስ ሠርተን የምንሸጠው። ዋጋውን መወሰን እንችል ነበር። ወጪ ለመቀነስ መንገዶችን እንፈልጋለን” ብሏል። ፋብሪካው በአንድ ቀን በአማካይ አንድ ሚሊዮን ምርት ይልካል።

ሠራተኞቹ ከልብስ በስፊያ ማሽን ላይ አይነሱም
የምስሉ መግለጫ,ሌሊቱ ቢጋመስም ሠራተኞቹ ከልብስ በስፊያ ማሽን ላይ አይነሱም

ሺፕሜትሪክስ የተባለው ተቋም እንደሚጠቁመው፣ ሼን በፋሽን ኢንዱስትሪው ታዋዊ ሆኗል። ለሼን ምርት የሚያቀርበው ጉዎ ኩዊንግ ኢም በዚህ ይስማማል። “ምን ያህል እንዳደገ ማየት ችያለሁ። በቻይና ጥሩ የሚባል ድርጅት ነው። ቶሎ ስለሚከፍል በጣም እየጠነከረ እንደሚሄድ አምናለሁ” ይላል። ፋብሪካው መክፈል የሚጠበቅበትን ገንዘብ በሚሊዮን የሚቆጠር ቢሆንም እንኳን ሳይዘገይ እንደሚከፍል ይናገራል።

የግለሰቦች ንብረት የሆነው ሰፈር ወደ 66 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ ይገመታል
የምስሉ መግለጫ,የግለሰቦች ንብረት የሆነው ሰፈር ወደ 66 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ ይገመታል

አነስተኛ ገንዘብ ስለሚከፍላቸው የሚያማርሩ ሠራተኞች በርካታ ቢሆኑም በፋብሪካው ደስተኛ የሆኑም አልታጡም።

አንድ ሠራተኛ “ቻይናውያን ለዓለም ማበርከት የምንችለው አስተዋጽኦ ነው። የምንሠራው ረዥም ሰዓት ነው። ግን እንደ ቤተሰብ ነን፣ እንግባባለን” ብላለች።

ሁሉም ሠራተኞች ወደ ቤታቸው ከሄዱ በኋላ ቀርተው የሚሠሩ የበለጠ ገንዘብ ለማግኘት እንደሚጥሩ አንድ የፋብሪካ ባለቤት ተናግሯል።

አሁንም ድረስ በለንደንም ይሁን ቺካጎ፣ በሲንጋፖርም ይሁን ዱባይ፣ በሁሉም አገራት ሸማቾች በአነስተኛ ገንዘብ ልብስ ለማግኘት መሞከራቸውን ይቀጥላሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 944

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>