Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

በሰሜን ወሎ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ህፃናትን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን የዳሰሳ ጥናት አመለከተ

$
0
0

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ከፍተኛ ምግብ እጥረት የእናቶች እና የህጻናት ሕይወት ማለፉ በዳሰሳ ጥናት ተረጋገጠ።

ካለፈው ወር ጀምሮ በወረዳው ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን ቢቢሲን ጨምሮ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፤ ለዕይታ የሚረብሹ ምሥሎችም ይፋ ሆነዋል።

የአካባቢውን የምግብ እጥረት ለማረጋገጥ አጭር ዳሰሳ ያደረገው ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ቀውሱ ከተነገረው በላይ “ከባድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ብሏል።

ስድስት ባለሞያዎችን ያካተተ ቡድን በቡግና ወረዳ አራት “ቁልፍ” ቀበሌዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ የህክምና አገልግሎት እጦት እና የውሃ ችግር ማኅበረሰቡ መጎዳቱን አመልክቷል።

ቡግና ወረዳ በድርቅ የሚታወቅ አካባቢ ከመሆኑ ባለፈ የሰሜኑ ጦርነት ጠባሳ ያረፈበት እና ባለፈው ዓመት የጎርፍ እና የበረዶ አደጋዎችን በማስተናገዱ ማኅበረሰቡ “ፍሬ” እንዳላገኘ አርሶ አደሮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወረዳው ከአንድ ዓመት በላይ በፋኖ ኃይሎች መያዙን ተከትሎ፤ ወደ አካባቢው ማደባሪያን ጨምሮ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓቶች፣ የአንቡላንስ አገልግሎት፣ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም የሴፍቲ ኔት እገዛዎች መቋረጣቸው ታውቋል።

“ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ተዳምረው ነው [ማኅበረሰቡን] ለእንዲዚህ ዓይነት ችግር የተዳረገው” ሲሉ የወረዳውን የቀውስ ምክንያት የተናገሩት አንድ የጥናት ቡድኑ አባል፤ የሰው ሕይወት ማለፉንም ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ባለሙያው ምልከታ ባደረጉባቸው እና ጤና ጣቢያ ባላቸው አራት ቀበሌዎች እናቶች እና ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በምግብ እጥረት መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

ቢቢሲ የተመለከተው እና የወረዳውን የምግብ እጥረት እና የጤና ሁኔታን የሚዳስሰው ጥናት ከወሊድ ጋር በተያያዘ ከተመዘገቡ ሞቶች ውጪ አምስት ህፃናት እና ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ይገልጻል።

ሦስት ህፃናት በቆብ ቀበሌ (ክላስተር) ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ብርቆ እና ቅዱስ ሀርቤ በተባሉ ቀበሌዎች ደግሞ ሁለት የህፃናት ሕይወት አልፏል።

ዜና ምንጭ BBC NEWS


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>