Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ዊንዲ ሸርማን ለምን ኢህአዴግን ዴሞክራሲያዊ ነው አለች? የአሜሪካም መንግስትም ቢሆን ስለምን ከኢህአዴግ ጎን ሊቆም ቻለ/ፈለገ?

$
0
0

sherman-1024x693መልሱ አንድና አንድ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ይሁኑም መሳሪያ ይያዙም፣አክቲቪስቶች፣ሲቪል ተቋማትና ድርጅቶች ወሬ በማብዛት ተጽዕኖ መፍጠር የማይችል ተቋም ባለመፍጠራቸው አሜሪካኖች ስለተረዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ላይ መከራ እንዲበዛ ያደረጉት ጠንካራ ተቋም መፍጠር ባለመቻላቸው በሺህ የሚቆጠር ተቋም ፈጥረው፣..

ዓላማቸው ግን ተመሳሳይ የሆነ ድርጅቶች እንደ አሸን መፍላቱና የጋራ መግባባት የሌለበት የዝና ፖለቲካ ላይ በመጠመዳቸው ነው፡፡ የኢሳትን ተቋም ያክል ተጽእኖ ፈጣሪ ተቋም እስካሁን አላየንም፡፡ ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በህይወት ዘመናቸው ካበረከቱት አስተዋጽኦ ተቋም መሰረቱ ሊባል የሚችለው በኔ እይታ ኢሳት ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ኢሳት የፖለቲካ ተቋም አይደለም፡፡ ብታምኑም ባምኑም ያ ማለት ለየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት የወገነ አይደለም፡፡ በተቃራኒው ለህዝብ እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካ ተቋማት እርስ በርስ እየተወቃቀሱ(የወያኔም እጅ እንዳለበት ሆኖ) አንድ የረባ ስራ የሰራ ፓርቲም ሆነ ግንባር የለም፡፡ ምናልባት በኔ እይታ ሰማያዊ ፓርቲ እየተንገዳገደም ቢሆን ተጽእኖ ፈጣሪ ተቋም ልንለው እንችላለን፡፡ ከውጪ ደግሞ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ደግሞ እንደ ተቋም ባማኑበት መንገድ መሬት ላይ ስራ እየሰራ ተጽእኖ እየፈጠረ የሚገኝ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ከነዚህ ውጪ ያሉት ድርጅቶች በሙሉ ብንገመግም በአንድ ዓመት ውስጥ ምን ስራ ሰርተዋል? እንደምታውቁት ስራ ላይ ያለ ተቋም ቢያንስ በኢቲቪ ዜና ላይ እንሰማለንና፡፡ ወደ ዋናው ቁም ነገር ስመለስ ታዲያ የአሜሪካ መንገስት ስለምን ከኢህአዴግ ጎን ሊቆም ቻለ የሚለውን ምስጢር ፈትሾ የጋራ አቋም መውሰዱ ተገቢና ብልህ ስትራቴጂ ይሆናል፡፡ በኔ ግምት የአሜሪካ መንግስት ከወያኔ ጎን ሊቆም የቻለበት ምክንያት፡-

አንድ
የሃይል ሚዛን ለጊዜው ማን ጋር እንዳለ በመረዳት
ሁለት
የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከመጮህ ውጪ በጋራ ተባብረው የጋራ ጠላታቸውን መዋጋቱ ላይ መለያየታቸው መቼውንም ቢሆን የማይፈታ ስለመሰላቸውና በመገንዘባቸው
ሶስት
ከወያኔ በኋላ ያለ መረጋጋት ቢፈጠር ምስራቅ አፍሪቃ የስጋት ቀጣና ስለሚሆን ወያኔ ቢቀጥል ይሻላል የሚል እሳቤ በአሜሪካኖቹ መኖር
አራት
ወያኔ የትኛውንም የአሜሪካንን ፍላጎት መቶ በመቶ ለሟሟላት ዝግጁ በመሆኑና ይህንንም በተግባር እያረጋገጡ መምጣታቸው
አምስት
ሀገር ቤት የሚገኘው ህዝብ አለመቃወምን፣ከመታሰር ባርነትን እንደ ባህል ወስዶ መኖር የሚፈልግ፣ ጥቂቶች መስዋእትነት ከፍለው እንዲያልፍለት የሚፈልግ ዜጋ መኖሩን አሜሪካኖች ከኛ በላይ መገንዘባቸው
በአጠቃላይ ወደድንም ጠላንም የአሜሪካና አውሮፓ መሪዎችም፣ተቋማትም በየጊዜው ተቃዋሚዎችን እየጠሩ የሚያናግሩት መረጃ ለመሰብሰብ እንጂ ምንም ሊፈይዱ አይደለም፡፡ አዳሜ እከሌ እንትናን አናገረ ምናምን እያላችሁ ራሳችሁ አታጃጅሉ፡፡ ማንም የውጪ ተቋም ሲያናግር የተቋዋሚዎች እንቅስቃሴ ምን ያህል ደረጃ ላይ ደርሷል፣የህዝቡ ብሶት ምንድነው፣ቀጣይ የተቃዋሚ እቅድ ምንድነው፣ስንት ሰው ታሰረ፣ተሰደደ እያሉ የጥናት ፕሮፖዛል ለመጻፍ ወይም Research paper ለመስራት እንጂ ውጤት ለማምጣት ነው ብላችሁ የምታላዝኑ ከሆነ ተሸውዷችኋል፡፡ ያ ማለት የሚሰራው የዲፕሎማሲ ስራ ዋጋ የለውም እያልኩ አይደለም፡፡
በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት በሰማያዊ ፓርቲና በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ምክንያት እየታፈሱ ለሊት ለሊት እየተገረፉ የሚያድሩትን ወጣቶች የምንደርስላቸው ወይም የምናድናቸው በጋራ ከልብ ወተትን ስንተገብር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ወደ መሬት መውረድ አለበት፡፡ የራሳችንን ሀገር ራሳችን ብቻ ነው የምንገነባው፡፡ ያኔ አሜሪካም፣አውሮፓም ከጎናችን የመሰላፈቸው ነገር ያኔ ይታያል፡፡
ድል የሰፊው ህዝብ ነው፣(ደርግ ስታይል)



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>