Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ሰበር ዜና – ከማህከላዊ ማሰቃያ እስር ቤት!

$
0
0
የአንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሰላማዊ ታጋዮች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከሀያ ቀን በፊት በወያኔ አፋኝ ቡድን መታፈናቸው ከተሰማ ወዲህ ወጣቶቹ በማህከላዊ ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ መገኘታቸው ታውቋል..

11070480_793005004117769_6875115708675681738_nይሄንን አስመልክቶ በዛሬው ቀን 10/07/07/ ከ 8/ሰሀት በኃላ ያሉበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ወደ ቦታው በመሄድ ጥየቃ ለማድረግ ብንሞክርም ጥየቃ እንደማይቻል ነገር ግን ስንቅ ብቻ ማስገባት እንደሚቻል ተገልጾልን የቅርብ ቤተሰብ የሆነ ሰው ብቻ ከሆናችሁ ግን ወደ ቢሮ ቁጥር/35/ በመሄድ አስመዝግባችሁ መገናኘት ይቻላል ቢባልም ወደ ቦታው በመሄድ ስንጠይቅ እንደዚ የሚባል እስረኛ የለም ተብሉዋል፡፡

ቀደም ሲል እስረኞቹ መኖራቸው ከመዝገብ ተረጋግጦ መጠየቅ የሚችለው ቤተሰብ ብቻ ነው፡፡ በተባልነው መሰረት የጠየቅን መሆኑን ብንገልጽም የተባሉትን ሰዎች አናውቃቸውም በማለት ሁለት የተለያየ ምክንያቶች ሲሰጡ ለማየት ተችሉዋል፡፡

ነገር ግን ወጣት ብርሀኑ ተ/ ያሬድ ከወላጅ እናት ጋር ለጥቂት ደቂቃ ቢሆንም ያገኙት ሲሆን በመልካም ሁኔታ እንደሚገኝ ለቤተሰቡ መግለጹን ለማወቅ ተችሉዋል፡፡ የወያኔ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲን ካፈረሰ በኃላ ድርጊቱን የተቃወሙ አባሎች ላይ ከፍተኛ መንገላታት እና አፈና እየተፈጸመባቸው የሚገኝ ሲሆን ይሄንን አስመልክቶ ከሀያ ቀን በፊት ከሸዋ ሮቤት የታፈነው ወጣት ዘሪሁን ገሰሰ እስካሁን የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በማህከላዊ ማጎሪያ እስር ቤት ከሚገኙት ሰላማዊ ታጋዮች ጋርም እንደሌለ ለማወቅ ተችሉዋል፡፡



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>