Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 941

የታሰረው ሦስት ትውልድ – ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ለመጠየቅ

$
0
0

ryot Alemuትላንት ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ሲል የአውራምባ ልጆች (እኔ፣ አቤል አለማየሁ እና ኤልያስ ገብሩ) ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተገኘን፡- ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ለመጠየቅ፡፡ ርዕዮትን ከሰኞ እስከ አርብ ለ10 ደቂቃ መጠየቅ ይቻላል….

ryot-Alemu

በዚያች 10 ደቂቃ ከሴቶች ክልል ለጥየቃ የሚወጡት ሁለት እስረኞች ብቻ ናቸው፡፡ ርዕዮት ዓለሙ እና ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ፡፡ እናም ታሳሪዎቹ ከውስጥ ወደ መጠየቂያው አጥር መጡ፡፡ በተወሰነ ርቀት ቆመው ጠያቂዮቻቸውን ያነጋግሩ ጀመር፡፡
ከርዕዮት ዓለሙ በስተግራ በኩል ፈንጠር ብለው ጠያቂዎቻቸውን የሚያነጋግሩት ወ/ሮ እማዋሽ “ከግንቦት 7 ፓርቲ ጋር በመመሳጠር ሕገ-መንግስታዊውን ሥርዓት ለመናድ” አሲረዋል ከተባሉት የኢህአዴግ ጄኔራሉች ጋር የተከሰሱ ናቸው፡፡ በዚህ ክስ የተነሳ ነው ሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓም የ25 ዓምት እስር የተፈረደባቸው፡፡
እናም ትናንትም የዘወትር ጠያቂዎቻዋው ከፊት ለፊታቸው ቆመዋል፡፡ አንደኛዋ ጠያቂያቸው እማሆይ ናቸው፤ የመነኩሴ ቆብ አድርገዋል፣ ነጠላቸውን እንደነገሩ አጣፍተዋል፣ መቋሚያ ተመርኩዘዋል፡፡ በግምት ዕድሜያቸው ወደ 90 ዓመት ይጠጋል፡፡ የታሳሪዋ የወ/ሮ እማዋይሽ ወላጅ እናት ናቸው፡፡ ከእሳቸው ጎን “የወርቅ ፍልቃቂ” የምትመስል ለጋ ወጣት ቆማለች፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን ትባላለች፡፡ (ፎቶዋን ይመልከቱ፡፡) እማሆይ እና ናርዶስ ያለቅሳሉ፡፡ ታሳሪዋ ወ/ሮ እማዋይሽ እንባቸውን ወደውስጥ እያመቁ እነሱን ያፅናናሉ፡፡፡፡ እናት፣ ልጅ እና የልጅ ልጅ በቃሊቲ ቅጥር ግቢ በዚህ መልኩ ማዶ ለማዶ ቆመው ሲላቀሱ ማየት ልብ ያደማል፡፡ እናም ሃዘናቸውን እያየሁ ለራሴ “እነዚህ ሰዎች የታሰረው ሦስት ትውልድ ተምሳሌት ናቸው” አልኩ፡፡ ( በወቅቱ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ በሌላ ቀን “የታሰረው ሦስት ትውልድ” በሚል ርዕስ በዝርዝር ተርከዋለሁ- አሁን ወደ ተነሳሁበት ዋንኛ ጉዳይ ላምራ)
ryot Alemu 2ከላይ እንደነገርኳችሁ የተመደበልን የጥየቃ ደቂቃ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂያ ያህል ሲቀር የ25 ዓመቷ ፍርደኛ ወ/ሮ እማዋይሽ፣ ለልጃቸው ናርዶስ ሙሉጌታ የጆሮ ጌጥ በስጦታ አበረከቱላት፡፡ እናም “መልካም ልደት!” አሏት፡፡ ናርዶስ ስጦታዋን ተቀብላ እንባዋን እንደጅረት ለቀቀችው፡፡ አ…..ህ!! ከዚህ በኋላ የተሰማኝን ስሜት ለመናገር ቃል ያጥረኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ትናንት ግንቦት 16 ቀን 2005 ናርዶስ 19ኛ ዓመት የልደት በዓሏን የምታከብርበት ቀን ነበረ፡፡ እሷ ግን “መልካም ልደት” የማይባልበት ቃሊቲ ናት፤ እያለቀሰች፡፡
እናም ለዚህች ለጋ ወጣት ምንድነው የሚባለው!? መልካም ልደት!?….እን…ጃ!? ከዚህ በኋላ ስንት ልደት ይሆን በዚህ መልኩ የምታከብረው?! አላውቅም! ማንም አያውቅም!…እናም ለዚች ልጅ ልደት ምንድነው!? ወዘተ…. ይኼ ለራሴ ያቀረብኩት ጥያቄ ነው፡፡
ለማንኛውም ወግ ነውና “መልካም ልደት!” ማለት ነው የሚሻለው!!
(በነገራችን ላይ በትናንትናው ዕለት በመብራት መጥፋት ምክንያት ይህንን ማስታወሻ ልፅፍ አልቻልኩም ነበር፡፡ ፎቶዋን ብቻ ነበር በሞባይል ፖስት ያደረኩት፡፡ እናም ፎቶዋን ብቻ አይታችሁ ለናርዲ መልካም ልደት ለተመኛችኋላት የፌስቡክ ሸሪኮቼ ሁሉ በእሷ ስም ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡)
መ – ል – ካ – ም ልደት ናርዲ!!!!
የሚቀጥሉት ዓመታት የደስታ ልደት በዓል የምታከብሪበት ይሆኑልሽ ዘንድ በፅኑ እመኝልሻለሁ!!



Viewing all articles
Browse latest Browse all 941

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>