በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘው ክስ መዝገብ የተከሰሱት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጉዳይ በመያዝ የሕግ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ድብደባ ተፈፀመባቸው…
ድብደባው የተፈፀመባቸው ዛሬ እነ አብርሃ ደስታ በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተገኝተው የሚጠበቅባቸውን የሕግ አገልግሎት ሰጥተው ከፍርድ ቤት ሲወጡ ቅጥረኛ በሆነ ግለሰብ ድብደባ ሊፈፀምባቸው ችሏል።
ደብዳቢው ድብደባ ከፈፀመ በኋላ እሩጦ ለማምለጥ ያደረገው ሙከራ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን አስደናቂ ትብብር የተያዘ ሲሆን፤ ጉዳዩ ለፖሊስ በማመልከት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል።
