
ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የ 14 ቀን የጊዜ ገደብ ጠይቋል። ዳኛው ተጠርጣሪዎቹ የሚናገሩት ነገር ካለ የፈቀዱላቸው ሲሆን ሶስቱ እንደተናገሩት ስለ ጉዳዩ ምንም እንደማያቁ ለምን በዚ ወንጀል እንደተከሰሱ እንዳልገባቸውና ንፁሀን እንደሆኑ ተናግረዋል።
ችሎቱ በቀጣይ ህዳር 22, 2007 የተቀጠረ ሲሆን ፖሊስ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ሁሉ አሰባስቦ እንደሚያቀርብ ተናግሯል የሀና ቤተሰቦች በበኩላቸው ሀና የተናገረችው የሶስቱ ተጠርጣሪዎችን ስምመያዛቸውንና ሁሉም መረጃዎች ሲቀርቡ በደንብ ግልፅ እንደሚሆን ተናግረዋል።
ለሀና ቤተሰቦች ትልቅ መፅናናትን እመኛለሁ!!!!
