Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ዶክተር ህወሓት በመስቀለኛ መንገድ ላይ

$
0
0
ከእንግዲህ ወዲያ ግዜው ለዶክተር ህወሓት የዋዛ አይመስልም፡፡ ታግዬለታለሁ፤ ልማትም ዴሞክራሲም አጎናፅፌዋለሁ፣ ታማኝ ደጀኔም እሱ ነው ብላ የምትመካበት የትግራይን ህዝብ በአይነቱ የተለየና ከባድ ፍጥጫ እየገጠማት ነው፤ ህወሓት በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች…

በሙስና የተጨማለቀውን መዋቅርዋ ሳይውል ሳያድር ካላፀዳች፤ በመልካም አስተዳደር እጦት በከፍተኛ ደረጃ የተማረረውን ህዝብ በኣስቸኩዋይ ካላረመች፤ የውሸት ዳታን እየጋገርኩ ህዝብን በባዶ ተስፋ እደልለዋለሁ ማለትዋን አቁማ ቀጥተኛ የእርምት እርምጃ ካልወሰደች የሚታገሳት የለም፡፡ ዓረና ትግራይ ኖረ አልኖረ ህዝቡ አንቅተነዋል አብቅተነዋልም ፤ ህዝቡ የህወሓት የተጭበረበረ ና ባዶ ፕሮፖጋንዳ የሚሸከም ትከሻ የለውም ፤በትግራይ ድርጅት ኖረ አልኖረ ህዝቡ በራሱ የጭን ቄስል ሆኖባታል፡፡ ለዚህ ነው ዶክተርዋ በወሳኝ ምዕራፍላይ (በመስቀለኛ) መንገድ ላይ ትገኛለች የምለው፡፡
የትግራይ ህዝብ መተኪያ የሌላቸው ወርቅ ልጆቹን ከፍሎ ፍትህና ርትዕ፣ ዕድገትና ብልፅግና አገኛለሁ ብሎ 23 ዓመት ሙሉ በትዕግስት ቢጠብቅም ትግስቱ ከንቱ መሆኑ በመረዳቱ ከህወሓት ግንባር ለግንባር በመፋጠጥና ምሬቱንና ብሶቱን ከፍ ባለ ድምፅ ማስተጋባት ጀምሯል ፡፡ ሰሞኑን በሀገረ ሰላም የገጠማትን ፍጥጫ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በህወሓት የተጠለፈው የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ይዞ የጭቁኑን ህዝብ ድምጽ በመሆን እየታገለ የሚገኘው ዓረና ትግራይም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ህዝባዊ መሰረቱ እየሰፋና ስር እየሰደደ ይገኛል፡፡ ዛሬ ዛሬ የዓረና ቢሮዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሰልፈው ለአባልነት የሚመዘገቡባቸውና ብሎም ጫንቃቸው ላይ የተጫነውን አፉኝ ስርዓት ለማስወገድ የበኩላቸውን ሚና የሚጫወቱበት ማዕከላት እየሆኑ ነው፡፡ ይሄንን ጥልቅ የህዝብ ብሶትና የፍትህ ጥማት የተረዳው ፓርቲያችን ዓረና ትግራይ በረመጥ እየተራመደ ህዝባዊነቱን እያረጋገጠ ነው፡፡
ህወሓት 23 ዓመት ሙሉ ብንመክራት ብንመክራት… ኣሻፈረኝ ብለ የውሸት መንገድ ይዛ ህዝባዊ ተልዕኮዋን ዘንግታ በደመነፍ ስትነጉድ ስለቆየች አሁን የመጨረሻው መጀመሪያ እርከን ላይ በመድረሷ ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እጅግ ተቸግራለች፡፡ በውሸት የነጎዱት መንገድ ለመመለስ ያስቸግራል ማለት እንግዲህ እንደዚሁ ዓይነት ነው፡፡ ዶክተርዋ የህዝብ ልብ መጨበጥ ያልቻለችው ምንም የሰራችው ጥሩ ነገር ስለሌለ ሳይሆን በአገዛዝ ዘመንዋ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ በብልሹ አስተዳደር ከመዘፈቅዋ በተጨማሪ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማለትም በወደብ፣ በኢትዮጵያ አንድነት፣ በሉአላዊነት እና በዲሞክራሲ ጉዳዮች አሳፋሪ አቋም በመያዝዋ እና ለህዝብ ሳይሆን ለስልጣንዋ ከምንም በላይ አብዝታ በመጨነቅዋ ነው፡፡ በተለይ በትግራይ የትግራይ ህዝብ በድህነት ሥር እየማቀቀ የህወሓት ባለስልጣናት ፊት ግን በምቾት እንደአልማዝ እያብለጨለጨ ህዝብን ለልመና እና ለብተና በማስገደድዋ አንዳንድ መልካም ሥራዎችዋ በዜሮ እንዲባዙ ምክንያት ሆኗል፡፡ ህወሓት መሪዎችዋ የሙስና ጠባቃነታቸው ስለተረጋገጠ፣ ፍፁም ሰላማዊ ትግል የሚያደርጉ ንፁሃን ተቃዋሚዎች ላይ የተለያዩ የፓለቲካ ድራማዎችና አሻጥሮች በመስራት እንደምታስወነጅልና ወህኒ እንደምትወረውር ስለተነቃባት ፤እንዲሁም ሁሉም የማምታታት መንገዶችዋ በመታወቃቸው ህዝቡም እንደተረዳው ስላወቀች ጭንቀትዋ ጨምረዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም ፍርሃትዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖባት በጀግኖቹ የዓረና አባላት ላይ በጅምላ የእስር ዘመቻ ከፍታለች፡፡ ዓረና ትግራይ ግን አብረሃ ደስታ እንዳለው “ዓረና ትግራይ በትግራይ ህዝብ ልብ ውስጥገብቷል፡፡ ህወሓት አታገኘውም የትግራይ ህዝብ ድምፅ ዓረና ወስዶታል” ፤ህወሓት ግን በመስቀለኛ መንገድ ላይ ተገትራ ትገኛለች፡፡
ዶክተር ህወሓት ዶክትሬት ዲግሪዋን ያገኘችው በጭቆና ነው፡፡ ዶክትሬት ዲግሪዋን ያገኘችው ህገመንግስቱን በመጣስ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ በተግባር በተደጋጋሚ በማሳየቷ እና በመላው ኢትዮጵያ ግዙፍ የጭቆና ኢንዱስትሪ ገምብታ በርካታ ጨቋኝ ካድሪዎችን በመፈብረኳ ነው›› ዶክተር ህወሓት መስቀለኛ መንገዱን በፖለቲካዊ ጥበብ ማለፍ ካልቻለች በቅርቡ የጭቆና ፕሮፎስርነትዋን ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>