Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ)

$
0
0

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ፡፡በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መልቀቂያቸውን ያስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሥልጣን መነሳታቸው ታውቋል….አቶ አለማየሁ ቀድሞውንም ሥልጣን ሲይዙ በከባድ ሕመም የሚሰቃዩ መኾናቸው እየታወቀ ሲኾን ምንጮች እንዳረጋገጡት አቶ አለማየሁ ወደ መንፈቅ ለሚጠጋ ጊዜ በውጭ አገር በሕክምና ላይ ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ ኮማ ውስጥ ይገቡም ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ጊዜ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ተክተው ይሠሩ የነበሩት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ ሲኾኑ የኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸውን ሥልጣን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድር እንደነበሩ ምንጮች ጨምረው አረጋግጠዋል፡፡

 



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>