Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 938

ሰበር ዜና ፀረሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን የሀብት ዝርዝር ላለማሳወቅ እያንገራገረ ነው

$
0
0

musenaፍኖተ ነፃነት  የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣኖችን የሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታቱ በፓርላማ መነጋገሪያ ሆነ፡፡የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ባለፈው ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም…. ለፓርላማ ባቀረቡት የ2005 በጀት የአስር ወር የዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ኮሚሽነሩ ባለፈው አመትም ተመሳሳይ ሪፖርት ሲያቀርቡ “በቅርቡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በዝርዝር ይፋ እናደርጋለን” ቢሉም በያዝነው አመትም ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ኮሚሽነሩ ሲመልሱም በአስደንጋጭ ሁኔታ “የሚገለፅና የማይገለፅ አለው” ብለዋል፡፡ ብቸኛው የተቃዋሚ ወኪል የሆኑ አቶ ግርማ ሰይፉ “የተሽዋሚዎች ሀብት የሚገለጽና የማይገለፀው ምንድነው?” የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቂ ምሳሽ እንዳላገኙ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም “ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሁንም የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብትና መረጃ ይፋ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ መውሰድ የለበትም” ካሉ በኋላ፣ ባለስልጣናቱን በሚመለከት የሚገለፅና የማይገለፅ መረጃ ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡



Viewing all articles
Browse latest Browse all 938

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>