Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 938

ሰማያዊ ፓርቲ አስደናቂ መግለጫ አውጥቷል።

$
0
0

መንግስት እንደለመደው ሰልፉ እንዳይካሄድ ይፈልጋል። ፓርቲው ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም ሰልፉን ለማድረግ መወሰኑን አስታውቋል። ፓርቲው በያዘው ጠንካራ አቋም ብቻ መንግስትን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል… የአዲስ አበባ መስተዳድር ለፓርቲው ደብዳቤ መልስ የሚሰጥ አይመስለኝም። መንግስት እንዲህ አይነት የማፍያ ስራ የሚሰራው ሁሌም ጠመንጃውን ተማምኖ ነው። የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ የመንግስትን ጠመንጃ ባለመፍራት ሰልፉን ለማካሄድ በመወሰናቸው ብቻ ሊደነቁ እና ሊደገፉ ይገባል። እነዚህን ደፋር መሪዎች በሰልፉ እለት በእስር ወይም በሌላ መንገድ እንዳናጣቸው፣ ሁለት ነገሮችን ማድረግ ይገባል እላለሁ። አንደኛው ህዝቡ በነቂስ መውጣት አለበት። ከ10 ሰዎች ይልቅ 100 ሰዎች ፣ ከ100 ሰዎች ይልቅ ሺዎች የተሻለ “የመፈራት ጉልበት” ይኖራቸዋል። ህዝቡ በነቂስ መውጣት ከቻለ፣ ፌደራሎች ሊገድሉም ሊያስሩም አይችሉም። መንግስት ሊያደርግ የሚችለው፣ ከህብረቱ ስብሰባ አንድ ቀን በፊት፣ መሪዎችን በየቤታቸው እየሄደ ማሰር ነው፤ ለዚህ መፍትሄው ደግሞ ከተቻለ ከአንድ ቀን በፊት የድርጅቱ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ውሎ እና አዳራቸውን በጽህፈት ቤታቸው ውስጥ ማድረግ ነው፣ ከተቻለ ከአሁን ጀምሮ! የፌደራል ፖሊሶች ሊያሰሩዋቸው ሲመጡ ደጋፊዎቹና አባሎቹ በመጮህ መቃወም። ጩኸት ብዙ ነገሮችን ይጋብዛል፤ ብዙ ሰዎች ይሰባሰባሉ፣ ሚዲያው ይመጣል፣ አለምም አይኑን ኢትዮጵያ ላይ ይተክላል። መንግስት ስብሰባውን ያለምንም ኮሽታ ማስኬድ ቢፈልግም ያልጠበቀው ጨኸት ስለሚገጥመው የሚኖረው አማራጭ መደራደር ነው። መንግስት ግን ያን የማድረግ ተፈጥሮ የለውም።
እንደኔ እንደኔ ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ አቋሙ ከቀጠለና መጠነኛ የብልጠት ስራዎችን ከሰራ ታሪካዊ ድል ይቀዳጃል። የፓርቲው ደጋፊዎች፣ አባላትና አመራሮች ከአሁን ጀምሮ እጅ ለጅ ቢያያዙ፤ አብረው ቢውሉ፣ ቢያመሹ፣ ከተቻለ ሌሎች ፓርቲዎችም አባሎቻቸውን፣ ደጋፊዎቻቸውን እና አመራሮቻቸውን ይዘው በድርጅቱ ጽህፈት ቤት ቢከትሙ ታሪካዊቷ “ታህሪር”ን በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ውስጥ ተመሰረት ማለት ነው።
እባካችሁ ሌሎችም ሀሳብ አዋጡ



Viewing all articles
Browse latest Browse all 938

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>