ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደርሱት አደጋዎች አብዛኛዎቹ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ናቸው ፈጣሪ ሲጠብቀን ከድርቅ በስተቀር(ችግሩ በአብዛኛው ሰው ሰራሽነው)ለመከላከል እጅግ የሚከብዱት ተፈጥሯዊ አደጋዎች ብዙም አልደረሱብንም…. የአደጉት ሀገሮች እጅግ ከባድ የሆኑትን የተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል በሚተጉበት በዚህ ዘመን እኛ ኢትዮጵያውያን መከላከል በምንችላቸው ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሕዝብ እያለቀነው።ከሁለት ወይንም ከሶስት አመት በፊት ይመስለኛል በባህርዳር ከተማ በሳትኮን ኮንስትራክሽን ለሚሰራ ህንፃ የሚሆን ደረጃውን ያልጠበቀ ከእንጨት የተሰራ መወጣጫ(scaffolding)ተደርምሶ 18 ምስኪን ለፍቶ አዳሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው አልፏል።ይህ አደጋ የደረሰው በስራ ተቋራጩ በሳትኮን እንዝላልነትና በመንግስት የቁጥጥር ማነስ ነው። ችግሩ ከደረሰ በኋላ ሕዝቡ ለምን ብሎ መንግስትን አስጨንቆ ስላልያዘ በመንግስትም በኩል በሳትኮን ላይ አሰታማሪ የሆነ ከባድ ቅጣት ስላልተጣለ ይህ ተመሳሳይ አደጋ በዚህ አመት ባምቢስ አጠገብ ከሚሰራ ህንፃ የ4 ንፁሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል። ከባህርዳር የሰሞኑ “አደጋዎች” ሳንወጣ ከፌደራሉ ግድያ ብንጀምር፦ =>አንድ ፌደራል እስካሁን ምክንያቱ ጥርት ብሎ ባልታወቀ ሁኔታ 16 ሰዎች በላይ ሲቀጥፍ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ እንዴት? ለምን? ተከሰተ ብሎ የመንግስት አካሎችን ማስጨነቅ አለበት? አንድ ግለሰብ አንድን አካባቢ አንድ ሰዓት ሙሉ አካባቢው ተቆጣጥሮ ይኸን ያህል ሰው ከገደለ በአካባቢው መንግስት የለም ማለት ነው።ይህ ክስተት ነገ በባ/ዳርም ሆነ ከባ/ዳር ውጭ ላለመድረሱ ዋስትና የለም። =>ከፌደራሉ ግድያ በኋላ አንድ ሚኒባስ ከእንጅባራ ወደ ባ/ዳር ሲጓ…ዝ ተጋጭቶ አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ሲያልቁ ይኸን አይነት አደጋ እንዳይደርስ ስለተደረገው ጥንቃቄ ያወራ የለም። ኢትዮጵያውያን በየቦታው በየአቅጣጫው በመኪና አደጋ እየረገፉ ነው እየተወሰደ ያለው ቅድመ ጥንቃቄ ከተወሰነ ጊዜ የሚዲያ ፍጆታነት ሲያልፍ አይታይም። => ሌላ አሳዛኝ አደጋ ከባ/ዳር የመንግስት ንብረት የሆነ ጀልባ ከ160 በላይ ሰዎችን ይዞ በጣና ሀይቅ ሲጓዝ በደረሰ አደጋ እስከአሁን ከ10 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል የደረሱበት ያልታወቀው በርካቶች ናቸው።ጀልባው እጅግ ያረጀ እንደነበር እየተሰማ ነው ይኸኔ ነው በውኑ ኢትዮጵያ ለዜጎቹ የሚጨነቅ መንግስት አላት ብሎ መጠየቅ! የሚያሳዝነው የወያኔ አገዛዝ አሁንም የቁጥር ጨዋታ እየተጫዎተ ይገኛል። አደጋው እንዴት ደረሰ ብሎ የሚመረምር አካል በቦታው በማሰማራት ፈንታ ፌደራል አሰማርቶ መረጃ እንዳይወጣ ያፍናል። ከላይ ለአብነት የባህርዳርን ብቻ አደጋ ያነሳሁት ወቅታዊነት ስላላቸው ነው ችግሩ ግን ሀገር አቀፍ ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መከላከል የምንችላቸው ሰውሰራሽ አደጋዎች እየደረሱ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ ነው እነዚህ ክስተቶች የደረሱት በሕዝባቸው ተጣያቂነት ባለባቸው የዴሞክራሲያዊ ሀገሮች ቢሆን ኖሮ ለዜጎቹ ግድ የሚሰጠው መንግስት ከሆነ በመጀመሪያ አደጋው እንዴት እንደደረሰ ይመረመራል ከዛ ስለወደፊቱ እንዴት ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበት ጥናት ይደረጋል ሕዝቡም መንግስትን አስጨንቆ ይይዛል። እኛ ሀገር ግን መንግስት ጉዳዩን ያድበሰብሳል ሕዝቡ ከንፈር ይመጣል አለቀ! ቆም ለምን!? እንዴት!? ብለን ካላሰብንና ተጠያቂ አካሎችን ወጥረን ካልያዝን መቸም በአደጋ ማለቃችን አይቆምም!
13/09/05 ሀና መታሰቢያ / posted by Issa Abdusemed/
Related articles
- Ethiopian Youth Initiative: Nurturing the Culture of Giving Back (kweschn.wordpress.com)
- Ethiopia Accused of Ethnic Cleansing Over Mass Amhara Evictions (worldnewscurator.com)
- አስደንጋጭ ዜና There Are 15 Million Mentally Ill People In Ethiopia (addisuwond.wordpress.com)
