Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

$
0
0

ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት… በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡A mass grave in Addis Ababa, Ethiopia

በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡

ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡

ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!

ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ



በጀግኖች አባቶቻችን ደም የተቦካው ሉአላዊ ግዛታችን ላይ የሚደረገውን ስውር ሴራ ያለማወላወል በፅናት እንታገለዋለን፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ታኅሣሥ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. (December 30, 2013)የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር የማካለሉ ሥራ ከመስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 9, 2009) ጀምሮ እየተከናወነ እንደሆነ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ዕለታዊ የሱዳን ጋዜጣ ሱዳን ትሪቢውን (Sudan Tribune) በመስከረም 8 ቀን 2002 ዓ.ም. (September 18, 2009) መዘገቡ ይታወሳል.. የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ ያንገበገባቸው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩት ዜጎቻችንም ራሳቸውን በተለያዩ “ኮሚቴዎች” እና “ግብረ ሃይሎች” በማደራጀት ለጉዳዩ ክፈተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ፓርቲያችን (ሰማያዊ)፣ ለነዚህ ሀገር ወዳድ ዜጎች ያለውን ከፍተኛ አክብሮት ለመግለጽ ይወዳል፡፡

 ሆኖም፣ የነዚህን ሀገር ወዳድ ዜጎችና አፍቃሪ-ኢትዮጵያውያን ጥሪና መግለጫዎች ከቁብም ካለመቁጠር፣ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሥውር የሥልጣን ማራዘሚያ ደባዎችን እየሸረበ እንደሚገኝ አጋልጠዋል። ወያኔ ራሱ ያቋቋመው “የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ኮሚቴ” አባላት ራሳቸው በተለያዩ ቃለ-ምልልሶች እንዳጋለጡት፣ ወያኔ በአባቶቻችን ደም ተላቁጦ ለተቦካውና የበርካታ ሰማዕታትን ህይወት ላስከፈለው የኢትዮጵያ ድንበርና የግዛት ሉዓላዊነት ግዴለሽነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊ ግዛትና ድንበር “በጫካ ውሎችና ስምምነቶች” እያመካኘ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች አሳልፎ መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡

ይህንንም ከፍተኛ የሆነ የሃገር ክህደትና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ለማስተባበል በመገንዘብ፣ የወያኔ-ኢህአዲግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ ላይ በመስከረም 2002 ዓ.ም መጨረሻ ላይ አንድ የማደናገሪያ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከዚህም የማደናገሪያ መግለጫ ውስጥ የሚከተሉትን ሦስት(3) አበይት ጉዳዮች መገንዘብ ይቻላል። እነርሱም፦

1ኛ. የኢትዮጵያና ሱዳን የፖለቲካ ኮሚቴ (Ethio-Sudan Political Committee) ተብሎ የሚጠራ ከፍተኛ አካል መኖሩንና የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) በፖለቲካው ኮሚቴ ሥር እንደሚሠራ አረጋግጧል፤ የዚህ የኮሚቴ መዋቀርና የአሰራር ሂደቱም ለረጅም ዓመታት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ተደብቆ የቆየ እንደሆነና፣ ወያኔ-ኢህአዲግም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ክትትል መጋለጡን ሲያውቅ ተጨንቆ ያወጣው ምስጢር ነበር።

2ኛ. የኢትዮጵያና የሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴም (Ethio-Sudan Joint Boundary Committee) ከጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. (October 15, 2009) እስከ ግንቦት 2002 ዓ.ም.(May 2010) ድረስ የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይስና ቅኝት እንደሚያደርግም ገልጾ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ ሲጋለጥ ያወጣው ሌላው ምስጢር ሲሆን፣ (ሱዳን ትሪቢውን ያወጣውን ዜና የሚያጎለምስ) እና የሱዳን ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንበሩን ለማካለል የሚያደርገውን ዝግጅት የሚያስተጋባ ነው።

3ኛ. የድንበር ክለላው ከግንቦት 2002 ዓ.ም. ( May 2010) በኋላ እንደሚደረግና ከዚህም ጋር አያይዞ ወያኔ-ኢህአዲግ ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት አምነው የተቀበሉት የድንበር ክልል እንዳለ አስምስሎ ለማቅረብም ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ወያኔ-ኢህአዲግ አሁን የሚያካሂደው “የድንበር-ክለላ ሂደት” ዳግም ድንበርን የመከለል ተግባር ( re-demarcation ) እንደሆነ መግለጹ ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ ይህ ማደናገሪያና ተራ ልፈፋ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማወናበድና ግዛቱን በጫካ ውሎችና ስምምነቶች አማካይነት አሳልፎ ከመስጠት የዘለለ ኢምንት እውነታ የለውም፡፡ ይሄንን በተመለከተም ያጠኑት ሊቃውንትንና በግዛቱ ላይ የሚኖሩትን ዜጎች ምስክርነት ሊያገኝ አልቻለም፤ አይችልምም፡፡

የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት “ያለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት የተቀበሉት የድንበር ክልል” የሚለው ሀተታ፤ ሜጀር (ሻለቃ) ጉዊን የተባለው የእንግሊዝ ጦር መኮንን በ1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) “አስምሬአለሁ” የሚለውን የወሰን ክልል ነው። ይሁንና አንድ በእንግሊዝ የቅኝ-ገዥነት አባዜ የሰከረ ሻለቃ ያሰመረውን መስመር መሠረት አድርጎ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉዓላዊነትን የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን “ለሱዳን ይገባታል” ብሎ መሟገቱ የፖለቲካ ቅጥፈት እንጂ ታሪካዊ ማስረጃ የለውም፡፡ የሚከተሉትም ታሪካዊ ዳራዎች የወያኔን ሙግት ውድቅ ያደርጉታል፦

1ኛ.ሻለቃ ጉዊን መሬቱን አካልያለሁ ሲልና በወረቀት ሲያሰምር፤ በኢትዮጵያ በኩል አንድም ተወካይ ስለአልነበረ የጉዊን የድንበር ማካለል ተግባር ከቅኝ ገዢዎች ማንአለብኝነት ተለይቶ የማይታይና የውል አፈጻጸም ሥርዓት የማይከተል በመሆኑ የተነሳ ተቀባይነት የለውም፡፡

2ኛ. የ1896 ዓ.ም.(እ.አ.አ.) የአድዋ ጦርነት ድል በቅኝ ገዥዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ መደናገጥ ምክንያት 1902 ዓ.ም. (እ.አ.አ.) አካባቢ እንግሊዝና ጣሊያን በጋራ በመመሳጠር የሰሜንና የምዕራብ ኢትዮጵያን ድንበር ለመግፋት የፈፀሙት ሴራ ስለሆነ፣ የሻለቃ ጉዊን ተልዕኮም ከዚያ ሴራ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ስለሆነም ተቀባይነት የለውም፡፡

3ኛ. ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በፊትም ይሁን ከዚያ በኋላ፣ ይህ ሻለቃ ጉዊን ከለለው የሚባለው መሬት ምን ጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ይዞታ ውጭ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይባስ ብሎም፣ በአፄ ቴዎድሮስና በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ግዛት አሁን ሱዳን ተብሎ ከሚጠራው ሃገር በጣም ወደ ውስጥ የገባ ነበር፡፡ ስለሆነም፣ የግዛት ጥያቄ ሲነሳ የይገባኛል ታሪካዊ መሠረት ያላት ኢትዮጵያ መሆኗን ለማስተባበል አዳጋች ነው፡፡

4.አሁን የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት በመጋቢት 22/2006 ዓ.ም ገደማ March 30, 2014 ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ-ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ግልጽነትና ተጠያቂነትን መርሆው ያላደረገው የወያኔ-ኢህአዲግ መንግሥት ግን አንዳችም መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያገኝ የተለመደ አፈናውን ገፍቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ በእልፍ-አዕላፍ ድንበር ጠባቂ ኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ተጠብቆ የኖረውን ዳር ድንበር፣ ወያኔ በተለመደ “የደጃዝማቾች ፈረስ መጠጫና ጉግዝ መጫወቻ ነው” በሚል ንፍገት አሳልፎ ለሱዳን ሊሰጠው ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሰፊ ውሃ-ገብና ለም ሉዓላዊ መሬት፣ የታሪክ ማስረጃዎችንና የኢትዮጵያውያንን መስዋዕትነት በማናናቅ ለባዕዳን ሊሠጥ አይችልም፡፡

ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ማስረጃዎችና በዓለም-አቀፍ የአሠራር ደንብ መሠረት፤ ወያኔ-ኢህአዲግ ከሱዳን ጋር የሚያደርገው የድንበር ክለላ ስምምነት ህገ-ወጥ ነው። ከዚህም ባሻገር፤ ከዋናው ባለጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት ይሁን የድንበር ክለላ ተግባር ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም።

ከዚህም ሌላ፣ ወያኔ-ኢህአዲግ የተወሰኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት ቆርሶ በመስጠት ሥልጣኑን በጎረቤት አገር ሱዳን ለማስባረክ ብሎ የሚያደርገው ሽር-ጉድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም፡፡ ውጤቱም “ታግዬላቸዋለሁ የሚላቸውን ብሄሮችና ብሔረሰቦች” ከማዳከምና ብሎም ለማፈራረስ የተጠቀመበተ ዘዴ የቅኝ ገዢዎች ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ ያሰመሩትን የድንበር መስመር በመቀበልና የቅኝ ገዢ ጠበብትን እንደ ምስክር በመጠቀም ነው። ይህም ተግባሩ፣ቀድሞውንም በቋፍ የነበረውን የወያኔ-ኢህአዲግን መንግሥት የፖለቲካ ቅቡልነት የሚያሳጣው መሆኑን ለማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ አልፎ-ተርፎም በዚህ ተግባሩም ዛሬም የቅጥረኛ ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ህዝቡ እንዲያውቀው እንፈልጋለን፡፡

ይህ የወያኔ-ኢህአዲግ ገዢ ቡድን ተግባር የሃገራችን ኢትዮጵያን ዓለም-አቀፍአዊ ክብር የሚጎዳ ስለሆነ ከተግባሩ እንዲታቀብ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም፣ ለጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ዝርዝር መረጃና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበትም ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ ይህን ሳያደርግ ቢቀር ግን፣ ፓርቲያችን የተጣለበትን የአባቶቻችንን ክብርና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መቼም ቢሆን ያለምንም ማወላወል የምንወጣ መሆናችንን ለጉዳዩ ባለቤት ለኢትዮጵያ ኅዝብ በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡

ሰላም፣ ተስፋ፣ ፍትህና እኩልነት በዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በተከበሩባት ኢትዮጵያ ዕውን ይሆናል!!!

Semayawi Party- Ethiopia's photo.
Semayawi Party- Ethiopia's photo.

በተቀነባበረ የመብራት ሀይል ሙስና ኢትዮጵያ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ተደረገ

$
0
0

በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል…


የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት ሃይል የቦርድ ሰብሰባ የሆኑት ዶ/ር ደብረ ጸዮን ገብረሚካኤል ስለአቶ ደበበ ምህረት ከሃላፊነት መነሳት ” እሱም የሚመሰገነውን ያክል ጉድለትም እንደነበረበት ይረዳል። ከሃላፊነቱ ሲነሳም አልደነገጠም።” በማለት መናገራቸው ይታወቃል። ምንም እንኳ ዶ/ር ደብረጺዮን አቶ ደበበ በብቃት ችግር እንደተነሱ አድርገው ለመገናኛ ብዙሀን ቢገልጹም፣ አቶ ምህረት ደበበ ግን በህወሃት ባለስልጣናት ስውር እጅ ሲቀነባበር የነበረውንና ኢትዮጵያን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ያደረገውን ከፍተኛ ሙስና ሲቃወሙ እንደነበር ለጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበው እና ለኢሳት የደረሰው የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ያስረዳል።
በ1999 እና በ2000 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ የሚረዱ ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ካወጣቸው አለም አቀፍ ጨረታዎች ጋር ተያይዞ በጨረታዎቹ ሂደት ላይ ግልጽነትና ኃላፊነት የጎደለው አሰራር መከሰቱንና ይህም የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ በማድረግ የምርመራ ውጤቱን በወቅቱ በስልጣን ላይ ለነበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትት መለስ ዜናዊ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፕሮግራምን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛሉ በማለት የሥርጭት (Distribution) ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ሁለት ዓለም አቀፍ ጨረታዎችን ለማውጣት ዝግጅት ጀመረ። ጨረታዎቹ በኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎችና በጨረታ ገምጋሚ የኮሚቴ አባላት ይሁንታ አግኝተው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በሁዋላ የመጀመሪያው ጨረታ በ1999 ዓ.ም፣ ሁለተኛው ጨረታ ደግሞ በ2000 ዓ.ም እንዲወጡ ተደረገ፡፡የጨረታዎቹን መውጣት ተከትሎም መረጃው የደረሳቸው ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በጨረታው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተለያየ ጊዜ ተደረጉትን ጨረታዎችም “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ” የተሰኘ የሕንድ ኩባንያ አሸናፊ መሆኑ በወቅቱ በይፋ ተነገረ።

ኩባንያው የጨረታው አሸናፊ ተብሎ ይለይ እንጅ ባቀረበው ሰነድ ላይ የገለጸው የትራንስፎርመር ዓይነት ኮርፖሬሽኑ በጨረታው ሰነድ ላይ ሊገዛው ካሰበው ዓይነት ጋር የሚመሳሰል ሆኖ ሳይገኝ ቀረ፡፡ ይህ አልተጠበቀ ክስተት ደግሞ በግዥ ሂደቱ ውስጥ ገና ከጅምሩ የሙስና ወንጀል ድርጊት የተጠነሰሰ መሆኑን አመላከተ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ያስቀመጠው የትራንስፎርመር ዓይነት “ሄርማቲካሊ ሲልድ” የሚል ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ኩባንያ ባቀረበው የውል ማቅረብያ ሰነድ (ኦፈር) ላይ “ትራንስፎርመር ዊዝ ኮንሰርቫቶር ዩኒት” የተባለ ነው።

“ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ” ያቀረባቸው ሰነዶች ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ያወጣውን መስፈረት እንደማያሟሉ ሲታወቅ ፣ የነበረው የመፍትሄ አማራጭ ጨረታዎቹን አሸንፏል ተብሎ የተለየው ኩባንያ ያቀረበው ትራንስፎርመር በኮርፖሬሽኑ የጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠው መስፈርት (ሰፔስፊኬሽን) አያሟላም በሚል በአሰራሩ መሰረት በቴክኒክ ግምገማ ውድቅ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ላይ አቶ ምሀረት ደበበ ተቃውሞ ያሰማሉ፤ ይሁን እንጅ የኮሚቴ አባላቱ ተቃውሞውን ወደ ጎን በመተውና አዲስ ቃለ ጉበኤ በመያዝ ኩባንያው ትክክለኛ የትራንስፎርመ ዓይነት ይዘው ለውድድር ከቀረቡ ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር እንዲወዳደር በማድረግ በህገወጥ መንገድ ቀጣዩን የ ፋይናንስ ግምገማ ሥርዓት እንዲያልፍ አድረጉ፡፡ በዚህ አግባብ ኮርፖሬሽኑን ወክለው በጨረታው የተሳተፉ አካላትም ሆነ ጨረታውን አሸነፈ የተባለው ኩባንያ ባለቤት በኪራይ ሰብሳቢነት ስሌት ያልተገባ ጥቅም ለመቀራመት እየተንደረደሩ መሆኑን የሚያሳይ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበላቸው።

የጨረታው ሂደት ቀጥሎ ኮርፖሬሽኑ እና የጨረታው አሸናፊ ኩባንያ በሚቀርቡ የትራንስፎርመሮች መጠንና በገንዘብ ጉዳይ ላይ ውል የሚዋዋሉበት ደረጃ ላይ ደረሱ። ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ጊዜያት ያወጣቸውን ሁለቱን ጨረታዎች የተመለከተ የውል ሰነድ ተዘጋጅቶም በሁለቱም ወገኖች ተፈረመ። የጨረታዎቹ አሸናፊ ነው የተባለው “ጉድላክ
እስቲል ቲዩብስ ሊምትድ” ኩባንያም ትራንስፎርመሮቹን በሰፕላየርስ ክሬዲት (supplier credit) እንደሚያቀርብ ተስማማ፡፡ በውሉ መሰረት ኩባንያው በአንደኛው ጨረታ ብዛታቸው 1950 የሆኑ የስርጭት ትራንስፎርመሮችን ወለዱን ጨምሮ በ8 411,946 የአሜሪካ ዶላር፤ በሌላኛው ጨረታ ደግሞ ብዛታቸው 3520 የሆኑ ትራንሰስፎርመሮችን ከነወለዱ በ17,695,686 የአሜሪካ ዶላር፤ በድምሩ ብዛታቸው 5470 የሆኑ ትራንስፎርመሮችን ወለዱን ጨምሮ በ 26 107 632 የአሜርካ ዶላር ለማቅረብ ስምምነቱ ተፈረመ።፡

የሁለቱ ጨረታዎች የመጀመሪያ ውሎች በዚህ መልክ በኮርፖሬሽኑና በጨረታው አሸናፊ ኩባንያ መካከል ይፈረሙ እንጅ በኩባንያው በኩል ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው መዘግየት የሚጠበቁ ውጤቶች ሊታዩ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ኩባንያው ገንዘቡን በራሱ ማቅረብ እንዳማይችልም ግልጽ እየሆነ መጣ፡፡ ይህን የተረዱ የጨረታው ኮሚቴ አባላትና የኩባንያው ባለቤት መፍትሄ ይሆናል ብለው ያሰቡትን አማራጭ ማፈላለግ ጀመሩ፡፡ አውጥተው ካወረዱ በኋላም ሌላ አዲስ ውል ቢኖር የፋይናንስ ችግሩን ይቀርፋል በሚል ሀሳብ ተስማሙ፡፡ በአዲሱ ሀሳብ ላይ ተቃውሞአቸውን የገለጹት አቶ ምህረት ደበበ እራሳቸውን ለማግለል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቀጥታ በውሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በጠ/ሚሩ ጽ/ቤት በኩል ትዕዛዝ ደረሳቸው። ኩባንያው መጀመሪያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈራረመው ውል በአዲሱ ውል እንዲተካም ተደረገ፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ የተፈረመው የዚህ የአዲሱ ውል ዋና ፍሬ ሀሳብም የመጀመሪያው ውል ተቀይሮ ግዥውን ፋይናንስ
የሚያደርግ ሌላ ሶስተኛ ወገን በውሉ ውስጥ እንዲገባ ማድረግ የሚል ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ቢዝነስ እንደሚሰራ የሚነገርለት “ኮብራ ኢንስታሌሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር” ግዥውን በገንዘብ አቅርቦት የሚደግፍ ተባባሪ (ፋይናንሲንግ አሶሺዬት)፣ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የትራንስፎርመሮቹ አቅራቢ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ደግሞ የትራንስፎርመሮቹ ገዢ በመሆን የሶስትዮሽ ውል እንደገና እንዲፈረም ተደረገ፡፡

ይሁን እንጅ ሌላ አዲስ ውል በሕንድ ኩባንያዎች መካከል መፈረሙም ታወቀ፡፡ ዉሉ በ“ጉድላክ እስቲል
ቲዩብስ”፤በ“ኮብራ ኢንስታሌሽንስ” እና ሌላ በሕንድ አገር ከሚገኘ የትራንስፎርመር አምራች የሆነ “ናሽናል ኤሌክትሪክ ኢክዩፕመንት ኮርፖሬሽን” በተሰኘው ኩባንያ መካከል የተፈረመ የሦስትዮሽ ውል ነበር፡፡ ኩባንያዎቹ ይህን ውል ሲፈራረሙ በኮርፖሬሽኑ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም እና የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ሥ/አስፈፃሚዎች የነበሩ ግለሰቦች በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ቢሆንም ከኮርፖሬሽኑ እውቅና ውጭ መሆኑ ግን በምርመራው ተደርሶበታል፡፡ ከምርመራው ውጤት ለመረዳት እንደተቻለው ይህ ሁሉ አካሄድና ቀና ደፋ ደግሞ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የተባለውን ኩባንያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሦስትዮሽ ከተፈራረመው ውል ማውጣት ነውና ይህም ተሳካለቸው፡፡ ስለሆነም “ኮብራ ኢንስታሌሽንስ” የተባለው ኩባንያ ከፋይናንሲንግ አሶሺዬት ወደ አቅራቢነት የውል ተቀባይ ወገን ተቀየረ፡፡

የኮርፖሽኑ የቀድሞው የስራ ሃላፊ አቶ ምህረት ደበበ ከኮርፖሬሸኑ እውቅና ውጭ የተደረገው ውል ያለአግባብ መሆኑን በመገንዘብ “ጉድላክ እስቲል ቲዩብስ” የተባለ ኩባንያ ከውሉ መውጣት እንደማይገባውና ቀደም ሲል ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተፈረመው የሦስትዮሽ ውሉ ጽንቶ መቆየት አለበት በሚል ማሳሰቢያም ጭምር ለመስጠት ጥረት አድርጓል፡፡ ይሁን እንጅ በአቶ ምህረት ደበበ የተሰጠውን ማሳሰቢያ የሚሰማ ጆሮ አልተገኘም፡፡ ይልቁንም ምርመራው እንዳረጋገጠው
ተጠርጣሪ የኮርፖሬሽ የሥራ ኃላፊዎች “ኮብራ” የተሰኘው ኩባንያ ትራንስፎርመሮቹን የማቅረብ የሕግ መሰረትና አቅሙ
ሳይገመገም እንዲሁም የኮርፖሬሽኑን ይሁንታ ሳያገኝ በሚያዚያ ወር ም ለ“ሪዘርቭ ባንክ ኦፍ ኢንዲያ” በጻፉት ደብዳቤ
ኩባንያዎቹ ከኮርፖሬሽኑ እውቅና ውጭ ለተፈራረሙት ውል ማረጋገጫ በመስጠት ኩባንያው ሕግን ባልተከተለ መንገድ የትራንስፎርመሮቹ አቅራቢ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ትራንስፎርመሮቹን የሚያቀርብ ኩባንያ ለመለየት የተጀመረው ድራማ በዚህ መልኩ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ የሚሆነው
ደግሞ የግዥ አፈጻጸም ተግባራትን ማከናወን ነው፡፡ በዚህ የግዥ አፈጻጸም ተግባር ውስጥ በኮርፖሬሽኑ የሲስተምና የደንበኞች አገልግሎት ድጋፍ ክፍል ኃላፊ እና የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ፕሮግራም ኢንጂነሪነግ ፕሮሰስ የስራ
ሂደት ተወካይ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊ በዋናነት ተሳታፊዎች ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች የትራንስፎርመሮቹን ግዥ አፈጻጸም በተመለከተ “ኮብራ” የተሰኘው ኩባንያ ባለቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካኝነት ለኮርፖሬሽኑ ያቀረበውን የአፈፃፀም ዋስትና ተከትሎ ዋስትናው ውሉ በሚያዘው ፎርማት (ቅፅ) መሰረት ያልተዘጋጀ መሆኑን እያወቁ ሕጉ ከሚያዘው አሰራር ውጭ ኩባንያው እንዲያልፍ ረድተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሁለቱም ጨረታዎች በቀረቡ የአፈፃፀም ዋስትናዎች ላይ “… በግዥው አፈጻጸም ውስጥ የባንክ ዋስትና ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በዋስትና ሰጪው ባንክ የገንዘብ መጠየቂያ ደብዳቤ በሕንድ መንግስት ባንክ የሚሰጥ ሆኖ ፓሪስ በሚገኘው የናቲክሲስ የማድሪድ ቅርንጫፍ ባንክ ተቀባይነት ካገኘበት ቀን በኋላ ብቻ ነው” የሚል ይዘት ያለው ቅድመ ሁኔታ የሰፈረ መሆኑን እያወቁ እንዲሁም የኩባንያው ባለቤት ግዴታውን በውሉ መሰረት ሳይፈፅም ቢቀር ኮርፖሬሽኑ ወዲያውኑ የአፈፃፀም ዋስትናውን መውረስ የሚያስችለው መሆኑን እየተረዱ ይህን ሁኔታ ለሚመለከተው የኮርፖሬሽኑ አካል ሳያሳውቁ እንደ ዋዛ አልፈውታል፡፡

“ኮብራ” የተባለው ኩባንያ በበኩሉ ትራንስፎርመሮቹን ለማቅረብ “ጉድላክ” ከተባለው ኩባንያ ላይ የተረከበውን ኃላፊነት
ሳይወጣ ጊዜ ነጎደ፡፡ ኮርፖሬሽኑም ትራንስፎርመሮቹ በወቅቱ መቅረብ እንዳልቻሉና ኩባንያው በውሉ መሰረት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንዳልሆነ መገንዘብ ችሏል፡፡ መገንዘብ ብቻም ሳይሆን ኩባንያው በዉሉ መሰረት ግዴታውን ሳይፈጽም ቢቀር የአፈፃፀም ዋስትናውን ለመውረስ የሚያስችለውን መብትም ለመጠቀም ሲባል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብዳቤ
አቅርቧል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ያቀረበው የአፈፃፀም ዋስትና ውርስ ጥያቄ በባንኩ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፡፡ ለዚህ በዋና ምክንያትነት የሚጠቀሰው ደግሞ የአፈጻጸም ዋስትናው በቅድመ ሁኔታ የተገደበ መሆኑ ነው፡፡

በዚህ አግባብ ኮርፖሬሽኑ የግዥ አፈጻጸም ዋስትናውን መውረስ የማይችልበት ሁኔታ ስለተፈጠረ ለኪሳራ ከሚዳረግ ይልቅ የሚቀርብለትን የትራንስርፎርመር ዓይነት ለመቀበል አጣብቅኝ ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በእርግጥ ኮርፖሬሽኑ
ሊገዛ ያቀዳው የትራንስፎርመር ዓይነት ቀርቦለት፣ የአፈጻጸም ዋስትናውን መውረሱ ቀርቶ ትራንስፎርመሩን በተገኘ ጊዜ
ለመቀበል ቢችል እንኳ ባልከፋ ነበር፡፡ አሁን ኮርፖሬሽኑ ከሁለት ያጣ እንደሚባለው ሆኗል፡፡ ወይ ገንዘቡን አሊያም
በጨረታ ሰነዱ የገለጸውን የትራንስፎርመሮች ዓይነት ለማግኘት አልቻለም። የምርመራው ውጤት እንዳመለከተው በድርጊቱ ውስጥ ተሳታፊዎች የነበሩ በቁጥር ሰባት የሚደርሱ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የጨረታው ገምጋሚ ኮሚቴ አባልትን ጨምሮ የ“ጉድላክ” እና የ“ኮብራ” ኩባንያዎች ባለቤቶች በአንጻሩ የማይገባቸውን ጥቅም ለመቀራመት የወጠኑትን ውጥን ከዳር ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡

እነዚህ በሁለቱም ጎራ በጨረታው ላይ የተካፈሉ አካላት የጨረታውን ሂደት ፍትሃዊነት በማሳጣትና ግባቸውን ያልተገባ ጥቅም መቀራመት አደርገው በመንቀሳቀስ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ውሎች ውስጥ ኮርፖሬሽኑ ሊገዛ ካሰባቸው የትራንስፎርመር ዓይነቶች ውጭ እንዲቀርብ ሁኔታዎችን የማድበስበስ ተግባራትን መፈፀም ቀጠሉ፤ ቀደም ሲል በሁለቱም የጨረታ ሰነዶች ላይ የሰፈረውና ኮርፖሬሽኑ ሊገዛ ያሰበው የትራንስፎርመሮች ዓይነት “ሄርማቲካሊ ሲልድ” የሚለው ሲሆን ከዚህ መስፈርት ውጭ ከአቅራቢዎች ጎራ ሌላ ዓይነት መስፈርት ከመቅረቡም በተጨማሪ ኮርፖሬሽኑ አዲስ፣ ያላገለገሉ እና የቅርብ ስሪት የሆኑ የትራንስፎርመሮች ዓይነት እንዲቀርብለት ያስቀመጠውን መስፈርት ወይም ስፔስፊኬሽን ኩባንያዎቹ ባቀረቡት ሰነድ ላይ ሳይካተት ታልፏል፡፡

እነዚህ ተግባራት ተደማምረው ሕገ-ወጥ የግዥ አሰራር የበላይነትን ይዞ የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የኩባንያዎቹ
ባለቤቶች የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ማሳለጫ መንገድ እንደሆናቸው የምርመራው ውጤት ያስረዳል፡፡ የኩባንያዎቹ ባለቤቶችም ከጨረታው ገምጋሚ ኮሚቴ አባላትና በጨረታው ተሳታፊ ከነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ያመቻቹትን ይህን ሕገ-ወጥ አካሄድ በመጠቀም ኮርፖሬሽኑ የማይፈልጋቸው የትራንስፎርመሮች ዓይነት ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማደረጋቸውንም ምርመራው ያሳየናል፡፡

በጨረታው ተሳታፊ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከትራንስፎርመሮቹ ጥራት ጋር በተያያዘ ጎልተው የታዩ ችግሮችን ለመሸፋፈን የተለያዩ እርምጃዎች ወስደዋል፡፡ ከዚህ አኳያም ትራንስፎርመሮቹ በሙያተኞች እንዲፈተሽ አድርገዋል፡፡ በውጤቱም የዛጉና የዘይት መንጠባጠብ የሚታይባቸው፣ የሲሊካ ጄል እና ከፍተኛ የመብረቅ መከላከያ የሌላቸው፣ የታፕ ቼንጀር ማስሪያ ብሎኖች የሌሏቸውና የተሰበሩ ትራንስፎርመሮች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ትራንስፎርመሮቹ ኮርፖሬሽኑ ከሚፈልጋቸው ዓይነት ውጭ ከመሆናቸው በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው በተደረገው ምርመራ ግልጽ ሆኗል፡፡ ከዚህም በመነሳት በጨረታው ሂደት ውስጥ በዋናነት ተሳታፊ የነበሩ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ስራ አስፈፃሚ፣ የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ሥ/አስፈፃሚ እንዲሁም የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም የቴክኒክ ክፍል ቡድን መሪ የነበሩ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ለ“ጉድላክ” እና “ኮብራ” ኩባንያ ባለቤቶች ደብዳቤዎችን ፅፈው ነበር፡፡ ውስጥ ለኩባንያዎቹ የጻፉዋቸው ደብዳቤዎች ይዘት ትራንስፎርመሮቹ በውሉ መሰረት ያልቀረቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ሲሆን በነዚህ ደብዳቤዎች መሰረት የሥራ ኃላፊዎቹ ለኮርፖሬሽኑ ጥቅም ውግንና ያሳዩ ይመስላል፡፡

ይሁን እንጅ የምርመራ ውጤቱ እንደሚጠቁመው እነዚህ የሥራ ኃላፊዎች ለኮርፖሬሽኑ ያሳዩ የሚመስለው ውግንና ዘለቄታ አልነበረውም፡፡ ከ2001 ዓ.ም በኋላ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከኩባንያዎች ጋር በተጻጻፉት ደብዳቤዎች መሰረት ትራንስፎርመሮቹ እንዲቀየሩ ከማድረግ ይልቅ በኩባንያዎቹ የቀረበላቸውን የጥገና መርሃ ግብር ተቀብለውና
አፅድቀውት በመላክ ትራንስፎርመሮቹ ያለአግባብ እንዲጠገኑ አድርገዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በኮርፖሬሽኑ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የኢንጂነሪንግ ክፍል እና የአገር አቀፍ
ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የሳፕላይ ቼይን የሥራ ኃላፊዎች ትራንስፎርመሮቹ ብልሽት ያለባቸው ሆነው እያሉ
ሙሉ በሙሉ እንደተጠገኑና ስራ ላይ እንደዋሉ በመግለፅ፣ አንድ ጊዜ እንዲጠገኑ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንዲተኩ በሚል ያለ በቂ ሙያዊ ፍተሻ ተገቢ ያልሆነ የውሳኔ ሃሳብ በመስጠትና የውስጥ ማስታወሻዎችን በመጻጻፍ ትራንስፎርመሮቹ በአዲስ እንዳይተኩ በማድረግ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በግዥው ሂደት ውስጥ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘትና ለኩባንያዎቹ ባለቤቶች ለማስገኘት በማሰብ በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ተካፋይነት በሚፈፀም ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በድርጊቱ ውስጥም በስልጣን ያለአግባብ መገልገል፣ የመንግስት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት እና ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ድርጊቶች የተፈጸሙ መሆናቸው ታይቷል፡፡ በዚህ አግባብ በተፈጸሙ ብልሹ አሰራሮች ሳቢያ በአገር ጥቅም ላይ ከ26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱም ተጠቅሷል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሰባት የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ በአራት የጨረታ ኮሚቴ አባላትና የ“ጉድላክ” እና የ“ኮብራ” ኩባንያ ባለቤቶች ላይ ተገቢውን ማስረጃዎች አሰባስቦ በሁለት የክስ መዝገቦችና በስድስት ክሶች በማጠናቀር ጉዳዩን ለመጀመሪያ ጊዜ ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቀርቧል፡፡ የአቶ ምህረት ደበበ የስልጣን ዝውውር የጀርባ ፍጥጫ ሌላው የግምገማ ታሪክ ይህን ሲመስል፣ በተፈጠረው አለመግባባት ስራውን በአግባቡ እንድመራው በወጣው ህግ እና ደንብ መመራት አልቻልኩም ሲሉ ያቀረቡት መልቀቂያ ጥያቄ በዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ተቀባይነት አግኝቶ ምንም በቂ ሃላፊነት ወደ ሌላው የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል።
አቶ ምህረት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ እና የሙስናውን ድራማ ከጀርባ ሆነው ሲመሩት የነበሩት ከፍተኛ ተጠቃሚ የሆኑት የህወሀት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ሳይውሉ፣ በመካከለና የአመራር ቦታ ላይ ያሉ የተወሰኑ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
በቅርቡ አንድ የህንድ ኩባንያ የኤልክትሪክ ኮርፖሬሽንን ማኔጅመንት ለመምራት ውል መዋዋሉ ይታወቃል


በ”ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ”ና በሁለት ተጨማሪ መጽሀፎች ላይ የቀረበ አጭር አስተያየት

$
0
0

ፋሲል የኔዓለም   በፖለቲካው ዓለም ጉልህ ስፍራ ያላቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አዲስ መጽሃፍ ያነበብኩት ዘግይቼ ነው ፤ ለመዘግየቴ ሶስት መሰራታዊ ምክንያቶች ነበሩኝ፣… አንዱና ዋናው ዶ/ሩ በተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አመለካከት በመገናኛ ብዙሃን በስፋት ስላቀረቡ በመጽሀፉ ውስጥ እምብዛም አዲስ ነገር ያቀርባሉ የሚል እምነት ስላልነበረኝ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ዶ/ሩ ራሳቸው በከፊል የጠቀሱት ነው፣ “ በአገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለ የተቃዋሚ ድርጅት አመራር አባል መሆኑን ሲመለከት፣ ከቅንጦትም ባሻገር በተወሰነ ደረጃ “ የስራ ፈትነት” ወይንም የበለጠ ጠርጣራ ( cynic) ለሆነ ሰው “ በተግባር ስራ ለመስራት ካለመቻል “ የመጣ፤ ተግባራዊ ድክመትን ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ሊመስል ይችላል” የሚለው ነው። ሶስተኛው ምክንያቴ ደግሞ ፣ ፋሽን በሚመስል መልኩ በአገር ቤት የሚኖሩ ፖለቲከኞች በተከታታይ መጽሃፎችን በማሳተማቸው ለእነሱ ቅድሚያ ለመስጠት በመፈለግ ነው።Ethiopian books review

ዶ/ር ብርሃኑን ያነበብኩት ሁለቱ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች -ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ” እንዲሁም ኢ/ር ሃይሉ ሻውል “ ሕይወቴ እና የፖለቲካ እርምጃዬ” በሚሉ ርዕሶች ያሳተሙዋቸውን መጽሃፎች ካነበብኩ በሁዋላ በመሆኑ፣ በሶስቱም ስራዎች ላይ መጠነኛ ንጽጽር ለማድረግ አስችሎኛል።

ዶ/ር መረራ ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ ያለውን የአገራችንን ፖለቲካ ግሩም በሆነ መንገድ አቅርበዋል፤ መጽሃፉ ብዙ አስቂኝ ገጠመኞች የተካተቱበት በመሆኑ ፣ በቋንቋና በዓርትዖት በኩል የሚታይበትን ጉልህ ችግር አይተን እንዳላየን እንድናልፈው ያስገድደናል። መጽሀፉ በጥሩ ዓርታዒ እንደገና ቢታረምና ቢታተም “ የተዋጣላቸው” ከሚባሉት የአገራችን መጽሀፎች ተርታ የመመደቡ እድል ከፍተኛ ነው። ዶ/ር መረራ የአገራችንን ህልውና እየተፈታተነ የመጣውን፣ በ1960ዎቹ ተዘርቶ በእነ አቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ተኮትኮቶ ያደገውን የብሄር ፖለቲካ መነሻ ፣ ያመጣውን ግሳንግስ እና የግሳንግሱን ማራገፊያ መፍትሄ አስቀምጠዋል። መፍትሄ ብለው ያስቀመጡትም በመጽሀፉ የመጨረሻ ገጽ እንደሚከተለው ሰፍሯል፣ “ …ለታሪክም ለህዝብም አስቀምጬ (ማለፍ) የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ ፣ አብዛኛው የትግራይ ሊሂቃን “ ስልጣን ወይም ሞት” ብሎ ስልጣን ላይ የሙጥኝ እስካለ ድረስ ፣ አብዛኛው የአማራ ሊህቃን በአጼዎች ዘመን የነበረውን የበላይነትን መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሃኑ የኦሮሞ ሊህቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠና የምትወጣ አይመስለኝም። በሌላ ቋንቋ ለነዚህ መሰረታዊ በሽታዎቻችን መድሃኒት እስካላገኘን ድረስ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ፈጽሞ የምታገኝ አይመስለኝም።” ( ገጽ 264)። ምንም እንኳ “አብዛኛው” የሚለው ቃል አወዛጋቢ ሊሆን እንደሚችል ቢሰማኝም ፣ ዶ/ሩ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ በትኩረት ሊታይ እንደሚገባው ሳላስታውስ አላልፍም፤ በተለይ” እነዚህ የሶስቱ ብሄሮች ሊህቃን ህልማቸውን እንዲተው ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” የሚለው ጥያቄ ለእኔ ቁልፍ ይመስለኛል። ዶ/ር መረራ በዚህ ዙሪያ የተብራራ መልስ ቢሰጡ ኖሮ መጽሃፋቸውን የበለጠ ሙሉ ማደረግ ይችሉ ነበር እላለሁ።

የኢንጂነር ሃይሉ መጽሀፍ የአገራችንን የፖለቲካ ችግር ከግለሰቦች ባህሪ ጋይ ያያዘው በመሆኑ ብዙም ክብደት የሚሰጠው ሆኖ አላገኘሁትም፤ ንድፈሃሳባዊ ትንተናዎች ይጎድሉታል፣ የተዓማኒነት ችግሮችም አሉበት( በተለይ ከቅንጅት መሪዎች ጋር ስለነበረው የሽምግልና ሂደትና ከዚያ በሁዋላ ስለተፈጠሩት ኩነቶች) ፤ ለተተኪው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት ስለመኖሩም በእጅጉ እጠራጠራለሁ፤ በእርግጥ ኢ/ር ሃይሉ ብዙ ውጣውረዶችን አልፈው እስካሁን በህይወት ለመቆየት መቻላቸው እድለኛ ሰው እንደሆኑ በመጽሃፋ ለማየት ችለናል፣ አገራቸውን የሚወዱ ሰው መሆናቸውንም አስገንዝቦናል። ኢ/ር ሃይሉ የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን መንገድ በመከተል መጽሀፉን በሌላ ሰው በማስጻፋቸው ስለጸሃፊነት ችሎታቸው አስተያየት ለመስጠት አያስችልም ።

የዶ/ር ብርሀኑ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” የሚለው ርዕስ ዘጊ ወይም ለማንበብ የማይጋብዝ ነው፤ በትምህርቱ አለም የዘለቁና የጥናትና ምርምር ወረቀቶችን ለማንበብ ፍላጎት ያላቸው ምሁራን ካልሆኑ በስተቀር፣ እንደ እኔ አይነቱ ተራ አንባቢ በርዕሱ ማልሎ መጽሀፉን ለማንበብ ስለመነሳሳቱ እጠራጠራለሁ። መጽሀፉ ውጫዊ ገጽታው ባያማልልም ውስጣዊ ይዘቱ ግን ድንቅ ነው። እንደምንም የጀመርኩትን መጽሀፍ እየተጨነቁና እየፈራሁ፣ እያዘንኩና ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ፣ እግረ-መንገዴንም የጸፊውን እይታ፣ የትንታኔ እና የቋንቋ አጠቃቀም ችሎታ እያደነቁኩ ጨርሸዋለሁ። መጽሀፉን እንደጨረስኩ የተናደድኩበት ነገር ቢኖር ጻሃፊው የኢትዮጵያን ችግሮች እንዲያ አድርገው ካቀረቡ በሁዋላ መፍትሄውን በይደር በመተዋቸው ነው።

ከዚህ ቀደም የአገራችንን ሁለተናዊ ችግሮች ማለትም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተፈጥሮና የህዝብ ብዛትን በአንድነት አጣምሮ፣ በአገራችን ህልውና ላይ የደቀኑትን ፈተናዎች ቅልብጭ አድርጎ ያሳየ ከገብረህይወት ባይከዳኝ “መንግስትና የህዝብ አስተዳደር” በሁዋላ የተጻፈ መጽሀፍ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፤ ይህን ስል ሌሎች ድንቅ የፖለቲካ መጽሃፎች አልተጻፉም እያልኩ አይደለም፤ የዶ/ር ብርሃኑን መጽሀፍ ለየት የሚያደርገው የተለያዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮችን ለይተው በማውጣት እርስበርስ ያላቸውን ትስስር ከግሩም ትንተና ጋር ሁሉም ሊረዳውና ሊጠቀምበት በሚችለው መንገድ ማቅረባቸው ነው ። (የምጣኔ ሀብት ትምህርት ( economics) የማይገባው ሰው እንኳ ቢሆን፣ መጽሀፉን አንብቦ ስለአገራችን ኢኮኖሚ ለመረዳት አይሳነውም።) መጽሃፉ የባራክ ኦባማን The Audacity of Hope እንዳስታወሰኝ ብገልጽ ያጋነንኩ አይመስለኝም፣ አጋነኸዋል የምትሉኝ ካላችሁም ” አንብቡትና ሞግቱኝ።

የዚህ መጽሀፍ ትልቁ መልእክት፣ ለእኔ እንደገባኝ፣ “የአገራችን ችግር ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በመገንባት ይፈታል” የሚለው አስተሳሰብ እንደሚታሰበው ቀላል አለመሆኑንና ከአሁኑ መፍትሄ ካልተበጀለት በሁዋላ ላይ ይዞት የሚመጣው ችግር ቀላል አለመሆኑን ማሳየት ነው ። የብሄር ፖለቲካው በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ፣ በአገራችን ልማትን ለማምጣት የሚገጥሙ ፖለቲካዊና መዋቅራዊ ችግሮች፣ ከአካባቢ ውድመትና ከህዝብ ብዛት ጋር ተያይዞ በመጽሀፉ በዝርዝር ቀርቧል። በአሁኑ ጊዜ በአገራችን እየታየ ያለውን የገቢ አለመመጣጠንም 1500 ብር የሚያወጣውን የአንድ መለኪያ ውስኪ ግብዣ በምሳሌነት በማንሳት በደቡብ አፍሪካ እንደታየው በአገራችንም ለወደፊቱ ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ጣጣ ጸሀፊው በደንብ አሳይተውናል።

መጽሀፉ የውጩ ፖለቲካ በአገራችን ፖለቲካ ላይ የሚያሳርፈውን ተጽዕኖ እንዲሁም የአለማቀፉ የንግድ ስርዓት በኢትዮጵያ እድገት ላይ ያለውን ተጽእኖ ቢያካትት ኖሮ የበለጠ ድንቅ ይሆን እንደነበር አስባለሁ ። ከዚያ በተረፈ ግን መፍትሄዎቹ በሌላ ክፍል እንደሚቀርቡ መገለጹ በመጽሀፉ ላይ በቂ ክርክር እንዳይነሳ ያደረገው ይመስለኛል። በመጽሀፉ በቀረቡት ችግሮች እና ትንተናዎች ላይ ተቃውሞ የሚኖረው ሰው ይኖራል ብየ አላስብም፣ ተቃውሞ የሚነሳው ችግሮችን ለመፍታት በሚቀርቡት የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ እንደሚሆን በመገመት ቀጣዩ መጽሃፍ አወያይ ( አካራካሪ) ይሆናል እላለሁ።

ስለአገራቸው እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ ሁሉ መጽሀፉን እንዲያነቡት እመክራለሁ ( የዶ/ር መረራንም ጨምሮ)። በተለይ በሰላማዊው የትግል ሜዳ ለመፋለም የሚያስቡ ጀማሪም ሆኑ ነባር ፖለቲከኞች የብርሀኑን መጽሀፍ በማንበብና በምርጫ ክርክር ወቅት ይዞ በመቅረብ ( የመፍትሄው መጽሀፍ ቶሎ እንደሚደረስ በመገመት) ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፤ ስልጣኑን ይረከባሉ ብዬ ባላስብም።


ሰበር ዜና፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

$
0
0

አቶ መላኩ የሞገቱበት የአዋጅ አንቀጽ እንዲስተካከል ተወሰነ ሰበር ዜና፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ በሙስና ወንጀል የተከሰሱት አቶ መላኩ ፈንታን ክስ መመልከት ያለበትን ፍርድ ቤት በሚመለከት ዛሬ የተወያየው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክሱ መታየት ያለበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት መሆኑን ለማሳየት ተከሳሹ የጠቀሱት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች..

zz

 

አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ሆኖ እንዲስተካከል በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ውሳኔው ስምንት ተቃውሞና ሁለት ድምፀ ተአቅቦ ተመዝግቦበታል፡፡

የአዋጁ ንኡስ አንቀጾች እንደሚያስረዱት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ ሳሉ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚያጠፉት ጥፋት የሚጠየቁት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያደረገው ውይይት ባለሥልጣናቱ በዚህ መልኩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚጠየቁ ከሆነ ጥፋተኛ ወይም ነፃ ቢባሉ እነሱ ወይም መንግሥት ይግባኝ የሚሉበት ዕድል አይኖርም፡፡ ይህ ደግሞ ሁለቱንም ወገን የሚጎዳና የይግባኝ መብትን የሚፃረር ነው፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የአቶ መላኩ ክስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የመታየት ዕድል አይኖረውም፡፡


Tens of thousands of African migrants protest in central Tel Aviv

$
0
0

You go to the Interior Ministry to get a visa, there are long lines, in the end you don’t get a visa. You’re on the street, they catch you without a visa – you go to jail.’..

Haartez:-Tens of thousands of African migrants held a protest in Tel Aviv’s Rabin Square on Sunday morning, against efforts to round them up and send them to a detention center.

Tens of thousands of African migrants protest in central Tel Aviv

“Yes to freedom, no to jail,” protesters chanted at the Tel Aviv rally, which also included several dozen Israelis.

Separately, hundreds of migrants held a separate rally in Eilat, the seaside resort town where many African asylum seekers or labor migrants work in the tourism industry.

“We want the government to pay attention to people,” said Konda, a Sudanese citizen who is one of the leaders of the protest and did not want to be identified by his full name. “All the doors have closed. People have nowhere to go, nothing to do. The immigration police are working all the time, catching people. You go to the Interior Ministry to get a visa, there are long lines, in the end you don’t get a visa. You’re on the street, they catch you without a visa – you go to jail. A large portion of the people are in jail now. We want to say that we deserve to live, we deserve human rights.”

Hundreds of asylum seekers, out of the estimated 49,000 migrants from Eritrea or Sudan living in Israel, have been taken into custody or ordered to report to a detention center over the past two weeks.

Eritrean and Sudanese workers across the country were told by protest organizers to skip work Sunday through Tuesday. The unofficial strike is expected to affect the many restaurants, cafes, hotels and janitorial companies employing African migrants.

“Our strike is not an act against the employers but a form of protest,” said the statement released by human rights activists involved in the protest. “We are aware of the risk of striking, that we are liable to lose our jobs and our incomes. This step is meant to clarify to Israelis society: We fled here because of the danger to our lives in our countries of origin. We are seeking political asylum. Like every person, we also want to earn an income so we can live in dignity – but work is not the reason we came to Israel.”

Protest organizers are calling for the law authorizing the opening of the Holot detention center to be overturned, as well as for Israel to stop rounding up migrants and to release all those jailed under the new law. They are also calling on Israel to honor the UN Refugee Convention and give reasonable consideration to all asylum requests.

They plan to contact the United Nations representative for refugees and foreign embassies in Israel to ask the world body to pressure Israel “to take on its share of the responsibility for the asylum seekers.”

The organizers sought permission for a march through Tel Aviv but did not receive a permit from the city. Last month an estimated 1,000 Sudanese and Eritrean migrants, along with Israeli human rights activists,marched through the streets of Tel Aviv to urge the government to consider the asylum requests of migrants from Africa and release the approximately 3,000 held in Israeli custody.

The recently opened Holot detention center is considered an open detention center because migrants held there are allowed to leave during daylight hours, but they must report for roll call three times a day, in an effort to keep them from getting a job. The facility “ought to be called a jail,” says a flyer announcing the strike.

“Our only sin is that we ran away from political persecution, forcible military service, dictatorship, civil war and genocide,” the flyer says.

Organizers are holding a planning meeting for African migrants Monday morning in Levinsky Park in Tel Aviv, to discuss the next steps in the protest


የደቡብ ሱዳን አዙሪት… …ከሪፍረንደም ወደ ደም!

$
0
0

የደቡብ ሱዳን አዙሪት… …ከሪፍረንደም ወደ ደም!

“እኔ ደቡብ ሱዳንን ነፃ አወጣት ዘንድ የተመረጥኩ የኑዌሮች ልጅ ነኝ… ተከተሉኝ ወደ ነፃነት እንሂድ!” በስተመጨረሻም ሱዳናውያን ከዘመናት የእርስ በርስ ጦርነትና የጎሳ ግጭት ትርፍ እንደሌለ ገባቸው…

   ከጠመንጃ የተሻለ አማራጭ ለመውሰድ ፈቃዳቸው ሆነ፡፡ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲና የሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ በፈረሙት የሰላም ስምምነት፣ ከ25 ዓመታት በላይ የዘለቀውን የእርስ በርስ ግጭት መቋጫ አበጁለት – እ.ኤ.አ በ2005 ዓ.ም፡፡ ይህን ስምምነት ተከትሎ ሱዳናውያን፣ ዕጣ ፋንታቸውን በፍጥጫ ሳይሆን በምርጫ፣ በደም ሳይሆን በሪፈረንደም ለመወሰን ተስማሙ፡፡ ከአጠቃላዩ የደቡብ ሱዳን ህዝብ 99 በመቶ ያህሉ፣ የሱዳንን ሁለት መሆን ደግፈው ድምጻቸውን ሰጡ። ሃምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም፡፡ ይህቺ ቀን ከ11 ሚሊዮን ለሚበልጡት ደቡብ ሱዳናውያን ልዩ ትርጉም አላት፡፡ የዘመናት ደም መፋሰስ የተቋጨባት፣ የአዲስ ንጋት ጮራ የፈለቀባት፣ ነጻነት የታወጀባት ልዩ ቀናቸው ናት – አዲሲቷ ደቡብ ሱዳን 195ኛዋ አገር ሆና አለምን የተቀላቀለችበት፡፡

ለሩብ ምዕተ አመት ከዘለቀ የእርስ በርስ ግጭትና ደም መፋሰስ በኋላ፣ ሱዳንን ሰሜን ከደቡብ ለሁለት የሚከፍል ድንበር ተሰመረ፡፡ “የነጻነት ቀን መጣች!!” የሚል መዝሙር ከደቡብ ሱዳን ሰማይ ስር ተዘመረ። ይህ ክስተት ከአለም ፖለቲካዊ ስኬቶች አንዱ እንደሆነ ተነገረለት፡፡ ከደቡብ ሱዳን ሰማይ ስር የሰላም ጀንበር ወጣች ተብሎ አገር በደስታ ፈነጠዘ። ደስታ፣ እልልታና ጭፈራ ሆነ፡፡ የአዲሲቷ ደቡብ ሱዳን ባንዲራ፣ በነጻነት ዝማሬ ታጅባ ከፍ ብላ ተሰቀለች። ለሁለት አመታት አንጻራዊ የሰላም አየር ከሚነፍስበት ሰማይ ስር በነጻነት ተውለበለበች፡፡ ወደሶስተኛው አመት መንፈቅ ያህል እንደተጓዘች ግን፣ ያልተጠበቀ አውሎንፋስ ሳይታሰብ ከተፍ ብሎ ከወዲያ ወዲህ ያራግባት ጀመር፡፡ ከሱዳን ለመገንጠልና ነጻ ለመውጣት በአንድነት አብረው ለዘመናት ሲዋደቁ የኖሩ የደቡብ ሱዳን ጎሳዎች፣ የጋራ ጠላታቸውን ባሸነፉና ነጻ ወጣን ባሉ በሁለት አመታቸው እርስ በርስ ጦር ለመማዘዝ ተዘጋጁ፡፡ ጎሳ ድንበር ሆኖ አይለያየንም ብለው አብረው ለመኖር የተስማሙ ደቡብ ሱዳናውያን፤ ጎራ ለይተው ሊታኮሱ፣ ጎሳ መድበው ሊጫረሱ፣ ዳግም ለሌላ ጦርነት ክተት አውጀው ተነሱ፡፡ ተነጋግረው ያወረዱትን፣ በቃን ብለው የጣሉትን ደም የለመደ ጠመንጃ ዳግም መልሰው ጨበጡ፡፡ ወደ አደባባይ ወጡና እርስ በርስ ተበጣበጡ፡፡ ከሁለት አመታት በፊት በሪፈረንደም ነጻነታቸውን ያወጁት ደቡብ ሱዳናውያን፣ ከሳምንታት በፊት አዲስ ግጭት ውስጥ ገብተዋል። አዲሲቷን ደቡብ ሱዳን ይመሩ ዘንድ በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር፣ መንበራቸው ላይ ሶስት አመት ሳይቆዩ ነቅናቂ መጥቶባቸዋል፡፡ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር ናቸው፣ በሳልቫ ኬር ላይ አማጽያንን አስታጥቀው የዘመቱባቸው፡፡ ሲጀመር ስልጣን ፈላጊዎች ያሴሩት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ነው ተብሎ የተነገረለት የሰሞኑ የአገሪቱ ግጭት፣ እየዋል እያደር ግን የአገሪቱን ጎሳዎች ጎራ ለይቶ ያሰለፈ መረር ያለ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄ መሆኑ እየለየ መጥቷል፡፡ ከአገሪቱ ህዝብ አብላጫውን ቁጥር (ከህዝቡ 15 በመቶ) የሚይዙት የዲንቃ ጎሳ አባላት ሲሆኑ፣ የኑዌር ጎሳ አባላት ደግሞ 10 በመቶ በመያዝ በብዛት የሁለተኛነትን ደረጃ ይይዛሉ፡፡

ሳልቫ ኬር ከዲንቃ፣ ማቻር ደግሞ ከኑዌር መሆናቸው የሁለቱን ግጭት የግለሰቦች ብቻ ሳይሆን የጎሳዎች ጉዳይ አድርጎታል እየተባለ ነው፡፡ በአብዛኛው ሳልቫ ኬር የወጡበት የዲንቃ ጎሳ አባላትን የያዘው የደቡብ ሱዳን መንግስት ጦር፣ ከኑዌር ጎሳ የሆኑት የቀድሞው ምክትል ፕሬዜዳንት አስታጥቀው ያሰለፏቸውን አማጽያን ለመደምሰስ ታጥቆ ተነስቷል፡፡ በአሜሪካ የሰላም ኢንስቲቲዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ ፖለቲከኛ ጆን ቴሚን እንደሚሉት፣ ኬርና ማቻር እንዲህ በይፋ ባይታኮሱም በወንበር ጉዳይ በጥርጣሬና በጥላቻ ሲተያዩ የኖሩ የረጅም ጊዜ ባላንጣዎች ናቸው። የግጭቱ ሰበብ ብዙዎች እንደሚሉት ነዳጅ በገፍ የመጥለቅ ጉጉት ብቻ ሳይሆን በእነዚህ ባለስልጣናት መካከል ያለው የስልጣን ሽኩቻና የዘመናት ታሪክ ያለው ያልተፋቀ የጎሳ ልዩነት ነው ባይ ናቸው ፖለቲከኛው፡፡ ሳልቫ ኬር ባለፈው ሃምሌ የቀድሞውን ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻርን ጨምሮ ሌሎች የካቢኔ አባላትን ማባረራቸው፣ ከዘመናት የእርስ በርስ ግጭት ለአፍታ አርፋ የነበረችውን አገር ዳግም ወደከፋ ነገር ሊከታት የሚችል መንገድ ጠርጓል። በአጭር የስልጣን ዘመናቸው ህገመንግስቱን የጣሱ በርካታ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል ተብለው የሚታሙት ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር፣ በካቢኔው ላይ ያሳለፉት ውሳኔ ብዙዎችን አበሳጭቷል፡፡ የወሰዱት እርምጃ የስልጣን ጥመኛነታቸውን ብቻም ሳይሆን ዘረኛነታቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡ የሱዳን ትሪቢዩኑ ዘጋቢ አቲያን ማጃክ ማሉ እንደሚለው፣ ሳልቫ ኬር ባባረሯቸው የካቢኔ አባላት ምትክ የሾሟቸው አብዛኞቹ ባለስልጣናት፣ በእርስ በርስ ጦርነቱ ጊዜ ከካርቱም ባለስልጣናት ጋር ይሰሩ የነበሩና አሁንም ድረስ ቅርበትና ወዳጅነት ያላቸው ናቸው፡፡

ይህም በሹም ሽሩ ውስጥ የሱዳን እጅ ሳይኖርበት አይቀርም የሚል ጥርጣሬን በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል፡፡ በዚህ አወዛጋቢና ፍትሃዊ አለመሆኑ የሚነገርለት ሹም ሽር ከምክትል ፕሬዚደንትነታቸው ተነቅለው የተባረሩት ማቻር፣ ቂም ቋጥረው ነበር ወደ ትውልድ ቦታቸው ዩኒቲ ግዛት የሄዱትና የኑዌር ጎሳ አባላትን ለአመጽ የቀሰቀሱት፡፡ “ሳልቫ ኬር የሚሉት አምባገነን የሚመራው የዲንቃ ጎሳ መንግስት፣ ከአገራችን ጠራርጎ ሊያጠፋን ተነስቷል፡፡ እኛ ኑዌሮች በድህነት ስንማቅቅ፣ እነሱ ግን ነዳጅ እየቸበቸቡ ሊንደላቀቁ ማነው የፈቀደላቸው?!… ተነሱ እንጂ ጎበዝ!” ብለው ቀሰቀሱ ማቻር፡፡ ድሮም በመንግስት ስልጣን አናሳ ቦታ ይዘናል፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታችንም ፍትሃዊ አይደለም ብለው እርር ትክን ይሉ የነበሩት ኑዌሮችና የሌሎች አናሳ ጎሳዎች ወታደሮች ናቸው፣ የማቻርን ጥሪ ሰምተው ነፍጥ ያነገቡት፡፡ ከፕሬዚዳንቱ ታማኝ የጸጥታ ሃይሎች ጋር የከረረ ግጭት ውስጥ የገቡት፡፡ “ልብ አርጉልኝ!… ማቻር የሚሉት ሴረኛ መንግስቴን ሊፈነቅል ነው!” ሲሉ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ አቤት አሉ ሳልቫ ኬር፡፡ ማቻር በበኩላቸው፣ “ያለ ስሜ ስም እየሰጠኝ ነውና አትስሙት!… ሰውየው እልም ያለ ሙሰኛና አምባገነን ነው!” በማለት ውንጀላውን አስተባበሉ፡፡ ሁለቱም ያሉትን ሲሉ፣ የሁለቱም ጦር ተግቶ መታኮሱን ቀጠለበት፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት እየሰፋ የመጣው ጦርነት ከአገሪቱ አስር ግዛቶች አምስቱን አዳርሷል፡፡ ታማኝ ምንጮቼ ያላቸውን ጠቅሶ ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው፣ ደቡብ ሱዳናውያን የጎሳ መደባቸው እየታየ ብቻ ግድያና ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መረጃን ዋቢ በማድረግ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፣ እስካለፈው ማክሰኞ ብቻ በግጭቱ ከ1ሺህ በላይ ዜጎች ሞተዋል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ ባሉ የጅምላ መቃብሮች ውስጥ እየተገኙ ያሉ አስከሬኖች የሟቾችን ቁጥር ከፍ እያደረገው ነው ተብሏል፡፡ የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ቤኒቱ ውስጥ ባለ የመቃብር ስፍራ ብቻ 34 አስከሬኖች ሲገኙ፣ በአቅራቢያዋ ካለ የወንዝ ዳርቻም የሌሎች 20 ሟቾች አስከሬን ወድቆ ተገኝቷል፡፡ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ናቪ ፒላይ በበኩላቸው፤ የማቻር ወታደሮች በተቆጣጠሩት አንድ አካባቢ 75 አስከሬኖች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡ ፍለጋው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥርም ከዚህ በእጅጉ እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡ የመንግስት ጦር ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያለባቸውንና 95 በመቶ የአገሪቱ ኢኮኖሚ የተመሰረተባቸውን በአማጽያኑ በቁጥጥር ውስጥ የገቡ ቤኒቱን የመሳሰሉ ቦታዎች ለማስለቀቅ መታኮስ ከጀመረ ሁለት ሳምንታት አልፈዋል። የአማጽያኑ ጦር የአገሪቱን መዲና ጁባን ለመቆጣጠር 200 ኪሎ ሜትሮች ብቻ እንደቀረው ሲናገር፣ መንግስት በተራው እየጠራረግኋቸው ነው እያለ ይገኛል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ በነዳጅ አምራችነቷ ወደምትታወቀው የላይኛው አባይ ግዛት ዋና ከተማ ማላካል የተዛመተው ግጭት፣ ቀስ በቀስ ወደ ቦርና ሌሎች ከተሞች መስፋፋቱን ቀጥሏል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች ከኑሯቸው ተፈናቅለው በርእሰ መዲናዋ ጁባና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ተበትነው ይገኛሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ከመጣባቸው መከራ ለማምለጥ ወደ ቢሮው ለመጡ ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ዜጎች ከለላ ለመስጠት የቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ 24 ሺህ ያህል ተፈናቃይ ዜጎች ከመጣው መዓት ለማምለጥ በጫካዎች ውስጥ ተደብቀው እንደሚገኙና፣ ሌሎች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩም በአብያተ ክርስቲያናት ቅጽር ግቢ እንደተጠለሉ ዘ ጋርዲያን ባለፈው ማክሰኞ ዘግቧል፡፡ 6ሺህ 800 ሰላም አስከባሪዎችን በስፍራው ያሰማራው የተመድ የጸጥታው ምክርቤት፣ ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱን በማጤን ተጨማሪ 5ሺህ 500 ወታደሮችን ለማሰማራት ውሳኔ ላይ ደርሷል። ያሰማራቸውን ፖሊሶች ቁጥርም ከ900 ወደ 1ሺህ 323 ከፍ ለማድረግ አቅዷል። ይህ እርምጃ ተፈናቃይ ዜጎችን ለመርዳት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ባይካድም፣ የተመድ ዋና ጸሃፊ ባንኪሙን ግን፣ ግጭቱ ፖለቲካዊ እንደመሆኑ ፖለቲካዊ እንጂ ወታደራዊ መፍትሄ እንደማይኖረው ተናግረዋል፡፡ ግጭቱ በአገሪቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የነዳጅ ምርት ስራ በከፍተኛ ሁኔታ እየደናቀፈ ይገኛል፡፡ የደቡብ ሱዳን የፔትሮሊየም ሚንስትር ስቴፈን ዲሁ ዳው እንዳሉት፣ በዩኒቲ ግዛት ይከናወን የነበረው የነዳጅ ምርት፣ ግጭቱ መከሰቱን ተከትሎ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል፡፡ ይህም 250 ሺህ በርሜል ከነበረው የአገሪቱ ዕለታዊ የነዳጅ ምርት 45 ሺህ በርሜል ያህል ቅናሽ አስከትሏል፡፡

ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለም የአገሪቱን የነዳጅ ምርት ክፉኛ እንደሚጎዳው ይጠበቃል፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው፤ በደቡብ ሱዳን የተከሰተው ግጭት አገሪቱ ለአለማቀፍ ገበያ በምታቀርበው የነዳጅ ድፍድፍ አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል በሚል ስጋት፣ የተለያዩ ኩባንያዎች ባለፈው ማክሰኞ በነዳጅ ዋጋቸው ላይ የተወሰነ ጭማሪ አድርገዋል፡፡ የተለያዩ የአለም አገራት በጉዳዩ ላይ የተለያየ አቋም መያዛቸው እየተነገረ ነው፡፡ ልዕለ ሃያሏ አሜሪካ የአሸባሪዎች ስፖንሰር ከምትላት ሱዳን ተገንጥላ ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች አገር መሆኗን አጥብቃ ስትደግፍ ነው የኖረችው፡፡ ለወደፊት ከነዳጇ የመቋደስ ዕድል ይኖረኛል ብላ የምታስበዋ አሜሪካ፣ ደቡብ ሱዳን ወደ ሌላ ጦርነት እንድትገባ አትፈልግም፡፡ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርም፤ ኬርና ማቻር ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጥሪያቸውን ልከዋል፡፡ ድርድሩን የሚያመቻች ልዩ ልኡክና ዜጎችን ከአደጋው የሚያተርፉ 150 ያህል ልዩ የባህርና የአየር ሃይል አባላትንም በጅቡቲና ኡጋንዳ በኩል ወደዚያው ልከዋል፡፡ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኡጋንዳና ኬኒያን የመሳሰሉ አገራት ዜጎቻቸውን ከደቡብ ሱዳን ለማስወጣት እየተጣደፉ ይገኛሉ፡፡ እስካሁን 380 አሜሪካውያንና 300 የሌሎች አገራት ዜጎች በአፋጣኝ ከደቡብ ሱዳን እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ በአገሪቱ የተቀሰቀሰው ቀውስ እንዲህ እንደዋዛ በአጭር ጊዜ እልባት አግኝቶ የሚበርድ አለመሆኑን የሚናገሩ ተንታኞች ብዙ ናቸው፡፡ በወቅታዊ አለማቀፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቀው ሱፍያን ቢን ኡዝያር፣ ጉዳዩ የስልጣን ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ የጎሳ ጥያቄ ጭምር መሆኑ አሳሳቢና የበለጠ አስከፊ እንደሚያደርገው ይናገራል፡፡ ሳልቫ ኬር ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ለተቀናቃኞቻቸው የማይተኙና ወንበራቸውን ላለማስነካት ታጥቀው የቆሙ መሆናቸውን የገለጸው ኡዝያር፣ ማቻር በበኩላቸው ቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የመሆን አላማ እንዳላቸው በአደባባይ ሲናገሩ መሰማቱን ጠቁሟል፡፡ መለሳለስ የማይታይበት የሁለቱ ሰዎች አቋም ነገሩን የበለጠ እንደሚያከረውም ተናግሯል፡፡ አሜሪካ፣ ኖርዌይና ኢትዮጵያ የሚመሩት ቡድንም ወደ አገሪቱ በማምራት ችግሩ በሰላማዊ ድርድር የሚፈታበትን መላ ለመፈለግ የራሱን ጥረት አድርጓል፡፡ አሜሪካ ወደ ደቡብ ሱዳን የላከችውን ልዩ ልኡክ በመምራት ወደ ጁባ ያመሩት ዶናልድ ቡዝ፣ ሁለቱን አካላት ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ ለማግባባት ጥረት አድርገዋል፡፡

ኬርና ማቻርም ለውይይት ፈቃደኛ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ ነገሩ ከልብ አይመስልም፡፡ ማቻር ውይይቱን ማድረግ የምችለው በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ አጋሮቼ ሲፈቱ ብቻ ነው ሲሉ፣ ኬር በበኩላቸው ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ አልፈልግም ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ቆራጥ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ መቀጠላቸውም ሆነ፣ የአማጽያኑን ጦር የሚመሩት ማቻር አዲስ ወታደራዊ መንግስት በመመስረት ላይ እንደሚገኙ ፍንጭ መስጠታቸው፣ በዚች አገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰላም የመውረድ ተስፋ እንደሌለ ያመላክታል ብሏል ኡዝያር። ይልቁንም አገሪቱ ወደባሰ የእርስ በርስ ጦርነት የመግባት ዕድሏ ሰፊ ነው ባይ ነው፡፡ ከአለማቀፍ ሰሞንኛ መነጋገሪያ የቀውስ አጀንዳዎች አንዱ የሆነው የሁለቱ ሃይሎች ግጭት፣ በብዙዎች የተለያየ ትንተና እየተሰጠበት ይገኛል፡፡ ድህነት፣ የጎሳ ፖለቲካ፣ አምባገነንነት፣ ኢ- ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፣ የስልጣን ጥም፣ የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት… እና ሌሎችም ጉዳዮች ለደቡብ ሱዳን ግጭት መነሻ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ የሱዳን ትሪቡዩኑ ዘጋቢ የአቲያን ማጃክ ማሉ ብያኔ፣ ‘ሌሎችም’ ከሚለው መደብ ውስጥ ይፈረጃል፡፡ ማሉ እንደሚለው፣ የሰሞኑ የደቡብ ሱዳን ግጭት ንጉንዲንግ ከተባሉት የኑዌር ነብይ ትንቢት የመነጨ፣ የማቻር ቅዠት ነው፡፡ ከመቶ አመታት በፊት በህይወት የነበሩት እኒህ የኑዌር ጎሳ አባል የሆኑ የተከበሩ ነብይ፣ በአንድ ወቅት “ከኑዌር ጎሳ የሆነ ጥርሰ ፍንጭትና ግራኝ ሰው ደቡብ ሱዳንን ነጻ ያወጣታል፣ ህዝቧንም በወጉ ይመራል” የሚል ትንቢት ተናግረው ነበር፡፡ ትንቢቱ ከተነገረ ከዘመናት በኋላ፣ ሬክ ማቻር ወደራሱ ተመለከተ፡፡ እሱ የኑዌር ጎሳ አባል ነው፡፡ እሱ ጥርሰ ፍንጭት ነው፡፡ እሱ ግራኝ ነው፡፡ ማቻር፤ በኑዌሮች መካከል ግራ እጁን ወደላይ ከፍ አድርጎ በፍንጭት ጥርሱ እየተፍለቀለቀ እንዲህ ሲል ተናገረ…“እኔ ደቡብ ሱዳንን ነጻ አወጣት፣ ህዝቧንም በወጉ እመራ ዘንድ የተመረጥኩ የኑዌሮች ልጅ ነኝ!!… ተከተሉኝ ወደ ነጻነት እንሂድ!!…” በደል ያንገበገባቸው፣ ጭቆና የሰለቻቸው፣ ደማቸው የፈላባቸው ኑዌሮችም፤ ሌሎች ተበዳይ ጎሳዎችን አግተልትለው፣ የጀግና ልጃቸውን ማቻርን ዱካ ተከትለው፣ ወደ ጁባ ሊተሙ ጠመንጃቸውን ወለወሉ – ይላል አቲያን ማጃክ ማሉ፡፡

addisadmass news paper. 04 January, 2014 Written by አንተነህ ይግዛው

Image


የህወሓት ስራ እስፈጻሚ ኣካል ዉስጣዊ ኣጀንዳቸው በተመለከተ በመቀሌ ከተማ ያደረጉት ስብሰባ ካለ መግባባት ተበተነ፣

$
0
0

ህ.ወ.ሓ.ት ክፍተኛ የስራ ኣስፈጻሚ ኣካላት ሁነው በተለያየ የሃላፍነት ቦታ የሚገኙ የስርኣቱ ባለስልጣናት፤ በ ታህሳስ 8 2006 ዓ/ም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ባካሄዱት ምስጣራዊ ስብሰባና በተነሳው ኣጀንዳ መስማማት ላይ ሳይደርሱ፤ ተበታትነው እንደወጡ ከዉስጥ ኣዋቂዎች የደረሰን መረጃ ኣመለከተ.. መረጃው ኣክሎ በስብሰባው የህ.ወ.ሓ.ት ኣስፈጻሚ ኣካል ሁነው በሚንስተር መኣርግ ደረጃ ያሉና የክልሉ ኣስተዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆኑ፤ በዉስጣቸው የሚፈጸም የህዝብ እና የኣገር ሃብት ብክነት በነማን እየተፈፀመ እንዳለ በግልጽ መታወቅ ኣለበት የሚል ኣጀንዳ በመነሳቱ ምክንያት ያልተዋጠላቸው እንዳንድ የስራኣቱ ኣመራሮች የተነሳው ኣጀንዳ እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችለዋል፣ ከነዚህ የህዝብ ገንዘብ በመዝመት ሃብት ያካበቱ ተብለው የተገለጹ ኣባይ ወልዱ፤ በየነ ምክሩ፤ ኪሮስ ቢተው፤ ኣለቃ ጸጋይና የሱ ሚስት የሆነችው ቅዱሳን ነጋ ሲሆኑ በስብሰባው ወቅት በመጀመርያ ሙሱና የመፈጸም ተግባር በዉስጣችን መጽዳት ኣለበት የሚል ጥያቄ መነሳቱ ደስታ ስላልፈጠረላቸው ያላቸው ሃላፍነት ተጠቅመው ስብሰባው ያለ ምንም ፍሬ እንዲበተን የሚቻላቸውን እንዳደረጉ የደረሰን መረጃ ኣክሎ ኣስረድተዋል:: source ዴ.ም.ህ.ት cv Posted by Addisu Wond.



እስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አዲሱን የአንድነት አመራር «ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት» አላቸው፤

$
0
0

የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን ያገኘውና በእድሜ ልክ እስራት በገዢው መንግስት ተበይኖበት ቃሊቲ የሚገኘው አንዷለም አራጌ ትላንትና ጠዋት ሊጠይቁት የሄዱትን አዳዲሶቹን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች «ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት፤.. ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋ አለኝ» ማለቱ ተገልጿል።

ባሳለፍነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን እና ካቢኔያቸውን በምርጫ አሰናብቶ በአዲስ የሾመው አንድነት ፓርቲ፤ አዳዲሶቹ ተሿሚዎች ስልጣናቸውን ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ ሥራቸውን ያደረጉት በእስር ቤት የሚገኙትን የፓርቲዎቻቸውን አባላት መጠየቅ ነበር። በዚህም መሠረት አዳዲሱ አመራር እስርቤት ከሚገኙት የድርጅቱ አመራሮችና አባላት የሚያበረታቱ ምክሮችን መቀበሉን ለመረዳት ተችሏል።

አንዷለም አራጌ በአዲሱና በወጣት በተገነባው የአንድነት ፓርቲ አመራር ደስተኛ መሆኑን ገልጾ «ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት፤ ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋ አለኝ» ብሏቸዋል። ይኸው የአንድነት ፓርቲ አመራር እዛው ቃሊቲ የሚገኙትን እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የሕሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ጠይቆ መከልከሉ የታወቀ ሲሆን ወደ ዘዋይ ያመራው የአንድነት ፓርቲ ቡድን እዛው እስር ቤት የሚገኙትን የአንድነት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንንና በዚያ የሚገኙ ሌሎች እስረኞችን መጎብኘታቸውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሕወሓት/ ኢሕአዴግ አስተዳደር «በሽብርተኝነት ወንጀል» ተከሷል፤ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ደግሞ የሕሊና እስረኛ ነው የሚባለው አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም ከእስር ቤት ተቃዋሚዎች የእኔን እስር ቤት መማቀቅ ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም፤ ሕዝቡን ለማታገል ልትጠቀሙበት ትችሉ ነበር ሲሉ የነበረውን ድክመት መግለጹ አይዘነጋም።


ኬሳ ኬሳ አዱሬን ቢነሳ…(ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት) ክፍል 1( በቶሎሳ በቀለ)

$
0
0

ይድረስ ታሪክ ለመታንሻፈፉ እና በብሄር ለማጋጨረት ለምትጠሩ ሁሉ

አባቴ አንድ ነገር ሳይጥማቸው ሲቀር ‹‹ኪሳ ኬሳ አዱሬን ቢኒሳ..›› ይላሉ፡፡ ‹‹ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት..›› ማለት ነው፡፡ ይህ የኦሮሞን አባባል የተጠቀምኩት የኦሮሞ ልጆች ላይ ነብር መስለው ድመት የሆኑ የተገላበጠ ገመና ያላቸው እንደ እባብ ቆዳቸውን እየሸለቀቁ ወደ እሳት የሚገፉት ስንኩል ሰዎች ስላሉ ነው፡፡ ለእነዚህ የታሪክ ዝቃጮች ጥያቄ ማቅረብና እና እውነታውን ማሳየት እፈልጋለሁ…..መጀመሪያ ደረጃ ለጁዋር እና ብጤዎቹ መጠየቅ የምፈልገው….የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ታሪክ አለው ወይ? ኢትዮጵያስ ከኦሮሞ ህዝብ የተነጠለ ታሪክ አላት ወይ? እንደ አለመታደል ሆኖ ጥሩ አስተዳደር ያላገኘው ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ተረግጦ ተበድሎ እኩል እየተበደለ፣ እየሞተ ነው የኖረው፡፡
አሁን ኦህዲድን ከመሰለ አሸርጋጅና ወገኑን በላ ድርጅት ጀምሮ ለመጣው ሁሉ ሲሰግዱ እጅ መንሻ የሚያቀርቡት የኦሮሞን ልጅ ጭዳ አድርገው ነው፡፡ ይሄ ስልጣን ፈላጊ ኦሮሞ የኦሮሞን ልጅ አሳልፎ መስጠት በፊትም የነበረ ነው፡፡ እውነት እንነጋገር ካልን የአኖሌን ጭፍጨፋ እውን ምኒልክ ነው የፈጸመው? የኦሮሞን ልጅ አጥንት ሲበላው የሚታየው ለገዢው አካል አሸርጋጅ ሆኖ የሚያጎበድድ የኦሮሞ ልጅ ነው፡፡ የኦሮሞን ህዝብ የጨፈጨፈው ጎበና ዳጬ ሆኖ ሳለ አንድም ቀን ስትጠሩት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ለምን?…
ስላለፈውና ያልሆነውን ሆነ ብሎ በማውራት ለነገም ስቃይን ማስቀመጥ ምን ይሰራል? እውነት እንነጋገር ከተባለ ማንም ጥሩ ጎን ቢኖረውም መጥፎ ጎን እንዳለውም መዘንጋት የለበትም፡፡ ምኒልክ ሰው ነው ሁሉ ነገሩ ጥሩ ነው ማለት አይቻልም፡፡ እሺ እንዳላችሁት ጎበና ዳጬን በማዘዝ ኦሮሞ ህዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋል ብለን እናስብ፡፡ ግን በስልጣን ዘመናቸው ጥሩም ነገር ማድረጋቸውን አንዘንጋ፡፡
በተጨማሪ የጣሊያንን ወረራ ኃይል ምኒልክ በድል ተወጥተው ባያሸንፉ (የአድዋ ድል..የጥቁር ህዝብ ኩራት) ባይከሰት በጣሊያን ቅኝ ብንገዛ ኖሮ ዛሬ ስምህ ወይም ስማችን ማን ይሆን ነበር? ሮቤርቶ፣ ካርሎስ..ኪኪኪኪ…ይሄ ስምና ማንነት ላይ የሚመጣውን ለውጥ እንተወው፡፡ የኦሮሞ ዋነኛው ስርዓት፣ ባህል፣ እምነት..ዋቄፈታ፣ ዋቄፋና ነው፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ማንነት መገለጫ የሆነው ኢሬቻስ ይደረግ ነበር? የገዳ ስርዓትስ ይኖር ነበር? ቅኝ ግዛት ዋነኛ አላማው እንደዚህ አይነት የማንነት መገለጫዎችን ማጥፋት መሆኑን እንዴት ረሳችሁት፡፡ የመዳ ወላቡስ ታሪክ ይቀጥል ነበር ወይ?
ሌላም ነገር ልጠይቅ ወደድኩ፡፡ ዛሬ ምሁር ለመምሰል አነጋገር የምታሳምሩ ታሪክ መስራት ሲያቅታችሁ ከመቶ አመት በፊት የተፈጸመን ነገር እያነሳን እርስ በእርሳችን እንድንናቆር መንገድ ከምትጠርጉ ለኦሮሞ ህዝብ የሚበጀውን ለምን አትጠቀሙም፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ምኒልክ ነው ወይስ ወያኔ ነው የኦሮሞ ህዝብ ራስ ምታት? ዛሬ የኦሮሞን ልጅ እየገደለ፣ እያሰቃየ፣ ለስደት እየዳረገ ያለው ገዢው ወያኔን ለምን ታግላችሁ መጣል አትሞክሩም? ይህን ብታደርጉ ነው ለኦሮሞ ልጅ እውነተኛ ተቆርቋሪ የምትሆኑት፡፡ ያለበለዛ ወዲያልኝ ወዲያ ዋጋም የለሽ ብሬን መልሽ እንደተባለው አይነት ናችሁ፡፡ አሁን እየሞትን ባለፈ ታሪክ ላይ የምታላዝኑ… (ሀሬ ዱቴ ኩር ኢንጀጠኒ..) ይላል አባቴ፡፡ የሞተ አህያ ኩርር…አይባልም እንደማለት ነው፡፡
ከደቡብ አፍሪካ ብሎም ከማንዴላ ምን መማር አለብን? ብሔራዊ እርቅ…ያለፈን ይቅር ብሎ በሰላም መኖር ነው የሚበጀው፡፡ የኦሮሞ ህዝበ እሰከዛሬ ያየው እያየ ያለው ሰቆቃ ይበቃዋል፡፡ አሁንም ቢሆን ኢህአዴግ በስሩ የፈለፈለው ኦህዲድ የሚባል የአሸርጋጆች ቡድን የወገናቸውን ደም መጣጮች ህዝቡን እየሸጡት ነው፡፡ መድረስ ያለብን አሁን በስቃይ ውስጥ ላለው ህዝብ ነው፡፡
በቀጣዩ ክፍል እንገናኝ


ተወደደም ተጠላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በኦሮሞና በአማራው እጅ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

$
0
0
Imageበአንድ ወቅት የወያኔ ፈጣሪ ስብሃት ነጋ የለውን ብንመለከት የአክሱም ስርወ መንግስት አጋሜውን፣ ተንቤኑንና እንደርታውን አይመለከተውም ብሎ ለቪኦኤ መግለጫ ሲሰጥ አይመለከታቸውም የተባሉት ትግራውያን እንዴት ብለው ሲቃወሙ አልሰማናቸውም… በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ደግሞ ያ የወያኔ ማፈሪያ መለስ ዜናዊ የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነወ፣ ባድመ ለሶማሌው ምኑ ነው የሚል ርካሽና መናኛ Analogy እያቀረበ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባዶነት እንዲሰማውና ሉኣላዊነቱን ለማስከበር ምንም ስሜት እንዳይኖረው ለማድረግ ብዙ ሲወተውት ሰምተነው ነበረ፡፡ በጣም የሚገርመውና የማይረሳው ቁም ነገር ደግሞ ይህ ነበር፡፡ የአክሱም ሐውልት ለወላይታ ምኑ ነው ሲለው የተናደደው የጋሽ ቶጋ ልጅ ተሾመ ነው ሮም የነበረውን የአክሱም ሐውልት ያስመለሰው፡፡ ብዙ ውስብስብና አስቸጋሪ ውጣ ውረዶች ቢኖሩበትም ባድመ ምኑ ነው የተባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ውለታ ቢሶቹን ትግራዮች የታደጋቸው፡፡ ወያኔ የኦሮሞን ሕዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት በአሁን ሰዓት የሚጠቀምበትን ስልት እምዬ ምኒልክ እንዳልተጠቀሙበት ነው፡፡ የታሪክ ተመራማሪ ባልሆንም እንዳንድ እውነታዎችን ብጠቅስ ለተመራማሪዎች ግብዓት ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከሰፈረበት የመልካምድር አቀማመጥ አንጻር ባህሉ ልዩነት ሊኖረው ችሏል፡፡ እኔ ባህል ስል የእምነት ባህል፣ የአለባበስ ባሕል፣ የጋብቻ ባህል፣ የአኗኗር ባህል፣ ወዘተ. ነጮቹ Cultural Diffusion እንደሚሉት ሊመጋገብ ይችላል፡፡ በሸዋ አካባቢ ያለው ኦሮሞ ከአማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ ጋር ተቀራርቦ በመኖሩ በሁለቱ ቢሔረሰቦች መካከል እንዳንድ የባህል ውርርስ ቢታይ ዛሬ ወያኔ እንደሚያናፍሰው ሳይሆን አብሮ በመኖር ሂደት የተፈጠረ ማህበራዊ ግኑኝነት በመሆኑ ሊፋቅ የማይችል ነው፡፡ በሐረር አካባቢ የሚኖር ኦሮሞ እንዳንድ ባህል ከሶማሌ፣ ከአደሬ፣ ከአፋር፣ ከኢሳ፣ ወዘተ በአለባበስ፣ በንግግር ፣ በጋብቻ፣ ወዘተ ቢመሳሰል ምንም ሀጢአት የለውም፡፡ የቦረና ኦሮሞ ከገሪ፣ ገሪ መሮ፣ ሶማሌ፣ ወዘተ ባህል ሊለዋወጥ ግድ ነው፡፡ የአርሲ ኦሮሞም እነደዚሁ ከአካባቢው ህዝብ ጋር የባህል ልውውጥ ሊኖረው ይችላል፡፡ ታዲያ ምንድነው ችግሩ? ምን ይሁን ነው የሚባው? ሕዝብ ለሕዝብ አብሮ በመኖር ሂደት ባህል ሊጋራ መቻሉ ዛሬ እንደ ሃጢአት ተቆጥሮ የአሮሞንና አማራን ሕዝብ ለረጅም ጊዜ አብረው በመኖር ያካበቱትን ማህበራዊ እሴት አፈራርሶ 150 ዓመት ወደ ኋላ ለመሄድ ጊዜን Rewind ለማድረግ እንደመሞከር ነው፡፡ እንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ እኔ አማራ ነኝ፡፡ ብሆንም ግን ተወልጄ ባደግሁበት አካባቢ እየተመገብኩ የኖርኩትን ጩኮና ጨጨብሳ የኦሮሞ ባህላዊ ምግብ ስለሆነ ያንተ ባህል አይደለምና ተው ብሎ ከፊቴ የሚቆም ምን ዓይነት ኃይል ያለው ሰው ሊኖር ይችላል? የሰው ስም እየጠቀስኩ እከሌ የሚባል ኦሮሞ ብዬ አስተያየት ለመስጠት ብቸገርም በተለይ አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ግን ለምን ስለ አብሮነት አጥብቀው አይከራከሩም ብል የተሳታትኩ አይመስለኝም፡፡ አንድነት ኃይል ነው፡፡ ከአምባላጌ ተራራና ከደደቢት የተነሱ እፍኝ የማይሞሉ መሃይም እረኞች በነደፉት የተሳሳተ የመከፋፈል ፍልስፍና ለምን ምርኮኛ ሆኑ ብዬ ብጠይቃቸው ከድፍረት አይቆጠርብኝም፡፡ ምክንያቱም እንደ አቶ ቡልቻ ካለ አንጋፋ ምሁርና ታዛቢ ሽማግሌ ለኦሮሞው ከትግሬው ይልቅ አማራው በዘር፣ በሃይማኖት፣ በባህል ትስስር፣ ወዘተ. እንደሚቀርበው ይጠፋቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ የዶ/ር በያንን ወቅታዊ የእርምት መግለጫ ስለተከታተልኩ አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ዶ/ሮ መራራ ጉዲና ግን ግዴታው ነው፡፡ ለምን ቢባል ኦሮሞና አማራን ለመለየት የተዘጋጀው የወያኔ ወንፊት ሸዋ ላይ ሲደርስ ጥቅጥቅ ይልና ኦሮሞንና አማራን ለመለየትና ለመከፋፈል አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል ብዬ አምናለሁ፡፡ ወደድንም ጠላንም በአንድ ነገር መስማማት አለብን፡፡ አሁን ያለንበት ጊዜ የሥልጣኔና ወደፈት የመራመድ እንጂ የወያኔው ፈላስፋ መለስ ዜናዊ አጥልቆልን የሄደውን የመከፋፈልና የመለያየት ጥቡቆ አናወለወቅም ብለን የምንጃጃልበት ወቅት አይደለም፡፡ ወያኔ የራሱን አገር እያለማና ሕዝቡን እያበለፀገ ኦሮሞና አማራን ግን እንደ ጀዋር ዓይነት፣ አረቦች ወሰክ የሚሉት ዓይነት ካድሬ በማሰለፍ ለማጋጨት ሲሞክር ይታያል፡፡ ለማጠቃልል በመጀመሪያው አንቀጽ ላይ ነሳሁተን የስብሃት ነጋን አባባልና የትግራይ ህዝብን ዝምታ አሁንም እደግማለሁ፡፡ የአክሱም ስልጣኔ ተንቤንን፣ እነደርታንና አጋሜን አይመለከትም የሚል ከፋፋይ ፍልስፍና ቢያቀርብም የእነዚህ ሦስት አውራጃ ትግሬዎች ግን በአሁኑ ሰዓት ከሌላው ትግራይ ሕዝብ ጋር አብረን ተጠቃሚ ነን፣ ደግሞስ ይሄ የጃጀና የዞረበት ሽማግሌ የፈለገውን ቢያወራ ማን ይሰማዋል በማለት የስርዓቱ ተጠቃሚነታቸውን ቀጥለውበታል፡፡ ኦሮሞና አማራም ልክ እንደዚሁ ጀዋርም ሆነ ሌላ ከፋከፈይና ገንጣይ ወያኔ የሚያወራውን ቦታ ባለምስጠት ስለወደፊቱ ማሰብ አለባቸው፡፡ ተወደደም ተጠላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በኦሮሞና በአማራው እጅ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ፍቅር፣ ሰላምና ብልጽግና ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን።

ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?

$
0
0

(ግርማ ሞገስ)ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው…

ethiopia-school

 ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ (1886-1919) ሁሉ የቁጭት ጥያቄ ነበር። በጣት የሚቆጠረው የነገብረ ሕይወት ትውልድ የውጭ ትምህርት ቀስሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ባፄ ምኒልክ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ ለዘመናዊነት በር የተከፈተው ባፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን እንደነበር፣ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1942 ዓመተ ምህረት (እ.ኤ.አ. 1950) የአዲስ አበባ የተፈጥሮና የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ መከፈቱን፣ ኮሌጁ የተደራጀው በኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በንቃት ይሰሩ በነበሩ ካናዳውያን እየሱሳውያን (Jesuits) ሲሆን የተማሪዎቹ ቁጥር ከ100 በታች እንደነበር ክፍሉ ታደሰ (The Generation, p. 15-16) ያመለክታል። እሱም ቢሆን እጅግ ዘግይቶ የመጣ በውቅያኖስ ላይ ያረፈ ትንሽ ጠብታ ያህል ነበር። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

የሬሳው ስንብት (ነብዩ ሲራክ)

$
0
0

እጣ ፈንታ …. ዘመኑ በፈቀደው የአረብ ሃገር ስደትን በኮንትራት ስራ የሳውዲን ምድረ በዳ የባለ ጸጎች ሃገር የረገጠከው ራስክን ደግፈህ ፣ ወላጅ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ወገኖችህን ለመደገፍ ነበር ። በሳውዲ ቆይታህ በትዕግስት ስታልፍ ያስብከውን ሁሉ ባይሳካም ጋብቻ መስርተህ ሌላዋን የኮንትራት ሰራተኛ ስደተኛ እህትክን ባንድ አቅፈህ… ፣ ራስክን በሙያ አንጸህ የተረጋጋ ኑሮን በመኖርህ ላይ እንዳለህ ሳታስበው በውስጠ ደዌ በሽታ ተወጋህ ! ክፉውን ሁሉ የስደት ህይወት በትዕግስት ገፍተህ ደስተኛ ሆነህ ኑሮን ትገፋ እንደነበር አህትህና ባለቤትህ ቅሪት ገላህን ወደ ሃገር ለመሸኘት ለስንብት ስንጓዝ አጫውተውኛል። ፎቶህን አይቸ በህይወት ዘመንህ በአንድ አጋጣሚ አውቅህ እንደነበር ሳውቅ ደነገጥኩ ፣ ድንጋጤየን ዋጥኩት ! ነፍስህን ይማረው ወንደም አለምNebiyu Sirak

ስንብት …
ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት !

ከሬሳው ማስቀመጫ መስሪያ ቤት ሃላፊ ጋር ላፍታ ባደረግነው ቆይታ የሰማሁት አሳዛኝ ነባራዊ ሁኔታ ውስጤን አደማው ። ሬሳውን ወደ ምንቀበልበት የጓዳ በር ለየራሳችን ቆዛዝመን ደረስን: ( ታሞ ፣ እህት ሚስቱ አስታምመውት ፣ ማንነቱ ታውቆ እና ወደ ሃገር መላኪያ ገንዘብ ተገኝቶ ዛሬ ወደ ሃገር ለመሄድ ተዘጋጅቷል ፣ ከምሽቱ 9:45 … የብርቱ ወዳጀ አብሮ አደግ ከፈን ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ወጣ … በተዘጋጀው የእንጨት ሳጥን ሆኖ ወደ አንቡላንስ ከመሸኘቱ በፊት በስትሬቸር እየተገፋ መጣና ለስንበት ፊቱ በአንድ የፊሊፒን የሬሳው ክፍል ሰራተኛ ተገለጠ … ያ ዘንካታ አይኑን ጨፍኖ ታጋድሟል …አንጀንታቸው የሚላወሰውን እህት ፣ ሚስት፣ ጓደኞች እና ጎረቤቶች ሃዘናቸውን እንደፈለጉ ጮኸው በማይገልጹበት ግቢ የወንድማቸውን በድን ተሰናበቱት … በሬሳው ክፍል ሃላፊ ባጫወተኝ አሳዛኝ ታሪክ ተጽናንቸ የነበርኩት እኔም እህት የወንድሟን ፣ ሚስት የባሏን ግንባር እየሳሙ በታመቀ የሃዘን ስሜት ድምጻቸውን አርቀው እያነቡ ሲሰናበቱት ሳይ ብርክ ያዘኝ !

ሽኝት …

በእርግጥም እኒህኞቹ ወገኖችም ሆኖ ታሞ አስታመውት የሞተው ወንደም እድለኛ ነው! ነገ የሃገሩን አፈር ፣ ታሞ እያለ እናቱን ናፍቆ ሁለቴ ለመሄድ ተነስቶ በተመለሰበት አውሮፕላን ዛሬ በድኑ በውድ ዋጋ ተጭኖ ይደርሳል ! እናት እና ልጅ ተነፋፍቀው አልተገናኙም: ( እናም አልሰሜ እናት አለም ነገ ሬሳ ለመቀበል በጠዋት መርዶ ይጠብቃታል !

ህይወት እንዲህ ነው የሞተውን ነፍስ ይማር ! እናት እና መላ ቤተሰብ ጽናቱን ይስጣችሁ ሌላ ምን ይባል?


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ እና የኢትዮጵያ ምህዳር ጋዜጣ አዘጋጆች ለውሣኔ ተቀጠሩ

$
0
0

በህገመንግስቱ ላይ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ የህዝብን ሃሳብ በማናወጥ እና “ጨፍጫፊ” በማለት የመንግስትን መልካም ስሙን በማጥፋት የተከሰሰው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ በመከላከያ ማስረጃነት ያቀረበው የቢቢሲ ዶክመንተሪ ፊልም፣ የቢቢሲ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ሲል ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለውሣኔ ቀጥሯል…

ተከሳሹ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያዘጋጀው ነው በሚል በመከላከያ ማስረጃነት የቀረበው የድምጽ ምስል ዶክመንተሪ ፊልም በእርግጥም የቢቢሲ ስለመሆኑ ጥያቄ በማስነሳቱ ከጣቢያው ሃላፊዎች ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ቀደም ባለው ቀጠሮ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠው፡፡ ከትናንት በስቲያ በዋለው ችሎት የተከሳሽ ጠበቃ ለፍ/ቤት እንዳስረዱት፤ ማረጋገጫውን ለማግኘት ከቢቢሲ ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ጠቁመው ለዚህኛው ቀጠሮ ሊደርስላቸው ባለመቻሉ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሠጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ቀደም ሲል በአቃቤ ህግ የቀረበበትን ማስረጃ ይከላከሉልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮች ለፍ/ቤቱ ከማሰማቱም በተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ መከራከሩ ይታወሳል፡፡

ለፍ/ቤቱ ካቀረባቸው የመከላከያ የሰነድ ማስረጃዎች መካከልም 4 ገጽ ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ሪፖርት፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ “ኢትዮጵያን አመጽ አያሰጋትም” ሲሉ የሠጡት ቃለ ምልልስ፣ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት እንዲሁም ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ቢቢሲ በፎከስ ኦን አፍሪካ ያሠራጨውና ፍ/ቤቱ ማረጋገጫ የጠየቀበት ዘገባ ይገኙበታል፡፡ ተከሣሹ ባቀረባቸው የመከላከያ ማስረጃዎች ላይ አስተያየቱን የሰጠውን አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ የቀረቡት ማስረጃዎች ከክሱ ፍሬ ሃሳብ ጋር ግንኙት የላቸውም ብሎ የተከራከረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ሣይቀበለው ቀርቷል፡፡ አቃቤ ህግ በቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ላይ ያለውን አጠቃላይ አስተያየት በቀጣዩ ቀጠሮ ለማቅረብ ፍ/ቤቱን ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ፍ/ቤቱም የተከሳሽን የቢቢሲ ዘገባ ማረጋገጫ ለመቀበልና የአቃቤ ህግን አጠቃላይ የማስረጃ አስተያየት ሠምቶ ውሣኔ ለመስጠት ለየካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

በሌላ በኩል ሐዋሣ በሚገኘው የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት፤ የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ የ300ሺህ ብር የፍትሃ ብሔር ክስ ያቀረበባቸው የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ አሳታሚና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ደግነው እንዲሁም ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ወርቁ ባለፈው ረቡዕ ፍ/ቤት ቀርበው የቃል ክርክር ካደረጉ በኋላ፣ የፍ/ቤቱን ውሣኔ ለመስማት ለጥር 20 ቀን 2006 ተቀጥረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍ/ቤቱን ሂደት ለመከታተልና ስለዘገባው ማብራሪያ ለመስጠት ወደ ሃዋሣ በሄደበት ወቅት የትራፊክ አደጋ የደረሰበት ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ስለ አደጋው ፖሊስ አዲስ አበባ ድረስ መጥቶ ቃሉን የተቀበለ ሲሆን፤ እስካሁን ግን ክስ እንዳልተመሠረተ የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

አዲስ አድማስ


የባለሥልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ?

$
0
0

የሃብታቸው መጠን ይፋ የሚደረገው  ከስልጣን ሲወርዱ ይሆን? (ያመለጡን አሉ!) በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም ሊካተት ይገባል (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!) “Grand corruption” አለ የሚባለው ገንዘብ ሚኒስቴር ሲዘረፍ ነው እንዴ?    የእነቴሌ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት “ፅድቁ ቀርቶብኝ–” ያሰኛል!….
ኢትዮ- ቴሌኮም በየበዓሉ የሚልከው የ “እንኳን አደረሳችሁ” መልካም ምኞት አሁን አሁን “ሙስና” እየመሰለኝ መጥቷል፡፡(ግራንድ ኮራፕሽን ሳይሆን ሚጢጢዬ ሙስና!) ለነገሩ ቢመስለኝም እኮ አይፈረድብኝም፡፡ ለምን መሰላችሁ? ዓመቱን ሙሉ በብዙ የአገልግሎት አሰጣጦች ችግር ሲያማርረን ከርሞ — በዓል ሲደርስ እንደ ደህና አገልጋይ “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን ሊደልለን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? (“ደለለኝ — ደለለኝ” ነው ያለችው ድምፃዊቷ) ነፍሷን ይማረውና! እውነቴን እኮ ነው… ኔትዎርክ ሳይኖር፣ ኢንተርኔት ተቋርጦ፣ የቢሮና የቤት ስልክ ጠፍቶ… እንዴት ነው “እንኳን አደረሳችሁ” የሚለን? (ያውም ለእኛ አሻፈረኝ በሚለን ኔትዎርክ!) እኔ የምለው —- እኛና ቴሌ የምንተዋወቀው በስልክ አገልግሎት አይደለም እንዴ? (ከዚያ ውጭ የት ስንተዋወቅ ነው!) ከሁሉም የሚገርመኝ ደሞ ”ከመጪው ዘመን ጋር አገናኛችኋለሁ” የሚለው ፉከራው ነው፡፡ (“ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” አሉ!) እንኳንስ ከመጪው ዘመን… ከዛሬ ጋር እንኳን መች ተገናኘን! (ማን ነበር “አቅምን አውቆ ማደር ጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ ነው” ያለው?!) አሁንማ ከምንፈልገው ሰው ጋር መገናኘት አይደለም— ሂሳብ ለመሙላትም ኔትዎርክ ማግኘት መከራ ሆኗል (ቴሌኮም በነፃም እንኳን ገንዘብ አልቀበልም እያለን እኮ ነው!) እስካሁን የውሃና የመብራት መ/ቤቶች ለገና በዓል “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት አለማለታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምናልባት ሳልሰማቸው ብለውን ከሆነ ግን የእነሱንም ከ“ሙስና” ለይቼ አላየውም፡፡ ለምን ብትሉ… ገንዘብ የምንከፍልበትን ዋናውን አገልግሎት በቅጡ ሳናገኝ በየበዓሉ “እንኳን አደረሳችሁ” ማለት ለእኔ ተራ መደለያ ነው፡፡

(የመረረው ደንበኛ አታውቁም!?) ለነገሩ እዚህ አገር እኮ ቀድመው የሚናደዱት አገልግሎት ሰጪዎቹ እንጂ ደንበኞች አይደሉም፡፡ እኛ ደህና አገልግሎት የሚሰጠን አጣን ብለን ከመናደዳችን በፊት እነሱ ቀድመውን ይናደዱብናል (“ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ” አለች አስቱ!) እናላችሁ—የበዓላት ጊዜው ድለላ ቀርቶብን አንዴም ክፍያው ተቋርጦ የማያውቀውን የውሃና የመብራት አገልግሎት ሳይቆራረጥ፤ሳይጠፋ እናገኝ ዘንድ ለብዙ መቶኛ ጊዜ እንማጠናለን፡፡ (“Where is my beef?” አለ ፈረንጅ!) ምን እንደሚገርመኝ ታውቃላችሁ? ሦስቱም የመንግስት ተቋማት ለአገልግሎታቸው መቋረጥ የሚሰጡት ሰበብ ሁሌም ተመሳሳይ ነው – እንደሰነፍ ተማሪ እየተኮራረጁ፡፡ (አዲስ ሰበብ መፍጠር ሮኬት ሳይንስ ሆነ እንዴ?) እናላችሁ —- ውሃም መብራትም ኔትዎርክም የሚጠፉትና የሚቆራረጡት በ“ልማቱ” የተነሳ ነው፡፡ መብራት ለምን ይቋረጣል? ግድቦች እየተሰሩ ስለሆነ! ኔትዎርክ ለምን ይጠፋል? ኔትዎርክ እየተስፋፋ በመሆኑ! ውሃ ለምን ትጠፋለች? አዲስ የውሃ መስመር እየተዘረጋ ነዋ! ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ታገደ? ልማቱን ለማፋጠን! እኔ የምለው ግን —- ነባሩ አገልግሎት ሳይቋረጥ፣ እኛም ሳንማረር — ልማቱን ማስፋፋት እንዴት አቀበት ይሆንብናል? ሳስበው ግን አቀበት ሆኖብን አይመስለኝም፡፡ በልማት ሰበብ የስንፍናን ካባ ደርበን ለሽ ስላልን ነው፡፡

(ልማትና እንቅልፍ መቼም ተስማምተው አያውቁም!) አሁን የምፈራው ግን ምን መሰላችሁ? ለምን ሙስና ያለቅጥ ዓይን አወጣ ብለን ስንጠይቅ —“የፀረ- ሙስና ዘመቻው ስለተጧጧፈ” የሚል ምላሽ እንዳንሰማ ነው፡፡ (ነገሩ ሁሉ እኮ ምፀት ሆኗል!) እኔ የምላችሁ ግን… ለምንድነው ግን ጦቢያን እንዲህ የጠላናት? ብንጠላትማ ነው… በየመንግስት መ/ቤቱ ቱባ ቱባ ሹማምንቶች የአገር ሀብት ዘርፈው የተያዙት! ብንጠላትማ ነው— ከአገርና ከህዝብ ላይ እየዘረፍን የ15 ሚ.ብር ዶዘሮች ስንገዛ ቅንጣት ታህል የማይቆረቁረን! ብንጠላትማ ነው… ከመንግስትና ከባለሀብት ላይ እየነጠቅን በሚስትና በዘመዶቻችን ስም በየባንኩ ብዙ ሚሊዮን ብሮችና ዶላሮች የምናከማቸው! ብንጠላትማ ነው… በሙስና ገንዘብ መንትፈን በየቦታው ግራውንድ ፕላስ 2 ምናምን የምንገነባው! የጠላነው ግን ጦቢያን ብቻ እንዳይመስላችሁ… ራሳችንንም ነው!! ቤተሰቦቻችንንም ነው!! ልጆቻችንንም ጭምር ነው!! በሙስና ተይዘን የመገናኛ ብዙሃን ዜና መክፈቻ ስንሆን ቀድመው የሚያፍሩብን እኮ ቤተሰቦቻችን ናቸው፡፡ ልጆቻችን ናቸው፡፡ ወዳጆቻችን ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ የሾመን መንግሥት ነው። የመለመለን ፓርቲ ነው፡፡

የማታ ማታም የጠላናት ጦቢያ—- በተራዋ አንቅራ ትተፋናለች፡፡ “እኒህ ከእኔ ማህፀን አልወጡም!” ብላ ትክደናለች (“ሰው የዘራውን ያጭዳል” አለ ታላቁ መፅሐፍ!) አሁን አሁንማ ወዳጆቼ… በመዲናዋ ዙሪያ እንደ እንጉዳይ የፈሉትን አማላይ ህንፃዎች ስመለከት ልቤ ድንግጥ ማለት ጀምሯል (“ከሙስና ነፃ” የሚል ታፔላ ይለጠፍባቸው!) ምን ህንፃዎቹ ብቻ… በኢቴቪ ብቅ እያሉ ስለ ኪራይ ሰብሰባቢዎች ፀረ – ልማት እንቅስቃሴ የሚደሰኩሩንን የመንግስት ሹማምንቶችም መጠራጠር ከጀመርኩ እኮ ቆየሁ! (ከቫይረሱ ነፃ የሆነውና ያልሆነው አይለይማ!) እንዴ…አንዳንዶቹ እኮ “አገሩን የሚወድ ሰው ሙስና አይፈጽምም” ብለው በነገሩን ማግስት ነው “ቫይረሱ” እንዳለባቸው በኢቴቪ የዜና እወጃ የምንሰማው! (ዕድሜ ለፀረ – ሙስና ኮሚሽን!) እኔ የምለው ግን —- የፀረ ሙስና ኮሚሽን በአገራችን Grand corruption የለም የሚል ነገር የተናገረው በግምት ነው እንዴ? በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዳልሆነማ ራሱ እያሳየን እኮ ነው፡፡ (Grand corruption ቀላል አለ እንዴ!) የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቁንጮ ቁንጮ ሃላፊዎች ሲፈጽሙ የከረሙትን ሙስና ምን ልንለው ነው? (መቼም “ግራንድ ኮራፕሽን” ነው ለማለት የገንዘብ ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ መዘረፍ ያለበት አይመስለኝም!) እኔ የምለው ግን—-የመንግስት ባለስልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አያልቅም እንዴ? ለነገሩ የአንዳንዶቹን የሃብት መጠን ለመመዝገብ እኮ አመትም የሚበቃው አይመስልም፡፡

ቦቴው፣ ዶዘሩ፣ ቪላው፣ በየባንኩ ያለው ገንዘብ፣ የጦር መሳሪያው፣ (የጦር መሳሪያም እንደ ሃብት ይቆጠራል እንዴ?) እኔማ አንዱ ወዳጄ “የባለስልጣናት ሃብት ተመዝግቦ አልቋል” ሲለኝ — እንግዲያውስ ከስልጣን ሲወርዱ ይሆናል ይፋ የሚደረግልን ብዬ ጠረጠርኩ፡፡ (አንዳንዶቹ እኮ ሃብታቸው ሳይታወቅ እያመለጡን ነው!) በነገራችሁ ላይ የባለስልጣናቱን የሃብት ምዝገባ ጉዳይ ያነሳሁት ክፉ አስቤ አይደለም፡፡ ባለስልጣን ባየሁ ቁጥር “የሙስና ቫይረስ ይኖርበት ይሆን?” እያልኩ በመጠርጠር ሃጢያት እንዳልገባ ሰግቼ ነው፡፡ ከደሙ ንፁህ የሆኑ ባለስልጣናትስ ለምን ያለምግባራቸው ይጠርጠሩ? እናላችሁ —- የባለሥልጣናቱ የሃብት መጠን ቶሎ ተጠናቆ ይፋ ቢደረግ በጥርጣሬ ዓይን ከመተያየትና መረጃ ላይ ካልተመሰረተ ሃሜትና አሉባልታ እንድናለን፡፡ ሃሜት እኮ ሃጢያት ነው! መረጃ እንደ መንፈግ ግን አይሆንም!! የሃብት ምዝገባው ገና ካልተጠናቀቀ—- ይህችን ማዳበሪያ ሃሳብ ተቀበሉኝ (መዝጋቢውን አካል ማለቴ ነው!) ምን መሰላችሁ… በሃብት ምዝገባው ላይ የትዳር አጋርም መካተት አለበት የሚል ሃሳብ ስላለኝ ነው (መነጣጠቅ ተጀምሯላ!) በመጨረሻ አንድ የቤት ሥራ ጣል አድርጌ ልሰናበት፡፡ ይሄ የሥነ ዜጋ (ሲቪክ ኤጁኬሽን) ትምህርታችን እንደገና ይቀረፅ ይሆን እንዴ? (ሙስናው ቅጥ አጣ ብዬ እኮ ነው!)



የአሰብ ጉዳይ:- “ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም”

$
0
0

ከአብርሃ ደስታ   ገና በጠዋቱ “ዓሰብን ማስመለስ አለብን የምትለው እንዴት ነው? ወደ አላስፈላጊ ጦርነትና ደም ማፋሰስ ልታስገቡን ፈለጋቹ?” የሚል አስተያየት አዘል ጥያቄ አገኘሁ።
መጀመርያ ወደ ጭንቅላታችን መምጣት ያለበት ጉዳይ ‘የዓሰብ ወደብ የማነው?’ የሚል ነው… ዓሰብ የኢትዮጵያ ልአላዊ ግዛት (ንብረት) ስለመሆኑ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ (በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት) ማረጋገጫዎች አሉን። ዓሰብ የኛ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ምክንያት የለም። ማስረጃዎቹ (ማረጋገጫዎቹ) እዚሁ ፌስቡክ ላይ ባልፅፋቸውም በወደቡ ባለቤትነታችን ጥርጣሬ አይግባቹ። ስለዚህ ጥያቂያችን ፍትሐብሄር ነው።
ሁለተኛ ጉዳይ ዓሰብ የኛ ቢሆንም አሁን ያለው ግን በኤርትራ ቁጥጥር ስር ነው። ንብረት ሃብታችን ተነጥቀናል ማለት ነው። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘ዓሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል?’ የሚል ነው። መልሱ: ‘አዎ! ያስፈልጋታል’ ነው። የባህር በሯን የተነጠቀች ብቸኛዋ ትልቅ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። በአሁኑ ግዜ የባህር በር የአንድ ሀገር የህልውና በር ነው። የህልውና በሩ መዘጋት የለበትም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ንብረቷ (ወደቧ) የማስመለስ መብትም ታሪካዊ ግዴታም አለባት።
ሦስተኛ ‘እንዴት ነው ወደቡን ማስመለስ የምንችለው?’ የሚል ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ዓሰብ የኢትዮጵያ ቢሆንም በመሪዎቻችን ሐላፊነት የጎደለው ዉሳኔ ምክንያት ለኤርትራ ተሰጥቶ ይገኛል። ‘ወደባችን አለ አግባብ ለኤርትራ በመሰጠቱ ምክንያት ዓሰብን የማስመለስ ጉዳይ ከባድ ሊያደርገው ይችላል’ የሚል ሐሳብ ቢነሳ አግባብነት አለው። ጦርነትም ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ሊቀቅ ይችላል።
ግን ማትኮር ያለብን ስለ ጦርነት አይደለም፤ ስለ ዓሰብ ንብረትነት እንጂ። ዓሰብ የኛ መሆኑ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማረጋገጥ (ማሳመን) ይኖርብናል። በዓሰብ ጉዳይ ፅኑ አቋም ይዘን የኢትዮጵያም የኤርትራም ህዝብ እንዲገነዘበው መጣር አለብን። የዓለም ህዝብ ይሁን መንግስትታት ይደግፉናል። ምክንያቱም የባለቤትነት መከራከርያ ነጥባችን ጠንካራ ነው። የዓለም አቀፍ ሕግም ይደግፈናል። ዓሰብ የኢትዮጵያ ስለ መሆኑ የሚመሰክግሩ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችም አሉ።
አራተኛ ዓሰብ የኛ መሆኑ ቢናረጋግጥና ለዓለም መንግስታትና ማህበረሰብ ቢናሳውቅ እንኳ እንዴት ዓሰብን መመለስ እንችላለን? የኤርትራ መንግስትኮ ፍቃደኛ አይሆንም፣ ጦርነት ሊነሳ ይችላል … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች መነሳታቸው አይቀርም። ግን ችግር የለውም። ዓሰብ የኛ መሆኑ ካረጋገጥን ‘ንብረታችን መልስልን’ ብለን የመጠየቅ መብት አለን። የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ላይሆን ይችላል። ጦርነትም ሊከፍት ይችላል።
እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም።
ጦርነት ስለማንፈልግ ዓሰብን በሰለማዊ መንገድ የምንረከብበት መንገድ እናመቻቻለን። የኤርትራ መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ይችላል ብለን ግን ሃብት ንብረታችን ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም። ጦርነት ተፈርቶኮ የሀገር ግዛት አሳልፎ አይሰጥም። ጦርነት ተፈርቶኮ ልአላዊ ግዛትን ከማስከበር ወደኋላ አይባልም። በባድመ ጉዳይ ጦርነት ዉስጥ የገባነው ጦርነት ስለምንፈልግ ሳይሆን ልአላዊ ግዛታችን የማስከበር፣ ሀገራችን ከወራሪዎች የመከላከል ሀገራዊ ግዴታ ስላለብን ነው። ጦርነት ፈርተን እጃችንና እግራችን አጣጥፈን የባድመን መሬት ለሻዕቢያ ወራሪዎች አሳልፈን አልሰጠንም።
(በኋላ በፖለቲካዊ ዉሳኔ፣ በመሪዎቻችን ግድየለሽነት ምክንያት ባድመን መስዋእት ከፍለን በደም አስመልሰን ሲናበቃ በእስክርቢቶ ለወራሪዎች ተላልፎ ተሰጠ እንጂ። በጦርነት የተመለሰ ንብረት በድርድር ሲከሽፍ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ነው። የባድመ ጉዳይ …!)
ምንም እንኳ ጦርነት ባንፈልግም ሃብት ንብረታችን ግን አሳልፈን አንሰጥም። ጦርነት መስዋእት ይጠይቃል። ግን ለሀገራችን መስዋእት ብንከፍል ችግሩ ምንድነው? ለሀገራችንኮ መሞት አለብን። በምንክያት መስዋእት መሆን እንቻላለን። ደግሞኮ ኢህአዴጎች የዓሰብን ጉዳይ ስናነሳባቸው ‘ጦርነት ናፋቂዎች’ ይሉናል። እኔ ግን ለሀገር መስዋእት ብንከፍል ጉዳት የለውም ባይ ነኝ። እንኳንም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለሶማሊያም እየሞትን ነው። ይቅርታ ለሶማሊያም እየሞትን አይደለንም። ምክንያቱ ላልታወቀ ጉዳይ ነው በሶማሊያ እየሞትን ያለነው። ወታደሮቻችን በሀገረ ሶማሊያ እየሞቱ ያሉ ለምን ዓላማ ነው? ዜጎቻችን ዓላማው ለማይታወቅ ጉዳይ በሶማሊያ ከሚሞቱ ለሀገራችን ቢሞቱ አይሻልም ነበር? ኢህአዴጎች ‘ጦርነት ጥሩ አይደለም’ ይሉናል። ጦርነት ጥሩ አለመሆኑ ቢያውቁ ኑሮ ለምን በሶማሊያ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው አያስገቡም?
አዎ! ጦርነት ጥሩ አይደለም። በተቻለ መጠን ጦርነትን ማስወገድ አለብን። ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም።
አሜን!


አብዛኞቹ በሰሜን አሜሪካ የሰፈሩ በተለይም ከባሌ የመጡ የኦነግ ደጋፊዎች በተጭበረበረ ዶክመንት በመሆኑ ምርመራ እንዲካሄድ ስቴት ዲፓርትመንትን መጠቆም አለብን

$
0
0

ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም ከባሌና ከአርሲ ወደ ሰሜን አሜሪካ የገቡ ኦሮሞ ስደተኞች በተጭበረበር ዶክመንቶች እድሜን በመቀነስና እንዲሁም የውሸት ልጅ ወይም አባት በመሆን አጭበርብረው መግባታቸው ሚታወቅ ነው….

207914_1031208416394_3325_n

 

ይህንን fraud  ለስቴት ዲፓርትመንትና ለተገቢው የስቴት የመንግስት አካላቶች በማሳወቅ ይህንን Grand Immigration Fraud ማጋለጥ ተገቢ ብቻ ሳይሆን አማራጭ የሌው እርምጃ ይሆናል:: በቅርቡ ፔቴሽን ምናዘጋጅ ሲሆን ማግኘት ሚኖርባችሁን የስቴትና የመጋቨርመንት ተወካዮችን ስልኽና ኢሚል ኣስፈላጊውን መረጃ አናወጣለን

ለአሜሪካ ሚዲያዎች CNN, FOX, and MSNBC ጉዳዩን በቀጥታ በመጻፍ ይህ Grand immigration fraud ተገቢው ትኩረት እስኪያገኝ ድረስ መስራታችንን እንቀጥላለን:: ዝርዝሩን በቅርቡ ይዘን እንወጣለን:: (58)


አቶ ያረጋል አይሸሹምና ሌሎች ተከሳሾች ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተፈረደባቸው

$
0
0

0e84eca69664957576938d96db3fd6c5_XLየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹምና አብረዋቸው ተከሰው የነበሩ አምስት ተከሳሾች፣ ከስድስት እስከ 15 ዓመታት የሚደርስ ጽኑ እስራትና ከ20 ሺሕ ብር እስከ 60 ሺሕ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ጥር 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ተፈረደባቸው…

በመንግሥት ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሥልጣን ያላግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው፣ በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሥርቶባቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ፣ ኅዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥፋተኛ መባላቸው ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃና ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ በመስማት፣ አዲስ ከተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመርያ ቁጥር 2/2006 እና ከሌሎች የሕግ ድንጋጌዎችን አንፃር ፍርድ ቤቱ በመመርመር፣ አቶ ያረጋል አይሸሹም ሰባት ዓመት ጽኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ወስኗል፡፡ አቶ ያረጋል ጥፋተኛ የተባሉት በአንድ ክስ ሲሆን፣ ከሌሎቹ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መሥራታቸው በኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን  በመዘርዘር ነው፡፡ አቶ ያረጋል ክሱ በተመሠረተባቸው ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፌዴራል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነበሩ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩትና የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ወቅት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ የተባሉት አቶ ሀብታሙ ሂካ፣ በሦስት ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውንና ካቀረቡት የቅጣት ማቅለያዎች አራቱ ተይዘውላቸው፣ 15 ዓመታት ጽኑ እስራትና 45 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ጥፋተኛ የተባሉትም በሦስት ተደራራቢ የሆኑ ሥልጣንን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው፣ በኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች እንደተረጋገጠባቸው ፍርድ ቤቱ በውሳኔው በዝርዝር አስረድቷል፡፡

አቶ አሰፋ ገበየሁ የተባሉት ግለሰብ ደግሞ 15 ዓመታት ጽኑ እስራትና 60 ሺሕ ብር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ሲሆን፣ ለቅጣቱ መነሻ የሆነው የወንጀል ድርጊት ከሌሎቹ ተከሳሾች ጋር ግብረ አበር በመሆን በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆናቸው በሦስት ተደራራቢ ሥልጣን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በሰውና በሰነድ ሊያስረዳ በመቻሉ መሆኑን የቅጣት ውሳኔው ያብራራል፡፡

አቶ አሰፋ የኮንስትራክሽንና ዲዛይን አክሲዮን ማኅበር የዲዛይን ስቱዲዮ ክፍል ኃላፊና የጌዲዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ወኪል ሆነው በሚሠሩበት ወቅት፣ የወንጀል ድርጊቱን ሊፈጽሙ መቻላቸውን ውሳኔው ይጠቁማል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት አቶ ጌዲዮን ደመቀ የተባሉት ተከሳሽ 14 ዓመታት ጽኑ እስራትና 60 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በሦስት ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውንም በዝርዝር አስረድቷል፡፡ የጌዲዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅም ናቸው፡፡ የጋድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ አድገህና የኮለን ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መክብብ ሞገስ ደግሞ በአንድ ክስ ጥፋተኛ የተባሉ መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውሶ፣ በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆንና በዋና ወንጀል አድራጊነት ሥልጣንን ያላግባብ የመገልገል ሙስና ወንጀል መፈጸማቸው፣ በኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው ስድስት ዓመት ጽኑ እስራትና 25 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በአቶ ገዛኸኝ አድገህ ላይ የተወሰነው ቅጣት በልዩነት በአብላጫ ድምፅ፣ ማለትም አንድ ዳኛ የጥፋተኛነት ፍርድ በሚሰጥበት ወቅት ‹‹በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል›› በማለት ሲለዩ፣ ሁለት ዳኞች ‹‹ጥፋተኛ ናቸው›› በማለታቸው የቅጣት ውሳኔው መሰጠቱን መዝገቡ ያብራራል፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ አቶ ያረጋል አይሸሹምን ጨምሮ በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ የመሠረተ ቢሆንም፣ በሰባተኛነት ተካተው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የአቶ ሀብታሙ ሂካ ወንድም አቶ ኃይለ ገብርኤል ሂካ በብይን በነፃ ተሰናብተዋል፡፡

ፍርደኞቹን ለቅጣት ያበቃቸው የወንጀል ድርጊት ተፈጸመ የተባለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሠሩ በክልሉና በፌዴራል መንግሥት በጀት ተይዞላቸው እንደነበር ከተገለጹት የግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ፣ የጣና በለስ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትና የአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋም ጋር በተገናኘ ተፈጽሟል በተባለ የሙስና ወንጀል መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ፍርደኞቹ ክልሉ በመስከረም ወር 1992 ዓ.ም. ያወጣውን የግዥ መመርያ ቁጥር 1/92 አንቀጽ 9.1 እና 2 ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ፣ እንዲሁም ከ300 ሺሕ ብር በላይ የሚፈጸም የአገር ውስጥ ግዥ በክልሉ የፋይናንስ ቢሮ መፅደቅ እንደሚኖርበት በመመርያው አንቀጽ 22.3.ሐ እና 231 1ኛ ሰንጠረዥና 23.2 ሥር የተደነገገውን ግልጽ መርህ መተላለፋቸውን የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

ለፕሮጀክቶቹ የተመደበው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን አቶ ያረጋልና አቶ ሀብታሙ እያወቁ፣ በግልጽ ጨረታ የተሻሉ ተወዳዳሪዎችን በመጋበዝ ማጫረትና ማሠራት ሲገባቸው፣ የሦስቱንም ፕሮጀክቶች ጨረታ በሕገወጥ መንገድ ለጌዲዮን አማካሪ ድርጅት መስጠታቸውን፣ የግዥ ዘዴ ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ‹‹ሥራው አስቸኳይ ነው›› በማለት በውስን ጨረታ እንዲፈቀድ ማድረጋቸውን፣ ከመመርያ ውጪ የጨረታ ሰነድ ለኮንስትራክሽንና ዲዛይን አክሲዮን ማኅበርና ለጋድ ኮንስትራክሽን ድርጅት እንዲላክ ማድረጋቸውን፣ ሥራው በማጓተቱ 2,832,450 ብር ተጨማሪ ክፍያ መውጣቱንና ሁሉም ተከሳሾች በመንግሥት ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸውና በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡


‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት››

$
0
0

ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው፣  የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
zየምርጫ 97ን ቀውስ ተከትሎ ወደ እስር ቤት ከገቡት የቀድሞዎቹ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው፣ በቅርቡ የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ስለአዲሱ ሊቀመንበርነታቸው፣ ስለመጪው ዓመት ምርጫና ሌሎች ጉዳዮች ነአምን አሸናፊ አጋግሯቸዋል…
ሪፖርተር፡- አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን አመራሩ ላይ ወጣቶች አይታዩም በማለት የሚተቹ አሉ፡፡ የእርስዎን ዳግም ሊቀመንበር ሆኖ መመረጥንም እንደ ምሳሌ ያነሱታል፡፡ ለምንድነው ወጣቶች ወደ አመራር የማይመጡት?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ያለባቸው መራጮች ናቸው፡፡ መራጮችንና የአንድነት አባላትን መጠየቅ ነው፡፡ በመሠረቱ አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው፡፡ ባለፈው ሥራ አስፈጻሚም ሆነ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የወጣቱ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር፡፡ በጠቅላላ ጉባዔው ሰባ በመቶ አካባቢ ወጣት ነው፡፡ የተወዳደርኳቸው ሰዎችም ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ነገር መጠየቅ ያለባቸው አባላትና ጉባዔው ናቸው፡፡
መጠየቅ ያለበት እኔ ፍላጎት ኖሮኝ ወጣቶችን ወደታች ገፍቼ ድርጅታዊ ሥራ ሠርቼ ብመጣ ኖሮ ነበር፡፡ ወጣቶችን ወደታች ተጭነሃል ማለት ይቻል ነበር፡፡ ዋናው ማየት ያለብን ጠቅላላ ጉባዔውና አጠቃላይ ሒደቱ ዲሞክራሲያዊ ነበር ወይስ አልነበረም ነው፡፡ በእኔ ግምት አንድነት ፓርቲ ለዲሞክራሲያዊ አሠራር ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ፓርቲዎች የሚበልጠው ያለ አይመስለኝም፡፡ ለዚህም የምገልጸው በምክር ቤታችንም በሕገ ደንባችን መሠረት የምንሰበሰበው በሦስት ወር አንዴ ነበር፡፡ ምክር ቤቱ ግን በዓመት እስከ 20 ጊዜ ይሰበስባል፡፡ ምክንያቱም የጀመርነውን አጀንዳ በምናደርገው ሰፊ ውይይት መጨረስ አንችልም፡፡ አጀንዳ ጨርሰን አናውቅም፡፡ አራት አጀንዳዎች ቀርበው እንደሆን ሁለቱን ጨርሰን ሁለቱን ደግሞ ለሚቀጥለው ጊዜ እናስተላልፋለን፡፡ ይህ ደግሞ የዲሞክራሲያዊ ውይይት ነፀብራቅ ነው፡፡
እኔ እንዲያውም ቅስቀሳ አላደረግኩም፡፡ የእኔ ተወዳዳሪዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ወይም አይደለም? የሚለው ነው ጥያቄው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ነበር፡፡ ለምን ወጣቶች አልመጡም ለሚለው የእነሱ ምርጫ ነው፡፡ እኔ በአብዛኛው የተመረጥኩት በወጣቶች ነው፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊትም እንዳደረግኩት ወጣቶችን የማሳተፍ አመለካከትና ባህሪ አለኝ፡፡ እኔ አመራር በነበርኩበት ጊዜ በሕገ ደንቡ መሠረት በሥራ አስፈጻሚ 13 አባላት ነው የሚኖሩት፡፡ እኔ ግን ወጣቶች ወደፊት እንዲቆጠሩ ስድስት አባላት ድምፅ የመስጠት ሥልጣን ሳይኖራቸው አስገብቻለሁ፡፡ ደንቡ ስለማይፈቅድልኝ ነው እንጂ ባለድምፅ ሆነው መግባት ይችሉ ነበር፡፡ ደንቡ ግን አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ ድምፅ አልባ ከመሆናቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ የአመራር አባል ነበሩ፡፡
አቶ ግርማ ሰይፉም የዚያ አባል ነበሩ፡፡ ሌላው ወጣቱን ለዚህ ቦታ ማንም አልከለከለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ ሜካኒካል ይሆናል፣ ኮታ ይሆናል፡፡ ወጣቶች መምጣት አለባቸው፡፡ የኮታ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ የመብት ጉዳይ ነው እንጂ የሚሰጣቸው ስጦታ አይደለም፡፡ ስለዚህ በአንድነት ፓርቲ ለወጣቶችም ሜዳው ክፍት ነው፡፡ ነገ ጠዋት የላቀ ከመጣ ምክር ቤቱ በወጣት ሊተካ ይችላል፡፡ ከፖለቲካም አንፃር መታየት ያለበት ስብጥሩ ነው፡፡ ከወጣቶችም፣ ከጐልማሶችም፣ ከአዛውንትም ያ ስብጥር ነው መሆን ያለበት፡፡ ወጣትም ሆኖ ሽማግሌም ሆኖ የራሱ የሆነ ችግር አለበት፡፡ ያንን የሚያቻችለው መቀላቀሉ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በተቃዋሚውም ሆነ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉት የ60ዎቹ ትውልድ አባላት አመራርነት የሚያበቃውና ወጣቶች በሰፊው ወደ መሪነት የሚመጡት መቼ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- በእኔ በኩል በአመዛኙ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ፖለቲካ የሚለው አይሠራም፡፡ ባለፈው አላየነውም አሁንም አይታይም፡፡ የአንድነት ዕድሜ ስድስት ዓመት ነው፡፡ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ፕሬዚዳንቶችን ለውጧል፡፡ የመጀመሪያዋ ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች፡፡ የወጣቶች ተወካይ ነበረች፣ የ60ዎቹ አይደለችም፡፡ ከዚያ እርሷ ስትታሰር እኔ ተጠባባቂ ሆኜ ኃላፊነቱን ተረከብኩ፡፡ ከዚያ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሆነ፣ አሁን እኔ መጣሁ፡፡ ማንም ፓርቲ በስድስት ዓመት ውስጥ አራት ፕሬዚዳንት የቀየረ የለም፡፡ ይህ የሚያሳየው የአንድነትን ዲሞክራሲያዊነት ነው፡፡ በመሠረቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቃት ባለው ከ60ዎቹ በኋላ ባለው ትውልድ መተካት አለበት፡፡ ያ የእኔ እምነት ነው፡፡ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች መጪውን ትውልድ አብቅተው መተካት እንዳለባቸው እምነቴ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን አንድነትን እንደ ምሳሌ ከወሰድነው መጀመሪያ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወጣት መሪ ነበሩ፡፡ ከዚያ እሳቸው ሲታሰሩ እርስዎ መሪ ሆኑ፡፡ ቀጥሎ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አሁን ደግሞ ተመልሰው እርስዎ መጡ፡፡ በአንድነት ውስጥ ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ውጪ ያው የ60ዎቹ ትውልድ አባላት ስለሆናችሁ ከዚያ አንፃር ለማለት ፈልጌ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ትክክል ያልሆነ ምዘና ነው፡፡ ምንድነው የ60ዎቹ ፖለቲከኞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ቅድም እንዳልኩህ ስብጥሩን ነው ማየት ያለብን፡፡ ብርቱካን በነበረችበት ጊዜም ሆነ አሁን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች ጥቂት ናቸው፡፡ ምናልባት በጣት የሚቆጠሩ [እኔ፣ ነጋሶ፣ አስራት]፡፡ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩት አብላጫዎቹ ከ60ዎቹ በኋላ የመጡ ትውልዶች ናቸው፡፡ በአሁኑ ብሔራዊ ምክር ቤት ውስጥ ከ35 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉት 72 በመቶ ናቸው፡፡ የ60ዎቹ አሉበት፡፡ ነገር ግን በአብላጫው ወጣቶች ናቸው፡፡ በእኔ ካቢኔ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ያለነው ሁለት ሰዎች ነን፡፡ ከ15 ሰዎች አንድ ሰው የ60ዎቹ ሆኖ ላይ ስለተቀመጠ የ60ዎቹ ተፅዕኖ አለ ለሚባለው ምዘናው ትክክል አይመስለኝም፡፡ መታየት ያለበት ይዘቱ ነው፡፡ የ60ዎቹ ትውልድ አባላት እንዲያውም የት እንዳሉ ግራ ይገባኛል፡፡ አንዳንድ ቦታ መሪ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ የፓርቲው መዋቅር መፈተሽ ካለበት የ60ዎቹ የፖለቲካ ተሳፊዎች ወጥተው ዳር የቆሙ ይመስለኛል፡፡ ደግሞም የተፈጥሮ ሒደት ነው፣ የፖለቲካም ሒደት ነው፣ የታሪክም ሒደት ነው፡፡ መታየት ያለበት የግለሰቦች የ60ዎቹ ትውልድ መሆን ሳይሆን ስብጥሩ ውስጥ ስንት አሉ የሚለው ነው፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን እንደ አዲስ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው መጥተዋል፡፡ ለፓርቲው ምን አዲስ ነገር ይዘው መጡ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኛ ፓርቲያችንን የምንመራው በሥርዓት ነው፡፡ ፓርቲው በ2002 ዓ.ም. የስትራቴጂ ዶክመንቱንና የአምስት ዓመት ዕቅዱን በመጽሐፍ መልክ አውጥቶታል፡፡ የአነድነት ፓርቲ መሠረታዊ ራዕይና ግብ በዚያ ውስጥ ነው የሚታየው፡፡ እዚያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ነው ሁላችንም በቀጣይነት እየገነባን የምንሄደው፡፡ ነገር ግን በ2002 እና በ2003 ዓ.ም. ያወጣነው የስትራቴጂ ግንባታ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መዛመድ አለበት፣ መቀነባበር አለበት፡፡ ስለዚህ በዚያ መንገድ አንዳንድ ለየት ያሉ ሙከራዎች አካሂዳለሁ፡፡
የመጀመሪያው ሙከራዬ አንድነት ምናልባት ካሉት ፓርቲዎች በጉልህ ጠንክሮ የሚታይና መዋቅሩ ታች ድረስ የወረደ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲያው እንደ ሌላው ጉልበት ወይም አቅም አለን ባንልም በቂ የመንቀሳቀስ ችሎታ አለን የሚል ግምት አለኝ፡፡
ይህንን የአመራር መርህ ከአንድነት አቅምና ሕዝባዊ ገጽታ አንፃር የተለየ (Rebranding) እንዲሆን አደርጋለሁ፡፡ ለምሳሌ አንዱ ያደረግኩት ሥራ አስፈጻሚውን በአብዛኛው ወጣትና አዲስ ነው ያደረግኩት፡፡ በትምህርታቸው ብቁ የሆኑ ናቸው፡፡ በትምህርት ብትሄድ አሁን ከ15 ሰዎች ስድስቱ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሰባቱ የመጀመርያ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ ዲፕሎማ አላቸው፡፡ አሁን ይኼ አዲስ ምልክት (New Branding) ነው፡፡ ሁለተኛ እነዚህን ሰዎች ስመድብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ችሎታ እንዲኖራቸው አንዱ መሥፈርት ነበር፡፡ አሁን ዘመኑ ወደዚያው እያመራ ነው፡፡ ስለዚህ በኢንፎርሜሽን ግንኙነታችን ከውጭው መረጃ እኩል አንድነት መራመድ አለበት፡፡
ሌላው ትኩረት የምሰጠው ወጣቶችን የማብቃት ሥራ ነው፡፡ ወጣቶች በቅተው ፓርቲውን እንዲመሩ አደርጋለሁ፡፡ አሁን እኔ እዚህ ሆኜ ወጣቶችን ነው ወደፊት እንዲሮጡ የማደርገው፡፡ ይህን ካደረግኩ በኋላ በእኔ እምነት ክርክርም መካሄድ አለበት፡፡ እስካሁን የተካሄደው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ውጤት አላስገኘም፡፡ ይኼ ምንም የምንክደው አይደለምና ይህ ለምንድን ነው የሚለው ብዙ ጊዜ ይረብሸኛል፡፡ ወይ ማቆም አለብን ወይ መሥራት አለብን፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተበጣጠሱ ዘጠና ፓርቲዎች አሉ፡፡ ከዘጠናዎቹ ደግሞ ጉልህ የሆኑት አሥር አይሆኑም፡፡ አሥሩም አብረው መሥራት አልቻሉም፡፡ በጥምረትም በግንባርም አልተቻለም፡፡ ለምንድን ነው? ለአሥሩም ቢሆን አሥር መሪዎች አሉ፣ አሥር ፕሮግራሞች አሉ፡፡ አሥሩም እንግዲህ አሥር መሪ ኖሮዋቸው ፖለቲካ ይመራሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ በብሔራዊ ምክር ቤትና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስገኛለሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡
በእኔ እምነት እንግዲህ አንድነት ፓርቲ ግንባርና ጥምረት ውስጥ አይገባም፡፡ ወደ ውህደት አንድ አመራር አንድ ፕሮግራም ወዳለው እንቅስቃሴ እንገባለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ የእኔ ሐሳብ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ስብሰባ ላይ ፈንጥቄያለሁ፡፡ ይህ መሆን አለበት፡፡ የተጀመሩት ውህደቶች በሚቀጥሉት ሦስት ወራት  ማለቅ አለባቸው ብሎ ጠቅላላ ጉባዔው ወስኗል፡፡ ወይ እንዋሀዳለን ወይ እንለያያለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ አንድ የማየው እስከ 2007 ዓ.ም. ወይም በዚህ ዓመት ለእኔ የውህደት ዓመት ነው ብዬ የምገምተው፡፡ ወይ እንዋሀዳለን አለበለዚያ በሰላም ተለያይተን ሁላችንም ጉልበታችንን በየአካባቢው በትብብር እናጠናክር የሚል አመለካከት አለኝ፡፡
ይህን ካደረግኩ በኋላ ከኢሕአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) እንዲኖረን እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት፡፡ ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያያቸው እንደ ጠላት ከዚያም አልፎ እንደ ሽብርተኛ ነው፡፡ ይኼንን ነገር ለሚያስብ ሰው እኮ በጣም ነው የሚያስደነግጠው፡፡ በእኛም በኩል ኢሕአዴግን የምናየው እንደ አውሬ ነው፡፡ ምናልባት የሠራውን ሥራ ሁሉ ዋጋ (Credit) ያለመስጠት አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖለቲካችን ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖአል፡፡ ያ መቆም አለበት፡፡ ትልቁ ኳስ ያለው ኢሕአዴግ ዘንድ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ወደፊት በማደርገው እንቅስቃሴ ገንቢ ግንኙነት አድርገን ያለውን የፖለቲካ ምኅዳር ለሁላችንም እኩል ማድረግ አለበት፡፡ ኢቴቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ለምንድነው የኢሕአዴግ ብቻ የሚሆነው? መብት እኮ አለን፡፡ ለኢቴቪ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ የጻፍነው ምንድነው የኢሕአዴግን ኮንፈረንስ ከባህር ዳርና የኢሕአዴግን ብሔራዊ ምክር ቤት በቀጥታ ስታስተላለፉ ነበር፡፡ የእኛን ግን አልዘገቡም፡፡ ለኢሕአዴግ 99 በመቶ ሰጥተው ለእኛ ግን አንድ በመቶ እንኳን አይሰጡንም፡፡ ይኼ ሁሉ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳየው የኢሕአዴግን ድክመትና ስህተት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ለብዙ ፓርቲዎች የእንዋሀድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም እንደታየው ብዙ ውህደቶች ምርጫ ሲደርስ ከመሰባሰብ በዘለለ ብዙም ሲገፉበት አይስተዋልም፡፡ የ97ቱን ቅንጅት ማስታወስ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን እርስዎ የሚያቀርቡት ሐሳብ በምን ይለያል? ከዚህ ቀደም ተሞክረው እንደከሰሙት እንደማይሆንስ ማረጋገጫው ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የቅንጅት ራሱን የቻለ ጉዳይ አለው፡፡ ቅንጅት አልተዋሀደም ነበር፡፡ ለዚህም ነው ቅንጅት ግንባር ደረጃ አልደረሰም የሚባለው፡፡ ለቅንጅት ከፍተኛውን ድቀት ያስከተሉት የኢሕአዴግና የቅንጅት መሪዎች ናቸው፡፡ በወቅቱ ኢሕአዴግ ያልጠበቀው የፖለቲካ አድማስ ነው የመጣበት፤ በ97 ምርጫ አልጠበቀውም ነበር፡፡ አራቱ ፓርቲዎች ማለትም መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ቀስተ ደመናና ኢዴሊ ሆነው ቅንጅት የተመሠረተው ኅዳር ላይ ነበር፡፡ ኅዳር ላይ ተመሥርተን ግንቦት ላይ ነው ከፍተኛ ዕርምጃ ያሳየነው፡፡ ያ ሁኔታ ኢሕአዴግ ያለውን ግምት በጣም ነው ያዛባው፡፡ ኢሕአዴግ አቅም አይፈጥሩም የሚል ግምት ነበረው፡፡ ገና ስንፈጠር በምርጫው አካባቢ አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠርን፡፡ የምርጫው ዕለት ምሽት በአጠቃላይ የምርጫው ሒደት ተናጋ፡፡ በዚያ ምክንያት ቅንጅት ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ገባ፡፡ ኢሕአዴግ ትኩረት አደረገብን፡፡
በዚያ ምክንያት እኛም ወደ እስር ቤት ገብተን ከዚያ ደግሞ ወጣን፡፡ ያው ነገሩ ትክክል ስላልነበር መውጣት እንደነበረብን እኔ አምናለሁ፡፡ ከወጣን በኋላ ደግሞ እኛ አንድ መሆን አልቻልንም፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ብሶት ተፈጠረ፡፡ እንደገና ቅንጅትን ለአቶ አየለ ጫሚሶ ሰጡት፡፡ በዚያ በዚያ በመካከላችን ችግሩን በሰከነ ሁኔታ ለማራመድ አልቻልንም፡፡ በዚህ በኩል የራሱ የኢሕአዴግም የእኛም ድክመት ነበር፡፡ ከዚያ በፊትም በተፈጠሩት ስብስቦች እንደዚሁ የመሪዎች ብዛት ነው ችግሩ፡፡ አሁን እኔ የምለው ውህደት ከሆነ አንድ መሪ ሊኖር ይችላል፡፡ ውህደቱም መፈጸም ያለበት በዲሞክራሲያዊ መርሆዎች መሆን አለበት፡፡ ውህደት ላይ ዲሞክራሲያዊ ባህል መፍጠር አለብን፡፡ አመራር አንድ መሆን አለበት፡፡ ሕግ፣ ሥነ ሥርዓትና ደንቡ መታየት አለበት፡፡ እናም ዲሲፕሊን ሊኖረን ይገባል፡፡ የባህሪ ለውጥም ያስፈልገናል፡፡ ከዚህ አንፃር አንደኛ እኛ አመራሮች የባህሪ ለውጥ ያስፈልገናል፡፡ ያ እስከሆነ ድረስ እኔ ውህደት ይወድቃል ብዬ አላስብም፡፡ አልተሞከረም፡፡ በተጨባጭ ብሔራዊ ዕይታ ያለው ውህደት እኮ እስካሁን አልተካሄደም፡፡
ሪፖርተር፡- ከዚህ ከውህደቱ ጋር በተያያዘ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይስ እንዴት ነው የሚታየው? ብሔራዊ የሆነ ፓርቲ ይኖራል፤ ኅብረ ብሔራዊ የሆኑ ፓርቲዎችም ይኖራሉ፡፡ ይህስ ለውህደቱ እንቅፋት አይሆንም?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኔ ሁላችንም ወደ ብሔራዊ ምክክር መምጣት አለብን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለምሳሌ ብሔር ተኮር የሆነ ፓርቲ ከእኛ ጋር ሲዋሀድ ብሔራዊ ቅርፅ መያዝ አለበት፡፡ አለበለዚያ ብሔር ተኮርና ኅብረ ብሔር ሊዋሀዱ አይችሉም፡፡ ምንድነው ጠቃሚው ነገር? ዲሞክራሲ እስከሆነ ድረስ ለምሳሌ የእኛ ፕሮግራም የግለሰብንም የቡድንንም መብት ያከብራል፡፡ የብሔረሰብ ጉዳይ ከሆነ የቡድን ጉዳይ ነው፡፡ ያ እስከተጠበቀ ድረስ ማንኛውም የብሔር ፓርቲ እኛን ይቀላቀላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ያ ነው ጠቃሚው ነገር፡፡ የፕሮግራሙ ዕይታ ብሔር ተኮር የሆኑትን ፓርቲዎች ፍላጐት ማሟላት አለበት፡፡ የብሔረሰቡ ቋንቋ፣ የብሔረሰቡ የመወሰን መብትና ባህል ማሟላት አለብን፡፡ ይኼ የኢትዮጵያ ነፀብራቅ ነው፡፡ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች የምንልበት ጉዳይ አይደለም፡፡ እኩልነት እስካለ ድረስ የብሔረሰብ ጉዳይ አይነሳም ባይ ነኝ፡፡ ፍትሕ፣ እኩልነት፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እስካሉ ድረስ ችግር ያለ አይመስለኝም፡፡
ሪፖርተር፡- አንድነት አሳካዋለሁ ወይም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አመጣዋለሁ የሚለው የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የእኛ ሊበራል ዲሞክራሲ ነው፡፡ ሊበራል ዲሞክራሲ ሆኖ የቡድንና የግለሰብ መብትን አንድ ላይ እናከብራለን፡፡
ሪፖርተር፡- በሊበራል ዲሞክራሲ የቡድንም የግልም መብት ይከበራል ብለዋል፡፡ ነገር ግን የፍላጐት መጋጨት አይኖርም? በቡድን መብትና በግለሰቦች መብት መካከል ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነው የሚወሰነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንት ሰዎች ናቸው እንደዚህ የሚሉት? ሊኖርም ይችላል፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አሥር ሰዎች ሁለቱን አባረው ማካሄድ አይችሉም የሚል ይኖራል፡፡ 90 በመቶ ከደገፈው የ90 በመቶ ይሆናል ለሚለው የዲሞክራሲ ውሳኔ ነው የሚጠይቀው፡፡ እኛም ተወያይተንበታልና የሚወሰነው በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄድ አገር አቀፍ ምርጫ አለ፡፡ አንድነት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በምርጫው ለመሳተፍና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ምን ምን ሥራዎችን እየሠራ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- አንደኛ የራሳችንን አቅም እየገነባን ነው፡፡ ከጠቅላላ ጉባዔያችን ዕይታ አግኝተናል፡፡ በዚያ ዕይታ ለምሳሌ የውህደቱ አንዱ ዓላማ በምርጫ የማሸነፍ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድነት ብቻውን ከሚሮጥ ሦስትና አራት ፓርቲ ሆነን ልክ እንደ ቅንጅት ብንሮጥ የተሻለ ውጤት እናገኛለን በማለት፣ በውህደቱ ለምርጫው አንድ የጐለበተ አቅም ለመፍጠር የምናደርገው ስትራቴጂ ነው፡፡ ሁለተኛው ፕሮግራማችንንና ርዕዮተ ዓለማችንን ልክ እንደ ሚሊዮኖች ንቅናቄ ወደታች እናወርደዋለን፡፡ አንድ የሕዝብን ዕይታ የሚስብ ከምርጫ 2007 ጋር የሚገናኝ ፕሮግራም እናወጣለን፡፡ ሕዝብን ለማንቀሳቀስ ከዚህ በተጨማሪ አንድነት የዲሞክራሲ ምርጫ ፓርቲ ነው፡፡ ለማንኛውም ሁልጊዜ ለምርጫ ይዘጋጃል፡፡ አሁን ስትራቴጂያችንን ከልሰን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር አማራጭ ፖሊሲዎችን እንቀርፃለን፡፡ ከአማራጭ ፖሊሲዎች በመነሳት የምርጫ ማኒፌስቶ እናዘጋጃለን፡፡ በእኔ ዕይታ እስከ ሰኔ ድረስ ካለፈም እስከ ነሐሴ ድረስ አንዱና ትልቁ ሥራችን ይህንን የምርጫ ፖሊሲና ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ነው፡፡ ከዚያ ብቁ የሆኑ ዕጩዎችን ከካቢኔያችን ውስጥ እንመለምላለን፡፡ ከየቦታው ብቁ የሆኑ ታዛቢዎችንም እንመርጣለን፡፡ ይህ ሒደት ነው፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባ እናካሂዳለን፡፡ እንደዚሁም ሕዝባዊ ንቅናቄ ይኖረናል፡፡ እየሄድን ራሳችንን ወደ ሕዝብ የምናወርድበት፡፡ ይህን ሁሉ ለማድረግ ግን የምርጫ ፓርቲ ብንሆንም ምርጫ ውስጥ ጥልቅ ብለን አንገባም፡፡ ሜዳው ለሁላችን እኩል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ስለዚህ ከላይ እንዳልኩት ለዚህ ነው ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) ከገዥው ፓርቲ ጋር የምናደርገው፡፡ ይኼ ሜዳ ለሁላችንም እኩል እንዲሆን ነው የምንፈልገው፡፡ ኢትዮጵያ የጋራችን ነች፡፡ ኢሕአዴግ አንድ ፓርቲ ነው፡፡ እኛም አንድ ፓርቲ ነን፡፡
የምርጫው ሕግ በሕገ መንግሥቱና በምርጫ ቦርድ ሕግ መሠረት መካሄድ ስላለበት ያንን እንጠይቃለን፡፡ ምርጫ ቦርድ የኢሕአዴግ ከሆነ፣ ሚዲያው የኢሕአዴግ ከሆነ፣ የፍትሕ አካላቱ የኢሕአዴግ ከሆኑ እኛ ያን ጊዜ የምንወስነው ውሳኔ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከትዝብትም ጭምር እስካሁን ያሉት ተቋማት ለእኔ ዲሞክራሲያዊ አልነበሩም፡፡ የ2002 ምርጫ በጣም ያዘንኩበት ምርጫ ነበር፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን 99.6 በመቶ የሚያገኝ ፓርቲ የለም፡፡ በዓለም ላይ ዲሞክራሲያዊ በሆነና ውድድሩ በእኩል ሜዳ ላይ ተካሂዶ በእዚህ ውጤት ማሸነፍ አይቻልም፡፡ በዓለም ዙሪያ በአብዛኛው መንግሥት በቅንጅት እየተፈጠረ ነው፡፡ እንግሊዝን ውሰድ የኮንሰርቫቲቭና የሌበር ፓርቲ ቅንጅት ነው፡፡ ጀርመን፣ ጣሊያንና ኖርዌይም እንዲሁ ቅንጅት ነው፡፡ ምክንያቱ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ውድድሩ ነፃ ነው፡፡ እናም ስለዚህ 99.6 በመቶ በጭራሽ ሊሆን አይችልም፡፡ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ያለ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና የኅብረተሰብ ክፍል ባህሪ ባለበት አገር ይኼ አይቻልም፡፡ ይኼ ነገር መለወጥ አለበት፡፡ እናም ለምርጫ እንዘጋጃለን፡፡ ነገር ግን ሜዳው ሁላችንንም እኩል ማስተናገድ አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- የመጫወቻ ሜዳው ለሁላችሁም እኩል መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ትችላላችሁ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ለምሳሌ በምርጫ 97 ሚዲያው ትንሽ ወደ ኢሕአዴግም ቢያደላ ተከፍቶ ነበር፡፡ እንዲያውም የእነሱ ሜዳ ከፍ የእኛ ሜዳ ዝቅ ቢልም፣ ነገር ግን የመወዳደርያ ቦታ ነበረው፡፡ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ክርክሮች ለሕዝብ የወጡት በ97 ምርጫ ነበር፡፡ በ2002 ምርጫ ሚዲያው ታፍኖ ነበር፡፡ ሚዲያው የሕዝብ ጥያቄ አላስተናገደም፡፡ ዝም ብሎ ለይስሙላ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተሂዶ አንዳንድ ነገሮች መነጋገራችንን ሕዝብ ሊሰማው ይችላል፡፡ ነገር ግን በሆነ እጅ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነበር፡፡ ያ መሆን የለበትም፡፡ እናም ትልቁ ምሳሌ የ97 ምርጫ የሚዲያ ጉዳይ ነበር፡፡ ሚዲያው ያን ጊዜ ተከፍቶ ነበር፡፡ በእኩልነትም ባይካሄድም ያን ጊዜ እንደ እኩል ነው የወሰድነው፡፡ እንደዚያ መሆን አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ አንድነት የፀረ ሽብር ሕጉ ይሰረዝ የሚል አቋም ይዞ እየተከራከረ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በመላው ዓለም ሽብርተኝነት ትልቅ ሥጋት ሆኗል፡፡ በእኛ አገር የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አጠቃቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማሰኘት ነው የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት እንደ ፓርቲ አማራጭ የፀረ ሽብር ሕግ አለው ወይ ይሰረዝ ሲል ምን ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- መጀመርያ ሽብርተኝነትን መዋጋት የኢሕአዴግ ብቻ አይደለም፡፡ የማንኛውም ዜጋ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይኼ ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴው አስከፊ፣ ከሰው ልጅ ባህሪ በተለየ የሰው ልጅን መንፈስ የሚሰብር፣ የሰው ልጅነትን የሚቀንስ ነው፡፡ አንድነትም ሆነ እኔ እንደ አንድነት አመራር እንደዚሁም እንደ ዜጋም እንዋጋለን፡፡ የእኛ ችግር የፖለቲካ መሣሪያ አይሁን ነው፡፡ የአንድነት አባላትና እኔ ከኢሕአዴግና ከገዥው ፓርቲ በምንም መልኩ አናንስም፡፡ ይህን ችግር ለመዋጋት፡፡ ይኼ የዜግነት ግዴታዬ ነው፡፡ ማንም ቢሆን ወገኑ እንደዚያ ሲጠፋበት ካልተዋጋ ከሰውነትም ከሰብዕናም መውጣት አለበት፡፡ ነገር ግን የእኛ አጽንኦት የፀረ ሽብር፣ የፕሬስና የመያዶች ሕግ የፖለቲካ መሣሪያ መሆን የለባቸውም ነው፡፡ የፖለቲካ መሣርያ ከሆኑ መሰረዝ አለባቸው ነው፡፡ የሕዝብ ተሳትፎ ያለበት ይሁን ነው፡፡ የሁላችንም የጋራ ሥጋት ነው፡፡ ሁላችንም መሳተፍ አለብን፡፡ የፀረ ሽብር አዋጅ ሲወጣ እኛ አልተሳተፍንበትም፡፡ ፓርላማውም እንደሰማሁት በጥልቀት አልተሳተፈበትም፡፡ ይህ አዋጅ የሕዝቡ አዋጅ መሆን አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ማንም ከማንም ያነሰ የለም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ስትጠቃ እኔ የመጀመርያው ተዋጊ ነኝ፡፡
ሪፖርተር፡- የፓርቲያችሁ ድረ ገጽ አብዛኛውን ጊዜ ቶሎ ቶሎ መረጃዎች ሲጫኑበት አይታዩም፡፡ በአብዛኛው የቆዩ መረጃዎች ናቸው ያሉበት፡፡ የእርስዎን ሊቀመንበር ሆኖ መመረጥ እንኳን በትኩሱ ይፋ አላደረገም፡፡ አሁን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት የመረጃ ዘዴዎችን መጠቀም ወደ ሕዝብ ዘንድ ለመድረስ ዓይነተኛ ሚና ስለሚኖረው ድረ ገጻችሁ ለምንድነው መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ ለሕዝብ የማያደርሰው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ያለፉትን መውቀስ አይሁንብኝና ድክመታችን ነው፡፡ እኔም አይቼዋለሁ፡፡ ዘገምተኛ ነው፡፡ አሁን ‹‹አክቲቭ›› እናደርገዋለን፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግረንበታል፡፡ ጠንካራ የሆነ የሚዲያ ግሩፕ አለን፡፡ ነገር ግን እነርሱ ያንን ረስተው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አንስቼ ተነጋግረናል፡፡ የተነጋገርነውም አንደኛ ድረ ገጾችን ዘገምተኛና የነቃ አይደለም፡፡ ሰዎችን የሚስብ ባለመሆኑ ይህ ድረ ገጽ በሥነ ሥርዓት አሁን ለኢትዮጵያውያንም፣ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡም አንድነት የሚሠራውን በየቀኑ ማንፀባረቅ አለበት፡፡ ድረ ገጹ ወቅታዊነት ይጐድለዋል፡፡ ሁኔታዎችን ብልጭ የሚያደርገው ጊዜው ካለፈ በኋላ ነው፡፡ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት እንዲስተካከል የሕዝብ ግንኙነት ይሠራዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ላለፉት ዓመታት ፖለቲካው ላይ ብዙም አይታዩም ነበር፡፡ አሁን ደግሞ እንደገና ተመረጡ ሲባል እሳቸው ፖለቲካ አልተውም እንዴ የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ እርስዎ ከፖለቲካ ወጥተው ነበር?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- አይደለም፡፡ አንደኛ ለአንድ ዓመት ያህል ተራ አባል ነበርኩ፡፡ ተራ አባል መሆንም አንዳንድ ጊዜ ወደ ላይም ወደታችም ያሳይሃል፡፡ ከዚያ ወደ ምክር ቤት አስገቡኝ፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤት ከገባሁ አንድ ዓመቴ ነው፡፡ እዚያ በንቃት እሳተፍ ነበር፡፡ ነገር ግን ራሴን ከሚዲያ አግልዬ ነበር፡፡ እንዲሁ ዝም ብዬ የምናገረው ነገር የለኝም ብዬ ራሴን ከሚዲያው አውጥቼ ነበር፡፡ በመሠረቱ ወደዚህ መምጣትም መቶ በመቶ የእኔ ፍላጐት አልነበረም፡፡ የፓርቲ አባላት ፍላጐት ነው፡፡ የፓርቲ አባላት ፍላጐት በመሆኑ ምክር ቤትም እንደነበርኩ ይኼ ሐሳብ ተንሸራሽሮአል፡፡ ከዚያ በኋላ ያልጨረስከው ነገር ስላለ ግባና እስቲ ጨርሰው የሚል ነው፡፡ እኔ እንግዲህ ያመጣኝ ምርጫው ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ፖለቲካ በቃኝ ብለው ነበር?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ፖለቲካ በቃኝ አላልኩም፡፡ የፖለቲካ አመራርነት ግን ይበቃኛል ብዬ ነበር፡፡ ከፖለቲካ አልወጣሁም ነገር ግን ከፖለቲካ አመራርነት ወጥቼ ነበር፡፡ ይህንን እኔ የማምንበት ነው፡፡ ሌላ ለምን አናይም? አንዳንድ ጊዜ ጥላ አጥልተን መኖሩንም እኔ አልፈልገውም፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች ጥላ ሁነው እነርሱ ብቻ ተሰይመው ታች ያለውን አጥልተውበት፣ ታች ያለው ዝም ብሏል፡፡ እንደዚያ መሆንም አልፈልግም፡፡ ያንን ጥላዬን ከአመራርነት አውጥቼ ልጆቹ ወደ ፀሐይ ወጣ ይበሉ ብዬ ነበር፡፡


ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል

$
0
0

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣…

(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

guta dinqa

 ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በተለያዩ አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጸመው ጥቃትና በደል፣ አለሁላችሁ የሚል መንግሥት በሌለበት ጊዜ —- ዛሬ ታሪካዊትዋ ኢትዮጵያ፣ ራሳቸውን የሚያከብሩና ኩራት ራታችን የሚሉት ኢትዮጵያውያን አልቀው ለሆድ በየሰው አገር መሰደድ ባህል በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ውርደት ደጋግሞ የነፍሱን ኡኡታ ባሰማበት ጊዜ በድንገት አንገታችንን ቀና አድርጎ ኩራታችንን ሊያስጎነጨን የሞከረ ሰው ተገኘ! ኢትዮጵያ ሁሌም የተአምር አገር ነች።

Capitain_Guta_Dinka

ሻምበል ጉታ ዲንቃ

በታላቁ ሰው በኔልሰን ማንዴላ እረፍት ምክንያት አንድ ተደብቆ የኖረ ክቡር ኢትዮጵያዊ ብቅ አለ፤ ማንዴላ ለሥልጠና በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ ምናልባትም እንግሊዞች ማንዴላን ሊያስገድሉ ከጠባቂዎቹ አንዱ የነበረውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ዓላማቸውን ለመፈጸም አቅደው ነበር፤ ወታደሩ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ሀሳቡን ለውጦ ገንዘቡን ለአለቃው ሰጠ፤ ማንዴላ ከሞት ተረፈ፤ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ራሱንና አገሩን የሚያስከብር ሥራ ሲሠራ የሚኮሰኩሳቸው ባለሥልጣኖች ለእነሱ የማይተላለፍ ክብር በመሆኑ ተዳፍኖ እንዲኖር አደረጉት፤ እነሱ ሞተው ወይም ተሰድደው ሲያልቁ የተዳፈነው ምሥጢር ብቅ አለ፤ ባለሥልጣኖቹ ሸልመውት ይሆናል፤ ግን አላከበሩትም፤ ሻምበል ጉታን ያከበረው የማንዴላ ሞት ነው፤ የሚያሳዝነው ማንዴላ ይህንን የሱን ሕይወት ለማትረፍ ሁለት ሺህ ፓውንድ ያጣውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ሳያውቀው መሞቱ ነው።

የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪካቸው ተቀብሮ የቀረው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ታዴዎስ ታንቱ ሥራዬ ብሎ የተረሱ አርበኞችን ከመቃብር እያወጣ ያስተዋውቀናል፤ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሥራ በአንድ ሰው በበጎ ፈቃድ የሚሠራ ሳይሆን ዋና የመንግሥት ተግባር ነው።

ሻምበል ጉታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባይሆንም ራሱን ችሎ ለኔልሰን ማንዴላ መቃብር ደርሶአል፤ በአገር ደረጃ በሥልጣን ወንበሮቹ ላይ ለአገር የሚያስቡ ሰዎች አለመኖራቸውን ለማወቅ ግሩም ማስረጃ ነው፤ ለቀብር የሄደው ባለሥልጣን ሻምበል ጉታን ይዞ ቢሄድ ኖሮ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ክብርና ጌጥ ይሆንለት ነበር፤ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብም ሆነ ለዓለም በመላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር አልሸጥም-አልለወጥም ብሎ የኔልሰን ማንዴላን ሕይወት ማትረፉን በማስታወቅ አገሪቱን ያስከብር ነበር፤ የታፈነው ታሪክ አፈትልኮ ሲወጣ ከስደተኞች ጋር ተያይዞ መሆኑ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአደባባይ መክሸፍ የሚያሳይ ነው፤ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ ተቀበለው፤ መንግሥት ያፈነውን ክብር ስደተኞች አጌጡበት!

ለእኔ አሁን አንድ ጥያቄ ይቀራል፤ ሻምበል ጉታ የአገሩን ክብር ከራሱ ጥቅም በላይ በማድረጉ፣ የተቀበለውን አደራ በመጠበቁ ቢያንስ ሁለት ሺህ ፓውንድ አጥቷል፤ እንዳጣ ሊቀር ነው? ቢያንስ የከፈለውን ሁለት ሺህ ፓውንድ ወይስ ያንን አሥር እጥፍ አድርገን እንከፍለዋለን? ሻምበል ጉታን የምናመሰግነው በርጥቡ ነው በደረቁ? እኛ ያለጥርጥር ኮርተንበታል፤ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የሱን ክብር በመጋራት ራሳችንን አክብረናል፤ ሻምበል ጉታም በእኛ እንዲኮራና በእኛ እንዲከበር ማድረግ ያለብን ይመስለኛል፤ ስለዚህ ምን እናድርግ? ለራሱ ክብር፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ክብር ሲል የከፈለውን  እስቲ ከወሬ ያለፈ ነገር እናስብና ለዚህ ጀግና የምንችለውን አድርገንለት እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥህ እንበለው።


Viewing all 931 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>