Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

የእኛ “መንግስት” (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ተመስገን ደሳለኝ

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ  አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ  ሁሉ ጥቅም ነው…ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ  ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም”

ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1  ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!

ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!›  የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡

እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…

በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…

 

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤ ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው››  ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?

ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ..

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ- ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤

የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡

ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን››  በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትርመለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባት እንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን›  የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?

በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው?  ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን?  …ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ  መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com



ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በህንዳዊ ፕሮፌሰር ሲማሩ ነበር(ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም…

ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!

ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡

እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…

በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤ ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ተመስገን ደሳለኝጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?

ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ..

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤

የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡

ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባትእንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?

በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን?…ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡


የግዳጅ ሰልፉን ለማምከን ታጥቀን እንነሳ! ~ ድምጻችን ይሰማ

$
0
0

‹‹የሃሰት ፕሮፖጋንዳ መደጋገም የእምነት መብት ጥያቄን ህገወጥ አያደርገውም!›› (ውድ ኮሚቴዎቻችን ለሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ካስገቡት ደብዳቤ ርእስ የተወሰደ)ለአመታት የህዝቡን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ህገወጥ በሆኑ ተግባራት ላይ መሰማራት የመረጠው መንግስት በግትርነት አቋሙ መግፋትና ከህዝብ ጋር መጋጨቱን ቀጥሎበታል.. ትናንት በህዝብ ዘንድ የሀሰት ቋት ተደርጎ የሚቆጠረው ኢቲቪ እንደዘገበው የፊታችን እሁድ ነሐሴ 26/2005 ‹‹አክራሪነትን›› ለማውገዝ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል፡፡ የሰልፉ አዘጋጅ ተብሎ የተገለጸው ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› ተብሎ የሚጠራው ተቋም ሲሆን ተቋሙ ‹‹ከሁሉም ሃይማኖት ተመርጠዋል›› ተብለው የተሰባሰቡ ግለሰቦች ጥምረት እንደሆነም ይታወቃል፡፡

በመሰረቱ ህዝበ ሙስሊሙ አክራሪነትን በጽኑ እንደሚያወግዝ እና በፀረ አክራሪነት ትግል ስም በእምነቱ ላይ የተቃጣበትን ጥቃት ግን እስከመጨረሻ እንደሚታገለው በተደጋጋሚ በግልጽ አስረድቷል፡፡ ዛሬ በግፍ እስር የሚገኙት ኮሚቴዎቻችንም ለመንግስት ባስገቧቸው ደብዳቤዎች በማያሻማ ቋንቋ ያስቀመጡት የማይቀየር አቋም ይኸው ነው፡፡ እኛ ‹‹አክራሪነትን ለማውገዝ ይካሄዳል›› የተባለለትን ሰልፍ የምንቃወመው መንግስት አክራሪነትን በመዋጋት ሽፋን ሃይማኖታዊ ጭቆና በንጹሀን ላይ እየፈጸመ በመሆኑ እና ለሁለት አመታት ያለከልካይ ሲያደርስ የነበረው እጅግ ከፍተኛ የህግ ጥሰት ዛሬ ወይንም ነገ የሚያስጠይቀው ሆኖ ሳለ ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል በመሆኑ ነው፡፡

የዚሁ ሰልፍ ዜና በይፋ የተገለጸው ገና ዛሬ ቢሆንም በየቀበሌው ያሉ የመንግስት ካድሬዎች ግን ከቀናት ጀምሮ ከየቀበሌው እየተሰባሰቡ ህዝቡን በግዳጅ የሚያስወጡበትን መንገድ ሲመካከሩ ቆይተዋል፡፡ በየቤቱ በመዞርም ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ቢያንስ 3 ሰው መገኘት እንዳለበት ሲያስጠነቅቁ እና ሲዝቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በፊት እንደዘገብነውም የግል ድርጅቶች ሳይቀሩ እንዲገኙ በማስጠንቀቂያ መልክ ትእዛዝ ወርዶ የማስገደድ ዘመቻ ተሰርቶባቸዋል፡፡ በግዳጅ ሰልፉ ማታለል የሚፈልጉት ማንን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ የሰልፉ እውነተኛ አዘጋጅና አስገዳጅ ራሱ መንግስትና ካድሬዎቹ ሆነው ሳለ ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰልፍ ጠራ›› ተብሎ በኢቲቪ መዘገቡ ለብዙዎች አሳፋሪ የሚሆንባቸውም ለዚሁ ነው፡፡

በመሰረቱ ሰልፉ መንግስት ያለመለትን ግብ ሊመታ እንደማይችል ሊታወቅ ይገባል፡፡ የግዳጅ ሰልፍ እስካሁንም ሲደረግ ቆይቷል፤ አዲስም አይደለም፡፡ የሚደረገው አዲስ አበባ ላይ ከመሆኑ ውጪ የተለየ ነገርም የለውም፤ ያው የተለመደው የቀበሌ ካድሬዎች ማስፈራሪያና ‹‹አይናችሁን ጨፍናችሁ ተታለሉ›› ጉትጎታ ነው፡፡ በህዝበ ሙስሊሙም ሆነ በሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ዘንድ ጥያቄያችን በሚገባ ታውቋል፡፡ የመብት ጥያቄ መሆኑን በተደጋጋሚ በሚያደርጉት ልባዊ ድጋፍ እውቅና ሰጥተዋል፡፡ መንግስት እስካሁን ሙስሊሙን ስጋት አድርጎ ለመሳል ሲያደርገው የነበረው ከልክ ያለፈ ጥረት አንዳችም አመኔታ አላስገኘለትም፡፡

‹‹ጦርነቴ ከአክራሪነት ጋር ነው›› ሲል የቆየው መንግስት እየገደለ እና እደበደበ ያለው ሰላማዊውን ሙስሊም መሆኑን ያላየ ኢትዮጵያዊ የት አለና? ‹‹ጥቂት አሸባሪዎች ጋር ነው ግብግቡ›› ሲል ቢቆይም ዘመቻው ግን ተራው ሰላማዊ ሙስሊም ላይ መሆኑን ያልተረዳ አካል የት አለና? እያስፈራራ፣ እየደበደበ፣ እየዘረፈ፣ እያሰረ፣ እያሰደደ፣ እየገደለ ያለው ራሱ መንግስት መሆኑን የማያውቅ ኢትየጵያዊ የት አለና?

ደጋግመን ስንናገር እንደነበርነው የመብት ጥያቄ ያነሳው ህዝብ ነው – በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ! ህዝብ ደግሞ ለፕሮፓጋንዳ አይሸነፍም፤ ምክንያቱም ፕሮፓጋንዳ ራሱ የሚያስፈልገው ህዝቡን ለማሳመን ነው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ደግሞ የሚፈልገውን ያውቃል፡፡ ዘመቻው ማን ላይ እንደሆነ ይረዳልና ሊታለል አይችልም፡፡ ለዘመናት አብረውን የኖሩት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም ጥያቄያችንን ተረድተዋል፡፡ እየደረሰብን ያለውን በደል አይተዋል፡፡ እናም እነሱም ሊታለሉ አይችሉም፡፡ በዳዩ መንግስት፣ ተበዳዮቹ እኛ መሆናችን ሐቅ ነውና ያለሀሰት ፕሮፓጋንዳ ጋጋታ እንደረፋድ ጸሀይ ግልጽ ብሎ መታየቱ አይቀርም፤ ኢንሻአላህ! ቀላል ህዝባዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ ይልቅ ተራራ መቧጠጥ የቀለለው መንግስት የግዳጅ ሰልፍ ልክ እንደከዚህ ቀደሞቹ የከሸፉ ሙከራዎች ባለቤቱን ሀፍረት አከናንቦ ማለፉ የሚቀር አይደለም!

እንደህዝብ የሚፈጸምብንን ከፍተኛ በደል ተቋቁመን በትእግስታችንና ሰለማዊነታችን ጸንተናል፡፡ እንደህዝብም ንጽህናችንን አስመስክረናል፡፡ መንግስት ግን በሚሰራው ወንጀል ከማንም በላይ ራሱን እያጋለጠና ተቀባይነቱን እየሸረሸረ ነው፡፡ በተጨማሪም ህዝበ ሙስሊሙ የጁምአ ተቃውሞውን ላልተወሰነ ጊዜ በማቆም የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ለመንግስት የማሰቢያና የጥሞና እድል ለመስጠት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህ የእፎይታ ግዜ አሁን ከሚታዩ ሁኔታዎች በመነሳት መከለሱ ግዴታ እየሆነ ይመስላል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በማንኛውም ወቅት አስፈላጊውን መስዋእትነት እየከፈለና የሰላማዊ ትግል ስልቶችን እየለዋወጠ ለመብቱ የሚያደርገውን ትግል መቀጠል የሚችል ህዝብ ነው፡፡

አዎን! እንደህዝብ ሚሊዮኖች ሆነንና ተባብረን የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን በአላህ ፍቃድ ድባቅ እንመታለን! የእሁዱ የመንግስት የግዳጅ ሰልፍ ፕሮፓጋንዳ ያለጥርጥር ይከሽፋል! በጭራሽ አላማውን ሊያሳካም አይችልም! ህዝቡ በዚህ የሀሰት ድግስ ላይ እንዳይካፈል የማድረጉ ርብርብ እንደተጠበቀ ሆኖ ሰልፉ ቢካሄድ እንኳን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የመዲናይቱን ከተማዎች የሚያጥለቀልቀው የዒድ ህዝባዊ ማእበል በአንድነት ወጥቶና ተቀላቅሎ ትክክለኛ ድምጹን ሊያሰማና በደሉን ሊያሳውቅ የሚችልባቸው ስልቶች ከሌሎች በርካታ አማራጮች ጋር ቀርበው ምክክር እየተደረገባቸው ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ‹‹የሃሰት ፕሮፖጋንዳ መደጋገም የእምነት መብት ጥያቄን ህገወጥ አያደርገውም!›› በሚል ርዕስ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የመንግስትን እኩይ አላማ የማሰናከል ዘመቻ ይካሄዳል፡፡ መንግስት የጠራው ሰልፍ በሃገራችን ሰምተን የማናውቀው አዲስ የመጥፎ ታሪክ ጅማሮ በመሆኑ ስለነገዋ ኢትዮጵያ እና ስለነገው ትውልድ ሁሉ የሚጨነቅ ኢትዮጶያዊ ይህንን ጥፋት በመከላከል የበኩሉን ድርሻ የመወጣት ግዴታ እንዳለበትም ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በዘመቻው ላይ መላው ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በተጨማሪም እያንዳንዱ ሙስሊም በየመንደሩ ሰልፉን አስመልክቶ እየተሰራ ያለውን ህገወጥ ተግባር በማጋለጥና መረጃውን በማዳረስ ከፍተኛ ርብርብ የማድረግ ስራ ላይ መሰማራት በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ሁላችንም እንበርታ! መረጃዎችን ትንሽ ትልቅ ሳንል እያጣራን ማሰራጨቱ ለትግላችን ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ተግባር ነውና አንዘናጋ! ጊዜው እየሄደ ነው! ጨለማው ጥቅጥቅ ባለ ቁጥር ንጋቱ እየተቃረበ መሆኑን እያሰብን በትግላችን እንበራታ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

አላሁ አክበር!


የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ! -ግርማ ሞገስ

$
0
0

“አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ሰላማዊ ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም  ይቀጥላል፡፡” የሚለውን መርሃቸውን አንድነቶች ካስተዋወቁን ከርመዋል.. ባለፈው ሳምንት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮምያ የተተከሉት መረን የለቀቁ አምባገነን አስተዳደሮች እና ደህንነቶች የፈጸሙባቸውን ወደር የለሽ የአንደበት፣ የሳይኮሎጂ እና የአካል ጥቃት በፈገግታ በመቀበል እየሞቱ ሳይገድሉ በሰላማዊ ትግል ህገ-መንግስቱን ለማስከበር ያላቸውን ጽናት ደግመው አሳይተውናል አንድነቶች። አንድነቶች የሚሰብኩትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያ እንደገና ባለፈው ሳምንት ተመልክታለች። የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች አረመኔነት አሳፋሪ ነበር። በፍጹም የስልጣኔ አየር የነፈሰባቸው አይመስሉም። ዘመናዊ አስተሳሰብ ለአንድ ቀንም የጎበኛቸው አይመስሉም። ይባስ ብሎ የባሌ ሮቢ እና የፍቼ አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች ከህጋዊ የመንግስት መዋቅር ውጪ ጸረ-ነፃነት ወረበሎች (ቦዘኔዎች) ያደራጁ ይመስላሉ። ይኽ ጉዳይ ጥናት ሊደረገበት ይገባል።

Read more : http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2013/08/Yemillionoch-Dimtse-be-oromiya.pdf


ተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!?

$
0
0

bbbተስፋሁንን መግደል ለኢህአዴግ ተስፋ ይሆናታልን….!? አብዲሳ የብዙ ጊዜ ወዳጄ ነበር፡፡ በየገጠሩ እየዞርን በርካታ ስራ አብረን ሰርተናል፡፡ የዋህነቱ እጅግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በየክልሉ ስንዞር አበሉን የሚጨርሰው “ቸገረኝ” ላለው ሁላ መበስጠት እንደነበር አብረነው የሰራ ሁላ እርሱን የምንለይበት ባህሪው ነው.. ይሄ ልጅ በአንዱ ቀን ለስራ ልንሄድ የተቀጣጠርንበት ቦታ ሆነን ስንጠብቀው ስንጠብቀው ሳይመጣ ቀረ… ስልኩን ብንደውልልት አይሰራም፡፡ ካለንበት እየተንቆራጠጥን… ወደ ሶስት ሰዓት ድረስ ዘግይተን ጠበቅነው የውሃ ሸታ ሆነብን… ምን ሆነ ብለን እየተጨነቅን እንጀራ ነውና ጉዟችንን ቀጠልን…

አብረን ስንጓዝ ከነበርነው መካከል አብዲሳን በቅጡ የምናውቀው ሰዎች “ይሄኔ አንድ የታመ ሰው አጋጥሞት ሆስፒታል ሳላደርስ አልሄድም ብሎ ነው…” ….ወይ ደግሞ “…አንዱ ገንዘብ ተቸግሮ አጋጥሞት  ምንም ሳያስቀር ገንዘቡን ሰጥቶ ወደ እኛ መምጫ ራሱ ተቸግሮ ይሆናል …” ካልሆነ ግን “…ዘራፊዎች አግኝተው ጉድ አድርገውት ሊሆን ይችላል…. እያልን መገመታችንን ተያያዝነው…

ግምታችን ሁሉ ትክክል አልነበረም፡፡

አብዲሳ በስንተኛው ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት መታየቱን ሰማን… በየዋህነቱ የተቸገረ በመርዳቱ የምናውቀው አብዲ “አሸባሪ” ተብሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ አብዲሳ “አሻባሪ” ከተባለማ እኛ ምን ልንባል ነው… ብለን ራሳችንን እንደ ነውጠኛ የምናየው እኛ በጣም ተደነቅን!

አብዲ ወደ አምስት ወራት በማዕከላዊ፣ ወደ አምስት አመት በቃሊቲ እንዲሁም ሁለት ሶስት አመት ነው መሰለኝ በዝዋይ ማሰሪያ ቤቶች ቆይቶ ነፃ ነህ ተብሎ እስኪሰናበት ድረስ በአስር ቤቱ ውስጥ ሲደርስበት በነበረው መከራ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ታድያ ከእስር ቤት ሊወጣ አካባቢ አንድ ባለስልጣን ብጤ ሰውዬ ጎብኝተውት ነበር፡፡

እስር ቤቱ እንዴት ነበር… ሲሉ ጠየቁት፡፡ አብዲሳ ምን አላቸው መሰልዎ… እስር ቤቱ እንዴት እንደሆነ ራስዎት ገብተው ካላዩት በስተቀር እንዲህ ነው ብዬ  ብነግሮት አይገባዎትም ፡፡ አላቸው፡፡

ይሄው ሰሞኑን ወንድማችን ተስፋሁን ጫመዳ በእስር ቤት በደረሰበት ስቃይ የተነሳ ህይወቱ ማለፏን ሰማን፡፡ ተስፋሁን በ1999 ዓ.ም መንግስት ኬኒያ ድረስ አፍኖ ወሳጆቹን ልኮ ለኬኒያ ፖሊስ ሽልጉን ከፍሎ፤ (የኬኒያ ፖሊስ እንኳንስ ከፍለውት እንዲሁም ጤዛ ነው) ብቻ በትብብር ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ነበር… ከዛም በታሰረበት ሆኖ ሞተን ሰማን!

ለዚህ ጉዳይ የሚሰማ ቢኖር የኬኒያን መንግስት ራሱ ፍርድ ቤት ማቆም የሚገባ ይመስለኛል፡፡

ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ራሱ፤ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል እግዜሩም እኛም የምንጠይቀው ግን የገዛ መንግስታችን ነው፡፡ አዎ መንግስታችን እጁ ላይ የተለያዩ ሀገራት ብድር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሰዎች እምባ የተለያዩ ሰዎች ደምም አለበት፡፡

ተስፋሁን ለምን እንዲሞት ተፈረደበት… እውን ለሀገሪቱ ደህንነት ስጋት ሆኖ ነውን… የሚለውን በፍጹም!!! ለማለት፤ እነ አብዲሳን ያየነው እኛ ምስክሮች ነን፡፡ ምስኪኑ አብዲሳ ስምንት አመት ታስሮ በነፃ ከመፈታቱ በፊት “የሀገር ስጋት ሽብርተኛ!” ተብሎ ነበር የታሰረው፡፡  በእስር ቤት የደረሰበትን ስቃይ ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠላ ነው፡፡ የነገረኝን በሙሉ ለማሳየት በፊልም እንጂ ጽሁፍ የሚገልፀው አይደለም፡፡

እሺ ኢንጂነር ተስፋሁን የኦነግ ወይም የሌላ ተቃዋሚ አባል ወይም ደጋፊ ወይም እንዳሻቸው ይሁኑ ባይ ነው እንበለው፡፡ ግን እርሱን በመግደል የሚቃወሙ ሰዎችን ተስፋ ማስቆረጥ አልያም  ቁጥራቸውን መቀነስ ይቻላል….

ኢህአዴግ በጫካ እያለች ታጋዮቿ እና ሰላዮቿ ደርግ በቁጥጥር ስር ሲያውላቸው ቀጥታ አብዮታዊ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ውጤቱ ግን ምንድነው  የሆነው… ብለው የጠየቁ እንደሆ፤  ውጤቱ ብሶቱን እያጠነከረው ቁጭቱን እያባሰው እምቢ ባይነቱን እያበረታው ነው የሄደው…!

ዛሬ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ፍዳቸውን እያዩ ነው… የምር ለኢህአዴግ እናስባለን የምትሉ ሰዎች የእነ ተስፋሁን ግድያ የኢህአዴግ ተስፋ ሟጠጡን ያሳያልና…. ይሄ ነገር መሞቻሽ ነው ብላችሁ ምከሯት፡፡ እምቢ ካለች ግን መከራው ይመክራታል፡፡

ምክር!

ባለስልጣኖቻችን ሆይ እናንተ ማረሚያ ቤት የምትሏቸው እስር ቤቶች መግደያ ቤት እየሆኑ ነው፡፡ ብልጥ ከሆናችሁ…. አብዲሳ እንዳለው ራሳችሁ ገብታችሁ ሳታዩት በፊት በእስር ለሚማቅቁ ወገኖቻችን መላ ፈልጉ!

ተስፋሁን ጫመዳ ነፍሱን ከደህናው ስፍራ ያሳርፍልን! ለቤተሰቦቹም መጸናናትን ይስጥልን!


ህወሓቶች ‘ሁኔታችን አይታቹ ደግፉን’ ይሉናል

$
0
0

ባለፈው ሳምንት ነው፤ በአንድ የሰሜን አሜሪካ ከተማ። የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የተጋሩ ፌስቲቫል ተገኝተው ድጋፍ ለማሰባሰብ በረሩ። ከትግራይ ተወላጆች ጋር ለመወያየት መድረክ ተከፈተ.. ተሳታፊዎቹ ስለ ልማትና መልካም አስተዳደር ችግር፣ ስለ ሐውዜን ጉዳይ፣ በትግራይ ተወላጆች ስለሚደርስ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወዘተ አንስተው ይጠይቃሉ። ባለስልጣናቱም ሲመልሱ፣ “እኛ ‘ኮ ብዙ ጠላቶች አሉብን። እኛን ለማጥፋት የሚሯሯጡ ኃይሎች አሉ። እኛ’ኮ ‘ትግሬ ወደ መቀሌ ዕቃ ወደ ቀበሌ’ የሚሉን ሞታችንን የሚጠባበቁ ኃይሎች ይዘን ነን ያለነው። ይህ ሁኔታችን እያወቃቹ እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ትጠይቃላቹ? እንዴት ህወሓትን ይህን ያህል ትጠላላቹ? ሁኔታችን ኮ መረዳት አለባቹ።”
ይገርማል። ህወሓቶች ጥያቄ መመለስ ሲያቅታቸው ‘ጠላት እየመጣ ነው፣ ህወሓቶች ከሌለን የትግራይ ህዝብ አደጋ ዉስጥ ይወድቃል’ ይሉናል። መጀመርያ የትግራይን ህዝብ ጠላት ማነው? ለምንስ ጠላት ሆነ? ጥላቻው ማን ፈጠረው? ‘የትግራይ ህዝብ ጠላት አለው’ ብለን እንኳ ከተነሳን ማድረግ ያለብን የትግራይን ህዝብ ማፈን አይመስለኝም። ምክንያቱም ህዝብ ማፈን ህዝቡ ደካማ እንዲሆን ማድረግ ነው። ደካማ ከሆነ ደግሞ ለጥቃት ይዳረጋል።
በትግራይ ህዝብ ያንዣበበ አደጋ ካለ መፍትሔው ሌሎች ህዝቦች መበደል ነው? አይመስለኝም። በትግራይ ህዝብ ስም ሌሎች ህዝቦች መበደል ጠላትን ማፍራት ነው። በትክክል ስጋቱ ካለ የትግራይ ህዝብ መብቱ ተከብሮለት አማራጭ የፖለቲካ ድርጅት እንዲኖረው ሊፈቀድለት ይገባል እንጂ ሊታፈንና ሊዳከም አይገባም።
የትግራይን ህዝብ ከጥቃት ማደን የሚችሉ የህወሓት ባለስልጣናት ብቻ ናቸው ያለ ማነው?


መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን! ሰማያዊ ፓርቲ

$
0
0

ፓርቲያችን ሰማያዊ በህገ መንግሥቱ በተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱን ተጠቅሞ ለመንግሥት ጥያቄዎችን በማቅረብ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አድርጓል…

 semayawi party's protest call in Addis Ababa

መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሰወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል፡፡

ይሁን እንጂ ፓርቲያችን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል፡፡ በተጨማሪም ለመንግሥት መዋቅር ዜጐች በዚህ ሰልፍ እንዲወጡ በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኑዋሪዎች አረጋግጠናል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በመስቀል አደባባይ የጠራውን ተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እየጠየቅን ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡

በመጨረሻም መንግስት ዜጐችን ያለፈቃዳቸው በማስፈረም ተገደው ሰልፍ እንዲወጡ ማድረግ ህገ ወጥ ስለሆነ፣ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን፡


4 ለ 3 በጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ላይ የተደረገ ክርክር

$
0
0

አንድነት ፓርቲ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን በህዝብ ድጋፍና ጥያቄ ለማሰረዝ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ የሚፈለገውን ግብ ለመምታቱ በገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ኢቴቪ በአዋጁ ዙሪያ የፓርቲዎችን አቋም የሚያንጸባርቅ መድረክ ማዘጋጀቱ ማሳያ ነው…ኢህአዴግ ካድሬዎቹ አዋጁን በማንበብ አንድነቶች ለሚያነሱት መከራከሪያ ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ ትዕዛዝ ማውረዱም ሌላኛው የአደባባይ ድል ነው፡፡

በነቢብ የህዝብ በገቢር የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ኢቴቪ በአዋጁ ላይ ያላቸውን አቋም እንዲያንጸባርቁ የጋበዛቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ በአቶ በቀለ ነጋዓ፣አንድነት በሃብታሙ አያሌው፣ኢዴፓ በሙሼ ሰሙ፣ሰማያዊ በይልቃል ጌትነት፣ ኢህአዴግ በሽመልስ ከማል፣በጌታቸው ረዳና በኢቴቪው ጋዜጠኛ ተወክለዋል፡፡

ክርክሩ በተራ መቀስ የተቆራረጠ መሆኑ

ኢህአዴግ ከምርጫ 1997 በኋላ በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት የሚተላለፉ ክርክሮች ፎብያ የተጠናወተው በመሆኑ live debate አይመቸውም፡፡እናም ክርክሩ በቀጥታ አለመተላለፉ ለባለ መቀሶቹ ጥቅሙ ከፍ ያለ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው፡፡በሁለት ክፍል የተላለፈው ክርክር በተራ መቀስ መቆረጡን ለመመስከር ሶስተኛ አይን የማያስፈልግበትን አንድ ሁለት ነጥብ ልጥቀስ፡፡ከመሬት ተነስተው የኢህአዴጉ ተወካይ ተቃዋሚዎችን‹‹እንዴት ድራማ ነው ትላላችሁ››በማለት ይወርፏቸው ጀመር፡፡ክርክሩን ስራዬ ብሎ የተከታተለ ሰው እኚህ ሰው ለምን ያልተጻፈ ያነባሉ ብሎ ሊፈላሰፍ ይችላል፡፡ነገሩ ግን መዛባቱን የፈጠረው የሽመልስ ንግግር ሳይሆን ኢቴቪ ነው፡፡ ማለቴ መቀሱ፡፡

ጌታቸው ከዚህ በፊት አብሮኝ በአንድ መድረክ ሰርቷል ያሉትንና አሁን የአሰላለፍ ለውጥ በማድረጉ አንድነትን የተቀላቀለውን ሃብታሙን በነገር ወጋ ሲያደርጉት ታዝቢያለሁ፣ሃብታሙ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ የሚለው ነገር እንደሚኖር መጠርጠሬ አልቀረምና ተራው ደርሶ የሚለውን ለማድመጥ ጆሮዬን ቀሰርኩ ነገር ግን የሃብታሙ ንግግር ከመሃል እንደጀመረ በሚያሳብቅ መልኩ ለጌቾ ይሰጠዋል ብዬ የጠበቅኩት ምላሽ ሳይቀርብ ቀረ፡፡ሴኮ ቱሬ ክርክሮችን በመቆራረጥ ጥበብ የተካኑ እንደነበሩ በአንድ ወቅት የድሮው ልደቱ (አዲስ ልደቱ እንዳሉ ስለማምን የቀድሞው ለማለት ተገድጃለሁ)ተናግረው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ሴኮ አሁን ስለሌሉ የኢቴቪ አዲሱ መቀስ ብዙም በቆረጣ ባለመካኑ ቆረጣው አይን ያወጣ ሆኖበታልና አልተሳካም፡፡

ያልተጠየቀ ‹‹መመለስ›› የጆሮ ህመም ይሆን?

ተቃዋሚዎች በአንድነት በሚባል መልኩ አዋጁ ከህገ መንግስቱ እንደሚጋጭ በመግለጽ ጭብጥ ለማስያዝ ሞክረዋል፡፡ሽመልስ እሳት ለብሰውና ከአንድ የህግ ባለሞያ በማይጠበቅ መልኩ እየደጋገሙ‹‹እንትን››እያሉ በሰጡት መልስ ‹‹ተቃዋሚዎች የእኛ አዋጅ የአሜሪካንን ወይም የአውሮፓን ስለማይመስል ህግ ለመሰኘት ብቁ አይደለም ይላሉ››ብለዋል፡፡አዋጁ የሰብዓዊ መብትን ይጋፋል ሲባሉም አራምባ በመርገጥ ‹‹ ለሽብርተኞች በሩን በመዝጋቱ የእኛ ህግ ከሁሉም የተሻለ ነው››ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ያልሰማ ጆሮ የሚሰጠውን መልስ ለማወቅ የሽመልስንና የጌታቸውን ንግግሮች ማድመጥ አቻ የሚገኝለት አይመስለኝም፡፡ለነገሩ በዋናነት የኢህአዴግ ዋነኛ ችግር ምላስ እንጂ ጆሮ የሌለው መሆኑ አይደል፡፡ተቃዋሚዎቹ አዋጁን በተመለከተ ለሚያነሷቸው ውሃ የሚያነሱ መከራከሪያዎች ኢህአዴጋዊያኑ ከተነሳው ሃሳብ ጋር ተያያዥነት የሌለውን ምላሽ መስጠታቸው ሟቹን መለስን በብዙ ነገር እንዳስታውስ አድርጎኝ ነገሩ የወል ችግራቸው መሆኑን ደመደምኩ፡፡

በዚህ አይነት በፖለቲካ ውሳኔ እንዳንረሸን ሰጋሁ

ሽብርተኞችን የመፈረጅ ስልጣን ፓርላማው አልተሰጠውም የሚለው መከራከሪያ በአቶ ሽመልስ አስደንጋጭ መልስ ተሰጥቶታል፡፡ፓርላማው ህግ የማውጣት እንጂ ህግ የመተርጎም ስልጣን የፍርድ ቤቶች በመሆኑ የፍርድ ቤቶችን ስራ ለፍርድ ቤቶች መስጠት ሲገባው ያወጣውን ህግ ለመተርጎም መሄዱ ህገ መንግስታዊ ጥሰት ነው ሲባል ሽመልስ ‹‹ይህ የፖለቲካ ውሳኔ ነው››ብለው አረፉት፡፡በእኛ አገር የፖለቲካ ፣የውድብ፣የቡድን ውሳኔ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡በፓርላማው ካሉት 547 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 545 በመውሰድ ቤቱን ተቆጣጥሯል፡፡በዚህ የአንድ ፓርቲ ጉባዔ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተላለፈ ማለት ምን አይነት ትርጉም እንደሚኖረው ለታዛቢ እንተወው፡፡ደግሞስ የማስረጃ፣የምስክርናየህግ ድንጋጌን የሚፈልግ ትልቅ ጉዳይ እንዴት ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲይዝ ይደረጋል?ከዚህ በላይ ፍትህን መስቀል ከወዴት ይገኛል?

አወያይ ጋዜጠኛ ወይስ ኳስ አቀባይ?

የኢቴቪው ጋዜጠኛ ስሙን ከኢህአዴግ ተወካዮች ተራ አለማስመዝገቡ ብስጭቴን እንዳናረው መሸሸግ አይኖርብኝም፡፡ከመነሻው ‹‹ኢትዮጵያን የሽብር ስጋት ያሰጋታል ወይስ አያሰጋትም››የሚል ጥያቄ አንስቶ በአገሪቱ የደረሱ ጥቃቶችን በፊልም ማሳየት ምን ሊባል ይችላል?ይህንን ፊልም የሚመለከቱ ሰዎች ከመነሻው የጥያቄው መነሳት አስፈላጊነት ላይታያቸው እንደሚችል መገመት ባይከብድም አወያዮ ፊልሙን ጋብዟል፡፡

ፓርላማው ድርጅቶችን መፈረጁን በተመለከተ ፓርቲዎቹ ሲወያዮ የጋዜጠኛ ማልያ ያጠለቀው አወያይ ጣልቃ ገብቶ ‹‹የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስታወስ ያህል ፓርላማው የፈረጀው አልቃይዳ፣አልሻባብ፣ኦነግ፣ኦብነግንና ግንቦት ሰባትን ነው››ብሏል፡፡እንኳን ይህችን ያለ ሰፈሯ የመጣችን ዝንብ ለምናውቅ ሰዎች የጋዜጠኛው ማስታወሻ ግልጽ ናት‹‹ተቃዋሚዎች የሚከራከሩት ለአልቃይዳ ነው››ለማለት ነው፡፡ክርክሩ ግን ፓርላማው ከስልጣኑ ውጪ እየተጓዘ በመሆኑ ነገ ሌሎች ሰላማዊ ፓርቲዎችን ሽብርተኛ በማለት ሊፈርጅ ይችላል የሚል ነበር፡፡አወያዮ ልክ የኢህአዴግ ተወካዮች አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ሲሰማውና የማርያም መንገድ ሲያጡ ዘው ብሎ በመግባት መውጫ መንገድ ያመቻቻል፡፡ኳሷ በተቃዋሚዎች እጅ በኢህአዴግ ሜዳ እየተንከባለለች ወደ ጎል ስትደርስ ጋዜጠኛው ፊሽካ ነፍቶ ኳሷ እንድትመለስ ያደርጋል፡፡

በእስካሁኑ ክርክር ለበቀለና ለሃብታሙ ኮፊያዬን አወልቃለሁ     

ክርክሩ ነገ ምሽት እንደሚለጥቅ ኢቴቪ ቃል ገብቷል፡፡የመጨረሻው ክርክር ቀርቦ ፋይሉ ከመዘጋቱ በፊት በግሌ ባደረግኩት ዳሰሳ የመጀመሪያው ምሽት የክርክር ኮከብ አቶ በቀለ ነግዓ የሁለተኛው ምሽት ፈርጥ ደግሞ ሃብታሙ አያሌው ነበር፡፡ሙሼ ረጋ ብሎ የሚያነሳቸው ነጥቦች ቦታ ሊሰጣቸው የሚገባቸው እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡

በቀለ ዘና እና ረጋ ብለው የሚወረውሯቸው ቃላቶች ድንጋይ ሆነው  በኢህአዴግ ላይ የሚያርፉ ቢሆኑ አቶ በረከት ስምኦን በሁለት ምርጫዎች ወግ እንደጠቀሰው ናዳ ሆነው ኢህአዴግን ከመንበሩ ባፈናቀሉት ነበር፡፡ ሃብታሙ ታሊባንን እንደ አገር በመውሰድና የጸረ ሽብርተኝነትን የምንቃወመው››በማለት ከመናገሩ ውጪ ነጥብ በነጥብ ያነሳቸው ሃሳቦች የሚጣል ነገር አልነበራቸውም፡፡ እንግዲህ ደግሞ ለነገው የነገ ሰው ይበለን፡፡



በሹመኛ የመጅሊስ አባላትና በመንግስት መካከል አለመግባባት መንገሱ ተሰማ!! (ድምፃችን ይሰማ)

$
0
0
አንዳንድ የወረዳ መጅሊስ ሹመኞች ‹‹መንግስት በሚያዘጋጀው ሰልፍና ስብሰባ ዲናችንን አናሰድብም›› የሚል አቋም ይዘዋል!
 በመጪው እሁድ ነሀሴ 26 መንግስት በግዳጅ ሊያካሄደው ካሰበው ሰልፍ ጋር በተገናኘ በሹመኛ የመጅሊስ አባላትና በመንግስት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ… አለመግባባቱ የተፈጠረው በመንግስት የቅስቀሳ ስብሰባዎች ላይ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ተደጋጋሚ ዘለፋ እና የማንቋሸሽ ተግባራት በመበራከቱና መንግስትም ሁኔታውን ለመግታት ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

‹‹የሕግ ጉዳይን ለሕግ ትተን አክራሪዎችንና ጽንፈኞችን በሰላማዊ ሠልፍ እናወግዛለን››  የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተወካዮች

 ባለፈው እሁድ የመንግስት ሀላፊዎች ከመጅሊስ የወረዳ ሹመኞች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እና ግምገማ የመጅሊሱ ሹመኞች ለመጪው እሁድ የመንግስት ሰልፍ በቂ ቅስቀሳ እያደረጉ እንዳልሆነና ይህ መስተካከል እንዳለበት ያሳሰቡ የመንግስት ሀላፊዎች የሰጡትን ገለጻ ተከትሎ ሹመኞቹ ባደረጉት ንግግር ‹‹በየስብሰባው የሚገኙ የመንግስት ሰዎች ዲናችንን እየተሳደቡብን ሞራላችን እየተነካ ነው›› ያሉ ሲሆን ‹‹በዚህ አቅጣጫ ህብረተሰቡ አግልሎን በዚህ በኩል ደግሞ መንግስት ዲናችንን እያሰደበብን ከመሀል ሆነን እየተጎዳን በመሆኑ መንግስት ዘለፋውን ያስቁምልን›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በስብሰባው የተገኙ የመንግስት ሀላፊዎች በበኩላቸው የመጅሊሱን ሹመኞች በሰጡት አስተያየት ምክንያት የገሰጿቸው ሲሆን ተሳታፊዎች የፈለጉትን አስተያየት የመሰንዘር መብት አላቸውም ብለዋል፡፡ የመጅሊስ ሹመኞቹ ‹‹ካድሬዎቹ እየሰጡ ያሉት ስሜታዊ አስተያየት ሙስሊሙን እየጎዳ ስለሆነ ሊቆም ይገባል›› በሚል መረር ያለ ወቀሳ ቢያቀርቡም የመንግስት ሀላፊዎች ‹‹የሀገር ጉዳይ ስለሆነ ማንም በስሜት ቢናገር አይፈረድበትም›› በሚል ምላሽ ሰንዝረዋል፡፡ ሀላፊዎቹ አክለውም ሰልፉ ወሳኝ ምእራፍ የሚከፈትበት በመሆኑ ሁሉም የመጅሊስ አባል ከነቤተሰቡ መሳተፍ እንዳለበት አስጠንቅቀው ሰልፉ መንግስት ጠላቶቹን የሚለይት በመሆኑ በሰልፉ አለመሳተፍ የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ እንደሆነ በዛቻ መልክ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በስድስት ኪሎ ስብሰባ ማእከል የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባዘጋጀው ስብሰባ ተሳታፊ የመንግስት ካድሬዎች የእስልምናን ክብር የሚያራክሱ ዘለፋዎችና የእምነቱን ተከታዮች ክብር የሚያናንቁ ውንጀላዎች መሰንዘራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በርካታ የመጅሊስ ሹመኞችም አንገታቸውን ደፍተው ከስብሰባው ለመውጣት ተገደዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰኞ እለት ከቀኑ አስር ሰአት ላይ የክፍለ ከተማ ሃላፊዎች በዚሁ ሰልፍ ጉዳይ ላይ ከየወረዳው መጅሊስ ሹመኛ አባላት ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ስብሰባ መንግስት አስደንጋጭ ሪፖርት ቀርቦለታል፡፡ በተለይም በየካ፣ በአራዳ፣ አዲስ ከተማና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ያሉ አንዳንድ የመጅሊስ አባላት ባቀረቡት ሪፖርት አባላቱ እንኳን ታች ወርደው ህብረተሰቡን ለመቀስቀስ ቀርቶ የራሳቸው የመጅሊስ አባላቶች እንኳ ለመሳተፍ ፈቃደኞች እንዳልሆኑና ‹‹መንግስት በሚያዘጋጀው ሰልፍና ስብሰባ ዲናችንን አናሰድብም›› የሚል ምላሽ እንዳቀረቡ ታውቋል፡፡ የመጅሊስ ሹመኞቹ የሰልፍ ተሳታፊዎችን ቃል እንዲያስገቡበት በመንግስት በተሰጣቸው ፎርም ምን ያህል ሰው እንዳሰፈሩ የመረመሩት የመንግስት ሀላፊዎች አንዳንዱ እራሱንና ቤተሰቦቹን ብቻ ያስመዘገበ መሆኑና ሌሎቹ ደግሞ ባዶ ወረቀት ማስረከባቸው ሀላፊዎቹን በብስጭት እንዲወራጩ አድርጓቸዋል፡፡

ይህ ሁኔታ ያስደነገጣቸው የመንግስት የክፍለ ከተማ አመራሮች ከዚህ በኋላ የየወረዳ ካቢኔ አባላት ከመጅሊስ ሹመኞች ጋር አብረው እየዞሩ ጥሪ እንዲያቀርቡና ጉዳዩም የሞት ሽረት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ይህ ሰልፍ እንዲሳካ እባካችሁ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ›› በሚል በተማጽኖ ጭምር ትእዛዝ ሲሰጡ የነበሩት የመንግስት ሀላፊዎች የመጅሊስ ሹመኞች ጥሪውን ሲያካሄዱ ሃይማኖታዊ አለባበስን ተግባራዊ እንዲደርጉ አዘዋል፡፡ ‹‹ይህ ሰልፍ ከተሳካ ቀጣዩ ስራችን መስጂዶችን ከሙስሊሙ እየነጠቅን ለናንተ ማስረከብ ነው የሚሆነው›› ብለውም ንግግራቸውን አሳርገዋል፡፡ በአዲስ አበባ ደረጃ ቀጣይ ሪፖርት ለመስማት እና ለመገምገም ነገ ሐሙስ ስብሰባ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እሁድ የሚካሄደውን የግዳጅ ሰልፍ የሃይማኖቶች ጉባኤ ነው ያዘጋጀው በሚል መንግስት ቢገልጽም ሰልፉን ሙሉ በሙሉ መዋቅሩን በመጠቀምና ከፍተኛ ፋይናንስ በማፍሰስ እያስተባበረ ያለው መንግስት መሆኑ ይታወቃል፡፡

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎችን በድጋሜ አስጠነቀቁ

$
0
0

ESAT  ኢሳት ዜና :- መንግስት ባዘጋጀው በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ” የአገሪቱ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአክራሪዎችንና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴዎች ከመደገፍ ካልተቆጠቡ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል..

 

ማንኛውም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በሚያደርጉትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጡት አቶ ሐይለማርያም፣ የጥፋት ሀይሎችን ለማምከን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ጸረ ሰላም እንቅስቃሴዎች ሊወገዙ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የበላይ ጠባቂ ሼክ ኪያር መሃመድ አማን በበኩላቸው ፣ የመቻቻል ባህሉ ለትውልድ መተላለፍ አለበት ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የተለያዩ ባለስልጣናት እና እንግዶች ንግግር አድርገዋል።

መንግስት በቅርቡ በንጹህን ሙስሊሞች ላይ በወሰደው እርምጃ ሊጸጸት ቀርቶ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና መንግስት የሀይል አማራጭ ብቸኛው መፍትሄ ነው ብሎ እንደሚያምን ከአቶ ሐይለማርያም ንግግር መረዳት መቻሉን ዘጋቢያችን ገልጿል።

በእስር ላይ ከሚገኙት ድምጻችን ይሰማ አመራሮች ጋር ስለመነጋገር ወይም ችግሩን በሰላም ስለመፍታት ከሀይማኖት አባቶችም አለመነሳቱን አውስቷል።

የስብሰባው አላማ መንግስት ስለወሰደውና ስለሚወስደው የሀይል እርምጃ ከሁለቱም የሀይማኖት መሪዎች ድጋፍ ማግኘትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከዘጋቢያችን ሪፖርት ለመረዳት ይቻላል።

 


ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!

$
0
0

የነፃነት ጐህ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 11 ቁጥር 3 ”መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሀይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ” ይላል…በሀገራችን ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በወታደራዊው ደርግ እንዲሁም አሁን ስልጣን ላይ ባለው ወያኔን ጨምሮ ሁሉም ሀይማኖቶች ከመንግስት ጣልቃገብነት ነፃ ሆነው አያውቁም። ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነት እና አንድነት ለብዙ ሀይማኖቶች መሰረታዊ እሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶች ላለፉት 22 ዓመታት በዘረኛው የወያኔ መንግስት እየተሸረሸሩ እና እየተመናመኑ ዛሬ ከነአካቴውም ለመጥፋት ተቃርበዋል፡፡ ስለመሰረታዊ የሰው ልጅ መብት እና ነጻነት እንዳይወራ የወያኔ የጥይት አፈሙዞች በእያንዳንዱ ሰው እና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ተደቅኗል፡፡የእምነት ቦታዎችንም ሳይቀር በመድፈር ህዝበ-ምዕመኑ የኔ የራሴ የሚለው የአምልኮ ቦታ እና የአምልኮ ስርዓት እንዳይኖረው እያደረገ ነው።

ወያኔ አምባገነናዊ ስርአቱን ለማስቀጠል ሲል የዕምነት ተቋማትንና መሪዎቹን በቁጥጥሩ ስር ሲያደረግ ኖሯል፡፡ ይህ አንባገነናዊ ድርጊት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይም ተግባራዊ በመደረጉ ምዕመናኑ የመንግስትን ድርጊት በመቃወም ላለፉት ሁለት ዓመታት ጠንካራ ሰላማዊ ትግል አድርገዋል፤ እያደረጉም ይገኛሉ፡፡ መንግስት አለመግባባቱን ለመፍታት የቀረቡለትን ሶስት ጥያቄዎች ከመፍታት ይልቅ በማን አለብኝነት የትግሉን ግንባር ቀደም መሪዎች ከማሰር ባለፈ በምዕመናኑ ላይ ኢሰብአዊ ጥቃቶችን ማድረሱ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡  ለወያኔ ህገመንግስትን የመጣስ ድርጊት አዲስ ባህሪው ባይሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣውን ማጠናከሩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡ ይህ የመንግስት ሀይሎች ድርጊት ችግሩን ከማባባስ ባለፈ የሚያመጣው መፍትሄት አይኖርም፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላነሷቸው ግልፅ የመብት ጥያቄዎች ብልሀት የተሞላበት ምላሽ መስጠት ያቃተው ወያኔ እየወሰዳቸው ያሉት ኢህገመንግስታዊ እርምጃዎች፤ በሙስሊሙ ሕብረተሰባ ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ከመንግስት ሌላ ተጠያቂ የሚደረግ አካል አይኖርም፡፡ ስለሆነም ይህ አይነቱ ህገወጥና ሀላፊነት የጎደለው ድርጊት እንዳይቀጥል ማድረግ ከተጠያቂነት ያድናል፡፡ መንግስት የተበደሉ ዜጎችን ቅሬታ በማጣራትም በህገወጥ ድርጊት በፈፀሙ ሃይሎቹ ላይ በአፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ሲከሰቱ ሃይማኖታዊ ወይም መንፈሳዊ የሆኑ መፍትሔ ማፈላለግ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡ በእምነት ተቋማት ውስጥ ለሚነሱ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መልስ መፈለግ ችግሩን ከማስፋፋትና ወደ አላስፈላጊ ውዝግቦች ከመክተት ውጪ የሚፈጥረው በጎ ለውጥ አይኖርም፡ ፡ የቤተ-ክርስቲያን አለመግባባቶችን ቤተ-መንግስት ለማስታረቅ ሲሞክር ምን ይፈጠር እንደነበር ታሪክ ደጋግሞ አሳይቶናል። በቅርቡ እንኳ በዋልዳባ ገዳምና በምእመናኑ ላይ የተቃጣው ሰይጣናዊ፤ በትዕቢትና በማናለብኝነት የእምነትን ቀይ መስመርን በመጣስ የተወሰደ ጥቃት ሁለቱንም የወያኔ ቁንጮዎች መለስ ዜናዊንና አባ ፓውሎስን ግብአተ መሬት ማፋጠኑ ይታወሳል። መንግስታዊ ጣልቃ ገብነቶች ከእለት ወደ እለት እየገዘፉና እየጠነከሩ ሲመጡ የችግሮች ስር መስደድም የዚያኑ ያህል እየከፋ ይመጣሉ፡፡ ስለዚህ በእስልምና እምነት ላይ እየተደረገ ያለው መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት በሀገሪቱ ህገ-መንግስት ላይ የተገለፀውን መንግስትና ሀይማኖት መለያየታቸውን የሚጥስ በመሆኑ አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ግድ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በክርስትና እምነት እንደተደረገው ሁሉ፤ የህዝበ ሙስሊሙ ፀሎትና ልመና ጣልቃ ገብተው እየበጠበጡ ያሉ አምባገነኖች ላይ መቅሰፍት እንደሚያወርድ ጥርጥር የለውም።

በአወሊያ መጅሊሱ እንዲወርድ ሲባል የተጀመረው ሰላማዊ አቀራረብ አሁን ከአዲስ አበባም አልፎ ወደሌሎች ክፍለ ሀገራት  ደርሶ መሳሪያ አማዟል፡ ፡ ለዚህም ማሳያ በቅርቡ በመዲናችን አዲስ አበባ፤ ደሴና ኮፈሌ ላይ የመንግስት ሃይሎች በንፁሃን የሙስሊም ወገኖች ላይ ያደረሱት መጠነ ሰፊ ጥቃትና ግድያ መጥቀስ ይቻላል። በዚህም ሊያበቃ እንደማይችልም ሁኔታዎችን ተመልክቶ መገመት ይቻላል፡፡ ፖለቲካዊ ማንነት ባላቸው ግለሰቦችና ካድሬዎች ቤተ-እምነቶችን መምራት የኋላ ኋላ ይዞ የሚመጣው መዘዝ ሀገራዊ ቀውስ ነው፡፡ ለተቃውሞ የወጣውን ህዝበ ሙስሊም ሰለፊያ በሚል ቅፅል መጠሪያ ስም በመስጠት ዓላማቸውንም ከሽብር ጋር በማያያዝ መፈረጅ ሁኔታውን ከማባባስ ውጪ ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም፡፡

ሕጋዊ መብትን በግልም ሆነ በኅብረት መጠየቅ ሽብርተኛ አያደርግም፤ ሽብርተኛ የሚያደርገው መብታቸውን የሚጠይቁትን መግደል፣ መደብደብና ማሰር ነው፤ ዓለማዊውን ሥርዓት የማይነካውን፣ ከአምላኬ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር የመረጥሁትን መንገድ አክብሩልኝ፤ በሌላ መንገድ ወደአምላኬ እንድሄድ አታስገድዱኝ ማለት ሽብርተኛነት አይደለም፤ ሽብርተኛነት የሚሆነው በሰዎች ላይ ባዕድ የሚሉትን እምነት መጫን ነው፤ ሽብርተኛነት የሚሆነው አትጫኑብኝ እያለ በሰላማዊ መንገድ የሚጮኸውን ሰው መደብደብ፣ ማሰርና መግደል ነው፤ ሽብርተኛነት የሚሆነው የሰዎችን ቅዱስ ቦታ በጥይትና በደም ማርከስ ነው፤ ሽብርተኛነት የሚገለጠው ሰላሜን ጠብቁልኝ እያለ በሚጮኸው ሰው ሳይሆን በጉልበቱ ብቻ ተማምኖ ሰላምን በሚያደፈርሰው ነው፤ ሕዝብ ሰላምን ሲያገኝ ይሠራል፤ ያመርታል፤ ኑሮውን ያሻሽላል፤ ይዝናናል፤ ይህ ሁሉ ጥጋብን ያመጣል፤ ሲጠግብ የሚያስቸግረውን እንዳይጠግብ መበጥበጥ የሚፈልጉ አይጠፉም፡፡ ጮሌነት ዕድሜ አለው፤ የጮሌነት ዕድሜ በጣም አጭር ነው፤ ነገር ግን ጠንቁ ከነኮተቱ በልጅ ላይ ያርፋል፤ የጮሌው ኃጢአት ልጁን አዋርዶ ያቃጥላል፤ ማንም ለማንም የሚመኘው መንገድ አይደለም፡፡

ስለዚህ ሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄያቸውን ህገ-መንግስቱ በፈቀደላቸው በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ እስካቀረቡ ድረስ መንግስት አግባብነት ያለውን መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የሃይማኖቶች ነፃነትን በዚህ አካሄድ እየጨፈለቁ መሄድ ትርፉ ስርዓታዊ ኪሳራ ብቻ ነው፡፡ የሃይማኖቱ ተከታዮች ይወክሉናል ብለው የመረጧቸውን የአመራር አባላትንም ሆነ ምዕመኑን ማሰር፤ ማንገላታትና መግደል በሀገሪቱ ውስጥ ህገ- መንግስታዊነት እና የህግ የበላይነት ያለመኖሩ ማሳያ ነውና ይኼ አምባገነናዊ እርምጃ በአስቸኳይ መቆም አለበት።

ድል ለጭቁኑ ህዝበ ሙስሊም!!

ፀሃፊውን በኢሜል yentsanetgohe@gmail.com ያገኙታል።


ጋባዥ: የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የሰሜን አሜሪካ አንድነት ፓርቲ ደጋፊ ግብረ ኃይል

$
0
0

ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ

 
በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥
 
 1)የፓርላማ አባል የተከበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ 
2)የአንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነፃነት ቦርድ ሰብሳቢ እና አቶ በላይ ፈቃዱ በረዳ
 
በኢትዮጵያችን  በአቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ  እንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ… እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ስለሚያደርጉ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል። የአንድነት ፓርቲ መሪዎችን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ።   በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥
 
1)ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ 
2) ድረገጾች፥ ዘሐበሻ፣ ኢትዮሚዲያ፣ ኢትዮሚዲያ ፎረም፣ አቦጊዳ፣ ኢትዮሪቪው እና ሌሎች 
3) ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ከረንት አፌር
 ቴ
ሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥
  • ቀን፥ ቅዳሜ ነሐሴ   25 ቀን 2005 ዓ.ም. (Saturday, August 31, 2013) – ከሁለት ቀኖች በኋል!
  •  ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Estern Time)
  • በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥   267-507-0240  ይደውሉ እና    201820  ኮድ ይጠቀሙ   ውድ የድረገጾች አስተናጋጆች፥
 የጊዜ እጥረት እየተፈታተነን ነው። ስለዚኽ ይኽን ጥሪ በድረገጾቻችሁ ላይ በማውጣት የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ወገናችን ሁሉ ስለቴሌ-ኮንፍረንሱ እንዲያውቅ እንድታደርጉልን በአክብሮት ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ለቴሌ-ኮንፍረንሱ ሁለት ቀኖች ብቻ ስለቀሩን ጥሪው እንደደረሳችሁ በድረገጾቻችሁ እንደምታሰፍሩልን ተስፋ እናደርጋለን።
 እስከዚያ በአክብሮት መልካሙን እንመኛለን!

Teleconfernce


ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው

$
0
0

ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ..ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ፀሐፊን፣ ሊቀመንበሩንና የሰልፍ አስተባባሪዎችን ለማነጋገር ጥሪ እንዳቀረበላቸው ታውቋል፡፡በፀጥታ ዙሪያ ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን የሚለው የፖሊስ መጥሪያ ፓርቲው የእሁዱን ስብሰባ እንዲሰርዝ ለማግባባት ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲያቸው የእሁዱን ስብሰባ ለማካሄድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ተናግረው፤ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ ከያዙት አቋም እንደማያስቆማቸው ለኢሳት ተናግረዋል፡፡በታሪክ፣ በሞራልም ሆነ በህግ ተጠያቂ የሚያስደርገን ነገር ስለሌለ ሰላማዊ ሰልፉ የማይቀር መሆኑን የፓርቲው አመራር ተናግረዋል፡፡በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማህበራት ፍቃድ ጽ/ቤት የፓርቲውን ሰልፍ ህገወጥ ነው ማለቱን አስመልክቶ የተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ‹ሕጋዊ ወይም ህገ ወጥ› የሚባል ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡የፓርቲው የሰልፍ አስተባባሪ ዝግጅት ክፍል ለእሁድ ሰልፍ የሚያደርገው ዝግጅት ከገዥው ፓርቲ የተለያየ ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡መብራት በተደጋጋሚ የመጥፋት ተግባርና በመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ በፀጥታ ሀይሎች ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡የኢህአዴግ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ ህዝቡ ለእሁድ የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ እንዲወጣ ቅስቀሳ ማድረግ ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡መንግስት እያስተባበረ የሚገኘው የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ ህዝቡ አክራሪነትን እና ጽንፈኝነትን ለማውገዝ በሚል የተጠራ ቢሆንም እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ ያለመ እንደሆነ የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ሁለት ቀን ብቻ የቀረው የእሁዱ የመንግስትና የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያጋጠመ ክስተት ተደርጎ ታይቷል፡፡


ወታደራዊ ትጥቅ ማ ምረቻ ፋብሪካ በቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት

$
0
0

576820_643438789017118_1777115518_nሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ..

ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም፡፡

በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል፡፡


አንድነት ፓርቲ በአሜሪካ ኤምባሲ ቅር መሰኘቱን ገለፀ

$
0
0

11አንድነት ለዲሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ቅር መሰኘቱን ገለፀ። ፓርቲው በኤምባሲው ላይ ቅሬታውን የገለፀው የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆነው ወጣት ዳንኤል ተፈራ ለፓርቲው የስራ ጉዳይ ለአንድ ወር ወደ አሜሪካ እንዳይሄድ በመደረጉ ነው.. የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳና ወጣት ዳንኤል ተፈራ በጋራ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት ኤምባሲው ቪዛ በመከልከሉ የፓርቲውን ስራ መስተጓጎሉን ተናግረዋል። ወጣት ዳንኤል ወደ ዋሽንግተን ለማቅናት ግብዣ የቀረበው አሜሪካን ሀገር በሚገኙ የፓርቲው ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች አማካኝነት ሲሆን በቅርቡ ፓርቲው የጀመረው ‘‘የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት’’ የተባለውን ሕዝባዊ ንቅናቄ በአሜሪካን ተገኝቶ ገለፃ እንዲያደርግና ድጋፍ የማሰባሰቡን ተግባር ለማጠናከር ነበር። ይሁን እንጂ ኤምባሲው የዳንኤል ተፈራን ወጣት መሆን በማየት ብቻ ቪዛ መከልከሉ የኤምባሲው የስራ ኃላፊዎችን የአመለካከት ችግር ማሳያ መሆኑን ወጣት ዳንኤል የገለፀ ሲሆን በቀጣይም ፓርቲው በዚሁ ጉዳይ ላይ ኤምባሲውን ማብራሪያ እንደሚጠይቅም አመልክቷል። ወጣት ዳንኤል ቪዛ ከማግኘቱ በፊት ደመወዙን፣ የቤት መኪና እና የቤት ካርታ በቅድመ ሁኔታ እንዲያቀርብ መጠየቁ አሳዛኝ መሆኑን ገልጿል። ‘‘እኔ ቤተሰብ ያለኝ ሀገሬን የምወድና ከፓርቲው ተልእኮ ውጪ አንድም ቀን በአሜሪካን ሀገር የመቆየት ፍላጎት የለኝም’’ ያለው ወጣት ዳንኤል በኤምባሲው ድርጊት ማዘኑን ገልጿል። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ ዕድሜ ልክ የተፈረደበት አቶ አንዱአለም አራጌ ቪዛ መከልከሉ አይዘነጋም። ጉዳዩን በማስመልከት የኤምባሲውን የህዝብ ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ሮበርት ፖስትን ለማነጋገር ብንሞክርም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ባለመስራቱ ልናገኛቸው አልቻልንም።



ሰበር ዜና ተወሰነ አላሁ ዓክበር የትኛውንም አይነት አክራሪነት ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደሚያወግዝ በእሁዱ ሰልፍ በአደባባይ ያስመሰክራል!

$
0
0

posted By Issa Abdusemed ጁምአ ነሐሴ 24/2005    ‹‹አክራሪነትን ሕገ-መንግስቱ ቢፈቅድ እንኳን አንቀበለውም!›› ኮሚቴዎቻችን
ለዚህች አገር ሰላም እና ደህንነት መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገን ከአክራሪነት ሊርቅ ይገባዋል!
አክራሪነት ማለት ድንበር ማለፍ ማለት ነው… አክራሪነት ዜግነት የለውም፣ በእምነት አይወሰንም፣ በቦታ አይከለልም፣ በሐገር አይለይም፡፡ በግል፣ በህብረት፣ በመንግስት ደረጃ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ አክራሪነትን ከማንም በፊት ያወገዙት ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ስለሆኑና የጥፋት አቅጣጫ መሆኑን ስለጠቆሙን አክራሪነትን ለመቃወም ከማንም በፊት ቀድመን የምንገኘው እኛው ነን፡፡ አክራሪነትን የምንቃወመው መሰረታችን ለአክራሪነት የሚመች ስላልሆነ ነው፡፡ ተቻችሎ መኖርም ቋሚ አጀንዳችን ስለሆነ ነው፡፡ ለዚህች አገር በሰላም መኖር ሁሉም ወገን ከሁሉም አይነት አክራሪነት ርቆና እውነተኛ የሰላም ፈላጊ ሆኖ መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ህዝቦች በጋራ በተግባቡበት ህግ በሰላም የመኖር፣ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር የአስተምህሮታችን መሰረት ሲሆን በሚሊዮኖች ፊርማ ወክለን በግፍ የታሰሩትን ኮሚቴዎቻችንን ጨምሮ መስዋእትነት የምንከፍልለት ሰላማዊ ትግላችን በኢትዮጵያ የሃይማኖት ነፃነት እና የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር ሂደት አካል ነው፡፡ አክራሪነት ማለት ግን ዛሬ ፖለቲከኞች እንደሚጠቀሙት ተለክቶ እንደሚሰፋ ልብስ ሊያጠቁት የሚፈልጉትን አካል ሁሉ በልክ በልኩ አሰፍተው አልብሰው የሚያጠቁበት መቆመሪያ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሁለት አመታት ስንቃወም የኖርነውም መንግስታዊ ሃይማኖት (አህባሽ) በመንግስት ሙሉ እቅድ እና ትግበራ አማኞችን ለመከፋፈልና የእርስበርስ ፀብ ለመፍጠር ከሌሎች ሃይማኖቶችም ጋር አብሮ የመኖር ገመድን ሊበጥስ ‹‹ከመንግስት የወረደ ነውና ተቀበሉት›› ተብሎ ስለተጫነብን ነው፡፡ መሪዎቻችንም ሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ንፁሃን በእስር የሚማምቅቁት ብሎም በርካቶች የሞቱትና የተደበደቡት ‹‹እኔ ከመረጥኩላችሁ ውጭ ትክክለኛ እምነት የለም›› የሚልን አክራሪነት በመቃወም እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ መንግስት የእምነት መብት መጠየቃችንን አክራሪት ሲል ፈርጆታል፡፡ ይህ መብት መጠየቅን በአክራሪነት የሚፈርጅ ፖለቲካዊ አክራሪነትን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ በሃገራችን ተጨባጭ ፅንፈኛ የፖለቲካ አካሄድ የትክክለኛው አክራሪነት መፈልፈያ መሆኑን እያየን ነው፡፡ በዚህ አክራሪነት ከማንም በላይ የተጠቃነው እኛ ነንና አክራሪነትን በፅኑ እናወግዘዋለን፡፡ ይህንንም ለማሳየት ነው የእሁዱን ሰልፍ የምንሳተፈው፡፡

የነሃሴ 26 ሰልፍ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቹ ጋር የሚገናኝበት፣ ስለሃገሩ ስላም ያለውን ቀናዒነት የሚያሳይበት መድረክ በመሆኑ ሙስሊሙ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቹ ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ አድራሻ በመለዋወጥ ጠንካራ አብሮነትን የሚያጠናክርበት ነው፡፡ ትናንት የጥምቀት በዓሉን ታሳቢ በማድረግ የተቃውሞ መርሃግብሩን የከለሰለትና ቦታ ከቀየረለት ህዝበ ክርስቲያን ጋር ነሃሴ 26 በአንድነት ቆሞ አክራሪነትን በጋራ እያወገዘ ሰላማዊነቱን ያስመሰክራል፡፡ በተጨማሪም የነሃሴ 26 የቅዋሜ መድረክ ከሁሉም እምነት ተከታዮች ጋር ያለንን ትስስር የምናጠናክርበትና ሰላማዊ የመብት ጥያቄአችንን ይበልጥ የምናስረዳበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ሰልፉን እንደጠራው የሚነገርለት የሃይማኖት ጉባኤ ውስጥ ያሉ የሃይማኖት አባቶች ለዚህች ሃገር እውነተኛ የሰላም አስተማሪና ተጠሪ መሆናቸውን፣ ለችግሮች መፍትሄ በማፈላለግ በመሰለፍ ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ የምንልበትም ዕለት ነው፡፡

ሰልፉ የሃይማኖቶች ጉባኤ ከሚባለው ተቋም ጋር ህዝብ የሚኖረው የመጀመሪያ የአደባባይ ግንኙነት በመሆኑ የተቋሙን አሰላለፍ በተግባር ለማየት ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ በመሰረቱ የሃይማኖቶች ጉባኤ መንፈሳዊ መሪዎች ያሉበት በመሆኑ ‹‹አክራሪነትን እናወግዛለን›› በሚል መሪ ቃል በጠሩት ሰልፍ የአደባባይ ውንብድና ቢፈፀም በወከላቸው አማኝ እና በተወከሉለት እምነት ላይ ታላቅ ክህደትን መፈፀም ነው የሚሆነው፡፡ መንግስትም ይህንን ሰልፍ ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማዋል ከተሯሯጠ በሃገሪቱ እምነት የሚጣልበት ነፃ ተቋም ፈፅሞ አለመኖሩን ማስመስከር ሲሆን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ደግሞ ያለ እፍረት መደበኛ ተግባሩ እንዳደረገው ለመላው ኢትዮጵያዊ በገሃድ የሚያውጅበት አጋጣሚ ይሆናል፡፡ በዚህ አጋጣሚም መንግስት ሰልፉን ለሃገራዊ መግባባት እንዲያውለው አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ዜጎች በሃይማኖታቸው ተከብረው መብት በመጠየቃቸው ሳይሸማቀቁና ሳይበደሉ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ ለማቆየት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ መንግስት እድሉን በአወንታዊ መልኩ ሊጠቀምበት ይገባል እንላለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን ‹‹የሃይማኖቶች ጉባኤ ጠርቶታል›› ለተባለው ሰልፍ ተሳትፎ መንግስት የህዝብን ጓዳ ማስጨነቁ፣ ሰልፉን በማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በማስፈፀም በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብነቱን በግልፅ እያሳየ ነው፡፡ መንግስት ‹‹አክራሪነትን እዋጋለሁ›› በሚል ሽፋን እምነታችንን ክፉኛ ጣልቃ ገብቶበታል፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹አክራሪነትን እናወግዛለን›› በሚል ሽፋን ህዝብን በግዳጅ ጭምር በማስወጣት ይህን ሰልፍ ከሃገራዊ መግባባት ይልቅ ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት አስቦ ከሆነ ተግባሩን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ይህ ተግባር የመንግስት መዋቅር ከዚህ ቀደም ፖለቲካን ሽፋን አድርገው የሃይማኖት እና የቡድን አጀንዳን ለማስፈፀም ለሚሯሯጡ አመራሮች እንደተጋለጠ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ በሙሉ መዋቅሩ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካዊ ቁማር ለመጫወት አስቦ ከሆነ በፅኑ እናወግዘዋለን፡፡

በመሆኑም ይሄን ሽፋን ገልጠን በማውጣትና መንግስት ሊደበቅበት ያሰበበትን ካባ በማውለቅ ‹‹አክራሪነትን አዎ እናወግዛለን!››፣ ‹‹በአክራሪነት ሽፋን ግን በእምነታችን ጣልቃ መግባትንም በተመሳሳይ እናወግዛለን›› ልንል ወደ ሰልፉ እንተማለን፡፡ በሰልፉ ላይ በመገኘት መንግስት ሰልፉን ከተቀመጠለት ስያሜ ውጪ ለህገ ወጥ ተግባሩና ፖለቲካዊ ትርፍ ማጋበዣው መጠቀሚያ እንዳያደርገው እናደርጋለን፡፡ ሃላፊነት በጎደለውና ከልክ ባለፈ ንቀት የሙስሊሙን እምነት ለመበረዝ ሲሞክርና አማኙን በማንገላታት ለመፍጠር የታለመው ሀገራዊ ትርምስ አልሳካ ሲል ዛሬ አሰላለፍን በመቀየር በሃይማኖቶች ሽፋን ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት የተቀመረ ስሌት ካለ እንደማይሳካ የፊታችን እሁድ በተግባር እናስመሰክራለን፡፡ ይህን ክፉ ራዕይ ዳግም መና ለማስቀረት ዛሬም ከሃገር ወንድምና እህቶቻችን ጋር እምነትና አስተሳሰብ ሳይለየን እጅ ለእጅ በመያያዝ ለዘመናት በገዢዎች ያልተናደውን አንድነታችንን እናጠናክራለን፡፡

የነሃሴ 26 ሰልፍን ስንሳተፍ አክራሪነትን በመቃወም እና አብሮነትና ተቻችሎ መኖርን በተግባር እናሰይበታለን፡፡ ሆኖም አክራሪነትን ከመቃወም ውጭ በሰልፉ ላይ የሚስተናገዱ ማንኛውንም አይነት አፍራሽ መርሃ ግብሮች ካሉ በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ሁሌም ደጋግመን ስንገልጸው እንደነበረው ሁሉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄም ሆነ እንቅስቃሴ ሰላማዊ፣ አገራዊ እና ህዝባዊ መሆኑን እንዲሁም ይምነት እንጂ የፖለቲካ ጉዳይ አለመሆኑን እና ከመብት እና የፍትህ ጥያቄ ውጭ የተለየ መልክ እና ይዘት እንደሌለው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አሁንም ደግመን ማስረገጥ እንሻለን:: በመሆኑም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሙሉ ከእነ ቤተሰቡ ነቅሎ በመውጣት በእሁዱ የተቃውሞ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ተላልፏል፡፡ ሁላችንም እዛው እንገናኛለን፡፡ ለእለቱ ከሚቀመጠው መርሐግብር ክንውን ሳንላቀቀ የተቀመጠውን ብቻ በመፈጸም አክራሪነትን ከሌሎች ኢትዮጵያውን እህቶችና ወንድሞች ጋር በመሆን በተግባር እናወግዛለን፡፡ የእለቱን የመርሐግብር አፈጻጸም አስመልክቶ በቀጣዩ ፖስት ላይ ይመልከቱ፡፡

አላሁ አክበር!


ሰቆቃ በሰማያዊ ፓርቲ አባላቶች ላይ!

$
0
0
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፓርቲው ከወራት ጀምሮ ባቀደው መሰረት ለዛሬ ነሐሴ 26 እንዲደረግ ላቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት በቢሯቸው ተፍ ተፍ በማለት ላይ እንዳሉ በግምት 1(አንድ) ሰዓት አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የፌደራል ፖሊሶች የፓርቲውን ጽ/ቤት ከበው የእገታውንድራማ  ጀመሩ ማንም ከፓርቲው ጽ/ቤት እንዳይገባና እንዳይወጣ ከለከሉ…የእገታው ድራማ ከ20-25 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ያህል ከቆየ በኋላ የታገቱትን የፓርቲውን አመራርና አባላት እያንገላቱ “ኮድ ፖሊስ” እና “ኮድ 35″ ታርጋ ባላቸው ቶዮታ ሃይሉክስ መኪና ከተጫኑ በኋላ ወደተለያዩ ቦታዎች ተወሰዱ።ከነዚህ ውስጥ ወደ 19 የሚጠጉት የተወሰዱት ጃንሜዳ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ነው።ጣቢያው እንደደረሱ ጫማቸውን አውልቀው እንዲንበረከኩ ተደረጉ ከዛ ስልካቸውን ተንጥቀው ለደቂቃዎች አስፀያፊ የስድብ ናዳና እንግልት ወረደባቸው ይህ ከሆነ በኋላ በከብቶች ሽንትና ጭቃ ወደጨቀየው የፖሊስ ጣቢያው ጀርባ ተወስደው በደረታቸው እንዲተኙ ከተደረገ በኋላ አራት የሚሆኑት #ፌደራልፖሊሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ደበደቧቸው እነርሱ በስቃይ እያቃተቱ በተኙበት ትተዋቸው ሄዱ።ከአሰቃቂው #ድብደባ በኋላ አስራዘጠኙም በቪዲዮ እንዲቀረፁ ተደረጉ የሰማያዊ ፓርቲ አርማ ያለበትን ቲሸርት እንዲያወልቁም ተደርጉ ቲሸርቱን ሁለተኛ እንዳይለብሱ እና ወደ ፓርቲው ፅ/ቤትም ሁለተኛ እንዳይሄዱ ዛቻ በተቀላቀለበት ቃና ማስተጠንቀቂያ ተሰጣቸው።ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ከሌሊቱ 6፡00 ከጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ተለቀቁ በእልህና በድብደባ ስቃይ እየተወለካከፋ ተደጋግፈው ከጣቢያው ወጡ። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የደመቀ ሰልፍ እናደርጋለን ብለው ባሰቡበት የዛሬዋ እለት በግፈኛው አገዛዝ የደረሰባቸውን ድብደባ በየቤታቸውና ክሊኒኮች ተኝተው በማስታመም ላይ ይገኛሉ። (ድብደባ ከደረሰባቸው የአይን እማኞች እንዳገኘውት)
#ሀናመታሰቢያ 26/12/05

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክርቤት አስቸኳይ ስብሰባ እያደረገ ነው

$
0
0

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዛሬ ነሃሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ አንድነት የጀመረውን የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ክንውኖች ገምግሟል… ምክርቤቱ ቀሪዎቹ የንቅናቄው መርሀ ግብሮች በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ከእስካሁኑ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ 33ቱ ፓርቲዎች የአንድነት ፓርቲን ህዝባዊ ንቅናቄ በመቀላቀል የመስከረም 5ቱን ሰላማዊ ሰልፍ በጋራ ለማካሄድ መወሰናቸውንም ምክር ቤቱ በደስታ ተቀብሏል፡፡

ብሔራዊ ምክርቤቱ ከሰአት በኋላ በሚያደርገው ስብሰባ በመጪው መስከረም ወር መጨረሻ ለሚደረገው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ የሚቀርቡ ሰነዶች ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍም ይጠበቃል፡፡   DSC02371DSC02372DSC02373

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5537#sthash.5OXhSB2w.vpur0rbk.dpuf


Semayawi attacked, beaten up and ransacked.

$
0
0

by Abebe Gellaw

In the evening of Saturday August 31, Semayawi Party headquarters around Ginfle, Addis Ababa, was buzzing like a bee hive as nearly one hundred party activists and organizers were busy making posters…

September 1, 2013

, writing slogans, stacking flags and other paraphernalia needed for a colorful rally. They were making the final push for a peaceful demonstration they had planned to hold the next morning with their supporters.Semayawi attacked, beaten up and ransacked

These peaceful and law-abiding citizens were doing what true political activists were supposed to do. They wanted to demand justice and freedom. They wanted to petition their rulers to respects the rights of citizens who are being routinely abused, tortured and killed in broad daylight. They only wanted to ask the thuggish TPLF regime to free all prisoners of conscience jailed on trumped-up terrorism and treason charges. They wanted to demand the TPLF to respect its own constitution. They were not preparing to commit acts of terrorism or bank robbery.

Suddenly there was a blackout. Electricity to Semayawi’s headquarters was cut off. Apparently hundreds of heavily armed ‘federal police’ officers had already besieged the office like terrorists.

Yidenekachew Kebede, the party’s legal affairs head and coordinator of the rally was heading to his office. ESAT reached him in good time on his cell phone. He was describing the situation in detail. He was very upset that such a criminality happens with impunity. He was outraged that the TPLF is treating Ethiopians worse than prisoners of war in their own country.

The young lawyer was outraged that the constitution, which the TPLF never respected, was being violated by armed thugs and criminals again. It was another evidence of lawlessness and tyranny that the TPLF has imposed on the people of Ethiopia. Those who were eager to demand freedom and justice for their people became victims of criminality. While he was telling ESAT that his colleagues and friends were under siege, a federal police officer snatched his phone and the line was cut off. Apparently he was detained.

TPLF federal squad broke into the office and ransacked and beat Semayawi’s leaders and members. The party’s chairman Eng. Yilkal Getnet was also arrested and taken to a police station around Gedam Sefer. The thugs reportedly targeted everyone and even savagely attacked and kicked women. They detained all of Semayawi’s operatives found on the party’s premises for hours, kicked and tortured them. Scores of people were even made to roll over mud and dung in a bid to humiliate and degrade them. They were stat at and insulted by TPLF’s thugs.

According to Eng. Yilkal, he was released after a few hours. Other members who were also said to have been roughed up, beaten up and tortured were also freed. But the headquarters has reportedly been trashed. Documents, equipment, and all the materials prepared for the rally were taken away by the federal squad.

Ethiopians in the Diaspora has been expressing outrage on Facebook and Paltalk rooms. What has been the focus of angry discussion is how long the state-sponsored terrorism can go on. The decision to launch an illegal attack against a political party operating legally is another affront to law and order. TPLF’s thuggery and lawlessness has posed serious challenges to every law-abiding citizen. People are abused and tortured without any ground.

Semayawi is a relatively budding political party that should have been accorded protection. But TPLF’s paranoid has reached a critical and dangerous point. The more cornered it is, the more dangerous it is becoming. The attack against Semawi only reveals the level of fear gripping the TPLF and its cronies.

In a press release it issued, Semayawi has vowed to press for justice and rule of law. It emphasized that nothing will distract it from making demands and voicing the concerns of the people of Ethiopia.

In the meantime, Muslim Ethiopians are also being hunted down across the country. TPLF organized a rally in the metropolis on the day and at the venue where Semayawi had planned to stage a protest demonstration. The worst part is that TPLF is trying to create religious conflict among Christians and Muslims. The two religions have co-existed harmoniously for over a millennium. The futile efforts only reveal the fact that TPLF is desperate to survive.

No matter what the TPLF does, the struggle for equality, dignity, justice and freedom continues…


Ethiopia arrests top security official His arrest may be a prelude to the arrest of Azeb Mesfin, aka “Mother of Corruption”

$
0
0

Her liutenants are being rounded up for corruption  and it may be a matter of time before she joins them at Kaliti..

untitled
August 31, 2013

WASHINGTON, DC – A top Ethiopian security official has been arrested on corruption charges, a radio affiliated to the ruling party said on Friday.

The official, Woldeselassie Woldemichael, a close friend and confidant of Azeb Mesfin, the widow of the late Prime Minister Meles Zenawi, was thrown into jail as part of the ongoing hunt for officials who have amassed wealth on grounds of corruption.
Woldeselassie was a close friend of Gebrewahd Woldegiorgis, former deputy head of Revenue and Customs Authority, who has been in jail for months accused of corruption.

Observers say the arrest of the ranking security official could be a prelude to the arrest of Azeb, who is billed “Mother of All Corruption” in the country.

“It is a matter of time before Azeb joins the ranks of the corrupt officials now behind bars,” a source said.

Azeb was recently relieved of her post as CEO of EFFORT, the business oligarchy that has never been audited despite comprising major multi-billion-dollar companies such as Sur Construction, Mesfin Engineering, Almeda Textiles, and nearly two dozen business enterprises that have been the cash cow of the Meles-Azeb family and their inner-circle liutenants.

When Meles Zenawi was alive, Azeb was the most feared and powerful woman who at party meetings lashed out at current security chief Getachew Assefa for corruption and extravagant lifestyle. Azeb had insisted that Getachew should be fired and her favorite, Woldeselassie, promoted.

The once powerful and aggressive woman is slowly turning into the most vulnerable following the death of her husband in August last year. She now doesn’t have any known official job. Critics have been blaming her for being corrupt on the one hand and incomptetent on the other that she can’t work as CEO of EFFORT. Though not officially reported, there were anti-Azeb protests at a number of EFFORT-affiliated companies that called for her removal.

Azeb has been counting on the political clout of Abai Woldu, a TPLF politburo official who is at loggerheads with the Addis-Ababa-based Getachew Assefa and behind-the-scene powerful man, Debretsion Gebremichael, who is deputy chairman of TPLF and minister of Communication and Information Technology.

In reality, many consider Debretsion as Number One in the power hierarchy, and his side leading the anti-corruption campaign means the days of Azeb as the spoilt brat of the palace are over.


Viewing all 931 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>