Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all 931 articles
Browse latest View live

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ

$
0
0
Aug 16.2013   በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በኖርዌይ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት  የኢትዮጵያ ስደተኛ ማህበር በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበረሰብ የተገኙ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ  ከየድርጅቶቻቸው ተወክለው የተገኞት ተወካዮቻቸውም ንግግር አድርገዋል ..
የሰላማዊው ሰልፎ ዋና አላማ  ሃገራችንን ኢትዮጵያ ለሐሃያ ሁለት አመታት በዘረኛውና ከፋፋዮ ወያኔ ገዢ መንግስት ያደረሰባትን የዘር ማጥፋት፣ ከትውልድ ቄያቸው በግዳጅ ማፈናቀል ፣የሐይማኖት ነጻነት አለመኖር ህዝቦቿም ወደ ማይወጡት ችግር ውስጥ በማስገባት ለስደትና ለመከራ በመዳረግ ከዛም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋና ግድያ እንዴሁም በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የሚያደርሰውን እስር፤ ድብደባ ፤ እንግልት በመቃወምና  የኖርዌ መንግስት ከአምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ጋርየምታደርገውን  ግኑኝነትና የምትሰጠውን እርዳታ እንድትመረምር  የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር።
በፕሮግራሞ ላይም ከኖርዌይ ፖለቲከኞች የተለያዩ ፓርቲዎች ተጋበዥ ሲሆን ሓገራቸው በአሁን ሰአት የምርጫ ጊዜ ስለሆነ ጥቂቶቹ ሊገኙ ስላልቻሉ በቴሎፎን ድጋፋቸውን ገልጸዋል  ከመሐከላቸውም  ከቬንስትረ ፓርቲ ወኪላቸውን በመላክ በኢትዮጵያ መንግስት ያላቸውን ተቃውሞና ለሰላማዊ ሰልፈኛው ድጋፋቸውን  በላኩት መልእክተኛ አስነብበዋል በመጨረሻም ከዲቬሎፕመት ፈንድ ተወካይ የመጣው ባለስልጣን አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላ መልእክታችንን ተቀብለዋል።
በመዝጊያውም  የተለያዩ መፈክሮች ከተሰሙ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ እንደ ሐገራችን  መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኛውን በድብደባና የገባበት ገብቶ ለመያዝ በማሳዳድ  ሳይሆን በዲሞክራሲ መብታችን የፈለግነውን ተናግረንና ተቃውመን በሰላም ተጠናቋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይም ከተሰሙት መፈክሮች በጥቂቱ,TPLF is evil, There is apartheid in Ethiopia, Don’t remove indigenous people from their livelihood, We need freedom of religion., Regime change is needed in Ethiopia now, We need freedom of speech, ድምጻችን ይሰማ እኛ ሙስሊም ክሪስቲያን ኢትዮጵያኑች አንድ ነን አንለያይም , ሞት ለወያኔ  በሚሉ መፈክሮች ያሸበረቀና ሌሎችንም መፈክሮች ያካተተ ነበር። ሰላማዊ ሰልፉም በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ kl 13; 00 ተጀምሮ በ 14፡30 ተጠናቋል ቸር ያሰማን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር
እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌይ
16.08.2013


ለአቶ መለስ ሙት አመት መታሰቢያ የመንግስት ሰራተኞች በግድ እንዲገኙ ታዘዙ

$
0
0

576820_643438789017118_1777115518_n

 ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል በልዩ ልዩ…
ፕሮግራም ታስቦ እንደሚውል ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ምሽትና ነገ ሻማ በማብራት እንዲዘክሩት ታዘዋል።
አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ኢቲቪ አቶ መለስ ዜናዊ ከተናገራቸው ንግግሮች መካከል እያለ ሲያቀርብ መሰንበቱ እንዳሰለቻቸው ተናግረው፣ የፓርቲው ካድሬዎች በየመስሪያ ቤቱ የሚገኙ ሰራተኞች በግድ ተገኝተው እንዲዘክራቸው ማስፈራሪያ አዘል ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ነሃሴ 7 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ የመለስ ዜናዊ የአረንገዴ ልማት ማዕከል የመሰረት ድንጋይ በአድዋ
ፓርክ የተጣለ ሲሆን የዚህን ፕሮጀክት ወጪ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳዳር ለመሸፈን ቃል መግባቱን መዘገባችን ይታወቃል።
ከሃያት ሆስፒታል ፊት ለፊት ማረፊያውን የሚያደርገው ማዕከሉ ከ100 ሄክታር በላይ ስፋት ሲኖረው ፥ በተለያዩ
የአረንጓዴ ዕፅዋት በመሸፈን በውስጥ ትላልቅ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካትታል ተብሏል።
ባለፉት 15 ቀናት የአዲስአበባና የክልል ከተሞች ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ዕለቱን ለማሰብ የችግኝ
ተከላ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን መንግስትም በዚህ አጋጣሚ የመለስን ሌጋሲ ለማስቀጠል የገባውን ቃል ዳግም
ያደሰበት አጋጣሚ መሆኑን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሲናገር ከርሟል።
አቶ መለስ ዜናዊ ታምመው በሕክምና ሲረዱ መቆየታቸው በከፍተኛ ሚስጢር ተይዞ ከቆየ በኃላ ነሃሴ 14 ቀን 2004
ዓ.ም መሞታቸውን መንግስት በይፋ ማመኑ የሚታወስ ነው፡፡
ገዢው ፓርቲ የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ እየተጠቀመበት ነው በሚል ሲተች ቆይቷል። አቶ መለስ በኢኮኖሚው ዘርፍ መጠነኛ ለውጥ እንዳመጡ ቢነገርላቸውም፣ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት በማዳከም፣ አገሪቱን ወደብ አልባ በማድረግና የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ይወቀሳሉ። በህይወት በነበሩበት ጊዜ በተለይም ኢፈርት የተባለ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ተቆጣጥሮ ዬያዘ የንግድ ኩባንያ እንዲቋቋም በማድረግ አንድን ብሄር ብቻ ለመጥቀም ተንቀሳቅሰዋል እየተባሉ በተቃዋሚዎቻቸው ይተቹ ነበር።
ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመለስን ፋውንዴሽን በበላይነት እየመሩ ይገኛሉ።

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ሊፈቱ ይሆን?

$
0
0

ዘጋቢ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስ  በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሽብርተኝነት ክስ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት አራቱ ኢትዮጵያውያን መሀከል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ… ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌና አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር በ2004 ዓ.ም ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ምላሽ ሳያገኙ ለረዥም ጊዜ መቆየታቸው ሲያነጋግር ሰንብቷል፡፡ በተለይ ሲውዲናውያኑ ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያውያኑ ጋር በተመሳሳይ ወቅት ይቅርታ ጠይቀው አፋጣኝ ምላሽ ማግኘታቸውና በአንጻሩ የእነውብሸት ይቅርታ ከአመት በላይ መዘግየቱ ተገቢ አለመሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ከአንድ አመት በላይ ቆይታ በኋላ ሐምሌ 25 2005 ዓ.ም የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ማህተም አርፎበት ለወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ በተላከ ደብዳቤ የይቅርታ ጥያቄያቸው ለፕሬዝዳንቱ ቀርቦ ውድቅ መደረጉ ተገልጾላቸዋል፡፡ ወ/ሮ ሂሩት ከእነ ውብሸት ጋር ባንድ መዝገብ ተከሰው 19 አመት የተፈረደባቸው ሲሆን የይቅርታ ጥያቄውንም ያቀረቡት በተመሳሳይ ወቅት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ለጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ለአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር የደረሳቸው ደብዳቤ አለመኖሩን አረጋግጠናል፡፡

የወ/ሮ ሂሩት ይቅርታ በፕሬዝዳንቱ ውድቅ መደረጉን አስመልክቶ ልጃቸው ፍጹም መሰለ እናቱ ከተፈረደባቸው በኋላ ይግባኝ ከማለት ይልቅ ይቅርታ መጠየቅ የወሰኑበት ምክኒያት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ቀርበው “እንኳን ሀገር ውስጥ ያሉት ውጪ ያሉትም ቢሆኑ ዛሬ ይቅርታ ከጠየቁ ከነገ ጀምሮ ነጻ ናቸው” የሚል ቃል መግባታቸው እንደሆነ ገልጾ ይግባኝ የምንልበት አማራጭም አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገቡት ቃል በተቃራኒ ይቅርታው ውድቅ ተደርጓል መባሉ እንዳሳዘነው ተናግሯል፡፡ ፍጹም አክሎም “ለሲውዲናውያን የተሰጠው ዕድል ለኢትዮጵያውያን ጨርሶ ይከለከላል የሚል ዕምነት ስለሌለን የይቅርታ ጥያቄውን በድጋሚ በሽማግሌዎች በኩል እናቀርባለን” ብሏል፡፡

የአቶ መለስ ዜናዊን ሙታመት አስመልክቶ በርካታ እስረኞችን ለመፍታት መንግስት በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ያረጋገጡት ምንጮቻችን ጋዜጠኛ ውብሸትና አቶ ዘሪሁን ደብዳቤ ያልደረሳቸው ከሚፈተቱት እስረኞች ዝርዝር ውስጥ ገብተው ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡


የአልቃይዳው አመራር ሙሀመድ አልዛዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

$
0
0

የአልቃይዳው አመራር ሙሀመድ አልዛዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለየግብፅ የፀጥታ ሀይሎች የአልቃይዳ ከፍተኛ አመራርና በመስከረም አንዱ ጥቃትና በለንደኑ የትራንስፖርት ጥቃቶች እጁ እንዳለበት የሚታመነውን የአይማን አልዛዋሪን ወንድም መሀመድ አልዛዋሪን በጋዛ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ገለፁ…

አሸባሪው መሀመድ አልዛዋሪ  የማሀመድ ሙርሲ ደጋፊ  ሲሆን በግብፅ ውስጥ አሁን ባለው ተቃውሞ ውስጥም ተሳታፊ ነው ፡፡

በግብፅ ካይሮ ከተማ በ1951 የተወለደው መሃመድ አልዘዋሪ ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር በ1980ዎቹ አጋማሽ በፓኪስታን የተገናኙ ሲሆን የአልቃይዳ መረብ ዋና አስተባባሪና የቢላደን ቀን እጅ እንደነበርም ይታመናል፡፡

መሃመድ አልዘዋሪ በ1999 እ.ኤ.አ በግብፅ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን በኬንያና ታንዛኒያ የአሜሪካ ኢንባሲዎች ላይ ለደረሰውም ጥቃት ተጠያቂ ነው ይባላል፡፡

የአክራሪው ጂሀዲ ሳላፊስት ቡድን መሪ የሆነውን መሃመድ አልዘዋሪን እ.ኤ.አ በ2001  አሜሪካን ካወጣቻቸው እጅግ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ይገኝበታል፡፡

ምንጭ፡-ሜይል ኦን ላይን


በውቀቱ ስዩም – ስለ ድምፃዊ ኢዮብ መኰንን ሞት ከተናገረው

$
0
0

2

 ከጥቂት አመታት በፊት ባንድ የበጎ አድራጎት ትርኢት ላይ ለመሳተፍ፣ከዘፋኞች ጋር ወደ ደሴ ተጉዠ ነበር፡፡የተሣፈርንበት አውቶብስ ጉንጫቸውን በጫት አሎሎ በወጠሩ ዘፋኖች ተሞልቷል…ዘፋኞቹ ሲሻቸው ይተራረባሉ፣ ሲሻቸው ይጮሃሉ፣ይጨፍራሉ፡፡የአውቶብሳችን ሽማግሌ ሹፌር ሳይቀር፣ አልፎ አልፎ መሪውን እየለቀቀ በማጨብጨብ በ‹‹ቅወጣ›› ከዘፋኞች እንዳማያንስ በማሳየት ላይ ነበር፡፡በጫቱም፣ በጭፈራውም የሌለበት ድምጻዊ ኢዮብ መኮንን ብቻ እንደሆነ ተመለከትሁ፡፡ በርጋታ ተቀምጦ፣ ባውቶብሱ መስኮት አሻግሮ፣ የሚሮጡ የግራር ዛፎችን ይመለከታል፡፡ልዩነቱ ግልጽ ነበር፡፡ ድሮ ድሮ፣ኢዮብ መኮንን አቤሴሎም የሚዘናፈል ረጅም ጸጉር ያለው ጎልማሳ ነበር፡፡ድንገት ጸጉሩን ተሸለተ፡ከጸጉሩ ጋርየጥንት ባህርይውን አራገፈ፡፡ጭምት መንፈሳዊና በመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር የነደደ ምእመን ሆነ፡፡ በተገናኘን ቁጥር፣ኢዮብ ስለ ስለ እምነት እንድንወያይ ይፈልጋል፡፡ብዙ ጊዜ እምነት የሚያጠብቅ ሰው አንዳች ችግር ይኖርበታል ብየ አስብ ነበር፡፡ኢዮብ ግን እጅግ መልካም ሊባል በሚችል ሕይወቱ ይሄንን አመለካከቴን ውድቅ አድርጎብኛል፡፡ የዛሬ ሳምንት ገደማ ኢዮብ ዘፈን በመሥራት ላይ ነበር፡፡እና ላንድ ዜማው ግጥም እንደሠራለት ጋበዘኝ፡፡ከዚህ በፊት የሞርኳቸው የዘፈን ግጥሞች ስለከሸፉብኝ ግብዣውን ለመቀበልአመነታሁ፡፡ግን ደሞ ወድያው፣ በኢዮብ ድምጽ ግጥሜን ተዘፍኖልኝ ለማየት ጓጉዋሁ፡፡ውሀ ልማት አካባቢ፣ ሌክስፕላዛ ሕንጻ ሥር መኪናው ውስጥ ቁጭ ብለን ዜማዎችን ማድመጥ ጀመርን፡፡ዘፈኑ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች አብዛኞቹ ወደ መዝሙር ያዘነብላሉ፡፡ ኢዮብ ዘፈኑን ለፈንጠዝያ ሳይሆን ለስነምግባር ግንባታ ሊጠቀምበት ፈልጓል፡፡አንድ በጣ…ም ልብየሚበላ የሶማሌ ዘፈን አስደመጠኝ፡፡ ‹‹ሶማሊኛ ትችላለህ እንዴ?>> ‹‹አዎ፣ትግርኛም አውቃለሁ!›› ‹‹የት ተማርከው?>> ‹‹አስመራ፣የወታደር ልጅ መሆኔን አትርሳ›› ከዘፈን ውጭ ምን ታደርጋለህ? ‹‹ኦን ላይን፣ ጊታር እየተማርሁ ነው፡፡ቆይ ላሳይህ››…ላፕቶፑን ለኮሰና ጥቂት አስጎበኘኝ፡፡ከዛ ከመኪናው ስወርድ የመኪናው እጀታ ስለማይሠራ ወርዶ ከውጭ ከፈተልኝ፡፡ኢዮብ ብዙ ብሮችን መቆጠር የሚችል ልጅ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ይሁን እንጂ እንኳን መኪናውን የመኪናውን እጀታ ማስቀየር አልፈለገም፡፡ምናልባት፣ዓመት በአልን ጠብቆ ልብስ የሚቀይር ብዙ ሰው ባለበት አገር ውስጥ፣መኪና መቀያየሩን እንደ ኃጢአት ቆጥሮት ይሆናል፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ልኡል የተባለ ዘፋኛ ጓደኛየ የኢዮብን በድንገት መውደቅ ሲነግረኝ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ዘፋኞችና አዘጋጆች መጠበቂያው ክፍል ላይ ተደርድረው ይተክዛሉ፡፡ዘሪቱ፣ዳግማዊአሊ፣እቁባይ በርሄ፣አጃቸውን አገጫቸው ላይ ጭነው፣ተቀምጠዋል፡፡የኢዮብባለቤት ወድያ ወዲህ እየተንቆራጠጠች ታነባለች፡፡ ዛሬ ደግሞ ይሄው ሞቱን ሰማሁ፡፡ለካ፣ወደ ደሴ የሚሄደውም አውቶብስም ሆነ፣ሌክስ ፕላዛ ሕንጻ ስር፣ የቆመው ቪታራ መኪናው መዳረሻቸው አንድ ነው፡፡መቃብር!! ኢዮብ!!! በጠፈሩ ውስጥ፣ ያለ ግብ ከሚዞሩ ኮረቶች፣ያለ ምክንያት ከሚበሩ ኮከቦች በቀር ምንም የለም ብየ እንደማምን ታውቃለህ፡፡ይሁን እንጂ ለዛሬ እንኳ፣ የኔ እምነት ከሽፎ ያንተ እምነት እውነት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡በምድር ለገጠመህ መራራ እጣ ሰማያዊ ካሳ(ጉማ) እንድታገኝ እመኛለሁ፡፡


ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው! “እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” ኦባንግ

$
0
0

እሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው… ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም “እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ።
“አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እሳቱ ፊትና መልክ ይዞ ሲቀጣጠል አላነውም እንጂ በርካታ የማቀጣጠያ ቅመሞች ተዘጋጅተውለት ለመንደድ በዝግጅት ላይ ነው። መንደዱ የማይቀረው ይህ እሳት ቢነሳ የሚያጠፋው የለም” የሚሉት አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጥላቻው በሰፈር ደረጃ ከርሯል ይላሉ።

q

በየመንደሩ ህዝብ እንዲቧደን ተደርጓል። ሚና ለይቷል። አገር የሚመራው መንግሥትም ችግሩን ከመፍታትና አገሪቱን ከስጋት ከማላቀቅ “ጥሪ አይቀበልም” በሚል የሃይል ርምጃ መምረጡ ነገሮችን ይበልጥ እንዳወሳሰበ ይናገራሉ።
በየአቅጣጫው ያሉ ወገኖች ቆም ብለው ሊደበቁት ከማይችሉት ከህሊናቸው ጋር ሊነጋገሩ እንደሚገባ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ግብጾች ግብጾችን ገደሉ፣ ገና ቀውሱ ይቀጥላል። ይህ እጅግ ዘግናኝ የሆነው ቀውስ እኛ ዘንድ ሳይደርስ ወደ እርቅ እናምራ። ለእውነተኛ እርቅ ጊዜው አሁን ነው” በማለት አንገብጋቢ ያሉትን ጥሪ ያስተላልፋሉ።
“ላለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያ ላይ ከየአቅጣጫው የተረጨው መርዛማ ፖለቲካና፣ ሰብአዊነት የጎደለው አስተዳደራዊ መዋቅር የፈጠረው ውጥረት ወደ መፈረካከስ እየነዳን ነው” በማለት የስጋቱን መጠን የሚጠቁሙት አቶ ኦባንግ ፣ በግብጽ የተፈጠረው ቀውስ በሃይል ሊቆም የማይችልበት ደረጃ ሲደርስ ምዕራባዊያንም ሆኑ አሜሪካ የሃዘን መግለጫ ከማውጣት የዘለለ ስራ አለመስራታቸው ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ትምህርት ሊሆን እንደሚገባ ያሰምሩበታል።
በሩዋንዳ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሰዎች አልቀዋል። በኮሶቮ ህዝብ ተጨፍጭፏል። ዳርፉር ንጹሃን የጥይት ራት ሆነዋል። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሃያላን መንግስታትና “ድርጅቶቻቸው” በእነዚህ አገራት ውስጥ ነበሩ። እያወቁት ነው የሆነው። ግን ጉዳዩ የጥቅም ችግር ስለማይፈጥርባቸው አገራቱ በደም ጎርፍ ሲታጠቡ በዝምታ ተመልክተው እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኦባንግ፣ “ሶሪያ ስትፈርስ፣ ከ100 ሺህ ሰው በላይ ሲያልቅና አሁንም እያለቀ ባለበት ሁኔታ እልቂቱን ማስቆም እየቻሉ ዝምታን መርጠዋል” በማለት አቶ ኦባንግ ከነዚህ አገሮች፣ በተለይም “አሁን ግብጽ ላይ በተፈጠረው ችግር ካልደነገጥንና ለሚቀርበው የእርቅ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የማንዘጋጅ ከሆነ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጥያቄው የስልጣን ሳይሆን አገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሞት አደጋ የመግፈፍ አንደሆነ፣ ይህ አሁን ያንዣበበው የቀውስ ደመና ባስቸኳይ ካልተገፈፈ መከራው የሁሉም ወገን እንደሚሆን ጥርጥር እንደማያሻው የጠቆሙት አቶ ኦባንግ “ንጹህ ልብናና ንጹህ ህሊና ያላችሁ ውጡ፣ ለእውነተኛ እርቅ እንስራ፣ አገሪቱንም እናድን፣ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና እኛው አገራችንን በማስቀደም እንታደጋት” ሲሉ ከወትሮው በተለየ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው በዓመጽ መፈንቅለ መንግሥት የተደረገባቸው ፕሬዚዳንት ሙርሲን የሚደግፉ የሙስሊም egyptወንድማማች ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ የሃይል ርምጃ ከመወሰዱ በፊት በግብጽ ይህ ችግር ሊደርስ እንደሚችል የወተወቱ ነበሩ። ፕሬዚዳንት ሙርሲ ከስልጣን የተወገዱበት አግባብ ቀውስ ሊያስነሳ እንደሚችል ቢነገርም ሰሚ ባለማግኘቱ ቀውሱ ግብጻዊያንን እርስ በርስ አጋደለ። ግብጾች ግብጾችን ጨፈጨፉ። እስከ ሁለት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች የተገደሉበት ይህ ቀውስ እንዴት ሊቆም እንደሚችል ፍንጭ የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የሰዓት እላፊ፣ ግድያና እስር ዓመጹን ሊገታው አልቻለም። ይልቁኑም መሳሪያ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ግብጽን በጥይት እያመሷት ነው። እየገደሉም ነው።
w

በኢትዮጵያም በተለያዩ ወቅት የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን በጸረ ሽብር ህግ፣ በእስር፣ በድብደባ፣ በግድያ፣ በማስፈራሪያና በጡንቻ የማስተናገዱ አዝማሚያ ከእለት እለት መጠናከሩ የሚከፋቸውን ሰዎችና ቡድኖች እያበራከተ ነው። የተፈናቀሉ ወገኖች ተበራክተዋል። በተፈናቀሉና መሬታቸው እየተቸበቸበ ያሉ ወገኖች ምሬት የከፋ ደረጃ ደርሷል። ሚዛናዊ ያልሆነው የአስተዳደር መዋቅርና የኢኮኖሚ ልዩነት የፈጠረው ቅሬታ በቃላት የሚገለጽ አልሆነም። እንደ አቶ ኦባንግ ሁሉ እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ በማመን እየሰሩ እንደሆነ የሚናገሩትና ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ታዋቂ ምሁር ለጎልጉል እንደተናገሩት “በአሁኑ ወቅት ጥላቻው ከርሮ ህዝብ በገሃድ ስምና ብሔር እየለየ ፊት ለፊት መናገር ጀምሯል፤ የኑሮው ውድነት፣ የመብት ረገጣው፣ ዕንግልቱ፣ … የጥላቻውን መጠን አደባባይ ላይ እንዲታይ እያደረገው መጥቷል። አገራችን ያለችበት መንገድ አደጋ አለው። እርቅ የግድ ነው” ብለዋል፡፡
እኚህ ምሁር “ኢህአዴግ ውስጥ እርቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑና አሁን በየአቅጣጫው ያለው ችግር የሚያሳስባቸው ወገኖች ስላሉ እነዚህን ወገኖች በመቅረብ ለእውነተኛ እርቅ ለመስራት ጊዜው አሁን፣ ለዚያውም ሳይረፍድ በቶሎ ሊሆን ይገባል። ይህንን ካላደረግን ሁላችንም እናዝናለን። ይቆጨናል። በቀላሉ ልናልፈው ወደ ማንችልው ጣጣ ውስጥ ሳንገባ እንረባረብ” በማለት ተናግረዋል። አስተያየት ሰጪው በቅርቡ ራሳቸውን ገልጸው አስተያየት እንደሚሰጡ፣ ለጊዜው የተጀመሩ ስራዎችን በነጻነት ለመስራት ሲሉ ራሳቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡበትን ምክንያት ተናግረዋል።
“አገር እንደ ሰው አካል ነው። አንድ ቦታ ሲታመም ስሜቱ የሙሉው አካሉ እንጂ የተጎዳው አንድ ክፍል ብቻ አይደለም” በማለት የማጠቃለያ አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሲቋቋም ዓላማው ሁሉም ነጻ የማውጣት ታላቅ ዓላማ አንግቦ በመሆኑ በዚህ ረገድ በቅርቡ የእርቅ ተግባሩን ሊከውን የሚያስችለውን እቅዱንና የድርጊት መርሃ ግብሩን ይፋ እንደሚያደርግ፣ ለዚሁም ተግባራዊነት ኮንፍራንስ እንደሚያዘጋጅ አመልክተዋል።
በነጻ አውጪ ስም መደራጀትና መታገል ሙሉውን አካል /አገር/ ሊያድን እንደማይችል ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሁን ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ከንባታ፣ ሲዳማ፣ ከፊቾ … እያልን በተበጣጠሰ አመለካከት ከማነከስ የአገራችንን ህልውና በአንድ ትልቅ አጀንዳ ውስጥ በማካተት ለመስራት ድርጅታችን ለሚያቀርበው ጥሪ ህዝብና ጥሪ የሚደረግላቸው ወገኖች ሁሉ ቀና ምላሽ ሊሰጡ ይገባል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሙስሊም፣ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ ወዘተ በማለት ከብሄርና ጎሳው ልዩነት በተጨማሪ መለያየት መፈጠሩ የአገሪቱን እጣ ፈንታ አሳዛኝና አደጋ እንኳ ቢፈጠር ለተግሳጽ የሚፈራ ሰው እንዳይኖር ማድረጉ አሳሳቢ የሆነባቸው በርካታ ዜጎች አሉ። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት ግን ሁሉም ቦታ የፖለቲካ ኮተት የሌለባቸው፣ ንጹህ ልብና ያላቸውና ህሊናቸውን የሚያከብሩ አሉ። እነዚህ ወገኖች ብቸኛ አማራጭ በሆነው እርቅ ላይ አበክረው መስራት እንደሚገባቸው አመልክተዋል። እሳቸው የሚመሩት አኢጋንም ለእንደዚህ አይነቶቹ ንጹሃን በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም “አሁን ችግር በተባባሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ‘እርቅ’ እንደ መፍትሄ የሚቀርበው፣ ዓለም አሁን ከመቻቻል ሌላ አማራጭ ስለሌላት ስለሆነ እኛም እርቅ ላይ ያለአንዳች ማቅማማት መስራት ይገባናል፤ ይህ ዕርቅ ግን በደፈናው ምህረት የሚያሰጥ ሳይሆን በፍትህ ላይ የተመሠረተ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “ድርጅታችን እርቅ ላይ ያለው ሃሳብ ከሌሎች በተለየ የተቋቋምንበት፣ የሰፋና የተፈጠርንበት መሰረት በመሆኑ ይህንን ሃላፊነት በመውሰድ እስካሁን የሰራናቸውን ስራዎች ውጤት ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን፤ ይህም እንደወቅቱ ሁኔታ ተለዋዋጭ ሳይሆን የጋራ ንቅናቄው ገና ከጅምሩ የወጠነውና እስካሁን ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ጉዳይ ነው። ኢህአዴግም ሰላም ስለሚያስፈልገው፣ ባለስልጣኖቹም መኖር ስለሚፈልጉ፣ ደጋፊዎቹም ዋስትና ስለሚያሻቸው የተቃዋሚ ወገኖችም አገራቸውን ስለሚያስቀድሙ፣ ሁሉም ወገኖች ቀና ምላሽ ይሰጣሉ ብለን እናምናለን” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።


የሽብርተኝነት አዋጁ፤ የጠሉትን መምቻ? – ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0

ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት በስራ ላይ ካዋላቸው አዋጆች መካከል የ‹‹ፀረ-ሽብር ህጉን ..ያህል ያጨቃጨቀ የለም ቢባል ከእውነቱ ብዙም አልራቀም፡፡ በርግጥ ከተቃውሞ አቅራቢው አብዛኛው በደፈናው ‹‹ህጉ አያስፈልግም›› የሚል አልነበረም፡፡ ህጉ ‹‹ሽብርተኝነት››ን የገለፀበት መንገድና አንዳንድ አንቀፆቹ ለትርጉም አሻሚ በመሆናቸው ከስርዓቱ ባህሪ አኳያ ለፖለቲካ ጥቅም የሚውሉበት ዕድል መኖሩ አይቀሬ ነው የሚል ስጋት ነበር፡፡ የህግ ረቂቁ ለተወሰኑ የምዕራብ ሀገራት ዲፕሎማቶች ይመለከቱት ዘንድ በተሰጣቸው ጊዜም ተመሳሳይ ስጋት ሲያነሱ፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ ‹‹ሽብርተኝነት››ን ከየትኛውም የአለማችን ሀገር እጅግ በሰፋ መልኩ ስለሚተረጉም መሰረታዊ መብቶችን ሊዳምጥ እንደሚችል ጠቅሶ መጽደቁን ለመቃወም ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም፡፡


‹‹ፖለቲካ እና ኮረንቲ›› “መፍራት ያለብን ብቸኛው ነገር ፍርሃትን እራሱን ነው” እንዲሉ

$
0
0

የፍራቻ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ፍራቻ -እውነቱ እና ፍርሃቱ

በፍቃዱ ዘ ሃይሉ  የፍራቻ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ፍራቻ – ጥንድ በኢትዮጵያ መሪዎችና ሕዝቦች መሀል የተጋረጡ የጦር መሳሪያዎች ናቸው… ሕዝቡ ካልፈራ ፖለቲከኞቹ የፍራቻ ፖለቲካ ይጫወታሉ፣ ፖለቲከኞቹ የፍራቻ ፖለቲካ ካልተጫወቱ ሕዝቡ ፖለቲካን ይፈራል፡፡ የሁለቱም ውጤት አንድ ነው፤ ውጤቱም ሕዝቡ መሪዎቹን የሚያስከፋ ነገር መናገርም ሆነ መተግበር ይፈራል፡፡

የፍራቻ ፖለቲካ፤ በገዢው እና ተቃዋሚዎቹ Image ጥንት፣ ወትሮም ንጉሥ የማይከሰስ በመሆኑ መንግስታት ሕዝቦቻቸውን ማስፈራራታቸው የደንብ ያህል ነበር፡፡ ‹‹የተማረ ይምራን›› መባል ከተጀመረበት እና ደርግ የንጉሡን መንበር ከተረከበበት ጊዜ ወዲህም ግን ‹‹ደንቡ›› አልቆመም፡፡ ደርግ ‹‹አብዮቱን›› ሊቀለብሱ የሚንቀሳቀሱትን በሙሉ እንደማይምራቸው በሕዝብ ፊት ምሎ ዘመተባቸው፡፡ አብዮቱን ከሚቀለብሱት እንዳንዱ ላለመሆን የፈራ በሙሉ የኢሠፓ አባል ሆኖ በወንድሙ ላይ ዘመተ፡፡ ቀሪው ‹‹መሀል መስፈር›› የፈለገውም፣ ከፍራቻው’ጋ እንደተሟገተ 17 ዓመታት ኖረ፡፡

ኢሕአዴግ ቀርቶ የፍራቻ ፖለቲካ የቀረ ከመሰለ በኋላ ግን መልኩን ቀይሮ መጣ፡፡ አብዮቱን መቀልበስ፣ ሕገመንግስቱን መቀልበስ በሚል ተተካ፡፡ መንግስት የተቃወመውን ሁሉ በሆነ ስም በመፈረጅ ስለሚወነጅል፣ ላለመፈረጅ የሚሰጋው ሁሉ ወደወጣበት ምሽግ ተመልሶ ገባ፡፡ ‹‹ፖለቲካ እና ኮረንቲ›› የሚለው አባባል የተፈጠረው ያኔ ነው፡፡

የፍራቻ ፖለቲካን፣ ኢሕአዴግ በሌላም አካሔድ ይጫወትበታል፡፡ እንደገዢው ፓርቲ ዲስኩር ከሆነ፣ ኢሕአዴግ ከወረደ ወይም ተቃዋሚዎች ወደስልጣን ከወጡ የብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ/ነፃነት ተዳፍኖ ይቀራል፣ የሃይማኖቶች እኩልነት አደጋ ላይ ይወድቃል፣ ልማቱ ይደናቀፋል… ወዘተ፣ ወዘተ፡፡

የዚህኑ ግልባጭ ተቃዋሚዎችም ይጠቀሙበታል፡፡ ኢሕአዴግ ካልወረደ ብሔር ብሔረሰቦች እርስ በእርሳቸው ይባላሉ፣ የኢትዮጵያ አንድነት እመቃብር ይወርዳል፣ ሃይማኖተኞች ጽንፈኛ ይሆናሉ፣ ኢኮኖሚው ተጣምሞ ይቀራል… ወዘተ፣ ወዘተ፡፡ ሙግቶቹ እውነትነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን የፖለቲካዊ ጫወታም ሆነ የምጣኔ ሃብታዊ ትንታኔ እና ትንቢት ለማይገባው ምስኪን ግን ያኛው ከመጣ፣ ይሄኛው ከወረደ ወይም ያኛው ካልመጣ ይሄኛው ከሰነበተ ነገሩ ሁሉ ምስቅልቅሉ ወጥቶ፣ ሕዝቦች ሁሉ አደጋ ላይ ወድቀው…በሚል ፍርሃት ሙሉ ራዕይ ታቅፎ ይቀራል፡፡ ለሁሉም እንደመፍትሄ የሚቆጥረው ደግሞ ሽሽት /ስደትን/ ነው፡፡

የፖለቲካ ፍራቻ፤ በተመልካቹ ሕዝብ

የ2011 Legatum Prosperity Index፤ ኢትዮጵያን ከ110 አገሮች ጋር አወዳድሮ በብልፅግናዋ 108ኛ ባስቀመጠበት ሪፖርቱ Safety & Security ንዑስ ዘርፍም 106ተኛ ይበቃሻል ለማለት ያበቃውን ምክንያት ሲዘረዝር፣ “The Ethiopian government has been known to engage in political violence and, globally, Ethiopia is the country where expression of political views is perceived by the population to be most restricted. This may be contributing to the rate of flight of professionals, intellectuals, and political dissidents, which is among the 20 highest rates in the world.” (‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በፖለቲካዊ አመጾች ላይ እጁን በማስገባት ይታወቃል፣ በዓለምአቀፍ ደረጃም ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አመለካከትን ማንፀባረቅ በጣም የተገደበባት አገር ተደርጋ በዜጎቿ ትታሰባለች፤ ይህ ምናልባትም፣ ከዓለማችን ችግሩ የከፋባቸው 20 አገራት መካከል ኢትዮጵያን ላሰለፋት፥ የባለሙያዎች፣ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ስደት መንስኤ ሳይሆን አይቀርም፡፡››) ብሏል፡፡

Personal Freedom ብሎ በሰየመው ንዑስ ዘርፍም ኢትዮጵያ ውራ (110ኛ) ሆናለች፡፡ ሲዘረዝረውም እንዲህ ብሎ ነው፤ “Ethiopia ranks among the bottom 10 countries for citizens’ freedoms in expression, belief, association, and personal autonomy.” (‹‹ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ሐሳብን፣ እምነትን፣ ማሕበርን፣ እና የመግለፅ ነፃነት፣ እና የግል አቋምን ለማንፀባረቅ ከማይመቹ የዓለማችን 10 አገሮች ተርታ ትሰለፋለች፡፡››)

ሐሳብን ለመግለፅ ካለመቻል ጀርባ ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን የማይገልፁት/ለመግለጽ የሚፈሩት ፖለቲካዊ አመለካከታቸውን ብቻ አይደለም ሃይማኖታዊ፣ ፆታዊ ጉዳዮቻቸውንም ጭምር ነው፡፡ ለዚህ አንዱ አስተዋፅዖ አዋጪ ‹‹የመቻቻል ምሳሌ›› የሚባለው ነገር ግን ‹‹መቻቻልን›› በጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስቀመጠው ባሕላችን ነው፡፡ ‹‹መቻቻል›› በአገራችን አናሳው ብዙሐኑን ሲችል በሚል እሳቤ ተውጦ መክረሙ አጨቃጫቂ አይደለም፡፡ ስለዚህ አፈንጋጭ አመለካከቶች እውነታ ቢኖራቸውም እንኳን ተቀባይነት አይኖራቸውም፣ ሌላው ቀርቶ አፈንጋጭ አሳቢው ከሐሳቡ’ጋ ተግባብቶ እንዳይኖር ዱላ ይበዛበታል፡፡ ይህ ባሕል የወለደው ፍራቻ ፖለቲካዊ አስተሳሰብን የማንፀባረቅ፣ አንፀባርቆ ተቀባይነት የማጣት ፍራቻን ይወልዳል፡፡

ሕዝባችን ይፈራል፣ እንዲፈራም ታሪኩ ያስገድደዋል፤ ነገር ግን የሚፈራው በብትር የሚቀጣውን መንግስት ብቻ ሳይሆን በቃላት እና በማግለል የሚቀጣውን የራሱን ማኅበረሰብም ጭምር ነው፡፡ በዚህም የራሱን ሐሳብ ለራሱ አፍኖ በማለፍ ለአገሪቱ ለውጥ የሚበጁ በርካታ አማራጭ ሐሳቦችን አፍኖ ገድሏል፡፡ ይህንን ዓይነቱን ሕዝባዊ ፍራቻ አምባገነን መንግስታት ይፈልጉታል፣ እንዲለመልም እንጂ እንዲኮሰምን አያደርጉም፡፡ ለአምባገነን መንግስታት፣ ፍርሃት ከሰራዊቱ ይልቅ ሕዝቡን ከተቃውሞ ያቅብላቸዋል፡፡

በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ደፋር ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና አፈንጋጭ ሃይማኖተኞች ሲገደሉ ነበር፣ እየታሰሩ እና እየተሳደዱ ነው፡፡ ይህ እውነታ ግን ከሕዝባዊው የፍራቻ አድማስ የበለጠ አይደለም፡፡ በግሌ የኢሕአዴግ መንግስትን ካጠነከሩት ጉዳዮች መካከል የሕዝቡ ፍራቻውን ከእውነተኛው ስጋት (risk) በላይ ማግነን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ለዚህም ነው ይህንን መጻፌ!

“መፍራት ያለብን ብቸኛው ነገር ፍርሃትን እራሱን ነው” እንዲሉ ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት፣ ፍርሃታችንን እንፍራው፡፡



No doubt the struggle for having a system that is fair and free to all citizens will prevail sooner, not later!!

$
0
0

253152_246996372104704_556922296_n Raswork Mengesha Membership

MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM!

Keep going patriotic Ethiopians with your peaceful, constitutional/lawful, legitimate, rightful, and above all with the struggle to save a beloved homeland! Yes, history in general and our political history in particular is not short of evidences… that illegitimate and dictatorial regimes make their deadly swords much more sharper whenever they are challenged by the people who get much more determined to reaffirm their freedom and fundamental human rights . Yes, we are witnessing that those bunch of frustrated ruling elites are behaving and acting just like mad dogs at this time of defining moment. The Brave sons and daughters of beloved country; as you broke the fear and silence that was imposed by those members of the ruling circle who have no any other positive power but the killing machine.  We UDJ support organization in Sweden sincerely believe and support the struggle and assure you  that we will together break the political culture of ruling with a banner of the gun.

 

Udj Support organization in Sweden.


የሰማያዊ ፓርቲ ያላቻ ጋብቻ (ከአቶ ይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0

Yidenachew-KebedeAugust 21, 2013
መንግስት ተግባሩን ሣይወጣ ቀርቶ መንደርተኛና ቧልተኛ ሲሆን እንዴት ያሳፍራል ! ይህን ለመፃፍ ያነሣሣኝ አዲስ ዘመን ጋዜጣ “ የሰማያዊ ፓርቲ ጥቁር ተግባራት ” በሚል በገፅ 3 አጀንዳ ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪን በተጨማሪ ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እና በሬዲዮ ፋና በዜና እና በልዩ ዘገባ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች፤በተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄዱ ጥቃቅን አነስተኛ ስብሰባዎችና ሰልፎች የሚሰሙ መፈክሮች የመንግስትን ፍርሃቱን እና ውንጀላ በሚገባ የሚያሳዩ በመሆናቸው ነው…Yidenachew Kebede

መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄ አቅራቢዎች የሚያስርበት እና የሚያሰቃይበት አዋጅ ማውጣት ይቀለዋል፤ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም መነሻውን 4 ኪሎ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረሻውን ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ያደረገ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ተደርጓል፡፡ በዕለቱም ለመንግስት የቀረበለት ጥያቄ የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዲስተካከሉ፣የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣በዓይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲቆም በዚህም ምክንያት የታሰሩት እንዲፈቱ፣የኑሮ ውድነቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚል ጥያቄዎች ናቸው፤እጅግ በሰለጠነ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄው ለመንግስት የቀረበ ሲሆን መንግስትም ለዚህ ምላሽ የሦስት ወር የጊዜ ገደብ ተሰጥቶታል፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ስም ማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሎበታል፤መንግስት ስም ለማጥፋት ብሎ ያነሳቸው አንኳር ሀሳቦች መሰረታዊ የሰው ልጅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስት ይህን ለመረዳት ተጨማሪ 22 ዓመታት ቢያስፈልገውም ህዝብ ግን ያጣውን ነፃነት ለማግኘት ትግሉን ይቀጥላል፤ ለህዝብ የመብት ጥያቄ የሆኑት መንግስት ለመወንጀል የሚያነሳቸው ሃሳቦች በጥቂቱ እንመልከት፡፡

1ኛ. “በ1997 ዓ.ም በቅንጅት ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዛሬ ደግሞ በአዲስ ኮፍያ የሚንቀሳቀሱ” የተባለው ቁጥር አንድ ውንጀላ ነው፤ ምላሹ ደግሞ ፡- ይህ ሀሳብ ከእውነት የራቀ አይደለም ከዛሬ 8 ዓመት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ይቅሩና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ለነፃነት እና ለመብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተደረገበት ወቅት ነው፤ በወቅቱ ለሚፈለገው ነፃነት ደም ተከፍሎበታል፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ባዶ እጁን አደባባይ ወጥቶ “ድምፃችን ይከበር” በማለቱ አገርን ሊወር እንደመጣ ጠላት በመከላከያ ሠራዊት ለዛውም በሰለጠኑ ነፍሰ ገዳይ ታሪክ ሁሌም የሚዘክራቸው ኢትዮጵያውያን በግፍ ገሏል፤ በዚህም ምክንያትና በሌሎች የሚፈለገው ነፃነት ታጥቷል፡፡ እናም ያኔ ያጣነውን ነፃነትና መብት መንግስት በአዲስ ኮፍያ ቢለውም እጅግ በሠለጠነና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በአዲስ እስትራቴጂ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈቀደው መልክ ተደራጅቶ ይህን አምባገነን ስርዓት ታግሎ ለማሸነፍ የሚያደርገው ጥረት ወንጀል የሚሆነው ምኑ ላይ ነው?

2ኛ. “በውጭ ከሚገኙ ፅንፈኛ አክራሪ ኃይል ጋር በመቀናጀት በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት” ይህ ሁለተኛው ውንጀላ ነው፤ ሌባ አባት ልጁን አያምንም የሚባለው ተረት ለዚህ ውንጀላ ተስማሚ ይመስለኛል ምክንያቱም ያሁን መንግስት የበፊት አማፅያን (ወያኔዎች) ከሱዳን፣ ከሶሪያና ከግብጽ ከመሳሰሉት አገራት የጦር መሣሪያና ስልጠና እንዲሁም መሸሸጊያ በማግኘት አዲስ አበባ ቤተ መንግስት መግባታቸውን የሚታወቅ ነው፤ እነሱ በክደት የፈጸሙት ሁሉ ሌላው ያደርገዋል የሚል ከንቱ አሳብ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የተመሠረተው በኢትዮጵያውያን ነው ትግሉም ሆነ ዉጤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ ሌላው ደግሞ በአረቡ አለም የታየው አብዮት ኢትዮጵያውያን ከ8 ዓመት በፊት በአስደናቂ ሁኔታ የተገበርነው ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ከ8 ዓመት በፊት ያጣነው አብዮት መንግስት አልሰማና አልለወጥ ካለ የአረቡን አብዮት በኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታና ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በመስቀል አደባባይ ወጥተን ብናደርገው ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?

3ኛ. “ከውጭ አሸባሪ ግንቦት ሰባት ቴሌቪዥን ጣቢያ ‘ኢሳት’ ጋር በመቀናጀት” ይሄ ደግሞ ሦስተኛ ውንጀላ ነው በመሠረቱ በአገር ቤት ያለው የዳኝነቱ ስርዓት እውነተኛ ፍትህ የሚሠጥ ቢሆን ኖሮ “መልካም ስምና ዝናን በማጉደፍ በተጨማሪም መረጃን የማግኘት መብት በመንፈግ” የወንጀል ክስ መመስረት ይቻል ነበር ግን ምን ዋጋ አለው?፡፡ ይህን ለማለት የፈለኩት አንደኛ ኢሳት መረጃን ለተጠሙ በዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጲያውያን አይንና አንደበት የሆነ ሚዲያ እንጂ የግለሰብ ወይም በተወሰኑ ቡድኖች የሚንቀሳቀስ ሚዲያ አይደለም፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሚዲያው የእገሌ ድርጅት ነው መባሉ የስም ማጥፋት ወንጀል ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ መረጃን ማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ነው፤ ይሁን እንጂ በአገራችን እኛ የመረጥነው ሳይሆን መንግስት የመረጠልን ሚዲያ ነው የምንመለከተው፣ የምንሰማውና የምናነበው ለዚህም ማሳያ በአገር ውስጥ ትክክለኛ መረጃ የሚያስተላልፉ ጋዜጠኞች መጨረሻቸው ስደት ወይም እስራት ነው፤ ከሀገር ውጭ ያሉ ሚዲያዎች ደግሞ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ይታፈናሉ በዚህ ምክንያት መረጃ የማግኘት መብታችን በኃይል ተከልክለናል፡፡

4ኛ. “የጥቂት ሙስሊም አክራሪዎች አጀንዳ በመደገፍ አደባባይ ይዞ መውጣት” አራተኛ ውንጀላ መሆኑ ነው፤ ጥቂት፣ አነስተኛ፣ ጥቃቅን የመንግስት አፍ መፍቻ ከሆኑ ሰነባብተዋል፤
“ጥቂቶች ቆራጦች ያልተንበረከክነው
ዛሬን እንሞታለን ነገ ታሪክ ምስክር ነው”
የሚለው የእናንተ የትግል መዝሙር አስታወሰኝ እባካችሁ ትላንትና ለጥቂቶች የነበራችሁ ከፍተኛ ግምት ዛሬ የት ገደል ገባ? የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል የጥቂቶች አይደለም የአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ሙስሊም የሀይማኖት ነፃነት ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ለአገር የቆመ ፓርቲ ለመብትና ለነፃነት በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ እያለ መብትና ነፃነታቸውን ለማስመለስ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ “ድምፃችን ይሰማ” ለሚሉ እውነት ነው ድምፃቸው ይሰማ ብሎ ሰማያዊ ፓርቲ ድምፁን ቢያሰማ የሚያስወነጅለው ምክንያቱ ምንድን ነው?

5ኛ. “ሰማያዊ ፓርቲ ሠልፍ ላይ መካከለኛ እድሜ ላይ ያሉና አዛውንቶች ጭራሹንም በሰልፉ ላይ የሉም በአብዛኛው ለአክራሪዎች ወግኖ የቆመ ኃይል ነው” ይሄ በአምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ከውንጀላ ይልቅ በኢህአዴግ ቋንቋ የሠልፉን ገፅታ ጥላሸት ለመቀባት ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ሁሉንም የህብረተሠብ ክፍል ያካተተ እንደነበር የአለም ሚዲያ የዘገበው ነው፤በጣም የሚገርመው በ1997 ዓ.ም አደባባይ የወጣውን ወጣት “ አደገኛ ቦዘኔ ” በማለት ሠልፈኛውን እና የሠልፉን ዓላማ የተለየ ለማድረግ መንግስት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፡፡ አሁን ደግሞ ከ8 ዓ.ም በኋላ በተካሔደው የተቃውሞ ሰልፍ ወጣቱ ብቻ ነው የተገኘው በማለት ለወጣቱ ያለውን ንቀት መንግስት በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ እኔ የምለው! ወጣቱ ስለሀገሩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ አያገባውም እንዴ? በተጨማሪም ተገፋን፣ ተበደልን ከሚሉ ሰዎች ጋር ወግኖ መቆም ጥፋቱ ምን ላይ ነው? በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ታስቦና ታቅዶ የሚፈፀም በደልና መገፋት በኔ አልደረሰም ተብሎ እንዴት ይታለፋል፤ ዛሬ ከተገፉትና ከተበደሉ ወገኖች ጋር ወግኖ ያልቆመ ነገ ለሱ ማን ሊቆምለት ነው?

በአጠቃላይ ከላይ የተገለፁት ሀሳቦች በመንግስትና ካድሬዎች እና ሚዲያዎች የሚነዙ አሉባልታ ወሬዎች መሆናቸውን ለማሳያት ለመንደርደሪያነት የቀረበ ፅሁፍ ነው፡፡ መንግስት ከሰሞኑ የተያያዘው ነገር ቢኖር ከስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍ ባለ ሁኔታ የሃይል እርምጃ መውሰድ ነው፤ለዚህም ማሳያ በተለያዩ ከተሞች በእስልምና እምነት ተከተዮች ላይ ግድያ እና ድብደባ እንደሁም እስራት እየተካሄደ ነው፤ ቀጣዩ ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች መሆናቸው የዘፈን ደርዳርታ እስክስታ ነው እንደሚባለው ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጀምሮ እስከታችኛው የስልጣን እርከን የተቃዋሚ ፓርቲ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲን መንግስት የነገር አባት ( ሽማግሌ) በመሆን በቅርብ ከማያገኛቸው ነገር ግን እንዲህ አይነቱን ውንጀላ ለመፈረጅ ከሚመቻቸው ከግንቦት ሰባት እና ከሙስሊም አክራሪዎች ጋር ፓርቲውን እየዳሩት ይገኛል ፤ጋባቻው ግን ያላቻ ጋባቻ ነው፡፡

በመሆኑም መንግስት በተሠጠው ጊዜ አላፊነቱን በመወጣት እኛ ተበዳዮቹ ብቻ ሳንሆን እናተም በዳዮቹን በጋር በነፃነትና በእኩልነት የምንኖርበት አገር በማቅናት ሁሉ በህግ ፊት እኩል ሆኖ የሚዳኝበትን ጊዜ እናቅርበው፤ አለበለዚያ የምትፈሩት ህዝባዊ አብዮት መምጫው ቀን እሩቅ አይደለም፡፡
ይድነቃቸው ከበድ


ደብዳቤ ከመለስ ዜናዊ (ይድረስ ለጓድ ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ)

$
0
0

ካለሁበት ቦታ ጓዳዊ ሰላምታየ ይድረስህ። ከመጣሁ ጀምሮ ደብዳቤ ልጽፍልህ አስቤ ሳይሳካልኝ ስለቀረ እስከአሁን ቆየሁ። እዚህ ከመጣሁ ብዙ ነገር አጋጥሞኛል። በየጊዜው ብዙ ሰወች ስለሚመጡ፣ ስለናንተ ብዙ ነገር ይደርሰኛል…

f44997cb312b542bbd55c895274ee230_XL220px-Meles_Zenawi_-_World_Economic_Forum_Annual_Meeting_2012
እኔ ያለሁበት ቦታ በጣም የተለየ ቢሆንም፣ እዚህ ከመጣሁ በጣም ብዙ ሰው አግኝቻለሁ። ብዙወች ያውቁኛል። እኔም የማውቃቸው ብዙ ናቸው። ተሰባስበው ያነጋገሩኝ ብዙወቹ እኔ በተለያየ መንገድ ከምድር ወደዚህ የላኳቸው ናችው።
እንድሁም ታዋቂ የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞችም በቦታው ነበሩ። የኢትዮጵያዊያኖችን በይበልጥም የዘመዶቻቸውን ቁስል ላለመቀስቀስ ስል ስም አልጠራም። ዝርዝሩን ከፈለግክና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲናገር ከፈቀድክለት ይነግርሃል። የደህንነት መስሪያ ቤታችን ያረጋግጥልሃል።

በጣም ቁጥር ስፍር የሌላቸው፣ ትግራይን ለማስገንጠልና ኤርትራን ነፃ ለማውጣት ብለህ፣ ከኢትዮጵያ ጦር በኩል፣ ከህወሃት በኩል፣ ከሻብያ በኩል፣ ያስጨረስከን ነን ይሉኛል። በጣም የገረመኝ ሁሉም በአንድ ሆነውና ተስማምተው ነው
ያነጋገሩኝ። በተደጋጋሚ ያቀረቡልኝም ጥያቄ እኛን አስጨረሰህ ትግራይና ኤርትራ ምን የተሻለ ነገር አገኙ፤ ህዝቡ ከመለመን፣ ከመሰደድ፣ ከርሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከአምባገነን አገዛዝ ነፃ ወጣ ወይ የሚል ነበር። እንድሁም በትግራይ ተራራወች የጨፈጨፍናቸው የደርግን ግድያ ሸሽተው የነበረ የኢህአፓ ወጣቶች፣ በአዲስ አበባ ጎንደርና ሌሎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው በአጋዚ አነጣጣሪ ተኳሾች በኔ ትዛዝ ያስገደልኳቸው፤ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላና በደቡብ ህዝቦች በዘር ለያይተን ያጋደልናቸውና፣ በበደኖ፣ አርባጉጉ ከነህይወታቸው ገደል ያስጨመርናቸው፣ የብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል በማለት ቀስቅሰን በየጫካውና በየከተማው ኦነጎች ናችሁ እያልን የገደልናቸው የወለጋ፣ ባሌ፣ ጅማና ሃረር ወጣቶች፤ እንዲሁም ነፍጠኛ በማለት ፈርጀን እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ ያደረግናቸው ገበሬወች ነበሩ። በተጨማሪም በኤርትራ በየዋሻው ታስረው በርሃብና በግዳጅ ስራ ጠያቂ ሳይኖራቸው ያለቁ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ በተለያዩ ቦታወች እየተያዙ እንዲገደሉና እንዲሰወሩ ያደረግናቸው ኢትዮጵያዊያን በጣም ብዙ ነበሩ። እነዚህም ያናገሩኝ በአንድ ላይ ሆነው ነው። ሌሎቹ ቁጥራቸው የሚበዛው ከኢሳያስ ጋር በነበረን የግል አለመግባባት በባድሜ ስም ጦርነት ከፍተን ያስጨፈጨፍናቸው ነበሩ። ሁሉም እንዲወክላቸው የመረጡዋቸው፣ እቤታቸው በር ላይ በህወሃት ተኳሾቸ ያስገድልኩዋቸው መምህር አሰፋ ማሩ ነበሩ። ሁሉም ባንድ ቃልና በከፍተኛ ትዕግስት አናገሩኝ። አንተም ወደዚህ ትመጣለህን ብለው የተወሰኑት ቀለዱብኝ። ያሉበትን አለም የሚገዛው፣ እውነት፣ ሰባአዊነትና ትግስት ነው። ብዙወቹ ለአገር ሰማዕታት የሚሰጥ ልዩ የክብር ቦታ ተሰጥቷቸዋል።

የኔ መምጣት እንደተሰማ ካናገሩኝ ውስጥ ራስ አሉላ አባ ነጋ፣ አጼ ምኒሊክ፣ አጼ ዩሃንስ፣ ደጃችህ ገረሱ ዱኪ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ በላይ ዘለቀ፣ ሞገስ አስገዶም፣ አብርሃም ደቦጭ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ አርበኞች ነበሩ። ከሁሉም ግን ራስ
አሉላ በጣም ተበሳጭተዉና ደማቸው ፈልቶ፣ ይህን ከሃዲ አምጡልኝ በማለት፣ ምን ለማድረግ ነው ስንት ህዝብ መስዋዕት ሆኖ ያቆያትን አገር ለማፍረስ ይህን ሁሉ ያደረግከው በማለት ጠየቁኝ። እኔም በፀፀትና በፍርሃት መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። ከዚያም ከፊቴ ጥፋ ብለው አባረሩኝ። እኔም በሁለት እሳት መካከል ሆንኩ፣ አንዱ በስራዬ የተፈረደብኝ ሌላው ደግሞ የደረሰብኝ ፀፀት ነበር። ከዚያም ሃጢያቴን ለመናዘዝ አባታችን መምጣታቸውን ስለሰማሁ መፈለግ ጀመርኩ። እንደምንም አገኘኋቸው። እንደፊቱ የሚፈሩኝ መስሎኝ አባት ያሳልሙኝ ብዬ ጠጋ ስል፣ ክላ በማለት መቋሚያቸውን አንስተውና እኔንም አሳስተህ አስቀስፈኸኛል ብለው አባረሩኝ። ተስፋ ባለመቁረጥ ስፈልግ ሌላ አባት አገኘሁ። ቀረብ ብዬ አባት ሃጢያቴን መናዘዝ፣ ንስሃ መግባትና ካለሁበት እሳት መውጣት እፈልጋለሁ ስላቸው፣ ስለአንተ ቀድሜ ብዙ ሰምቻለሁ፣ መብርቅ መትቶህ በድንገት ነው እንዴ ወደዚህ የመጣህው አሉኝ። አይ አይደለም፣ ለረጂም ጊዜ ታምሜ ነበር አልኳቸው። እሳቸውም መልሰው ታዲያ የንስሃ እድሜ ተሰጥቶህ ይህን ሁሉ ጉድ ሃጥያት ተሸክመህ እንዴት ሳትናዘዝ ትመጣለህ ብለው በመገሰጽ ይቅርታ መጠየቅና ንስሃ መግባት ያለብኝ ግፍ በፈፀምኩበት በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት መሆኑን ነገሩኝ። በዚህም የተነሳ ይህን ደብዳቤ ፃፍኩልህ።

ጓድ ሃይለማርያም፣ በቅርብ የመጡ ብዙ ሰወች አገኘሁ። ከሁሉም የሰማሁት ተመሳሳይ ነው። አንተና የህወሃት ኢህአድግ ሰወች የመለስን “ሌጋሲ” (ውርስ) ሳይበረዝ ሳይከለስ እንቀጥላለን እያላችሁ ትፎክራላችሁ አሉ። ይህ የምትሰሩት
ስራ ሃጢያቴን እያባዘው ነው። አዜብ የመለስ ህይወት ታሪክ ሲነገር ገድሉ በአግባቡ አልተገለፀም አለች አሉ። ይህ ሁሉ ለኔ ምን ይጠቅመኛል? ያለሁበት ቦታ ውሸት፣ ከንቱ ውዳሴና ማሞካሸት የሚያስፈልገው አይደለም። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት የማይቀረው እየመጣ መሆኑን አውቄ እንኳ የሰረፀብኝን ትዕቢት ማሸነፍ፣ እውነቱን መቀበል፣ ያጠፋሁትን መናገርና ይቅርታ መጠየቅ አልፈለግኩም። እንዳውም እስከመጨረሻው ጊዜ ድረስ ከከፋፋይና ዘረኛ ስራየ አልተገታሁም።

አሁን ሌላ ሰው ነኝ፤ አልዋሽህም። ሃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ስክድና ሚልዮኖችን እንዳሸበርኩ ሁሉ፣ ጥላየን ስፈራ፣ ራሴን በከንቱ ስከላከል ኖሪያለሁ። እናንተም በፍርሃትና በጭንቀት ተሸፍናችሁ ማየት ያልቻላችሁትን እኔነቴን ልግለጽላችሁ። መሪ መሆን ማለት ከምንም ነገር ቅድሚያ ሃላፊነት መውሰድ ነው። ምንም እንኳ በስሬ የተሰለፉት እበላ ባዮች የተንኮል ተልዕኮየን ለማሳካት ቢረዱኝም፣ በአገሩ ጉዳይ ገለልተኛ ሁኖ፣ የተጫነውን ሁሉ ተሸክሞ የሚኖረው ብዙ ኢትዮጵያዊ ላደረግኩት በደል በዝምታው አስተዋፅዖ አድረጓል። እኔም ለማደርገው ሁሉ ሃላፊነት ሳይሰማኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳሰቃይና ስጨርስ ኖሪያለሁ። አንተ ደግሞ የኔን ስራ ያለምንም ለውጥ እደግማለሁ ብለህ መነሳትህ፣ ከምንም ነገር በላይ አሳሰበኝ።

እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ የተጠናወተኝን አገር የመከፋፈልና ኤርትራን የማስገንጠል አባዜ ሳነበንብ በወንጀል ላይ ወንጀል ስሰራ ወደዚህ መጣሁ። ኢትዮጵያን ነፃ ለማወጣት ሳይሆን ትግራይን ለመገንጠል፣ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር
(ህወሃት) ብለን ተነስተን በብዙ ሺወች የሚቆጠሩ የትግራይን ወጣቶች በከንቱ አስጨረስን። ያአገር ድንበር ለማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንን በግፍ ጨፈጨፍን። በመሰሪና መርዝ በሆነ ቅስቀሳችን በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረውን ህዝብ አታለልን። ስውር ተልእኳችንን አሳካን።

ብዙ ኢትዮጵያዊያንና በለንደኑ ጉባኤ ያደራደሩን ፈረንጆች ሳይቀሩ የመከሩኝን ባለመስማት፣ ለኢሳያስ የገባሁትን ቃል ለመጠበቅና፣ ለአንድ አገር እድገት የባህር በር አያስፈልግም በማለትና የሃሰት ታሪክ በመፍጠር፣ ኤርትራን ከናት አገሯ
አስገንጥየ፣ ቀሪውን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠመንጃ ሃይል አፍኘ፣ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለት የተለየ ሃሳብ ያቀረቡትንና የተቃወሙትን ሁሉ ተራ በተራ አጠፋሁ። ኢትዮጵያን ያለባህር በር አስቀረሁ። ኤርትራን ከማስገንጠል አልፌ በአለም አቀፍ መድረክ የመጀመሪያውን እውቅና ለኤርትራ ሰጠሁ። በኢትዮጵያ ስም ተበድሬ ከፍተኛ ገንዘብ ለኤርትራ አስተላለፍኩ። ስራየ ሁሉ የኤርትራን ጥቅም ማስጠበቅ ሆነ።

የውጭ ጥቃት ይመጣል ተብሎ ሲሰጋ፣ አገሪቱን ከጥቃት ሊከላከል የሚችለውን የባህርና አየር ሃይል በተን። መውጫና መግቢያችን በትንሿ አገር ጂቡቲ መልካም ፈቃድ የሚወሰን ሆነ። ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላምና በአንድነቱ
እንዳይኖር፣ ጠባብ የዘር ፖለቲካ በመስበክና በህገመንግስቱ ዉስጥ የብሄረሰቦች መብት ያለገደብ እስከመገንጠል የሚለውን በማጽደቅ፣ አገሪቱን ጣሊያኖቹ ባሳዩን መንገድ በዘር ከፋፈልን፣ የአገሪቱን አንድነትና ደህንነት ለአደጋ ተጋልጦ እንዲኖር ህጋዊ መሰረት አስቀመጥን። ኢትዮጵያዊነትና የጋራ እሴት የሆነውን ሁሉ መግደል ዋናው ስራየ ሆነ። በአጭሩ በአዲስ አበባ የሚኖር የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባርን ዓላማ አስፈፃሚና የኢሳያስ አምባሳደር ሆንኩ። በጣም የሚያስገርመው የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የሚለውን ስማችንን እንኳ ሳንቀይር ኢትዮጵያን ይህን ያህል ዘመን መግዛታችን ነው።ይህን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ አለ ብየ ሳይሆን ነገርን ከስሩ በየ ነው። ለነገሩ እኛ መግዛት ከጀመርን የተወለዱትና የኛን ዘረኛ ቅስቀሳ እንደወተት እየጠጡ ላደጉት ወጣቶች ይህን ስራየን ባሳውቃቸው ምን ይከፋል።

የፈለግኩትን ሁሉ አፍርሸ እንደገና እገነባዋለሁ የሚል ከንቱ አመለካከት ነበረኝ። በዚህም መሰረት ያአገሪቱን ምሁራን አባርሬ ሌላ ምሁራንን በራሴ አምሳል እፈጥራለሁ በማለት፣ የተለየ ሃሳብ ያላቸውንና ይተቹኛል ብየ የፈራኋቸውን
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ችሎታ የላቸውም በማለት፣ ለአገር በሚጠቅሙበትና ብዙ ሊያስተምሩ በሚችሉበት እድሚያቸው፣ አባረርኩ። ያገሪቱን ምሁራን በማሳደድ ያለፍላጎታቸው የባዕድ አገር አገልጋይ እንዲሆኑና ብዙወችም
ተበሳጭተውና ተሰቃይተው እንዲሞቱ አደረግኩ። ለዚህ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ትልቅ ሚና ተጫውታልኛለች። በየመስርያ ቤቱ የኛን የዘር ፖለቲካ የማይቀበሉትን ሁሉ አባረርን። ምንም ችሎታው በሌላቸው ታጋዮች ተካን። ታማኞቻችንን በከፍተኛ ቦታ ለመመደብ ብዙው ሰው ድንጋይ መፈልፈያ እያለ በሚጠራው ሲቭል ሰርቪስ ኮሌጅ በማስገባት ዲግሪ አደልን። እንዲሁም ከአውሮጳ የተልዕኮ ዩኒቨርስቲወች “ድፕሎማ ሚልስ” በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ዲግሪ በመግዛት አደልን። ዛሬ እኔ ሳነጥስ አብረው ያነጥሱ የነበሩት በስሬ ያሰማራኋቸው አድርባዮች ሁሉ ባለ ማስተርስ ዲግሪ ተብለዋል። ለምን ያን ያህል የውጭ ምንዛሬ እንደአወጣሁና ትምህርት መርጃውን ራሴ እያተምኩ እንዳልሰጠኋቸው እስካሁን ለራሴም አልገባኝም። ታዲያ ነገሩ ሁሉ የኔን ቃላት እንደ ፀሎት መድገምና ድንቁርናን በአገሪቱ ማባዛት ሆነ።

ፈረንጆቹን ለማታለል፣ ከፍተኛ ብድር ለመበደርና ዕርዳታ ለማግኘት፣ የተጋነነና የውሸት መረጃ በመሰብሰብ፣ ለማስመሰል ያህል ህንጻ በመገተር ትምህርትን አስፋፋሁ አልኩ። ለህሊናቸው የሚገዙትንና የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ምሁራን
በስለላ ድርጅታችን ተብትበን በመያዝ አሽመደመድናቸዉ። ባጭሩ ተቋማቱ የካድሬ መፈልፈያና፣ እንደኮብል ድንጋይ ቀርጸው ካስቀመጡባቸው የማይንቀሳቀሱ፣ ሰምተውና አስበው የማይጠይቁ፣ አምባገነንን የሚያመልኩ በቀቀኖች ማምረቻ ሆኑ። በአገሪቱ እኔው ምሁር፣ እኔው ተመራማሪ፣ እኔው ህግ፣ እኔው ህግ አውጭ፣ እኔው ዳኛ፣ እኔው ፖሊስ፣ እኔው የጦር መሪ ሆኜ ኖርኩ።

በዘረኝነት መርሃችን የትግራይን ህዝብ እንዲጠላ ለማድረግና ምንጊዜም የኛ ደጋፊ ለማድረግ በሸርብነው ሴራ፣ ለሙን የጎንደርና፣ የወሎን መሬት ወደ ትግራይ ከለልን። ብዙ የዋህ ኢትዮጵያዊያን የትም ክልል ይሁን የኢትዮጵያ አካል
እስከሆነ ድረስ ብለው ተቀበሉት። የግል ደጋፊወቻችንን ሰፊና ዘመናዊ እርሻ እንዲኖራቸው በሁመራ ሰሊጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ በማድረግ የዛሬ ሃብታሞች የነገ አገር መሪዎችን ፈጠርንበት። ቀሪው ኢትዮጵያን የመግዛት ዘመናችን ካለቀ ግን፣ በጠባቡ አመለካከታችን ትግራይን ገንጥሎ ወደ ኤርትራ ለመቀላቀል የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጀን። ለዚህም እርዳታ እንድናገኝና ቀደም ብሎ በጫካ እያለን የተደረገልንን ውለታ ለመመለስ የጎንደርን ሰፊ ለም መሬት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያውቅ፣ ለሱዳን አሳልፈን ሰጠን። በተወሰነ የህውሃት መሪወች በተቆጣጠርነውና ከኢትዮጵያ ተዘርፎ፣ ከመንግስት ባንኮች ተውስዶ፣ በተቋቋመው፣ በግልጽ ባለቤትነቱ በማይታወቀው፣ የሂሳብ አያያዙ በማይመረመረው፣ ግብር በማይከፍለው፣ በትግራይ ልማት ድርጅት (ኤፈርት) ስም፣ ሌላ ባለሃብቶችን በማዳከም፣ ያአገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጠርን።

ሌላው ወንጀሌ የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት በማስመልከት የፈፅምኩት ነው። መሬት የመንግስት ነው ብለን ስንነሳ የረቀቀ የረጅም ጊዜ ዓላማ ይዘን የኢትዮጵያን መሬት ለመሽጥ፣ ለፈለግነው ደጋፊወቻችን ለመስጠት መሆኑን የተረዱ ብዙ
አልነበሩም። የኢትዮጵያን ህዝብ ከመመገብ አልፎ ለሌላ አገር ይተርፋል የተባለውን ቆላማ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች ለመሽጥ በነበረን የረጅም ጊዜ ዕቅድ መሰረት፣ መጀመሪያ ያደረግነው ህዝቡን በዘር መከፋፈልና ካአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ እንዳይሰራ ማድረግ ነበር። በዚህም ከበሽታና ከርሃብ ተርፈው የተቋቋሙትን ሰፋሪወች ከጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ባሌና ደቡብ ህዝቦች እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ አደረግኩ። የብዙ ህፃናትና ደካሞች ህይወት ሳይቀር አለፈ። ብዙ የመሃል አገር ሰወች በአርባጉጉ፣ በበደኖ እና ሌሎች ቦታወች ነፍጠኛ እየተባሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ብዙ የመንግስት ሰራተኞች ክልላችሁ አይደለም እየተባለ ተባረሩ። የኢትዮጵያ ባንድራ ተወረወረ። ኢትዮጵያዊነት እዲጠፋ፣ ጎሰኝነት እንድነግስ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘመቻ አደረግን። በዚህ ረገድ እነ ጓድ ታምራት ላይኔና አሰን አሊ በዘረኛ ቅስቀሳቸው ያደረጉት አስተዋጾዖ ከፍተኛ ነበር። ዛሬ ግን ታምራት እኔና ባለቤቴን እግዚአብሄር በተደጋጋሚ በገሃድ መጥቶ አናገረን እያለ ፈረንጆቹን ያታልላል አሉ። ድሮም ብልጣ ብልጥ ነበር። በዕውነት እግዚአብሄር ከቀረበው ቅድሚያ የኢትዮጵያን ህዝብ ነበር ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት። በዚህም መሬት ስሪትና ዘረኛ መርህ በሚስጥር በሚደረግ ስምምነት ሰፋፊ በአገር የሚተካከል መሬት ለነ ካራቱሪ፣ ሸህ አላሙዲንና ሌሎችም ሸጥን። በጋምቤላና ሌሎች ቦታዎች ብዙ ህዝብ ተገደለ፣ ተፈናቀለ፣ ሰፊና ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብቱ ተጨፈጨፈ። መሬቱ ሃላፊነት በጎደለው መንገድ በኬሚካል እንዲበከልና የአካባቢው ህዝብ በበሽታ እንዲለከፍ ተደረገ። እንዲሁም የከተማውን ቦታ ዋጋ ጣራ በማድረስ ከመንግስት የተጠጉና መሬት በተለያየ መንገድ በእጃቸው የገባ ደጋፊወቻችንን ሚሊዮነሮች እንድሆኑ አድርገናል። እኛን ያልደገፉትን ግን ኪራይ ሰብሳቢ በማለት በማሰር አሰቃይተናል።

ጓድ ሃይለማሪያም፣ ካደረግኩት ነገር ሁሉ አንተን ወደ ስልጣን ማስጠጋቴ የተሻለ ስራ የሰራሁ መስሎኝ ነበር። ምክንያቱም ፈርሃ-እግዚአብሄር አለህ ሲባል ሰምቸ ስለነበር ነው። እንዲሁም ደግሞ አንተ እንደ እኔ የሰው ህይወት እያጠፋህ፣ በሰው አካል ላይ እየተረማመድክ የመጣህ ጨካኝ ስላልሆንክ ነው። በተጨማሪም የተማርክ በመሆንህ የምታገናዝብና በራስህ የምትተማመን ትሆናለህ በየ ስለገመትኩ ነው። ምንም እንኳ ከስሬ ያላችሁትን ሁሉ ረግጬ በመያዝ፣ በኔ አዕምሮ እንድታስቡ ባደርጋችሁና የህወሃት ሰወች አላሰራም ቢሉህም፣ በምድር ሳልኖር ግን ይህን ያክል እኔን የምትፈራበትና፣ እኔን ለመሆን የምትጥርበት ጉዳይ አልገባኝም። ይህን ስራህን ያዩ ኢትዮጵያዊያን “the cloned” መለስ
እያሉ እንደሚጠሩህ ሰማሁ። “ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ” ማለትህንም ሰማሁ። እንዴት ብትፈራኝ ነው? በዕውነት ይህ ለኔ ይገባልን? ደግሞ መለስ “የሚማሩበት፣ የሚመራመሩበትና በርካታ ለመጪው ትውልድ አመራር አባላት በቂ የመነሻ ሃሳብ የሚያገኙበት በጥቅሉ ለጥልቅ ጥናትና ምርምር አንጡራ ሀብት ነው” ብለህ ማለትህ አሽሙር መናገርህ ነው። ጥሩ ብልሃል። የሰራሁት ወንጀል በዕውነትና በአግባቡ ተጠንቶና በመረጃ ተደግፎ ተጠናቅሮ ይቀመጥ ማለትህ ከሆነ ጥሩ ብለሃል። በትክክል እውነቱ ከወጣና ከተጠና የኔን ወንጀል ባለመድገም ከኔ የምትማሩት ብዙ ነገር አለ። አንተ ባትነግራቸውም ግን ብዙ ኢትዮጵያዊያን መረጃቸውን ሰብስበው ቀን እየጠበቁ መሆኑን አውቃለሁ። የትም ማምለጥ
አይቻልም፤ ወዮላችሁ።

ሰው እድሜው ሲጨምር ይበልጥ ራሱን ይሆናል ይባላል። አንተ ግን በየዕለቱ እኔን ለመሆን እየጣርክ ነው። ምነው አዕምሮህን ለኔ ባሪያ የምታደርገው? አንተ እኔ በየድንጋዩ ስር ስደበቅ፣ ስትማር፣ ስትመራመርና ስታስተምር ነበር።
እኔ በኮሚንስት አመለካከቴ እግዚአብሄርን ሳልፈራ እንዴት የሰውን ህይወት እደማጠፋ ሴራ ሳውጠነጥን ብዙውችን ስረሽን ሳስረሽን፣ አንተ የእግዚአብሄርን ቃል ስታነብ ነበር። ራስህን ሁን እንጂ ጓድ ጠቅላይ ሚንስተር። እኔን ሁነህ በጠባብ ህወሃቶች ከምትወደድ፣ ራስህን ሆነህ፣ ለህሊናህ ተገዝተህ ብትጠላ አይሻልምን?

ሌጋሲ ሌጋሲ የምትሉትና ባስለመድኳችሁ ጥራዝነጠቅ ቃላት የምታደናግሩት፣ ህዝቡ አይገባውም ብላችሁ ይሆን? እኔ ከዚህም ከዛም የባዕዳን ቃላትና ቁንጽል ሃሳብ በመቦጨቅ አንድ ጊዜ ትራንስፎርሜሽን፣ ሌላ ጊዜ ኪራይ ሰብሳቢ
ልማታዊ ባለሃብት እያልኩ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳደናግርና ሳሳስት ኖሪያለሁ። አሁንማ ሰዉ ሲሰክር ሁሉ የሚሰዳደበው ኪራይ ሰብሳቢ እያለ ነው አሉ። እኔ ኪራይ ሰብሳቢ (ሬንት ሲከር) የሚለውን ሃረግ ስዋስ ያደረግኩት መርሁን ላጥላላ በተቃራኒው ግን ከህወሃት የተጠጉትን የስልጣን ባለቤት ብቻ ሳይሆን፣ በኪራይ ሰብሳቢነት መርህ፣ ማለትም መንግስት የሚያደርገውን ቁጥጥር፣ እገዳና አዋጅ በመጠቀምና፣ አዲስ ምርት ወይም አዲስ ሃብት በመፍጠር ሳይሆን፣ የነበረውን በመሰብሰብ፣የመንግስት የሆነውን መሬትና ንብረት በመሸጥ፣መንግስት የሚያወጣውን ጨረታ በአቋራጭ በመውሰድ፣ እንዲበለጽጉ በማድረግ፣ ሚሊዮነሮች እንድሆኑ ነው። በዚህም፣ በቅርቡ አቦይ ስብሃት እንደገለጠላችሁ፣ የኔ ዋናው ዓላማ የአሁኑን ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሃብታቸው ተጽኖ ኢትዮጵያን ሲገዙ የሚኖሩ የአገሪቱን ሃብት የሚቆጣጠሩ፣ የህወሃት የገዢ መደብ መፍጠር ነው። ብዙ ሰው ሊረዳ ያልቻለውና የኔ ውስብስቡ አላማ ከጊዚያዊ ስልጣን መያዝ አልፎ ለመጭወቹ ምእተ ዓመታት የሚቆይ ገዥን መፍጠር ነው። ለዛም ነው የኔን ልጅ እንግሊዝ አገር ሳስተምር፣ አቦይ እንደነገራችሁ የሱን ልጆች ጣሊያንና ቻይና በመላክ፣ እንዲሁም የሌሎች ጓዶቻችንን ልጆች አሜሪካ አውሮፓ ልከን በማስተማርና ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተሻለ አዋቂ በማስመሰል ለቀጣይ ገዥነት እያዘጋጀን ያለነው። በአገር ውስጥ ግን ከመቀሌ በስተቀር ህንጻ ገተርን እንጅ ሌላውን ኢትዮጵያው ማደንቆር፣ ማዳከምና የትምህርት ጥራት እንዲወድቅ ነው ያደረግነው። በተጫማሪም ወጣቱን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለን፣ የጋራ መግባቢያ እንዳይኖረው፣ ካንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ፣ ከጎሳው ውጭ ለአገር እንዳያስብ አድርገነዋል።

በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ማለትህን ሰማሁ። ታዲያ እስር ቤቱን ሁሉ ያጣበቡት የኦሮሞ ወጣቶች፣ ነፃ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪወችና የሙያ ማህበር መሪወች ከኔ ጋር በምን ተጣልተው መሰለህ። እኛ ያገባናል ብለን
በጠመንጃ ሃይል፣ የሺዎችን ህይዎት አጥፍተን፣ ስልጣን ስንይዝ፣የፈለግነውን ሁሉ ያለገደብ ስናደርግ፣ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ግን ሰው የዘር ሃረጉ እየተቆጠረ አይገደል፣ አይፈናቀል፣ የመናገር መብቱ አይታፈን፣ መሰረታዊ ሰበአዊ መብት ይከበር፣ ስላሉና በሰላም በበዕራቸው ስለታገሉ ስንቶቹን በእስር፣ በድብደባ፣ አሰቃየን። ስንቶቹን ገደልን። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት ስላሉ፣ የሰው ልጅ በቋንቋው ተለይቶ መገደል የለበትም ስላሉ አስቃይተን የገደልናቸውና የብዙ ኢትዮጵያዊን ህይወት ያተርፉ የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ሰምቻቸው ቢሆን ኖሮ፣ የብዙ ኑፁሃንን ህይወት ማዳንና የግፍ ግድያን ማስቆም፣ ብቻ ሳይሆን ወንጀለኞች እንኳ ፍትህ የሚያገኙባት ኢትዮጵያን በፈጠርን ነበር። ስህተታችንን ሊጠቁሙ የሚችሉትንና የህዝብ አይን፣ ጆሮና አንደበት የሆኑትን የግል ጋዜጠኞችን አሰርን፣ ብዙወች አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ አደርግን። ዛሬ የመንግስትን ሃብት የሚዘርፉትን ባለስልጣናት የሚያጋልጥ ነፃ ጋዜጠኛ በመታፈኑ፣ ትንሹን ሌባ የሚያጋልጠው፣ ትልቁ ዘራፊ ሆኗል። ስንንቃቸው፣ ስናዋርዳቸውን ስናሳድዳቸው የነበሩ ጋዜጠኞች ናቸው አሉ፣ በአገር ውስጥ እውነቱን የሚናገር ጋዜጠኛ በጠፋበት ጊዜ፣ በተሰደዱበት አገር ሁነው የኔን ዜና ዕረፍት እንኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያሰሙት። ዛሬ ለህይወታቸው ሳይፈሩ የህዝብ መብት ይከበር ብለው በሰላም ስለጠየቁ፣ የኔና አገዛዝ ብልሹ አሰራር ስለተቹ፣ አስረን የምናሰቃያቸው እነ እስክንድር ነጋ፣ ብርሃኑ አራጌ፣ የኦሮሞና የኦጋዴን ወጣቶች፣ንጹሃን የፖለቲካ እስረኞች ካልሆኑ ምን ሊሆኑ ነው።

በህዝቡ መካክል ልዩነትን መፍጠርን የነበረም ልዩነት ካለ ማባባስ ዋናው የመግዣ ስልቴ ነበር። በዘር መካካል የማይታረቅ ልዩነት እንዲኖር መርዛማ የሃሰት ታሪክ በመፍጠርና የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው ብሎ በመቀስቀስ
ብዙዎችን ማሳሳትና በጠባብ የዘር ፖለቲካ እንዲጠመዱ አድርገናል። በሃይማኖት መካከልና ልዩነት መኖሩ የስልጣን እድሜየን ለማራዘምና የኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊዎችን ያዳክምልኛል ብየ በማሰብ፣ ልዩነቱ እየሰፋ ሲሄድ ዝም ብየ
ከመመልከትም አልፌ ልዩነቱን ለማስፋት የሚረዱኝን ግለሰቦች ስልጣን ላይ እንዲወጡና ነገሩን እንዲያባብሱ አድርጊያለሁ። ይህ ሁኔታ ደግሞ በቅርብ ጊዜ የምዕራባዊያንን ቀልብ ለመሳብ ረድቶኛል። በተጨማሪም የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘትና ተቃዋሚዎችን ለማፈን፣ እንደ ሶማሊያ ያለውንም አለመረጋጋት ተጠቅሜበታለሁ።

አኔና ህወሃት በደርግ ጊዜ የነበረዉን ጊዚያዊ ችግርን በዘላቂ በሽታ ተካን። ለመጭው ትውልድ ያተርፍንለት በቀላሉ የማይነቀል የዘረኝነት በሽታ ነው። የጎሰኝነት መጨረሻው ምን እንደሆነ ከሶማሊያ የበለጠ ሊያስተምረን የሚችል
ምን ነገር ይኖራል? በቅርብ ጊዚያት በግብፅ፣ ሶሪያ፣ቱኒሲያና ሊቢያ የተከሰተው ነገር ባግባቡ ላስተዋለው ትልቅ ትምህርት ነው። ከምንም ነገር በላይ የታፈነ ህዝብ በድንገት ተነስቶ ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ አሳይቶናል። የአምባገነኖች
መጨረሻቸው ምን እደሆነ ታይቷል:: ዛሬ አድናቆታቸው ያልተለየህ ሃያላን ቀን ሲጥልህ ከጎንህ እንደማይቆሙ ከሆስኒ ሙባረክ ሁኔታ የተማርክ ይመስለኛል። ብዙወቻችሁ የኔ እድል ላያጋጥማችሁና ባቋራጭ ወደዚህ አትመጡ ይሆናል። ዘመኑ የመረጃ ጊዜ በመሆኑና ከህዝብ የተደበቀ ነገር ሊኖር ባለመቻሉ ለፍርድ በምትቆሙበት ጊዜ የሚከላከልላችሁ ነገር ካለ የራሳችሁ ስራ ብቻ ነው። አስተውሉ። ጥሩ መሪ ችግር ድንገተኛ አደጋ ሁኖ ከመምጣቱ በፊት ያስተውላል ሲባል
አልሰማህምን?

ጨካኝ መሪን ባያሳድገውም ብዙ ጊዜ የሚወልደው አምባገነን መሪ ነው። የኔ ትልቁ ፍራቻ፣ ከኔ የባሰ ጨካኝ መሪ ኢትዮጵያን እንዳይቆጣጠራት ነው። ደርግ አገሪቱን ለኛ እንዳስረከበው፣ እኔና እኔ የፈጠርኩት አምባገነን ስርዓት ደግሞ አገር ሊመሩና ለኢትዮጵያ ሊያስቡ የሚችሉትን ሁሉ ተራ በተራ በማጥፋት፣ የአገሪቱን አንድነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ለሚችሉና በድንገት ስልጣን ላይ ለሚወጡ ክፉ አምባገነኖች ኢትዮጵያን አመቻቸናት። ላንተ ያወርስኩህ ኢትዮጵያ ይህች ናት። ስለዚህ የኔ ዋናው መለዕክት የመለስ ሌጋሲ፣ የመለስ ሌጋሲ የምትለውን ትተህ ራስህን ሁን። እኔም ልረፍበት። የአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መሪ ሁን። ከኔ መጥፎና ዘረኛ አገዛዝ ተማር። ዛሬ በመካድ የነገን ተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም። እኔ የፈጸምኩትን ስህተታት አትድገም። ይህን መልዕክት ደግሞ በስርህ ለተሰለፉት ባለስጣኖችህና ኢትይጵያዊያን አስተላልፍልኝ። ለኢትዮጵያ መልካም ነገር ታደርግ ዘንድ እግዚአብሄር ብርታቱን፣ ጥበቡንና ድፍረቱን
ይስጥህ።

ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን
መለስ ዜናዊ
ከላይኛው ቤት


Ethiopia’s Muslim Activists Pave a Path for Nonviolent Political Activism

$
0
0
By Terrence Lyons
 
A year after Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn came to power following the death of longtime leader Meles Zenawi in August 2012, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) remains firmly in control.. It has continued to govern through a collective leadership that includes three deputy prime ministers from the Amhara, Tigray and Oromo wings of the coalition; Hailemariam hails from the Southern People’s Party. Party discipline and coherence has held, although the lead-up to elections in 2015 may reveal destabilizing fissures. But while older opposition parties and armed movements have been marginalized, a social movement of Ethiopian Muslims is an important new development.

Rapid economic growth has been key to Ethiopia’s stability. The economy grew by more than 10 percent annually over the past decade, and while growth has slowed down it remains higher than the African average. Recent data, however, suggest that earnings from coffee and gold, Ethiopia’s two largest sources of export revenues, have declined. The World Bank also raised concerns that Ethiopia’s boom has relied too heavily upon public investment and that sustained growth will require a significant increase in private investment.

The political opposition to the EPRDF—currently divided into camps based on whether they subscribe to ethno-national or pan-Ethiopian goals and whether they operate in exile or have remained in the country—has struggled to find channels to influence Ethiopian politics. After competitive elections in 2005 and the subsequent crisis that led to the arrest of much of the opposition leadership and the collapse of the main opposition coalitions, the regime effectively criminalized dissent. Restrictions on independent media and civil society limit the ability of Ethiopians to mobilize outside of the structures of the ruling party. The EPRDF’s dominance was evident in local elections this year, in which it and its affiliated parties won all but one seat nationwide.

As a result, opposition political parties that challenged the regime in 2005 now play virtually no role in national politics. The Semayawi, or Blue, party organized a notable demonstration in June and has some following among the youth, but its potential to challenge the regime is limited. Berhanu Nega, a politician who had considerable influence in 2005, is now operating in exile without a significant presence in the country. Repression and the use of anti-terrorism laws, as well as weak structures and leadership, limit the opposition’s ability to operate within Ethiopia.

Meanwhile, several groups, notably the Oromo Liberation Front (OLF) and the Ogaden National Liberation Front (ONLF), remain engaged in protracted armed struggles, but Addis Ababa has effectively managed these military challenges. Oromo nationalism remains potent, but the OLF leadership is divided and discredited. Promising talks between the ONLF and Addis Ababa collapsed in October 2012, but there are officials on both sides that see advantages from a negotiated settlement. The government would like to end the war in order to concentrate on development of the region’s natural gas and other resources. Some Ogadenis recognize that they are unlikely to win the military contest and wish to end the ferocious counterinsurgency campaign in the region. But reaching a durable agreement, a recent International Crisis Group report accurately notes, will require “unprecedented concessions from both sides.”

Finally, the ongoing demonstrations by Ethiopian Muslims, who make up approximately 40 percent of the country, provide an important model of politics outside of the ruling party that relies upon neither armed struggle nor the strategies of electoral competition on a hopelessly lopsided playing field. The demonstrations began 18 months ago to protest government interference in Islamic affairs and the regime’s links to the Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council. The movement has been extraordinarily disciplined and nonviolent and has succeeded in part by focusing on a specific set of issues. Demonstrations have been held after Friday prayers in Addis Ababa but also notably in other towns across Ethiopia.

Muslim activists emphasize that they are operating within the framework of the Ethiopian constitution and that they are not seeking to overthrow the regime. The Ethiopian government, in contrast, has consistently claimed that the protests were organized by extremists bankrolled from overseas and seeking to establish an Islamist state. More recently Addis Ababa has identified neighboring Eritrea as the source of this alleged external support. The movement’s leadership was arrested July 2012 and charged with terrorism in October.

Earlier this month there were clashes between Ethiopian security forces and Muslims reportedly following the arrests of three local imams in Kofele, a town in the Oromo region. A heavy police presence and arrests in Addis Ababa following the Eid al-Fitr ceremonies celebrating the end of Ramadan on Aug. 8 further raised the temperature and tensions. Government spokesman Shimeles Kemal alleged that the arrests were of “Salafist elements who tried to create disturbances.”

Despite the government’s arrests and condemnations, the Ethiopian Muslim demonstrators have shown that sustained, nonviolent political activism is possible in Ethiopia. What is not clear, however, is the movement’s future. Many leaders in the older ethno-nationalist movements, including those with large Muslim constituencies, such as the Oromo and Somali, view the multiethnic nature of the movement with trepidation. Others, including leaders in the Semayawi party, view it as a vehicle to advance pan-Ethiopian political ideas. Some Muslim activists propose a strategy of sustained low-level protest that avoids confrontation and recognize that a quick victory is impossible. To move more assertively would spark a military crackdown, and the movement’s leadership is likely to lose control if there is violence. The key dynamics to watch in the lead-up to elections in 2015 are therefore competition within the ruling party and the potential for the Ethiopian Muslim movement to create new space for political activism.

Terrence Lyons is associate professor of Conflict Analysis and Resolution and co-director of the Center for Global Studies, George Mason University.

Photo: Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, Cape Town, South Africa, May 6, 2011 (World Economic Forum photo).


መንግስት በሙስሊሙ መካከል ክፍፍል መፍጠርን በማሰብ በራሪ ወረቀቶችን መበተን ጀመረ! ~

$
0
0

ከድምጻችን ይሰማ

በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈል ያግዘኛል ያለውን ወረቀት እየበተነ ይገኛል…. ባለፉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ሙስሊሞች በብዛት ይኖሩባቸዋል ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች መንግስት እየበተነው የሚገኘው ወረቀት ሙስሊሙ ሊታገላቸው ይገባል ያላቸውን ወገኖች እንዲያጋልጥ ጠይቋል፡፡

ነሐሴ 17/2005
‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆናችሁ ሙስሊም ወገኖቻችን ሆይ!›› በሚል ርእስ እየተበተነ ያለው ወረቀት ‹‹የገንዘብ ምንጫቸው የተነካባቸው አክራሪዎች›› ባስነሱት ግርግር ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሊሳተፍ አይገባም በሚል ደጋግሞ ይጠይቃል፡፡
ይህ ወረቀት ሸሪአን የደፈሩ፣ ከሌሎች እምነቶች ጋር ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ፣ አሕባሾች ከአገራችን ይውጡ የሚሉ በማለት ‹‹አድመኞች›› በሚል ስያሜ የጠራቸውን ወጎች ሙስሊሙ አንዲታገላቸውና እንዲያጋልጣቸው ያሳስባል፡፡ በተጨማሪም በዚሁ መንግስት በበተነው ወረቀት ‹‹የመውሊድን ስጋ መብላት ጥንብ እንደ መብላት ነው፡፡ በመውሊድ ፕሮግራም ላይ መገኘት ሀራም ነው እያሉ ሲያላዝኑ የነበሩ የነብዩ ጠላቶች›› የሚሉ አረፍተ ነገሮችን በማከል የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እና እንቅስቃሴ እንደተለመደው የክፍፍል አጀንዳ በመፍጠር ለማኮላሸት ጥረት አድርጓል፡፡ መጅሊስን ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚንቀሳቀሱ መንግስትንም ለመገልበጥ ህልም ያላቸው በሚል ወረቀቱ የሚገልጻቸውን ወገኖች ሙስሊሙ ካልታገላቸው ነገ መዘዙ ለራሱ ለሙስሊሙም ይተርፈዋል በሚልም አክሏል፡፡
የዚህ አይነት መሰል መልእክት ያላቸው ወረቀቶች በተለያዩ ጊዜያት በመንግስትና በመንግስታዊ ሃይማኖት ባለሟሎች ሲበተኑ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በወረቀቶቹ በሙስሊሙ መካካል ውጥረት ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ ሀሳቦችን በማጎን በሙስሊሙ መካከል ግጭት ለመፍጠር እና መንግስት እንደሚሻው ችግሩ በሙስሊሞች መካከል ያለ ችግር ነው የሚል ምስል ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ዘር ጾታና አስተሳሰብ ሳይለይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ህብረተሰብ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ ማሳተፉና ሙስሊሙ መንግስት በሚሰራው ተግባር ቁጣውን ያለማቋረጥ ለሁለት ዓመታት ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወቅ ቢሆንም ይህን እውነታ ያልተቀበለው መንግስት ግን ተስፋ መቁረጥ በተጫነው ስሜት ሙስሊሙን ለመከፋፈል የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሎበታል – ፈጽሞ የሚሳካ ባይሆንም፡፡
ከሰሞኑ መንግስት በእስልምና እምነት ተከታዮችና በክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል ግጭት ለመፍጠር ያለሙ ወረቀቶችን በክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ ፖሊሶች ባሉባቸው አካባቢዎች ጭምር ሲበትን መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳ፡፡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሙስሊሞች ያነሱትን የሕገ መንግስቱ ይከበር ጥያቄ በመረዳታቸው መንግስት በሚዲያው ሲሰራቸው የቆዩ መሰል ቅስቃዎች ዋጋ አልባ ሆነው ቆይተዋል፡፡ የተነሱ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችን ለማፈን መብት የጠየቁ ዜጎችን ማሰር፣ መደብደብ፣ መግደል እንዲሁም በሕዝቦች መካከል የግጭት እሳት ለማንደድ መጣር የችግሩን መሰረት የማይፈታና አገሪቷን ወደ ሌላ አሰቃቂ ሁኔታ የሚመራት መሆኑን መንግስት ታሳቢ ሊያደርገው እንደሚገባ ተደጋግሞ በተለያዩ ወገኖች ተጠይቋል፡፡
አላሁ አክበር!


ሰበር ዜና በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላት ይሰግዱ የነበሩ ሙስሊምቸ ተደበደቡ፡፡

$
0
0

በዛሬው የጁምአ ሶላት ላይ በአንዋር መስጅድ በተገኙ እናቶችና እህቶች ላይ የዱላ ናዳ አውርዷል :የኢህዴግ ታጣቂዎች በሙስሊም እህቶቻችን ላይ ይህን አይነት ጥቃት የፈፀመበት ምክንያት ከመስጅዱ ግቢ ውጭ መስገድ አይቻልም በሚል ያልተለመደ ሰበብ መሆኑ መንግስት ሙስሊሙን ለመጨፍለቅ ቆርጦ መነሳቱን በግልፅ የሚያረጋግጥ ተግባር ነው:

የጁምአ ሶላት በሚሰገድባቸው ሁሉም መስጅዶች የሰጋጆች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ከመስጅዱ ቅጥር ግቢ ውጭ ወጥቶ መስገዱ ለአመታት የተለመደ መሆኑ የማይታበል ሆኖ እያለ ዛሬ ወያኔ ህዝበ ሙስሊሙን በተለይም እህቶቻችን ለማጥቃትና አሸማቆ ከመስጅድ ለማስቀረት እንደ ጮማ ምክንያት ተጠቅሞበታል:

በጭቆና ብዛት የሚጠነክር አቋም እንጅ በዱላና በማሸማቀቅ የሚደበዝዝ አላማ ይዘን እንዳልተነሳን ወያኔ መገንዘብ ተስኖታል ።


አምስተኛው ባርነት – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው…

በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየና አስገራሚም ነው። እመለስበታለሁ። ባሪያ ማለት፣ የጌታውን እጅ አይቶ የሚያድር፣ በራሱ ነጻነት የሌለው፣ ሰምቶ የመቀበል እንጅ ሰምቶ የመመለስ መብት የሌለው፣ በግዑዝና በነጻ-ሰው መካከል ያለ ፍጥረት ነው። ባርያ ሰውን ሰው የሚያደርገውን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ በመሆኑ፣ ከሰው ተርታ የሚመደበው ስለሚመገብ፣ ስለሚለብስ፣ መጠለያ ስላለው፣ ቋንቋ ስለሚጠቀም እና አውራጣት ስላለው ብቻ ነው፤ ከዚያ በተረፈ ግን የጭነት እንስሳ ማለት ነው። ባሪያ በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠሩ ክፉና ደጉን የመለየት ስልጣን ቢሰጠውም ፣ ስልጣኑን በጌታው በመነጠቁ ፣ ሁልጊዜ የጌታውን ደግ ነገር ብቻ እያየ እና እያመሰገነ የሚኖር ፍጥረት ነው።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየው አምስተኛው የባርነት መንገድ 40 በ60 ከሚባለው የቤት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው፤ በዚህ የባርነት መንገድ ለመጓዝ የወሰነው ደግሞ ዲያስፖራው ( በውጭ የሚኖረው) ኢትዮጵያዊ ነው። መንግስት ለዲያስፖራው 40/በ60ን ሲያዘጋጅ ሁለት አላማዎችን ታሳቢ አድርጎ ነው- ዲያስፖራው ጥሮ ግሮ ያገኘውን ሀብት ሰብስቦ ደቋናውን ለመሙላት እና ዲያስፖራው ስለነጻነቱ እንዳይጠይቅ ወይም መንግስትን እንዳይቃወም አፍ ለማዘጋት።

40 /በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ እናት እና አባቱ፣ እህትና ወንድሙ፣ በአጠቃላይ የአገሩ ሰዎች ቢገደሉ፣ ቢታሰሩ ፣ ቢሰደዱ፣ ቢራቡ ፣ ቢጠሙ፣ ” ለምን?” ብሎ አደባባይ ወጥቶ የመጠየቅ እና የመቃወም ነጻነት አይኖረውም፤ ነጻነቱን በ40/በ60 ተገፎአል። ለሌላው መብት ሊሟገት ቀርቶ፣ በጥፊ ቢመታም እንኳን፣ “ጥፊው እንዴት ይጣፍጣል፣ እባክህ ግራ ጉንጨንም ድገምልኝ” ከማለት ውጭ፣ “ለምን ትመታኛለህ?’ ብሎ የአባትና እናቱን ወኔ ቀስቅሶ ብድሩን የመመለሻ ልብ አይኖረውም። እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው፣ ብርሀኑ ነጋ፣ እና ሌሎችም፣ ከስጋቸው ድሎት ነጻነታቸውን ያስቀደሙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ባርነት በቃን በማለታቸው፣ ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት ተነጥቀዋል። 40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ ስለወገኑ ለመጮህ ከእንግዲህ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከተሞች እጅግም አይታይም፣ ለይሉንታ ቢታይ እንኳ ፊቱን በወረቀት ሸፍኖ ከሁዋላ ከመሰለፍ የዘለለ ሚና አይኖረውም። በነጻነት አገር እየኖሩ ገንዘብ ከፍሎ፣ በፍላጎት ባርነትን መምርጥ ማለት ይህ አይደለምን? የሚገዛ የለም እንጅ እነዚህ ሰዎች እኮ መንግስት ቢሸጣቸው እንኳ ምንም የሚናገሩ አይደሉም። ገንዘብ ተከፍሎ ባሪያ አድርጉን ብሎ የሚጠየቅበት አሰራር በታሪክ ታይቶ ይታወቃልን?

በአገር ቤት ያለው ህዝብ ለ 20/በ80 ቢመዘገብ አይገርመኝም፤ በባርነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ፣ አንድ ቀን ራሱን ነጻ እስኪያወጣ፣ ለጊዜው ተመችቶት ይኑር። ባሪያም እኮ ልብሱን ይቀይራል፣ የምኝታውን ሳር ተባይ ሲወርበት በሌላ ሳር ይተካዋል፤ ባበርነት ስር ያለው የአገር ቤት ሰው በነፍሱም በስጋውም ሊበደል አይገባውም፤ ቢያንስ እስከ ጊዜው በስጋው ይደሰት። ዲያስፖራው ግን የኢትዮጵያን ምድር ከለቀቀባት ጊዜ ጀምሮ ከባርነት ነጻ ወጥቷልና በነጻነት መኖር የሚችለበት እድል አለው፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ነጻነት ለመታገል ሁኔታው ተመቻችቶለታል፤ ይህን ነጻነቱን ግን እራሱ ገንዘብ ከፍሎ ሊሸጠው ይደራደራል። ፍርፋሪ እየተጣለለት ወደ ቄራ የሚወሰድ እሪያ መጨረሻው ሞት እንደሆነው ሁሉ፣ 40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራም መጨረሻው ባርነት ነው። አምስተኛው ባርነት!



The Totolamo-Kofele blood bath victims named, death toll still climbing

$
0
0

The Horn Times update August 24, 2013 by Getahune Bekele-South Africa  “Wolahi, Wolahi…” swears 85 year old Totolamo village barley farmer and cattle herder Hajji Abdinur Shifa when a reporter asked him if he know any terrorist hiding in his village. His face looks like a paint of sorrow and grief.. His wife affectionately called by the villagers, Adiyo, was too fragile to talk about the August 3 2013 blood bath that turned their agriculture and livestock rich village into an inferno.Totolamo-Kofele blood bath victims named

“My son took three bullets and died a day later at Sashemene general hospital. The body that was weakening by fasting could not respond well to treatment and he succumbed to his wounds without saying goodbye. His killers (federal police commandos) did not allow us entry to the hospital. My son Abdulkarim is dead but he will live in my heart until I join him in paradise…,” the respected elder said wiping his tears with a piece of garment.

On that fateful day, 3 August 2013, Abdulkarim Abdinur Shifa, 39, was at Erob Gebeya mosque loading onto his van sacks of barley, corn, and potato donated by farmers to be distributed among the needy in the city of Sashemene for Eid celebration.

When he was about to leave, bullets started raining down and the scream of women and children filled the salubrious air of Totolamo. Tigre people Liberation Front gunmen in police uniform massacred eleven people including an elderly imam and an infant.

The tragedy touched every household from Totolamo to Kofele in southwest oromyya.

In the land famed for its sylvan beauty, despite the aroma of ripe corn, the stench of death still hangs in the air. The approach of the delightful month of September did not lift the gloom of the August blood bath. According to our sources from Sashemene general hospital, currently the death toll stands at sixteen- all Muslims and close relatives.

The Horn Times manage to obtain the names of 14 victims of the August 3 slaughter…

1. Adam Jamal 2. Lenco Jilcha 3. Habib Wabe 4. Gachano Tuse 5. Muhammad Debel Ouse 6. Jamal Arsho Arsi 7. Muhammad Eidao 8. Amman Buli 9. Muhamud Hassan 10. Rashid Burka 11. Abush Ebrahim 12. Mamush Ebrahim 13. Tuke Besso 14. Abdulkarim Abdinur Shifa

Furthermore, two hundred young men arrested on 3 August 2013 are still languishing in Kofele town police prison without any charge.

infohorntimes@gmail.com


የባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አፈና ተፈፀመበት

$
0
0

Millions of voices for freedom - UDJአንድነት ታርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት፡፡ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ… አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መንግስት ያደራጃቸው ሀይሎች ሁከት ለመፍጠር መዘጋጀታቸው በመታወቁ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ሰልፉ እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡


ሰበር ዜና ከባሌ ሮቤ: የባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አፈና ተፈፀመበት

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መንግስት በባሌ ሮቤ ያሰበውን የደም ማፋሰስ ሴራ አክሽፈዋል   አንድነት ፓርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት…. ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መንግስት ያደራጃቸው ሀይሎች ሁከት ለመፍጠር መዘጋጀታቸው በመታወቁ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ሰልፉ እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡ – See more
የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መንግስት በባሌ ሮቤ ያሰበውን የደም ማፋሰስ ሴራ አክሽፈዋል፡፡የአከባቢው ባለስልጣናት ያደራጇቸው ሀይሎች ሰልፉ በሚካሄድበት ወቅት ግጭት ለፈጥሩ ተዘጋጅተው እንደነበር ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ አመራሮች በሳል ውሳኔና ሀገር ወዳድ የባሌ ዞን የፖሊስ አካላት ለፓርቲው በሰጡት መረጃ መንግስስታዊ ውንብድና ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ -
በሌላ ዜና
አንድነት ፓርቲ በፍቼ ከተማ እያካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በአማርኛ በኦሮሚኛ መፈክሮች እየተስተጋቡ ነው ፡፡

የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ” ፣
መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም” ፣
ሙስና ስርአቱ መገለጫ ነው”፣
ውሸት ሰለቸን
የፀረሽብር ህጉ የህገመንግስት ጥሰት ነው” የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

Breaking News: በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ሽያጭ የተጠራው ስብሰባ ሳይጀመር ተበጠበጠ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሴንት ፖል ሚኒሶታ የአባይን ቦንድ ለመሸጥ የኢትዮጵያ መንግስት አዳራሽ ተከራይቶ ለዛሬ ኦገስት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከ ቀኑ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት ስብሰባ የጠራ ሲሆን ስብሰባው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ብጥብጥ ተነሳ..

 

በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን “ወያኔን አናምንም፤ 2 ሰዓት ብሎ ጠርቶ ስብሰውን ቀድሞ ሊጀምርና ሊነሳበት የታቀደውን ተቃውሞ ሊያከሽፍ ይችላል” በሚል ገና ከጠዋቱ ስብሰባው ይደረግበታል የተባለበት አዳራሽ በር ላይ ሲጠባበቁ ቆይተዋል። ልክ ስብሰባው ሊጀመር 1 ሰዓት ሲቀረው አንድ የስርዓቱ ደጋፊ የሆነ ሰው ካሜራ ይዞ “ከአባይ በፊት ሰብአዊ መብት ይከበር፤ የታሰሩት ይፈቱ” በሚል ለተቃውሞ የተሰባሰበውን ሕዝብ ሊቀርጽ ሲጠጋ ሕዝቡ “ሃገር ቤት ቪድዮ የቀረጻችሁት ሳያንስ እዚህ ልትቀርጹ ነው ወይ?” በሚል ልጁን ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ካሜራውን ሰባብረውበታል ያሉት የአይን እማኞች ወዲያውም ከ20 የሚበልጡ የሴንት ፖል ከተማ ፖሊስ መኪናዎች አካባቢውን በመክበብ ብጥብጡን አርግበውታል።

የሴንት ፖል ፖሊሶች መቃወም ትችላላችሁ፤ ሆኖም ግን ሰውን መደብደብ አግባብ አይደለም በሚል ለተቃውሞ የተዘጋጁትን ሲበትኑ ሕዝቡም “በአባይ ስም የሚደረገው ሕገወጥ ስብሰባ ነው” በሚል ለፖሊስ በማመልከታቸው ፖሊስም የቦንድ ሽያጩ አይደረግም ሲል ቃል ገብቷል።

ሕዝቡ ፖሊስ የቦንድ ሽያጩ ተሰርዟል ቢላቸውም ማረጋገጫ የለንም በሚል በአካባቢው የሚገኝ ሲሆን ብጥብጡን ተከትሎ በሴንት ፖል ፖሊስ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ወዲያው ተለቀዋል።

የኢሕአዴግ መንግስት በሚኒሶታ የአባይ ቀን በሚል ቦንድ ለመሸጥ የተከራየው የላኦ ኮምዩኒቲ አዳራሽ አድራሻ 320 University Ave W St Paul, MN 55103 ነው።

ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ከፎቶ ግራፍ እና ቪድዮዎች ጭምር ይዛ ትመለሳለች።

ይጠብቁን፤ ይመለሱና ይመልከቱን።


ኢሕአዴግ እሁድ በአ.አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፤ ድምጻችን ይሰማ “መንግስት ሙስሊሙን እየዘለፈ ነው” አለ

$
0
0

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዛሬ እንደዘገበው “አክራሪዎች በእምነት ስም የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመቃወም እሁድ ነሃሴ 27/2005 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ” ብሏል… በሌላ በኩል ድምጻችን ይሰማ “አክራሪነትን ለመዋጋት ተብለው በተዘጋጁ ስብሰባዎች ጸረ እስልምና የሆኑ ዘለፋዎች እተበራከቱ ነው!” ሲል ተቃውሞውን አሰማ።

ኢሕአዴግ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በሰላም አብሮ ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲል ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ “ለእስልምና ጥላቻ ያላቸው የመንግስት ሃላፊዎችና ካድሬዎች አጋጣሚውን የእስልምናን ሃይማኖት ለማራከስ ተግባር እያዋሉት ነው” ብሎታል።

“ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በእምነት ስም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ ጥረት የሚያደርጉ አካላትን በመቃወም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡” ሲል የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲዘግብ ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ “መንግስት አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል እያዘጋጃቸው ባሉ ስብሰባዎች የእስልምና ሃይማኖት ላይ ዘለፋዎች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በየክፍለ ከተማውና ወረዳዎች ለካድሬዎች እና የሀይማኖት አባቶች ተብለው በሚካሄዱ ስብሰባዎች ‹‹የእስልምና ሃይማኖት የአክራሪዎች መፈልፈያ ነው››፣ ‹‹እስልምና የሚባል ነገር ነው ሰላም የነሳን›› ከሚሉ ተነስቶ ሌሎችም በርካታ ስድቦች እና ዘለፋዎች እየተንጸባረቁ ነው፡፡ በተለይ ባለፈው ረቡእና ሐሙስ የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባዘጋጀውና በስድስት ኪሎ ስብሰባ ማእከል በተደረገው ስብሰባ ሲንጸባርቅ የነበረው ስሜት ሕዝቡ ያወረዳቸው የመጅሊስ ሹመኞችን ጨምሮ ኢማሞችን ሁሉ አንገት ያስደፋ እንደነበር ታውቋል፡፡ ብዙዎችንም የመንግስትን አካሄድ በድጋሚ እንዲያጤኑት የጋበዘ ሆኗል፡፡” ብሏል።

“የሁሉም ሀይማኖት ተከታዩች በተገኙበት የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሀይማኖት ተከታዮቹ አብሮ በሰላም ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በርሁን አርአያ ገልጸዋል” ሲል ዜናውን ያተተው ኢቲቪ የሀይማኖት እኩልነት ባልተከበረበት ወቅት ጭምር ህዝቡ ጠብቆ ያቆየውን የመቻቻልና የአብሮነት እሴት ጥቂት አክራሪዎች ለማደፍረስ መሯሯጣቸውን ለመቃወም ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በዕለቱ እንደሚሳተፉ ርዕሰ ደብር በርሁን አርአያ ጠቁመዋል ካለ በኋላ እሁድ 27/2005 በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሁሉም ቤተ እምነት መሪዎች እና ተከታዮቻቸው የሰላም መልእክቶችን በመያዝ ከየአቅጣጫው ወደ መስቀል አደባባይ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል” ሲል ዘገባውን አጠናቋል።

ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ “በዚህ በቢሮ ሀላፊው አቶ ጸጋዬ ሀይለማርያምና በደህነነት መስሪያ ቤት ሀላፊዎች በተመራው ስብሰባ የተገኙና ቀድመው ንግግር የሚያደርጉበት አጀንዳ የተሰጣቸው የፓርቲ ካድሬዎች በከፍተኛ ሁኔታ የእስልምናን ሃይማኖት የሚያራክሱ ንግግሮች ሲያደርጉ ከመታየታቸውም በላይ አንዳንዶች ለእስልምና ያላቸውን ጥላቻ ከመግለጽ ጭምር አንኳ አልተቆጠቡም፡፡ የሱና ምልክት የሚንጸባረቅባቸው አካላትን መንግስት ሊታገላቸው እንደሚገባ ያሳሰቡት እነዚህ ካድሬዎች የእስልምና ሃይማኖት መንፈሳዊ ተግባራትን ሁሉ የአክራሪነትና አሸባሪነት መገለጫዎች አድርገው ሲፈርጇቸው ተደምጧል፡፡ አቶ ጸጋዬ ኃይለማርያም ከመንግስታዊው ሃይማኖት የማጥመቅ ዘመቻ ጀምሮ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ሲዘልፉና በሙስሊሞች መካከል የልዩነት እሾህ ለመትከል ሲሯሯጡ የቆዩ ግለሰብ እንደሆኑ በድምጽ ማስረጃ ጭምር መጋለፁ ይታወሳል፡፡” ብሏል።

Short URLhttp://www.zehabesha.com/amharic/?p=6736

posted by Gheremew Araghaw

 

Rate this:

 


Viewing all 931 articles
Browse latest View live