Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 937

ኤቨርተን ከሊቨርፑል፡ የመርሲሳይ ደርቢ ለመጨረሻ ጊዜ በጉዲሰን ፓርክ ይደረጋል

$
0
0
የመርሲሳይድ ደርቢ

ጉዲሰን ፓርክ ማብቂያው ደርሷል።

ለዘመናት የኤቨርተን ስታድየም ሆኖ ያገለገለው ጉዲሰን ፓርክ በያዝነው የውድድር ዘመን መጨረሻ ይፈርሳል። አዲሱ ብራምሊ-ሙር ዶክ ስታድየም እየተጠናቀቀ ነው። በጉዲሰን ፓርክ የመጨረሻው የመርሲሳይድ ደርቢ ረቡዕ ምሽት ይካሄዳል። ኤቨርተን ሊቨርፑልን በጉዲሰን ፓርክ ሲያስተናግድ ለ120ኛ ጊዜ ነው። ሁለቱም ክለቦች 41 ጊዜ ድል ቀንቷቸዋል። የዛሬውን ማን ይረታ ይሆን?ይህ ጨዋታ ባለፈው ታኅሣሥ ነበር እንዲሄድ መርሀ ግብር የወጣለት። ነገር ግን በወቅቱ በነረበው ከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ግጥሚያው እንዲዘገይ ሆኗል። በዴቪድ ሞየስ አሠልጣኝነት እያንሰራራ ያለው ኤቨርተን የሊቨርፑልን የዋንጫ ጉዞ ያሰናክለው ይሆን? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው። የመርሲሳይድ ደርቢ በጉዲሰን ፓርክ መካሄድ የጀመረው በአውሮፓውያኑ 1894 ነው። የመጀመሪያውን ጨዋታ የረታው ኤቨርተን ነበር። ሁለቱ ቡድኖች 119 ጊዜ ሲገናኙ ኤቨርተን 141 ጎሎች ሲያስቆጥር ሊቨርፑል ደግሞ 147 ኳሶች ከመረብ አገናኝቷል። ምንም እንኳ ሊቨርፑል ከከተማ ተቀናቃኙ ኤቨርተን የተሻለ ስኬታማ ቢሆንም ጉዲሰን ፓርክ ግን ሁሌም ፈታኝ ስታድየም ነው። ካለፉት 12 ደርቢዎች ዘጠኙ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ ሊቨርፑል ሁለት ጊዜ፤ ኤቨርተን ደግሞ አንድ ጊዜ አሸንፏል። ኤቨርተን ባለፈው የውድድር ዘመን የየርገን ክሎፕን ቡድን 2- 0 በመርታት ለዋንጫ የነበራቸውን ግስጋሴ ማሰናከሉ የሚታወስ ነው። ዴቪድ ሞየስ ድጋሚ ወደ ቀደመው ክለባቸው ከመጡ በኋላ ኤቨርተን እየተነቃቃ ይመስላል። ሞየስ ከመሾማቸው በፊት ከ19 ጨዋታዎች ሦስቱን ብቻ ነበር ማሸነፍ የቻለው። ኤቨርተን ያለፉትን ሦስት የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች በመርታት ከወራጅ ቀጣናው በ9 ነጥብ ርቆ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሞየስ ኤቨርተንን ከአውሮፓውያኑ 2002 እስከ 2013 ድረስ አሠልጥነዋል። ቡድኑን ከወራጅ ቀጣና ከማውጣታቸውም በላይ አንድ ጊዜ ለኤፍ ኤ ዋንጫ ፍፃሜ አብቅተውታል። በጉዲሰን ፓርክ ለመጨረሻ ጊዜ የሚካሄደው የመርሲሳይድ ደርቢ ረቡዕ ምሽት 4፡30 ይጀምራል። ሊቨርፑል ይህን ተስተካካይ ጨዋታ ካሸነፈ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አርሰናል በ9 ነጥብ ርቆ ለዋንጫው የሚያደርገውን ግስጋሴ ይቀጥላል። ቀያዮቹ ባለፉት 19 ጨዋታዎች አልተሸነፉም። 14 ጊዜ ድል ሲቀናቸው፤ 5 ጊዜ አቻ ወጥተዋል። አልፎም በ19 ጨዋታዎች ግብ አስቆጥረዋል። በ21 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሰንጠረዥ የሚመራው ሞሐመድ ሳላህ ከሜዳው ውጪ 13 ግቦችን ሲያስቆጥር 8 ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አመቻችቶ አቀብሏል።

የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ክሪስ ሱተን ባስቀመጠው ግምት የመርሲሳይድ ደርቢ 1 አቻ ይጠናቀቃል ብሏል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 937

Trending Articles