በኢትዮጵያ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ዘርን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ ድርጅት በ1942 ዓ.ም ለጣሊያን በባንዳነት አድረው ሲያገለግሉ በነበሩ የትግራይ ጎጠኞች ተመሠረተ… ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ሀገራችን በፋሽስት ጣሊያን ተወራ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ደረታቸውን ለጦር እግራቸውን ለጠጠር ሳይሰስቱ እየሰጡ አገራቸውን ለወራሪ አናስደፍርም ብለው በየጋራውና በየሸንተረሩ ተሰማርተው በኋላ ቀር መሣሪያ ጠላትን ሲፋለሙ ፤ለገንዘብ ወይም ለርካሽ ቁሳዊ ጥቅም ሲሉ ለጠላት አድረው ያገራቸውን ምስጢር የሸጡ፣ከጠላት ጐን ተሰልፈው አገራቸውን የወጉና ያደሙ ባንዳዎች “ቀዳማይ ወያኔ” ብለው በዘር ተደራጁ።
“ቀዳማይ ወያኔ” የሌቦችና የዘራፊዎች ስብስብ ስለነበረ፤በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትዕዛዝ በልዑል ራስ አበበ አረጋይ አማካኝነት በ1943 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። ይሁን እንጂ በ1966 ዓ.ም የተደረገን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ ሌላ ወያኔ በ1968 ዓ.ም በአቶ ስብሃት ነጋ ተፈጠረ። ይህ በአቶ ስብሃት ነጋ የተመሠተው ሀገር በቀል ፋሽስት ማዕከላዊ አቋሙ “አማራ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው” የሚል በመሆኑ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ የአማራን ነገድ ለማጥፋት ዕቅድ አውጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።
አቶ ስብሃት በዘረኝነትና በአልኮል የደንዘዘ ኋላቀር ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተመለከት ባላው የተሳሰተ የፖለቲካ አቋም ይታወቃል። ለአብነት “ገዛ ተጋሩ” በተሰኘው የዘረኞች ውይይት ክፍል ውስጥ አሰብ ወደብና የአማራ ነገድን በተመለከተ የሚከተለውን ዘረኛ አቋም አንጸባርቋል። “አሰብ የኤርትራ ወደብ ነው። በዚህ ወደብ ላይ የባለቤትነት ጥያቄ የሚያነሱ የደርግ ሥርዓት ናፋቂና ነፍጠኞች ብቻ ናቸው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት አማራ መሬት ስንገባ እናድንሃለን እያልነው የአማራ ገበሬ በሙሉ የወጋንም ንቃተ ህሊናው ትንሽ ስለሆነ ነው ብሏል።”
ይህ ከቂምና ከጥላቻ በስተቀር ፍቅርን የማያውቅ የወያኔ ትግሬ በእርጅና ዘመኑ እንኳ ራሱን መግራት ያቃተው በመሆኑ፤ “ስልጣንን ከኦሮቶዶክስና ከአማራ እጅ ነጠቅናት ይህም የትግላችን ውጤት ነው” ማለቱን ሰምተናል። ባለፉት አርባ ዓመታት የትኛው አማራ፤ የትኛው ኦሮቶዶክስ ስልጣን ይዞ ነበር ቢባል ግን መልስ የለውም። የከሃዲው ስብሃት ነጋ አባባል ግን ለአማራ ነገድና ለኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን ያለውን ሥር የሰደደ ጥላቻ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። መለስ ዜናዊም በህይወት ዘመኑ ለቤተክርስትያኒቷና ለአማራ ነገድ ባለው ጥላቻ መሠረት ቤተክርስትያኒቷን ለማፍረስ የቻለውን ሁሉ አድርጓል። የአማራንም ነገድ ለማጥፋት ብዙ አረመኔያዊ ተግባራትን ፈጽሟል።በእርሱ የአገዛዝ ዘመን 2.4 ሚሊዮን በላይ አማራ ከቁጥሩ ጎድሎ የት እንደገባ ሳይታወቅ ቀርቷል።
ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የአማራ ነገድ የት ገባ ተብሎ የተጠየቀው መለስ ዜናዊ ያለምንም ሃፈረትና ታሪክና ሰው ምን ይለኛል ሳይል “በኤድስ አልቋል” ብሎ በድፍረት መልስ ሰጥቷል።ይሄ በጣም አሳፋሪ እና ነውር ነገር ነው። በተለይም አገርን እመራለሁ ብሎ በህዝብ አናት ላይ ከተቀመጠ ሰው አንደበት ሲወጣ። የወያኔ ፋሽስቶች እንዲህ ያለውን አሳፋሪንና ነውር ነገረን ለይተው አያውቁም ማለት አይቻልም። አንድን ነገድ ለይተው “በኤድስ አለቀ” ብለው መናገራቸው በአማራ ነገድ ላይ የፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በግልፅ ያረጋግጣል።
በአጠቃላይ የወያኔ ፋሽስቶች ለአማራ ነገድ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋትና ወንጀል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ተደርሷል።የሩቁን እንኳን ብንተወው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ተፋፍሞ በቀጠለው አማራን ከቤትና ከንብረቱ በግፍ የማፈናቀል ዘመቻ ከ100 በላይ አማሮች ተገድለዋል። በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ጎዳና ላይ ተጥለው በርሃብ ፣በብርድና በበሽታ በመሞት ላይ ይገኛሉ።ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ማስቆምና ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ቢሆንም ዘራቸው በመጥፋት ላይ ያለው የአማራ ነገድ አባላት ራሳቸውን ለማዳን የወያኔ ፋሽስቶችን ማግለልና ከህብረተሰቡ እንዲነጠሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
Related articles
- በኖርዌይ የወያኔ ጀሌዎች ሲደነብሩ ሲባረሩ የሚያሳየውን ፎቶ (addis12.wordpress.com)
- ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ! (yourfreedomvoice.wordpress.com)
- Ethiopia: The sorry and dangerous acts of Woyane ethnic warlords and their stooges (ethioviews.com)
- Ethiopian Youth Initiative: Nurturing the Culture of Giving Back (kweschn.wordpress.com)
- Ethiopia: The sorry and dangerous acts of Woyane ethnic warlords and their stooges (ethioviews.com)
- የንጉሠ – ነገሥቱ ንግግር፣ የዛሬ ሃምሳ አመት (beaimero.wordpress.com)
