Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 945

የመሬት መንቀጥቀጦች አስከፊ የሚሆኑባቸው 7 ምክንያቶች

$
0
0

ማክሰኞ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም. ቻይና ቲቤት ውስጥ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በርካታ ሰዎች ሞተዋል። በርዕደ መሬት መለኪያ 7.1 የተመዘገበው የመሬት ነውጥ በአውሮፓውያኑ 2019 አሜሪካ ከተከሰተው ጋር ይመሳሰላል።

በአሜሪካ ግን አንድም ሰው አልሞተም። ከሰዎች ሞት እና ንብረት ውድመት አንጻር የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያደርሰውን ጉዳት የሚወስኑ ሁኔታዎችን እንመልከት።

1. ርዕደ መሬቱ መጠን እና የሚቆይበት ጊዜ

የመሬት መንቀጥቀጥ የሚለካው በሞመንት ማግኒትዩድ ስኬል ሲሆን፣ ይህም ሬክተር ስኬልን የተካ መለኪያ ነው።

ርዕደ መሬቱ የሚሰጠው ቁጥር በምን ያህል ኃይል ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ይጠቁማል።

ከ2.5 ያነሰ ከሆነ በመለኪያ መሣሪያ እንጂ ለሰዎች ላይሰማ ይችላል።

እስከ 5 ሲደርስ ግን ሰዎችም ይሰማቸዋል፣ ጉዳትም ያደርሳል።

የቲቤት የመሬት መንቀጥቀጥ 7.1 የደረሰ ሲሆን፣ አምና በቱርክ እና ሶሪያ የተከሰተው 7.8 ተመዝግቧል።

ይህ መጠን ከስምንት ከፍ ያለ ከሆነ “አደገኛ” ይባላል። በተከሰተበት አካባቢም ውድመትን ያስከትላል።

ርዕደ መሬቱ ከጥንካሬው ባሻገB መንቀጥቀጡ የቆየበት ጊዜም ይታያል። ምክንያቱም ጉዳት የሚያደርሰው በቆየበት ጊዜ ልክ በመሆኑ ነው።

የፓስፊክ ኖርዝዌስት ሴስሚክ ኔትወርክ “አነስተኛ ርዕደ መሬት ጥቂት ሰከንድ ይወስዳል። በ2004 በሱማትራ [ኢንዶኔዢያ] የተከሰተው ዓይነት ሲሆን ደግሞ እስከ ሁለት ደቂቃ ይቆያል” ይላል።

ዜና ምንጭ BBC NEWS


Viewing all articles
Browse latest Browse all 945

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>