ኦባንግ ሜቶ
አሰላሙ አሌይኩም፣ እንደምን አላችሁ፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone፡፡ የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡
ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ ይህም ቀውስ በአንድ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ለዓመታት ሲጠራቀምና ሲከማች የቆየ ነው፡፡ የአገራችን የወደፊት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስበን በመሆኑ እናንተም ይህንኑ ሃሳብ እንዳቀርብ በጠየቃችሁኝ መሠረት እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በመሥራት ለአገራችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ማምጣት እንዴት እንደምንችል ሃሳቤን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
በቅድሚያ ጥያቄዎችን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ፤ ባለፉት ዓመታት ካገኘነው ውጤት በተሻለ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የምናበረክተው አስተዋጽዖ ምንድነው? ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ስናካሂደው የነበረው ትግል ነጻነትና እኩልነት የሰፈነባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድንመሠርት ያላስቻለን ለምንድነው? ካለፉት የትግል ልምዶቻችን እንደገና እንድንቃኘው የሚያስፈልጉን የትኞቹን ነው? በለመድነውና በባህል በተቆራኘን ራሳችን ለሽንፈት በሚዳርግ መንገድ አሁንም መቀጠል ይገባናል? ወይስ የእኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ውስጥ የተካተተ ባይሆንም ከሌሎች ቡድኖች በሚደርሱብን ምክንያት አጸፋ መመለሳችንን እንቀጥል? መፍትሄ ፍለጋ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ከመንገድ ወጥተናል? ከወጣንስ እንዴት መመለስ እንችላለን? ካልወጣን ያለምነውን ከግብ ማድረስ ለምን ተሳነን? ለችግራችን መፍትሄ እንዳናገኝ የሳትነው የት ላይ ነው?
[1] አቶ ኦባንግ ይህንን ጽሁፍ በንግግር ያቀረቡት ሐምሌ 9፤2008 (July 16, 2016) የኢትዮጵውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት በተጠራው ስብሰባ ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በአገራችን ፖለቲካ ከተከሰተው ለውጥ አኳያ በጽሁፉ ላይ መጠነኛ ለውጦች ተደርገዋል፡፡
–
