Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የ 2007 5ኛው አጠቃላይ ምርጫ የመጨረሻዋቹ ቀናት ገመናዎች በአስቸካ ይ ይታረሙ

$
0
0

/ ከዓረና ትግራይ የተሰጠ መግለጫ /  ዓረና መድረክ ያለፉት ምርጫዎች አስከፊ ገፅታዎችና በተለይ በ2002 አጠቃላይ ምርጫ ገዢው ፓርቲ የፈፀመው የዓፈና ትግባርና ውጤቱ በመቃወም ችግሩ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ሲታገለው እንደቆየና በ2007 ዓ/ም የሚካሄደው 5ኛው አጠቃላይ ምርጫ በተመሳሳይ ችግር እንዳይደናቀፍ በሃገሪቱ የፖለቲካ ድባብና ለነፃ ምርጫ ጋሬጣ በሆኑ ጉዳዮች ከመንግስት ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቅርቦ በገዢው ፓርቲ ህወሓት/ ኢህአዴግ ግትር አsም ሳይሳካ ቀርቶአል ..

ዓረና መድረክን ያሳሰበው በ2007 ምርጫ የተደቀነው ችግር ግን አልቀረም በምርጫ እቅድ ደረጃ የተቃዋሚዎች የምርጫ ድምፅ ዜሮ ለማድረግ የሚያስችል የተባለለት የአፈና እቅድ በመንደፍ መጀመሩን በወቅቱ በመረጃ አስደግፈን ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አድርገናል ፡፡

ምርጫ 2007 ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን በጠላትነት ፈርጆ በክትትል ወጥመድ በማስገባት የሰላማዊ ተወዳደሪ ፓርቲዎችን የነፃነት ስሜት በመግደል መጀመሩን፡ሓምሌ 2006 ዓ/ም የወጣው የህወሓት እቅድ ዋቢ በማድረግ ለህዝብ ይፋ ማድረጋችን ይታወሳል ፡፡ የምርጫ ውድድር መጀመር ይፋ እንደተደረገም በ 2007 ዓ/ም ምርጫ የተቃዋሚዎች ድምፅ ዜሮ ለማድረግ በሚል የምርጫ ህጉን በሚንዱ የማስፈፀምያ ስልቶች ታጭቆ የወጣው የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ እቅድ ህዝቡ እንዲያቀው ይፋ ማድረጋችን ይታወቃል፡፡ ከታሕሳስ 2007 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው ይህ ሰነድ ሲመረመረመር መሰረታዊ የነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ምሶሶዎችን የሚንድ እና የህወሓት / ኢህአዴግ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ባህሪ ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ የምርጫ እቅድ ሰነዱ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ለልማት ብቻ የሚያገለግል የመንግስት መዋቅር እንጂ የፓርቲ መዋቅር አይደለም ሲባልለት የሰነበተው ከምርጫ 2007 ዓ/ም አካያ የህዝቡን ውሳኔ ለመቆጣጠር እስከ (1-5) ኔትወርክ የሚደርስ ኣደረጃጀት መፍጠሩ ለህ.ወ.ሓ.ት/ኢህኣዴግን እንደምቹ ሁኔታ በመቁጠር ለ5ኛ ብሄራዊ ምርጫ ለማዘጋጀት እንደማይቸገር ያስባል፣ እቅዱመራጭ ህዝብ በልማት ቡድን’በኔትዎርክንና በኣባ ወራን ጨምሮ ኣንጥሮ ማወቅ ራሱ የቻለ ተግባር አድርጎ ያቅዳል፣ የቀበሌዎች የምርጫ እቅድ እስከ ታችኛው የልማት ጉጅሌና ኔትዎርክ የሚባሉ የስር ኣደረጃጀቶች በዕድሜና በፆታ መለየት ይላል፣ የመራጮች ምዝገባ ምርጫ ቦርድ ካስቀመጠው ለምሳሌ የ ሕንጣሎ ወጀራት ከ ጥር 1-10 እንዲጠቃለል ያቅዳል፣የመራጮች ምዝገባ በየልማት ቡድኑ እንደሰራዊት በተደራጀ ኣን ይመዘገባል ይላል ፣
የምርጫ ምዝገባ በምርጫ ቀን ለማክተት፣ በምርጫ ዋዜማ ለሚደረገው የድምፅ ኣወጣጥ ልምምድ በሚያመች በተፋሰስ ልማታዊ ጉጅሌና በኔት ወርክ መፈፀም አለበት ብሎ ያቅዳል፣ የመራጮች ምዝገባ ኣስካል(ልማታዊ ቡድን)ለቀበሌ ‘ቀበሌ ለወረዳ፣ ወረዳ ለዞን በየዕለቱ የምዝገባ ሪፖርት ያደርጋል፣ በቀበሌ ፕሮፖጋንዳ’ኣደረጃጀት’ሊጎች’የትምህርት ዘርፍ የምርጫ ጉዳይ እንዲመሩ ሲደረግ የቀበሌ ኣስተዳዳሪ ደግም ምርጫንና ሌሎች ኣስተዳደራዊ ጉዳዮች(ልማት)ኣማክሎ ይመራል ተብሎለታል፡፡ከላስተር ተብለው የሚታወቁት የወረዳው የመንግስት መዋቅር ምርጫንም እንደሚመሩና በየቀኑ ለወረደው ስራ ኣስፈፃሚ የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ ፡ የሁሉም ጽሕፈት ቤት መኪኖች'(የትራንስፖርት) በየክላስተሩ ይመደባሉ ይህንኑ ያደናቃፈ የጽሕፈት ቤት ሓላፊ ምርጫው እንዳደናቀፍ ይቆጠራል፣መፈክር-የምርጫው ማስፈፀምያ ተብለው ከተዘረዘሩት መፈክሮች ኣንዱ “ምዝገባ በልማት ጉጅለኣችን ! “ የሚል ሆኖ የመራጮች ምዝገባ በየግል ሳይን በልማት ቡድንና በኔትዎርክ ያደርጋል፣ በሚል እቅድ ህወሓት /ኢህአዴግ በ2007 ምርጫ ላይ የመዘዘው የጥፋት ሰይፍ ነው፡፡
የመንግስትን መዋቅር በማዝመት የተቃዋሚዎች ድምፅ ዜሮ ለማድረግ መከጀል በሰላማዊ ምርጫ ላይ የሚፈነዳ ቦንብ ከመቅበር አይለይም !!
1. የተቃዋሚዎች ድምፅ ዜሮ እናደርገዋለን ማለት በኣንድ በኩል ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲኖር ኪሎሜትሮች ተጉዘን እንቀበላቸዋለን የሚለው የህ.ወ.ሓ.ት/እህኣዴግ ኣንደበት እውነት ኣለመሆኑን ሲያመለክት በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚዎች ድምፅ ዜሮ በሆነ የህ.ወ.ሓ.ት/እህኣዴግ ድምፅ 100% ስለሚሆን ቢያንስ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ የማይቀበሉ “ኪራይ ሰብሳቢዎች” የሚለው የገዢው ፓርቲ ዘፈን የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እንጂ መሰረተ ቢስ መሆኑን ይመለከታል፣
2. ህ.ወ.ሓ.ት/እህኣዴግ የተቃዋሚዎች ድምፅ ዜሮ በማድረግ ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ሁሉ 100% በተደራጀ እንዲመዘገብ ኣድርጌ 99% የነበረው የ 2002 ድምፅ በ 2007 ምርጫ 100% በማድረግ ያቀደው በይፋ የመንግስት’ንብረትና ሃብት’የመንግስት የሰው ሃይል’የመንግስት የስራ ጊዜ ኣዝምቶ በመጠቀም መሆኑን ይፋ ማድረጉ ሆኖ ይህም በይዘቱ የምርጫ ዴሞክራሲ በ2007 ዓ/ም ኣበቃለት የሚል ግልፅ ኣዋጅ መሆኑን፣
3. ምርጫው በኢህኣዴግ “ኣሸናፊነት” ለማወጅ የመንግስት የፅሕፈት ቤት መኪኖች ለማሰማራት የሚያጎበድድ የመንግስት ሓላፊ ወየለት የሚል የገዢ ፓርቲ እቅድ ፓርቲው ተወዳዳሪ ሳይሆን ጠቅላይና ኢ-ሕገ መንግስታዊ’ኣሳታፊ ሳይሆን ኣሳዳጅ መሆኑን እቅዱ በራሱ ይመሰክርለታል፣
4. የእህአዴግ ኣባል ፓርቲዎች የብኣዴን ‘የህ.ወ.ሓ.ት ‘የኢህዴድ’የዴህዴድ የምስረታ በኣል ኣከባበራቸው ከምርጫ እቅዳቸው ይዘት ሲቃኝ በምርጫ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ፍላጎት መኖር ይቅርና እህኣዴግ ማለት የኢትዮåያ መንግስት ማለት እንደሆነ &መንግስትና ፓርቲን የሚለይ ኣጥር ጭራሱን በይፋ መደርመሱን ማወጅ ‘የፓርቲዎች ህልውና በሶቭየት ሕብረት’ በደርግ ጊዜ እንደነበረው ስልጣን የያዘው ፓርቲ(ኢህኣዴግ) እስከ ደገፉ ብቻ መሆኑን፣ ነው፣፣
5. መመረጥና ኣለመመረጥ የዜጋው የግል ሉኣላዊ ውሳኔ እያለ ምዝገባና ማድመጥ በተደራጀና በሰራዊት ሰልፍ እንዲሆን ማቀዱ የህዝቡን ሉእላዊ የራሱን ጉዳይ በራሱ በነፃነት የመወሰን መበቱ ጠራርጎ መውሰዱ እያለ የ2007 የሀ.ወ.ሓ.ት/ኢህኣዴግ የምርጫ እቅድ መሪ መፈክር “ምርጫችን የሉእላዊነታችን መገለጫ ነው! ” ማለቱ የማስመሰል ገፅታው ስር የሰደደ መሆኑን ያሳያል፣
ዓረና ትግራይ የምርጫው ሂደት እየተበላሸ መሆኑን እየተገነዘበም ቢሆን የሚከሰቱ ችግሮች ለመራጩ ህዝብ በማሳወቅ ችግሮችን የታገልን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ እድሎች እንዳይከስሙ መታገል በሚል አቅጣጫ እየተመራን በመላ ትግራይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 29 እጩ ተወዳዳዎች፣ ለትግራይ ክልል ምክር ቤት 68 እጩ ተወዳዳሪዎች በማቅረብ በገዢው ፓርቲ ተከታታይና መልከ ብዙ ፈተናዎች ቢደቀኑብንም የህዝብ ውክልና ለማግኘት ስንሰራ በተለይ ለርጫው ቀን እንደተቃረብን ዓይን ያወጣ የገዢው ፓርቲ የምርጫ ውድድርን የማጥፋት እርምጃ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎ በእጩ ተወዳዳዎቻችንና በምርጫ ታዛቢ ወኪሎች ያነጣጠረ ዘመቻ ተከፍቶብናል ፡፡
የ 2007 5ኛ ው አጠቃላይ ምርጫ የመጨረሻዋቹ ቀናት ገመናዎች በአስቸካይ ይታረሙ!!
የምርጫው እንቅስቃሴ እንደተጀመረ የምርጫው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ያለ መከሰሰ መብታቸው በሕግ የተጠበቀላቸው የዓረና መድረክ እጩ ተወዳዳሪዎቻች ያልታሰበ ክስ በማሴር በአኩሱም የደብረ ገነት ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳ አቶ አስመላሽ ገ/እግዚአብሄር ፣ በአፅቢ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳ አቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ፣በወርቂ አምባ ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆነው አቶ ብርሃን ንጉስ በማሰር በስንት ውጣ ውረድ ቢፈቱም በተወዳዳዎች ነፃነት የፈጠረው ስጋት ቀላል አልነበረም
የመጨረሻው ሳምንት ዋዜማ ገዢ ፓርቲ መላው የመንግስት መዋቅር በማሰለፍ የተያያዘው ዘመቻ የዓረና መድረክ የእጩ ተወዳዳዎች ፓስተሮች እየተከታተሉ መቅደድና ማጥፋት፣ ታዛቢዎችን ማደንና ማስፈራራት ደጋፊዎችን ማሸማቀቅ የሚጠቀሱ ናቸው ፡፡ሁኔታው ልምርጫ ቦርድ ተወካየችና ለፖሊስ ቢቀርብም በአንዳንድ ቦታዎች ከእነዚህ አካላት አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱም ታዝበናል ፡፡ ህወሓት / ኢህአዴግ የትግራይ ህዝብ የለውጥ ፍላጎትና ዓረና/ መድረክን የመምረጥ ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑን እንደተገነዘበም ይህ የህዝቡ ታግሎ የተቀዳጀው መብቱ መሆኑን አውቆ እንደማክበር በየጊዜው ሲያሞካሸው የነበረው የፖለቲካ ፓርቲዎች የስነ ምግባር ደንብ በመርገጥ የዓረና / መድረክን በሃሰት በፀረ ሰላምነት በመወንጀል ሲዳክር ተስተውሎአል፡፡ ይህም ህወሓት / አአዴግ ለቀጣዩ 5 የመንግስት የስልጣን ዘመን የሚጠቀስ አማራጭ ሳይኖረው እራሱ በሚፈጥረው የፀረ ሰላም ድባብ በሚፈጠር የስጋት ፖለቲካ ተመረጥኩኝ ለማለት ስለሚፈልግና በፀረ ሰላም የሃሰት ክስ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት የፖሊታካ ምክንያት ማበጀቱ የሚያመለክት ነው፡፡

በምእራባዊ ዞን ትግራይ የዓረና እጩ ተወዳዳዎች እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሴራ እተገደበ ይገኛል ፡ ግንቦት 08 ቀን 2007 ዓ/ም በአደባይ ከተማ የእጩወች ፖስተር ለመራጩ ህዝብ ለማስተዋወቅ ለህዝብ ይፋ በሆነ ቦታ የተለጠፉት ፖስተሮች ተከታትለው ከምሽቱ 12፡30 -1፡00 ባለው ጊዜ በቀበሌው አስተዳደር አይዞህ ባይነት ከህግ በላይ በመሆን ለ4ኛ ጊዜ በተመሳሳይ ተግባር በሕግ አስከባሪዎች ሊጠየቅ ባልቻለ ለገዢው ፓርተና ለፀጥታ ሃይሎች ቅርበት ያለው ግለሰብ የዓረና ትግራይ እጩ ተወዳዳዎች ፖስተር በመቅደድ ከህዝቡ እይታ እንዲጠፋ ተደርጎአል ፡፡ ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ/ም የዓረና እጩ ተወዳዳሪዎች የሆኑት አቶ ሓጎስ፣ አቶ ገብረአየዝጊና ሃለቃ ዘካርያስ የተባሉት በሁመራ ከተማ የእጩ ተወዳዳዎች ፖስተር ሲለጥፉ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች እየተከታተሉ ፖስተሩን እየቀደዱት እንደሆነ ታወቆአል ፡፡የቃፍታ ሁመራ እጩ ተወዳዳሪዎቻችን መኪናና ጀኔረተር ተከራይተው ለቅስቀሳ እንደተዘጋጁ የመንገድ ና ትራንስፖርት ሃላፊዎች መኪና መከራየት ተከልክሎአል በማለት የሌለ ሕግ አውጭ ሆነው የመቀስቀስ መብታችን ከመርገጥ ባለፈ ላልተጠቀምንበት ግልጋሎት ገንዘብ እንድንከፍልና ለኪሳራ እንድንዳረግ ተደርጎአል፡፡
እጅግ ዘግናኝ ሊባል የሚችል የምርጫ አፋና እየተፈፀመ የሚገኘው ደግሞ በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ/ሽሬ/ ነው፡፡ በአስገደ ፅንብላ ወረዳ የሚገኙ የዓረና ትግራይ አባላት ለሂወታችን በሚያሰጋ አፈና ውስጥ ነው የምንገኘው ብለው በማሳወቃቸው ሁኔታው ለማረጋገጥ ወደ ቦታው የተንቀሳቀሱ የአስገደ ፅንብላ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት መም/ ገብረስላሴ ዴስታ ና ያታሕታይ ቆራሮ እጩ ተወዳዳ የሆኑት ሃለቃ ደመቀ ገብረ ስላሴ በቦታው እንደተገኙ የዘላዝለ ቀበሌ አስተዳደሪ፣የቀበሌው የሚሊሻ ኮማንደር ፣የቀበለ የግብርና ሰራተኛ ፣ከሌሎች ሁለት የህወሓት አባላት በመሆን ድብደባ የፈፀሙባቸው ሲሆን በቦታው በነበሩ ሰዎች ታቀውሞ ድነዋል፡፡በዚሁ ዘላዝለ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የዓረና ትግራይ ደጋፊ ወ/ሮ ፃድቃን የተባሉት ለህዝብ የሚታደለው የምርጫ ቅስቀሳ ፅሑፍ ለህዝብ በማደላቸው በቀበሌ የህዝብ ስብሰባ ቆመው እንዲጋለጡ በማድረግ የታወጀ የማዋረድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል ፡፡ሌሎች 4 ገበሬዎች የዓረና ፅሑፍ ለሰው ሰጥታችሁዋል የተባሉ እንዲታሰሩ በማድረግ ይቅርታ እንዲጠይቁ መገደዳቸውና ይቅርታ አልጠይቅም ያለው አቶ ሓጎስ ግርማይ የተባለው በእስር ሆኖ ቤቱ እየተበረበረ እንደሚገኝና የዓረና ትግራይ እጩዎች ፖስተር እንደተቀዳደና ለህዝብ የሚታደለው ፅሁፍ እንደተወሰደ የአከባባው እጩ ተወዳዳዎቻችን አረጋግጠዋል ፡፡
በደቡብ ምስራቅ ዞን /በቀድሞ በአብዛኛው እንደርታ አውራጃ በመባል ይታወቅ የነበረው/ ባሉት የምርጫ ክልሎች ፓስተሮች ተቀዳደው ፣ ታዘቢዎችና እጩ ተወዳዳዎችን የማዋከብ ስራ ተጡዋጥፎ ይገኛል ፡፡ በምስራቃ ዞን አፅቢ ወረዳ ለቅስቀሳ የተሰማሩ 7 የዓረና አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ውለው ያለ ምንም ምክንያት ቅስቀሳውን ለማናቀፍ ብቻ ለግማሽ ቀን መታሰራቸው፣ በሓውዜን ወረዳ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደር አቶ ፍስሃ ፀጋይ ብእናታቸው የሙት መታሰብያ እንዳይገኙ ከተገኙ ግን በመታሰብያው የሚመጡ ቄሶችና ነዋሪዎች እንዳይገኙ እንደሚደረግ በቀበሌ አስተዳዳዊችና ካድሬዎች በተፈፀመባቸው ዛቻ ከእናታቸው የሙት መታሰብያ መገለላቸው፣በሕንጣሎ፣ በወጀራት እና በውቕሮ ለቅስቀሳ የተሰማሩ መኪኖች በፖሊሶች እንደተያዙና እንቅስቃሴአቸው እንደተገቱ፣ በአፅቢ ፣በአላማጣና በሌሎች አካባቢዎች የህወሓት ካድሬዎች በትጥቅ ትግል የተገኘውን ስልጣን በካርድ አታገኙም በማለት ማስፈራራታቸውንና ፣ የህዝቡን ነፃ ድምፅ ለመንጠቅ ሲባል የመንግስት ሰራተኛች እስከ ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ/ም በየቀበሌው ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ይህ እውነታው በመላ የትግራይ አከባባዎች በጠነከረ ሁኔታ እየተፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ተግባር ሕገ መንግስቱን ክፉኛ የሚንድና የህዝብ ስልጣንን በጉልበት ከመንጠቅ የማይለይ ና የትግራይ ህዝብ የከፈለው መስዋእትነትና የሰማእታትን አደራ ክፉኛ የሚያበላሽ ተግባር በመሆኑ በአስቸካይ እንዲቆም ዓረና ትግራይ ይጠይቃል !! በህዝብ መብት መቀለድ በእሳት መጫወት መሆኑንም ለማስገንዘብ እንወዳለን ፡፡
ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ/ም
መቐለ



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>