Image may be NSFW.
Clik here to view.
በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 8 ላይ አንደተገለጸው ህዝቦች የሉዓላዊነት ምንጮች ናቸው። ይህንንም እምነታቸውን፣ ማንነታቸውን አና ሰብዓዊ መብታቸውን ለሚያከብር ተወካይ በመስጠት አንደሚገልጹት አንቀጹ ይናገራል…
ለዚህም ነው ‹‹ምርጫ የሰላማዊ ትግል አንዱ መገለጫ ነው›› የሚባለው። በምርጫ መሳተፍ የአንድ ጥሩ፣ አገር ወዳድ እና ጤናማ ዜጋ መገለጫ ነው። ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላለፉት ሶስት ዓመታት በዘመቻ መልክ የተለያዩ በደሎች ሲፈጸሙበት ከርመዋል። ግና ይህ ሁሉ በደል ቢደርስበትም ፍጹም ሰላማዊነቱን ጠብቆ እነሆ ዛሬ ላይ ደርሷል። በትግል መድረክ የተለያዩ ኣማራጮች ቢኖሩም ሙስሊሙ ዛሬም ትግሉ በተነሳበት መርህ በመቆም ረጅሙን ጉዞውን በአላህ ፈቃድ ቀጥሏል። የተበደለ ህብረተሰብ ሉአላዊነቱን በመጠቀም ያጠፋ ከስህተቱ እንዲማር ማድረግ፣ ከህዝብ ጋር ተጣልቶ ልማትም ሆነ ብልጽግና ሊሳኩ የሚችሉ አማራጮች አለመሆናቸውን ማስገንዘብ ይችላል።
ከሶስት አመት በፊት ኢትዮጵያዊያን ሙሊሞች ህጋዊነትን ጠብቀው፣ ተወካይ መርጠው፣ ጥያቄያቸውን ግልፅ አድርገው እና መንግስት ባለስልጣናት ዘንድ ቀርበው የሙስሊሙን ሶስት ሃይማኖታዊና ህገ-መንግስታዊ ጥያቄዎች አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን መንግስት ከመነሻው የሃይማኖት ተቋማትን በእጅ አዙር መቆጣጠሩን ቀድሞውኑ የቆረጠበት ጉዳይ ነበርና የሙስሊሙን ህጋዊ ወኪሎች በሐሰት ወንጅሎ ወደ እስር ቤት በመወርወርና ሰላማዊ እንቅስቃሴውን በሐይል ለማቆም ጥረት ማድረግን መረጠ፡፡ መንግስት ያላወቀውና አሁንም ሊገባው ያልቻለው ዋናው ነጥብ ግን ሰላማዊ ትግል በዱላና በነፍጥ የሚሸነፍ ትግል እንዳልሆነ ነው፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.

Clik here to view.
