Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ሊያልፍልን ነው ሲሉ የባህር ራት ሆነው አረፉት

$
0
0

አጥንታችን ድረስ ዘልቆ እየሰረሰረን ያለው ሀዘናች በቀላሉ የሚሽር አልሆን እያለኝ ነው። ይህ ወንድማችን እንዳልካቸው ይባላል የኮተቤ ብረታ ብረት አካባቢ የትውልድ መንደሩ መኖሪያ ሰፈሩ ነበር…

እንዳልካቸው የተሻለ ኑሮ ናፍቆ ራሱንና ቤተሰቡን ሊረዳ ሰሀራ በረሀን አቋርጦ በሊቢያ አድርጎ ወደ አውሮፓ የመሻገርን ተስፋ ሰንቆ ሀገሩን ጥሎ ከተሰደደ
ረዥም ጊዚያት ተቆጥረዋል። ነገር ግን እንደተነገረው የማይቀለው የስደት አለም የወንድማችንን ህይወት ቀላል አላደረገውም። በሞት ጥላ እንደመሄድ የከበደውን የሰሀራን በረሀ የቋርጥ ዘንድ ግድ ብሎታል ።
በሊቢያ ለአመታት የመከራ ፅዋን ጠጥቷል። ሰሞኑን በብዙ ዋጋ መክፈልና ጥረት የተጠየቀውን ከፍሎ ከሊቢያ ትሪፖሊ ወደ ጣሊያን ለመግባት ከብዙ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ጋር በጀልባ ጉዞ ጀምረዋል። ህልሙ ሊሳካ፣ እንደተስፋ ምድር በሩቅ እያየ የተመኛትን አውሮፓን ሊረግጥ. ነገር ግን አልተሳካም። ችግርና ፖለቲካ ሀገር አስጥሎ ያሰደዳቸውን ምስራቅ አፍሪካውያን ውጦ አልጠግብ ያለው ገዳዮ ሜዲትራኒያን ባህር እንዳልካቸውን ጨምሮ ከአራት መቶ በላይ ስደተኞች ወጦ የህይወት ዘመናቸው እንዲያከትም አስገደደ። ክፉ ባህር ፣ የድሀ ደም ጠጥቶ የማይጠግብ አረመኔ ባህር፣ የወገኖቻችን ገዳይ ግኡዝ የማይንቀሳቀስ አይ ኤስ አይ ኤስ ሜዲትራኒያን።
የእንዳልካቸው መርዶ በመጨረሻው ሰአት በተሰናበታቸው፣ ወደ መርከቧም ሲሳፈር በአይናቸው በብረቱ ባዮት ጓደኞቹ በስልክ ለቤተሰቦቹ ተረዳ። የተሻለ ነገር ናፍቀው ያን ሁሉ በረሀ ያን ሁሉ ስቃይ አሳልፈውት ሊያልፍልን ነው ሲሉ የባህር ራት ሆነው አረፉት። የቤተሰብ ለቅሶ ከበደ መሪር ሀዘን፣ ከልብ የማይወጣ ሀዘን፣ ልብና ቅስም የሚሰብር ሀዘን። ከጓደኛየ ጋር ኮተቤ ብረታብረት እቤታቸው ተገኝተን አዘንን አለቀስን። ለኔ የነእንዳልካቸው አሟሟት በግፍ ታርደው ከተገደሉት ወንድሞቻችን የሚለይብኝ አይደለም። አንዳንዴ ሀዘን እንዲህ ሲከፋ የልብን ስብራት፣ የውስጥን ህመም አውጥቶ ለመናገር የትኞቹ ቃላት፣ ምን አይነት ሆህያት ብቁ እንደሆኑ አይገባኝም። ድህነት ክፉ ነው ያዋርዳል፣ አንገት ያስደፋል፣ ዝቅ ያደርጋል እንደ ሰይጣን የምጠላውን ድህነት ከሰይጣን በላይ ጠላሁት። ከሁሉ የከፋው ደግሞ ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት የወገኖቻችንን በአለም ዙሪያ የሚጮሁ ሰቆቃወችን ላለመስማታች ማረጋገጫ አለማግኘታችን ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እንደሞት የከበዱ ክፉ ቀናትንም እያሳለፍን ግን አንድ ነገር በደንብ ይገባናል። በዘመናት መካከል የማይለወጠው፣ ተለውጦም የማያውቀው የደሀደጎች አባት፣ የመበለቶች ዳኛ፣ የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነው ልኡል እግዚአብሔር መልካም አምላክ ነው። እሱ ብቻ መጽናኛችን ነው

11164812_878636988841675_4199497620178178504_n



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>