Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ቴድሮስ አድሃኖም መዋሸቱን ቀጥሏል? ኢትዮጵያውያን አሁንም ከየመን ለመውጣት እርዳታ አላገኙም

$
0
0

ትላንት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (Agence France‑Presse) እንደዘገበው ከሆን ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲህ ብለዋል “ኢትዮጵያ በሁቲ አማጽያን ከስልጣን የተባረረውን የየመን መንግስት በቆራጥነት ትደግፋለች፣ ሳውዲ አረብያ የየመን መንግስትን ወደስልጣን ለመመለስ ጣልቃ መግባትዋም ትክክለኛ እርምጃ ነው” ብለዋል..
በአሁኑ ሰዓት ኃይለማርያም ኢትዮጵያ “በቆራጥነት ትደግፈዋለች…”

dr_tedros_adhanom

ያሉት የየመን ምንግስት ፕሬዝዳንት አገር ጥለው በመሸሽ ሳውዲ አረብያ የሚገኙ ሲሆን አማጽያኑ ደግሞ ዋና ከተማዋን ሰንዓንና የወደብ ከተማዋን ኤደንን ተቆጣጥረው ይገኛሉ።
በቅድሚያ ከ50,000 በላይ ኢትዮጵያውያውያን መውጫ አጥተው በሳውዲ አረብያ የጦር አውሮፕላኖች እየተደበደቡ ባለበት ሁኔታ እና አማጽያኑ መላውን የመን እየተቆጣጠሩ ባለበት ሁኔታ ለተባረረው ይየመን መንግስት በግልጽ ድጋፍ መስጠት የሚያሳየው ነገር ቢኖር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወያኔ አዛዦቻቸው ምን ያህል በየመን መውጫ አጥተው ለሚገኙት ለኢትዮጵያውያን ደንታ እንደሌላቸው ያሳያል።
ይህ በዚህ እንዳለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውን መስሪያ ቤት የሚመሩት ቴድሮስ አድሃኖም የተለመደ “የአዛኝ ቅቤ አንጓች” ውሸታቸውን ማውራት ቀጥለዋል።
ቴድሮስ አድሃኖም በራሳቸው ጌዜ በጀልባ ተንጠላጥለው ጅቡቲ የደረሱትን ኢትዮጵያውያን ከየመን ያስወጡ በማስመሰል “እስካሁን 30 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ደርሰው ኢንባሲያችን ተቀብሏቸዋል” ብለዋል።
ቴድሮስ አድሃኖም አያይዘውም “ሰንዓ የሚገኘው ኤምባሲያችን ወደ ዛሬ አጥቢያ የጦር መሳሪያ ድብደባ ደርሶበታል፡፡ አምባሳደሩም ሌሎች ዲፕሎማቶችም ደህና ናቸው፡፡ የብዙ አገሮች ኤምባሲዎች የተዘጉ ቢሆንም ከዜጐቻችን በፊት አንወጣም ብለው ዜጐቻችንን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ላሉ ዲፕሎማቶችና አስተዳደር ሰራተኞች ምስጋናየን አቀርባለሁ፡፡” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብዬ ለተባረረው የየመን መንግስት በግልጽ ድጋፋቸውን እየሰጡ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ አማጽያኑ በተቆጣጠሩት ከተማ የሚገኘው ኢምባሲያቸው በዚያ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ ምሽግ ቆፍረው የሚገኙት።



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>