Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ዘርን ያማከለ ቅነሳ እና በአዲስ የመተካት ስራ ሊጀመር ነው::

$
0
0

Samoraበመከላከያ ሰራዊቱ በተለያዩ እዞች ውስጥ የተነሳውን የጥቅማ ጥቅም እና ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የአማራ እና ኦሮሞ መኮንኖች ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ እንደሚቀነሱ እና በአዲስ እንደሚተኩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል…

በየእለቱ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድን ተጠንቷል ባለው መሰረት በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እና ከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆኑ ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊት ውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል ተነጋግሮበታል::እነዚህን የሰራዊቱን መኮንኖች በመቀነስ በአዳዲስ እና ታማኝ መኮንኖች መተካት ያስፈልጋል ያለው ስብሰባው አዳዲስ የመኮንንነት ማእረጎች ብዛት ላላቸው ታማኝ መኮንኖች እንደሚሰጥ ጠቁሟል

Samora
በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በመተባበር የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲው እና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችን በማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::የሰራዊቱ የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት ተጠና የተባለው ጥናት ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅ በመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተው በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያል ብለዋል::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>