በዛሬው ዕለት በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡
ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)…
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ (የም/ቤት አባል)
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ሞገስ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል)
25. ሙሉጌታ ተፈራ
26.ኤፍሬም ሰለሞን(የአዲስ አበባ ስራ አስፈፃሚ)
ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡
የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም!!!
