Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

የተማሪዎች ስልጠናው ወደ ሙስሊሞ ኮሚቴ አፈላላጊ ዞሯል * ‹‹ጠበቆቹ በፖለቲካ ዘመቻ ተጠምደዋል!››

$
0
0
ባለፈው ሳምንት ለተማሪዎች በሚሰጠው ስልጠና ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ አጀንዳ መሆናቸውን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስልጠናው ወደ ሙስሊሙ እንቅስቃሴና የኮሚቴው ጠበቃዎች መዞሩን ለማወቅ ተችሏል…

ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚሰጠው በዚህ ስልጠና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊና መንግስት የሙስሊሙ ጉዳይ እልባት እንዲሰጥ የጠየቁ አካላት በአክራሪነት ፈርጇቸዋል፡፡ ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፈተናዎች›› በሚለው ሰነድ የሙስሊሙ ማህረሰብ እንቅስቃሴ ደም ለማፍሳሰስ እየጣረ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡
ከዚህም ባሻገር የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቆች ከጥብቅና ይልቅ የፖለቲካ ስራ እንደሚሰሩ በሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በሰነዱ ገጽ 46 ላይ ‹‹ጠበቆቻቸው በእየ ዕለቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመጣስ በሰፊ የፖለቲካ ዘመቻ የተጠመዱ ናቸው፡፡›› ሲል ያትታል፡፡
ሰነዱ ለስርዓት ግንባታ እንቅፋት ናቸው የሚላቸው የሁለቱንም እምነት ተከታዮች ሲሆን ‹‹በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሽፋን አገራዊ አጀንዳዎችን አስቀድመው ከሚፈታተኑን ኃይሎች ባልተናነሰ ደረጃ ደግሞ በሚያገኙት የገንዘብ ጥቅማጥቅም ተደልለው አገራችን የጀመረችውን የእኩልነት ጉዞ የሚያጥላሉ፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓታችንን ጥላሸት የሚቀቡ ኃይሎች አሉ፡፡›› ሲል የሁለቱን እምነት ተከታዮች ይወቅሳል፡፡
ሰልጣኞቹ የላኩልንን የሰነዱ ክፍል እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡
blue
blue 2
ምን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>