ሕወሓትን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል..
መፍትሔው አንድ እና አንድ ነው = “የትጥቅ ትግል” = ካልተተኮሰ አይደፈርስም አይጠራም !!!
በምንም ተአምር አትታለሉ፤ ኢሕአዴግ በምንም ሁኔታ ሥልጣኑን አሳልፎ ለማንም አይሰጥም። ከተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፈለገ ዓይነት ስምምንነት ቢያደርግ፣ ሥልጣኑን ያጋራል ማለት አይደለም። ቁራሽ ሥልጣን ጠብቃችሁ ከሆነ ዳግም ተሞኝታችኋል። በዚህ አጋጣሚ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሽብር የታወቀው ሕወሓት ከወደቀ የብአዴን እና ኦሕዴድ በህይወት መኖር ያበቃለታል።
ኢሕአዴግ ሃብትና ሥልጣን አያጋራም። ሁሌም የበላይ ሆኖ ሌሎችን መምራትና መቆጣጠር ብቻ ነው የሚፈልገው። ሌሎቹ እሱን እንዲያጅቡት ነው እቅዱ። ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታትም ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለመታየት የሚያስችለውን እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ አይመለስም። ኢሕአዴግ ገንዘብ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ዘራፊዎች የሚሰበስበው፣ ከትላልቅ ሃገራት የጸጥታ ድርጅቶች ጋር የሚሰራው፣ ከአለም አቀፍ አሸብር እና ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር በጋራ የሚንቀሳቀሰው ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እያፈሰ በአሸባርነት የሚወነጅለው ፣ ገንዘብ እየረጨ በየመንደሩ የራሱን ሚሊዮነር የሚቀፈቅፈውና ሰራዊቱን የሚያንጸው ለሃገር ብሎ አይደለም። ለአንድ ግልጽ ዓላማ ነው፤ ሥልጣኑን ላለማጋራት፤ ሥልጣን አጠገብ ማንንም ላለማድረስ! …..ያ መታመን ያለበት እውነት ነው።
ከኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የጠበቃችሁ፤ ከኢሕአዴግ ሥልጣን መጋራት የፈለጋችሁ፤ ከኢሕአዴግ የእምነት፣ የፕሬስና የሃሳብ ነጻነት የጓጓችሁ፤ ‘ከኢሕአዴግ ጋር ተስማምቶ መሥራት ይቻላል’ የምትሉ፤ ተስፋ ቁረጡ። እንኳን አብሮ ለመሥራት ለመወዳደር እድል የማይሰጥ ፈሪ ድርጅት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል። ከኢሕአዴግ ጋር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚቻለው፤ ከኢሕአዴግ በታች ሆኖ መሥራት። ጫማ እየላሱ ‘ጌታዬ!’ ማለት። ያንን የሚመርጥ የፖለቲካ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መንቀሳቀስና መሥራት ይችላል። ጥሩ ቢሮ ይሰጠዋል። ግዙፍ ባጀት ይመደብለታል። ዓመታዊ ጉባዔውን ሼራተን መደገስ ይችላል። በየምክንያቱ ቤተመንግሥት መግባት መብቱ ይሆናል። የመገናኛ ብዙሃን ችግር አይገጥመውም። እስር፣ ዛቻና ወከባ ሕልም ሆነው ይቀሩለታል። ‘ባሪያ የተቃዋሚ ድርጅት’ እየተባለም ይወደሳል።
ስለዚህ እያንዳንዳችን ኢሕአደግን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት በትጥቅ ትግል በሙሉ ሃይል ተባብሮ በመታገል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ማረጋገጥ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት እና ድርሻ መሆኑን መገንዘብ ግደታችን ነው። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!! #ምንሊክሳልሳዊ
