!![unnamed]()
ውድ ኢትዮጵያኖች የድጋፍ ማህበራችን የአንድነት ፓርቲ የነደፈውን የትግል መስመር ለማገዝ ከስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዎ ጋር በመተባበር የርዳታ ማሰባሰብያ ፕሮገራም ይጀምራል። አንድነት ፓርቲ በነደፈው ፕሮገራም መሰረት በሃገራችን ፍትህና ዲሞክራሲ እንዲኖር በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ፓርቲው እስከዛሬ ያካሄደውን መራራ ትግል በመቀጠል በሰላማዊ ሰልፎች በአዳረሽ ሰብሰባዎችና አሁን ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መርሆው የሃገር አንድነት የህዝብ አኩልነትና ዲሞከራሲያዊነት በኢትዮጵያ እስኪረጋገጡና እስኪከበሩ ድረስ ህዝቡን ለትግል በማነሳሳት ላይ ይገኛል።
የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን ከማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች ጋር በመሆን በሃገራችን ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ ለማምጣት የሚታገል የሃገር ወዳድ ማህበር ነው። የድጋፍ ማህበራችን ለዚህ ዓላማ ከሚታገሉ ማህበራትና ተቁዋማት ጋር በመተባበር ሢሠራ የቆየ ማህበር እንደመሆኑ አሁንም የአንድነት ፓርቲ የሚለዮኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርሆ የጀመረውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከስዊድን የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋር በመተባበር ለመስራት ወስንዋል።
ከሃገር እርቀን የምንኖር ኢትዮጵያውያን በትንሹ ልናደርግ የሚገባንና ልናደርግም የምንችለው በሃገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል የሞራልና የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ነው። አኛም በስዊድን የምንኖር ኢትዮጵያውያን ይህንን የተቀደሰ መርሆ ለመደገፍ የአንድነት የድጋፍ ማህበር ትግሉን ለመደገፍ በየወሩ መጨረሻ ቅዳሜ በሚያዘጋጀው የውይይት ቀን (የጌትቱጌዘር የውይይት መድረክ) በተለይ የሚለዮኖች ድምዕ ለመሬት ባለቤትነት መርሆንና ዓላማ የተጀመረውን ትግል ለማገዝ አፕሪል 26 ቀን 2014 ከ14፡00 ሰዓት ጀምሮ የርዳታ ማሰባሰብያ ፕሮገራም ይጀመራል።
በሜይ 1 ቀን የዓለም ሰራተኞች ቀንም ከሚደረገው ሰላማዊ ሰለፍ መልስ ከ 1600 ሰዓት ጀምሮ የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ይቀጥላል።
በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ የሚኖሩ ማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የዚህ ትግል አካል ሊሆን ይገባል። በሃገራችን ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አሰፈላጊ ነው። የአንድነት የድጋፍ ማህበርና የስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በዚህ ቀን ሔገርሸቴን ቬገን 165 ቱነልባና አሰፑድን ወይንም ኦርንሽበሪ በሚገኘው አዳረሽ እንድትገኙና የፕሮግራሙ ተካፋይ እንድትሆኑ ባአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
እርዳታችሁን በፖሰትጂሮ ለመክፈል ለምትፈልጉ የአድነት የድጋፍ ማህበር ፖሰትክጂሮ ቁጥር 399590-9 ወይንም በኢትኦጵያ ድምዕ ራዲዎ ፖሰትጂሮ ቁጥር ማሰገባት የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን በገንዘብ ማስገቢያው ቅፅ መልክት መጻፊያ ቦታ ላይ ”milion vices” ብለው እንዲጠቅሱ በአክብሮት እናሳስባለን።
ከሰላምታ ጋር
የአንድነት የድጋፍ ማህበርና የስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮ
