Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 945

የሳውዲ አረቢያ ሁለት ከተሞች ከከባድ አቧራ አዘል አውሎ ነፋስ እና ዶፍ ዝናብ ተረፉ !

$
0
0

እለተ ረቡዕ Apr 2 2014 ምሸት ከበረሃማ የሃገሪቱ ክፍል የተነሳው አቧራ አዘል አውሎ ነፍስ እና ዶፍ ዝናብ ከተማይቱን ሪያድ እና ጣይፍ ከተማን ስጋት ላይ ጥሏቸው እንደ ነበር የሚናገሩ ምንጮች እንደዚህ አይነት የአየር ፀባይ ያልተለመደ በመሆኑ ህዝቡን ስጋት ወስጥ ጥሎት እንደነበር ገልጸዋል.. ለሰአታት የወረደው ጭቃ አዘል ዝናብ አቧራ ተሸክሞ የመጣውን አውሎ ነፋስ አቅጣጫ እንዳስለወጠው እና በተለይ ከተማይቱን ሪያድ በአቧራ ከመመታት እንደተረፋት የሚናገሩ ነዋሪዎቹ ይህ ዝናብ እና አቧራ አዘል አውሎ ነፋስ በሰውም ሆነ በንበረት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳላደረሰ ገልጸዋል። ለአያሌ አመት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚኖሩ የሪያድ እና አካባቢው ነዋሪዎች እንደዚህ አይነት አቧራ እና አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ያልተለመደ እንገዳ « የፈጣሪ ቁጣ » መሆኑን ገልጸው ቀደም ሲል ሪያድ ከተማ በጎርፍ መጠቃቷን አስታውሰው ይህ ድነገተኛ ዝናብ አዘል አውሎነፋስ በህብረትሰቡ ዘንድ ከፈተኛ ፍረሃት እና ድንጋጤን ፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል ። ይህ ዝናብ አዘል አውሎ ነፋስ አቅጣጫ ለውጦ ወደ ሀገሪቱ በረሃማ አካባቢ ባይነጉድ ኖሮ በህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይቸል እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በሳውዲ አረቢያ የክረምቱ ወራት መገባደድን ተከትሎ መዲናይቱ ሪያድ አልፎ አልፎ ቀለል ባለ አቧራ አዘል አውሎ ነፋስ እና ዶፍ ዝናብ እንደምትጠቃ ይታወቃል።10170929_260673617448006_2099588660_n[1]



Viewing all articles
Browse latest Browse all 945

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>